ቀጥታ፡

ባህር ዳር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽሬ ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 23/2018 (ኢዜአ)፦  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ እና ምድረ ገነት ሽሬ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተካልኝ ደጀኔ በ21ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ባህር ዳር ከተማ መሪ ሆኗል።

የባህር ዳር ከተማው ሰለሞን ገብረክርስቶስ በራሱ ላይ በ37ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ምድረ ገነት ሽሬን አቻ አድርጋለች።

ውጤቱን ተከትሎ ባህር ዳር ከተማ በ37 ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ ስምንተኛ ከፍ አድርጓል።

በዘንድሮው ዓመት በሊጉ በርካታ ጨዋታዎች (16 ጊዜ) አቻ የወጣው ባህር ዳር ከተማ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።

ምድረ ገነት ሽሬ በ30 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።  ቡድኑ ባለፉት ስምንት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ዛሬ አስቀድሞ በተካሄደው የ29ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያይተዋል።

የ29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በዛሬዎቹ ጨዋታዎች ፍጻሜውን አግኝቷል።

የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም