ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ አባላት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ አባላት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 9/2018 (ኢዜአ)፦ የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን፣ ታዳጊ ሕፃናትና ቤተሰቦቻቸውን ያካተተ የዳያስፖራ አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል።
አባላቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራ አገልግሎት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የሁለተኛ ትውልድ ዳያስፖራ አባላቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የአንድ ወር ቆይታ የስፖርት ውድድር እንደሚያደርጉና የተለያዩ አካባቢዎችን እንደሚጎበኙም ተገልጿል።
ጉብኙቱ ታዳጊዎቹ የበለጠ ስለሀገራቸው እንዲገነዘቡ የሚያደርግ እንደሆነም ተመላክቷል።