ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ጎረቤት ሀገራት በአግባቡ ሊረዱት የሚገባ መሠረታዊ ጉዳይ ነው - የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬው
Aug 29, 2026 6
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፤ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ጎረቤት ሀገራት በአግባቡ ሊረዱት የሚገባ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬው ገለጹ። ኢትዮጵያ ካላት የሕዝብ ቁጥርና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት አንጻር የባሕር በር የማግኘት ጉዳይን የህልውና አጀንዳ አድርጋ እየሰራች ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀጣናው ግዙፍ ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና መቀጠል እንደማትችል በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያ ይህንን ጥያቄዋን በንግድና ሰጥቶ መቀበል መርህ ለማሳካት በቀጣይነት እንደምትሰራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው አይዘነጋም። በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ያደረጉት የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬው ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የባሕር ወደቦች ለአንድ ሀገር ንግድና ኢንቨስትመንት እጅግ ወሳኝ መሆናቸውን አመልክተዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ጎረቤት ሀገራት በአግባቡ ሊረዱት የሚገባ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። የባሕር በር የማግኘት ሂደቱ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጋራ ጥቅምና ዕድገትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊከናወን እንደሚገባም አመልክተዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት መካከል ሊኖር ከሚገባው የትብብር ማዕቀፍ ጋር የሚተሳሰር መሆኑንም ነው ያነሱት። በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረኮች ድምፃቸውና ፍላጎታቸው ተሰሚነት እንዲያገኝ በጋራና በትብብር መስራት እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት። በተጨማሪም የደቡብ ንፍቀ ክበብ ሀገራት በዓለም አቀፉ ሥርዓት ውስጥ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ አፍሪካ ለዚህ ትብብር ዋነኛዋ ድምጽ ሆና እየወጣች ስለመሆኑም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ የህብረቱ መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን አፍሪካን ከኢስያ አህጉር ጋር በማስተሳሰር ረገድ መግቢያ በር ሆና እያገለገለች እንደምትገኝም የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬው ተናግረዋል። ትብብርን እና በሕግ ላይ የተመሠረተውን ዓለም አቀፍ ሥርዓት ለማስጠበቅ ተመሳሳይ አመለካከት ባላቸው ሀገራት መካከል የበለጠ ወዳጅነት እና አንድነት እንዲኖርም ጥሪ አቅርበዋል።
በአማራ ክልል በፍትህ ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው
Aug 29, 2026 15
ባህር ዳር፤ ነሃሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በፍትህ ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች በአማራ ክልል የሚገኙ የፍትህ ተቋማትን የሪፎርም አተገባበር ጎብኝተዋል። ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት በክልሉ በፍትህ ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ዘመኑን የዋጁ አስደናቂ ስራዎች ናቸው ብለዋል። በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተተገበረው በዲጂታል የተደገፈ የኢ-ፋይል አሰራር ፍትሃዊ፣ ግልጽና የተገልጋዩን እንግልት መቀነስ ያስቻለ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል። ተገልጋዮች ጉዳያቸውን ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ በመከታተል አስተማማኝ ፍትህ እንዲያገኙ መደረጉ የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል የተሄደበትን ርቀት የሚያሳይ ነው ብለዋል። በክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያም ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠርና የዲጂታላይዜሽን አሰራርን እውን በማድረግ የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል። በቴክኖሎጂ የዳበረ የፍትህ ስርዓት ለማስፈን በተሰራው ስራ የአመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑን መገንዘባቸውን ጠቁመው፤ በጉብኝታቸው ትልቅ ተሞክሮ ማግኘታቸውን አረጋግጠዋል። በቀጣይ በመተጋገዝና በአብሮነት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከክልሉ የፍትህ ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉዓለም ቢያዝን በበኩላቸው የዳኝነት ስራ ከፖሊስ የወንጀል መከላከልና የተጠናከረ ምርመራ ተግባር ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዲጂታላይዜሽን ትግበራ ቀልጣፋና ፍትሃዊ የፍትህ አሰጣጥ እንዲኖር ያስቻለ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም ከከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ለይግባኝ ይመጡ የነበሩ ባለጉዳዮች ባሉበት ቦታ ሆነው ጉዳያቸውን በመከታተል ገንዘብንና ጉልበታቸውን እንዲቆጥቡ አስችሏል ብለዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች ያደረጉት ጉብኝት ልምድ ከመለዋወጥ ባሻገር ተግባራትን በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። የሪፎርም ትግበራውን እስከ ታች ድረስ ለማውረድ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል። በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አመራሮች ተገኝተዋል።
በሶማሌ ክልል የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ ነው - ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ
Aug 29, 2026 61
ጅግጅጋ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የተቋማትና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ፤ የክልሉን ኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪና ቢሮ አዲስና ዘመናዊ የህንፃ ግንባታ አስጀምረዋል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግርም በክልሉ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። ከልማት ስራዎች በተጓዳኝ የመንግስት አገልግሎቶችን ምቹ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል። በዛሬው እለትም የክልሉን ኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪና ቢሮ አዲስና ዘመናዊ የህንፃ ግንባታ መጀመሩን ገልጸው፤ የተቋማትና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች ይቀጥላሉ ብለዋል። ከዚህ ጎን ለጎን የትምህርት፣ የውሃ፣ የመንገድ፣ የጤና የዲጂታል ልማትና ሌሎችም ስራዎች በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል። በክልሉ ከተሞችም ይሁን በገጠር ሰው ተኮር የሆኑ ልማቶችን የመገንባትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ዋነኛ ትኩረታችን ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ቀጣዩን የምህርት ዘመን ስኬታማ ለማድረግ ትኩረት ተደርጓል
Aug 29, 2026 52
ወልቂጤ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ቀጣዩን የምህርት ዘመን ስኬታማ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን በህብረተረብ ተሳትፎ የታተሙ ከ160 ሺህ በላይ መጽህፍትን በዞኑ ለሚገኙ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች አስረክበዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት በቅድመ-መደበኛ ትምህርት ላይ መስራት ተማሪዎች ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል። በመሆኑም ለትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፤ ግብዓቶችን በማሟላት የ2019 የትምህርት ዘመንን ስኬታማ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ይጠናከራሉ ብለዋል። እንደሀገር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተያዘውን አቅጣጫ ውጤታማ እንዲሆን ዘርፉን የመደገፍ ሥራ በትኩረት እንደሚከናወንም አመልክትዋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በበኩላቸው፤ በክልሉ ለ2019 የትምህርት ዘመን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ለዚህም በክልሉ ላሉ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ መጽሃፍት መሰራጨታቸውንም በማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የመገንባትና ደረጃቸውን የማሻሻል ሥራ መከናወኑንም አመልክተዋል። የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም በዞኑ ለቅድመ አንደኛ፣ ለአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 160ሺህ 169 መጽሃፍት መሰራጨታቸውን ገልጸዋል። መጽሃፍቱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የታተሙ ሲሆን ከ37 ሚሊዮን ብር በላይም ውጪ የተደረገባቸው መሆኑንም አስታውቀዋል። በተጨማሪም በህዝብ ተሳትፎ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ለመማር ማስተማር ሥራው ዝግጁ መደረጋቸውን ተናግረዋል።
የሀዋሳ ከተማን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚመጥኑ ውጤታማ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ -ከንቲባ ጥራቱ በየነ
Aug 29, 2026 56
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ የሀዋሳ ከተማን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚመጥኑ ውጤታማ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለፁ። በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ጽህፈት ቤት "ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" በሚል መሪ ሀሳብ የጽዱ ኢትዮጵያ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ ጥራቱ በየነ፤ የከተማዋን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚመጥኑና ከተማዋን ውብ፣ ጽዱና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ የሚያግዙ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል። በከተማዋ ከኮሪደር ልማት ሥራ ጋር በተያያዘ ሰፋፊ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች እንዲሁም በየአካባቢው የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች መገንባታቸውንም አመልክተዋል፡፡ ሃዋሳ ውበትና ጽዳት መለያዋ መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባ ጥራቱ፤ ከከተማዋ ዕድገትና ኢንቨስትመንት መስፋፋት ጋር ተያይዞ በቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት ላይ ውስንነቶች እንዳሉ ተናግረዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፣ በ2019 ዓ.ም የከተማዋን አድገት የሚመጥን አዲስ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥፍራ ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ከከተማዋን ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር ተጣጥመው እየተከናወኑ ያሉ ውጤታማ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል። የሃዋሳ ከተማ የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሹምባሻ በበኩላቸው በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ከአካባቢ ጥበቃ ሥራ ጋር የተሰናሰለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በከተማዋ በየመንደሩ ቆሻሻ የሚሰበስቡና ለይተው የሚያስወግዱ ማህበራትን በማደራጀት ጽዱ አካባቢን የመፍጠር ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
የሚታይ

ኢትዮጵያ እንደ ሕዳሴ ግድብ ሁሉ የባሕር በር ጥያቄዋንም ማሳካት የምትችል ታላቅ ሀገር ናት - ኡስታዝ ጀማል በሽር
Aug 28, 2026 361
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ እንደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሁሉ የባሕር በር ጥያቄዋን ማሳካት የምትችል ታላቅ ሀገር መሆኗን የዓባይ ንጉሶች ሚዲያ ባለቤት ኡስታዝ ጀማል በሽር ተናገሩ። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የውሃ ሀብቶቿን በራሷ አቅም አልምታ መጠቀም እንደምትችል ያሳየ መሆኑንም ገልጸዋል። ኡስታዝ ጀማል በሽር፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ኃይል በማስተሳሰር ትብብርን ከማጠናከር አኳያ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር ያላት ትብብር በጋራ ተጠቃሚነትና ልማት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ታላቁ የህዳሴ ግድብ በተግባር ማሳየቱንም ነው የጠቆሙት። ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን እንዳትጠቀም የሚከለክላት ማንም አካል እንደሌለ ጠቅሰው የሀገሪቷ የመልማት መብት ዓለም አቀፍ ህጎችና መርሆዎችን ያከበረ እንደሆነም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን ተጠቅማ በቀጣይ ለማከናወን ያሰበቻቸው ስራዎች ሀገሪቷን ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል። እየተጠናቀቁ ያሉ የመስኖ ግድቦች፣ አብዛኛው ስራ የተጠናቀቀው የኮይሻ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክትና ሌሎች ስራዎች የኢትዮጵያን የልማት ውጥን እውን የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች ያሰበቻቸውን እያሳካች መሆኑን ጠቅሰው፤ በከተማ ልማት፤ ቱሪዝም እንዲሁም በምክክር የመግባባት ዴሞክራሲን በመገንባት ረገድ ውጤታማ ስራ እያከናወነች ስለመሆኑ አብራርተዋል። አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የሆነውን የባሕር በር ጥያቄ በይፋ አንስታለች ነው ያሉት። የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ እና በፍትሃዊነት የመልማት ጥያቄ መሆኑን በማንሳት፤ ይህንን ማሳካት ደግሞ የትውልዱ የማይቀር እውነት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘቷ አይቀሬ መሆኑን ጠላት ሳይቀር እየመሰከረው ያለው ሃቅ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ እንደ ሕዳሴ ግድብ ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶች ሁሉ የባሕር በር ጥያቄዋንም ማሳካት የምትችል ታላቅ ሀገር ስለመሆኑም ኡስታዝ ጀማል ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ከታይላንድ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሳደግ ትሰራለች- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)
Aug 28, 2026 311
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ ከታይላንድ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሳደግ እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከየታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬው ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ሀገራት ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ትብብር ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።   የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት በኢትዮጵያና ታይላንድ መካከል ያለውን የዲፕሎማሲና ፖለቲካ ግንኙነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማሳደግ የሚያስችል ገንቢ ውይይት አድርገናል ብለዋል። ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከር እንደሚያስችልም ገልጸዋል። የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው በበኩላቸው፤ ታይላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና ትብብር ማጠናከር ትፈልጋለች ብለዋል። የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብርን በማጠናከር ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያላት እምቅ አቅም ላይ እሴት መጨመር የሚያስችል ልምዳችንን እናካፍላለን ብለዋል። በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ለማጠናከር በጋራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል። ታይላንድ በቅርቡ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ በመክፈት ትብብሯን ወደ ላቀ ደረጃ ታሸጋግራለች ብለዋል። የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ታሪካዊውን “የታይላንድ-አፍሪካ ኢኒሼቲቭ” በይፋ ለማስጀመር አዲስ አበባ የገቡት ዛሬ ማለዳ ነበር።
የአፍሪካን የኢኮኖሚ ውህደት ለማፋጠን የድንበር ላይ አሰራሮችን የሚያሳልጥ ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል - የአፍሪካ ሕብረት
Aug 28, 2026 280
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ውህደት ለማፋጠን የሀገራትን የድንበር ላይ አሰራሮችን የሚያሳልጥ ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ሕብረት ገለጸ። ‎የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽንና የዓለም ባንክ ያተዘጋጁ''አፍሪካን ማቀናጀት፤ ከተበታተኑ ትስስሮች ወደ ኢኮኖሚያዊ ማዕከላት'' የተሰኘ አዲስ አህጉራዊ የጥናት ሪፖርት ይፋ ሆኗል።   የጥናት ሪፖርቱም የአፍሪካን ከቀረጥ ነፃ የንግድና የምርት ትስስር በማጠናከር የአህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣናን በዘመናዊ መሠረተ ልማት በማስደገፍ የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ ውህደት ማጠናከር እንደሚገባ አመላክቷል። በሕብረቱ ኮሚሽን የኢኮኖሚ ልማት፣ ንግድ፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና ማዕድን ኮሚሽነር ፍራንሲስካ ታቾፕ ቤሎቤ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ አፍሪካ በተሰናሰለ አሠራርና መሠረተ ልማት የሚመራ የኢኮኖሚ ውህደትን ማሳለጥ ያስፈልጋታል። ይህም የአህጉሪቱን የተበታተነ የገበያና የግብይት ሥርዓት ውጤታማነት በማሻሻል አፍሪካን የጠንካራ ኢኮኖሚ ማዕከል ለማድረግ ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል። የአፍሪካ ኢኮኖሚ ውህደት በሚፈረሙ ስምምነቶች ብቻ አይሳካም ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ውህደት ለማፋጠንም የሀገራትን የድንበር አሠራሮችን የሚያሳልጥ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል። የአፍሪካን አህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት የትብብር ማዕቀፍ በውጤታማነት በመተግበር የአህጉሪቷን ዜጎች የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ንግድና ኢንቨስትመንትን ማፋጠን እንደሚገባ ተናግረዋል። ለዚህም የአህጉሪቷን አባል ሀገራት የድንበር ላይ መተላለፊያ፣ ጉምሩክ፣ ታሪፍና የዲጂታል ክፍያ እንቅፋቶችን ማስወገድ የሚያስችል ቀልጣፋ አሠራር መዘርጋት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የአህጉሪቷን የኢኮኖሚ ውህደትን ለማሳለጥ የሚደረጉ ጥረቶችም ጥሬ ዕቃን ከመላክ የተላቀቀ የኢንዱስትሪ፣ የኃይልና የትራንስፖርት እሴት ሰንሰለት የሚያጎለብት ነው ብለዋል። ይህም የበለፀገችና የተሳሰረች አፍሪካን የመገንባት የአጀንዳ 2063 ራዕይን በማሳካት የአፍሪካዊያንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያሻሽል የኢኮኖሚ ምኅዳር መፍጠር እንደሚያስችል ገልጸዋል።   የዓለም ባንክ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣናዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ንዲያሜ ዲዮፕ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የአፍሪካ የተቀናጀ መሠረተ ልማትና የሎጂስቲክስ ሥርዓት ለኢኮኖሚ ውህደት አስፈላጊ ነው ብለዋል። የአህጉሪቷን የኢኮኖሚ ውህደት ለሚያሳልጥም የተቀናጀ የመሠረተ ልማት አቅርቦትን በመገንባት የአርሶ አደሩን፣ የኢንዱስትሪና ገበያን በቀጥታ የሚያገናኝ ምኅዳር መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። የመሠረተ ልማቶች ትስስር አህጉራዊ የግብርና ገበያዎችንና የፋብሪካ ምርቶችን በማጠናከር ለአፍሪካውያን ሰፊና ዘላቂ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ጠቅሰዋል። የዓለም ባንክ የንግድ እንቅፋቶችን በመቀነስ፣ የድንበር ተሻጋሪ አሠራሮችን በማቃለል የአፍሪካን እውነተኛ የኢኮኖሚ ውህደትና የሥራ ዕድል በሚፈጥሩ መሠረተ ልማቶች ላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
የታይላንድ–አፍሪካ ኢኒሼቲቭ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብርን ለማጠናከር አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው
Aug 28, 2026 282
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ)፦ የታይላንድ–አፍሪካ ኢኒሼቲቭ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብርን ለማጠናከር አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ሲሉ የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉአንግኬትኬኦ ገለጹ። የታይላንድ-አፍሪካ የትብብር መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።   የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉአንግኬትኬኦ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ታይላንድ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደ ላቀ የስትራቴጂያዊ አጋርነት ለማሳደግ የሚያስችል አዲስ ማዕቀፍ ይፋ አድርገዋል። ሚኒስትሩ በዚሁ መድረክ ላይ የጉብኝታቸው ዋነኛ መነሻ ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የተመሰረተው ይህ የትብብር ማዕቀፍ በተለይም ከአፍሪካ ኅብረት እና ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ECOWAS) ጋር ያለውን ተቋማዊ ትብብር በይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው። በተጨማሪም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና እና በደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀገራት ማኅበር (ASEAN) መካከል ጠንካራ የኢኮኖሚ ድልድይ ለመፍጠር ታስቧል። ዓላማውን ከዳር ለማድረስም የታይላንድ የንግድ ልዑክ በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ የመንግሥት እና የግል ዘርፍ ተወካዮች ጋር በመገናኘት የንግድ ማኅበረሰቡን የሚያስተሳስር ውይይት እንደሚያደርግ ተገልጿል።   በሌላ በኩል ታይላንድ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ለማጎልበት ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የሚተገበር እና ሦስት ሚሊዮን ዶላር በጀት የተመደበለት አዲስ የድርጊት መርሐ ግብር ይፋ አድርጋለች። መርሐ ግብሩ በዋናነት በግብርና፣ በምግብ ዋስትና እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ በተለያዩ የአፍሪካ አካባቢዎች የግብርና ማሠልጠኛ ማዕከላትን ለማቋቋም ይውላል። በፈረንጆቹ 2028 የደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀገራት ማኅበር ሊቀመንበርነትን የምትረከበው ታይላንድ፣ በማኅበሩ እና በአፍሪካ ኅብረት መካከል በምግብ እና ኃይል ዋስትና እንዲሁም በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዙሪያ ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደምትሠራ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ጎረቤት ሀገራት በአግባቡ ሊረዱት የሚገባ መሠረታዊ ጉዳይ ነው - የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬው
Aug 29, 2026 6
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፤ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ጎረቤት ሀገራት በአግባቡ ሊረዱት የሚገባ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬው ገለጹ። ኢትዮጵያ ካላት የሕዝብ ቁጥርና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት አንጻር የባሕር በር የማግኘት ጉዳይን የህልውና አጀንዳ አድርጋ እየሰራች ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀጣናው ግዙፍ ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና መቀጠል እንደማትችል በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያ ይህንን ጥያቄዋን በንግድና ሰጥቶ መቀበል መርህ ለማሳካት በቀጣይነት እንደምትሰራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው አይዘነጋም። በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ያደረጉት የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬው ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የባሕር ወደቦች ለአንድ ሀገር ንግድና ኢንቨስትመንት እጅግ ወሳኝ መሆናቸውን አመልክተዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ጎረቤት ሀገራት በአግባቡ ሊረዱት የሚገባ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። የባሕር በር የማግኘት ሂደቱ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጋራ ጥቅምና ዕድገትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊከናወን እንደሚገባም አመልክተዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት መካከል ሊኖር ከሚገባው የትብብር ማዕቀፍ ጋር የሚተሳሰር መሆኑንም ነው ያነሱት። በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረኮች ድምፃቸውና ፍላጎታቸው ተሰሚነት እንዲያገኝ በጋራና በትብብር መስራት እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት። በተጨማሪም የደቡብ ንፍቀ ክበብ ሀገራት በዓለም አቀፉ ሥርዓት ውስጥ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ አፍሪካ ለዚህ ትብብር ዋነኛዋ ድምጽ ሆና እየወጣች ስለመሆኑም አብራርተዋል። ኢትዮጵያ የህብረቱ መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን አፍሪካን ከኢስያ አህጉር ጋር በማስተሳሰር ረገድ መግቢያ በር ሆና እያገለገለች እንደምትገኝም የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬው ተናግረዋል። ትብብርን እና በሕግ ላይ የተመሠረተውን ዓለም አቀፍ ሥርዓት ለማስጠበቅ ተመሳሳይ አመለካከት ባላቸው ሀገራት መካከል የበለጠ ወዳጅነት እና አንድነት እንዲኖርም ጥሪ አቅርበዋል።
ለውጥ እና ነውጥ፤ የአትክልተኛው ማስታወሻ የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል
Aug 29, 2026 193
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ) ፦ ፖለቲከኛ ግርማ ሰይፉ በባለፉት ስምንት ዓመታት በኢትዮጵያ የታዩትን የለውጥ ሒደቶችና የፖለቲካ ውጣ ውረዶችን የሚተነትን "ለውጥ እና ነውጥ፤ የአትክልተኛው ማስታወሻ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፋቸውን ነገ ያስመርቃሉ። ነገ ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ 9:00 ላይ የሚመረቀውን መጽሐፍ ምክንያት በማድረግ አቶ ግርማ ሰይፉ ለኢዜአ እንዳሉት፤ መጽሐፉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ከጸብና ከጠመንጃ መራቅ እንዳለበት ለማስገንዘብ እና የተዛቡ ትርክቶችን ለማስተካከል አዎንታዊ ሚና ይኖረዋል። መጽሐፉ የተሳካና የተሟላ የሀገረ መንግሥት ግንባታን ዕውን ለማድረግ ጠቃሚ ምክረ-ሀሳቦችን ያቀረበ መሆኑን ጠቁመዋል። ልዩነቶችና አለመግባባቶች በምክክር ብቻ መፈታት እንዳለባቸው በመግለጽ፣ የብሔራዊ ምክክርን አስፈላጊነት በአጽንኦት አንስተዋል፡፡ መጽሐፉ ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የዳር ተመልካች ሳይሆኑ መሪ ተዋናይ እንዲሆኑ እንደሚያስገነዝብ ገልጸው፤ ከመገፋፋት ይልቅ ሁሉም ወገን በትብብር ለመሥራት ፈቃደኛ መሆን አለበት ብለዋል። ኢትዮጵያውያን በጋራና በትብብር ሲቆሙ ብቻ ፈተናዎችን መሸጋገር፣ እንዲሁም ድህነትንና ኋላቀርነትን ማሸነፍ እንደሚችሉ መጽሐፉ ማብራራቱን ተናግረዋል። በነገው ዕለት በሚካሄደው የመጽሐፉ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል። መጽሐፉ በስድስት ምዕራፎች የተከፋፈለና 270 ገጾች ያሉት መሆኑን ገልጸዋል። በነገው ዕለት በይፋ ከተመረቀ በኋላ በሁሉም መጽሃፍት መድብሮች ለገበያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል።
ለተሻለ ነገ መሰረት የጣለው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ
Aug 29, 2026 155
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ሀገራዊ መግባባትን በማጠናከር የኢትዮጵያን አንድነትና እድገት ለማረጋገጥ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ለአርባ ስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት ተጠናቋል። በጉባኤው ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የዘለቁ የአለመግባባት ስብራቶችን በሐሳብ የበላይነትና በጥበብ መፍትሔ መስጠት እንደሚችሉ በተግባር አሳይተዋል፡፡ ኢዜአ ያነጋገራቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ ምክክሩ ኢትዮጵያ ወደ አንድነትና የተሻለ ልማትና እድገት የምትሸጋገርበት ትልቅ ድል ነው። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ሀምሳ አለቃ አብዱ ሁሴን እንደገለጹት፤ ምክክሩ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎችን ያካተተ፤ ለሀገር የሚበጁ ጉዳዮች ላይ የተመካከሩበት ስኬታማ ሁነት ነው። ምክክሩ ለዘመናት የዘለቁ አለመግባባቶችን ለመፍታት ችግሮችን በምክክር ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ለማምጣት ያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ የአንድነት የአብሮነት እሴቶች እንዲጎለብቱ ያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ሃሊማ መሃመድ በበኩላቸው፤የሀሳብ ልዩነትን በኃይል ለመፍታት መመኮር ጊዜው ያለፈበት አካሄድ መሆኑን ጠቁመዋል። ምክክሩ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ጠቅሰው፤በምክክር የምትገነባ ሀገር አሸናፊ ናት አሁን ኢትዮጵያ የአሸናፊነት ጉዞዋን ጀምራለች ብለዋል። ምክክሩ ለትውልድ የሚበጅና ለሀገር አንድነት መሰረት የተጣለበት ከመሆኑም በላይ ለሌሎች ሀገራትም ምሳሌ የሚሆን ነው ያሉት ደግሞ አቶ አበበ ኮምቤ ናቸው። ወይዘሮ ዘሪቱ አስቤ በበኩላቸው፤ቀደም ሲል በሀገሪቱ ችግሮችን ለመፍታት በጠረጴዛ ዙሪያ የመመካከር ልምድ እንዳልነበረ አንስተዋል። ምክክሩ በችግሮች ላይ በመመካከርና በመፍታት ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።
ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባትና ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን የሚከናወኑ ተግባራት የሚበረታቱ ናቸው
Aug 29, 2026 155
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባትና ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን የሚከናወኑ ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ወጣት ፉአድ መሀመድ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ዜጎች እርስ በእርስ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት አውድ ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል። ይህንንም ኢትዮጵያ ባካሄደችው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ማሳካት መቻሏን ተናግሯል። የሀገሪቱን ሁለንተናዊ እድገት ለማፋጠን በፖለቲካው ዘርፍ ከሚሰሩ ተግባራት ባለፈ ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው በፍጥነት ተጠናቆ የተመረቁበት እና አዳዲስ ደግሞ የተጀመሩበት ሁኔታ መኖራቸው ለሀገር እድገት ሚናቸው የጎላ መሆኑን አንስቷል። ለአብነት በሀገር እና በህዝብ ጥረት ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የሕዳሴ ግድብ በማንሳት ፕሮጀክቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንዲሻሻል እና ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ ያደረገ መሆኑን የሚያኮራ ተግባር ነው ሲል ገልጿል። ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚደረጉ ጥረቶች የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንደሆነም ተናግሯል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወጣት ራህመት ዲኖ በበኩሏ፤ ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ማረጋገጧን ገልጻለች። እኛ ዜጎችም ከመንግሥት ጋር በጋራ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በላቀ ደረጃ እንዲቀጥሉ ተሳትፏችንን ልናጠናክር ይገባል ብላለች። የሀገርን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ፣ ልማትን ለማፋጠን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን የገለጸው ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት ዘሪሁን ፍቃዱ ነው። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ በሆነና ህዝቦችን በነቂስ ባሳተፈ መንገድ መከናወኑ የዴሞክራሲ አካሄዳችን እየዳበረ መሆኑን ማሳያ ነው ብሏል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ዮናስ ደስታ በበኩሉ፤ መንግሥት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በማጠናቀቅ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየወሰደ ያለው ቁርጠኛ እርምጃ የሚደነቅ ነው ብሏል። ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት እየተጣለ መሆኑ የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፋንታ ብርሀኑ የሚያደርግ ተጠቃሽ እርምጃ መሆኑንም ተናግሯል። በቀጣይም የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ ሕዝቡ በልማቱ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን በመንግሥት የሚደረጉ ጥረቶች ሊቀጥሉ እንደሚገባ አመልክቷል።
የምክክር መድረኩ የቆዩ ችግሮችን በውይይት በመፍታት ሀገርን የማሻገር ፅኑ ፍላጎት የታየበት ነው
Aug 28, 2026 254
ጂንካ፤ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ) ፡-ሀገራዊ የምክክር መድረኩ የቆዩ ችግሮችን በውይይት በመፍታት ሀገርን የማሻገር ፅኑ ፍላጎት የታየበት መሆኑን ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው የተሻለች ሀገርን የመገንባት አዲስ ተስፋን የፈነጠቀና ለችግሮች በውይይት መፍትሔን በመሻት ሀገርን የማሻገር አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ የተከፈተበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው። በመድረኩ ላይ የተደመጡት የጋራ እይታዎች፣ የሰጡት ገንቢ አስተያየቶችና የታየው የነቃ ተሳትፎ ህዝቡ ያለፉ አለመግባባቶችን በመሻገር ወደ ተሻለ የታሪክ ምዕራፍ ለመሸጋገር ያለውን ፅኑ ፍላጎትና የጋራ ቁርጠኝነት ግልጽ አድርጎ ያሳየ ነበር። ኢዜአ ያነጋገራቸው የጂንካ ከተማ ነዋሪዎችም፤ የምክክር መድረኩ የቆዩ ችግሮችን በውይይት በመፍታት ሀገርን የማሻገር ፅኑ ፍላጎት የታየበት ነው ብለዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ጋሻው ገላው፤ ምክክር ለሀገር ብቻ ሳይሆን በግል ህይወትም ችግሮችን ቀርፎ የተሻለ ህይወት ለመምራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ሀገራዊ የምክክር መድረኩ አለመግባባቶችን በውይይትና በምክክር የመፍታት መሠረት መጣሉን የጠቆሙት አቶ ጋሻው፤ ተነጋግሮ የመግባባት ባህል እንዲጎለብት ማስቻሉንም ገልጸዋል። መሰረቷ የፀናች ህብረ-ብሔራዊት ሀገርን ለመገንባት የእያንዳንዱ ዜጋ ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ ያነሱት ደግሞ አቶ ቅዱስ መንገሻ ናቸው። በሀገራዊ የምክክር መድረኩ የተነሱ ሀሳቦች ብዙሃኑን ያማከሉ፣ አካታችና ሀገር የሚያሻግሩ በመሆናቸው፤ ለተፈጻሚነታቸው ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል። ሀገርን ማሻገር ከተፈለገ ከግል ፍላጎት ይልቅ የሀገርን ፍላጎትና ብሔራዊ ጥቅም ማስቀደም እንደሚገባም አብራርተዋል። "ችግሮቻችንን በውይይት የመፍታት ዕድል በማጣታችን በጥቃቅን ጉዳዮች አለመግባባት ውስጥ የምንገባበት ጊዜ አብቅቶ አዲስ የዲሞክራሲ ምህዳር ተፈጥሯል" ያሉት ደግሞ ሌላው የጂንካ ከተማ ነዋሪ አቶ እሸቱ ፈይሳ ናቸው። የምክክር መድረኩ የሀሳብ የበላይነት የታየበትና ሀገርን ወደ ለውጥ ምዕራፍ ለማሻገር በህዝቡ ውስጥ ያለውን ጉጉትና ፅኑ ፍላጎት ያየንበት ነው ብለዋል። በምክክር መድረኩ የተነሱ ሀሳቦች ተፈጻሚ ሆነው የታለመው ሀገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉም አመልክተዋል።    
ኢትዮጵያ ከታይላንድ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሳደግ ትሰራለች- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)
Aug 28, 2026 311
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ ከታይላንድ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሳደግ እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከየታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፑዋንግኬትኬው ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ሀገራት ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ትብብር ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።   የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት በኢትዮጵያና ታይላንድ መካከል ያለውን የዲፕሎማሲና ፖለቲካ ግንኙነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማሳደግ የሚያስችል ገንቢ ውይይት አድርገናል ብለዋል። ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከር እንደሚያስችልም ገልጸዋል። የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው በበኩላቸው፤ ታይላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና ትብብር ማጠናከር ትፈልጋለች ብለዋል። የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብርን በማጠናከር ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያላት እምቅ አቅም ላይ እሴት መጨመር የሚያስችል ልምዳችንን እናካፍላለን ብለዋል። በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ለማጠናከር በጋራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል። ታይላንድ በቅርቡ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ በመክፈት ትብብሯን ወደ ላቀ ደረጃ ታሸጋግራለች ብለዋል። የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ታሪካዊውን “የታይላንድ-አፍሪካ ኢኒሼቲቭ” በይፋ ለማስጀመር አዲስ አበባ የገቡት ዛሬ ማለዳ ነበር።
የኢትዮጵያውያን የወል እውነት- ሀገራዊ ምክክር
Aug 28, 2026 268
በሙሴ መለስ ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የጋራ መኖሪያ እና የብዝሃነት ውበት ደምቆ የሚታይባት ሀገር ናት ። ዛሬ ላይ ለመድረስም በርካታ ውጣ ውረዶችን፣ እና የታሪክ ምዕራፎችን ተሻግራለች። በነዚህ ምዕራፎች ውስጥም በአብሮነትና በጋራ ሃገራዊ እሳቤ ከተገነቡት የጋራ ማንነቶች ባልተናነሰ መልኩ ያጋጠሙ የታሪክ ስብራቶች የልዩነት እና ያለመግባባት መንስኤ የሚሆኑበትን አጋጣሚም አስተናግዳለች። ልዩነቶችን በጉልበት ወይም በኃይል ሳይሆን፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር እና ከነጣይ ትርክት ይልቅ ወደ ሃገራዊ መግባባትና የጋራ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣትም ሃገራዊ ምክክሩ የራሱን ቁልፍ ሚና በመወጣት በሃገራችን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑ ይታወቃል። ከአራት ዓመታት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ የህብረተሰቡን አጀንዳዎች በባለቤትነት የማሰባሰብ ሂደቱን በስኬት አከናውኗል። የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ምሁራን፣ ዳያስፖራዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በአንድ መድረክ የተሳተፉበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ለ46 ቀናት ተካሄዶ በስኬት መጠናቀቁ ተበስሯል። ይህ ጉባኤ ዜጎች ሃሳባቸውን በነፃነት የገለጹበት፣ የጋራ መግባባት ላይ የደረሱበት በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥም የጠመንጃ የበላይነትን በማስቀረት፣ የሀሳብ የበላይነትና የሰላማዊ የውይይት ባህልን ለማስፈን ምቹ ምህዳር የፈጠረ አካታች አካሄድ ነው። ከጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሐሳቦችና የተገኙት ልምዶች ወደ ተግባር እየተሸጋገሩ፣ በየደረጃው በሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ውይይቱ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍትም ነው። የጋራ ትርክት ህዝቦች በታሪካቸው፣ በአሁኑ ሁኔታቸው እና በወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ላይ ያላቸው የጋራ መረዳትና ስምምነት ሲሆን ይህም አብሮነትን ለማጎልበት ጠንካራ መሰረት ይጥላል። ለዘመናት በጦርነት፣ በኃይልና በፖለቲካ ሽኩቻ ሲንከባለሉ የቆዩ የትርክት ስብራቶችም ከጠመንጃ ይልቅ በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ክርክር ለመፍታት ስለመቻሉም ትልቅ ማሳያ ነው። በምክክሩ ላይ በመላው ሃገሪቱ አሉን የሚሏቸውን ጥያቄዎችና ቅሬታዎች በኃይል በጦር መሳሪያ ለመፍታት ነፍጥ አንግበው ሲታገሉ የነበሩ አካላት ሁሉ እንዲሳተፉ መደረጉም የሒደቱን ስኬታማነት ለዓለም ማህበረሰብ ያሳየ ነው። ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች፣የፖለቲካ አመለካከቶችና የኅብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ አራት ሺህ ተመካካሪዎች የየራሳቸውን የተናጠል ፍላጎት ብቻ ከማንጸባረቅ ተቆጥበው በተለዩ ስምንቱ አበይት አጀንዳዎች ላይ በጋራ መስማማታቸውም የወል ትርክት ግንባታን የውጤታማነት ጉዞ ስኬት በተግባር የገለጠ ነው። ይህ ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሳይሆን ለሀገር ህልውና እና ለጋራ ዕድገት ቅድሚያ የመስጠት ትልቅ የፖለቲካ ብስለትም ነው። ይህ ሂደት እያንዳንዱ ዜጋ በሀገሩ ላይ ሙሉ ባለቤትነትና ደህንነት እንዲሰማው የሚያደርግ ሲሆን የጋራ አገርና የጋራ ዕድል አለን የሚለውን እሳቤ በማጉላትም የወል ትርክትን በጽኑ መሠረት ላይ ይገነባል። ምክክሩ በጥቂት የፖለቲካ ልሂቃን (Elites) መካከል ብቻ የተደረገ ውይይት ሳይሆን እስከ ወረዳ ድረስ ያሉትን የታችኛውን የህብረተሰብ ክፍሎች፣ አርሶ አደሮችን፣ አርብቶ አደሮችንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ መሆኑም ትልቅ ትርጉም አለው። ከሕዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ የፈለቁት ምክረ ሀሳቦች ለሀገራዊ ትርክት መጠንከር ወሳኝ ሚና ከመጫወት ባለፈ ሂደቱ በህዝቡ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ያደርገዋል። ምክክሩ ያረጋገጠው ትልቁ እውነት የኢትዮጵያውያን ዕጣ ፈንታ የተሳሰረ መሆኑንና የወል ትርክት ግንባታ የሀገር ህልውና ዋስትናነቱን ነው። ልዩነቶችን ውበት፣ ውይይትን ደግሞ መሳሪያ በማድረግ የተጀመረው ይህ ጉዞ ኢትዮጵያ በቀደመ ታሪኳ የገጠሟትን የታሪክ ስብራቶች በመጠገን ወደ ዘላቂ ብልጽግና፣ ዲሞክራሲና እውነተኛ አንድነት እንድትሸጋገር ያስችላታል።

ማህበራዊ
በአማራ ክልል በፍትህ ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው
Aug 29, 2026 15
ባህር ዳር፤ ነሃሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በፍትህ ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች በአማራ ክልል የሚገኙ የፍትህ ተቋማትን የሪፎርም አተገባበር ጎብኝተዋል። ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት በክልሉ በፍትህ ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ዘመኑን የዋጁ አስደናቂ ስራዎች ናቸው ብለዋል። በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተተገበረው በዲጂታል የተደገፈ የኢ-ፋይል አሰራር ፍትሃዊ፣ ግልጽና የተገልጋዩን እንግልት መቀነስ ያስቻለ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል። ተገልጋዮች ጉዳያቸውን ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ በመከታተል አስተማማኝ ፍትህ እንዲያገኙ መደረጉ የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል የተሄደበትን ርቀት የሚያሳይ ነው ብለዋል። በክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያም ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠርና የዲጂታላይዜሽን አሰራርን እውን በማድረግ የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል። በቴክኖሎጂ የዳበረ የፍትህ ስርዓት ለማስፈን በተሰራው ስራ የአመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑን መገንዘባቸውን ጠቁመው፤ በጉብኝታቸው ትልቅ ተሞክሮ ማግኘታቸውን አረጋግጠዋል። በቀጣይ በመተጋገዝና በአብሮነት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከክልሉ የፍትህ ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉዓለም ቢያዝን በበኩላቸው የዳኝነት ስራ ከፖሊስ የወንጀል መከላከልና የተጠናከረ ምርመራ ተግባር ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዲጂታላይዜሽን ትግበራ ቀልጣፋና ፍትሃዊ የፍትህ አሰጣጥ እንዲኖር ያስቻለ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም ከከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ለይግባኝ ይመጡ የነበሩ ባለጉዳዮች ባሉበት ቦታ ሆነው ጉዳያቸውን በመከታተል ገንዘብንና ጉልበታቸውን እንዲቆጥቡ አስችሏል ብለዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች ያደረጉት ጉብኝት ልምድ ከመለዋወጥ ባሻገር ተግባራትን በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። የሪፎርም ትግበራውን እስከ ታች ድረስ ለማውረድ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል። በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አመራሮች ተገኝተዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ቀጣዩን የምህርት ዘመን ስኬታማ ለማድረግ ትኩረት ተደርጓል
Aug 29, 2026 52
ወልቂጤ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ቀጣዩን የምህርት ዘመን ስኬታማ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን በህብረተረብ ተሳትፎ የታተሙ ከ160 ሺህ በላይ መጽህፍትን በዞኑ ለሚገኙ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች አስረክበዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት በቅድመ-መደበኛ ትምህርት ላይ መስራት ተማሪዎች ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል። በመሆኑም ለትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፤ ግብዓቶችን በማሟላት የ2019 የትምህርት ዘመንን ስኬታማ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ይጠናከራሉ ብለዋል። እንደሀገር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የተያዘውን አቅጣጫ ውጤታማ እንዲሆን ዘርፉን የመደገፍ ሥራ በትኩረት እንደሚከናወንም አመልክትዋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በበኩላቸው፤ በክልሉ ለ2019 የትምህርት ዘመን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ለዚህም በክልሉ ላሉ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ መጽሃፍት መሰራጨታቸውንም በማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የመገንባትና ደረጃቸውን የማሻሻል ሥራ መከናወኑንም አመልክተዋል። የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም በዞኑ ለቅድመ አንደኛ፣ ለአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 160ሺህ 169 መጽሃፍት መሰራጨታቸውን ገልጸዋል። መጽሃፍቱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የታተሙ ሲሆን ከ37 ሚሊዮን ብር በላይም ውጪ የተደረገባቸው መሆኑንም አስታውቀዋል። በተጨማሪም በህዝብ ተሳትፎ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ለመማር ማስተማር ሥራው ዝግጁ መደረጋቸውን ተናግረዋል።
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትምህርት ጥራት፣ በቴክኖሎጂና በፈጠራ ስራዎች ራሳቸውን በማብቃት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ አለባቸው
Aug 29, 2026 107
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትምህርት ጥራት፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በፈጠራ ስራዎች ራሳቸውን በማብቃት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሽኔ አስገነዘቡ። የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ ሀገር አቀፍ የትምህርት ኮንፍረንስ እያካሄደ ይገኛል። በኮንፍረንሱ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሽኔን ጨምሮ የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች ተገኝተዋል። ኮንፍረንሱ ለ15ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በየአመቱ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት የመፍትሄ ሃሳቦች የሚቀመጥበት መድረክ መሆኑ ተጠቅሷል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኩራ ጡሽኔ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የምክክር መድረኩ በሀገሪቱ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ የምርምር ስራዎችን ለማቀናጀት ያስችላል። መድረኩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት በመማር ማስተማር እና በጥናትና ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትብብር ላይ እያመጣ ያለውን አዎንታዊና የጎንዮሽ ተፅእኖዎች ላይ ያተኮረ መሆኑንም አንስተዋል። በተጨማሪም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በሰው ሃይል፣ በመሰረተ ልማትና ቤሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ዝግጁነት ላይም ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለትምህርት ጥራትን መረጋገጥ፣ ለጥናትና ምርምር ሂደት ብሎም ለመረጃ አሰባሰብና ትንተና አስተዋፅኦ እንዳለውም ገልፀዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለሰው ልጅ እገዛ የሚያደርግ በመሆኑ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ቴክኖሎጂውን በአግባቡ በመጠቀም የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመማር ማስተማር ሂደት፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ዩኒቨርቲዎችን የፈጠራ ማዕከል ለማድረግ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን መጠቀም አዋጪ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ጥራት፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በፈጠራ ስራዎች ራሳቸውን በማብቃት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።
የጎቤ እና የሺኖዬ ጨዋታዎች ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ መካሄድ አለባቸው
Aug 29, 2026 74
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሞ ባህል መሠረት በየዓመቱ በወጣቶችና ልጃገረዶች የሚካሄዱ የጎቤ እና የሺኖዬ ጨዋታዎች ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ መከናወን እንዳለባቸው የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ አሳሰቡ። ጎቤ እና ሺኖዬ በኦሮሞ የገዳ ሥርዓት ውስጥ የሚከወኑ፣ የክረምት ወቅት አልፎ የጸደይ (የብራ) ወቅት መግባቱንና የዘመን መለወጫን የሚያበስሩ ታላላቅ ባህላዊ የወጣቶች ጨዋታዎች እና ትውፊቶች ናቸው። የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ ዛሬ በሆራ ፊንፊኔ የጎቤ እና የሺኖዬ ጨዋታ ባህላዊ እሴታቸውን እና ወጉን ጠብቀው በሚካሄዱበት ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በወጣቶች እና ልጃገረዶች የሚከናወኑት የጎቤ እና የሺኖዬ ጨዋታ የኦሮሞ የቀደመ ባህላዊ እሴቱንና ወጉን በጠበቀ መልኩ መካሄድ እንዳለባቸው ገልጸዋል። ጎቤ እና ሺኖዬ ብራን ለመቀበል በወጣቶች እና ልጃገረዶች የሚካሄዱ ጨዋታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። በጎቤ እና ሺኖዬ ጨዋታዎች ስርዓት ውስጥ ሁሉም ነገር ወግ እና ወሰን ያለው መሆኑን የገለጹት አባ ገዳው፤ ጨዋታዎቹ ለአቅመ አዳም እና ሔዋን በደረሱ ወጣቶች እና ልጃገረዶች ብቻ የሚከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። በጨዋታውም ወጣቶች እና ልጃገረዶች እየተዘዋወሩ በመጨፈር ስጦታ የሚቀበሉበት እና "እንኳን ለብራ ወቅት አደረሳችሁ" የሚሉበት መሆኑን ገልጸዋል። የጎቤ እና ሽኖዬ ጨዋታዎች ባህላዊ እሴትን እና ወጉን ጠብቀው እንዲከናወኑ የሚመለከተው አካል ሁሉ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። የጎቤ እና ሽኖዬ ጨዋታዎች ከነሀሴ አጋማሽ ጀምሮ እስከ መስከረም እንደሚካሄዱ ታውቋል።
ኢኮኖሚ
በሶማሌ ክልል የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ ነው - ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ
Aug 29, 2026 61
ጅግጅጋ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የተቋማትና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ፤ የክልሉን ኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪና ቢሮ አዲስና ዘመናዊ የህንፃ ግንባታ አስጀምረዋል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግርም በክልሉ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። ከልማት ስራዎች በተጓዳኝ የመንግስት አገልግሎቶችን ምቹ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል። በዛሬው እለትም የክልሉን ኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪና ቢሮ አዲስና ዘመናዊ የህንፃ ግንባታ መጀመሩን ገልጸው፤ የተቋማትና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች ይቀጥላሉ ብለዋል። ከዚህ ጎን ለጎን የትምህርት፣ የውሃ፣ የመንገድ፣ የጤና የዲጂታል ልማትና ሌሎችም ስራዎች በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል። በክልሉ ከተሞችም ይሁን በገጠር ሰው ተኮር የሆኑ ልማቶችን የመገንባትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ዋነኛ ትኩረታችን ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።
በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የሐረር ከተማን የቱሪዝም መዳረሻነት እያሳደጉ ነው
Aug 29, 2026 63
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ) ፦ በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የሐረር ከተማን የቱሪዝም መዳረሻነት በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እያስገኙ መሆናቸውን የክልሉ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሚ አብዱልዋሲ ገለጹ። መንግሥት ካለፉት ዓመታት ወዲህ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶችን በመግለጥ፣ በርካታ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማትና ለነባሮቹም እሴት የሚጨምሩ ተግባራትን በማከናወን የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻነት እያሳደገ ይገኛል።   የክልሉ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሚ አብዱልዋሲ እንደገለጹት፤ የክልሉን እምቅ የቱሪዝም ሃብት አልምቶ በመጠቀም ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበ ነው። በተለይም በመደመር መንግስት ቱሪዝም ከዋና የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ አንዱ ሆኖ መወሰዱና ትኩረት መሰጠቱ ዘላቂነት ያለው እድገት እንዲመዘገብ ማስቻሉን ገልፀዋል። በዚህም ባለፉት ጥቂት ዓመታት በክልሉ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ከማልማት ባሻገር ነባር ቅርሶችን በመጠገንና በመንከባከብ ሰፋፊ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። በጁገል አለም አቀፍ ቅርስ እድሳትን ጨምሮ ነባርና አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ስራዎችና መሰል ተግባራት የክልሉ ቱሪዝም በፍጥነት እንዲነቃቃ እያደረገ መሆኑንም በማሳያነት ጠቅሰዋል። በተጨማሪም በዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት የሃገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሃገራት ጎብኚዎች ቁጥር እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በክልሉ የቱሪስት መስህብ ሃብቶችን የማስተዋወቅ፣ መዳረሻ ስፍራዎችን የማልማትና መሰረተ ልማቶችን የማሟላት ሥራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል።
በክልሉ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
Aug 29, 2026 101
ጉንችሬ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ። በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር የተገነቡት የጉንችሬ ጤና ጣቢያ እና የጉንችሬ ብራይት አንደኛ እና ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። ፕሮጀክቶቹን የመረቁት ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ለአብነትም ዛሬ ከተመረቁት የጤናና የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ የገበያ ማዕከላት እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታ መከናወኑን ጠቅሰዋል። ፕሮጀክቶቹ ለማህበረሰቡ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የክልሉ መንግስት የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ዛሬ የተመረቁት ፕሮጀክቶች መንግስት የማህበረሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመረውን ተግባር እውን ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያሉ ሲሉም አክለዋል። ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እና በእውቀት የታነጹ ምስጉን ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ፕሮጀክቶቹ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸውም አመልክተዋል። በክልሉ የሕብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ርስቱ ይርዳው የጉንችሬ እና በዙሪያው ያሉ ነዋሪዎች በጤናና በትምህርት ተቋማት እጥረት የተነሳ ሲቸገሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። መንግስት ህብረተሰቡንና ረጂ ድርጅቶችን በማስተባበር ያስገነባቸውና ዛሬ ለምረቃ የበቁት ፕሮጀክቶች ይህን ችግር እንደሚፈቱ ጠቅሰው፣ ማህበረሰቡ ፕሮጀክቶቹን ከመጠበቅ ባለፈ ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ የጤና ተቋሙ እና የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ በዞኑ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብቶ የመጨረስ ማሳያ ናቸው ብለዋል። ፕሮጀክቶቹ የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ የልማት ጥያቄን ምላሽ ለመስጠት ማስቻላቸውንም ተናግረዋል። የጉንችሬ ከተማ ከንቲባ አቶ አብድልቋድር ሂጅራ በበኩላቸው እንዳሉት፣ የማህበረሰቡን ጤና ለማሻሻል እና ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ የፕሮጀክቶቹ መገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በፕሮጀክቶቹ የምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የፌደራል፣ የክልል፣ የጉራጌ ዞን እና የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ ከታይላንድ ጋር ያላትን ዘመናት ያስቆጠረ ወዳጅነት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ፣ የንግድና የኢንቨስትመንት አጋርነት ለመቀየር ቁርጠኛ ናት- አምባሳደር ደዋኖ ከድር
Aug 29, 2026 102
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከታይላንድ ጋር ያላትን ዘመናት ያስቆጠረ ወዳጅነት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ፣ የንግድና የኢንቨስትመንት አጋርነት ለመቀየር ቁርጠኛ መሆኗን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ እስያና ፓስፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ደዋኖ ከድር ገለጹ። በኢትዮጵያ የታይላንድ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጂሩሳያ ቢራናንዳ በበኩላቸው ታይላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድና የኢኮኖሚ ትብብሯን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል። "ታይላንድ-ኢትዮጵያ፡ የቢዝነስ ግንኙነትን መገንባት" በሚል መሪ ሃሳብ የታይላንድ-ኢትዮጵያ የቢዝነስ ፎረም እየተካሄደ ነው። በፎረሙ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ እና የታይላንድ የንግድ ማህበረሰብ አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ እስያና ፓስፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ደዋኖ ከድር በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ረጅም ታሪክ ያለው ነው። ይህንን የፖለቲካ ግንኙነቱን ወደ ተጨባጭ የንግድና የኢኮኖሚ ትስስር ማሸጋገር እንደሚገባ ተናግረዋል። በተለይም ታይላንድ በቱሪዝም፣ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ በፋርማሲዩቲካልስ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ያላትን የበለጸገ ልምድ ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል። በተጨማሪም ታይላንድ አዲስ ይፋ ያደረገችውን "የአፍሪካ-ታይላንድ ኢኒሼቲቭ" አድንቀው፤ ጥረቱን ወደ ተጨባጭ የድርጊት መርሃ ግብር በመቀየር ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በኢንዱስትሪ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎች ያሏት ሀገር መሆኗንም ተናግረዋል። በዚህም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ የታይላንድ ኩባንያዎች እና የንግድ ማህበረሰብ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ የታይላንድ አምባሳደር ጂሩሳያ ቢራናንዳ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያና ታይላንድ ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው። ይህን የሁለቱን ሀገራት መልካም የፖለቲካ ግንኙነት ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋርነት እና ተጨባጭ የንግድ እድሎች መቀየር ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ ቁልፍ የኢኮኖሚ ማዕከል መሆኗን ጠቁመው፤ ሀገሪቱ ያላት ሰፊና እያደገ የመጣ ገበያ፣ ስትራቴጂካዊ መገኛ፣ የበለጸገ የግብርና ሀብት፣ የልማት አጀንዳ እና እየተስፋፋ ያለው መሰረተ ልማት ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ሰፊ የእድል የሚከፍት መሆኑን ገልጸዋል። ታይላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የምታደርገው አጋርነት የሥራ እድል የሚፈጥር፣ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር የሚያመጣ እንዲሁም ለጋራ ብልጽግና አስተዋፅኦ የሚያደርግ እንዲሆን እንደምትፈልግ አምባሳደሯ ተናግረዋል። የንግድ ማህበረሰቡ ከዛሬው መድረክ ወዳጅነትን ወደ አጋርነት፣ አጋርነትን ደግሞ ለጋራ ብልጽግና እንዲያውል ጥሪ አቅርበዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማደግና ዲጂታላይዜሽን የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ እያሻሻለ ነው
Aug 29, 2026 88
ቦንጋ ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማደግና ዲጂታላይዜሽን የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ እያሻሻለ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የቦንጋ ከተማ ነዋሪ ምሁራን ገለጹ። የመደመር መንግሥት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠንና አገልግሎቶችን ለማዘመን የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን በተግባር ማየታቸውንም ምሁራኑ ተናግረዋል። የኮሌጁ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምህር ምስጋናው ታደሰ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የዲጂታላይዜሽን ትግበራ የሀገር ልማትን ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን፣ የመንግሥት አሠራር ብቃትን ማሳደጊያ እና የዜጎችን ኑሮ ማሻሻያ መሣሪያ ነው። የመደመር መንግሥት ለዲጂታላይዜሽን በሰጠው ልዩ ትኩረት ውስጥ ተግባራዊ የተደረገው የዲጂታል 2025 እስትራቴጂ የዜጎችን የአኗኗር ሁኔታ በተጨባጭ ማሻሻሉንም ነው ምሁሩ የተናገሩት። በዚህ እስትራቴጂ በሞባይል ባንኪንግ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በኦንላይን አገልግሎቶችና በዲጂታል መታወቂያ ዘርፎች የተመዘገቡ ለውጦች ዜጎች የተለያዩ አገልግሎቶችን በቀላሉና በተፋጠነ መንገድ እንዲያገኙ ያደረጉ መሆኑን አንስተዋል። በኢኮኖሚው ዘርፍም አዳዲስ የንግድ ዕድሎችን የፈጠረ ሲሆን የዚሁ አካል የሆነው የ‘ኢትዮ-ኮደርስ’ ፕሮግራም ወጣቶችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ከመሆን ባለፈ የቴክኖሎጂ ፈጣሪ እንዲሆኑ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። በመሆኑም በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተገኙ አበረታች ውጤቶች ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጠንካራ መሠረት የጣሉ መሆናቸውን አስረድተዋል። ባለፉት ዓመታት በዘርፉ የተከናወኑት ተግባራት ዲጂታል ኢኮኖሚውን በማስፋፋት የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሻሻላቸውን የገለጹት ደግሞ የኮሌጁ የመረጃ ቴክኖሎጂ መምህር ታደሰ ዘውዴ ናቸው። ከዚህ ውስጥም የ‘መሶብ’ የአንድ ማዕከል አሠራር የመንግሥት አገልግሎቶችን ተደራሽነት በማሻሻል ዜጎች ጊዜና ወጪያቸውን በቆጠበ መልኩ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያደረገ መሆኑንም ለአብነት አንስተዋል። የዲጂታል 2025 መጠናቀቅን ተከትሎ የተተገበረው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በኢኮኖሚው ዘርፍና በማኅበረሰቡ ውስጥ ሰፊ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑንም ነው የገለጹት።
በአማራ ክልል የመሶብ አንድ ማዕከልን ጨምሮ ከ35 በላይ የዲጂታል አሰራሮችን ለመዘርጋት ተችሏል- ቢሮው
Aug 28, 2026 104
ባህር ዳር፡ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የመሶብ አንድ ማዕከልን ጨምሮ ከ35 በላይ የዲጂታል አሰራሮችን በመዘርጋት ቀልጣፋና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት መስጠት መቻሉን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው ባለፉት ሦስት ዓመታት በዲጂታላይዜሽን ትግበራ በተመዘገቡ ውጤቶችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ዛሬመግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የመሶብ አንድ ማዕከላትን ጨምሮ የተለያዩ ዘመናዊ መተግበሪያዎችን በማልማት ለህብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ተችሏል። የክልሉ መንግሥት በ25 ዓመት የስትራቴጂክና አሻጋሪ ዕቅዱ ለቴክኖሎጂው ዘርፍ በሰጠው ትኩረት መሠረት፣ አገልግሎት በሚበዛባቸው ተቋማት ላይ በማተኮር ከ35 በላይ የዲጂታል አሰራሮች መዘርጋቱን ነው የገለጹት። ቴክኖሎጂዎቹ በፍትሕ ሥርዓት፣ በፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ ኢንቨስትመንት በመሳብና በግብርናው ዘርፍ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲመጣ ማስቻላቸውንም አብራርተዋል። በተጨማሪም ቴክኖሎጂዎቹ የመንግሥት አካላት በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲሰጡ ከማድረጋቸው ባሻገር፣ ይስተዋሉ የነበሩ ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አስረድተዋል። በተለይም "መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በክልል ደረጃ በባህር ዳር፣ ደሴና ወልዲያ ከተሞች ተግባራዊ በማድረግ የህዝቡን እርካታ ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል። በተካሄደው የዳሰሳ ጥናትም እስካሁን ከ103 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በኩል ፈጣን ፣ ፍትሐዊና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት ማግኘታቸው መረጋገጡን አስገንዝበዋል። በአሁኑ ወቅትም የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ወደ ሌሎች ከተሞች ለማስፋት የግንባታና የቴክኖሎጂ ዝርጋታ ሥራው እየተፋጠነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በቀጣይ ዓመትም የዲጂታል 2030ን ግብ ለማሳካት ተጨማሪ ከ13 በላይ አዳዲስ መተግበሪያዎችን የማልማት ስራ እንደሚከናወን አብራርተዋል። በክልሉ በዲጂታል ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን ለህዝብ ለማስተዋወቅ ያለመ የፓናል ውይይትና የኤግዚቢሽን መርሃ-ግብር ከነሐሴ 28 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ እንደሚካሄድ ተመላክቷል።  
የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባዔ ኢትዮጵያ በክትባትና በጤና ምርምር ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ውጤቶች ለማስተዋወቅ ምቹ አጋጣሚ ፈጥሯል
Aug 28, 2026 149
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባዔ ኢትዮጵያ በክትባትና በጤና ምርምር ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ውጤታማ ተግባራት ለማስተዋወቅ ምቹ አጋጣሚ መፍጠሩን የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ገለጹ። በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ኮሚቴ ጉባዔ በትናንትናው ዕለት በስኬት መጠናቀቁ ይታወቃል፡፡ የጉባዔው ተሳታፊዎች በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩትን በመጎብኘት በሥራ ላይ ያሉ አቅሞችንና የምርምር ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡   የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በጉባዔው በጤና ምርምር ዘርፎች ያስመዘገበቻቸውን ውጤታማ ተግባራት ለአህጉሩ ተወካዮች ማጋራት ችላለች፡፡ በመድረኩ በጤና መረጃ ሥርዓት ትንተና፣ በአቅም ግንባታ እና በክትባት ዙሪያ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች አጋርታለች ብለዋል፡፡ ተጨባጭ ስኬቶቿን እንድታሳይ ከማስቻሉም በላይ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የጠበቀ የላቦራቶሪና የምርምር ትስስር እንድትፈጥር ማስቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ የጋራ ልምድ ለመለዋወጥ ትልቅ ዕድል መፍጠሩንም እንዲሁ፡፡ በጉባዔው ወቅት የቀረቡት የምርምርና የአቅም ግንባታ ሥርዓቶች በቀጣይ ለሚከናወኑ ሀገራዊና አህጉራዊ የጤና ሥራዎች በበጎ መነሻነት የሚያገለግሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ጉባዔው ለኢትዮጵያም ሆነ ለተሳታፊ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ መልካም አጋጣሚ እንደነበር አብራርተዋል፡፡   በጋምቢያ የጤና ሚኒስቴር የጤና አገልግሎት ዳይሬክተር (ዶ/ር) ሞሞዶ ንያሲ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት ሂደቱ እጅግ ፈጣንና በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ በተለይ የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ለአጠቃላይ የአፍሪካ አህጉር የሚመጥን ትልቅ የልህቀት ማዕከል መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የህክምና ባለሙያዎቻቸውንና ተመራማሪዎቻቸውን ለልምድ ልውውጥ፣ ለምርምር፣ ለፈጠራ ሥራዎችና ለትምህርት ሊልኩበት የሚችሉበት ተስፋ ሰጪ ኢንስቲትዩት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካን የጤና አጀንዳ በተሻለ ደረጃ ለማሳካትና አህጉራዊ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ከኢንስቲትዩቱ ጋር የጠበቀና የተቀናጀ የትብብር ግንኙነት ለመሥራት በጉጉት እንደሚጠብቁም ተናግረዋል፡፡
የስፔሻላይዝድ የውሃ ላቦራቶሪው የውሃ ጥራትን በማስጠበቅ የምርመራና ምርምር አቅም ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል
Aug 27, 2026 624
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፦ የስፔሻላይዝድ የውሃ ላቦራቶሪው የውሃ ጥራትን በማስጠበቅ የምርመራና ምርምር አቅም ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ የውኃ ጥራት ምርመራንና ምርምርን ለማጠናከር የተገነባውን ስፔሻላይዝድ የውኃ ምርመራ ላቦራቶሪ ዛሬ አስመርቋል።   የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታመና ኃይሉ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የውኃ ጥራትን በተሟላ መልኩ መመርመር የሕዝብ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር የውኃ ሀብትን በዘላቂነት ለመጠቀም የላቀ ሚና አለው። ላቦራቶሪው የሕክምናና የውኃ ማጣሪያ ሂደቶችን በተገቢው ለመምራትና የሀገሪቱን የምርመራ አቅም ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል። በተለይም ለመጠጥ፣ ለመስኖና ለኢንዱስትሪ የሚውል ውኃ ተገቢውን የጥራት ደረጃ እንደሚያሟላ ለመለየት ምርመራ የሚያካሂድ ሲሆን፣ የውኃ ምርመራ ውጤቶችን በአንድ ቦታ በማሰባሰብ ለምርምርና ለዕውቀት ማከማቻ ለማዋል ያስችላል ብለዋል። አንድ የውኃ ምንጭ በአንድ ወቅት ንጹሕ መሆኑ በሌላ ወቅትም ተመሳሳይ ጥራት እንዳለው አያረጋግጥም። በመሆኑም የውኃ ጥራት በየጊዜው በመመርመር ውጤቶቹ በዳታ መልክ መመዝገብና ለተለያዩ የልማትና የምርምር ሥራዎች መዋል እንዳለበት ጠቁመዋል። በላቦራቶሪው በኩል በሀገሪቱ በተበታተነ መልኩ የሚገኙ የላቦራቶሪ አቅሞችን በማስተሳሰር፣ ባለሙያዎችን በማሰልጠንና በአይኤስኦ ደረጃዎች የተመሠረተ የምርመራ ሥርዓት በመዘርጋት የሀገሪቱን የላቦራቶሪ አቅም ለማጠናከር እንደሚሠራም ተገልጿል።   በኢንስቲትዩት የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀምበርነሽ ክንፈ በበኩላቸው፣ የውኃ ናሙና እና ምርመራ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት ላቦራቶሪው ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል። ላቦራቶሪው ከውኃ ጥራት ምርመራ በተጨማሪ የውኃ ጥራት ምርምርና ሥልጠና እንዲሁም ከአቅም በላይ የሆኑ ምርመራዎችን በማከናወን እንደ ሪፈራል ላቦራቶሪ ሊያገለግል እንደሚችልም አስረድተዋል። በተጨማሪም የተፋሰስና የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የውኃ ናሙናዎችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት እንዲያስመረምሩና ከውኃ ጋር ተያያዥ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ዕድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል። ላቦራቶሪው በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር የውኃ ጥራትን ከማረጋገጥ ባለፈ የምርምር፣ የሥልጠና፣ የገቢ ማመንጫና የውኃ ዲፕሎማሲ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል ሲሉም ተናግረዋል።   ላቦራቶሪው በውኃ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካላዊ፣ አካላዊና ማይክሮባዮሎጂያዊ ይዘቶችን በመመርመር የውኃ ጥራትን ለማረጋገጥ ያግዛል ያሉት ደግሞ የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የስፔሻላይዝድ ላቦራቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አብዱረህማን ሰይድ ናቸው። ቀደም ሲል በሀገር ውስጥ ባሉ ላቦራቶሪዎች ሊከናወኑ ያልቻሉ አንዳንድ ምርመራዎች ወደ ውጭ በመላክ ይከናወኑ እንደነበር ጠቁመው፣ የምርመራ ውጤት ለማግኘት የሚወስደውን ጊዜም ያሳጥራል ብለዋል። በውኃ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ወይም ጎጂ ማይክሮኦርጋኒዝሞች ከተፈቀደው መጠን በላይ መኖራቸው በሰው ጤና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ስለሚችል፣ የውኃ ጥራትን በላቦራቶሪ መፈተሽ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።    
ስፖርት
አዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ ተከታታይ ድሉን ሲያስመዘግብ ቦርንማውዝ እና ኤቨርተን አቻ ተለያይተዋል
Aug 29, 2026 55
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬም መካሄዱን ቀጥሏል። በኮቨንተሪ ቢውልዲንግ ሶሳይቲ አሬና በተካሄደው ጨዋታ ሁል ሲቲ ኮቨንተሪ ሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል። ሊያም ሚላር በ82ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ አዲስ አዳጊው ሁልሲቲ ተከታታይ ድሉን በማስመዝገብ ያልተጠበቀ ጅማሮ አድርጓል። በአንጻሩ ሌላኛው አዳጊ ክለብ ኮቨንተሪ ሲቲ ተከታታይ የሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል። በቫይታሊቲ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ቦርንማውዝ እና ኤቨርተን አንድ አቻ ተለያይተዋል። አሌክስ ስኮት ለቦርንማውዝ፣ ጀምስ ታርኮስኪ ለኤቨርተን ግቦቹን አስቆጥረዋል። ታርኮስኪ በ91ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ኤቨርተንን አቻ አድርጋለች። በመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸው ሽንፈት ያስተናገዱት ሁለቱ ክለቦች የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል። ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከኒውካስትል ዩናይትድ በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ቀን ላይ በተካሄደ ጨዋታ ሊቨርፑል እና ኖቶንግሃም ፎረስት ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ ፍጻሜው ሽንፈት አስተናገደ
Aug 29, 2026 92
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዩጋንዳው ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ 3 ለ 0 ተሸንፏል። በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆቪያ ናካጎሎ፣ አግነስ ናቡኬንያ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ትዕግስት አዳነ በራሷ ላይ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ወክሎ የመሳተፍ ህልሙ ግማሽ ፍጻሜ ላይ ተገቷል። ንግድ ባንክ ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ይጫወታል። የዩጋንዳው ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ ለፍጻሜ አልፏል። በፍጻሜው ከኬንያ ፖሊስ ቡሌትስ እና ከደቡብ ሱዳን ዬ ጆይንት ስታርስ አሸናፊ ጋር ይጫወታል። ኬንያ ፖሊስ ቡሌትስ እና ዬ ጆይንት ስታርስ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ይጫወታሉ። የግማሽ ፍጻሜ አሸናፊ ቡድኖች ሰኞ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በፍጻሜው ይገናኛሉ። የማጣሪያ ውድድሩን የሚያሸንፈው ክለብ በሻምፒዮንስ ሊጉ ሴካፋ ዞንን ወክሎ መሳተፉን ያረጋግጣል። ነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሩዋንዳ ኪጋሊ የተጀመረው የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከነገ በስቲያ ይጠናቀቃል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሴካፋ ማጣሪያ ፍጻሜ ለማለፍ ከካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ ጋር ይጫወታል
Aug 29, 2026 96
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዩጋንዳው ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ ጋር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል። ጨዋታው ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ይካሄዳል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምድብ ሁለት በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል። በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚሰለጥነው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሶስቱ ምድብ ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ በማጠናቀቁ ምክንያት ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጅቡቲውን ኡጄኮን 11 ለ 0 በመርታቱ ባለው የግብ ክፍያ ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ እንዲያጠናቅቅ አስችሎታል። ንግድ ባንክ በምድቡ በካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ የ1 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል። ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ በምድብ ሁለት በስድስት ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በምድብ ሁለት አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ካዌምፔ እና ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ የጨረሰው ንግድ ባንክ ዳግም በግማሽ ፍጻሜው ተገናኝተዋል። ሁለቱ ክለቦች እ.አ.አ በ2024 በአዲስ አበባ በተካሄደው የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ማጣሪያ በግማሽ ፍጻሜ ተገናኝተው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፏል። ንግድ ባንክ በወቅቱ የማጣሪያ ውድድሩን በማሸነፍ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ መሳተፉ የሚታወስ ነው። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ኬንያ ፖሊስ ቡሌስ ከደቡብ ሱዳኑ ዬ ጆይንት ስታርስ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ይጫወታሉ። የግማሽ ፍጻሜ አሸናፊ ቡድኖች ሰኞ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በፍጻሜው ይገናኛሉ። የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከነሐሴ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሩዋንዳ ኪጋሊ እየካሄደ ይገኛል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማጣሪያ ውድድሩን ካሸነፈ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለሁለተኛ ጊዜ መሳተፉን ያረጋግጣል። በ2026 የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ ለመሳተፍ 36 ክለቦች በስድስት አህጉራዊ ዞኖች ተከፍለው የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል። በአህጉራዊ ቀጣናዎች በሚደረጉ ማጣሪያዎች አሸናፊ የሆኑ ክለቦች፣ የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ የሞሮኮው ኤኤስ ፋር እና ውድድሩን የሚያዘጋጀው ሀገር ተወካይ ጨምሮ ስምንት ቡድኖች በዋናው ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስታውቋል። የ2026 የካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ዋና ውድድር አዘጋጅ ሀገር በቅርቡ በአወዳዳሪው አካል ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
አካባቢ ጥበቃ
የሀዋሳ ከተማን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚመጥኑ ውጤታማ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ -ከንቲባ ጥራቱ በየነ
Aug 29, 2026 56
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ የሀዋሳ ከተማን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚመጥኑ ውጤታማ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የከተማዋ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለፁ። በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ጽህፈት ቤት "ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" በሚል መሪ ሀሳብ የጽዱ ኢትዮጵያ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ ጥራቱ በየነ፤ የከተማዋን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚመጥኑና ከተማዋን ውብ፣ ጽዱና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ የሚያግዙ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል። በከተማዋ ከኮሪደር ልማት ሥራ ጋር በተያያዘ ሰፋፊ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች እንዲሁም በየአካባቢው የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች መገንባታቸውንም አመልክተዋል፡፡ ሃዋሳ ውበትና ጽዳት መለያዋ መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባ ጥራቱ፤ ከከተማዋ ዕድገትና ኢንቨስትመንት መስፋፋት ጋር ተያይዞ በቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት ላይ ውስንነቶች እንዳሉ ተናግረዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፣ በ2019 ዓ.ም የከተማዋን አድገት የሚመጥን አዲስ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥፍራ ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ከከተማዋን ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር ተጣጥመው እየተከናወኑ ያሉ ውጤታማ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል። የሃዋሳ ከተማ የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሹምባሻ በበኩላቸው በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ከአካባቢ ጥበቃ ሥራ ጋር የተሰናሰለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በከተማዋ በየመንደሩ ቆሻሻ የሚሰበስቡና ለይተው የሚያስወግዱ ማህበራትን በማደራጀት ጽዱ አካባቢን የመፍጠር ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከብክለት የጸዳ ከባቢና ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር አስተዋጽኦ እያደረገ ነው
Aug 28, 2026 174
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22 /2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከብክለት የጸዳ ከባቢና ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የግሎባል ፈንድ የአፍሪካ ተወካዮች ቢሮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ሄንሪ ፎሙንዳም ገለጹ። በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 76ኛው የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ኮሚቴ ጉባኤ በስኬት ተጠናቋል። የአፍሪካ ሀገራት፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የጤና መሪዎች በተሳተፉበት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ዲጂታልና ሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዘ የጤና ሥርዓት ግንባታ በሽታን በመከላከልና አክሞ በማዳን አቅም ለአፍሪካውያን ምሳሌ የሚሆን ጥረት እያደረገች መሆኑ ተመላክቷል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከ50 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ለግብርና ምርታማነት፣ ለመድኃኒት ቅመማና ለአየር ንብረት ደኅንነት ውጤት እያስመዘገበች መሆኑ ተገልጿል። በመድረኩ ላይ የተገኙት ዶክተር ሄንሪ ፎሙንዳም ለኢዜአ እንዳሉት፤ በአፍሪካ ጠንካራና ዘላቂ ዋስትና ያለው የጤና ሥርዓት ለመገንባት ትብብር ወሳኝ ነው። የአፍሪካውያን ዕውቀት፣ የተፈጥሮ ጸጋና በቂ የሰው ኃይል የጤና ፋይናንስና የአስተዳደር ሥርዓቱን በማዘመን የራሳቸውን ጠንካራ የጤና ተቋማት መፍጠር እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ የጤና እክሎችን በመቀነስ የዜጎችን በሕይወት የመኖር ምጣኔ እንደሚያሻሽል ተናግረዋል። በዚህም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አፍሪካዊት ቀዳሚ ሀገር በመሆን ከብክለት የጸዳ ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል። አፍሪካውያን የጤና ሥርዓታቸውን በራሳቸው አቅም ለመገንባት ከአጋር አካላት ጋር የሚኖራቸው ትብብር በትይዩ እንጂ ሰጪና ተቀባይ እንዲሆን መፍቀድ እንደማይገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። የአፍሪካን የጤና ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ከጤና የተሻገረ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ራስን መቻል እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በአህጉሪቷ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አምራች ኢንዱስትሪዎች መካከል ትስስር ለመፍጠር መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥርም አብራርተዋል።
ለትውልድ የሚተርፍ ውርስ፡የአረንጓዴ አሻራ ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ
Aug 28, 2026 119
ድርቅ እና የደን መጨፍጨፍ ከኢትዮጵያ ጋር ለበርካታ ዓመታት ሲነሱ የቆዩ ጉዳዮች ናቸው። ኢትዮጵያ ይሄን ታሪኳን ለመቀየር ቆርጣ ከተነሳች ዓመታት ተቆጥረዋል።አረንጓዴ አሻራ-ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በአካባቢ ጥበቃ እና የማይበገር የአየር ንብረት ለውጥ አቅም ግንባታ ግንባር ቀደም የሆነ የለውጥ ሞተር ሆኗል። በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ብዝሃ ህይወትን ወደ ቀደመው ስፍራ ለመመለስ፣በረሃማነት ለመከላከል፣የደን ሽፋንን ከመጨመር አልፎ የአየር ንብረት ለውጥ የመከላከል ጥረቶች አስተዋጽኦ እስከ ማበርከት ደርሷል። የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦች እና ከፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ጋር በመሰናሰል ዘላቂ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ ኢኮኖሚ የመገንባት ትልም አለው። ኢኒሼቲቩ ድንበር ተሻጋሪ ተጽእኖ ያለው ነው ቢባል የተጋነነ አይሆንም።አረንጓዴ አሻራ በደን መልሶ ማልማት አማካኝነት ዛፎችን ወደ ይዞታቸው በመመለስ ወደ አየር ሊለቀቅ የሚችል በሚሊዮን ቶኖች የሚቆጠር ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ አምቆ በመያዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካርቦንዳይ ኦክሳይድን ከከባቢ አየር የማስወገድ እና የማከማቸት ጥረት ውስጥ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የካርቦን ዳይኦክሳይድን አምቆ መያዝ እና ማከማቸት በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። ድንበር ተሻጋሪው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአፍሪካ ቀንድ የመሬት መሸርሸርን ከመከላከል፣የደን ሽፋንን በመጨመር፣በረሃማነትን ከመከላከል እንዲሁም በአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የራሱን በጎ ሚና ተጫውቷል። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ አየር ንብረት ለውጥ ውይይቶች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሯ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን በመቀነስ ረገድ እያበረከተ ያለው ሚና እውቅና የተሰጠው ነው። መልከ ብዙው አረንጓዴ አሻራ በአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ አዲስ አማራጭን ይዞ የመጣ እንደሆነም ይነገርለታል። ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና አካባቢ ጥበቃ ስራ የውጭ እርዳታ ላይ ጥገኛ ከመሆን በሀገር ውስጥ አቅም ሀብት የማሰባሰብ ሞዴል መፍጠር ችሏል። ሀገር በቀል ፋይናንስ፣የማህበረሰብ ጉልበት እና የአይነት ድጋፎች ተዳምረው በአነስተኛ በጀት ፈጠራ የታከለበት የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ ማከናወን እንደሚቻል አሳይቷል። ኢትዮጵያ ከአረንጓዴ አየር ንብረት ለውጥ ፈንድ (GCF)፣ የዓለም ባንክ፣የተባበሩት መንግስት የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮግራም እና ሌሎች አጋሮች ለአካባቢ ጥበቃ ስራዎች የገንዘብ ድጋፍ እና የቴክኒክ ድጋፎችን አግኝታለች። የተገኘው ዓለም አቀፍ ድጋፍ የአካባቢ ጥበቃ ስራ በኢትዮጵያ የልማት ፖሊሲዎች የበለጠ እንዲተሳሰሩ አድርጓል። አረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥ ግቦችን ከኢኮኖሚ ልማት፣ ስራ ፈጠራ፣ አረንጓዴ ቱሪዝም እና ዘላቂ ግብርና ጋር በማስተሳሰር ሁሉን አቀፍ እይታን መፍጠር ጥሏል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለሀገሪቷ የደን ሽፋን መጨምርም ጉልህ ሚና ተጫውቷል። መርሃ ግብሩ ከመጀመሩ በፊት የነበረው የሀገሪቱ የደን ሽፋን 17 ነጥብ 2 በመቶ ሲሆን ባለፈው አመት በተጠናው ጥናት ሽፋኑ 23 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። አረንጓዴ አሻራ ከ20 ዓመት በፊት ከአራት በመቶ በታች የነበረውን የኢትዮጵያን የደን ሽፋን መልሶ እንዲያንሰራራ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የተራቆቱ አካባቢዎችን በፍጥነት ተንከባክቦ ማዳንና ምርታማ በማድረግ፣ የተራቆተ መሬትን በእጽዋት የማልበስ ስራ ላይ ጉልህ አበርክቶ አለው። አረንጓዴ አሻራ የደን ሽፋንን ማሳደግ ብቻ ሳይሆን የደኖች ብዝሃ ህይወት ዳግም እንዲያብብና የማይበገር የአየር ንብረት ለውጥ አቅም ግንባታ ላይ የድርሻውን ተወጥቷል። በአረንጓዴ አሻራ ለደን እና ለውበት ከሚተከሉት ችግኞች ባሻገር በጥምር ደን እርሻ ለፍራፍሬ እና መኖ የሚውሉ ምግቦች በብዛት በማምረት የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል። ሲጠቃለል አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ከመትከል ዘመቻ ያለፈ ነው።የአየር ንብረት ለውጥን የመከላከል፣ዘላቂ ልማትን የማረጋገጥ እና ዓለም አቀፍ ትብብርን የመፍጠር ትልቅ ለውጥ ያለው ኢኒሼቲቭ ነው። በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት የአየር ንብረት ግቦች እንዲሳኩ በፖለቲካ ቁርጠኝነት፣በማህበረሰብ ተሳትፎ፣ በፈጠራ መፍትሄዎች እና ሁሉን አቀፍ ተግባራት አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚችሉም የሚያመላክት ተምሳሌታዊ ኢኒሼቲቭ እንደሆነም ሊሰመርበት ይገባል። ዓለም በአየር ንብረት ስጋቶች ውስጥ እየኳተነች ባለችበት ወቅት የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ልምድ የተስፋ ጮራ የሆነና አረንጓዴ ትራንስፎርሜሽን አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ስኬታማ ሊሆን እንደሚችል በተግባር አሳይቷል። ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በተፈጥሮ ላይ እየሰራች ለትውልድ መጻኢ ጊዜን እየጠበቀች ነው።ይህ ተግባር ከሀገር አልፎ ድንበርን ተሻግሯል።
የመዲናዋን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Aug 26, 2026 714
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦የመዲናዋን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ የተከናወኑ ዘመናዊ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የከተማዋን ፈጣን እድገት የሚመጥን ዘመናዊ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታ እውን ለማድረግ በተከናወኑ የተቀናጁ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ጠቁመዋል። ከንቲባዋ ይህንን የተናገሩት የተገነቡ የተቀናጁ የትራንስፖርት ተርሚናሎች፣ የመኪና ማቆሚያዎችና የንግድ ማዕከላት ምረቃ መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።   ከተማ አስተዳደሩ ኅብረተሰቡ አገልግሎቶችን በፍጥነትና በጥራት የሚያገኝባቸውን በርካታ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት አብቅቷል ብለዋል። ዛሬው ለምረቃ የበቁት የታክሲና የአውቶቡስ አገልግሎት ትራንስፖርት የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ ዐረፍ ብሎ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ከተማዋ የጀመረችውን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ራዕይ እውን ለማድረግ በትራንስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታዎቹ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሀይል መሙያዎች መካተታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት ማቃለል የሚያስችሉ ሰፋፊ የመኪና ማቆሚያዎች ከነሙሉ አገልግሎታቸው ተዘጋጅተው ለሕዝብ ጥቅም ክፍት ተደርገዋል ነው ያሉት፡፡ ከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎት ከመመለስ ባሻገር የአካባቢ ጥበቃን ያማከሉ አረንጓዴ የትራንስፖርት አማራጮችን እያሰፋ እንደሚገኝም ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡ በዚህም በመዲናዋ አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለመገንባት በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ እነዚህ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች ከተማዋ ወደ አረንጓዴ ትራንስፖርት የምታደርገውን ሽግግር ያፋጥናሉ ብለዋል፡፡   በአሁኑ ወቅት የህዝብ ትራንስፖርትንና የግል ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የመኪና ማቆሚያ አቅም ከ180 ሺህ በላይ መድረሱን ከንቲባዋ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡ በእነዚህ የትራንስፖርትና የመኪና ማቆሚያ መሰረተ ልማቶች ግንባታና አገልግሎት አሰጣጥ ብቻ እስከ አሁን ከ20 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ሐብተማሪያም በበኩላቸው፤ ቢሮው ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ፍጥነትና ጥራት ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ብርቱ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡ መሰረተ ልማቶቹ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያቀላጥፉና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሀይል መሙያዎችን ያካተተ መሆኑን ጠቅሰዋል። በውስጣቸው የንግድ ሱቆች፣ ካፌና ሬስቶራንቶች፣ አሳንሰሮችና የቲኬት መቆረጫ ቢሮዎች እንደተገነባላቸውም ገልጸዋል።      
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1357
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1095
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች።   ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 1369
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል - አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና
Jul 29, 2026 1965
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርጉ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው እና የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ምክር ቤቱ አጀንዳ 2063 እና የህብረቱ መሪ ሀሳብን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የእርስ በእርስ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያሳዩት ፍላጎት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ በበጎ ፈቃደኝነት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይፋ ማድረጋቸው የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት የኢትዮጵያንና የኬንያን ፈለግ በመከተል ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራት የገቧቸውን ቃል ኪዳኖችና ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መተግበር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ለሚኒስትሮችና ሌሎች ልዑካን ላደረገችው አቀባበልም አመስግነዋል።
ሐተታዎች
የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች
Aug 28, 2026 107
አዲስ አበባ ነሀሴ 22/2018 (ኢዜአ) የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Homegrown Economic Reform) እቅዶችን በመተግበር በበርካታ ዘርፎች መሠረታዊ ለውጦችን እና ስኬቶችን ማስመዝገብ ተችሏል። በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል (አይሲቲ)፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ከማሳደግ ባሻገር የወደፊት ዘላቂ እድገት መሠረት ያኖሩ መሆኑን መናገር ይቻላል። በመሆኑም በአምስቱ ዋና ዋና ሴክተሮች የመጡ ውጤቶችና የተመዘገቡ ስኬቶችን በወፍ በረር እንቃኛለን። 1. በግብርና ዘርፍ የስንዴ ምርትና የውጭ ኤክስፖርት: የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መስፋፋት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት አስቀምጧል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ ሀገር መላክ የቻለችበትን እመርታዊ ስኬትም አሳይቶናል። የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭን በመተግበር በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና የማር ምርት እንዲሁም በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሩዝና ሻይ ልማትም ባለፉት አምስት አመታት እመርታዊ ለውጥ ተመዝግቧል። አርሶ አደሩ የመሬትና የውሃ ሀብቶችን አቃፊ በሆነ መንገድ በመጠቀም በዓመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችልበት አሰራር ተዘርግቷል። በዚህም የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሁነኛ የገቢ ምንጭ የሆነበትን እድል ፈጥሯል። ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የመቻል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል። በተለይም ደግሞ የቡና ምርታማነትና ጥራት በማደጉ ምክንያት በኤክስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማገኘት ተችሏል።   በዘርፉ በቀጣይም የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሜካናይዜሽን በማስደገፍ ምርታማነትን የማሳደግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የዝናብ ጥገኝነትን ለመቀነስ መጣር እንዲሁም የግብርና ምርቶችን ጥራት በማሻሻልና በማቀነባበር ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ዋጋ ማሳደግ ተገቢ ይሆናል። 2. የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ንቅናቄ በመፍጠር ቀደም ሲል ተቆልፈው የነበሩና በዝቅተኛ አቅምያመርቱ የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። የሀገር ውስጥ የምርት ፍላጎትን በመሸፈን ለውጭ ሀገር ምርቶች ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪም መቀነስ አስችሏል። ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የህግና የአሰራር ሁኔታዎችን በመፍጠር በርካታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል። ከተገነቡት የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮች (IAIPs) ጋር አርሶ አደሩን በማስሳሰር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲጠናከር ተደርጓል። የአምራች ዘርፉ መስፋፋት ለብዙ ሺህ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር የታቸለበት ሆኗል። በቀጣይም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በኃይል፣ በሎጂስቲክስና በግብአት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በመደገፍ ኤክስፖርትን ማሳደግ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች 80% እና ከዚያ በላይ የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት፣ በህዝብና በግል አጋርነት (PPP) አማካኝነት በትልልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ላይ የግሉን ዘርፍ አሳትፎ ማስፋፋት ትኩረት የሚደረግበት ይሆናል።   3. የዲጂታል (አይሲቲ) ዘርፍ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስልት ስኬቶችን በማስቀጠል ወደ "ዲጂታል 2030" እቅድ መሸጋገር ተችሏል። በ"መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በሌሎች ፖርታሎች አማካኝነት ህዝባዊ አገልግሎቶችን በበይነ-መረብ (Online) የመስጠት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዜጎችን መረጃ ማዕከላዊ የሚያደርግና ለፋይናንስ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች መሠረት የሆነውን የፋይዳ መታወቂያ ፕሮጀክት በላቀ መልኩ ማሳካት ተችሏል። የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኮደር ስልጠናም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ ታላቅ ሀገራዊ የስልጠና መርሃ ግብር ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።የዲጂታል አገልግሎቶች መዘርጋታቸው የፊት ለፊት ግንኙነትን በመቀነስ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የኢንቨስትመንት ምህዳሩን አሳልጧል። የቴሌኮም ዘርፍ ውድድር: የቴሌኮም ዘርፉን ክፍት ማድረግን ተከትሎ የኢንተርኔትና የኔትወርክ ተዳራሽነትንና ጥራትን በየገጠሩ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን እና የባንክ አገልግሎቶችን ይበልጥ ዘመናዊና የተቀናጁ ማድረግም አስፈላጊ ይሆናል። የሀገሪቱን የዲጂታል መሠረተ ልማት ከሳይበር ጥቃቶች የመጠበቅ አቅምን ማጠናከር። 4. የማዕድን ዘርፍ በዘርፉ ይስተዋል የነበረውን ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ በመግታት ህጋዊ አሰራርና ቁጥጥር እንዲሰፍን ተደርጓል። የህግና መመሪያዎች ማሻሻያ በማድረግ የማዕድን ዘርፉን ለውጭና ሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ማራኪ የሚያደርጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የወርቅ፣ የከሰል ድንጋይ፣ የሲሚንቶ ግብአቶችና የከበሩ ድንጋዮች ምርትን በማሳደግ ዘርፉ የሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ እንዲሆን ተሰርቷል። በተለይም የከሰል ድንጋይ ምርትን በሀገር ውስጥ አምርቶ በመተካት ለፋብሪካዎች ግብአት ማቅረብ ተችሏል። 5. የቱሪዝም ዘርፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)አነሳሽነት የተጀመሩት "ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች በመላ ሀገሪቱ በርካታ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መገንባት ተችሏል። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶች የከተሞችን ውበትና ለኑሮ ምቹነት ከመጨመራቸው ባሻገር ለከተማ ቱሪዝም ትልቅ እድል ፈጥረዋል። አዲስ አበባ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፈረንሶችን ባካሄደችበት የዲፕሎማሲና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን አጠናክራለች።   የሀገሪቱን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች የመጠበቅ፣ የማደስና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል። በድምሩ ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች ሀገሪቷን ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ማሸጋገር አስችለዋል። በመሆኑም እነዚህን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የታቀዱትን የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በተቀናጀ መልኩ መተግበር፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የግሉን ዘርፍ አሳታፊነት ማሳደግ በቀጣይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ዋነኛ የቤት ስራ ይሆናል።  
የአረንጓዴ አሻራ ስኬት፦ኢትዮጵያን የአየር ንብረት ጥበቃ ሞዴል ያደረገ ኢኒሼቲቭ
Aug 23, 2026 395
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረው በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን ከ54 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እ.አ.አ በ2027 በኢትዮጵያ በሚካሄድበት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ብዛት 65 ቢሊዮን የማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ነው።ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ምርታማነትን በማሳደግ፣ የደን ሽፋንን በመጨመር፣ የተራቆተ መሬትን ወደ ነባር ይዞታው እንዲመለስ በማድረግ እና አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። በዚህም በ2011 ዓ.ም 17.2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው ሥራ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ ችሏል።   ይህ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።በሁለተኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዋን ያስተዋወቀች ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራትም ለአህጉሪቱ ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እያከናወነች ላለው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠበት እና የሀገሪቱን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ውጤት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በመለገስ የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን በተግባር አሳይታለች።ይህም አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትንና አዎንታዊ የቀጣናዊ ትስስር ድልድይን እየገነባ ይገኛል። የድንበር ተሻጋሪ የወንዝ ተፋሰሶችን በመንከባከብ፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን ለጎረቤት ሀገራት በማዳረስ እና በጋራ ድንበሮች አካባቢ የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ እያከናወነችው ያለው ሥራ አህጉራዊ ሰላምና ትብብርን የሚያጎለብት አዲስ የዲፕሎማሲ መንገድ ከፍቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች የአህጉሪቱን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች ሆናለች።   ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነገር ግን ለጉዳቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ የአፍሪካ ሀገራት ፍትሃዊ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኙ ድምፅ በመሆን አህጉራዊ መሪነቷን አስመስክራለች። ይህም አፍሪካውያን በራሳቸው ሀገር በቀል መፍትሔዎች የአየር ንብረት ጥበቃን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ለአካባቢ ጥበቃ አርአያ የሚሆን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲሉ አድንቀውታል።   ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ከመጠቀም፣የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ እና ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር አጣጥማ የምታካሂደው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ላይ እውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።
ረብጣ ገንዘብ ከወጣባቸው ዝውውሮች እስከ አነጋጋሪ የህግ ለውጦች ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ምን ይዞ መጣ?
Aug 21, 2026 390
በሙሴ መለሰ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቀው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሰኔ እና ሐምሌ ወራት የተካሄደውን የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተከትሎ፣ ለተጫዋቾች በቂ የእረፍት ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከተለመደው አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲጀምር ተደርጓል። የመክፈቻው ጨዋታ በኢምሬትስ ስታዲየም የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን አርሰናል እና ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ በተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህ አዲስ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ከ2.14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርገዋል። ይህ የወጪ መጠን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች የአውሮፓ አራት ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣልያን ጀርመንና ፈረንሳይ) በጥምረት ካወጡት የገንዘብ መጠን በላይ ሆኗል። ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በመዘዋወር የክረምቱ ውዱ ተጫዋች መሆን ችሏል። ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አምርቷል። በተጨማሪም ሳንድሮ ቶናሊ ከኒውካስል ወደ ቶተንሃም በ100 ሚሊዮን ፓውንድ፣ እንዲሁም ብሩኖ ጉማሬሽ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል በ75 ሚሊዮን ፓውንድ መዘዋወራቸው የክረምቱን የዝውውር ገበያ ከሚጠቀሱ ዝውውሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዝውውር ወጪው ባሻገር፣ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በአዳዲስ አሰልጣኞች የታጀበ ሆኗል። በሊጉ ታሪክ ከፍተኛው በተባለ ደረጃ ዘጠኝ ክለቦች ውድድሩን በአዲስ አሰልጣኞች ይጀምራሉ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን ላይ በሊጉ ረጅም ጊዜ (ሰባት ዓመታት) የቆየው አሰልጣኝ ሆኗል። የቼልሲው ዣቢ አሎንሶ፣ የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ እና የሊቨርፑሉ አንዶኒ ኢራኦላ ከአዳዲሶቹ አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳሉ። ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ በቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዓመታቸውን ይጀምራሉ። የሊጉ የተሳታፊዎች ስብጥርን በተመለከተ፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ከሃል ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ጋር በመሆን ከታችኛው ሊግ አድገው ሊጉን ተቀላቅለዋል። በተቃራኒው ዌስትሃም ዩናይትድ፣ በርንሌይ እና ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ባለፈው የውድድር ዘመን መውረዳቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም የእንግሊዝ ክለቦች ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ባሳዩት አስደናቂ ብቃት ምክንያት፣ በዚህ የውድድር ዘመን ክብረ ወሰን የሆነ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ። አርሰናል፣ አስቶንቪላ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ እና ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ብራይተን በኮንፈረንስ ሊግ አገራቸውን ይወክላሉ። የሊጉ አስተዳደር የክለቦችን የፋይናንስ ወጪ የሚቆጣጠር አዲስ የወጪ ገደብ (Squad Cost Ratio) መመሪያን ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም መሠረት ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ እና ለዝውውር የሚያወጡት ጠቅላላ ወጪ ከገቢያቸው 85 በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ህጉን የሚጥሱ ክለቦችም የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ይገጥማቸዋል። የጨዋታ ፍጥነትን ለመጨመርና ሰዓት ማባከንን ለመግታት በርካታ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች በይፋ ስራ ላይ ይውላሉ። በእጅ ውርወራ (Throw-in) እና በመልስ ምት (Goal-kick) ላይ ሰዓት ለሚያባክኑ ተጫዋቾች ዳኛው አምስት ሴኮንድ የሚቆጥር ሲሆን፣ ጊዜ ካለፈ እጅ ውርወራው ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣል፤ የመልስ ምት ላይ ከሆነ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ያገኛል። ሌላው ሰዓት ማባከንን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ተጫዋቾች ታክመው ከወጡ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ አንድ ደቂቃ ውጭ እንዲጠብቁ የሚያስገድደው ደንብ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሚቀየሩበት ወቅት ከሜዳ ለመውጣት የ10 ሴከንድ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ይሁንና ጊዜው ካለፈ ተቀያሪው መግባት የሚችለው ጨዋታው በሚቀጥለው ጊዜ ሲቆም ብቻ ይሆናል። በዚህ የውድድር ዘመን የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔዎችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አጠራጣሪ ከሆነ ቫር ጣልቃ የመግባት ስልጣን ተሰጥቶታል፤ እንዲሁም በጨዋታ ወቅት በቫር እና በሜዳ ላይ ዳኛው መካከል የሚደረጉ የድምፅ ውይይቶች በሊጉ የጨዋታ ማዕከል በኩል ለደጋፊዎች በቀጥታ ይፋ ይደረጋሉ። በአጠቃላይ፣ የዘንድሮው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከአዳዲስ የህግ ለውጦች፣ ከከፍተኛ የዝውውር ወጪዎች እና አዳዲስ የአሰልጣኞች ሹመት ጋር ተያይዞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን ስቧል። አርሰናል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ፣ ማንቸስተር ሲቲ ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችና ክለቦች ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ አስደሳች እና አጓጊ የእግር ኳስ ጊዜን እንደሚያሳልፉ አያጠራጥርም።
ቡሄ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ምስረታ ታሪካዊ ቁርኝት
Aug 19, 2026 595
በሙሴ መለሰ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን የቡሄ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ባለበት በዚህ ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አጀማመሩንና ምስረታውን ከዚህ በዓል ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚታወስበት ነው። የክለቡ ምስረታና የቡሄ በዓል (የሆያ ሆዬ ጨዋታ) ቀጥተኛና የማይነጠል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ክለቡ በመስረታው ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት ቀርፎ የመጀመሪያውን ማሊያ ለመግዛት የበቃው በዚህ ዕለት በተሰበሰበ የሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ነበር። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መጀመሪያ ሲጠነሰስ በጆርጅ ዱካስና በአየለ አትናሽ አማካኝነት የነበረ ቢሆንም፣ ክለቡን በይፋ አደራጅቶ ለማቋቋም ግን የግድ የፋይናንስ አቅም ወይም ገንዘብ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ግን በሃገር ፍቅር ስሜት የተነሱት ዘጠኙ ወጣቶች ማለትም አየለ አትናሽ፣ ጆርጅ ዱካስ፣ ዮሐንስ ጥላሁን፣ ገብረመድህን ተፈሪ፣ ተፈራ ገብረእግዚአብሔር፣ ዓለማየሁ እጅጉ፣ መኮንን ደምሴ፣ አስፋው ያዕቆብ እና ክልቱ አያኖ ክለቡን በሚመሰርቱበት ወቅት ቤሳ ቤስቲን እንኳ ኪሳቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተሰብስበው በሰፊው ተወያዩ። በዚህ የውይይት ወቅት ነው ገንዘብ ለማግኘትና የክለቡን መመስረት እውን ለማድረግ የቡሄ ቀን እጅግ መልካምና ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የተረዱት። ዘጠኙ ወጣቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተው በታሪካዊው የቡሄ ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 1927 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ቡሄ ጨፍረው (ሆያ ሆዬ ብለው) በሚያገኙት ማናቸውም ነገር የክለቡን የመጀመሪያ ማሊያ ለመግዛት ቁርጥ የሆነ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በዚያን ጊዜ የነበረው የባህል ልማድ አሁን ካለው የተለየ በመሆኑ፣ ቡሄ ሲጨፈር የሚሰጠው ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ዳቦ ነበር። በመሆኑም ዘጠኙ ተጫዋቾችና መስራቾች ቀደም ሲል ከሚጨፍሩበትና ለምደውት ከነበረው አካባቢ ራቅ ብለው በመንቀሳቀስ በየቤቱ በር እያንኳኩ በደመቀ ሁኔታ ጨፈሩ፤ በዚህም ጥረታቸው በርካታ ቁጥር ያለው የሙልሙል ዳቦ በአንድነት ማሰባሰብ ቻሉ ታሪካዊውን ስራ ሰሩ። ይሁን እንጂ የተሰበሰበውን ይህንን በርካታ ዳቦ ወደ ጥሬ ገንዘብ ለመቀየር አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ሰራተኛ ሰፈር ለሚገኙ ወዛደሮች ለመሸጥ ዳቦውን በከረጢት ይዘው ጉዟቸውን ጀመሩ። በዚህ የጉዞ መስመር ላይ ሳሉ ግን ያልተጠበቀ ፈተና ገጠማቸው፤ በመንገድ ላይ ያገኟቸው “ዱርዬዎች” ከተሰበሰበው ዳቦ ላይ የተወሰነውን ነጠቋቸው። ወጣቶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዟቸውን በመቀጠል የተረፈውን ዳቦ ለሰራተኛ ሰፈሩ ወዛደሮች በመሸጥ ማሊያ መግዣ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው አስገቡ። ከዳቦው ሽያጭ የተገኘችው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በወቅቱ መገበያያ በትክክል ሁለት ጠገራ ብር ነበረች። የክለባችው የመጀመሪያ መለያ ቡናና ነጭ ነበር። ቡናና ነጭ መሊያን የገዙት ግን ፈልገው አልነበረም በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው በሁለት ጠገራ ብር ከፒያሳ «ግሪካዊ አውግስታስ ዱስ» ከተባለ ሱቅ በርካሽ ስላገኙት ነበር። ይህ በቡሄ ዕለት የተጀመረው ታሪካዊ የማሊያ ግዢ በኋላ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም. በይፋ ተመሠረተ። ክለቡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ማዕረግንና ቀዳሚነትን ተቀዳጀ። በ1928 ዓ.ም. በይፋ የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ ያደረገው ከ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ነበር። በዚሁ ታሪካዊ የመጀመሪያ ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበረው የ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ ሲያመራ፣ አስቀድመው ከተመረጡትና ቡድኑን ካደራጁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ባልታወቀ ምክንያት ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ድንገተኛ መቅረት ምክንያት ቡድኑ በሰው ጎደሎ ለመጫወት በተገደደበት ወሳኝ ሰዓት፣ መስራቾቹ በሜዳው አቅራቢያ መንገድ ላይ ሲጫወት ያገኙትን አንድ ታዳጊ ወጣት ተመለከቱ። ይህ ታዳጊ በወቅቱ ገና የ14 ዓመት ዕድሜ የነበረውና በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የሆነው ይድነቃቸው ተሰማ ነበር። ወጣቶቹም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ቡድኑን እንዲሞላ ድንገት ጋበዙት፤ እርሱም የቀረበለትን ጥሪ በደስታ ተቀብሎ በአጋጣሚ ወደ ሜዳ ገባ። ያለ ምንም ልምምድና ዝግጅት በድንገት የተሰለፈው ይድነቃቸው ተሰማ፣ በሜዳ ላይ ያሳየው አስደናቂ ችሎታና ቅልጥፍና ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፣ ለክለቡ የመጀመሪያውን ድል ያስገኙትን ሁለቱንም ታሪካዊ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ይኸው መንገድ ላይ ተገኝቶ በድንገት የተሰለፈው ታዳጊ ይድነቃቸው ነበር። ይህ ብቃት ገና በታዳጊነቱ በክለቡ ውስጥ ያለውን የማይተካ ቦታ ከማረጋገጡም በላይ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን የድል ጉዞ በደመቀ ሁኔታ እንዲጀመር አድርጓል። ቡሄ በዓል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያላቸው ታሪካዊ ቁርኝት የክለቡን ጥልቅ ህዝባዊና ባህላዊ መሰረት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ ፋና ወጊ የሆነው ይህ ታላቅ ክለብ፣ በታሪካዊቷ የነሐሴ 13 ቀን የቡሄ ዕለት የመስራቾቹ የ"ሆያ ሆዬ" ጨዋታና ከተሰበሰበው ሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ባገኟት ሁለት ጠገራ ብር የመጀመሪያውን ቡኒና ነጭ ማሊያ መግዛቱ፣ ክለቡ ከህዝብ ማህፀን የወጣ የህዝብ ሀብት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ከባህልና ከትውፊት ጋር የተቆራኘ አስደናቂ አጀማመር፣ ከጊዜ በኋላ በ1928 ዓ.ም. ለይፋዊ ምስረታው በር ከፋች ከመሆኑም በላይ፣ በታሪካዊው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ታላላቅ መሪዎችና ድንቅ ተሰጥኦዎች እንዲፈጠሩ መሰረት የጣለ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያ አዲሱ የቱሪዝም ከፍታ!
Aug 29, 2026 108
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ከሀገሪቷ ልዩ ፀጋዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ሀገሪቱ ያሏት ጉምቱ ታሪክ፣ ብዝሃ ባህል እና ልዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለአፍሪካ ስልጣኔ ያላትን ታላቅ ድርሻ የሚያመላክቱ ናቸው። ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንስቶ እስከ አክሱም ሀውልትና የጁገል ግንብ ድረስ ያሉት ቅርሶች የኢትዮጵያን የታሪክ ጥልቀት እና የባህል ትሩፋቶች በግልጽ ያሳያሉ። እነዚህ ታሪካዊ ሀብቶች በአሁኑ ወቅትም የውጭ ጎብኚዎች፣ ተመራማሪዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቀልብ መሳባቸውን ቀጥለዋል። ከታሪክ ሀብቶቿ ባለፈም ማራኪው የመልክዓ ምድር አቀማመጥ፣ ብቅ ያሉ የዱር እንስሳቶች እና የዜጎች እንግዳ ተቀባይነት የአኗኗር ዘይቤ ለዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። መንግስት ቱሪዝምን እንደ አንድ ዋነኛ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመውሰድ ስትራቴጂካዊ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተቀረጹት የ"ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ከማውጣት ባለፈ የገቢ መጠንን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ለውጥ እያስመዘገቡ ነው። ከዚህም መካከል በሶማሌ ክልል በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በዋቢ ሸበሌ ወንዝ ዳርቻ ተገንብቶ በቅርቡ የተመረቀው እና የ"ገበታ ለትውልድ" አካል የሆነው የሸበሌ ሪዞርት አንዱ ማሳያ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃቱ ወቅት እንደገለጹት፣ ሪዞርቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጠ የምስራቁ የሀገራችን ክፍል ትልቅ ማሳያ ሥራ ነው። ይህ ስራ በታችኛው የዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ አካባቢ ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል የፈጠረና የክልሉን የቱሪዝም ገጽታ የቀየረ ነው። በተጨማሪም በመዲናዋ አዲስ አበባ የተገነቡት የወዳጅነት አደባባይ፣ አንድነት ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚየም እና አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት አዳዲስና ተመራጭ የከተማ ቱሪዝም (Urban Tourism) መዳረሻዎች ሆነዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዋና ከተማዋ የተከናወነው ሰፊው የኮሪደር ልማት ሥራ የአዲስ አበባን መልክ በአዲስ ሁኔታ በመግለጥ፣ ከተማዋን ለሰው ልጅ ምቹ፣ ውብ እና የጎብኚዎች ዓይን ይበልጥ የሚያርፍባት የቱሪስት ማዕከል አድርጓታል። ከታሪካዊ ቅርሶች ጥበቃ አንጻርም እድሳት የተደረገላቸው ብሔራዊ ቤተ መንግስት (ኢዮቤልዩ)፣ የጎንደር የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስታት፣ የጅማ አባጅፋር ቤተመንግስት እና የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ለዘርፉ መነቃቃት የጎላ አበርክቶ እያበረከቱ ይገኛሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ በቅርቡ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እና የባልካሌ ውብ ተፈጥሮአዊ ጥንታዊ ቅርሶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ካርታ ይበልጥ አበልጽገውታል። ይህ ዓለም አቀፋዊ እውቅና የሀገሪቱን የባህል እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጥረት ማሳደጉ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ እነዚህ አካባቢዎች የሚመጡ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ የቱሪዝም ገቢን ለማሳደግ አስችሏል። በሌላ በኩል፣ የቱሪዝም ዘርፉን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ የአቪዬሽን እና የእንግዳ ተቀባይነት (Hospitality) አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ መሆናቸው ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መዳረሻ ማብዛት፣ የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ (e-Visa) አሰጣጥ መዘመኑ እና ወደ ተለያዩ የመዳረሻ አካባቢዎች የሚደረጉ የትራንስፖርት አማራጮች መቃናታቸው ጎብኚዎች ያለ ምንም እንግልት ሀገሪቱን እንዲጎበኙ መንገድ ከፍቷል። ይህም ሀገሪቱ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ለአፍሪካ እና ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ተፈላጊ ማዕከል እንድትሆን አስችሏታል። በተጨማሪም የዲጂታል ቱሪዝም ፕሮሞሽን እና የቅርሶች ጥበቃ ስራዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መደገፋቸው ለዘርፉ አዲስ ምዕራፍ አጎናጽፎታል። በማህበራዊ ሚዲያ እና በዲጂታል አማራጮች የሚሰሩ ማስተዋወቂያዎች የኢትዮጵያን ገጽታ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በአዲስ መልክ አስተዋውቀዋል። እነዚህ የተቀናጁ የልማት፣ የጥበቃ እና የማስተዋወቅ ስራዎች ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በመላው አህጉር ቀዳሚ የቱሪዝም መዳረሻ የመሆን ራዕይዋን በተግባር እያረጋገጡት ይገኛሉ። ይህንን የመንግስት ጥረት ተከትሎም ከባለሀብቶች እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የዘርፉ ተዋንያን የሚመጣው ተሳትፎና የኢንቨስትመንት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል። በአጠቃላይ እነዚህ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች፣ የታሪካዊ ቅርሶች ጥገና እና የተፈጥሮ መስህቦች ጥምረት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ ለኢኮኖሚ እድገት እና ለዘላቂ ልማት ያለውን ድርሻ ወደ ላቀ ደረጃ እያሳደጉት ይገኛል።
የኢትዮጵያውያን የወል እውነት- ሀገራዊ ምክክር
Aug 28, 2026 268
በሙሴ መለስ ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የጋራ መኖሪያ እና የብዝሃነት ውበት ደምቆ የሚታይባት ሀገር ናት ። ዛሬ ላይ ለመድረስም በርካታ ውጣ ውረዶችን፣ እና የታሪክ ምዕራፎችን ተሻግራለች። በነዚህ ምዕራፎች ውስጥም በአብሮነትና በጋራ ሃገራዊ እሳቤ ከተገነቡት የጋራ ማንነቶች ባልተናነሰ መልኩ ያጋጠሙ የታሪክ ስብራቶች የልዩነት እና ያለመግባባት መንስኤ የሚሆኑበትን አጋጣሚም አስተናግዳለች። ልዩነቶችን በጉልበት ወይም በኃይል ሳይሆን፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር እና ከነጣይ ትርክት ይልቅ ወደ ሃገራዊ መግባባትና የጋራ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣትም ሃገራዊ ምክክሩ የራሱን ቁልፍ ሚና በመወጣት በሃገራችን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑ ይታወቃል። ከአራት ዓመታት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ የህብረተሰቡን አጀንዳዎች በባለቤትነት የማሰባሰብ ሂደቱን በስኬት አከናውኗል። የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ምሁራን፣ ዳያስፖራዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በአንድ መድረክ የተሳተፉበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ለ46 ቀናት ተካሄዶ በስኬት መጠናቀቁ ተበስሯል። ይህ ጉባኤ ዜጎች ሃሳባቸውን በነፃነት የገለጹበት፣ የጋራ መግባባት ላይ የደረሱበት በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥም የጠመንጃ የበላይነትን በማስቀረት፣ የሀሳብ የበላይነትና የሰላማዊ የውይይት ባህልን ለማስፈን ምቹ ምህዳር የፈጠረ አካታች አካሄድ ነው። ከጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሐሳቦችና የተገኙት ልምዶች ወደ ተግባር እየተሸጋገሩ፣ በየደረጃው በሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ውይይቱ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍትም ነው። የጋራ ትርክት ህዝቦች በታሪካቸው፣ በአሁኑ ሁኔታቸው እና በወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ላይ ያላቸው የጋራ መረዳትና ስምምነት ሲሆን ይህም አብሮነትን ለማጎልበት ጠንካራ መሰረት ይጥላል። ለዘመናት በጦርነት፣ በኃይልና በፖለቲካ ሽኩቻ ሲንከባለሉ የቆዩ የትርክት ስብራቶችም ከጠመንጃ ይልቅ በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ክርክር ለመፍታት ስለመቻሉም ትልቅ ማሳያ ነው። በምክክሩ ላይ በመላው ሃገሪቱ አሉን የሚሏቸውን ጥያቄዎችና ቅሬታዎች በኃይል በጦር መሳሪያ ለመፍታት ነፍጥ አንግበው ሲታገሉ የነበሩ አካላት ሁሉ እንዲሳተፉ መደረጉም የሒደቱን ስኬታማነት ለዓለም ማህበረሰብ ያሳየ ነው። ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች፣የፖለቲካ አመለካከቶችና የኅብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ አራት ሺህ ተመካካሪዎች የየራሳቸውን የተናጠል ፍላጎት ብቻ ከማንጸባረቅ ተቆጥበው በተለዩ ስምንቱ አበይት አጀንዳዎች ላይ በጋራ መስማማታቸውም የወል ትርክት ግንባታን የውጤታማነት ጉዞ ስኬት በተግባር የገለጠ ነው። ይህ ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሳይሆን ለሀገር ህልውና እና ለጋራ ዕድገት ቅድሚያ የመስጠት ትልቅ የፖለቲካ ብስለትም ነው። ይህ ሂደት እያንዳንዱ ዜጋ በሀገሩ ላይ ሙሉ ባለቤትነትና ደህንነት እንዲሰማው የሚያደርግ ሲሆን የጋራ አገርና የጋራ ዕድል አለን የሚለውን እሳቤ በማጉላትም የወል ትርክትን በጽኑ መሠረት ላይ ይገነባል። ምክክሩ በጥቂት የፖለቲካ ልሂቃን (Elites) መካከል ብቻ የተደረገ ውይይት ሳይሆን እስከ ወረዳ ድረስ ያሉትን የታችኛውን የህብረተሰብ ክፍሎች፣ አርሶ አደሮችን፣ አርብቶ አደሮችንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ መሆኑም ትልቅ ትርጉም አለው። ከሕዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ የፈለቁት ምክረ ሀሳቦች ለሀገራዊ ትርክት መጠንከር ወሳኝ ሚና ከመጫወት ባለፈ ሂደቱ በህዝቡ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ያደርገዋል። ምክክሩ ያረጋገጠው ትልቁ እውነት የኢትዮጵያውያን ዕጣ ፈንታ የተሳሰረ መሆኑንና የወል ትርክት ግንባታ የሀገር ህልውና ዋስትናነቱን ነው። ልዩነቶችን ውበት፣ ውይይትን ደግሞ መሳሪያ በማድረግ የተጀመረው ይህ ጉዞ ኢትዮጵያ በቀደመ ታሪኳ የገጠሟትን የታሪክ ስብራቶች በመጠገን ወደ ዘላቂ ብልጽግና፣ ዲሞክራሲና እውነተኛ አንድነት እንድትሸጋገር ያስችላታል።
የኢትዮጵያ የከፍታ ጉዞ ማሳያ የአፍሪካውያን ኩራት - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
Aug 27, 2026 258
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከንግድ ተቋምነት ባለፈ የአፍሪካውያንን አንድነት፣ የነፃነት ታሪክና የጋራ ብልጽግና ስትራቴጂን በሰማይ ላይ የገነባ እውነተኛ የፓን አፍሪካዊነት ተምሳሌት ነው። አህጉሪቱ ገና ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ባልተላቀቀችበትና የእርስ በእርስ ትስስር በሌለበት እ.አ.አ ከ1945 ጀምሮ የአፍሪካን ሕዝቦችና መሪዎች በማገናኘት የታሪክ ህያው ምስክር ሆኖ አገልግሏል።ይህ አየር መንገድ፣ የአፍሪካ አዲስ መንፈስ የሚለውን መፈክሩን በተግባር ያረጋገጠ ብሔራዊና አህጉራዊ ኩራትም ነው። አየር መንገዱ ለአፍሪካዊያን የጋራ ዕድገት የሚሠራ መሆኑን የሚያረጋግጠው ዋነኛው ተግባሩ፣ የገንዘብና የቴክኒክ አቅም አንሷቸው የፈረሱ ወይም የተቸገሩ የሌሎች አፍሪካ ሀገራትን ብሔራዊ አየር መንገዶች በጋራ ባለቤትነት መልሶ የማቋቋምና የማጠናከር ዘላቂ ስትራቴጂው ነው። በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ትርፋማና ግዙፍ ተቋም ከመሆን ባለፈ የአህጉሪቱን የአቪዬሽን ዘርፍ በጋራ ለማሳደግ የአፍሪካ አየር መንገዶችን የማቋቋምና የመደገፍ” ስትራቴጂካዊ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል። ተቋሙ ከአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር (AFRAA) እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መንግስታት ጋር በመተባበር በአህጉሪቱ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን አስመዝግቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ እና የማኔጅመንት (የአመራር) አገልግሎት በመስጠት በርካታ አየር መንገዶችን በማቋቋምና በማጠናከር ቀዳሚውን ሚና እየተጫወተም ይገኛል። በዚህም በምዕራብ አፍሪካ ቶጎ ላይ መቀመጫውን ያደረገው አስካይ (ASKY) አየር መንገድ፣ የማላዊ አየር መንገድ፣ የዛምቢያ አየር መንገድ እና የኮንጎ አየር መንገድ የጊኒ አየር መንገድ እና ሌሎችም የአቪዬሽን ኢንቨስትመንቶች ላይ በሚያደርገው ተሳትፎ ጠንካራ ክንድነቱን አስመስክሯል። አየር መንገዱ አብዛኛውን የኩባንያዎቹን የባለቤትነት ድርሻና ትርፍ ለባለቤት ሀገራቱ መንግሥታት በመተው፣ የአመራር፣ የስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ የአፍሪካ አቪዬሽን በጋራ እንዲያድግ አድርጓል። በአቪዬሽን እሴት ሰንሰለት (Aviation Value Chain) ውስጥ ያለውን መዋቅራዊ የበላይነት በመጠቀምም ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች የተቀናጀ የቴክኒክና የስልጠና ድጋፍ ይሰጣል። ተቋሙ በእነዚህ አየር መንገዶች ውስጥ ስትራቴጂካዊ የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ፣ አብዛኛውን የኩባንያዎቹን የባለቤትነት መብትና የንግድ ትርፍ ለባለቤት ሀገራቱ መንግሥታት በመተው፣ ሙሉ የኦፕሬሽንና የማኔጅመንት ኃላፊነቱን በመውሰድ አፍሪካውያን ራሳቸውን እንዲችሉ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አየር መንገዶችን የማቋቋምና የማጠናከር ስራ ሙሉ በሙሉ በፓን አፍሪካዊነት እና በእውነተኛ አፍሪካዊ የትብብር መንፈስ ላይ የተመሠረተ ታላቅ አህጉራዊ ስራ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚከተለው ሁለገብ ስትራቴጂ ግቡ የገበያ የበላይነትን መቆጣጠር ሳይሆን፣ አቪዬሽን ለሌላቸው ወይም አየር መንገዶቻቸው ለፈረሱባቸው አፍሪካውያን ወንድም ሀገራት የቴክኒክና የአመራር አቅምን ማካፈልም ነው። የአፍሪካ አየር መንገዶችን በጋራ ባለቤትነት ሲያቋቁም የኢኮኖሚ ጥቅሙን ብቻ አስልቶ ሳይሆን፣ በአፍሪካ የነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሠረት የአህጉሪቱን የሰዎችና የዕቃዎች ዝውውርን በማቀላጠፍ የጋራ አፍሪካዊ ብልጽግናን ለማምጣት በማለም ነው። ይህ አካሄድ አህጉሪቱ ከውጭ አየር መንገዶች ጥገኝነት እንድትላቀቅ የሚያደርግ እውነተኛ የፓን አፍሪካዊነት መግለጫ ነው። የራሱን የአብራሪዎች ፣ የኢንጂነሮች እና የበረራ አስተናጋጆችን የሚያሰለጥንበትን ዘመናዊ የአቪዬሽን አካዳሚ በመገንባትም ለአቪዬሽን ዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ቁልፍ ሚናውን እየተጫወተም ይገኛል። የስልጠና እና የጥገና አቅሙ ከፍተኛ እንደመሆኑም ለተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የአቪዬሽን ባለሙያዎች ፣ እንዲሁም ከአህጉሪቱ ውጭ ላሉ አየር መንገዶች የስልጠና ፣የጥገና እና የቴክኒክ አገልግሎት በመስጠት የአህጉሪቱ የአቪዬሽን የጀርባ አጥንት መሆኑን አስመስክሯል። ይህ አህጉራዊ ትስስር ሀገራት የየራሳቸውን የአቪዬሽን ዘርፍ እንዲያጠናክሩና በንግድ፣ በቱሪዝም እና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ የአፍሪካ ህብረት የአጀንዳ 2063 ራዕይ እንዲሳካ የበኩሉን ሚና ይጫወታል። በየዓመቱ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን የሚያገኘው አየር መንገዱ እንደ ኤይር ባስ ኤ 350-1000 ያሉ ዘመኑን የዋጁ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመግዛት በአፍሪካ የመጀመሪያ በመሆን በብቸኝነት የሚያበር ሲሆን በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል እና ዘመናዊ የካርጎ (የጭነት) ተቋም በመገንባትም አገልግሎቱን አዘምኗል:: በመላው ዓለም 26 የሚሆኑ ታላላቅ አየር መንገዶች ያሉበት የስታር አሊያንስ አባል በመሆን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ ለሀገራችን የሚያስገኘው ገቢም ከዋነኛዎቹ የኢኮኖሚ አውታሮች ተርታ ቀዳሚው ያደርገዋል። ዓለምን ያስጨነቀው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበትና ታላላቅ ዓየር መንገዶች በኪሳራ ስራ ባቆሙበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለው ቁርጠኝነትና ጠንካራ አመራር አማካኝነት በካርጎ/በጭነት አገልግሎት ለአፍሪካዊያንና ሌሎች የዓለም ሃገራት መድሃኒቶችንና የህክምና መገልገያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ጭነቶችን በማጓጓዝ አለኝታነቱንም ትርፋማነቱንም አረጋግጧል። ለአፍሪካውያን የሚሰራ እውነተኛ አፍሪካዊ ተቋም መሆኑን በተግባር ያረጋገጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ዛሬም እንደ ትላንቱ የአህጉሪቱ የልማትና የአንድነት ድልድይ ሆኖ ቀጥሏል። አየር መንገዱ አሁንም የአፍሪካ አዲስ መንፈስ ሆኖ አህጉሪቱን ወደ ላቀ የብልጽግና እና የጋራ የከፍታ ምህዋር መምራቱን በጽናት ይቀጥላል።
ፕሬዝዳንቱ የገለጹት የኢትዮጵያ እውነት
Aug 26, 2026 806
ከሐምሌ 8 ጀምሮ በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል ሲካሔድ የቆየው የሃገራዊ ምክክር ጉባኤ ማጠቃለያ በስኬት ማለቁ ተበስሯል። የውጭና የሃገራት እንግዶች ፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች አባገዳዎች የኃይማኖት አባቶች ኮሚሽነሮችና ተመካካሪዎች በታደሙበት በዚህ መድረክ ላይ ፕሬዝዳንቱ ያሰሙት ድምጽ ጆሮ ገብ ነበር። የሁሉንም ትኩረት የሳበ። ለመሆኑ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ምን ብለው ነበር? በዚህ ንግግራቸውስ ምን መልዕክት አስተላለፉ? የሀገራዊ ምክክሩ በስኬት መጠናቀቅ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ታሪክ የማይታወቀውና ያልተለመደው የሆነበት ነው ። ይህ ምከክር ልዩነቶችን ከምክክር ይልቅ በኃይል ለመፍታት የመሞከር አባዜም ወደ ታሪክነት መሸጋገሪያው ነው ። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተረክ /political discourse/ ውስጥ በዘፈቀደ ሲገለጹ የሚሰሙት “ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች” ፣ “ኢትዮጵያ ልትበተን ነው” ፣ “ኢትዮጵያ ልትፈርስ” ነው የሚሉና መሰል አገላለጾች የፖለቲከኞች እንጀራ መብያ እንጂ የኢትዮጵያ መንገድ መገለጫ እንዳልሆነ ያነሳሉ። ይልቁንም ኢትዮጵያን የማይገልጹና ከፍላጎታችን፣ ከሀገራዊ መሻቶቻችን ጋር አብረው የማይሄዱት እነዚህ አገላለጾች መነሻቸው ዝንታለም በሌሎች ሀሳብና ርዕይ የሚነግዱ የሀሳብ ተከታዮች እንጂ ኢትዮጵያውያን ፈጽሞ የሚናገሩት ቃል አይደለም ይላሉ። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ጉዞ የሚሆነው መስቀለኛ ሳይሆን ቀጥ ያለ፣ ርቱዕ የእድገትና የህብረት መንገድ ብቻ መሆኑንም አስምረውበታል። ምክክር ማህበራዊ ባህላችን ውስጥ ያለንና የቆየ ሀብታችን ቢሆንም ይሄንን ነባር ባህል የፈተናዎቻችን መድህን የሀገር ግንባታችን ካስማ እንዲሆን መልክና ቅርጽ ተበጅቶለት ይፈጸም ዘንድ ቢያንስ በርሳቸው እድሜ እንደማያስታውሱ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ የዚህን ሂደት ታሪካዊ ዋጋና ሀገራዊ ፋይዳ በማሰላሰል ለሀሳቡ እውንነት ለተጉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ውጥንና ዓላማ ኢትዮጵያን ማዕከል በማድረግ ዘመንን ሊያሻግሩና ሀገርን ሊያጸኑ በሚችሉ የሀሳብ አውዶች ዙሪያ መወያየት እንደመሆኑም በመድረኩ የታየው ይሄው ነበር። በፕሬዝዳንት ታዬ የተገለጹት አምስቱ የሃገራዊ ምክክር ፋይዳዎች፦ በፕሬዝዳንት ታዬ የተገለጹት አምስቱ የሃገራዊ ምክክር ፋይዳዎችም መነሻቸው ይሄንኑ ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ። የጋራ መሻትን ማጎልበት ቀዳሚው ሲሆን ልዩነቶችን በመሻገር የጋራ እጣፈንታንና ራዕይን የሚያጸና እውቀት የተንሸራሸረበት መድረክ መፍጠሩ ነው። ሁለተኛው ደግሞ ምክክሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ስክነትና እርጋታ እንዲሸጋገሩ ያስቻለ፣ የፖለቲካ ውይይቱም ከስሜታዊነት ወጥቶ በሰከነ አስተዋይ በሆነ መንገድ እንዲመራም ያስቻለ መሆኑን ነው። ፕሬዝዳንቱ በሦስተኛነት የጠቀሱት የምክክሩ ትልቁ ፋይዳ ደግሞ የይቅርታ እና የስርየት ጎዳና እንዲፈጠር መሰረት መጣሉ ሲሆን ከደመኝነት እና ከተቃርኖ ፖለቲካ በመውጣት በይቅርታና በመተሳሰብ የጋራ ጉዞን ለመቀጠል ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ ነው። የተለመደው የፖለቲካ ማጠንጠኛ ከሆነው ከአምባጓሮና ከነፍጥ በዘላቂነት በመላቀቅ የፖለቲካ ልምምዳችን በሰላምና በመደማመጥ ላይ እንዲመሰረት ሃገራዊ ምክክሩ በር መክፈቱ በአራተኛነት ያነሱት ነጥብ ነው። ሌላኛው በአምስተኛነት የጠቀሱት የምክክሩ ማህበራዊ ፋይዳም በመከባበርና በሰመረ ቋንቋ፣ ከኃይለ ቃል በፀዳ መልኩ ለመወያየት የሚያስችል አቅም እንዳለን ያሳየንም ነው። እንደ ሀገር ፈተና ባጋጠመን ጊዜ አንዳንድ ወዳጅ ሀገራት ከናንተ የተማርነው በህብረት ቆማችሁ ቀኝ ገዢዎችን ማንበርከክ ሆኖ ሳለ ለምን የውስጥ ጉዳያችሁን ለመፍታት ወደ ነፍጥ ታደላላችሁ? የሚል የወዳጅ ጥያቄ አዘውትሮ እንደሚቀርብም አንስተዋል። መንግስት የነበረ አካል ፣ ወደ ሽፍትነት የተለወጠበትን አጋጣሚ ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ውጥንቅጥ ችግር ሲያጋጥማቸው መቼውንም ቢሆን መውጫ መንገድ አጥተው እንደማያውቁም ጠቅሰዋል። ለዚህም ህልውናችንን የሚፈታተኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙን ሀገር እየጠበቅንም፣ እየመከርንም ኢትዮጵያችንን ማፅናት መቻላችን ነው ብለዋል። የዚህ መሰረቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ስልጣኔ፣ እውቀትና እውነትን አጋምዳ የያዘች በመሆኗ ችግር ሲያጋጥመን በጋራ ቆመን ጠላትን የምንመክተው የዳበረ፣ የጥንት ሀገር ስልጣኔ ባለቤት በመሆናችን ነው ይላሉ። እንደኛ የፖለቲካ እይታ ቢሆን ሌላ ድርሳን ነበረ። አጋምዶ የያዘን ግን አንዱ ጥንታዊ ሀገር ባለቤቶች በመሆናችን ነው። ሀገር ደግሞ የጋራ ላብ፣ የጋራ ደም፣ ተከሻና ጉልበት ውጤት ናት ሲሉም ገልጸዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት የውስጥ ችግር ባጋጠመን ወቅት፣ በአለም አቀፍ መድረክ እጅግ የማይመቹ ቃላት በኢትዮጵያ ላይ ተነጣጥረው እንደነበረ አንስተው የጋራችንን ሳይሆን የተወሰኑ የክፋት መንገድን የመረጡ ኃይሎችን ብቻ በመመልከት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ትስስር ተበጥሷል፣ ወደነበረበት ለመመለስም ኢትዮጵያውያን ተስኗቸዋል በማለት ለማስተከዝ የሞከሩ እንደነበሩም አስታወሰዋል። አንዳንዶቹማ በዚህ ሀገራዊ የሀሳብ ጉባኤ ወቅት ሳይቀር የእንመካከር እንወያይ ሀሳብ ለሀሳብ እንለዋወጥ የሚለውን ጥሪ እንደ ትልቅ አጋጣሚ ከመውሰድ ይልቅ፣ ለክፋት መጠንስሻና ግጭት ማውጠንጠኛ ሊያደርጉ ሲባዝኑ መታዘባቸውን አንስተዋል። እነዚህን የመሰሉ ግለሰቦችና ቡድኖች የሺህ ዓመታት ጥብቅ ማህበራዊ ሸማችንን በቅጡ ያልተረዱ፣ የህዝባችንን የውስጥ ጥንካሬ ያላወቁ ናቸው ይሏቸዋል ፕሬዝዳንቱ። እኛ ኢትዮጵያውያን የተራሮች፣ የሸለቆዎች፣ የደጋዎች፣ የወንዞች ልጆች ነን። የኢትዮጵያ ህዝብ ወንዞቹን ለመሻገርና ለመግራት የሚያስፈልገውን ትዕግስት ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ነው። በእርግጥም አባይን የሚያቋርጥ ብቻ ሳይሆን ታሪክን የሚያሻግር ሁሉ ከነፋስና ወጀብ የበረታ ታላቅ የትዕግስት መከተሪያ ሊኖረው እንደሚገባ ያወቀ ብልህ ህዝብም ነው። ትዕግስት ስንቁ ነው። የሚሻገረውም በትዕግስተኛነትና በብርታት ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና 
Jun 17, 2026 12431
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል።   የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።   የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 22000
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15033
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20777
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 105311
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 79915
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 58263
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 55870
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 39916
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 39822
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 39297
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 37775
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 105311
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 79915
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 58263
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 55870
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 729
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።   በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው።   በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የአረቡ ዓለም ከግብፅ ምን አተረፈ?
Aug 19, 2026 667
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አካሄድ በታሪካዊ እውነታዎች እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ እየተመሠረተ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ጊዜ ያለፈባቸው የጂኦ ፖለቲካዊ የመጠላለፍ አካሄዶች ዋጋ ቢስነትና ጥቅም አልባነት በግልጽ እየታየ ይገኛል። ለብዙ አስርት ዓመታት ግብፅ የዓረብ ሊግን ለራሷ ጠባብ ፍላጎቶች እና ጂኦፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያነት በሰፊው ስትጠቀምበት ቆይታለች። ሆኖም ይህ ጥቅምና ጉዳትን ብቻ መሰረት ያደረገ ግንኙነት አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ የዓረቡ ዓለም ከግብፅ በምላሹ ያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ ምንም የሚል ነው ሲል “What Has the Arab World Gained from Egypt? Why Ethiopia Belongs in the Arab League?” ፀሐፊው እና በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት የሚተነትነው አስተያየት የሚሰጠው ጅብሪል ላሞ በኢዜአ እንግሊዘኛ ገጽ ባሳፈረው ሐተታ ላይ ፣ የግብጽ ፖሊሲዎች እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው አምባገነናዊ አስተዳደር የጋራ ጥንካሬን ከመፍጠር ይልቅ የቀጣናውን አለመረጋጋት ማባባሳቸውን ገልጿል። እነዚህ ፖሊሲዎች፣ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር አካባቢም ውጥረትን እያባባሱ እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካባቢዎች ለዓረቡ ዓለም የራቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ለዓረቡ ዓለም ደኅንነት፣ የባሕር ንግድ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ናቸው። የግብፅ ከፋፋይ ቀጣናዊ አካሄድ ከታዩባቸው ጉልህ ማሳያዎች አንዱ በኤርትራ ጉዳይ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ላይ የነበራት ታሪካዊ ጣልቃ ገብነት ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለመግታት በግብጽ ታስበው የተደራጁ ተገንጣይ ኃይሎችን እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ትደግፍ እንደነበረ ፀሐፊው አውስቷል። ከኢትዮጵያ የኤርትራ መገንጠል በምሥራቅ አፍሪካ ቀውስ የተሞላ ታሪክ ውስጥ አቢይ ክስተት ሲሆን፣ የውጭ ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች የሀገራትን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚያናጉ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዲፕሎማሲ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም ታስቦ የተዘረጋውን የኤርትራን የመገንጠል ፕሮጀክት በመደገፍና በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው። በተጨማሪም ግብጽ በደቡባዊ የቀይ ባህር ቀጣና የምታካሂደው ቀውስ የመፍጠር እንቅስቃሴ፣ ለዓለም አቀፍ የባህር ንግድና ለቀጣናው ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል። በባብ-ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ ውጥረቶችን በመቀስቀስ እና ተላላኪ ታጣቂ ቡድኖችን በማንቀሳቀስ፣ ወሳኝ የሆኑ የባህር መተላለፊያዎችን የጂኦፖለቲካዊ ግጭት መድረክ አድርጋዋለች። ይህም ለጠቅላላው የዓረብ ዓለም የኢነርጂና የምግብ አቅርቦት መሰረት የሆነውን የደህንነት መዋቅር አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ሲሉ ጅብሪል ላሞ ያብራራሉ። ጅብሪል ላሞ በጽሑፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ የግብፅ ግልጽ የራስ ወዳድነት እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን የሚፈጥሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ መቀላቀል ግን ለዓረቡ ዓለም እጅግ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ለውጥ አምጪ ዕድል ይዞ ይመጣል። በመደመር ፍልስፍና አሳታፊ ማዕቀፍ ሥር፣ ኢትዮጵያ ከማግለል ፖሊሲ ይልቅ የዓረቡን ዓለም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተሳሰር የሚያስችል የላቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት። በዚህም የአፍሪካ ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመቅረጽ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ታካፍላለች። የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ የመቀላቀል ጥረት ጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን፣ የተፈጥሮ የታሪክ ጥሪ ነው። ከ135 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጥልቅ የሥልጣኔ መሠረት ያላት ይህች የቀይ ባሕር ሀገር፣ አባልነቷ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያላት ቁርኝት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በጋራ ታሪክ፣ ባህል እና የደም ትስስር ላይ የተገነባ ነው። እንደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጥናቶች በታሪክ ደረጃ ከመካከለኛው እና ከቅርብ ምሥራቅ ታሪክ (Near Eastern Studies) ተመድቦ መጠናቱ፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከቀጣናው ጋር ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ውህደት የሚያረጋግጥ ሕያው ማሳያ ነው። የባብ-ኤል-ማንደብ የባህር ወሽመጥ በጭራሽ መሰናክል አልነበረም፤ ይልቁንም ንግድን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን በቀይ ባሕር በኩል ያገናኘ ዋንኛ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል። ከንጉሥ አብረሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች መካከል የጋራ የደም ትስስር እንደነበር የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የስነ ህይወት( ጄኔቲክስ) ጥናቶች፣ የዚህን ታሪካዊ ቁርኝት እውነተኛነት በግልጽ ያሳያሉ። በቋንቋና በባህል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው። የሀገሪቱ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ውርስ ከዓረብኛ፣ አራማይክና ዕብራይስጥ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በአረቢያ ልሳነ-ምድር መካከል ያለውን ጥልቅ የጋራ የሥልጣኔ ቁርኝት ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ተስደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ ማግኘታቸው የእስልምናን ህልውና የታደገ ታሪካዊ ክስተት ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱን ከዓረቡ ዓለም ጋር በጽኑ አስተሳስሯታል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዓረብ ሊግን በኢትዮጵያ ላይ እንደ ተቋማዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ መሣሪያ ግብጽ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ግብፅ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ዕድገት፣ የህዳሴውን ግድብም ሆነ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ሥጋት በሚያይ ጊዜ ያለፈበት ስሌት ላይ የተመሠረተ ነው። ግብፅ የራሷን የውሃ አቋም በሊጉ ላይ በመጫን፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጋለች። ጅብሪል ላሞ እንዳመለከተው፣ ከግብጽ የአግላይነት ፖሊሲ ይልቅ የዘመኑ ነባራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ትብብርን የሚጠይቁ ናቸው። በመደመር መርህ፣ ኢትዮጵያ ለዓረቡ ዓለም ለዘመናት ከቆዩ የጥላቻ መንገዶች በላቀ ሁኔታ የተሻሉ ጥቅሞችን ማቅረብ ትችላለች። እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ እና የአረንጓዴ ኃይል አቅሟ፣ ኢትዮጵያን ለቀይ ባህር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ አድርጓታል። የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የውሃ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ሥጋት በተጋረጠበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የውሃ ሀበት እና ለም መሬት ለቀጣናው ወሳኝ የግብርና-ኢንዱስትሪ አጋር ያደርጋታል። የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ብሔረተኝነት በመሻገር፣ የቀይ ባህርን ቀጣና የሥልጣኔ እውነታ መቀበል ይኖርባቸዋል። አረብ ሊግ እንደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ እና ሞሪታኒያ አባል ሀገራት መያዙ፣ ስብስቡ የተለያዩ ቀጣናዊ እውነታዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያሳያሉ። የዓረብ ሊግ ሙሉ አባልነት የኢትዮጵያን አፍሪካዊ ማንነት ሳይቀንሰው፣ አህጉሩን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የሚያገናኝ ዋነኛ ድልድይ የሚያደርጋት በመሆኑ፤ ሊጉ የኢትዮጵያን አጋርነት በመቀበል ለአዲስ አበባ ተገቢውንና ሕጋዊ ቦታዋን የሚሰጥበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ ጅብሪል ላሞ ፅሁፉን ቋጭቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም