ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀበሉ

አዲስ አበባ ፤ ታኅሣስ 30/2018(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ዛሬ መቀበላቸውንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

ጉብኝቱ የወል ፍላጎት በሆኑ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን ያካትታል ተብሎ እንደሚጠበቅም አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም