ምክር ቤቱ የ34 የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የ34 የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት አጸደቀ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 28/2018 (ኢዜአ)፦የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የ 34 ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።
ምክር ቤቱ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄዷል።
በስብሰባው የ34 የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በአንድ ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።