የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ያስገነባው ሕንጻ አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ተጨማሪ ዐቅም ይፈጥራል - ኢዜአ አማርኛ
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ያስገነባው ሕንጻ አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ተጨማሪ ዐቅም ይፈጥራል
ጅማ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በጅማ ከተማ ያስገነባው ሕንጻ አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ተጨማሪ ዐቅም እንደሚሆን የጅማ ከተማ ከንቲባ ጠሀ ቀመር ተናገሩ።
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በጅማ ከተማ የገነባውን ባለ ስምንት ወለል ሕንጻ ዛሬ አስመርቋል።
የጅማ ከተማ ከንቲባ ጠሀ ቀመር በዚሁ ወቅት፤ መንግሥት የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ እና ምቹ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር እየሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አስተዳደሩ በጅማ ከተማ የገነባው ሕንጻም ለማኅበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትና የሠራተኛውን ተነሳሽነት ለማሳደግ የሚያስችል ነው ብለዋል።
የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዲናኦል ሳቀታ በበኩላቸው፤ የተመረቀው ሕንጻ የተገልጋይ እርካታን የሚያሳድግ ነው ብለዋል።
ሕንጻው ለአካል ጉዳተኞችና ለተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ምቹ ሆኖ መሆኑን ገልጸው፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማሟላቱን አረጋግጠዋል።