ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና በተጠባቂው መርሐ ግብር አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና በተጠባቂው መርሐ ግብር አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በሲዳማ ቡና መካከል የተደረገው ተጠባቂ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
የሁለቱ ቡድኖች ፍልሚያ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል።
ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ36 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ግን ምንም ድል አላስመዘገበም።
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 55 ቢያሳድግም፣ ከተከታዩ መቻል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት ያገኘውን ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።