ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ አፍሪካውያንን አንድ በሚያደርጉ አሰባሳቢ አጀንዳዎች ላይ ትልቅ ሚና እየተጫወተች ነው - የጣና ፎረም የቦርድ አባል ጆይሴ ባንዳ (ዶ/ር)
Oct 27, 2025 6
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ አፍሪካዊያንን አንድ በሚያደርጉ አሰባሳቢ አጀንዳዎች ላይ ትልቅ ሚና እየተጫወተች ነው ሲሉ የቀድሞ የማላዊ ፕሬዝዳንትና የጣና ፎረም የቦርድ አባል ጆይሴ ባንዳ (ዶ/ር) ገለጹ። ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀድሞ የማላዊ ፕሬዝዳንት ጆይሴ ባንዳ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ አፍሪካውያንን በሚያሰባሰቡ የጋራ ዓላማዎች ዙሪያ ተጠቃሽ ሚና እየተጫወተች ነው። በቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአሁኑ አፍሪካ ኀብረት ምስረታ ሂደት የኢትዮጵያ ሚና ጉልህ መሆኑንም አስታውሰዋል። በአፍሪካ ሠላምና አንድነትን ማረጋገጥ የተሻለች አህጉርን የመገንባት ግብን ለማሳካት ወሳኝ እንደሆነ በማንሳት፥ አፍሪካውያን በጋራ ተቀራርበው እየተወያዩ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጡባቸው መድረኮች ሊጠናከሩ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ የጣና ፎረምን በመመስረት ችግሮቻችንን እንድንፈታ እያሰባሰበችን ነው ያሉት ጆይሴ (ዶ/ር)፥ አፍሪካን አንድ በሚያደርጉ አጀንዳዎች ላይ እየተጫወተች ያለው ሚና የሚደነቅ ነው ብለዋል። በልማት በኩልም የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎችን በማስተባበር እያስመዘገበ ያለው ስኬት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል።   በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ተንታኝ ፓ ኪዌሲ ሄቶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ አፍሪካውያን በአንድ ተሰባስበው የፖለሲ መፍትሄዎችን እንዲቀይሱ አስቻይ ሁኔታ እየፈጠረች መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ድልድይ ሆና እያገለገች ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን ፈለግ በመከተል ለአፍሪካ አንድነት መጠናከር ሊረባረቡ እንደሚገባ አመልክተዋል። በአፍሪካ ልንፈታቸው የለየናቸው ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እንደ ድልድይ ሆነው የሚያስተባብሩ በርካታ ተዋንያን ይፈልጋሉ ያሉት ፕሮፌሰሩ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ምሳሌ መሆን የምትችል ሀገር ናት ብለዋል።
አስተዳደሩ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ከመመከት አንጻር እያሳየ ያለውን ውጤታማ ሥራዎች ማጠናከር ይገባዋል - ቋሚ ኮሚቴው
Oct 27, 2025 20
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሀገር ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ከመመከት አንጻር እያሳየ ያለውን ውጤታማ ሥራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።   የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ባቀረቡት ሪፖርት፤ ሀገራዊ የሳይበር ቁጥጥርን ከማጎልበት አኳያ ውጤታማ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ተልዕኮ ተኮር ምርትና አገልግሎት ተደራሽነትን ከማስፋት አኳያም ውጤታማ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ቁልፍ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም መገንባቱን ጠቁመው፤ በሩብ ዓመቱ ለተመዘገቡ 13 ሺህ 443 የጥቃት ሙከራዎች ምላሽ መስጠት መቻሉን ተናግረዋል። በሩብ ዓመቱ በርካታ አገልግሎቶች ተደራሽ መደረግ መቻላቸውን ጠቁመው፤ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ አስተዳደር ስርዓት ተጠናቆ በይፋ መመረቁንም ገልጸዋል። በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ የኤሮ-አባይ የድሮን ማምረቻ፣ የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ስርዓት፣ ለበርካታ ከተሞች የካደስተር ኢ-ላንድ መተግበሪያን ጨምሮ ሌሎችንም ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትም የተቋሙን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም በማድነቅ ምላሽና ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮችንም አቅርበዋል። ከእነኚህም መካከል የሀገርን የሳይበር ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና የሳይበር ጥቃትን ቀድሞ ከመከላከል አንጻር የተቋሙ አሁናዊ ቁመና ምን እንደሚመስል ጠይቀዋል። በተጨማሪም የተቋሙ ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አጋርነት፣ ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከውጤት አንጻር ምን ማሳያ አለው የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና ማብራሪያዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ የሳይበር ደህንነትን ከማስጠበቅ አኳያ አስተማማኝ ሁኔታ ላይ መሆኑን ተናግረዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ የምላሽ አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ጠቁመው፤የተቋሙ ዝግጁነትም እያደገ መሆኑን አንስተዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አማካሪ ፍቅረስላሴ ጌታቸው ተቋሙ የተለያዩ ስምምነቶችን ከመፈራረም ባሻገር ስምምነቶችን ወደ ተግባር በመለወጥ ትልቅ ፋይዳ እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኢንፎርሜሽን አሹራንስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ሃኒባል ለማ በበኩላቸው፤ የስትራቴጂክ ዕቅዶችን በሶስት ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ዕቅድ መያዙን ጠቁመው፤ ይህም የመሰረተ ልማት ግንባታንና ሥራን መሠረት ያደረገ ነው ብለዋል።   በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሰቢ ፈቲህ ማሕዲ (ዶ/ር) በሰጡት ማጠቃለያ፣ አስተዳደሩ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ከመመከት አንጻር እያሳየ ያለውን ውጤታማ ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። በቅድመ መከላከልና ዝግጁነት የተሰሩ አበረታች ሥራዎችን ማጠናከር እንዳለበት ጠቁመው፤ ተቋሙ ብቁ የሰው ኃይልን ከማፍራት አኳያ የጀመራቸውን ውጤታማ ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።  
ተኪ ምርት አምራቾች የመንግሥት የግዥ መመሪያ የሰጣቸውን ሰፊ የገበያ ዕድል በአግባቡ እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ
Oct 27, 2025 28
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦ተኪ ምርት አምራቾች የመንግሥት የግዥ መመሪያ የሰጣቸውን ሰፊ የገበያ ዕድል በአግባቡ እንዲጠቀሙ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ጥሪ አቀረቡ። የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የመንግሥት ግዥ ሥርዓት ለአምራች ዘርፉ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በተመለከተ ለዘርፉ ተዋንያን ማብራሪያ ሰጥቷል።   መንግሥት የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል የግዥ መመሪያ አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ ነው ተብሏል። በግዥ መመሪያው በሀገር ውስጥ ለሚመረትና 20 በመቶ እሴት ለሚጨመርባቸው እንዲሁም በመልሶ መጠቀም ለሚመረቱ ምርቶች ቅድሚያ የሚሰጥበት ዕድል ተመቻችቷል። በውይይት መድረኩ የተሳተፉ አምራቶች ከውጭ ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ ምርቶች ተኪ ምርት አምራቾች ላይ ጫና እያሳደሩ መሆኑን ጠቅሰዋል። ለሀገር ውስጥ ምርቶች ጥራት ያለው አመኔታ ዝቅተኛ መሆንና የአመለካከት ክፍተት የገበያ እድሎችን እንዳንጠቀም የራሱ አሉታዊ ውጤት እንዳለው በምክንያትነት አንስተዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል መንግሥት የኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሕግና አሰራር ማሻሻያዎችን ከማድረግ ባለፈ የገበያ ትስስርን ለማሳደግ ተጨባጭ ሥራዎች እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ፣ አሁን ያለው የመንግሥት ግዥ መመሪያ የሀገር ውስጥ አምራችነትን የሚያበረታታና ገቢ ምርትን ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑን አንስተዋል። በተለይም ሀገር ውስጥ ከሚመረቱ ምርቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ለማስቀረት ተጨማሪ ቀረጥ ይጣላል ብለዋል። የሀገር ውስጥ አምራቾች በመንግሥት ተቋማት የተፈጠረውን የግብይት ሥርዓት በመጠቀም የገበያ ዕድላቸውን እንዲያሰፉ አስገንዝበዋል። መንግሥት የአምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ የሀገር ውስጥ ግዥን በስፋት እየተጠቀመ ቢሆንም የግዥ መመሪያውንና አሠራሩን በአግባቡ አለመጠቀም እንደሚስተዋል አመልክተዋል። በመሆኑም አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፎ ለውጭ ገበያ ምርቶችን የማቅረብ ዕድላቸውን አሟጠው እንዲጠቀሙ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ በበኩላቸው፣ ተኪ ምርት አምራቾች በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪነታቸው እየጨመረ መጥቷል ብለዋል። እሴት ለጨመሩ ኢንዱስትሪዎች የሚደረገው የ20 በመቶ ማበረታቻ አምራችነትን የሚያበረታታ መሆኑን ነው የተናገሩት።   የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሰረት መስቀሌ፥ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓቱ ቀልጣፋ መሆኑን ጠቅሰው፣ የመንግሥት ተቋማት ጥራት ያላቸው ምርቶችን ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች እንዲያገኙ እያደረገ ነው ብለዋል። የመንግሥት የግዥ መመሪያው ግልጽ የጨረታ ሂደትን ከመከተል ጀምሮ አምራች ኢንዱስትሪውን የሚያነቃቃ መሆኑን ጠቅሰው፥አምራቹ ስለ ግዥ አዋጁና መመሪያው ያለውን ግንዛቤ የበለጠ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግስት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር ያለውን ትብብር ያጠናክራል
Oct 27, 2025 36
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018 (ኢዜአ)፦ መንግስት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገንዘብ ሚኒስቴር ገለፀ። የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እ.አ.አ ከ2025 እስከ 2030 በኢትዮጵያ በጋራ የሚተገበሩ የልማት መርሃ ግብሮች ስትራቴጂ ይፋ ተደርጓል።   መርሃ ግብሮቹ ተቋማዊ አቅምንና የሰው ሀብትን ማጠናከር፣ የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ማሳደግ፣ የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም ላይ ያተኮሩ ናቸው። የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እንዳሉት፥ የኢትዮጵያን የልማት አጀንዳዎችና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መሳካት የልማት አጋሮች እያደረጉ ያለው ድጋፍ ጉልህ ነው። የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ባለፉት ዓመታት ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ በሥርዓተ-ፆታ እኩልነት እና በማኅበራዊ ልማት መስኮች አበረታች ስራዎችን ማከናወናቸውን አንስተዋል። ሁለቱ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ይፋ ያደረጓቸው አዲስ መርሃ ግብሮች ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ያለንን የጋራ ጥረት የሚያሳይና ከኢትዮጵያ የልማት እቅዶችና ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር የተሰናሰሉ ናቸው ብለዋል። የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትብብርና በመናበብ መስራት አስፈላጊ መሆኑን መንግስት ይገነዘባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ለዚህም ከአጋር አካላት በጋራ በመስራት የስራ ድግግሞሽን እንዲቀንሱ ይሰራል ብለዋል።   በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ተወካይ ሳሙኤል ዶ (ዶ/ር) በበኩላቸው ለአምስት ዓመት በሚተገበረው የልማት መርሃ ግብር ተቋማትን ለማጠናከር ይሰራል ብለዋል። ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን የልማት እቅዷ አካል በማድረግ አካታች ብልፅግናን ለማሳካት እየተጋች መሆኗን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድ ተወካይ ኮፊ ኩዋሜ በበኩላቸው መርሃ ግብሮቹ በሰው ሀብት ልማት ያለንን ትብብርና አጋርነት ለማጠናከር የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።   በስርዓተ-ጾታ፣ ስነተዋልዶ ጤና፣ ሴቶችንና ወጣቶችን ማብቃት ላይ ያተኮሩና ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለመሆን እየሰራች ያለውን ተግባር የሚያጠናክሩ ስለመሆናቸውም ነው ያብራሩት። የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድ በመርሃ ግብሩ ከፌዴራልና ከክልል ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር እንደሚያጎለብት ጠቁመዋል።    
የክልሉ ፖሊስ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ሃላፊነቱን እየተወጣ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
Oct 27, 2025 32
ባህር ዳር፤ጥቅምት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአማራ ክልል ፖሊስ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የፖሊስ አመራሮችና አባላት የማዕረግ ዕድገት፣ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።   በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፤ የክልሉ ፖሊስ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል። የፖሊስ ሃይሉ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ፅንፈኛ ኃይሉ ክልሉን ለማተራመስ ያቀደውን ሴራ በመቀልበስ በክልሉ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር የላቀ ሚናውን ተወጥቷል ብለዋል።   በመሆኑም የፖሊስ አባላትና አመራሮች እየተወጡት ላለው ግዳጅና ተልእኮ አድናቆታቸውን በመግለጽ የክልሉን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። በዛሬው እለት የተሰጠው እውቅና እና ሽልማትም በቀጣይ ለላቀ አፈፃፀም እንዲዘጋጁ እና ሌሎች ጀግኖችንም ለማፍራት የሚያነሳሳ መሆኑን አንስተዋል። የክልሉን ሰላም የማፅናት ስራ ውጤታማነት ከፍ ለማድረግም በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ለማስፋት የተጀመረው የሪፎርም ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የህዝቡ ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅና ልማቱ እንዲፋጠን የተጀመረው የህግ ማስከበር ተግባርም በላቀ ቁርጠኝነት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።   የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅና ልማቱን ለማፋጠን የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ፅንፈኛ ቡድን በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን በደል በመቀልበስ አስተማማኝ ሰላም በማረጋገጥ ረገድ ውጤታማ ተግባራት ማከናወን መቻሉን አመልክተዋል። በየደረጃው ዛሬ የተሰጠው የማዕረግ ዕድገት፣ዕውቅናና ሽልማትም ሙያዊ ስነ ምግባራቸውን ጠብቀው የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው፥ይህም ሰራዊቱን ለበለጠ የግዳጅ አፈፃፀም እንዲዘጋጅ ያደርጋል። የረዳት ኮሚሽነር ማዕረግ ዕድገት ያገኙት አየሁ ታደሰ በበኩላቸው፤ የተሰጣቸው ዕውቅናና የማዕረግ እድገት ለላቀ ግዳጅ አፈፃፀም አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ሶስት የምክትል ኮሚሽነር ማዕረግና ስምንት የረዳት ኮሚሽነር ማእረግን ጨምሮ ለሌሎች የፖሊስ አመራሮችና አባላት የማዕረግ ዕድገት፣ዕውቅናና ሽልማት የተሰጠ ሲሆን በየደረጃው ያሉ የስራ ኃላፊዎችና የፖሊስ አባላት ተገኝተዋል።
የሚታይ

የባሕር በር ባለቤትነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅ የህልውና ጉዳይ ነው - ሌተናል ሃለፎም መለሰ
Oct 27, 2025 69
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦የባሕር በር ባለቤትነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የቀድሞ የባሕር ኃይል ማህበር ሊቀ መንበር ሌተናል ሃለፎም መለሰ ገለጹ። ሌተናል ሃለፎም መለሰ ከኢዜአ ጋር በባህር በር ጉዳይ ላይ ቆይታ አድርገዋል። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የኢትዮጵያን የጠረፍ ጠባቂ በሚል በ1946 ዓ.ም በአዋጅ መሰረት የተጣለው የባሕር ኃይል እስከ ደርግ መንግስት ሥርዓት መውደቅ ድረስ በተደራጀ መልኩ መስራቱን ነው የገለጹት። የቀድሞ ባህር ሃይል የኢትዮጵያን የባሕርና ጠረፍ አካባቢ ደኅንነት በአስተማማኝነት መልኩ መጠበቁን ያስታውሳሉ። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የዓባይ ወንዝና ከባህር ተጠቃሚነት ለማራቅ ከጥንት ጀምሮ ያላቆመ ሴራ መኖሩን ያስታወሱት ሊቀ መንበሩ፤ ከደርግ መንግስት መውደቅ በኋላ አገሪቷ የባህር በር እንድታጣ መደረጉን ተናግረዋል። ዓባይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ብስራትን ያሰማ መፍትሔ ማግኘቱን ጠቅሰው፥ኢትዮጵያን የባሕር በር እንዳይኖራት ለማድረግ የተሸረበው ሴራም በውጭ ባዕዳንና በውስጥ ባንዳዎች የተፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል። የለውጡ መንግስት የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ለመመለስ አጀንዳ ማድረጉን አድንቀው፥የባሕር በር የሀገር ህልውና ማስጠበቂያና የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳለጫ መሳሪያ ነው ብለዋል። መንግስት የባሕር በር ጉዳይ በወሳኝ አጀንዳነት ወደፊት ማምጣቱ ታላቅ ጉዳይ መሆኑን አመልክተው፤የባሕር በር አልባነትም የመኖር አለመኖር የህልውና ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል። በዚህም የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄን ተገቢ ምላሽ ለማስገኘት ዜጎች በሁሉም ዘርፍ አንድነታቸውን በማጽናት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። በተለይም በኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተደረገውን ትብብር ለባሕር በር ባለቤትነት በአንድነት መስራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የክልሉ ፖሊስ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ሃላፊነቱን እየተወጣ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
Oct 27, 2025 32
ባህር ዳር፤ጥቅምት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአማራ ክልል ፖሊስ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የፖሊስ አመራሮችና አባላት የማዕረግ ዕድገት፣ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።   በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፤ የክልሉ ፖሊስ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል። የፖሊስ ሃይሉ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ፅንፈኛ ኃይሉ ክልሉን ለማተራመስ ያቀደውን ሴራ በመቀልበስ በክልሉ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር የላቀ ሚናውን ተወጥቷል ብለዋል።   በመሆኑም የፖሊስ አባላትና አመራሮች እየተወጡት ላለው ግዳጅና ተልእኮ አድናቆታቸውን በመግለጽ የክልሉን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። በዛሬው እለት የተሰጠው እውቅና እና ሽልማትም በቀጣይ ለላቀ አፈፃፀም እንዲዘጋጁ እና ሌሎች ጀግኖችንም ለማፍራት የሚያነሳሳ መሆኑን አንስተዋል። የክልሉን ሰላም የማፅናት ስራ ውጤታማነት ከፍ ለማድረግም በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ለማስፋት የተጀመረው የሪፎርም ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የህዝቡ ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅና ልማቱ እንዲፋጠን የተጀመረው የህግ ማስከበር ተግባርም በላቀ ቁርጠኝነት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።   የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅና ልማቱን ለማፋጠን የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ፅንፈኛ ቡድን በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን በደል በመቀልበስ አስተማማኝ ሰላም በማረጋገጥ ረገድ ውጤታማ ተግባራት ማከናወን መቻሉን አመልክተዋል። በየደረጃው ዛሬ የተሰጠው የማዕረግ ዕድገት፣ዕውቅናና ሽልማትም ሙያዊ ስነ ምግባራቸውን ጠብቀው የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው፥ይህም ሰራዊቱን ለበለጠ የግዳጅ አፈፃፀም እንዲዘጋጅ ያደርጋል። የረዳት ኮሚሽነር ማዕረግ ዕድገት ያገኙት አየሁ ታደሰ በበኩላቸው፤ የተሰጣቸው ዕውቅናና የማዕረግ እድገት ለላቀ ግዳጅ አፈፃፀም አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ሶስት የምክትል ኮሚሽነር ማዕረግና ስምንት የረዳት ኮሚሽነር ማእረግን ጨምሮ ለሌሎች የፖሊስ አመራሮችና አባላት የማዕረግ ዕድገት፣ዕውቅናና ሽልማት የተሰጠ ሲሆን በየደረጃው ያሉ የስራ ኃላፊዎችና የፖሊስ አባላት ተገኝተዋል።
የብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መከበር አካታች እና አሳታፊ የፌዴራል ስርዓትን ለማጠናከር  እያገዘ ነው 
Oct 27, 2025 99
አዳማ ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦የብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መከበር አካታች እና አሳታፊ የፌዴራል ስርዓትን ለማጠናከር እያገዘ መሆኑን የፌዴራሊዝምና ሕገ መንግሥት አስተምህሮ ማዕከል ገለጸ። ኢዜአ ያነጋገራቸው የፌዴራሊዝምና ሕገ መንግሥት አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ሃይለኢየሱስ ታዬ (ዶ/ር) እንዳመለከቱት፤ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውንና ማንነታቸውን በተሻለ መልኩ እየገለጹ እና እያስተዋወቁ ነው። ከእነዚህ ማስተዋወቂያ መድረኮች መካከል የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ ቀኑ መከበሩ ሕብረብሔራዊ አንድነትና ትስስርን ይበልጥ እያጠናከረ መሆኑን ተናግረዋል። የቀኑ መከበር በተለይም ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ባህላቸውንና ማንነታቸውን በአደባባይ እንዲያስተዋውቁ በማድረግ አካታች እና አሳታፊ የፌዴራል ስርዓትን ለማጠናከርም እያገዘ ይገኛል ብለዋል። በዚህም በፌዴራሊዝምና ህገ መንግሥት አስተምህሮ ዙሪያ ግንዛቤን በማሳደግ አንድነትን ለማፅናት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ከለውጡ ወዲህ የፌዴራል ስርዓቱን አካታችና ሚዛኑን ለማስጠበቅ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል። ከለውጡ በፊት አጋር ተብለው ይጠሩ የነበሩ ክልሎች ከለውጡ ወዲህ እንደ ሌሎች ክልሎች ወደ ውሳኔ ሰጪነት መምጣታቸውን አውስተው፤ ይህም ለፌደራል ስርዓቱ መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ትግሉ መለሰ በበኩላቸው፤ የብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ህዝቡ በፌዴራሊዝምና ህገ መንግሥት ዙሪያ ግንዛቤው እንዲያድግ የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል።   ዘንድሮም በዓሉ ሲከበር በፌዴራሊዝና በህገ መንግሥት ጉዳዮች ላይ የተሻለ ግንዛቤ በመፍጠር ሕዝቡ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ንቁ ተሳታፊ እንዲንሆን ይሰራል ብለዋል። የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ፌዴራሊዝም መምህር ሉል ዴቪድ፤ ከለውጡ ወዲህ የፌዴራል ስርዓቱ ሚዛናዊና አካታች እየሆነ ለመምጣቱ በርካታ አመላካች ጉዳዮች እንዳሉ ጠቅሰዋል።   ከእነዚህ መካከል ታዳጊ ክልል ተብሎ ሲጠራ የቆየው የጋምቤላ ክልል ከሌሎች ክልሎች እኩል የልማት ተሳትፎው እያደገ መምጣቱን በማሳያነት አውስተዋል። ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልም ሕብረብሔራዊ አንድነት፣ ትስስርና ግንኙነት እንዲጎለብት እንዲሁም ሕዝቦች ማንነትና ባህላቸውን የሚያስተዋውቁበት ትልቅ መድረክ መሆኑንም ገልጸዋል። የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በማስመልከት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተዘጋጀ መድረክ መካሄዱ ይታወሳል።
በአማራ ክልል ሰላምን በዘላቂነት የማጽናትና በተቀናጀ መልኩ ለልማት ምቹ መደላድል የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል - ዘላለም መንግስቴ(ዶ/ር)
Oct 27, 2025 99
ባሕርዳር ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል ሰላምን በዘላቂነት የማጽናትና በተቀናጀ መልኩ ለልማት ምቹ መደላድል የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ገለጹ። ‎ መምሪያው "ፅናት፤ ጀግንነትና ለዓላማ መስዋዕትነት የተቋማችን መገለጫዎች ናቸው" በሚል መሪ ሃሳብ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የፖሊስ አመራሮችና አባላት የዕውቅና መርሃ ግብር በባሕርዳር ከተማ እያካሄደ ነው። ‎‎በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።   ‎በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ‎የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)፤ በክልሉ ሰላቂ ሰላምና ልማትን የማረጋገጥ ጉዳይ በቅንጅትና በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። ‎በተለይም የልማት ጸር እና የህዝብ ጠላት የሆነውን ፅንፈኛ ቡድን የጥፋት እንቅስቃሴ በመከታተል ጠንካራ የህግ ማስከበር ስራ እየተከናወነ መሆኑን አንስተው እርምጃው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።   የመከላከያ ሰራዊትና የክልሉ የጸጥታ ሃይል በቅንጅት ባከናወኑት ህግ የማስከበር ተግባር ጽንፈኛ ቡድኑ እየተበታተነ መሆኑን ገልጸው በክልሉ ሰላምን በዘላቂነት የማጽናትና በተቀናጀ መልኩ ለልማት ምቹ መደላደል የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።   ‎የዛሬው እውቅና እና ሽልማትም ተልእኮና ግዴታቸውን በላቀ ሁኔታ ለፈፀሙ የፖሊስ አመራሮችና አባላት የተበረከተ መሆኑን አንስተዋል። የዕውቅና እና ሽልማት የተሰጠው የማዕረግ ዕድገት፣ የደመወዝ እርከን፣ የትምህርትና ሌሎች የማበረታቻ ሽልማቶች መሆናቸውም ተመላክቷል።
ምክር ቤቱ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ በመምከር ለህዝቡ ሰላምና ልማት መረጋገጥ በትብብር እየሰራ ነው
Oct 27, 2025 133
ወላይታ ሶዶ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ በመምከር ለህዝቡ ሰላምና ልማት መረጋገጥ በትብብር እየሰራ መሆኑን ገለፀ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ "ለዳበረ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ ስርዓት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ወሳኝ ነው" በሚል መሪ ሀሳብ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው።   የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ አቶ ጎበዜ አበራ በወቅቱ እንዳሉት በሀገሪቱ እየታየ ላለው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የድርሻውን እየተወጣ ነው።   ''የሀሳብ ልዩነት የእርግማን ተምሳሌት የሆነበት ጊዜ አልፏል'' ያሉት ሰብሳቢው ምክር ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የጋራ በሚያደርጉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ለህዝቡ ሰላምና ልማት በትብብር እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የክልሉ መንግስትም ምክር ቤቱን በአስፈላጊ ጉዳዮች ሁሉ እየደገፈ ስለመሆኑ አመልክተው በዚህም የተሻለ የዴሞክራሲ ስርዓት እየተገነባ እንደሚገኝ አንስተዋል። ለተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓትና ባህል ግንባታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም ፓርቲዎች መጪው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል። በክልሉ ቀደም ባሉት አመታት የዴሞክራሲ ስርዓት ባለመጎልበቱ የሀሳብ የበላይነት እንዲቀጭጭና የዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዳይረጋገጥ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን የተናገሩት ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ናቸው።   ችግሩን ለመፍታትም የለውጡ መንግስት የሀሳብ ነፃነት እንዲከበር በወሰደው ቁርጠኝነት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቁመዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች መቋቋሙ የዚሁ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህም ሀሳብን በሰለጠነ መንገድ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ በማምጣት ልዩነቶች በመነጋገር በመፈታታቸው ለክልሉ ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማገዛቸውን ገልጸዋል። በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብሔራዊ ጥቅምን በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ዙሪያ አንድ ላይ በመቆም ለህዝብ ሰላምና ልማት ላይ በትብብር መስራታቸውን አንስተዋል። ''የምንመራው ህዝብ አንድ ነው'' ያሉት አቶ ገብረመስቀል ''ሀሳባችንን ለህዝቡ አቅርበን በህዝቡ መዳኘት ባህላችን ሊሆን ይገባል'' ብለዋል። 7ኛው ሀገራዊ ምርጫም በሰላምና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸው ምክር ቤቱም የምርጫውን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለበትም አስገንዝበዋል። በመድረኩም የወጣቶች፣ የሴቶች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የጋራ ምክር ቤቱ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በክልሉ ባለፉት ሶስት ወራት በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)
Oct 27, 2025 74
ቦንጋ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት በሰላም፣በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ። የክልሉ የ2018 ዓ.ም የሶስት ወራት የፓርቲና መንግስት ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው ።   የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት ባለፉት ሶስት ወራት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች በተናበበ መልኩ ሲከናወን ቆይቷል። ለተግባራዊነቱም የአመራሩንና የሰራተኛውን አቅም በመገንባት የመንግስት አገልግሎቶችን ለማሳለጥ ጥረት መደረጉን አንስተዋል። በዚህም የክልሉን ሰላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደር ውጤታማ ማድረግ መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል። በተለይም በትምህርት፣ በጤናና የግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራቱን ጠቁመዋል። የግብርናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ተግባራትም በመኸር እርሻ 350 ሺህ ሄክታር መሬት በዋናዋና ሰብሎች በመሸፈን ከ10 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ አንስተዋል።   የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብርን ለማሳካት የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽኖች ወደ ስራ መግባታቸውንና የሻይ ልማትን በማስፋት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ መሰራቱን ጠቁመዋል። እነዚህን የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት የድጋፍና ክትትል ስራዎች እንደሚጠናከሩ ተናግረዋል። ለአንድ ቀን በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ የፓርቲና የመንግስት የሶስት ወራት የስራ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው። በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ በብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ነገ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ
Oct 27, 2025 163
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በነገው ዕለት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል። በዚህ መደበኛ ስብሰባ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዕለቱ በሚካሄደው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ተጠቁሟል። የስብሰባው ሙሉ ሂደትም በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ እንደሚተላለፍ ምክር ቤቱ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን ባልፈለጉ አካላት የተነጠቀችውን የባህር በር መጠየቅ መብቷ እንጂ ቅንጦት አይደለም
Oct 27, 2025 120
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን ባልፈለጉ አካላት የተነጠቀችውን የባህር በር መጠየቅ መብቷ እንጂ ቅንጦት አይደለም ሲሉ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ እንዳለ ንጉሴ አስገነዘቡ። ለጊዜውም ቢሆን ኢትዮጵያ የባሕር በሯን ያጣችበት ሂደት ሕጋዊ አለመሆኑን አንስተው፤ መንግሥት ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት እንዳለባት አምኖ አጀንዳ ማድረጉ ከሕግም ሆነ ከሞራል አንጻር ትክክል መሆኑን ጠቅሰዋል። በወቅቱ የነበረው የሽግግር መንግስት እንደ ባሕር በር ያሉ ቁልፍ ሀገራዊ ውሳኔዎችን የማሳለፍ ሕጋዊ መብት እንደሌለው እያወቀ፤ ኢትዮጵያን ባሕር በር አልባ ማድረጉን አውስተዋል። ለዓለምና አኅጉር አቀፍ ትላልቅ ተቋማት ምሥረታ ፊታውራሪዋ፤ ከጎረቤቶቿ ጋርም በሰላም ማስከበር፣ በወንዝ፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በመሠረተ-ልማት የተቆራኘችው ኢትዮጵያ ከሚናዋ አንጻር የባሕር በር ጥያቄዋ ሊደገፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን ባልፈለጉ አካላት የተነጠቀችውን የባህር በር መጠየቅ መብቷ እንጂ ቅንጦት እንዳልሆነም በአጽንኦት ገልጸዋል። ከሞራልም ሆነ ከሕግ አንጻር የተፈጸመው ስህተት መሆኑን አስገንዝበው፤ ኢትዮጵያ በአሻጥር የተቀማችውን የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንድታጠናክር መክረዋል። ይህ ተሳካ ማለት ጥቅሙ ለጎረቤት ሀገራት ጭምር መሆኑን በመገንዘብ፤ የኢትዮጵያ ደኅንነትና መልማት የቀጣናው ጭምር ስለሆነ ጥያቄዋ እንዲመለስ መደገፍ ይገባል ብለዋል። ከባሕር በር ጋር በተያያዘ ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ጆርዳን እንዲሁም ከአንጎላ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተሞክሮዎች መማር እንደሚገባ ጠቅሰው፤ አይቻልም የሚባል ነገር እንደሌለ አመላክተዋል።
የአካባቢያችንን ሠላምና አንድነት አጠናክረን ለማስቀጠል ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም እንሰራለን-የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች
Oct 26, 2025 162
ወልዲያ፤ ጥቅምት 16/2018(ኢዜአ):- የአካባቢያቸውን ሠላምና አንድነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም እንደሚሰሩ የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። 118ኛው የመከላከያ ሠራዊት የምስረታ ቀን በዓል ዛሬ በወልዲያ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።   በመድረኩ ላይ ከተገኙት ነዋሪዎች መካከል አቶ አበባው ወደደኝ እንደገለጹት፣ ሠራዊቱ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለሀገር ዳር-ድንበር መከበር መስዋዕትነት የሚከፍል መሆኑን ገልጸዋል። በአካባቢያቸው ታጥቆ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ጽንፈኛ ቡድን አደብ በማስገዛት የአካባቢያቸው ሰላምና ደህንነት ማስጠበቁን ገልጸው፣ ሰላሙን አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ከሠራዊቱ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል። የወልዲያ ከተማና አካባቢው ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ በተለያየ መንገድ ሲያደርጉት የነበረው እገዛ ማጠናከር እንዳለበትም ገልጸዋል። "ህዝቡ ለሠራዊቱ የተለመደ ደጀንነቱን ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሏል" ያሉት ደግሞ ሌላው የበዓሉ ተሳታፊና የከተማው ነዋሪ አቶ ቢሆነኝ ካሣው ናቸው። የህዝብን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ውድ ህይወቱን ጭምር እየከፈለ ላለውና የአገር ዘብ ለሆነው መከላከያ ሠራዊታችን የምናደርገው ድጋፍና የምንሰጠው ፍቅር በቀጣይም ሊጠናከር ይገባል ብለዋል። የዛሬው በዓልም ከሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ የጥፋት ተልዕኮ ያነገቡትን በቁርጠኝነት በመታገል የአካባቢያችንን ሠላም ለማስጠበቅ ዳግም ቃል የምንገባበት መሆን አለበት ብለዋል።   የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ኢትዮጲስ አያሌው የቀደሙ አባቶቻችን ያቆዩልንን የፍቅርና የአንድነት እሴት የአሁኑ ትውልድም አጠናክሮ ማስቀጠል ይኖርበታል ብለዋል። ይህ እሴት ተጠናክሮ በከተማው የልማት እንቅስቃሴ እንዲፋጠን ህብረተሰቡ ለአካባቢው ዘላቂ ሰላም ሌት ተቀን እየተጋ ያለውን የመከላከያ ሠራዊት በመደገፍ የድርሻውን ይወጣል ብለዋል። በሀገር መከላከያ ሠራዊት የ11ኛ ዕዝ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ኃላፊ ኮሎኔል አክሊሉ አበበ በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊት ዋና ተግባሩ የሀገርና የህዝብ ሠላምን ማስጠበቅ መሆኑን አንሰተዋል።   "ሠራዊቱን የሚያስጨንቀው የህዝብ ሠላም ሲታወክና የአገር ሉኣላዊነት ሲደፈር ነው፤ ለዚህም ሠራዊታችን ውድ ህይወቱን ጭምር እየከፈለ የህዝብ ሠላምና የሀገርን ዳር ድንበር ጭምር ያስከብራል" ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም ሠራዊቱ የባዳዎችን አጀንዳ ለማስፈጸም እየተላላኩ ያሉ የጥፋት ቡድኖችን እያሳደደና እየደመሰሰሰ ይገኛል ብለዋል።

ማህበራዊ
በአማራ ክልል በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶች የመስህብ ሀብቶችን ጎብኝተዋል
Oct 27, 2025 38
ደሴ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች የመስህብ ሀብቶችን መጎብኘታቸው ተገለጸ። የቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በደሴ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የቢሮ ኃላፊው መልካሙ ፀጋዬ እንደገለጹት፤ በክልሉ የመስህብ መዳረሻ ሥፍራዎችን በማልማት፣ ቅርስና ሙዚየሞችን በማደስና በመጠገን አበረታች ሥራ ማከናወን ተችሏል። በተጨማሪም በክልሉ ያሉ ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ቅርሶችን ለማስተዋወቅና የቱሪስቶችን ቆይታ ለማራዘም ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ገልጸዋል። በዚህም በመጀመሪያው ሩብ የበጀት ዓመት በክልሉ የሚገኙ መስህቦችን ከጎበኙ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ መገኘቱን አስታውቀዋል። ግሸን፣ መውሊድ፣ ሶለል፣ አሸንድዬ፣ ሻዳይ፣ እንግጫ ነቀላ፣ መስቀልና ሌሎች በዓላት በስኬት መከበራቸው ለገቢው መገኘት ምክንያት መሆኑንም ተናግረዋል። የበዓላቱ መከበር የክልሉን ባሕልና እሴት በመጠበቅና በማጎልበት ለትውልድ እንዲሸጋገር በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳላቸውም ገልጸዋል። ለቅርስና ሙዚየም እድሳትና ጥገና ከ461 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ ወደ ተግባር ለመግባት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቁንም የቢሮ ኃላፊው አንስተዋል። የጣና ሐይቅ፣ ደሴት፣ ገዳማት፣ ጥንታዊ የሾንኬ መንደርን፣ አገው ፈረሰኞችን ጨምሮ በክልሉ ያሉ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችንና ቅርሶችን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል። የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አስያ ኢሳ በበኩላቸው፤ ባለፉት ሦስት ወራት ከግሸን ደብረ ከርቤ፣ ከመውሊድና ሌሎች በዓላት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል። የሻዳይ፣ መስቀል፣ ቡሄና ሌሎችም የአደባባይ በዓላትን በስኬት ማክበር በመቻሉ የቱሪዝም ዘርፉ ተነቋቅቷል ያሉት ደግሞ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ እዮብ ዘውዴ ናቸው። በቀጣይም የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት፣ ሙዚየምና ቅርሶችን በመጠገን፣ በመጠበቅና በማስተዋወቅ የተሻለ ገቢ እንዲገኝ ይሰራል ብለዋል። በበጀት ዓመቱ ወደ አማራ ክልል ከሚመጡ ቱሪስቶች ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የመድረኩ ተሳታፊ አመራሮችና ባለሙያዎች ጠንክረው ሊሰሩ እንደሚገባም ተመላክቷል።
ባህላዊ እሴቶችን በማጥናት ሰንዶ ለትውልድ የማስተላለፍ ተግባር ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተከናወነ ነው-ሚኒስቴሩ
Oct 27, 2025 43
ሳጃ ፤ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ) ፡-ባህላዊ እሴቶችን በተገቢው በማጥናትና በመሰነድ ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል ተግባርን ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እያከናወነ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ። የየም ዓመታዊ የመድኃኒት ለቀማ ስነ-ስርዓት ''ሳሞ ኤታ'' በዞኑ ቦር ተራራ ላይ ዛሬ ተካሄዷል።   በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ እንዳሉት ባህላዊ እሴቶችን በማጥናት ሰንዶ ለትውልድ የማስተላለፍ ተግባር ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተከናወነ ነው። የየም ማህበረሰብ ባህላዊ የመድኃኒት ለቀማ ስርዓትም ጤናን ከመጠበቅ ባለፈ ተፈጥሮን የመጠበቅ እሴት አካል መሆኑን አንስተዋል። ሚኒስቴሩ ሀገር በቀል እውቀቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ ሁለንተናዊ ጠቀሜታቸውን ለማጉላት እየሰራ መሆኑን አንስተው ለመድሃኒት የሚውሉትን እፅዋት ተንከባክቦ ማቆየት የሁሉም አካላት ኃላፊነት መሆኑንም አመልክተዋል።   የአርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር) የየም ሃገር በቀል መድኃኒት አሰባሰብ ከፈውስ ባለፈ የአብሮነት ውጤት ነው ብለዋል። ። ይህን እሴት ለማስቀጠል ትውልዱ የባህል መድኃኒት አዋቂዎችን ጥበብ መውረስ እንዳለበትም ጠቁመዋል። በመድኃኒት ለቀማው ቦታ ላይ የተገኙት የሐረማያ ዩኒቨርስቲ የባህላዊ ህክምና መምህር እና ተመራማሪ ኤሊያስ አህመድ (ዶ/ር) እንዳሉት የየም ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በትውልድ ቅብብሎሽ የማቆየት ቱባ ባህልን ማስፋት ይገባል ብለዋል። ይህን ተግባር በሳይንሳዊ መንገድ ለማስፋትም ዩኒቨርሲቲው ጥልቅ ምርምር በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል። የየም ባህላዊ መድኃኒት ለቀማና ስርዓት ከፈውስ ህክምና ባለፈ ለቱሪዝም ሀብት ለማዋል እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ ናቸው።   በየዓመቱ ጥቅምት 17 ቀን ተለቅሞ የሚቀመመው መድኃኒት እስከ መጪው ዓመት ድረስ እንደሚያገለግልም ገልፀዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በተራራው ላይ ካሉ በርካታ የእፅዋት አይነቶች ቅጠል፣ ስራስርና ቅርፊት በመሰብሰብ ቤታቸው ወስደው በአግባቡ በማዘጋጀት ለሰውና ለእንስሳት የሚሆኑ መድኃኒቶችን ይቀምማሉ ብለዋል፡፡ በአካባቢው የሀገር ባህል መድኃኒት አዋቂው አቶ ጌታቸው ሃይለማርያም በበኩላቸው የሚቀመሙት መድኃኒቶች ህመምን ከመፈወስ ባለፈ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል ጠቃሚ እንደሆኑ ተናግረዋል።   በለቀማ ስነ-ስርዓቱ ላይም አባቶች እና እናቶች ስለ መድኃኒት አሰባሰቡ ለታዳጊዎችና ወጣቶች የሚያስተምሩበት እሴት እንዳለም አስረድተዋል። የፌደራልና የክልል አመራር አባላት፣ ከዩኒቨርስቲ የመጡ ተመራማሪዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ስነ-ስርዓቱን ታድመዋል።
በአማራ ክልል ውጤታማ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን የሚያጎለብቱ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Oct 27, 2025 41
ባሕር ዳር፤ ጥቅምት 17/ 2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ውጤታማ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን የሚያጎለብቱ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ። 4ኛው ክልላዊ የጤና ላቦራቶሪ (ቤተ-ሙከራ) ፌስቲቫል ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል። በፌስቲቫሉ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አብዱልከሪም መንግስቱ እንዳመለከቱት፤ የሕብረተሰቡን ድንገተኛ የጤና አደጋ ሥጋቶች ፈጥኖ ለመለየትና ምላሽ ለመስጠት የላቦራቶሪ (ቤተ-ሙከራ) አቅምን ማጎልበት ያስፈልጋል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ በጤና ተቋማት የላቦራቶሪ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት ረገድ አበረታች ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል። በሁሉም ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች የላቦራቶሪ (ቤተ-ሙከራ) መሳሪያዎችንና ግብአቶችን ተደራሽ በማድረግ የበሽታ ምርመራ ውጤታማነትን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም አንስተዋል። በበጀት ዓመቱም በጤና ጣቢያዎች የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎት ጥራትና ውጤታማነት ለማሳደግ እንዲቻልም 470 ተጨማሪ የላቦራቶሪ መሳሪያዎች እየተሰራጩ መሆኑንም ተናግረዋል። ይህም በሽታን መርምሮ ፈጥኖ ፈውስ ከመስጠት ባሻገር ለምርምር፣ ለፈጠራ ሥራና ለቴክኖሎጅ ሽግግር ትኩረት በመስጠት የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን እንደሚያስችል አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ አቅም ግንባታ ዳይሬክተር ዳንኤል መለሰ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር የላቦራቶሪ አገልግሎት ተደራሽነትን በማሳደግ የህክምናውን ዘርፍ ውጤታማነት ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ የኤች አይቪ ኤድስ፣ የቲቢ እና ወባ በሽታዎችን ፈጥኖ በመለየት ለማከምና ለመከላከል የሚያስችል አዳዲስ የላቦራቶሪ መሳሪያዎችን ተደራሽ የማድረጉ ተግባር መቀጠሉን ተናግረዋል። የአማራ ክልልም የላቦራቶሪ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ በሀገር ደረጃ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል። የላቦራቶሪ ተደራሽነት ጊዜው የሚጠይቀው ጉዳይ ነው ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ ናቸው። እንደክልል የላቦራቶሪ ተደራሽነትን በማሳደግ ለመጣው ለውጥ የክልሉ መንግስትና የባለድርሻ አካላት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። በፌስቲቫሉ ላይ የፌደራልና የክልሉ የዘርፉ አመራሮች ተገኝተዋል።
በእውቀትና በሥነ ምግባር የታነጸ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን የማፍራቱ ተግባር ይጠናከራል
Oct 27, 2025 51
ደብረብርሃን ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፡- በእውቀት፣ በክህሎትና ሥነ ምግባር የታነጸ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ የማፍራትን ተግባር ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመደቡለትን ከ3 ሺህ በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምሯል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ተግባር ተኮር የመማር ማስተማር ሂደትን በመከተል ተማሪዎችን በእውቀትና በክህሎት መገንባቱን ይቀጥላል። ተቋሙ በምርምር ላይ በመመስረት በእውቀት፣ በክህሎትና ሥነ ምግባር የታነጸ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን በማፍራት ለሀገራዊ እድገት መፋጠን ድጋፉን እንደሚያጠናክርም እንዲሁ። አዲስ ገቢ ተማሪዎችን "በቃል ኪዳን ቤተሰብ" ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በማስተሳሰር ቆይታቸው ይበልጥ የተመቻቸ እንዲሆን እንደሚሰራም አስረድተዋል። በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዲን አቶ ጊዜው ፈጠነ፤ በዋናው ግቢና እና በመሃል ሜዳ ካምፓስ ከ3 ሺህ በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን ተናግረዋል። የመማር ማስተማር ሥራውን የተሻለ ለማድረግም የተማሪዎች መኖሪያና መማሪያ ክፍሎች፣ የምግብ ቤት፣ ቤተ መጻህፍት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት መስጫና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች መመቻቸታቸውንም አስታውቀዋል። የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ኪሮስ አሸብር በበኩሉ፤ ለተማሪዎች እየተደረገ ያለው አቀባበል ከቀድሞ በእጅጉ የተሻለ ነው ብሏል። የተማሪ ኮሚቴዎች ተመድበው ከአውቶቡስ መናኸሪያና ከከተማው መግቢያና መውጫ በሮች ተማሪዎችን በመቀበል ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጿል። ልጃቸውን ዩኒቨርሲቲው ድረስ ካመጡት ወላጆች መካከል ወይዘሮ ዘርፌ ቶላ በሰጡት አስተያየት፤ በአካባቢው ሕብረተሰብ የተደረገላቸው አቀባበል ልጃቸው በቤቱ እንደሚማር ያህል እንደተሰማቸው ተናግረዋል። "የቃል ኪዳን ቤተሰብ " መመስረቱ ደግሞ የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማጠናከር ወሳኝ ተግባር መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌላው ወላጅ መሪጌታ ኢሳያስ ደምሴ ናቸው።    
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ አፍሪካውያንን አንድ በሚያደርጉ አሰባሳቢ አጀንዳዎች ላይ ትልቅ ሚና እየተጫወተች ነው - የጣና ፎረም የቦርድ አባል ጆይሴ ባንዳ (ዶ/ር)
Oct 27, 2025 6
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ አፍሪካዊያንን አንድ በሚያደርጉ አሰባሳቢ አጀንዳዎች ላይ ትልቅ ሚና እየተጫወተች ነው ሲሉ የቀድሞ የማላዊ ፕሬዝዳንትና የጣና ፎረም የቦርድ አባል ጆይሴ ባንዳ (ዶ/ር) ገለጹ። ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀድሞ የማላዊ ፕሬዝዳንት ጆይሴ ባንዳ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ አፍሪካውያንን በሚያሰባሰቡ የጋራ ዓላማዎች ዙሪያ ተጠቃሽ ሚና እየተጫወተች ነው። በቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአሁኑ አፍሪካ ኀብረት ምስረታ ሂደት የኢትዮጵያ ሚና ጉልህ መሆኑንም አስታውሰዋል። በአፍሪካ ሠላምና አንድነትን ማረጋገጥ የተሻለች አህጉርን የመገንባት ግብን ለማሳካት ወሳኝ እንደሆነ በማንሳት፥ አፍሪካውያን በጋራ ተቀራርበው እየተወያዩ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጡባቸው መድረኮች ሊጠናከሩ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ የጣና ፎረምን በመመስረት ችግሮቻችንን እንድንፈታ እያሰባሰበችን ነው ያሉት ጆይሴ (ዶ/ር)፥ አፍሪካን አንድ በሚያደርጉ አጀንዳዎች ላይ እየተጫወተች ያለው ሚና የሚደነቅ ነው ብለዋል። በልማት በኩልም የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎችን በማስተባበር እያስመዘገበ ያለው ስኬት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል።   በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ተንታኝ ፓ ኪዌሲ ሄቶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ አፍሪካውያን በአንድ ተሰባስበው የፖለሲ መፍትሄዎችን እንዲቀይሱ አስቻይ ሁኔታ እየፈጠረች መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ድልድይ ሆና እያገለገች ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን ፈለግ በመከተል ለአፍሪካ አንድነት መጠናከር ሊረባረቡ እንደሚገባ አመልክተዋል። በአፍሪካ ልንፈታቸው የለየናቸው ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እንደ ድልድይ ሆነው የሚያስተባብሩ በርካታ ተዋንያን ይፈልጋሉ ያሉት ፕሮፌሰሩ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ምሳሌ መሆን የምትችል ሀገር ናት ብለዋል።
ተኪ ምርት አምራቾች የመንግሥት የግዥ መመሪያ የሰጣቸውን ሰፊ የገበያ ዕድል በአግባቡ እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ
Oct 27, 2025 28
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦ተኪ ምርት አምራቾች የመንግሥት የግዥ መመሪያ የሰጣቸውን ሰፊ የገበያ ዕድል በአግባቡ እንዲጠቀሙ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ጥሪ አቀረቡ። የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የመንግሥት ግዥ ሥርዓት ለአምራች ዘርፉ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በተመለከተ ለዘርፉ ተዋንያን ማብራሪያ ሰጥቷል።   መንግሥት የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል የግዥ መመሪያ አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ ነው ተብሏል። በግዥ መመሪያው በሀገር ውስጥ ለሚመረትና 20 በመቶ እሴት ለሚጨመርባቸው እንዲሁም በመልሶ መጠቀም ለሚመረቱ ምርቶች ቅድሚያ የሚሰጥበት ዕድል ተመቻችቷል። በውይይት መድረኩ የተሳተፉ አምራቶች ከውጭ ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ ምርቶች ተኪ ምርት አምራቾች ላይ ጫና እያሳደሩ መሆኑን ጠቅሰዋል። ለሀገር ውስጥ ምርቶች ጥራት ያለው አመኔታ ዝቅተኛ መሆንና የአመለካከት ክፍተት የገበያ እድሎችን እንዳንጠቀም የራሱ አሉታዊ ውጤት እንዳለው በምክንያትነት አንስተዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል መንግሥት የኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሕግና አሰራር ማሻሻያዎችን ከማድረግ ባለፈ የገበያ ትስስርን ለማሳደግ ተጨባጭ ሥራዎች እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ፣ አሁን ያለው የመንግሥት ግዥ መመሪያ የሀገር ውስጥ አምራችነትን የሚያበረታታና ገቢ ምርትን ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑን አንስተዋል። በተለይም ሀገር ውስጥ ከሚመረቱ ምርቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ለማስቀረት ተጨማሪ ቀረጥ ይጣላል ብለዋል። የሀገር ውስጥ አምራቾች በመንግሥት ተቋማት የተፈጠረውን የግብይት ሥርዓት በመጠቀም የገበያ ዕድላቸውን እንዲያሰፉ አስገንዝበዋል። መንግሥት የአምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ የሀገር ውስጥ ግዥን በስፋት እየተጠቀመ ቢሆንም የግዥ መመሪያውንና አሠራሩን በአግባቡ አለመጠቀም እንደሚስተዋል አመልክተዋል። በመሆኑም አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፎ ለውጭ ገበያ ምርቶችን የማቅረብ ዕድላቸውን አሟጠው እንዲጠቀሙ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ በበኩላቸው፣ ተኪ ምርት አምራቾች በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪነታቸው እየጨመረ መጥቷል ብለዋል። እሴት ለጨመሩ ኢንዱስትሪዎች የሚደረገው የ20 በመቶ ማበረታቻ አምራችነትን የሚያበረታታ መሆኑን ነው የተናገሩት።   የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሰረት መስቀሌ፥ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓቱ ቀልጣፋ መሆኑን ጠቅሰው፣ የመንግሥት ተቋማት ጥራት ያላቸው ምርቶችን ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች እንዲያገኙ እያደረገ ነው ብለዋል። የመንግሥት የግዥ መመሪያው ግልጽ የጨረታ ሂደትን ከመከተል ጀምሮ አምራች ኢንዱስትሪውን የሚያነቃቃ መሆኑን ጠቅሰው፥አምራቹ ስለ ግዥ አዋጁና መመሪያው ያለውን ግንዛቤ የበለጠ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግስት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር ያለውን ትብብር ያጠናክራል
Oct 27, 2025 36
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018 (ኢዜአ)፦ መንግስት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገንዘብ ሚኒስቴር ገለፀ። የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እ.አ.አ ከ2025 እስከ 2030 በኢትዮጵያ በጋራ የሚተገበሩ የልማት መርሃ ግብሮች ስትራቴጂ ይፋ ተደርጓል።   መርሃ ግብሮቹ ተቋማዊ አቅምንና የሰው ሀብትን ማጠናከር፣ የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ማሳደግ፣ የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም ላይ ያተኮሩ ናቸው። የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እንዳሉት፥ የኢትዮጵያን የልማት አጀንዳዎችና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መሳካት የልማት አጋሮች እያደረጉ ያለው ድጋፍ ጉልህ ነው። የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ባለፉት ዓመታት ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ በሥርዓተ-ፆታ እኩልነት እና በማኅበራዊ ልማት መስኮች አበረታች ስራዎችን ማከናወናቸውን አንስተዋል። ሁለቱ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ይፋ ያደረጓቸው አዲስ መርሃ ግብሮች ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ያለንን የጋራ ጥረት የሚያሳይና ከኢትዮጵያ የልማት እቅዶችና ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር የተሰናሰሉ ናቸው ብለዋል። የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትብብርና በመናበብ መስራት አስፈላጊ መሆኑን መንግስት ይገነዘባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ለዚህም ከአጋር አካላት በጋራ በመስራት የስራ ድግግሞሽን እንዲቀንሱ ይሰራል ብለዋል።   በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ተወካይ ሳሙኤል ዶ (ዶ/ር) በበኩላቸው ለአምስት ዓመት በሚተገበረው የልማት መርሃ ግብር ተቋማትን ለማጠናከር ይሰራል ብለዋል። ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን የልማት እቅዷ አካል በማድረግ አካታች ብልፅግናን ለማሳካት እየተጋች መሆኗን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድ ተወካይ ኮፊ ኩዋሜ በበኩላቸው መርሃ ግብሮቹ በሰው ሀብት ልማት ያለንን ትብብርና አጋርነት ለማጠናከር የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።   በስርዓተ-ጾታ፣ ስነተዋልዶ ጤና፣ ሴቶችንና ወጣቶችን ማብቃት ላይ ያተኮሩና ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለመሆን እየሰራች ያለውን ተግባር የሚያጠናክሩ ስለመሆናቸውም ነው ያብራሩት። የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድ በመርሃ ግብሩ ከፌዴራልና ከክልል ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር እንደሚያጎለብት ጠቁመዋል።    
የባሕር በር ባለቤትነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅ የህልውና ጉዳይ ነው - ሌተናል ሃለፎም መለሰ
Oct 27, 2025 69
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦የባሕር በር ባለቤትነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የቀድሞ የባሕር ኃይል ማህበር ሊቀ መንበር ሌተናል ሃለፎም መለሰ ገለጹ። ሌተናል ሃለፎም መለሰ ከኢዜአ ጋር በባህር በር ጉዳይ ላይ ቆይታ አድርገዋል። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የኢትዮጵያን የጠረፍ ጠባቂ በሚል በ1946 ዓ.ም በአዋጅ መሰረት የተጣለው የባሕር ኃይል እስከ ደርግ መንግስት ሥርዓት መውደቅ ድረስ በተደራጀ መልኩ መስራቱን ነው የገለጹት። የቀድሞ ባህር ሃይል የኢትዮጵያን የባሕርና ጠረፍ አካባቢ ደኅንነት በአስተማማኝነት መልኩ መጠበቁን ያስታውሳሉ። የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የዓባይ ወንዝና ከባህር ተጠቃሚነት ለማራቅ ከጥንት ጀምሮ ያላቆመ ሴራ መኖሩን ያስታወሱት ሊቀ መንበሩ፤ ከደርግ መንግስት መውደቅ በኋላ አገሪቷ የባህር በር እንድታጣ መደረጉን ተናግረዋል። ዓባይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ብስራትን ያሰማ መፍትሔ ማግኘቱን ጠቅሰው፥ኢትዮጵያን የባሕር በር እንዳይኖራት ለማድረግ የተሸረበው ሴራም በውጭ ባዕዳንና በውስጥ ባንዳዎች የተፈጸመ መሆኑን ገልጸዋል። የለውጡ መንግስት የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ለመመለስ አጀንዳ ማድረጉን አድንቀው፥የባሕር በር የሀገር ህልውና ማስጠበቂያና የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳለጫ መሳሪያ ነው ብለዋል። መንግስት የባሕር በር ጉዳይ በወሳኝ አጀንዳነት ወደፊት ማምጣቱ ታላቅ ጉዳይ መሆኑን አመልክተው፤የባሕር በር አልባነትም የመኖር አለመኖር የህልውና ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል። በዚህም የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄን ተገቢ ምላሽ ለማስገኘት ዜጎች በሁሉም ዘርፍ አንድነታቸውን በማጽናት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። በተለይም በኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተደረገውን ትብብር ለባሕር በር ባለቤትነት በአንድነት መስራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
አስተዳደሩ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ከመመከት አንጻር እያሳየ ያለውን ውጤታማ ሥራዎች ማጠናከር ይገባዋል - ቋሚ ኮሚቴው
Oct 27, 2025 20
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሀገር ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ከመመከት አንጻር እያሳየ ያለውን ውጤታማ ሥራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።   የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ባቀረቡት ሪፖርት፤ ሀገራዊ የሳይበር ቁጥጥርን ከማጎልበት አኳያ ውጤታማ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ተልዕኮ ተኮር ምርትና አገልግሎት ተደራሽነትን ከማስፋት አኳያም ውጤታማ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ቁልፍ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም መገንባቱን ጠቁመው፤ በሩብ ዓመቱ ለተመዘገቡ 13 ሺህ 443 የጥቃት ሙከራዎች ምላሽ መስጠት መቻሉን ተናግረዋል። በሩብ ዓመቱ በርካታ አገልግሎቶች ተደራሽ መደረግ መቻላቸውን ጠቁመው፤ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ አስተዳደር ስርዓት ተጠናቆ በይፋ መመረቁንም ገልጸዋል። በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ የኤሮ-አባይ የድሮን ማምረቻ፣ የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ስርዓት፣ ለበርካታ ከተሞች የካደስተር ኢ-ላንድ መተግበሪያን ጨምሮ ሌሎችንም ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትም የተቋሙን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም በማድነቅ ምላሽና ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮችንም አቅርበዋል። ከእነኚህም መካከል የሀገርን የሳይበር ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና የሳይበር ጥቃትን ቀድሞ ከመከላከል አንጻር የተቋሙ አሁናዊ ቁመና ምን እንደሚመስል ጠይቀዋል። በተጨማሪም የተቋሙ ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አጋርነት፣ ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከውጤት አንጻር ምን ማሳያ አለው የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና ማብራሪያዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ የሳይበር ደህንነትን ከማስጠበቅ አኳያ አስተማማኝ ሁኔታ ላይ መሆኑን ተናግረዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ የምላሽ አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ጠቁመው፤የተቋሙ ዝግጁነትም እያደገ መሆኑን አንስተዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አማካሪ ፍቅረስላሴ ጌታቸው ተቋሙ የተለያዩ ስምምነቶችን ከመፈራረም ባሻገር ስምምነቶችን ወደ ተግባር በመለወጥ ትልቅ ፋይዳ እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኢንፎርሜሽን አሹራንስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ሃኒባል ለማ በበኩላቸው፤ የስትራቴጂክ ዕቅዶችን በሶስት ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ዕቅድ መያዙን ጠቁመው፤ ይህም የመሰረተ ልማት ግንባታንና ሥራን መሠረት ያደረገ ነው ብለዋል።   በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሰቢ ፈቲህ ማሕዲ (ዶ/ር) በሰጡት ማጠቃለያ፣ አስተዳደሩ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ከመመከት አንጻር እያሳየ ያለውን ውጤታማ ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። በቅድመ መከላከልና ዝግጁነት የተሰሩ አበረታች ሥራዎችን ማጠናከር እንዳለበት ጠቁመው፤ ተቋሙ ብቁ የሰው ኃይልን ከማፍራት አኳያ የጀመራቸውን ውጤታማ ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።  
የዲጂታልና የቴክኖሎጂ ፈጠራ አርበኛ የሆነ ትውልድ እየተፈጠረ ነው- ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል 
Oct 25, 2025 239
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ፣ ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት በተሰጠው ትኩረት የዲጂታልና የቴክኖሎጂ ፈጠራ አርበኛ የሆነ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ4ኛው ዙር ሰመር ካምፕ በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶችን አስመርቋል።   በመርሃ ግብሩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የሠላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ፣የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት በዲጂታል ዘመን ወቅቱን የዋጀ በክህሎት መር እውቀት የሠለጠነ ዜጋን ማፍራት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶታል። የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሳይበር ደህንነት እና ዘመኑ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ እውቀት የታጠቁ ወጣቶችን በተከታታይ የማሰልጠንና የማሰማራት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።   በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ስራ ለመስራት በሰው ኃብት ልማት በተለይ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ወጣቶች አቅም ለማጎልበት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የሳይበር ጥቃትን በብቃት የሚከላከልና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ህልምን የሚያሳካ የዲጂታል አርበኛ የሆነ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ በዲጂታል ዘርፉ ላይ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል እያደረገች ላለው ሽግግር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የበቃ የሰው ኃይል ወሳኝ ነው ብለዋል።   የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ዋና ዓላማ በዘርፉ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶች ክህሎት በማሳደግ እና በዘርፉ ለሀገር የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል። ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፥ ወቅቱን የሚመጥን ብቁ፤ ዕውቀት እና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት የሳይበር ታለንት ስልጠና አጋዥ መሆኑን ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ትስስር በመፍጠር እና በተቋሙ የሚሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች እውቅና እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።   የፈጠራ ስራዎችን የበለጠ ለማጠናከር የሚያግዝ የሥራ ፈጣሪዎች አቅም ማጎልበቻ ማዕከል ከፍቶ ወደ ስራ ማስገባቱንም ገልጸዋል። በዚህም በሰመር ካምፕ የፈጠራ ስራ ያላቸው ታዳጊዎች በማዕከሉ ውስጥ የፈጠራ ስራቸውን ማስፋትና ወደ ገበያ የሚያቀርቡበትን ዕድል ከመፍጠር ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በሰመር ካምፑ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች በበኩላቸው በቆይታቸው የተለያዩ ክህሎቶችን ማግኘታቸውን ገልጸው በቀጣይ ሀገራቸውን በዲጂታል ዘርፎች ለማገልገል ፍላጎት እንዳላቸው ጠቅሰዋል።   ወጣት አሌክሳንደር ሳሙኤል የኢ-ለርኒንግ ስርዓት ማበልጸጉን በማንሳት፥ የጀመረው ሥራ የትምህርት ስርዓቱን በዲጂታል ለማሳለጥ ዓላማ ያለው ነው ብሏል።   ሌላው ወጣት ኬና ቶልቻ በበኩሉ በቆይታው በኤሮስፔስ ዘርፍ ስልጠና መውሰዱን በመግለፅ፥ በድሮን ኦፕሬሽን ላይ እውቀት መቅሰሙን ጠቁሟል።   ወጣት ባስሌል መስፍን በበኩሉ በሶፍትዌር ማበልፀግ ስልጠና እንደወሰደ ጠቅሶ፥ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን የህዝብ ትራንስፖርት አጠቃቀም የሚያሳልጥ መተግበሪያ መስራታቸውን ገልጿል።
የታዳጊዎችና ወጣቶችን የፈጠራና ክህሎት አቅም ለማጎልበት የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Oct 25, 2025 128
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ የሆነ ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት የታዳጊዎችንና የወጣቶችን የፈጠራና የክህሎት አቅም ለማጎልበት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ4ኛው ዙር ሰመር ካምፕ በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶችን አስመርቋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የሠላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።   የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት በዲጂታል ዘመን ወቅቱን የዋጀ በክህሎት መር እውቀት የሠለጠነ ዜጋን ማፍራት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሳይበር ደህንነት እና ዘመኑ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ እውቀት የታጠቁ ወጣቶችን በተከታታይ የማሰልጠንና የማሰማራት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ጠቁመዋል። በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ስራ ለመስራት በሰው ኃብት ልማት በተለይ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ወጣቶች አቅም ለማጎልበት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል እያደረገች ላለው ሽግግር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የበቃ የሰው ኃይል ወሳኝ ነው ብለዋል። የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ዋና ዓላማ በዘርፉ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶች ክህሎት በማሳደግ እና በዘርፉ ለሀገር የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል። ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፥ ወቅቱን የሚመጥን ብቁ፤ ዕውቀት እና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት የሳይበር ታለንት ስልጠና አጋዥ መሆኑን ጠቁመዋል።
አጀንዳ 2063ን ለማሳካት የአህጉሪቱን ወጣቶች የፈጠራ አቅም  ማጎልበት ይገባል - ምክትል ሊቀ-መንበር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ
Oct 22, 2025 331
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2018(ኢዜአ):- የበለፀገች አፍሪካን ለመገንባት ቴክኖሎጂና ፈጠራን ከአጀንዳ 2063 ጋር ማቀናጀትና የወጣቶችን የፈጠራ አቅም ማጎልበት እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት የኢኖቬሽን ፌስቲቫል በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡   ፌስቲቫሉ "የአፍሪካ ህብረት ወጣቶችን የአህጉራዊ ኢኖቬሽን መሪ የማድረግ ተግባር" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የሚካሄድ ሲሆን ኢኖቬተሮች፣ የፖሊሲ አውጪዎች፣ የግሉ ዘርፍ መሪዎች እና የወጣት ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፌስቲቫሉ ለሀገር በቀል የኢኖቬሽን መፍትሄዎች እውቅና በመስጠት ስራዎችን የበለጠ ማላቅ ላይ ትኩረት የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ ፈጠራንና ቴክኖሎጂን ከአጀንዳ 2063 ጋር በማቀናጀት የበለፀገች አፍሪካን ለመገንባት መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡   አፍሪካን ለመለወጥና ለማሳደግ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ፈጠራን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የአህጉሪቱ የፈጠራ ችሎታ፣ የዲጂታል ለውጥ እና የሥራ ፈጠራ ዋና አንቀሳቃሽ ኃይሎች ወጣቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አህጉሪቱ በፈጠራ ዘርፍ የያዘችውን ግብ ማሳካት የሚችሉት ወጣቶች በመሆናቸው አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የሴቶች፣ የጾታ እና ወጣቶች ዳይሬክተር ፕሩደንስ ንግዌንያ በበኩላቸው ወጣቶችና ሴቶች የአፍሪካን የፈጠራ ምህዳር መሠረት መጣል ይገባቸዋል ብለዋል፡፡   አፍሪካ በፈጠራ ዘርፍ ማሳካት የምትፈልገውን ለውጥ እውን ለማድረግ በወጣቶችና ሴቶች የፈጠራ አቅም ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ የፌስቲቫሉ ተሳታፊ ወጣት ትመር ብርሃኔ አፍሪካዊያን በቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ዘርፍ ያለንን ዕውቀት በየጊዜው ማላቅ አለብን ስትል ተናግራለች፡፡   ወጣት አሜን ቢኒያም በበኩሏ የምንፈልጋትን አፍሪካ እውን ለማድረግ ፈጠራን እና ቴክኖሎጂን ማሳደግ ተገቢ መሆኑን ጠቅሳ ለዘርፉ የሚደረገውን ድጋፍ በማጠናከር የተያዘው ግብ ስኬታማ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝባለች፡፡   የኢኖቬሽን ፌስቲቫሉ እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት፣ አካታችና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ራዕይ አቀጣጣይ እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
ስፖርት
አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና አትሌት ትዕግስት አሰፋ የዓለም የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች እጩዎች ውስጥ ተካተቱ
Oct 27, 2025 43
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018 (ኢዜአ)፦ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና አትሌት ትዕግስት አሰፋ የዓለም የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ከስታዲየም ውጪ ዘርፍ እጩዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል። የዓለም አትሌቲክስ የዓለም ምርጥ አትሌት የተለያዩ ዘርፍ እጩዎችን ይፋ እያደረገ ይገኛል። የአትሌቲክሱ የበላይ አካል ዛሬ ባወጣው መረጃ ከስታዲየም ውጪ የዓለም ምርጥ አትሌት እጩዎች ዝርዝር ውስጥ በወንዶች አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና በሴቶች አትሌት ትዕግስት አሰፋ መካተታቸውን አስታውቋል። ታንዛንያዊው አልፎንስ ሲምቡ፣ ኬንያዊው ሰባስቲያን ሳዌ፣ ብራዚላዊው ካዮ ቦንፊም እና ካናዳዊው ኢቫን ደንፊ ሌሎች የወንዶች እጩዎች ናቸው። በትውልድ ኢትዮጵያዊቷ በዜግነት ኔዘርላንዳዊ የሆነችው ሲፋን ሀሰን፣ ኬንያውያኑ ፔሬዝ ጄፕቺርቺርና አግነስ ንጌቲች እንዲሁም ስፔናዊቷ ማሪያ ፔሬዝ በሴቶች ዘርፍ ተካተዋል። ከስታዲየም ውጪ የዓለም ምርጥ አትሌት ድምጽ አሰጣጥ ዛሬ የተጀመረ ሲሆን እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚቆይ የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል። በድምጽ አሰጣጡ ሂደት የዓለም አትሌቲክስ የባለሙያዎች ምክር ቤት 75 በመቶ እንዲሁም የዓለም አትሌቲክስ ቤተሰብ አባላት እና የሕዝብ ድምጽ 25 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ገልጿል። ምክር ቤቱና የአትሌቲክስ ቤተሰብ አባላት ድምጻቸውን በኢ-ሜይል የሚሰጡ ሲሆን ሌሎች የአትሌቲክስ አፍቃሪዎች በዓለም አትሌቲክስ የማህበራዊ ትስስር ገጽ አማራጮች መስጠት እንደሚችሉ ተጠቁሟል። የ2025 የዓለም ምርጥ አትሌቶች ሽልማት ህዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም በሞናኮ ይካሄዳል።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ዘላቂ የውሃና ኢነርጂ ልማት እንዲሁም ለጋራ ብልፅግና መሪ ሚና እየተወጣች ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Oct 27, 2025 94
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ዘላቂ የውሃና ኢነርጂ ልማት እንዲሁም ለጋራ ብልፅግና መሪ ሚና እየተወጣች ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ 2ኛውን የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሳምንት በሳይንስ ሙዚየም አስጀምረዋል።   በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ለታዳሽ ኃይል፣ ለውሃ እና ለአረንጓዴ ልማት በሰጠችው ትኩረት ለውጥ እያመጣች ሚሊዮኖችን ተጠቃሚ እያደረገች መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ የቀጣናው የኃይል ማዕከል እየሆነች ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለጂቡቲ፣ ለሱዳንና ለኬንያ ታዳሽ ኃይል እያቀረበች ነው ብለዋል። በቅርቡም ወደ ሌሎች ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደምትልክ ጠቅሰው፥ ይህም የጋራ ቀጣናዊ የብልጽግና ራዕይዋ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዚህ የላቀ ራዕይ ምሰሶ እንደሆነ ገልጸው፥ ግድቡ ጽናታችንን፣ አንድነታችንንና በአፍሪካ መጻኢ የጋራ ህልሞች ላይ ያለንን አቋም የሚያሳይ ነው ብለዋል። የግድቡ አገልግሎት ከኃይል ልማት ባሻገር ለብዝኃ ህይወት ጥበቃ፣ ጎርፍን ለመከላከልና በታችኛው ተፋሰስ ላሉ ሀገራት የተስተካከለ የውሃ ፍሰት እንዲያገኙ ያስችላል ነው ያሉት። ከፉክክር ይልቅ የጋራ ተጠቃሚነትንና ትብብርን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን በማንሳትም፥ ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿ የቀጣናው የትስስር መሠረቶች ናቸው በሚል ግልፅ አቋም እየሠራች እንደምትገኝ ገልጸዋል። ለአብነትም በአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ባለፉት ዓመታት ከተተከሉ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች አንድ ሦስተኛ ያህሉ በዓባይ ተፋሰስ መተከላቸውንና ይህም ለሌሎች ሀገራት ፋይዳው የላቀ መሆኑን አስረድተዋል።   በሌላ በኩል ኢኮኖሚያችን እያደገ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የባህር በር ማግኘት ለቀጣይ እጣፈንታችን ዋስትና የሚሰጥ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የባህር በር ለኢትዮጵያ የግድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የባህር በር ማግኘት ንግድን ለማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ውህደትን ለማጎልበትና ቀጣናዊ ትብብርን ለማሳደግ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር እጣፈንታዋ የተሳሰረ በመሆኑ በጋራ ለመልማት እና ዘላቂ ጥቅምን ለማስጠበቅ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ለማግኘት እየሠራች ነው ብለዋል። አፍሪካ ዘላቂ የውሃና ኢነርጂ ዋስትናዋን እንድታረጋግጥ ኢትዮጵያ መሪ ሚናዋን መወጣቷን እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።
‎እምቦጭን በዘላቂነት ለመከላከል የህብረተሰብ ተኮር ሥራ ውጤት እያስገኘ ነው
Oct 26, 2025 152
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-እምቦጭን በዘላቂነት ለመከላከል የህብረተሰብ ተኮር ሥራ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ‎በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትሩ አማካሪ ሞቱማ መቃሳ ገለጹ፡፡ በውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትሩ አማካሪ ሞቱማ መቃሳ ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ያቀደቻቸውን ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ለማከናወን የውኃ ሀብቷን መጠበቅ ወሳኝ ነው። ስለሆነም መንግስት በአገሪቷ የልማት እቅዶች ውስጥ የውኃ አስተዳደርና ጥበቃን ቅድሚያ ሰጥቶ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ‎ለአብነትም በአገሪቷ ውስጥ ምን ያህል የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ ሀብት እንዳለ በትክክል የመለየትና የመመዝገብ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።   ‎ይህን ሀብት ለየትኞቹ የልማት ዘርፎች በምን ያህል መጠንና ጥራት ለማዋል እንደሚቻል የውኃ አቅም ልየታ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የውኃ ሀብት አስተዳደርና ጥበቃ ስራ ከፍ ብሎ እንዲመራ ሚኒስቴሩ መዋቅራዊ ማሻሻያ ማድረጉንም አመልክተዋል። ‎ከፍተኛ ትኩረት ከሚሹ የውኃ አካላት ጥበቃ ጉዳዮች መካከል አንዱ በእምቦጭ አረም ምክንያት የሚከሰተውን ችግር ማቃላል መሆኑን አመልክተዋል። ‎እምቦጭ በፍጥነት የሚስፋፋና በየጊዜው ተመልሶ የሚመጣ መሆኑን ያወሱት አቶ ሞቱማ፤ በዘላቂነት ለማቃለል በየጊዜው አስቸጋሪ ፈተና መሆኑን አንስተዋል። ይህንን ችግር መፍትሄ ለመስጠት ሚኒስቴሩ በትኩረት እየሰራበት እንደሚገኝም አብራርተዋል። ‎ይህን ዘላቂ ችግር ለማቃለል ህብረተሰብን ያማከለ አሰራር ተቀይሶ በመተግበር ላይ እንደሚገኝና ውጤትም እየተገኘበት እንደሆነም አስታውቀዋል። በጣና ሐይቅና በሌሎች የውኃ አካላት ላይ የእምቦጭ አረምን ችግር ለመፍታት ከተጀመሩ ሥራዎች በተጨማሪ ህብረተሰብ ተኮር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ሞቱማ ተናግረዋል። ‎የውኃ ሀብት ጥበቃና አስተዳደር የሀገር ጉዳይ በመሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና መላው ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የደን ሽፋን ማደግና የፓርኮች ልማት አዕዋፍትንና የዱር እንስሳትን ከስደት ታድጓል
Oct 26, 2025 109
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተከናወነው ሥራ የደን ሽፋን ማደግና የፓርኮች ልማት አዕዋፍትንና የዱር እንስሳትን ከስደት እየታደገ መምጣቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ገለጹ። የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን 16ኛውን ዓለም አቀፍ የስደተኛ አዕዋፍ ቀንን "ለአዕዋፍት የተመቸ ማህበረሰብ እና ከተማ እንፍጠር" በሚል መሪ ሃሳብ በአቢጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ አክብሯል።   የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ቀኑን ማክበር ያስፈለገው ለህብረተሰቡ ስለ እንስሳት ሀብት ጥበቃ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው። አዕዋፋትና የዱር እንስሳት በመኖሪያ አካባቢያቸው በሚደርስ መራቆት ምክንያት ለስደት እንደሚዳረጉ ተናግረው፤ በዚህም ኢትዮጵያ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም ሳታገኝ መቆየቷን ገልጸዋል።   የአዕዋፍት እና የዱር እንስሳት ስደት ችግርን ከስር መሰረቱ ለመፍታት የጥበቃ ቦታዎችን ማልማትና ማስፋፋት እንደሚገባ ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በተከታታይ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአገር ደረጃ የደን ሽፋን ማደጉን ያወሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ይህም ለዱር እንስሳት ምግብና መጠለያ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው አብራርተዋል። የአካባቢ ጥበቃ እያደገ በመምጣቱ ሐይቆችም ወደ ድሮ ይዞታቸው መመለሳቸውን አመላክተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ፓርኮችን የመጠበቅ እና አዳዲስ የጥበቃ ስፍራዎችን የማልማት ተግባራት በስፋት ማከናወናቸውን ጠቁመዋል።   በአሁኑ ወቅት የአዕዋፋት እና የዱር እንስሳት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አመልክተው፤ የፓርኮችን ይዞታ በማሻሻልና ያሉትን በመጠበቅ ተሰደው የቆዩ የዱር እንስሳት ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማስቻሉንም አስታውቀዋል። የዱር እንስሳት ለአደጋ ተጋላጭነት በእጅጉ እየቀነሰ መምጣቱን አንስተዋል። ኢዜአ ከነጋገራቸው ጎብኝዎች መካከል አቶ ዘሪሁን ግርማ ፤ መንግስት ከባለድርሻ አካላት ጋር በደን ልማትና በዱር እንስሳት ጥበቃ ላይ እያከናወነ ያለው ተግባር ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል፡፡   ሌላኛዋ ከቻይና የመጡት ጎብኝ ፒንግ ሁ በበኩላቸው፤ አቢጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ ከዚህ በፊት አውቀዋለሁ፤ ሃይቆች ለመጥፋት የተቃረቡና ደኖችም ጥበቃ የማይደረግላቸው ነበሩ ብለዋል፡፡   አሁን ግን እጅግ ተለውጠው ሳቢ እና ማራኪ ሆነዋል፤ አዕዋፋትና የዱር እንስሳትንም በብዛት ተመልክቻለሁ ነው ያሉት፡፡ አቶ ጌትነት አማረ በበኩላቸው፤ መንግስት በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ላይ እያከናወነው ያለው ተግባርና እየመጣ ያለው ለውጥ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡   በጉብኝቱ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር፣ ባለድርሻ አካላት፣ አርቲስቶች፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና የባለስልጣኑ ሰራተኞች ተገኝተዋል።
ውብ ሐረርን ለትውልድ ለማሻገር …
Oct 26, 2025 129
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡- ሰሞኑን በሳንፍራንሲስኮ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ሐረር ከተማን ከፕላስቲክ ቆሻሻ ነፃ ለማድረግ የተጀመረው ኢንሼቲቭ እያስገኘ ላለው ውጤት ዕውቅና ተሰጥቷል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሐረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ለአሁኑ ነዋሪ ብሎም ለመጪው ትውልድ ጽዱ፣ ውብ እና ምቹ ሐረርን ለማንበር ያለሙ ስምምነቶች ተፈርመው እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል። ከእነዚህ ስምምነቶች አንዱ ‘ኪዩቢክ ፕላስቲክ ፕራይቬት’ የተሰኘ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት እና የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት በፈረንጆቹ ሚያዝያ 2024 የተፈራረሙት አንዱ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህ የውል ስምምነት መሠረትም፤ ቤት ለቤት እና ከድርጅቶች የሚሰበሰቡ ፕላስቲክና ፕላስቲክ ነክ ደረቅ ቆሻሻዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በከተማዋ ከሚሰበሰበው ቆሻሻ እስከ 48 በመቶ ያህሉ ፕላስቲክና ፕላስቲክ ነክ ቆሻሻ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ይህ ፕላስቲክና ፕላስቲክ ነክ ቆሻሻ በንፋስ ምክንያት እየተበተነ አካባቢን እንደሚበክል አስገንዝበው፤ ይህን ከማስቀረት አልፎ ከየቤቱና ድርጅቶች የሚወጣው የፕላስቲክ ቆሻሻ ተለይቶ ‘ፕሮሰስ’ ተደርጎ እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውል ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ከፕላስቲኩ በሚሠራ ጡብ የቤት ግንባታ እንደሚከናወን ተናግረዋል። ለአብነትም ከ500 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ፕላስቲክና ፕላስቲክ ነክ ቆሻሻ ወደ ፕሮሰስ በማስገባት፤ በሐረር ከተማ ጁገል አካባቢ ቤተ መጻሕፍት መገንባቱን አረጋግጠዋል። ከዚህ በመነሳት ወጪ ቆጣቢ ስለሆነ ለሌሎች ቤቶች ግንባታ እንደሚውልም በጥናት መረጋገጡን ጠቅሰዋል። የሚሰበሰበው የፕላስቲክ ቆሻሻ በበዛ ቁጥር እንደገና የሚሰጠው ጥቅምም በዚያው ልክ ያድጋል ብለዋል። ሕብረተሰቡን የማስተማር ሥራ መሠራቱን ጠቅሰው፤ በተለይ ሴቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር በሚሰበስቡት ፕላስቲክ ልክ ገንዘብ እየተከፈላቸውም መሆኑን ነው የገለጹት። እስካሁንም ከ600 በላይ ሴቶች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል። ቆሻሻን በአግባቡ በመሰብሰብ እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውል እየተደረገ ባለው ጥረት በሐረር ከተማ በየአካባቢው ይታይ የነበረው የፕላስቲክነክ ደረቅ ቆሻሻ መቀነሱን አረጋግጠዋል። አሁን እየተገኘ ያለው ውጤት በቀጣይ ብዙ ለመሥራት ዐቅም እንደሚሆንም አመላክተዋል። ለዚህ ጥሩ ጅማሮም ሐረርን ከፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለት ነጻ ለማድረግና ፕላስቲክ ቆሻሻን እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል እየተደረገ ላለው ጥረት በሳንፍራሲስኮ የተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ዕውቅና ሰጥቶናል ብለዋል። ከዕውቅናው በፊት የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በሐረር ተገኝተው ግምገማ ማድረጋቸውንም አውስተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህም በአንድ ወቅት መጥተው መጎብኘታቸውን እና ወደ ሌሎች ከተሞችም መስፋት ያለበት ጥሩ ተሞክሮ መሆኑን መግለጻቸውን ተናግረዋል። ሕብረተሰቡም ፕላስቲክን ከሌሎች ቆሻሻዎች ጋር ቀላቅሎ ከመጣል ተቆጥቦ በአግባቡ እንዲወገድ የማድረግ ልምዱ እየዳበረ መሆኑን አንስተው፤ለነዋሪ ምቹና ጽዱ ሐረርን ለማንበር በሚደረገው ጥረት የሕብረተሰቡ ሚና እንዲጠናከር ጠይቀዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ለአህጉሪቷ ለዘላቂና አስተማማኝ የምግብ ሥርዓት ግንባታ አባል ሀገራት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው  
Oct 24, 2025 214
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ):-ለአህጉሪቷ አስተማማኝና ዘላቂ የምግብ ሥርዓት ግንባታ አባል ሀገራት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡   በስብሰባው ላይ የአባል አገራት በግብርና፣ በእንስሳት፣ በዓሳ ሀብት፣ በገጠር ልማት፣ በውሃ፣ በአካባቢ እና በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፎች ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በስብሰባው የሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም የማላቦ አጀንዳ (እ.ኤ.አ 2014 እስከ 2025) መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን፤ በመጪዎቹ አስር ዓመታት የሚተገበረው የካምፓላ አጀንዳ (እ.ኤ.አ 2026 እስከ 2035) ጸድቋል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ እንደገለጹት፤ በአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብሎም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አባል ሀገራት የራሳቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል፡፡ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም የግብርና ግብዓቶችንና ምርጥ ዘርን መጠበቀ እንዲሁም ብዝሃ ህይወትን ማልማትና መንከባከብ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና የውሃ ኃብትን ከማሳደግ አኳያም ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ - ኒፓድ የግብርና፣ የምግብ ዋስትና እና የአካባቢ ዘላቂነት ዳይሬክተር ኤስቴሪን ፎታቦንግ የካምፓላ አጀንዳ (2026–2035) በአፍሪካ የግብርና-ምግብ ሥርዓቶች ላይ የለውጥ ምዕራፍ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ገልጸዋል፡፡   ከአጀንዳው ግቦች መካከልም ዘላቂ የምግብ ምርትን፣ አግሮ-ኢንዱስትሪያላይዜሽንን እና ንግድን ማጠናከር፣ ለግብርና-ምግብ ሥርዓት ለውጥ ኢንቨስትመንትና ፋይናንስን ማሳደግ ብሎም የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚሉ እና ሌሎችም ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ የካምፓላ አጀንዳ ስትራቴጂ እንዲሳከ ምቹ ሁኔታዎችን ሲያዘጋጅ መቆየቱንም ጠቁመዋል፡፡ የዩጋንዳ ግብርና ሚኒስትር ዴኤታ እና የአምስተኛው የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ተወካይ ፍሬድ ብዊኖ ክያኩላጋ የካምፓላ አጀንዳ የእንስሳት ሃብትን ማሳደግ ላይ ትልቅ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል፡፡   በዚህም ለእንስሳትና ለዓሳ እርባታ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ የእንስሳት መኖ ማሳደግ፣ ለእንስሳት ጤና እንዲሁም የዘረመል መሻሻልም ከትኩረት መስኮች መካከል ናቸው ብለዋል፡፡ የካምፓላ አጀንዳ የአፍሪካ ግብርና ልማት መርሃ ግብር ታላላቅ ግቦች መሳካት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀመረ
Oct 24, 2025 156
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ)፦11ኛው የጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። ከዛሬ ጥቅምት 14 እስከ 16/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው 11ኛው ጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በፎረሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት፣የዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ቀጣናዊ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የጣና ፎረም "አፍሪካ በተለዋዋጩ የዓለም ሥርዓት" በሚል መሪ ሃሳብ በባሕር ዳርና አዲስ አበባ ከተሞች በአፍሪካ የደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ለሶስት ቀናት የሚመክር ይሆናል። የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና ተሳታፊ ሙያተኞች በአፍሪካ የደኅንነት ጉዳዮችና በአፍሪካዊ መፍትሔዎች ልምድና ዕውቀታቸውን የሚያካፍሉበት ዝግጅትም ተጠባቂ የፎረሙ የመርሃ ግብር አካል ነው። በፎረሙ ላይ በመሪዎችና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ልዩ መልዕክተኞች ምክክር እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በቀጣናው መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል የተጀመሩ የቅንጅት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ኢጋድ
Oct 20, 2025 353
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) በቀጣናው የሚታየውን መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር የጀመራቸውን የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ። የኢጋድ ሶስተኛው የሰራተኛ፣ ስራ እና የሰራተኛ ፍልሰት የሚኒስትሮች ስብሰባ ዛሬ በኬንያ ናይሮቢ ተጀምሯል። “በኢጋድ ቀጣና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሰራተኛ ፍልሰት እና የሰዎች ዝውውር ህጋዊ ማዕቀፍን ማሻሻል” የስብሰባው መሪ ቃል ነው። በስብሰባው ላይ የኢጋድ አባል ሀገራት የሰራተኛ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ባለሙያዎች፣ ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(አይኤልኦ)፣ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት(አይኦኤም)፣ የአውሮፓ ህብረትና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል። በኢጋድ ቀጣና የሰራተኛ፣ ስራ እና የሰራተኛ ፍልሰት ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በቀይ ባህር መስመር ያለውን መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ይካሄዳል። በስብሰባው ላይ ከኢጋድ ቀጣና ውጪ የሚገኙ ዜጎች አባል ሀገራትን በነጠላ የመግቢያ ቪዛ መጎብኘት የሚያስችላቸውን የቪዛ ኢኒሼቲቭ ይፋ ይደረጋል። ኢኒሼቲቩ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርና ድንበር ተሻጋሪ ንግድን ማሳለጥ እንዲሁም ቱሪዝምን የማሳደግ ፋይዳ እንዳለው ኢዜአ ከኢጋድ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በአውሮፓ ህብረት የፋይናንስ ድጋፍ የሚተገበረው ነጻ የሰዎችና የቁም እንስሳት እንቅስቃሴ የህግ ማዕቀፍ ሁለተኛ ምዕራፍ ይፋ ይሆናል። ማዕቀፉ ህጋዊ የፍልሰት መንገዶች ለማጠናከር እና ቀጣናዊ ትስስርን የማሳካት ግብ ያለው መሆኑንም አመልክቷል። ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰንሰለትን መበጣጠስ፣ በፍልሰት በሌላ ሀገር የሚገኙ ዜጎች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ላይ ምክክር ያደርጋሉ። በውይይቱ ማብቂያ ሀገራት የጋራ መግለጫ እንደሚያወጡ የሚጠበቅ ሲሆን ደህንነቱ የተጠበቀ መደበኛ ፍልሰት፣ ጠንካራ የሰራተኛ አስተዳደር ስርዓት መፍጠርና ለሰዎች ዝውውር የተቀናጀ ቀጣናዊ ምላሽ መስጠት ላይ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን እንደሚገልጹ ተጠቁሟል። ኢጋድ በቀጣናው የሚታየውን መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር የጀመራቸውን የጋራ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክቷል። ዜጎች ህጋዊ አማራጮችን እንዲከተሉና የኢኮኖሚ ፈተናን ጨምሮ ለሌሎች ገፊ ምክንያቶች ዘላቂ መፍትሄ መስጠት በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝ ገልጿል። ስብሰባው ጥቅምት 10 እና 11 በባለሙያዎች፣ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሚኒስትሮች ደረጃ ይካሄዳል።
የአፍሪካ ሀገራት ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራምን በቁርጠኝነት ሊተገብሩ ይገባል- የአፍሪካ ህብረት
Oct 19, 2025 356
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 8/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካ ሀገራት ሁሉን አቀፍ የአፍሪካ የግብርና ልማት ፕሮግራም (ካዳፕ) አፈጻጸም ውጤታማነት ለማሳደግ በትኩረት እንዲሰሩ የአፍሪካ ህብረት አሳሰበ። ስድስተኛው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ መደበኛ ስብስባ ከጥቅምት 11 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል። በስብሰባው ላይ ሚኒስትሮች፣ ባለሙያዎች እና የልማት አጋሮች ይሳተፋሉ። የአፍሪካ የግብርና ኢኒሼቲቮች አፈጻጸም መገምገም እና ዘርፉ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከር የስብሰባው አላማ ነው። እ.አ.አ በ2023 በአዲስ አበባ የተካሄደውን አምስተኛው የልዩ ኮሚቴ ስብሰባ ውጤቶች ግምገማ ይደረጋል። የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም (ካዳፕ) የማላቦ ድንጋጌ (ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2025) ስኬቶች እና የካዳፕ የካምፓላ ድንጋጌ (ከእ.አ.አ 2026 እስከ 2035) አፈጻጸም ላይ ውይይት ይካሄዳል። የስርዓተ ምግብን ማጠናከር፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ምርታማነት ስርዓት መዘርጋት፣ የበካይ ጋዞችን ልህቀት መቀነስ እና ዘላቂ የውሃና ተፈጥሮ ሀብቶች አስተዳደርን ማጠናከር ሌሎች የምክክር አጀንዳዎች ናቸው። በአፍሪካ በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ኑሮ በማሻሻል ዘላቂ እድገትን ማምጣት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክረ ሀሳቦች ይቀርባሉ። ውይይቱ እ.አ.አ በ2026 በአዲስ አበባ የሚካሄዱትን የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባና የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚሆኑ አጀንዳዎችን እንደሚያዘጋጅ ተመላክቷል። የአፍሪካ ህብረት ግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር አጀንዳ 2063 ለማሳካት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ዘርፎች መሆናቸውን አመልክቷል። ህብረቱ የግብርና እና የገጠር ልማት የበለጠ ለማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክቷል። የህብረቱ አባል ሀገራት የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራምን በተጠናከረ ሁኔታ እንዲተገብሩ ጥሪ አቅርቧል። ስድስተኛው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ጥቅምት 11 እና 12 እንዲሁም ጥቅምት 14 በሚኒስትሮች ደረጃ እንደሚከናውን ኢዜአ ከህብረቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
የብዙዎች ቤት…
Oct 27, 2025 88
እስካሁን በተደረገ የጥናት ውጤት መሠረት ከ81 በላይ የአጥቢ እንስሣት፣ ከ450 በላይ የአዕዋፍ እና ከ400 በላይ የእፅዋት ዝርያዎች መኖሪያ ነው። ከእነዚህ መካከል አምስቱ የአዕዋፍ ዝርያዎች በዚህ ሥፍራ ብቻ ይገኛሉ፤ ከአምስቱ መካከል በተለይም የአንዷ ዝርያ ዓለም አቀፍ የዘርፉ ተመራማሪዎችንና ጎብኚዎች ቀልብ መሳቡ ይጠቀሳል። ከአካባቢው ተፈጥሯዊ አቀማመጥና የአየር ሁኔታ ጋር መጣጣም የቻሉ የቆላ እፅዋት (ዛፎች) በምቾት በስፋት እንደሚገኙበትም ይገለጻል። የተመሠረተው በ1958 ዓ.ም ሲሆን፤ ስፉቱም 591 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው፤ በቁጥርም ሆነ በሥብጥር የብዙዎች መኖሪያ የሆነው ይህ ሥፍራ አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ይሰኛል። መንግሥት በሰጠው ትኩረት ከነበረው በተሻለ ሁኔታ እንስሣቱም ሆኑ እፅዋቱ እየኖሩ ነው፤ ከሕገ ወጥ ድርጊትም እንዲጠበቁ ማድረግ መቻሉን የፓርኩ ኃላፊ አደም መሐመድ ለኢዜአ አረጋግጠዋል። በፓርኩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁንም ለ247 ወገኖች ቋሚ እና ለ2 ሺህ 535 ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል። ባሳለፍነው ዓመትም በ1 ሺህ 751 የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች እንደተጎበኘ ኃላፊው ገልጸዋል።
የክህሎቶች ልማት፤ የአፍሪካ ቀጣይ የእድገት ምዕራፍ እና ግንባር
Oct 15, 2025 640
አፍሪካ የተስፋ እና የበረከት አህጉር ብቻ አይደለችም የዓለም ቀጣይ የእድገት ዳርቻ እና ማዕከል ጭምር እንጂ። ህዝቧ እ.አ.አ በ2024 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተሻግሯል፤ እ.አ.አ በ2050 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከአንድ ትውልድ በኋላ ባለንባት ምድር ላይ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ ከአፍሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል። በጣም አስገራሚው ነገር ከ60 በመቶ በላይ አፍሪካውያን እድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ሲሆን ይህም አፍሪካን ወጣቷ አህጉር አድርጓታል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ወጣት ትልቅ የስነ ህዝብ ትሩፋት ነው። ይህን አቅም ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ከተቻለ አፍሪካን የዓለም ክህሎት መፍለቂያ፣ የፈጠራ እና ኢኖቬሽን ማዕከል ማድረግ ይቻላል።   ይሁንና የስነ ህዝብ ትሩፋት ብቻውን ልማት እንዲረጋገጥ አያስችልም። እውነተኛው ፈተና ያለው ይህን የተትረፈረፈ የሰው ሀብት በክህሎት የዳበረ፣ ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ራሱን ብቁ ያደረገ እና መፍጠር ወደ ሚችል የስራ ኃይል መቀየር ላይ ነው። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የሰው ኃይል “የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመፍጠር” የሚያስችል ዋንኛ ምሰሶ እንደሆነ ያስቀምጣል። ይህ አህጉራዊ ማዕቀፍ በእውቀት እና ሁሉን አቀፍ እድገት አማካኝነት የበለጸገች፣ የተሳሰረች እና ራሷን የቻለች አህጉርን የመፍጠር ራዕይን አንግቧል። አፍሪካ የሰው ሀብት ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ሀብቶች ባለጸጋም ናት። አፍሪካ የዓለማችን 30 በመቶ የማዕድን ሀብት የሚገኝባት አህጉር ናት። ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ፕላቲኒየም እና ሌሎች ውድ ማዕድናትን በስፋት ይገኙበታል። ማዕድናቱ አሁን ዓለም ላለችበት አረንጓዴ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ቁልፍ የሚባሉ ናቸው። የዓለማችን 60 በመቶ ያልታረሰ መሬት ያለው በዚችሁ አህጉር ነው። ይህ እርሻ የማያውቀው መሬት የዓለምን የምግብ ስርዓት በከፍተኛ ሁኔታ የመቀየር አቅም አለው። ከ10 ቴራ ዋት በላይ የፀሐይ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላት አፍሪካ ከአህጉር አልፋ የኢንዱስትሪ እና ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በኃይል የማመንበሽበሽ አቅም አለው።   የኢኮኖሚ ማዕበሉም ወደ አፍሪካ ያደላ ይመስላል። እ.አ.አ 2021 ገቢራዊ መሆን የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና 55 ሀገራትን የሚያስተሳስር እና 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተጠቃሚን በአንድ ማዕቀፍ ስር የሚያሳባስብ ነው። በአህጉር ደረጃ ዓመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ) 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል። አህጉራዊ የንግድ ማዕቀፉ በሙሉ አቅሙ ሲተገበር የአፍሪካ ሀገራትን የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ መጠን 50 በመቶ እንደሚጨምረው የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። ይህም ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትን የሚያፋጥንና አህጉሪቷ ጥሬ እቃዎችን ወደ ውጭ ልካ መልሳ ያለቀላቸውን ምርቶች በከፍተኛ ወጪ ከመግዛት ተላቃ ጥሬ ምርቶቿን በከፍተኛ ጥራት ወደ ማምረት ያሸጋግራታል። ይህ ትልቅ የኢኮኖሚ ትስስር እድል አፍሪካውያን በጋራ እንዲለሙ፣ የሙያ ክህሎት እንዲያሳድጉ እና የእውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ እንዲሁም ጠንካራ እና የማይበገር ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶች እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል። እነዚህ ሁላ ተስፋ ሰጪ አቅሞች የሚቃረን አንድ የማይካድ ሐቅ አፍሪካ ውስጥ አለ ይህ እውነት የአፍሪካን የእድገት አቅም በሚፈለገው መልኩ የሚመግብ የክህሎቶች እና የስራ ክፍተት ነው። በየዓመቱ በአፍሪካ ከ10 እስከ 12 ሚሊዮን የሚሆኑ ወጣቶች ወደ ስራ ይገባሉ። ይሁንና በአህጉሪቷ በዓመቱ የሚፈጠረው መደበኛ ስራ 3 ሚሊዮን ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።   እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ የቅርብ ጊዜ ሪፖርት ከሆነ ከአፍሪካ ወጣቶች መካከል አንድ ሶስተኛ ገደማው ስራ አጥ (Unemployment) ወይም ከአቅም በታች ሰራተኝነት (Underemployment) ውስጥ ነው። ይህ ስራ አለማግኘት ያለው በአፍሪካ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢነርጂ፣ ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታላይዜሽን እና ሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎች የሚገኙ ኩባንያዎች ክህሎት ያለው ሰው አጠረን እያሉበት ባሉበት ወቅት መሆኑ ትልቅ ጥያቄን ያስነሳል። በትምህርት ስርዓቱ እና በገበያው ፍላጎት መካከል እንዴት እንደዚህ አይነት አለመጣጣም ሊመጣ ቻለ? የሚል። በትምህርት እና በኢንዱስትሪው መካከል ባለው ያለመተሳሰር ችግር ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ 130 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ምርታማነት (productivity) ታጣላች። እዚህ ጋር መነሳት ያለበት ጉዳይ ፈተናው የአቅም ሳይሆን ትምህርት እና ስራን፣ ፖሊሲ እና ተግባርን እና ስልጠናን ከቴክኖሎጂ ጋር የሚያስተሳሰር መስመር አለመዘርጋቱ ነው። በአፍሪካ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት እየሰሩ ያሉት ከኢንዱስትሪው ርቀው ነው ማለት ይቻላል ይህም ተመራቂዎች የስራ ገበያው የሚፈልገውን ክህሎት እና አቅም እንዳይታጠቁ አድርጓል። ሌላኛው ፈተና በአፍሪካ የተንሰራፋው ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ ነው። አንዳንድ ጥናቶች የአፍሪካን ኢ-መደበኛ የኢኮኖሚ ድርሻ እስከ 85 በመቶ ያደርሱታል። ይህም ዜጎች ክህሎታቸውን እንዳያሳድጉ እና የብቃት ማረጋገጫን እንዳያገኙ እክል ፈጥሯል። የአፍሪካን ክህሎት ምህዳር በመቀየር የኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ የስራ እድል ፈጠራን ማሳደግ እና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ ላይ የጋራ ትብብርን ማጠናከር አበይት ትኩረቱ ያደረገ ሁለተኛው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።   “አፍሪካውያንን የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት የሚያፋጥኑበትን ክህሎቶች ማስታጠቅ” የሳምንቱ መሪ ሀሳብ ነው። ሁነቱን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው። በሁነቱ መክፈቻ ላይ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ እና የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የአባል ሀገራት ሚኒስትሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የልማት ተቋማት አመራሮች፣ መምህራን፣ ኢኖቬተሮች፣ የወጣት ተወካዮች እና የልማት አጋሮች ተሳትፈውበታል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ክህሎቶች ለሀገራዊ ግቦችና ለአህጉራዊ የ2063 የልማት አጀንዳዎች መሳካት ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ናቸው።   ኢትዮጵያ ለክህሎት ልማት በሰጠችው ትኩረት ተጨባጭ ለውጥ እያመጣች ነው ብለዋል። ክህሎት መር የፖሊሲ እርምጃችን ወጣቶች ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ የስራ ፈጣሪነት ባህልን በንቃት እያስተዋወቀ መሆኑን ተናግረዋል። ተመራቂዎች የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ እና እድገት እንዲያመጡ የሚያስፈልጋቸውን ስልጠና፣ ምክር እና የገንዘብ ድጋፍ እያመቻቸ መሆኑን አመላክተዋል። በስልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለውን ትብብር የማጠናከር ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው የህዝባችንን አቅም ወደ ውጤታማ፣ አሳታፊ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ወደሆነ የሥራ ኃይል መለወጥ አለብን ብለዋል።   ክህሎት የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል። የክህሎት ልማት ለአሳታፊ ዕድገትና ለተገቢ የሥራ ዕድሎች ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የትግበራ ዕቅድ አካል መሆኑን ጠቁመዋል። አባል ሀገራት ሀገራዊ ለውጦችን ከአህጉራዊ ፍላጎቶች ጋር ለማጣጣም በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የተሻለ፣ ፈጣን እና ይበልጥ አሳታፊ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለውን የለውጥ አቅም መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል። የፖሊሲ ወጥነትን እና ቀጠናዊ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል። የአፍሪካ ክህሎት ክፍተትን መሙላት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ለክህሎት ልማት መጠቀም እና በአጀንዳ 2063 አማካኝነት ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገትን ማረጋገጥ ላይ ውይይት ይደረጋል። በሳምንቱ የሚኒስትሮች እና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረኮች፣ የክህሎት አውደ ርዕዮች እና የገበያ ትስስር ሁነቶች እንዲሁም የወጣቶች እና የስራ ፈጣሪዎች ፎረም እንደሚካሄድ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ፎረሙ የአፍሪካ ኢኖቬተሮች የስራ ውጤቶች ይቀርቡበታል። የክህሎቶች ሳምንት ተሳታፊዎቹ በኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት እና በኢኖሼሽን ማዕከላት ውስጥ ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው የሚገኙ የሰው ኃይል ልማት ስራዎች ይጎበኛሉ። ሳምንቱ እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የአፍሪካ ክህሎት ልማት አስመልክቶ የጋራ አቋም መገለጫ እና የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።   የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት ለአህጉሪቷ የኢንዱስትሪ እና ክህሎት አጀንዳ ተጨባጭ አሻራ የሚያሳርፍ መሆኑን ህብረቱ ገልጿል። የመጀመሪያው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት እ.አ.አ ኦክቶበር 2024 በጋና አክራ መካሄዱ የሚታወስ ነው። የአፍሪካ ክህሎቶች ፈተናዎች ክፍተቶች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ እንዲሁም ምህዳሩን ለመቀየር አህጉሪቷ በዘርፉ አብዮት ያስፈልጋታል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህን የስነ ህዝብ ትሩፋት ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን ክህሎት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል መቀየር ይገባል። ይህን ለማድረግ የተቀናጀ እና አህጉር አቀፍ ጥረት ያስፈልጋል። የሁለተኛው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት ስኬት የሚለካው በንግግሮች እና በጋራ መግለጫዎች ሳይሆን ራዕዮቹን በአፍሪካ ትምህርት ተቋማት፣ ስልጠና ማዕከላት እና ኢንዱስትሪዎች በተጨባጭ በመቀየር እና ውጤት በማምጣት ነው። በዚህ ረገድም መንግስታት፣ የትምህርት ተቋማት፣ ኢንዱስትሪዎች እና ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የአፍሪካን የክህሎት ልማት መጻኢ ጊዜ በውድድር፣ በፈጠራ እና አሳታፊነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊገነቡ ይገባል። አፍሪካ ወጣቶቿ በክህሎት እና በእውቀት ከታጠቁ አፍሪካ የተለመቻቸውን ግዙፍ እቅዶች እና ትላልቅ ውጥኖች ባጠረ ጊዜ እንዲሳኩ ያስችላል።
 ከአረብ ሀገር የአመታት እንግልት በኋላ በሀገሩ ህልሙን እውን ያደረገው ወጣት...
Oct 9, 2025 623
ሐረር ፤መስከረም 29/2018 (ኢዜአ)፦በሐረር ከተማ ተወልዶ ያደገው ነስረዲን አህመድ፤ በውጭ ሀገር ሰርቶ መለወጥን በማሰብ ከአመታት በፊት ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ እንቅስቃሴ ጀመረ። የመጓዝ እቅዱም ተሳካለትና በዱባይ ለስምንት ዓመታት በስራ ላይ ማሳለፉን ያስታውሳል፤ በበረሃው ምድር ሌት ተቀን በስራ እየደከመ ህይወቱን ሊለውጥለት የሚችል ገንዘብ ለመያዝ ቢጥርም ባሰበው ልክ ሊሳካለት አልቻለም።   በመሆኑም ከስምንት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ በመመለስ ሰርቶ የመለወጥ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ ሳይውል ሳያድር ወደ ስራ ገባ። ከበረሃው ንዳድ ወጥቶ በሀገሩ ሰርቶና አልምቶ መለወጥን የሰነቀው ነስረዲን በሀረር የንብ ማነብ ስራን ከጀመረ ሶስት ዓመታት እንደሆነው ያስታውሳል። በምንሰራበት የስራ መስክ ሁሉ በትጋት ሌት ከቀን መስራት ከቻልን የማናሳካው ነገር አይኖርም የሚለው ወጣቱ አሁን በሀገሩና በወንዙ በስኬት መንገድ ላይ መሆኑን ይናገራል።   የነስረዲን የንብ ማነብ ስራ የተጀመረው በጥቂት ቀፎዎች የነበረ ቢሆንም በስድስት ወራት ውስጥ ግን 50 ቀፎዎች ማድረስ መቻሉን ያስታውሳል። በሀገሬ ህልሜ እውን እየሆነ ነው የሚለው ወጣቱ የንብ ማነብ ስራውን አጠናክሮ በመቀጠል አሁን ላይ የንብ ቀፎዎቹን 300 ሲያደርስ ለ30 የአካባቢው ወጣቶችም የስራ እድል ፈጥሯል። በአረብ ሀገር የቆየባቸውን ዓመታት በቁጭት የሚያስታውሰው ነስረዲን መልፋትና መድከም ከተቻለ በሀገር ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል እኔ ጥሩ ማሳያ ነኝ ይላል። ከአረብ ሀገር የአመታት እንግልት በኋላ ወደ ሀገሬ ተመልሼ የስኬት መንገድን ጀምሬያለሁ በቀጣይም ጠንክሬ እሰራለሁ ብሏል።   በቀጣይ ከንብ ማነብም ባለፈ የማር ማቀነባበርያ አነስተኛ ኢንዱስትሪ የማቋቋም ትልም እንዳለው ተናግሮ ለዚህም እንደሚተጋ አረጋግጧል። በዚሁ የልማት ፕሮጀክት ላይ የስራ እድል የተፈጠረለት ወጣት ሸዊብ መሀመድ፤ ከዚህ ቀደም ያለምንም ስራ ተቀምጦ መሽቶ ይነጋ እንደነበር አስታውሶ አሁን እያገኘ ባለው ገቢ ከራሱ አልፎ ቤተሰብ እየረዳ መሆኑን ተናግሯል።   ወጣት በድሪ ሙሳም፤ በነስረዲን ጥረት እርሱን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች ስራ የተፈጠረላቸው በመሆኑ ጥሩ ገቢ እያገኙ መሆኑን አንስቶ በቀጣይ እርሱም የራሱን ተመሳሳይ ስራ ለመጀመር ማቀዱን ገልጿል።   በሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ የንብ እርባታ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ኢብሳ ዩስፍ፤ የነስረዲን ጥረትና የአጭር ጊዜ ስኬት ለሌሎች ወጣቶችም ጥሩ ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል።   በመሆኑም በክልሉ የማር ምርታማነትን ለማጎልበት በከተማና በገጠር ወረዳዎች ላይ የንብ መንደር በመመስረት ዘርፉን የማጎልበት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የአፍሪካ መምህራን፤ የአህጉሪቷ መጻኢ ጊዜ ቀራጺዎች
Oct 3, 2025 828
አፍሪካ በወጣቶች የታደለች ሀገር ናት። ከአህጉሪቷ ህዝብ መካከል ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው እድሜው ከ25 ዓመት በታች መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ መጻኢ ጊዜን የሚወስነውን ወጣት ማን ያስተምረዋል? የሚለው ጥያቄ ቁልፍ ነው። ይህ ጥያቄ ከመማሪያ ክፍሎች እና መጻሕፍት ባለፈ የአፍሪካ ልማት አበይት አጀንዳ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም። በዓለም ደረጃ ትልቅ የእድገት እና የልማት ሞተር የሆነውን ወጣት በብዛት የያዘችው አፍሪካ ትውልዱን የሚቀርጽ መምህራን ውጪ ህልሟን ማሳካት የሚታሰብ አይሆንም። የአፍሪካ ህብረት በአህጉር አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት እ.አ.አ በ2030 በትንሹ 15 ሚሊዮን አዲስ መምህራን እንደሚያስፈልጉ አስታውቋል። ይህን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እና ጠንካራ ሪፎርሞችን ማድረግ ይጠይቃል። አፍሪካ የትምህርት መሰረተ ልማትን ለማሻሻል፣ የመምህራንን ቁጥር ለመጨመር እና በትምህርት ዘርፍ የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት 90 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ሲል ህብረቱ ገልጿል። ጉዳዩ ከትምህርት ባለፈ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አንድምታ ያለው ነው። መምህራን የእያንዳንዱ ክህሎት፣ ስራ እና ኢኖቬሽን የሀሳብ መሐንዲስ ናቸው። የአፍሪካ መጻኢ ጊዜ የመወሰን አቅም አላቸው። በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የመምህራን ትምህርት ስርዓታቸው ላይ ማሻሻያ እያደረጉ ይገኛል። የአፍሪካ መዲና የሆነችው ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ በርካታ ሪፎርሞችን እያደረገች ሲሆን ከዚህ ውስጥ አንዱ የመምህራንን አቅም መገንባት እና የብቃት ደረጃን ማሳደግ ይገኝበታል። የትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሄራዊ የመምህራን ልማት ንቅናቄ በማድረግ መምህራን በተለያዩ የትምህርት እርከኖች አቅማቸውን እንዲጎለብት ተከታታይ ስልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ነው። በአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም አማካኝነንት ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ መምህራን የዲጂታል ክህሎታቸው በማዳበር እና ተከታታይ የብቃት ምዘና በማድረግ አቅማቸውን እየተገነባ ይገኛል። በነዚህ ስራዎች የትምህርት ውጤት ላይ አበረታች መሻሻሎች ታይተዋል። መንግስት የሰለጠነ መምህራንን ቁጥር ማሳደግን የሪፎርሙ አካል አድርጎ እየሰራ ነው። ጋና የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆችን ወደ ዩኒቨርስቲ በማሳደግ ሙያዊ ልህቀትን ለማረጋገጥ እየሰራች ትገኛለች። ኬንያ ብቃት ላይ የተመሰረተ የስርዓተ ትምህርት ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ የመምህራን መማር ማስተማር የበለጠ ተግባር ተኮር እና ተማሪዎችን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን የጀመረችው ተግባር ተጠቃሽ ነው። ሩዋንዳ የስርዓተ ትምህርት አሰራሮቿን ከመምህራን ስልጠና ጋር በማጎዳኘት የመምህራን እጥረትን ለመቀነስ እና ክህሎታቸውን ለማሳደግ እየሰራች ነው። ለትምህርት ዘርፍ የሚመደበው በጀት በቂ አለመሆን፣ የተማሪ እና ክፍል ጥምርታ አለመመጣጠን፣ የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትስስር በሚፈለገው ደረጃ አለማደግ፣ የዲጂታል ክህሎት ማነስ እና ከፍላጎት አንጻር በቂ የሰለጠነ መምህራን አለመኖር የአህጉሪቷ የትምህርት ዘርፍ ፈተናዎች ናቸው። የፓን አፍሪካ የመምህራን ትምህርት ኮንፍረንስ በያዝነው ሳምንት በአፍሪካ ህብረት መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሄዷል። "በአፍሪካ የመምህራን ትምህርት ስርዓትን መቀየር” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ኮንፍረንስ የትምህርት ሚኒስትሮች፣ የመምህራን ማህበራት ተወካዮች፣ ምሁራን፣ የግሉ ዘርፍና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችና የልማት አጋሮች ተወካዮች ተሳትፈዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ በኮንፍረንሱ ላይ ባደረጉት ንግግር ትምህርት ለሰው ሃብት ልማትና ለምጣኔ ሀብት ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል። በአፍሪካ የሚፈለገውን ልማትና ዕድገት ለማምጣት የትምህርት ተደራሽነት ላይ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሪፎርሞችን ተግባራዊ ማድረጓንና በዚህም ውጤት መገኘቱን አንስተዋል። የመምህራንን አቅም ለመገንባት የተለያዩ ስልጠናዎች በመስጠት በኩልም የተሻለ ስራ መሰራቱን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ የጠቀሱት። የትምህርት ጥራትና የመምህራን እጥረት ላይ እንደ አህጉር አሁንም ያልተፈታ ችግር መኖሩን ጠቁመው፤ ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አባል ሀገራቱ ትብብራቸውን የበለጠ ማጠናከር አለባቸው ብለዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የትምህርት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ጋስፓርድ ባንያንኪምቦና በበኩላቸው በአፍሪካ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና ሳይንስና ፈጠራን የበለጠ ለማዳበር የመምህራንን አቅም ማሳደግ ወሳኝ ነው ብለዋል። ለዚህም ለመምህራን አቅም ግንባታ የተለያዩ ኤኒሼቲቮች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ገልጸው፤ የአፍሪካ የ2063 የልማት ዕቅዶች ዕውቀት መር በሆነ መንገድ ቢተገበሩ ውጤታማ ይሆናሉ ብለዋል። የአፍሪካ መምህራንን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ከፈጣንና ተለዋዋጭ ቴክኖሎጂ ጋር መላመድ እንደሚገባም ነው ያነሱት። በአፍሪካ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን የበለጠ ለማሳደግ የመማር ማስተማር ሂደቱን ከወቅቱ ጋር ማዛመድ ይገባል ብለዋል። በኮንፍረንሱ ላይ መምህራንንና ትምህርትን የተመለከቱ የተለያዩ አህጉራዊ ስትራቴጂዎች ይፋ ተደርገዋል። የአፍሪካ የትምህርት ስትራቴጂ (ከእ.አ.አ 2026 እስከ 2035 የሚተገበር) የአፍሪካ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ፣ የአፍሪካ ሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ስትራቴጂ እንዲሁም የአፍሪካ የትምህርት የክህሎት ልማት የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ሆነዋል። በተጨማሪም የአፍሪካ መምህራትን ማህበረሰብ የአሰራር ማዕቀፍ ወደ ትግበራ ገብቷል። ይፋ የሆኑት ስትራቴጂዎች እና የአሰራር ማዕቀፎች የመምህራን ትምህርት፣ ሙያዊ ልህቀት፣ መሰረተ ትምህርት፣ ዲጂታል ክህሎቶች እና ኢኖቬሽን ተኮር የማስተማር ዘዴ ላይ መዋቅራዊ ለውጦችን የማምጣት ግብ እንዳላቸው የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል። በኮንፍረንሱ ላይ የ2025 የአፍሪካ መምህራን ሽልማት የተካሄደ ሲሆን የዘንድሮው የዓለም የመምህራን ቀን በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተከብሯል። አህጉራዊው ሁነት በአፍሪካ የመምህራን ድምጽ የበለጠ ጎልቶ እንዲሰማ የማድረግ ፣ የትምህርት ኢንቨስትመንት መጠን እንዲያድግ እና የባለድርሻ አካላት ትብብርን የማጠናከር አላማ እንዳለው ተገልጿል። የመምህራንን አቅም ማሳደግ የአፍሪካ የትምህርት ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ አበይት ትኩረቶች መካከል አንደኛው መሆኑን ህብረቱ በመረጃው አመልክቷል። ህብረቱ እ.አ.አ 2024 የትምህርት ዓመት ብሎ በመሰየም የሰጠው ስትራቴጂካዊ ትኩረት የዚሁ ማሳያ ነው። የፓን አፍሪካ ኮንፍረንሱ የመምህራን ትምህርት የአፍሪካ የልማት አጀንዳ አበይት ትኩረት መሆኑ በግልጽ ታይቶበታል። የመምህራንን እጥረትን መቀነስ ብዙ መምህራንን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን ስልጠና ጥራት ያለው፣ ነባራዊ እውነታን ያገነዘበ እና መጻኢውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ መሆን ይኖርበታል። የአፍሪካ መንግስታት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች የመምህራን ትምህርት ስርዓትን መቀየር ትኩረታቸውን ባደረጉበት በአሁኑ ወቅት የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ የቀና የሚያደርገውን አፍሪካዊ ማን ያስተምራል? የሚለው ጥያቄ ተስፋ የሚሰጥ ምላሽ ያገኛል። የሰለጠነ፣ በክህሎት የዳበረ እና የኢኖሼሽን እውቀቱ ያደገ መምህር ለአፍሪካ ቀጣይ ጉዞ መቀናት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።  
ትንታኔዎች
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 1390
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ  7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 1942
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር  በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 2776
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 2907
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር።   ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል።   ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው።   የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው።   ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 695
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 523
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 6366
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 4843
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 55334
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 51170
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 31894
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 29400
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 25917
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 24472
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 24226
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 24064
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 55334
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 51170
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 31894
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 29400
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
''ቦር ተራራ'' የየሞች የፈውስ ምድር 
Oct 27, 2025 36
(በእንዳልካቸው ደሳለኝ ከወልቂጤ ኢዜአ ቅርንጫፍ) የም ዞን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ይገኛል። በዞኑ የቦር ተራራ ዋነኛው የመድኃኒት እጽዋት መገኛ እና ምንጭ በመሆኑ የሞች በየዓመቱ ጥቅምት ወርን ጠብቀው በ17ኛው ቀን ከዚህ ተራራ በህብር ሆነው የመድኃኒት እጽዋት ለቀማ ስነ-ስርዓት ያካሂዳሉ፤ ይሰባስባሉም ። የቀደምት የየም አባቶችና እናቶችን በማሳተፍ የሚከወነው የመድኃኒት እጽዋት ለቀማ ከባህር ጠለል በላይ 2 ሺህ 939 ሜትር ከፍታ ላይ በሚገኘው ቦር ተራራ ላይ ነው። በዚህ ተራራ ላይ በየዓመቱ ጥቅምት 17 ቀን የሞች ለዓመት የሚያገለግላቸውን የመድኃኒት እጽዋት ይለቅማሉ። ተግባሩንም አዋቂዎች በጋራ ሰብሰብ ብለው ለመድኃኒት የሚውለውን ቅጠል በጥሰው፣ ስር ምሰው፣ አስሰውና መርጠው ይሰበስባሉ። ይህም የመድኃኒት እጽዋት ለቀማ ስርዓት "ሳሞ ኤታ" ተብሎ ይጠራል ። አያምጣውና ህመም ሲከሰት ታማሚውን ሰው ወይም እንስሳን ከበሽታው ለመፈወስ የተዘጋጀው ባህላዊ መድሃኒት በባህላዊ ሃኪም ትዕዛዝ መሰረት በህመሙ ልክ ይታዘዝለታል። መድሃኒቱን ለመጠቀምም የጠቢባን አባቶችን ፈለግ ተከትሎ መፈፀም የግድ ይላል። የሞች አጅግ አስገራሚ እና አስደናቂ የሆኑ የበርካታ አገር በቀል ዕውቀቶች ባለቤት ናቸው ካስባሏቸው እሴቶች መካከል ይህ ለየት ያለው ክዋኔያቸው አንዱ ነው፡፡ አባቶች ታዳጊና ወጣቶችን አስከትለው ወደ ቦር ተራራ በመውጣት የሚፈፅሙት ባህላዊ ክዋኔ በመሆኑም ከትውልድ ወደ ትውልድ ቅብብሎሹን ጠብቆ እስከ አሁን እንዲዘልቅ እድርገውታል።   በየሞች ዘንድ የባህላዊ መድኃኒት አዋቂዎች ከሚባሉት መካከል አንዱ አቶ ጌታቸው ሃይለማርያም፤ የመድኃኒት ዕፅዋት ለቀማ ልምድን የቀሰሙት ከአባታቸው መሆኑን በመግለፅ አያታቸው ከቅድመ አያቶቻቸው በመውረስ እዚህ እንዳደረሱት ይናገራሉ። የቦር ተራራ ለመድሃኒት ዕፅዋት ለቀማው የተመረጠበትን ምክንያት ሲያስረዱም ቦታው ተራራ በመሆኑ ማንም ያልደረሰባቸው የተለያዩ እፅዋትን ለማግኘት አመቺ ከመሆኑ ጋር ያያይዙታል። በሌላም በኩል ጠዋት ፀሐይ ስትወጣ መጀመሪያ የምታገኘው ተራራውን በመሆኑና ክረምቱ አልፎ ጥቅምት ሲገባ የተለያዩ ቅጠላ ቅጠሎችን በብዛት እና በዓይነት ለማግኘት ተመራጭ ወቅት መሆኑም ቦታው የተመረጠበት ሌላኛው ምክንያት ነው ብለዋል። በጥቅምት 17 ለመድኃኒትነት የሚያገለግለው ዕፅዋት ቅጠልም በየፈርጁ ተለቅሞ እና ተቀምሞ ይቀመጣል ሲሉም አስረድተዋል። የተዘጋጀው ባህላዊ መድኃኒትም ለሰው ልጆችና ለቤት እንስሳት ያገለግላል ሲሉም አስረድተዋል፡፡ ይኸው በዚህ ቀን የተለቀመው የመድኃኒት ዕፅዋት ከዚህኛው ጥቅምት 17 እስከሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት 17 ድረስ እንደሚያገለግልም አቶ ጌታቸው አስረድተዋል፡፡ የባህል መድኃኒት ሰብሳቢዎች እና ተጠቃሚዎች ጊዜውን ጠብቀው ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ቦር ተራራ እንደሚመጡ የሚገልጹት የባህል መድኃኒት አዋቂው ዛሬ ዛሬ እሳቸውን ጨምሮ መድኃኒት ቤቶችን በመክፈት ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ የባህል መድኃኒቶችን በመሸጥ ኑሯቸውን እየመሩ የሚገኙ አያሌ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉም ይናገራሉ። ሌላኛው የባህል መድኃኒት አዋቂው አቶ ወልደመስቀል ጆርጋ በበኩላቸው በየሞች ዘንድ የተዘጋጀው የመድኃኒት ዕፅዋት ጥቅም ላይ የሚውለው ህመም ሲያጋጥም ብቻ ሳይሆን በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል መሆኑን ጠቁመው መድኃኒቶቹም ብቻቸውን እንዲሁም ከምግብ ጋር በመመገብ ለጥቅም እንደሚውሉም አንስተዋል። የየም ምድር የበርካታ የመድኃኒት ዕፅዋቶች መገኛ አካባቢ " የፈውስ ምድር " ነው የሚሉት ደግሞ በየም ባህላዊ መድኃኒት ዙሪያ ጥናት ያደረጉት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የፎክሎር መምህር እና ተመራማሪ ለማ ንጋቱ (ዶ/ር) ናቸው። ከየሞች አያሌ የባህል ዕሴቶች መካከል የባህል መድኃኒት ለቀማና ቅመማ አንዱና ዋነኛው የሀገር በቀል እውቀት ማሳያ መሆኑን ገልፀው የመድኃኒት ዕፅዋት ለቀማ ስነ-ስርዓቱ ከጥንት ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ዛሬ ላይ የደረሰ እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡   ማህበረሰቡ የራሱንም ሆነ የእንስሳትን ጤና የመጠበቅ የቆየ ባህል ያለው መሆኑን በጥናት መረጋገጡን ጠቅሰው የባህላዊ መድኃኒት ለቀማው ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚሳተፉበት ዓመታዊ ክዋኔ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ ሌላው ገራሚው ነገር ይላሉ አጥኚው ታላላቆች ታናናሾቻቸውን አስከትለው የለቀማ ሂደቱን የሚያስረዱበት መንገድ ደግሞ ስርዓቱ ለመጪው ትውልድ እንዲተላለፍ የሚያስችል ትውልድ ተሻጋሪ የሀገር በቀል እውቀት ሽግግር ስርዓት ማሳያ እንደሆነም ነው የገለጹት። በዚህም ሂደት የሚነገሩ ስነ-ቃሎች መሞጋገስ፣ ጭፈራና ደስታ ይስተናገድባቸዋል። ይህም ማህበራዊ ትስስርን ይበልጥ የሚጠናክሩበትን ሁነት የሚፈጥር ስርዓት ነው። የየም ዞን ባህል እና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ሞጋ በበኩላቸው የቦር ተራራ የመጀመሪያውን የማለዳ የፀሐይ ጎህ የሚፈነጥቅበት የንጋት ብርሃን ቀድሞ የሚያገኝ በመሆኑ፥ በዚህ አካባቢ የሚገኙ እጽዋት በሽታን የመከላከልና ፈዋሽነታቸው ከፍተኛ ነው ተብሎ ስለሚታመን ለዚህ ክዋኔ ቦታው መመረጡን ነው የሚገልፁት። ለዚህም ነው የሞች ይህንን ስፍራ ከሌሎች ቦታዎች አስበልጠው የሚወዱት፤ በየዓመቱም ጥቅምት 17 ቀን ወደ እዚህ ስፍራ በማቅናት ለዓመት ፍጆታ የሚያገለግላቸውን መድኃኒትም ይሰበስቡበታል ብለዋል። ጥቅምት 17 በየም ዘንድ ለየት የሚያደርገው ሌላው የመድሃኒት ዕፅዋት ለመልቀም እና ለመጠቀም ብቻ ሳይሆን የለቀማውን ትዕይንት ለመመልከት የሚመጡ ቱሪስቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸው ሌላው ትልቁ ትሩፋት ነው ይላሉ። የመድኃኒት ዕፅዋት ለቀማው ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት በመሆኑ፥ ለአብሮነት እና ሃገር በቀል እውቀት ለመቅሰም ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ነው አቶ መስፍን የገለፁት።    
የአፍሪካ የግብርና፣ ውሃ እና ከባቢ አየር አጀንዳ፤ እድሎች እና ፈተናዎች
Oct 20, 2025 456
አፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማሳካትና እንድትበለጽግ የጀመረችው ጉዞ ወሳኝ መዕራፍ ላይ ይገኛል። የአህጉሪቱን የመለወጥ ትልም ባሏት እምቅ ተፈጥሯዊ ጸጋዎች ላይ የተመረኮዘ ነው። ተዝቆ የማያልቀው የአፍሪካ ብዝሃ ሀብት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግና አይበገሬ አቅም መገባንት የሚያስችሏትም ጭምር ናቸው። ግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ ሀብቶቿ እና ብዝሃ ከባቢ የአየር ንብረቷ ከሀብቶቿ መካከል ይጠቀሳሉ። ግብርና አሁንም የአፍሪካ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው። ዘርፉ ለአህጉሪቱ 35 በመቶ የሚጠጋ አጠቃላይ ጥቅል ሀገራዊ ምርት(ጂዲፒ) አስተዋጽኦ ያደርጋል። 60 በመቶ ህዝብም በግብርና ስራ እንደሚተዳደር የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የልማት ፕሮግራም (ካዳፕ) ሰነድ ያሳያል። ከዚህም ውስጥ አብዛኞቹ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው።   ሴቶች በግብርናው ዘርፍ ካለው የሰው ኃይል የ50 በመቶ ድርሻው ይወስዳሉ። የአፍሪካ ህዝብ 60 በመቶ ድርሻ የያዘው ወጣት በግብርና ንግድ፣ እሴት መጨመርና የኢኖቬሽን ስራዎች ያለው ተሳትፎ እያደገ መጥቷል። የዓለም 60 በመቶ ያልለማ መሬት ያለው በአፍሪካ ነው። ሰፊ የውሃ ሀብቶችና እያደገ ያመጣው ብሉ ኢኮኖሚ(የባህር እና ሌሎች የውሃ ሀብቶች) ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ እድገትን የሚያረጋግጡ ናቸው። የመሰረተ ልማቶች ተደራሽነት ማደግ፣ ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶችና ኢኖቬሽንን የተመረኮዙ የፋይናንስ አማራጮችን መስፋት ግብርናን የምግብ ምንጭ ብቻ ሳይሆን ለኢንዱስትሪ ልማት፣ የስራ ዕድል ፈጠራ እና ንግድ መሳለጥ ትልቅ አቅም መሆን ይችላል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና በግብርና ምርቶችና አገልግሎቶች ያለውን አህጉራዊ የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ በማሳደግ ረገድ ትልቅ ዕድል ይዞ የመጣ ነው። የንግድ ቀጣናውን በሚገባ መጠቀም ከተቻለ እ.አ.አ በ2030 የግብርና ንግድ ልውውጡን በ30 በመቶ ማሳደግ እንደሚቻል ጥናቶች ያመለክታሉ። ግብርናው የተጠቀሱት ጥንካሬዎች ያሉት ቢሆንም ረጅም ጊዜ የዘለቁ መዋቅራዊ ፈተናዎች አብረውት ዘልቀዋል። የግብርና ምርቶች ላይ የሚፈለገውን ያህል እሴት አለመጨመር፣ የቴክኖሎጂ አጠቀቃምና የምርታማነት ውስንነት፣ የመሰረተ ልማቶች እና ሎጅስቲክስ በበቂ ሁኔታ አለመሟላት፣ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ክፍተቶች ከአየር ንብረት ለውጥና ሌሎች ተፈጥሯዊ አደጋዎች እንዲሁም እያደገ ከመጣው ህዝብ ጋር ተዳምሮ ግብርናውን እየፈተነው ይገኛል።   ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ማጠንጠኛ የሆነው ጉዳይ የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት(ካዳፕ) ነው። እ.አ.አ በ2003 የአፍሪካ ህብረት በሞዛምቢክ ባደረገው ስብሰባ የግብርና የምግብ ዋስትና ድንጋጌን አጽድቋል። ይህ ማዕቀፍ የማፑቶ ድንጋጌ ስያሜን በማግኘት የካዳፕ ትግበራ በይፋ እንዲጀመር አድርጓል። የማፑቶ ድንጋጌ እ.አ.አ በ2014 በማላቦ ድንጋጌ (ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2025 የተተገበረ) በአዲስ መልክ የታደሰ ሲሆን የተለያዩ ቃል ኪዳኖችን በውስጡ ይዟል። ይህም በካዳፕ አማካኝነት የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ከአጠቃላይ ዓመታዊ ጥቅል ምርታቸው(ጂዲፒ) ቢያንስ ስድስት በመቶውን ለግብርናው ዘርፍ እንደሚመድቡና በየሀገራቱ በዘርፉ በየዓመቱ በአማካይ ስድስት በመቶ እድገትን የማሳካት ግብ አለው። ረሃብን ማጥፋት፣ ድህነትን በግማሽ መቀነስ፣ የማይበገር አቅም መገንባትና የጋራ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ሌሎች ግቦች ናቸው። ካዳፕ የአፍሪካ ሀገራት በስርዓተ ምግብ ያላቸውን ኢንቨስተመንት በማሳደግ፣ በአፍሪካ የእርስ በእርስ የግብርና ንግድን በማሳደግና የፖሊሲ መሰናሰልን በመፍጠር ቁልፍ ሚና ተወጥቷል። ይሁንና የተመዘገቡት ውጤቶች ያልተመጣጠነ ልዩነት የሚታይባቸው ናቸው። የ2023 የካዳፕ የግምገማ ሪፖርት እንደሚያሳየው የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የማላቦ ግቦችን ማሳደግ የሚያስችል መንገድ ላይ እንዳልሆኑ ያስቀምጣል። ይሁንና 26 ሀገራት በተቀመጡ ግቦች መመዘኛ መሻሻል እንዳሳዩ ይገልጻል። ኢትዮጵያ፣ ብሩንዲ፣ ካሜሮን፣ ግብጽ፣ ማሊ፣ ጋና እና ጋምቢያ የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ። አብዛኞቹ ሀገራት በግብርና ኢንቨስትመንት፣ ምርታማነት እና የፖሊሲ ትግበራ ላይ ፈተናዎች እንዳሉበት ሪፖርቱ አመልክቷል። ሀገራት የሰነዱን ትግበራ ማፋጠንና ተቋማዊ ቅንጅትን ማጠናከር እንደሚገባቸው አሳስቧል።   የማላቦ ድንጋጌ ወደ መገባደዱ ላይ የሚገኝ ሲሆን የካዳፕ ቀጣዩ ምዕራፍ የካምፓላ ድንጋጌ ነው። ይህ የትግበራ ምዕራፍ ከእ.አ.አ 2026 እስከ 2035 የሚቆይ ነው። የካምፓላ ድንጋጌ ከማፑቶ እና ማላቦ ድንጋጌዎች ትምህርቶችን በመውሰድ የግብናውን እድገት ማላቅ ግቡ አድርጎ ይዟል። የካምፓላ አጀንዳ ኢኖቬሽን፣ ዲጂታላይዜሽን፣ አረንጓዴ እድገት እና አይበገሬነት ያላቸውን ሚና በማንሳት መስኮቹ ስርዓተ ምግብን ዘላቂና አካታች የማድረግ ግብን ማሳካት እንደሚያስችሉ አመልክቷል። በዚህ ማዕቀፍ እ.አ.አ 2050 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ህዝብ ይኖራታል ተብሎ የሚጠበቀውን አፍሪካን በራስ አቅም የመመገብ ውጥን የያዘ ነው። ይሁንና የግብርና ምርታማነት ከዓለም አቀፍ አማካይ የምርታማነት ምጣኔ አንጻር ሲታይ አሁንም ወደ ኋላ ቀረት ያለ ነው። ይህም አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች የተገደበ የፋይናንስ አቅርቦት ማግኘታቸው እንዲሁም የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው አለመደረጉ የችግሩ አብይ መንስኤ ሆኖ ይጠቀሳል። የአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎችና የከባቢ አየር ብክለት ፈተናዎቹ እንዲበረቱ አድርጓል። ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ የበይነ መንግስታት ፓናል(IPCC) አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እርምጃዎችን በፍጥነት ካልወሰደች እ.አ.አ በ2050 የግብርና ምርታማነቷ ከ20 እስከ 30 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ገምቷል። ከ250 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አፍሪካውያን ደህንነቱ ያልተረጋገጠ እና ንጽህናው ያልተጠበቀ የውሃ አቅርቦት ፈተና ውስጥ ይገኛሉ። በህዝብ ቁጥር መጨመር፣ በከተሜነትና ኢንዱስትሪ መስፋፋት ምክንያት ንጹህ የውሃ አቅርቦትን የማግኘት ጉዳይ የበለጠ ሊስፋ እንደሚችል ተመላክቷል። የአፍሪካ ህብረት የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩና ፈተናዎች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ለአባል ሀገራት የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል። የህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር የስራ ክፍሉ(DARBE) አማካኝነት የአፍሪካን ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞችና ኢኒሼቲቮች የተናበቡና የጋራ ግብ ያላቸው እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል። የአቅም ግንባታ፣ የቴክኒክ እና የፖሊሲ ድጋፍም የሚያደርግ ሲሆን ብሄራዊ እቅዶች ከአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሰነዶችና የአጋርነት ማዕቀፎች ጋር የተጣጠሙ መሆናቸውን ያረጋገጣል። የስራ ክፍሉ ከቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች ጋር አጋርነቶችን የማጠናከር ስራ ያከናውናል። ግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ አስተዳደር፣ የአየር ንብረት ለውጥ አይበገሬነት እንዲሁም የተፈጥሮ እና የብሉ ኢኮኖሚ ሀብቶች በዘላቂነት መጠቀም ላይ የተቀናጁ አሰራሮችን መፍጠር ላይም ይሰራል። የዘርፉ አጠቃላይ ስራዎች አካል የሆነው ስድስተኛው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል። በስብሰባው ላይ ሚኒስትሮች፣ ባለሙያዎችና የልማት አጋሮች ይሳተፋሉ። የአፍሪካ የግብርና ኢኒሼቲቮች አፈጻጸም መገምገምና ዘርፉ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከር የስብሰባው አላማ ነው። እ.አ.አ በ2023 በአዲስ አበባ የተካሄደውን አምስተኛው የልዩ ኮሚቴ ስብሰባ ውጤቶች ግምገማ ይደረጋል። የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) የማላቦ ድንጋጌ(ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2025) ስኬቶች እና የካዳፕ የካምፓላ ድንጋጌ (ከእ.አ.አ 2026 እስከ 2035) አፈጻጸም ላይ ውይይት ይካሄዳል። የስርዓተ ምግብን ማጠናከር፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ምርታማነት ስርዓት መዘርጋት፣ የበካይ ጋዞችን ልህቀት መቀነስና ዘላቂ የውሃና የተፈጥሮ ሀብቶች አስተዳደርን ማጠናከር ሌሎች የምክክር አጀንዳዎች ናቸው። በአፍሪካ በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ኑሮ በማሻሻል ዘላቂ እድገትን ማምጣት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክረ ሀሳቦች ይቀርባሉ። ውይይቱ እ.አ.አ በ2026 በአዲስ አበባ የሚካሄዱትን የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባና የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚሆኑ አጀንዳዎችን እንደሚያዘጋጅ ተመላክቷል። የአፍሪካ ህብረት ግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር አጀንዳ 2063 ለማሳካት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ዘርፎች መሆናቸውን አመልክቷል። ህብረቱ የግብርና እና የገጠር ልማት የበለጠ ማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም አመልክቷል። የህብረቱ አባል ሀገራት የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራምን በተጠናከረ ሁኔታ እንዲተገብሩም ጥሪ አቅርቧል። ስድስተኛው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ጥቅምት 11 እና 12 እንዲሁም ጥቅምት 14 በሚኒስትሮች ደረጃ እንደሚያከናውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። አፍሪካ ወደ ዘላቂ ግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ውሃ አስተዳደር እና አካባቢ ጥበቃ እያደረገች ያለው ጉዞ አንገብጋቢ አጀንዳና ሽግግሩን ለማፋጠን ወሳኝ ሚና አለው። አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የፋይናንስ ማነቆ፣ መሰረተ ልማቶች እና የፖሊሲ የመፈጸም አቅም ውስንነትን ጨምሮ የተለያዩ ፈተናዎች ቢኖሩባትም እድሎቿ ፈርጀ ብዙ ናቸው። በርካታ ያልለማ መሬት፣ ሰፊ የውሃ ሀብት፣ ወጣቶች እና የብሉ ኢኮኖሚ ሀብቶች በአፍሪካ ዘላቂ የግብርና እድገት ለማረጋገጥና ሁሉን አቀፍ ስርዓተ ምግብ ለመገንባት የሚያስችል ነው። ለአርሶ አደሮች በቂ የፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽ ማድረግን ጨምሮ አቅማቸውን መገንባት ቁልፍ ጉዳይ ነው። ሀገራት ብሄራዊ ፖሊሲዎቻቸውን ከአህጉራዊ ማዕቀፎች ጋር ማጣጣም ይኖርባቸዋል። ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት የአሰራር ማዕቀፍ መዘርጋት ይገባል። የተፈጥሮ ሀብትን በሚገባ መጠቀም፣ በኢኖቬሽን ላይ መዋዕለ ንዋይን ፈሰስ ማድረግና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር የምግብ ዋስትናዋን ያረጋገጠች፣ አረንጓዴ እና የበለጸገች አህጉር መገንባት ይቻላል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም