የ2019 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 7 ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የ2019 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 7 ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦ የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ለአዲሱ የውድድር ዓመት ቅድመ ዝግጅታቸውን እንዲያደርጉ፤ የውድድሩን ፎርማት በተመለከተ በደርሶ መልስ ጨዋታ ማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ክለቦችን በመጥራት ውይይት እንደሚካሄድም ገልጿል፡፡