ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርን ሹመት አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርን ሹመት አጸደቀ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 28/2018 (ኢዜአ)፦የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርን ሹመት አጽድቋል።
ምክር ቤቱ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።
በዚህም ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ወይዘሮ ሃይማኖት ዘለቀ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ የቀረበውን ረቂቅ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ወይዘሮ ኃይማኖት ዘለቀ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሪፖርተርነት እስከ አርታኢነት እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በሙያቸው አገልግለዋል፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት በምክትል ቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሀላፊ በመሆን ማገልገላቸው ተገልጿል፡፡
እንዲሁም በቀድሞ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በመስራት ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡