ሊድስ ዩናይትድ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል - ኢዜአ አማርኛ
ሊድስ ዩናይትድ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ በርንሌይን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ትናንት ማምሻውን በኢላንድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንቶኒ ስታክ፣ ኖሃ ኦካፎር እና ዶሚኒክ ካልቨርት ሉዊን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሉም ቹና ለበርንሌይ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ባለሜዳው ሊድስ በጨዋታው የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል።
በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሊድስ ዩናይትድ በ43 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 14ኛ ከፍ አድርጓል። ላለመውረድ በሚደረገው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
ከሊጉ አስቀድሞ መውረዱ የተረጋገጠው በርንሌይ በ20 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዟል።
በውድድር ዓመቱም 23ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛ ሳምንት እሶከ ሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።