ኢትዮጵያ እና ቻይና በዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታቸውን በይበልጥ ለማጠናከር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ቻይና በዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታቸውን በይበልጥ ለማጠናከር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 30/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እና ቻይና በተለያዩ በርካታ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታቸውን በይበልጥ አጠናክረው ማስቀጠል በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን ተቀብዬ በጽናት በሚጓዘው የኢትዮጵያ እና ቻይና የመንግሥት እና ሕዝብ ግንኙነት ላይ ተነጋግረናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀበሉ
ኢትዮጵያ እና ቻይና ለአስርት ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸውም ገልጸዋል።
ይኽ ግንኙነት በቅርቡ ወደ በሁኔታዎች የማይለዋወጥ የስትራቴጂክ ትብብር ማደጉንም አስታውቀዋል።
በተለያዩ የልማት ትብብር ርዕሰ ጉዳዮችን ለማከናወን ያለንን ጽኑ አቋም በማስቀጠል ላይ ውይይት አድርገናልም ነው ያሉት።
በኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ መሠረተ ልማት፣ የኃይል አቅርቦት እና ትራንስፖርት ብሎም አዲስ በመፈጠር ላይ ባሉ እንደኢ-ኮሜርስ፣ ዲጂታል ኢኮኖሚ፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና አረንጓዴ ኃይል ልማት ላይ ትብብራችንን ለማጠናከር ተወያይተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።