በመኸር ወቅት ከለማው የቅባት እህል 97 በመቶው ተሰበሰበ - ኢዜአ አማርኛ
በመኸር ወቅት ከለማው የቅባት እህል 97 በመቶው ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፤ ጥር 1/2018 (ኢዜአ)፡- በ2 ሚሊየን 607 ሺህ 240 ሔክታር ላይ የለማ የቅባት እህል መሰብሰቡን ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በ2017/18 የመኸር ወቅት 2 ሚሊየን 691 ሺህ 243 ሔክታር በቅባት እህል መልማቱን በሚኒስቴሩ የቅባት ሰብሎች ልማትና ድኅረ ምርት ዴስክ ኃላፊ ፍሰሐ ቶሎሳ ለኢዜአ ተናግረዋል።
ከዚህም 40 ሚሊየን 104 ሺህ 278 ኩንታል የቅባት እህል ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
እስካሁን ባለው ሂደትም በአጠቃላይ ከለማው ውስጥ በ2 ሚሊየን 607 ሺህ 240 ሔክታር ላይ የነበረው መሰብሰቡን አረጋግጠዋል።
ከተሰበሰበው ውስጥም 83 ነጥብ 135 በመቶው መወቃቱን እና 33 ሚሊየን 341 ሺህ 833 ኩንታል ምርት መገኘቱን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ከተሰበሰበው ውስጥ ቀሪ ምርት ተሰብስቦ ሪፖርት ያልተደረገ እና እየተወቃ ያለ መኖሩንም ጠቅሰዋል።
እስካሁን ከተሰበሰበው ምርት ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት ሰሊጥ፣ለውዝ እና አኩሪአተር መሆናቸውን አስገንዝበዋል።