ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ዛሬ በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች
Dec 13, 2025 18
አዲስ አበባ፤ታህሳሰ 4 /2018(ኢዜአ)፦በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ዛሬ በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች። 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ውድድር እየተካሄደ ነው:: ዛሬ በተደረጉ ውድድሮችም ኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች። በ1500 ሜትር ሴቶች ሀና ረጋሳ ውድድሯን በአንደኛነት በመፈፀም ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች። በተጨማሪም በ800ሜትር ሴቶች መርጋ ሀቃ የወርቅ ሜዳልያ አሸንፏል። ኢትዮጵያ በ5ሺ ሜትር እርምጃ ውድድር በህይወት አምባው አማካኝነት የውድድሩን 6ኛ የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች። በ3000ሺ ሜትር ወንዶች ጎይቶም መኮንን የነሀስ ሜዳልያ አሸንፏል።በመካከለኛ ሪሌይ የነሐስ ማዳልያ ተመዝግቧል። እንደ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ከ2ኛው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ወጣቶች ጨዋታዎች የተገኙ አትሌቶች በውድድሩ በአስገራሚ ውጤታማነታቸው ቀጥለዋል። #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ለቀጣይ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ስኬት መሰረት የጣሉበት ነው
Dec 13, 2025 47
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሆነው አኩሪ ታሪክ የሰሩበትና ለቀጣይ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ስኬት መሰረት የጣሉበት ነው ሲሉ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራር አባላት ገለጹ፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራር አባላት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል። የጉምሩክ ኮሚሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ደረሰ እንዳሉት፤ ግድቡ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ኮሚሽኑ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን አከናውኗል። ለግድቡ የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች በተሳለጠ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን ኮሚሽኑ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራቱን ለአብነት አንስተዋል። የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አዝዘው ጫኔ በበኩላቸው፤ ለህዳሴ ግድብ ይውሉ ለነበሩ ግብዓቶች ቅድሚያ ተሰጥቶ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቁመው፤ ግድቡ ጀምሮ መጨረስ በተግባር የተረጋገጠበት መሆኑን አስታውቀዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ፤ግድቡ የኢትዮጵያን ታላቅነት ለዓለም ያስመሰከረ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን አብሳሪ መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያውያን በትብብር እውን ያደረጉት ትውልድ ተሻጋሪ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በኮሚሽኑ የባህርዳር ቅርንጫፍ ኃላፊ አለነህ ማሃሪ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያውያን ከተባበርን ምንም ነገር ማሳካት እንደሚቻል በህዳሴ ግድብ ማረጋገጥ የቻልንበት ነው ብለዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ፤ ግድቡ የሚያመነጨው ኃይል ከኢትዮጵያም አልፎ ለጎረቤት አገራትም የኃይል ፋላጎት በማሟላት ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል። ለግድቡ ስኬት የሁሉም ኢትዮጵያዊ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ፕሮጀክቱ ለቀጣይ ስራዎች ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ የግድቡ ግንባታ ከግብ እንዲደርስ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
የባሕርዳር የኮሪደር ልማት ከጣና ሐይቅ ዳርቻ ጋር ተሳስሮ መልማቱ የከተማዋ ውበት ይበልጥ እንዲገለጥ አስችሏል
Dec 13, 2025 53
ባሕርዳር /ደብረብርሀን ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ የባሕርዳር የኮሪደር ልማት ከጣና ሐይቅ ዳርቻ ጋር ተሳስሮ እንዲለማ መደረጉ የከተማዋ ውበት ይበልጥ እንዲገለጥ ማስቻሉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ፣ የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የባሕርዳርን የልማት እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል። ከጎበኟቸው ልማቶች መካከል የኮሪደር ልማት፣ የአረንጓዴ መናፈሻ፣ የመንገድ፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትና የባሕርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ይገኙበታል። ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ ደረጃቸውን ጠብቀው እየተገነቡ የሚገኙ የኮሪደርና ሌሎች የልማት ስራዎች የከተማዋን ገፅታ በእጅጉ እየቀየሩ ይገኛል። የኮሪደር ልማቱ ከጣና ኃይቅ ዳርቻ ጋር ተሳስሮ መልማቱ የከተማዋ ውበት ይበልጥ እንዲገለጥ በማድረጉ የቱሪስቶች መዳረሻ ማዕከል እንድትሆን ማድረጉን ተናግረዋል። የከተማዋ የልማት ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መደረጉ የሚበረታቱ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ በቀጣይም የመኖሪያ ቤት ልማት እንዲስፋፋ፣ የአገልግሎት አስጣጥ እንዲሻሻልና ሌሎች ሕዝቡ ያነሳቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራም ሀሳብ አንስተዋል። የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ በበኩላቸው፤ ባሕርዳር ለሌሎች ከተሞች ምሳሌ ልትሆን በሚያስችላት አስደማሚ የለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኝ ከተማ መሆኗን ገልጸዋል። ከተማዋ በተፈጥሮ የተቸራትን ፀጋ ይበልጥ በኮሪደር ልማት አጉልቶ በማውጣት የተደረገው ጥረት ከተማዋ ዋነኛ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል። እየተከናወኑ የሚገኙ የኮርደር ልማት ስራዎች ለቱሪዝም መነቃቃት እንዲፈጠርና ገፅታዋ እንዲቀየር ያስቻሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በተመሳሳይ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች በደብረብርሀን ከተማ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም የኮሪደር ልማትን ጎብኝተዋል። ከጎብኚ አመራሮች መካከል በአሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ፤ በደብረብርሀን ከተማ እየተከናወኑ ያሉት የኢንቨስትመንት ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ተናግረዋል። ኢንዱስትሪዎች ከአካባቢው አርሶ አደሮች ግብአትነት በመጠቀም የገበያ ትስስር መፍጠራቸውን አንስተዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በበኩላቸው፤ የደብረብርሃን የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎች ከተማዋ ለኢንቨሰትመንት ምቹ መሆኗን እንደሚያሳይ ተናግረዋል። በተለይ ተኪና ለውጭ የሚላክ ምርት በማምረት ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች አበረታች እንቅስቃሴ ላይ እንደሆኑ ከጉብኝቱ መረዳታቸውን ገልጸዋል። የደብረብርሀን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ፤ በአካባቢው ሰላምን ከማፅናት ጎን ለጎን የልማትና የኢንቨስትመንት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አስረድተዋል።
በፕሪሚየር ሊጉ ቼልሲ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል
Dec 13, 2025 62
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ጀምረዋል። በስታምፎርድ ብሪጅ በተካሄደው ጨዋታ ቼልሲ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸንፏል። ከጉዳት የተመለሰው ኮል ፓልመር እና ማሎ ጉስቶ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ቼልሲ በ28 ነጥብ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። ኤቨርተን በ24 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። በሌላኛው ጨዋታ ሊቨርፑል ብራይተንን 2 ለ 0 አሸንፏል። ሁጎ ኢኪቲኬ የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል በ26 ነጥብ ስድስተኛ፣ ብራይተን በ23 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የሊቨርፑል አጥቂ ሁጎ ኢኬቲኬ በ47ኛው ሴኮንድ ያስቆጠራት ጎል የውድድር ዓመቱ ፈጣን ጎል ተመዝግቧል። ምሽት 5 ሰዓት ላይ የሊጉ መሪ አርሰናል ከዎልቭስ በኤምሬትስ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል። ከዚያ አስቀድሞ በርንሌይ ከፉልሃም ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በፀጥታና ደህንነት ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ጉባዔዎችን በስኬት ለማስተናገድ አስችሏል
Dec 13, 2025 60
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦በፀጥታና ደህንነት ተቋማት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ዓለምአቀፍ እና አህጉራዊ ጉባዔዎች በስኬት እንዲስተናገዱ ማስቻሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ። የፀጥታና ደህንነት ተቋማት 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባዔ (ኮፕ- 32) በስኬት እንዲጠናቀቅ ከወዲሁ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል። "ጠንካራ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ" በሚል መሪ ሃሳብ የፀጥታና የደህንነት ተቋማት የእውቅናና ምስጋና መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው። መርኃ ግብሩ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ የተዘጋጁ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ጉባኤዎችና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከበሩ ኃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት በስኬት መጠናቀቃቸውን አስመልክቶ እንደሆነ ተገልጿል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊ ጉባዔዎችን እንዲሁም ታላላቅ ሀገራዊ በዓላትን በታላቅ ስኬትና ሰላማዊ ሁኔታ ማስተናገድ ችላለች። እነዚህ ክስተቶች የሀገሪቷን የዲፕሎማሲ አቅም፣ የደህንነት ጥበቃ ብቃት እና ህዝባዊ ትብብር ያረጋገጡ ናቸው ብለዋል። በጸጥታና ደህንነት ተቋማት መካከል የነበረው ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ ለስኬታማነቱ አይተኬ ሚና መጫወቱን አንስተዋል። በጉባዔዎቹ የእንግዶችን ደህንነት ከማረጋገጥ ባሻገር፣ በመዲናዋ የተረጋጋ ሁኔታን በመፍጠር ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች ያለምንም እንቅፋት እንዲካሄዱ መደረጉን አመልክተዋል። ለዚህም በፀጥታና ደህንነት ተቋማት የተከናወኑት የሪፎርም ሥራዎች ዓለምአቀፍና አህጉራዊ ጉባዔዎችን በስኬት ለማስተናገድ አስችሏል ነው ያሉት። ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባዔን (ኮፕ- 32) እንድታስተናግድ መመረጧ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑን ገልፀው፤ ይህ ጉባዔ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ከወዲሁ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። እንዲሁም ለዓለም እና ለአፍሪካ ኢንተር ፖል ጉባዔም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ፖለቲካ

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የአፋር ክልል ህዝብ የፖለቲካ ተሳትፎና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነቱ በተግባር እውን ሆኗል - የሰመራ ሎጊያ ነዋሪዎች
Dec 13, 2025 44
ሰመራ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የአፋር ክልል ህዝብ የፖለቲካ ተሳትፎና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነቱ በተግባር እውን መሆኑን የሰመራ ሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ሃሳብ በዛሬው ዕለት በሰመራ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄዷል። የመድረኩ ተሳታፊ የሰመራ ሎጊያ ነዋሪዎች ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የአፋር ክልል ህዝብ የፖለቲካ ተሳትፎና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነቱ በተግባር እውን ሆኗል ብለዋል። በክልሉ የመስኖ ልማትን ጨምሮ ሌሎች የግብርና ስራዎችም በስፋት እየተከናወኑ በመሆኑ ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር የሚደረገው ጥረት እየተሳካ ስለመሆኑ አንስተዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ መሐመድ አብዱልቃድር በአፋር ክልል የተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ የልማት ስራዎች ለሀገርም ጭምር የሚጠቅሙ ስለመሆናቸው ተናግረዋል። ከዚህ በፊት በነበረው የመንግስት አስተዳደር የክልሉ ህዝብ የፖለቲካ ተሳትፎና የልማት ተጠቃሚነት ፍትሃዊነት የጎደለው እንደነበር አንስተው በለውጡ እኩልነትና ፍትሃዊነት በተግባር ተረጋግጧል ብለዋል። በክልሉ ወጣቱን ማዕከል ያደረጉ የልማትና የስራ ዕድሎች እየተመቻቹ መሆኑን ያነሳው ወጣት አሊ ሰላል፤ በዚህ ረገድ ጅምሮች ቢሆኑም በቀጣይ ብዙ መሰራት እንዳለበት አንስቷል። በተለይም ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ወንጀልን ለመከላከል ወጣቶችን በጥሩ ስነ ምግባር መቅረጽና በቂ የስራ እድል መፍጠር ይገባል ብሏል። የውይይት መድረኩን የመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)፤ በሁሉም አካባቢዎች የልማት ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል የሀገርን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ መንግስት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በአፋር ክልል የተከናወኑ እና በመከመናወን ላይ ያሉ ሁሉን አቀፍ የልማት ስራዎች ለዚህ ጥሩ ማሳያ መሆናቸውን አንስተው የህዝቡ ጥረትና ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። ከግብርና በተጨማሪ በኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድንና የዲጂታል ልማት ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች ለስኬት እንዲበቁ የጋራ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል። የለውጡ መንግስት አሳታፊና ህብረ ብሔራዊ አንድነት የተረጋገጠባት ጠንካራ ሀገር የመገንባት ዓላማ ሰንቆ እየሰራ ስለመሆኑ አንስተው በዚህም እመርታዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የፍትህ ሚኒስትሯ ሐና አርዓያስላሴ በበኩላቸው እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የህዝብን ተጠቃሚነት ማእከል ያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በሁሉም አካባቢዎች ገና ያልተነካ እምቅ የመልማት አቅም ያለ መሆኑን አንስተው በተለይ ወጣቶች ያለውን ፀጋ በመጠቀም በሀገራቸው ሰርተው ለመለወጥ በትጋትና በቁርጠኝነት መስራት አለባቸው ብለዋል።
በከተማው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል
Dec 13, 2025 62
ወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የከተማው ነዋሪዎች አመለከቱ። ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት "የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች'' በሚል መሪ ሀሳብ በወላይታ ሶዶ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ዛሬ ተካሂዷል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ታደሰ ሌራ በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም ስናነሳቸው የነበሩ የልማት ጥያቄዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ምላሸ እያገኙ ነው ብለዋል። በተለይም በሰላምና ጸጥታ ዘርፍ የተሰራው ስራ የወላይታ ሶዶ ከተማን እንቅስቃሴ የተረጋጋና ሰላማዊ ማድረጉን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል በከተማው የስራ አጥነት፣ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የመንገድ ግንባታዎች፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነት፣ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት አለመዘመን ችግሮችን ለመፍታት የተጀመሩ ጥረቶች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል። ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ አልማዝ አንጁሉ እንደገለጹት በከተማው የህዝቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበሩ የመንገድ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሌሎችም ልማቶች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም የከተማውን ውበትና እድገት የሚያፋጥን የኮሪደር ልማት ስራም እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል። ይሁንና የተጀመሩ የልማት ስራዎች ላይ መጓተት እየተስተዋለ በመሆኑ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል። በከተማው የህዝብ ጥያቄን መሰረት ያደረጉ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው ያሉት ደግሞ ሌላው አስተያየት ሰጪ ላቴኖ ላቁ ናቸው። ከተማው በርካታ ስፖርተኞች የሚወጡበት በመሆኑ ለዘመናዊ ስታዲየም ግንባታም ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አመልክተዋል። የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ችግር ለመፍታት የተጀመረው ስራ ከዳር እንዲደርስ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ በበኩላቸው የወላይታ ሶዶ ከተማ በፈጣን ዕድገት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው ከተማውን ለመለወጥ የጋራ ጥረት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል። በከተማው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የአገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን እንደሚገባም አመልክተዋል። በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከፍያለዉ ተፈራ ያለንን የሰው ኃይል፣ ለም መሬት፣ ውሃ እና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶችን በመጠቀም ለስኬታማነቱ መረባረብ ይገባል ብለዋል። የሀገርን ከፍታ የሚያረጋግጡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባም አመልክተዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ተፈሪ አባተ በበኩላቸው በክልሉ የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም ወጣቶች የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ማግኘት የሚያስችሏቸው ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል። ህዝቡ በተደጋጋሚ ሲያነሳቸው የነበሩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው የስቴዲየም ግንባታ ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ እታገኝ ኃይለማርያም እንዳሉት የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ የልማት ስራዎች በጥራትና በፍጥነት እየተከናወኑ ነው። ነዋሪዎችን ጭምር በማሳተፍ ከተማውን ንጹህ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተው ህዝቡ ለልማት ስራዎች ስኬታማነት የጀመረውን ተሳትፎ እንዲያጠናክር አስገንዝበዋል።
የህዝብን የልማት ተጠቃሚነትና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል
Dec 13, 2025 73
ሀዋሳ፤ ታህሳስ 4/2018 (ኢዜአ) ፡-የህዝብን የልማት ተጠቃሚነትና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። “የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሀሳብ በሀዋሳ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል። የውይይት መድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ በብልፅግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ መለስ ዓለሙ እና ሌሎችም የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። በመድረኩ የተሳተፉ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በለውጡ ዓመታት ህብረብሔራዊ አንድነትን በማስጠበቅ ለህዝብ የልማት ተጠቃሚነት፣ ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ መንግስት ያደረገው ጥረት ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ እና ሀጂ ኡመር ሁሴን፤ በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለህዝብ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል። በሲዳማ ክልል ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማት በሁሉም መስኮች የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ጥረቶችም ትልቅ ተስፋ የተሰነቀባቸው መሆኑን ነው የተናገሩት። በከተሞች የኮሪደር ልማት ስራን ጨምሮ የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎችን በማልማትና የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የተከናወኑ ተግባራትም የሚደነቁ መሆናቸውን አንስተዋል። ሌላው የመድረኩ ተሳታፊ ጋሻው ምትኬ (ዶ/ር)፤ በለውጡ ዓመታት በፕሮጀክቶች ክንውን፣ የግብርና ልማትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ተጨባጭ ውጤት መጥቷል ብለዋል። በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ጥሩ ጅምሮች ቢኖሩም በቀጣይ ብዙ የተቀናጀ ሥራ ይጠይቃል ሲሉ አጽእኖት ሰጥተዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ፤ የሀዋሳ ከተማን እምቅ ሃብቶች በማልማትና በማስተዋወቅ የቱሪዝምና ኢንቨስትመንት መዳረሻ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡ የሐይቁን ዳርቻ አሁን ላይ ለነዋሪዎችና ለቱሪስቶች ምቹ ማሪፊያ በሚሆን መልኩ ደረጃ በደረጃ የማልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አንስተዋል። የሀዋሳ ስታዲየም ግንባታን የማጠናቀቅ፣ በሀዋሳ ጉዱማሌ እየተገነባ ያለውን የባህል ማዕከል፣ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ፣ የታቦር ተራራ ልማትና ሌሎችም ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን አረጋግጠዋል። በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለስ ዓለሙ፤ መንግስት ላከናወናቸው ስራዎች ዕውቅና በመስጠት ሊሟሉ የሚገቡ ጉዳዮች መነሳታቸው በቀጣይ ለሚሰሩ የልማት ሥራዎች አስቻይ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ብለዋል። የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፤ የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራዎች የመንግስት ትኩረቶች ሆነው ይቀጥላሉ ሲሉ ገልጸዋል። በሀዋሳ ከተማ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አንስተው ለስኬት እንዲበቁ የመንግስት ጥረት እንዳለ ሆኖ ህዝቡም ትብብርና እገዛውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የአማራ ክልልን ሰላም ለማጽናትና የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት እንደግፋለን
Dec 13, 2025 76
ባሕር ዳር ፤ ታህሳስ 4//2018 (ኢዜአ)፡- የአማራ ክልልን ሰላም ለማጽናትና የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት እንደግፋለን ሲሉ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። "የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄዷል። በመድረኩ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል። በመድረኩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች የክልሉን ሰላም ለማጽናትና የህዝቡን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የመንግስት ያላሰለሰ ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ የመንግስት ጥረት ውስጥ የጸጥታ አካላት፣ በየደረጃው ያለው አመራርና የህዝቡም ተሳትፎ ትልቅ መሆኑን አንስተው የከተማዋ ነዋሪዎችም ይህንኑ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ሙሉ ምትኩ፤ የለውጡ መንግስት በሁሉም አካባቢዎች ለትውልድ የሚተርፉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በማጠናቀቅ ጥቅም ላይ እያዋለ ይገኛል ብለዋል። በባህር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት በተጨባጭ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታቸው እየታየ ስለመሆኑም አንስተዋል። በመሆኑም የአማራ ክልልን ሰላም ለማጽናትና የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መንግስት እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ በመሆኑ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉም ተናግረዋል። ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ወርቁ አላምረው፤ የባህር ዳርን ውበት ከጣና ሃይቅ ጋር በማስተሳሰር የጎርጎራ ግዙፍ ፕሮጀክትና ሌሎችም የልማት ስራዎችን ማድነቅ የግድ ይላል ብለዋል። እንደ ሀገር በርካታ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ክንውን እና የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ለማሳካት የሚደረጉ ጥረቶችም የጋራ ተስፋ የሰነቅንባቸው ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ የዝቡጥላ ካሳ፤ በተለያዩ ችግሮች ውስጥም ሆኖ መንግስት እያከናወናቸው ያሉ የልማት ስራዎች ይበል የሚያሰኙ መሆናቸውን አንስተው በቀጣይ የኑሮ ውድነትና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ጥረት ትኩረት ይሻል ብለዋል። የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባልና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)፤ በሁሉም መስክ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማጠናከር የህዝብን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች በማዳመጥ ተግባራዊ ምላሽ ከመስጠት በተጨማሪ ለችግሮች መፍትሄ የመፈለግ ስራም የመንግስት ትኩረት መሆኑን አንስተው የመድረኩም አላማ ይሄው መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የበርካታ ሀይሎች ዐይን ማረፊያ በመሆኗ ለማደግና የሕዝቦቿን ኑሮ ለመለወጥ በምታደርገው ጥረት ታሪካዊ ጠላቶች በባንዳዎች በኩል ለማሰናከል እየጣሩ መሆኑን አንስተው የተጀመረውን የለውጥና እድገት ግስጋሴ ሊያስቆማት የሚችል ሃይል የለም ብለዋል። ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ የሚነሳው ጥያቄ ተገቢ መሆኑን አንስተው መንግስት ነባራዊ ሁኔታውን ታሳቢ በማድረግ ችግሩን ለማቃለል ጥረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል። የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በበኩላቸው፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ግብርናን በማዘመንና ምርታማነትን በማሳደግ ከውጭ ይገባ የነበረን ስንዴ በራስ አቅም በማምረት ማስቀረት ተችሏል ብለዋል። ኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶቿ እንደተመኙት ወደ ኋላ የቀረች ሳትሆን በርካታ ተስፋ ሰጪ የልማት ስራዎችን እያከናወነች የቀጠለች መሆኑን ተናግረዋል። የአማራ ክልልን ሰላም ለማጽናትና የህዝቡን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመንግስት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው፤ የከተማዋን ሰላም የማጽናትና የልማት ስራዎችን በጥራት የማከናወኑ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል። በከተማው ገበያን ለማረጋጋት አምራቹና ሸማቱ ቀጥታ የሚገናኙበት የገበያ ማዕከል እየተመቻቸ መሆኑን አንስተው፤ ምርት ያለአግባብ በሚደብቁ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም አመልክተዋል። በመድረኩ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ ነጋዴዎች፣ ወጣቶችና ሴቶችን ጨምሮ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
የተጀመሩ የልማት ስራዎች ለስኬት እንዲበቁ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ጉዳይ የጋራ አጀንዳችን ሆኖ ይቀጥላል
Dec 13, 2025 95
ደሴ ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የተጀመሩ የልማት ስራዎች ለስኬት እንዲበቁ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ጉዳይ የጋራ አጀንዳችን ሆኖ ይቀጥላል ሲሉ ሲሉ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። "የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ቱሩፋቶች" በሚል መሪ ሃሳብ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በደሴ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይተዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች ሸሕ ኢሳ ፣ወይዘሮ ብርቱካን ታደሰ እና አቶ እንድሪስ መሀመድ በሪሁን እንደገለፁት፣ መንግስት ሕብረተሰቡን በማሳተፍ ሰላምን በመጠበቅ ልማትን ለማስፋፋት የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው። በከተማው የመንገድ አውታሮችን በማስፋት እና የስራ እድል መፍጠሪያ ሼዶች በመገንባት እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች የሚበረታቱ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይ የአስፋልት መንገድ፣ መሶብ አንድ ማዕከል፣ የሕዝብ መድሃኒት ቤቶች፣ የጤና እና የትምሕርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እየተደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል። በከተማው በደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ፣ በመብራት ሃይል ማነስና መቆራረጥ፣ በመሬት መንሸራተትና በክረምት ጎርፍ መከላከል ዙሪያ የሚስተዋሉ ክፍተቶች እንዲስተካከሉ ጠይቀዋል። ቀደም ሲል በመንግስት ቃል የተገቡና የተጀመሩ የደሴ-ኮምቦልቻ አቋራጭ መንገድ፣ ወሎ ቴሪሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ፣ አዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ የባቡር መንገድ ግንባታ፣ የመኖሪያ ቤት ችግር፣ ስርዓት አልበኝነት፣የኑሮ ውድነትና ስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት። የሰላም ጥሪውን በማይቀበሉ ሽፍቶችና ተላላኪዎች ላይም መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉ አመልክተው፤ መንግስት በሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የድሆችን እንባ እያበሰ በመሆኑ እኛም ሁለተናዊ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። ሆኖም በለውጡ መንግስት ያገኘነውን ልማት ለማውደም፣ የተጀመሩን ልማቶች ለማደናቀፍ የሚታትሩ የግል ጥቅመኞችን ማስተካከል ይገባል፣ እኛም ከመንግስት ጎን ተሰልፈን ልማታችንን እናስቀጥላለን ብለዋል። ተተኪ አመራር መፍጠር፣ ወጣቱን ማብቃት፣ ለወጣቱ መዝናኛ ማመቻቸትና በከተማው ደረጃውን የጠበቀ ስታዲዮም መገንባትና የጋራ ትርክትን ማጎልበት እንደሚገባም አንስተዋል። ነዋሪዎቹ ፤ ተጀመሩ የልማት ስራዎች ለስኬት እንዲበቁ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ጉዳይ የጋራ አጀንዳችን ሆኖ መቀጠል አለበት ሲሉ ተናግረዋል። ሕብረተሰቡን በማስተባበር ሰላሙን ከማስጠበቅ ባለፈ በለውጡ መንግስት ሰፋፊ የልማት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል ያሉት ደግሞ የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ናቸው። በከተማው የተከናወኑ አስፋልት መንገድ፣ የኮሪደር ልማት፣ መሶብ አንድ ማዕከል፣ ሌማት ቱርፋትና ሌሎችም በለውጡ መንግስት የተከናወኑና ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ያስቸሉ የልማት ተግባራት ናቸው ብለዋል። ሕብረተሰቡ ላነሳቸው ጥያቄዎችም ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት ተገቢው ክትትልና ጥረት እንደሚደረግ አረጋግጠዋል። በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ደሳለኝ በበኩላቸው፣ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ሕዝቡ የድርሻውን እየተወጣ ነው ብለዋል። ግብርናውን በማዘመን፣ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ ገበያን በማረጋጋትና በሌሎችም ሪፎርሞች ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ ለሕዝብ ጥያቄ መልስ መስጠት ተችሏል ብለዋል። አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ ከሰላም ጥሪው በተጓዳኝ ሕግ የማስከበር ስራው ይቀጥላል ብለዋል። የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን የበለጠ በማጠናከር የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ደግሞ በመድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ ናቸው። በሀገሪቱ ሕግ በማስከበር ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ሂደትም ሁሉም በመደገፍ የባዳና የባንዳን ተልዕኮ ለማክሸፍ መረባረብ ይገባናል ብለዋል። የወሎን የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የመረዳዳት ባሕል ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቅሰው፤ በደሴ ከተማ የተመለከትነው ልማትና ያደረግነው ውይይት ለብልጽግና ጉዟችን ተስፋ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሽዊት ሻንካ በበኩላቸው፣ በሃገሪቱ በኢኮኖሚው፣ በማሕበራዊና በፖለቲካው ዘርፍ የተመዘገቡ ድሎች የኢትዮጵያን ማንሰራራት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። በተለይ በስንዴ ልማት፣ ኮሪደር ልማት፣ ከተማ ልማት፣ በሌማት ቱርፋት፣ በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትና በሌሎችም ዲጂታል ቴክኖሎጂ አሰራሮች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል። በውይይቱ የተነሱ ሐሳቦችንም የእቅድ አካል በማድረግ የሕብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ሲሉ አረጋግጠዋል። በመድረኩም የፌዴራልና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በሕዝብና በመንግስት ጠንካራ ቅንጅት የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል የበኩላችንን እንወጣለን
Dec 13, 2025 89
ጎንደር፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ በሕዝብና በመንግስት ጠንካራ ቅንጅት የተመዘገቡ ወጤቶችን በማስቀጠል ለጉባ ብስራት የልማት ግቦች መሳካት የሚጠበቅባቸውን ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን የጎንደር ከተማ የህዝባዊ መድረክ ተሳታፊዎች ተናገሩ። በጎንደር ከተማ የተገነቡ የቅርስ ጥበቃና የመሠረት ልማት ስራዎችን በማድነቅ የንጹህ መጠጥ ውሃና የኃይል አቅርቦት፣ የዘላቂ ሰላም ግንባታና የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉዳዮች ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የተሟላ የመሠረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አረጋግጠዋል። የጎንደር ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች "የጉባ ብስራቶች፥ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ሃሳብ ከፌዴራል፣ ክልልና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር መክረዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በመድረክ መልዕክታቸው፥ ኢትዮጵያ ከህዝቦቿ እሴትና ጸጋ የሚመነጭ የልማት አቅም እየፈጠረች ነው ብለዋል። የጥበብ ማማና እንግዳ አክባሪ የሆነችው ጎንደር ታሪኳን የሚመጥን የልማት ሥራ ላይ መሆኗን ገልጸዋል። በቀጣይም በኢትዮጵያ በሀገራዊ ለውጡ ማግስት በአራቱም ማዕዘናት በሁሉም መስክ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ለመድረኩ መነሻ በጎንደር ከተማ በአማራ ክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ የልማት ስኬቶችና የቀጣይ የህዝብና መንግስት የልማት አቅጣጫዎችን አቅርበዋል። በዚህም ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የጎንደር ህዝብ የኢትዮጵያ አንድነትና ሕብረ ብሔራዊ ትሥሥር፣ ዘላቂ ሰላምና ሙስና፣ የመልካም አስተዳደርና ጉልህ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ሲያነሳ እንደነበር አስታውሰዋል። በዚህም በጎንደር ከተማም የኢትዮጵያን የመካከለኛ ዘመን የታሪክ መነሻነት በሚመጥን መልኩ ትናንትን ከዛሬ በማስተሳሰር ዛሬን ከነገ የሚያጋምድ ልማት መሰራቱን ተናግረዋል። የክልሉና የፌዴራል መንግስት በዘላቂ ሰላም ግንባታ መርህ የጽንፈኛ ኃይሎችን የጥፋት ተልዕኮ በማክሸፍ አስተማማኝ የሕግ የበላይነት የሚያረጋግጥ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የመደመር መንግሥት ለብዝኅ ኢኮኖሚ የሰጠው ትኩረት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝምና ማዕድን መስክ በክልልና ሀገር አቀፍ ደረጃ እመርታዊ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ ገልጸዋል። በአጠቃላይ በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ ፈጠራን ከፍጥነት በማሰናሰል በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ ማኅበራዊና ዲፕሎማሲያዊ መስክ የውስጥና የውጭ አሻጥርና ሴራ ያልገደበው ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት የሚያደርጉ አኩሪ ድሎች እየተመዘገቡ ነው ብለዋል። የመድረኩ ተሳታፊ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች፥ በጎንደር ከተማ የአፄ ፋሲለደስ አብያተ መንግስት ዕድሳት፣ የትምህርት ቤት ምገባ፣ የኮሪደርና ሌሎች የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ታሪክና ዘመናዊነትን ያሰናሰሉ ናቸው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጎንደር ከተማን ታሪክ በሚመጥን መልኩ ስኬታማ የልማት ስራዎች እንዲሰሩ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። የመንግስትን የሰላም አማራጭ የተቀበሉ ታጣቂዎች የክልሉንና የሀገርን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የኃይል አቅርቦት፣ ዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የኑሮ ውድነትን የማረጋጋትና ሌሎች ምላሽ የሚሹ ጉዳዮችን ጠይቀዋል። በሀገራዊ ምክክር መፍትሔ የሚሹ የጋራ ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ለጉባ ብስራት የልማት ግቦች ስኬት በትጋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ለተነሱ ጉዳዮች በሰጡት ምላሽ፥ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በገዛ ልጆቻችን አማካኝነት የጥፋት ተልዕኳቸው ተሸካሚ እያደረጉ ነው ብለዋል። በዚህም የትህትና መገለጫ የሆነው የጎንደር ህዝብ በተሳሳተ መንገድ የቆሙ ልጆችን በመምከር የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ የማድረግ ኃላፊነት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። በቀጣይም የጎንደር ከተማንና የኢትዮጵያን የተሟላ የመሠረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፥ በመድረኩ በተነሱ አስተያየትና ጥያቄዎች ለተሰሩት ዕውቅና ቀሪ ስራዎችን በማመላከት የቀረቡ ሃሳቦች የጎንደርን ህዝብ ሚዛናዊነት ያረጋገጡ ናቸው ብለዋል። በጎንደር የአፄ ፋሲለደስ አብያተ መንግስት ዕድሳትና የኮሪደር ልማት የተሰጠው ዕውቅና ለበለጠ የልማት ትጋት ጉልበትና ብርታት እንደሚሰጥ አስረድተዋል። በቀጣይም መንግሥት በህዝብ ተሳትፎ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጎለብቱ የልማት ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፥ የከተማዋን የልማት ትንሳኤ የሚያበስሩ ስኬቶች የጎንደር ከተማ ህዝብና መንግስት የትብብር ውጤት ናቸው ብለዋል። በቀጣይም የከተማዋ ነዋሪዎች ያነሷቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
መንግስት ሁለንተናዊ ልማትን በማረጋገጥ እድገትን ለማፋጠን የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ቁርጠኛ ነን
Dec 13, 2025 91
ዲላ ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ):-መንግስት አሳታፊና ሁሉን አቀፍ ልማትን በማረጋገጥ የሀገርን እድገት ለማፋጠን የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን የዲላ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። በዲላ ከተማ "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተጠናቋል። ነዋሪዎቹ በውይይቱ ላይ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ በግብርናና ቱሪዝም ልማት፣ በማህበራዊ ዘርፍ፣ በአረንጓዴ አሻራ እንዲሁም በኮሪደርና በማዕድን ልማት ተጠቃሽ ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል። የሌማት ትሩፋቱ በጌዴኦ ዞንና በዲላ ከተማም በተጨባጭ እየታየ መሆኑን አንስተው መንግስት አሳታፊና ሁሉን አቀፍ ልማት በማረጋገጥ የሀገርን አድገት ለማፋጠን እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል። ይሁንና በሃይል አቅርቦት፣ በመንገድ መሰረተ ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በአርሶ አደር ማበረታቻና በቱሪዝም መዳረሻ ልማት ያሉ ውስንነቶች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የሀገር ሽማግሌ ገብሩ ቀቀቦ፤ መንግስት እስከ ታች ወርዶ ህዝብን በማወያየት የሀገር እድገትን በጋራ ለማረጋገጥ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል። በከተማው ህብረተሰቡን በማሳተፍ በኮሪደርና በመሰረተ ልማት ስራዎች፣ እንዲሁም በትምህርት ልማትና በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በተከናወኑ ስራዎች መሻሻሎች እንዳሉ አንስተዋል። ይሁንና ከተማዋን ከወረዳ ጋር የሚያስተሳስሩ በፌደራልና በክልል መንግስት እንዲሁም በዞኑ አስተዳደር የተጀመሩ የመንገድ መሰረተ ልማቶች መዘግየታቸውን አንስተዋል። ከዚህ በተጨማሪም የሃይል አቅርቦት ውስንነት እንዳለ የገለጹት የሀገር ሽማግሌው፣ ችግሮቹ እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል። መንግስት አሳታፊና ሁሉን አቀፍ ልማትን በማፋጠን ሀገርን ለማሳደግ የጀመራቸውን ስራዎች እንደሚደግፉ ያነሱት ደግሞ ሌላው ተሳታፊ ወይዘሮ ተረፈች ወራሳ ናቸው። በተለይ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት፣ ገቢና ንግድ ዘርፎችን በማዘመን የተቀላጠፈ አገልግሎት እያገኘን ነው፤ ይህም ትልቅ ለውጥና ውጤት በመሆኑ በሌሎችም ዘርፎች መጠናከር አለባቸው ብለዋል። መንግስት ህብረተሰቡን በማስተባበር የትምህርት ስብራትን ለመጠገን እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ምቹ የመማሪያ አካባቢ መፍጠሩን ያነሱት ደግሞ መምህር ፈለቀ አየለ ናቸው። የኑሮ ጫናን ለመቀነስ የደመወዝ ማሻሻያ መደረጉን በመልካምነት አንስተው፣ በከተማው በተማሪዎች ምገባ፣ በመጻህፍት አቅርቦትና በመምህራን ልማት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል። ሀገራዊ የልማት ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑና ለብሔራዊ ጥቅም መከበር የድርሻቸውን እንደሚወጡ ያነሱት ደግሞ አቶ ከበደ ዱሌ የተባሉ ነዋሪ ናቸው። በሥራ እድል ፈጠራ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸው ጠቅሰው በተለይ በዲላና ይርጋጨፌ ከተሞች የተገነቡ አግሮ ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡ ጠይቀዋል። የውይይት መድረኩን የመሩት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መንግስት በልማትና በመልካም አስተዳደር ላይ የተነሱ ጥያቄዎች ተቀብሎ በየደረጃው ምላሽ ለመስጠት ይሰራል ብለዋል። ሁሉንም የልማት አቅሞች በመደመር ሁለንተናዊ ልማትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን የህብረተሰቡ የላቀ ተሳትፎ ያስፈልጋል ብለዋል። በተለይም የጉባ ብስራቶችን ከግብ ለማድረስ ህብረተሰቡ በየአካባቢው ሰላሙን ከመጠበቅ ባለፈ የጀመረውን የልማት ተሳትፎ ማጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል። የባህር በር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አስኳል መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ ሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ በባዳዎችና ባንዳዎች እንዳይደናቀፍ ውስጣዊ አቅም ማጠናከር አለብን ብለዋል። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው፤ ጌዴኦ ከሰው ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ የሚኖር ሠላም ወዳድ ህዝብ መሆኑን አንስተዋል። ይህም ትልቅ ባህላዊ እሴት መሆኑንን ገልጸው በአካባቢው ያለውን የተፈጥር ሀብት በማልማት ለወጣቶች የሥራ እድልና ለሀገራዊ እድገት ለማዋል ይሰራል ብለዋል። የለውጡ መንግስት ወደስልጣን ከመጣ ጊዜ አንስቶ ያለምንም ልዩነት የልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እየመለሰ መሆኑንና ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በመድረኩ በተለያዩ የልማት ዘርፎች እንዲፈቱ ለቀረቡ ጥያቄዎች በቀጣይ ምላሽ በመስጠት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ገልጸዋል።

ማህበራዊ
በክልሉ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ሥራ ውጤት እያመጣ ነው
Dec 13, 2025 71
ወልቂጤ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ):-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰቡን ያሳተፈ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ሥራ ውጤት እያመጣ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ "ወባን ማጥፋት ከእኔ ይጀምራል" በሚል መሪ ሀሳብ በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ በአዶሼና አቶርቸ ቀበሌ የወባ ሳምንት ተከብሯል። የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ በክልሉ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተከናወነው የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ሥራ ውጤት እያመጣ ነው፡፡ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ የጤና ኤክስቴንሽን አገልግሎትን በማጠናከር የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ፣ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የአልጋ አጎበር ስርጭትና የጸረ ወባ ኬሚካል ርጭት መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ህይወት ሰለሞን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት የወባ በሽታን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመቀነስ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል። በአሁኑ ወቅትም ስራውን አጠናክሮ በማስቀጠል የወባ በሽታን ለማጥፋት ባለድርሻ አካላትን ላሳተፈ ቅንጀታዊ ሥራ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡ እንደ ህይወት (ዶ/ር) ገለጻ፤ ባለፈው ዓመት በ222 ወረዳዎች የወባ በሽታ ስርጭትን ለመከላከል የጸረ ወባ ኬሚካል ርጭት የተካሄደ ሲሆን 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን አጎበርም ለህብረተሰቡ ተሰራጭቷል። በዚህ ዓመትም ህብረተሰቡን በማሳተፍ ውሃ ያቆሩ ስፍራዎችን የማዳፈን፣ የአልጋ አጎበሮችን የማሰራጨትና የጸረ ወባ ኬሚካል ርጭት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አክለዋል። በዞኑ 11 ወረዳዎች የወባ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ትኩረት ተድርጎ እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ ናቸው። የበሽታውን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ህብረተሰቡን ያሳተፈ የመከላከልና የግንዛቤ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡ በቸሃ ወረዳ የአዶሼና አቶርቸ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ እድሉ ገብሬ፤ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በሚሰጧቸው ሙያዊ ምክር ታግዘው የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎችን የማጽዳትና ውሀ የሚያቁሩ ስፍራዎችን የማዳፈን ሥራ ማከናወናቸውን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡ በወባ መራቢያ መንገዶች ላይ ግንዛቤ ማግኘቱ አካባቢውን በጋራ ከማጽዳት ባለፈ የአልጋ አጎበርን በመጠቀም ራሱን ከወባ በሽታ ለመጠበቅ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ የጤና ሚኒስቴር ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የተከበረው የወባ ሳምንት እንደ ሃገር ለ7ኛ ጊዜ እንደ ክልል ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።
አቅመ ደካማ ወገኖችንና የሀገር ባለውለታዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Dec 13, 2025 83
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ አቅመ ደካማ ወገኖችንና የሀገር ባለውለታዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ 106 የቀበሌ ቤቶችን ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው አቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞችና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚኖሩ የሀገር ባለውለታዎች በእጣ አስረክበዋል። በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክትም ከተማ አስተዳደሩ ለዘመናት የቆዩ ተደራራቢ ችግሮችን ለማቃለልና በድሕነት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር ለሆኑ የልማት ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የዚህም ዋነኛ ዓላማ የዜጎችን አጠቃላይ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻልና ከተማዋን ማዘመን እንደሆነም ነው ያመለከቱት። በመዲናዋ በተከናወኑ የሰው ተኮር የልማት ስራዎች እስካሁን ከ40 ሺህ በላይ የከተማዋ አቅመ ደካማ ወገኖችን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በመዲናዋ የሚከናወኑ ማህበራዊ የልማት ፕሮግራሞች ለነዋሪዎች ሰው ተኮር አገልግሎት በማቅረብ ረገድ ከተማ አስተዳደሩ በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል። በመዲናዋ የዜጎችን ሕይወት የሚያሻሽሉ የመኖሪያ ቤት ልማትና ሌሎች በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። መኖሪያ ቤት የተሰጣቸው ወገኖች በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ በሰው ተኮር ሥራዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረጉ አመስግነዋል።
ገዥ ትርክትን ለማስረጽ የሥነ-ጥበብ ፈጠራ ስራዎችን መጠቀም ተገቢ ነው
Dec 13, 2025 72
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ):- የሥነ-ጥበብ ፈጠራ ስራዎችን ለገዥ ትርክት እና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ መጠቀም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻህፍት ዋና ዳይሬክተር ሰርጸ ፍሬስብሀት ገለጹ። በኪነ-ጥበብ እና ሥነ-ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ የተዘጋጀ የጥበባትና ፈጠራ ኢንዱስትሪ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው። የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻህፍት ዋና ዳይሬክተር ሰርጸ ፍሬስብሀት፤ ሥነ-ጥበብ እና ሀገረ መንግስት በሚል ጽሁፍ አቅርበዋል። በዚህም ሥነ-ጥበብ ረቂቅ ሰብዓዊ ስሜቶች በትዕምርት የሚቀረጽበት ፈጠራ መሆኑን ገልጸዋል። እንዲሁም ማህበራዊ እውነታን በምስል የሚያንጸባርቅ እና ሰዎች ስለ ዓለም ያላቸውን ውበታዊ ግንዛቤ የሚገልጽ ክዋኔ መሆኑን ተናግረዋል። ሥነ-ጥበብ ተደራሲን ወይም የአድናቂን አእምሮ የመቆጣጠር እና ለገሀዱ ዓለም ከሚሰጠው ትርጉም በላቀ በምናብ ለተፈጠረው ጉዳይ ቀልቡን እንዲሰጥ ተጽዕኖ ማሳረፍ የሚችል ጥበብ መሆኑን ጠቁመዋል። ሀገራትን አጽንቶ ያቆመ ትልቅ ቁም ነገር ገዥ ትርክት መሆኑን ጠቁመው፤ ነጠላ ትርክት ኢትዮጵያን በግጭት አዙሪት ውስጥ እንድትገባ ማድረጉን ተናግረዋል። ለኢትዮጵያ ሥነ - ጥበብ ኢትዮጵያዊነት የደም ስሩ መሆኑን ገልጸው፤ ገዥ ትርክትን ለማጽናት መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል። በመድረኩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የክልል የባህልና ስፖርት ቢሮ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን እያከናወነ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Dec 13, 2025 88
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማ አስተዳደሩ በልደታ ክፍለ ከተማ 106 የቀበሌ ቤቶችን ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው አቅመ ደካሞች፣ የአካል ጉዳተኞችና የሀገር ባለውለታዎች ለሆኑ እና እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ የከተማዋ ነዋሪዎችን በመለየት ዛሬ በእጣ ማስተላለፉን ጠቁመዋል። አስተዳደሩ ከህዝብ ጋር በተደረገ ውይይት የተሰጡ ጥቆማዎችን ጭምር ተጠቅሞ ባደረገው ማጣራት ነዋሪዎቹ መለየታቸውን አንስተዋል። በዚህም ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የተዘነጉ፣ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን አቅመ ደካማ ወገኖችን እንባ በማበስና ከነበሩበት አስከፊ ሕይወት በመታደግ ነገን በተስፋ እንዲያዩ የሚያስችል ስራ መከናወኑን አመልክተዋል። በተለይም ከአራዳ ክፍለ ከተማ ከቁርጡሚ ወንዝ ዳርቻ ተነስተው በሶስተኛ ወገን ክርክር ምክንያት ሲንገላቱ የቆዩ ነዋሪዎች ዛሬ ችግሩ ተፈቶ የመኖሪያ ቤት ስላገኙ እጅግ ደስተኞች ነን፤ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ከንቲባዋ በመልዕክታቸው።
ኢኮኖሚ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ለቀጣይ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ስኬት መሰረት የጣሉበት ነው
Dec 13, 2025 47
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሆነው አኩሪ ታሪክ የሰሩበትና ለቀጣይ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ስኬት መሰረት የጣሉበት ነው ሲሉ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራር አባላት ገለጹ፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራር አባላት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል። የጉምሩክ ኮሚሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ደረሰ እንዳሉት፤ ግድቡ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ኮሚሽኑ ከመጀመሪያው ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን አከናውኗል። ለግድቡ የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች በተሳለጠ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን ኮሚሽኑ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራቱን ለአብነት አንስተዋል። የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አዝዘው ጫኔ በበኩላቸው፤ ለህዳሴ ግድብ ይውሉ ለነበሩ ግብዓቶች ቅድሚያ ተሰጥቶ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቁመው፤ ግድቡ ጀምሮ መጨረስ በተግባር የተረጋገጠበት መሆኑን አስታውቀዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ፤ግድቡ የኢትዮጵያን ታላቅነት ለዓለም ያስመሰከረ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን አብሳሪ መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያውያን በትብብር እውን ያደረጉት ትውልድ ተሻጋሪ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በኮሚሽኑ የባህርዳር ቅርንጫፍ ኃላፊ አለነህ ማሃሪ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያውያን ከተባበርን ምንም ነገር ማሳካት እንደሚቻል በህዳሴ ግድብ ማረጋገጥ የቻልንበት ነው ብለዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ፤ ግድቡ የሚያመነጨው ኃይል ከኢትዮጵያም አልፎ ለጎረቤት አገራትም የኃይል ፋላጎት በማሟላት ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል። ለግድቡ ስኬት የሁሉም ኢትዮጵያዊ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ፕሮጀክቱ ለቀጣይ ስራዎች ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ የግድቡ ግንባታ ከግብ እንዲደርስ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
የባሕርዳር የኮሪደር ልማት ከጣና ሐይቅ ዳርቻ ጋር ተሳስሮ መልማቱ የከተማዋ ውበት ይበልጥ እንዲገለጥ አስችሏል
Dec 13, 2025 53
ባሕርዳር /ደብረብርሀን ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ የባሕርዳር የኮሪደር ልማት ከጣና ሐይቅ ዳርቻ ጋር ተሳስሮ እንዲለማ መደረጉ የከተማዋ ውበት ይበልጥ እንዲገለጥ ማስቻሉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ፣ የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የባሕርዳርን የልማት እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል። ከጎበኟቸው ልማቶች መካከል የኮሪደር ልማት፣ የአረንጓዴ መናፈሻ፣ የመንገድ፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትና የባሕርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ይገኙበታል። ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ ደረጃቸውን ጠብቀው እየተገነቡ የሚገኙ የኮሪደርና ሌሎች የልማት ስራዎች የከተማዋን ገፅታ በእጅጉ እየቀየሩ ይገኛል። የኮሪደር ልማቱ ከጣና ኃይቅ ዳርቻ ጋር ተሳስሮ መልማቱ የከተማዋ ውበት ይበልጥ እንዲገለጥ በማድረጉ የቱሪስቶች መዳረሻ ማዕከል እንድትሆን ማድረጉን ተናግረዋል። የከተማዋ የልማት ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መደረጉ የሚበረታቱ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ በቀጣይም የመኖሪያ ቤት ልማት እንዲስፋፋ፣ የአገልግሎት አስጣጥ እንዲሻሻልና ሌሎች ሕዝቡ ያነሳቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራም ሀሳብ አንስተዋል። የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ በበኩላቸው፤ ባሕርዳር ለሌሎች ከተሞች ምሳሌ ልትሆን በሚያስችላት አስደማሚ የለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኝ ከተማ መሆኗን ገልጸዋል። ከተማዋ በተፈጥሮ የተቸራትን ፀጋ ይበልጥ በኮሪደር ልማት አጉልቶ በማውጣት የተደረገው ጥረት ከተማዋ ዋነኛ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል። እየተከናወኑ የሚገኙ የኮርደር ልማት ስራዎች ለቱሪዝም መነቃቃት እንዲፈጠርና ገፅታዋ እንዲቀየር ያስቻሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በተመሳሳይ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች በደብረብርሀን ከተማ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም የኮሪደር ልማትን ጎብኝተዋል። ከጎብኚ አመራሮች መካከል በአሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ፤ በደብረብርሀን ከተማ እየተከናወኑ ያሉት የኢንቨስትመንት ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ተናግረዋል። ኢንዱስትሪዎች ከአካባቢው አርሶ አደሮች ግብአትነት በመጠቀም የገበያ ትስስር መፍጠራቸውን አንስተዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በበኩላቸው፤ የደብረብርሃን የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎች ከተማዋ ለኢንቨሰትመንት ምቹ መሆኗን እንደሚያሳይ ተናግረዋል። በተለይ ተኪና ለውጭ የሚላክ ምርት በማምረት ላይ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች አበረታች እንቅስቃሴ ላይ እንደሆኑ ከጉብኝቱ መረዳታቸውን ገልጸዋል። የደብረብርሀን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ፤ በአካባቢው ሰላምን ከማፅናት ጎን ለጎን የልማትና የኢንቨስትመንት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አስረድተዋል።
ለቱሪዝም ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ቅርሶችና የመስህብ መዳረሻዎች እንዲለሙና እንዲተዋወቁ አቅም ፈጥሯል
Dec 13, 2025 71
ዲላ ፤ ታህሳስ 4/2018 (ኢዜአ) ፡- ለቱሪዝም ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ቅርሶችና የመስህብ መዳረሻዎች እንዲለሙና እንዲተዋወቁ አቅም መፍጠሩን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ገለጸ። የጌዴኦ ባሕላዊ መልከዓ ምድር አለም አቀፍ ቅርስ ዘለቄታዊ ጥበቃና እንክብካቤ ዙሪያ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በዲላ ከተማ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሕይወት ኃይሉ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ያላትን ቅርሶች በመጠበቅ፣ የቱሪስት መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸውን ለማሳደግ እየተሰራ ነው። በተለይም የቅርሶችን ደሕንነት ለማረጋገጥ የማሕበረሰብ አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል። የጌዴኦ ባሕላዊ መልከዓ ምድርም በአግባቡ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱን ጠቁመዋል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሀገር በቀል እውቀትና ባሕላዊ እሴቶች ሃብት የበለጸገ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ወይኒቱ መልኩ ናቸው። ለዚህም የጌዴኦ ባሕላዊ መልከዓ ምድር ጥሩ ማሳያ መሆኑን አንስተው፤ ባሕላዊ እሴቶቹ ለሰላም ግንባታና ለሕዝብ ትስስር ካላቸው ፋይዳ ባለፈ የቱሪዝም ሃብቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። ባሕላዊ ቅርሶችን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ እንዲሸጋገሩ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ፤ የጌዴኦ ባሕላዊ መልከዓ ምድር ጥምር ግብርና፣ የትክል ድንጋዮች መካነ ቅርስ፣ ጥብቅ ደኖችንና የድንጋይ ላይ ጽሑፎችን ያካተተ ብዝሃ መስሕብ ያለበት መሆኑን ተናግረዋል። መልከዓ ምድሩን ከባሕላዊ ስርዓት ጋር በማስተሳሰር በዘላቂነት እንዲጠበቅ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። በተለይ የመስህብ መዳረሻዎችን በማልማት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸውን ከማሳደግ ባለፈ ጥናትን መሰረት ያደረገ ዘላቂ የመሬት አጠቃቀም ተግባራዊ መደረጉንም አንስተዋል። በመድረኩ የፌዴራል፣ የክልልና የዞን አመራሮች፣ የዘርፉ ምሁራን፣ የባሕል አባቶችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በአካባቢው እምቅ ሀብቶች ለምተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለተጀመሩ ተግባራት ስኬት የበኩላችንን እንወጣለን
Dec 13, 2025 76
አርባምንጭ ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ):-የአርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው እምቅ ሃብቶች ለምተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተጀመሩ ጥረቶችን እናግዛለን ሲሉ የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ። "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ሃሳብ በአርባምንጭ ከተማ ህዝባዊ ኮንፈረንስ ተካሂዷል። ከአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎቸ መካከል አቶ ለማ ፖሎ በሰጡት አስተያየት፤ የመደመር መንግስት በአርባምንጭ ከተማ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት በማከናወን ከተማውን ከጎርፍ አደጋ ስጋት በመታደግ ተጠቃሚ አድርጎናል ብለዋል። በተጨማሪም ትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማትን በመገንባት እንዲሁም የመንግስት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል በማድረግ የህዝቡን ማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል በአትክልትና ፍራፍሬ እምቅ አቅም ላለው አርባምንጭ ከተማና አከባቢው የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እንዲቋቋም ጠይቀዋል። ሌላው አስተያየት ሰጪ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ በለጠ በቀለ በበኩላቸው፤ መንግስት በሀገሪቱ ህዝብን የሰላምና የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል ። በአካባቢውም የተለያዩ ልማቶች መከናወናቸውን ጠቁመው የገበታ ለትውልድ ኮንፈረንስ ሪዞርት እንዲሁም የአርባምንጭ ስታዲየም ግንባታ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የለውጡ መንግስት የሴቶችን እኩልነት ከማረጋገጥ በላይ በውሳኔ ሰጪነትና በስራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚ አድርጓል ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ሰላምነሽ ሠመረ ናቸው። በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሰማርተን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት እንድንላቀቅ አስችሎናል ሲሉም አክለዋል ። ነዋሪዎቹ መንግስት በአርባምንጭ ከተማና አካባቢው እምቅ ሃብቶች ለምተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለጀመራቸው ጥረቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጥዋል ። የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባልና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሸና ማብራሪያ ሰጥተዋል ። አቶ ሽመልስ በሰጡት ምላሽ፤ በለውጡ ዓመታት በሀገሪቱ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና ሌሎች ዘርፎች አስደናቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል። ብልጽግና ፓርቲ ለዘመናት ስር ሰደው የቆዩ ችግሮችን በመፍታት ጠንካራና የበለጸገች ሀገር ለመገንባት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተከናወኑ ያሉ የሰላምና የኢንሸቲቭ ሥራዎች ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል ከጋሞና ሌሎች አጎራባች ዞኖች ጋር የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንደሚጠናከር ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ባደረገችው እንቅስቃሴ አስደናቂ እመርታዎችን ማስመዝገቧን ጠቅሰው ህዝቡ የጉባ ብስራቶችን ጨምሮ ድህነትና ኋላቀርነትን ለማስወገድ በሚከናወኑ ተግባራት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ብልጽግና በመንግስት መሪነት እና በህዝቡ ትጋት የሚረጋገጥ በመሆኑ የሀገሪቱ ትልሞች እንዲሳኩ ህዝቡ የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ አመልክዋል። በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ፤ የመደመር መንግስት በየደረጃው የህዝቡን የልማት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል። የክልሉን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የአከባቢን ፀጋ ከህዝብ ጋር በማስተሳሰር ለውጥ ለማምጣት በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ከህዝቡ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በትኩረት እንደሚሠራ አመላክተዋል። በመድረኩ የፌደራል፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የጋሞ ዞን እና የአርባምንጭ ከተማ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የማህበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በክልሉ የኮደርስ ስልጠና መርሐ ግብር በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ነው
Dec 13, 2025 82
ሚዛን አማን ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ):- የኮደርስ ስልጠና መርሃ ግብር በተጠናከረና በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ አስታወቀ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ5 ሚሊዮን ዜጎች ነፃ የኮደርስ የስልጠና እድል በመመቻቸቱ እስካሁን በርካቶች የእድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስፋው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ 138 ሺህ ዜጎችን ለማሰልጠን ዕቅድ የተያዘ ሲሆን ከእነዚህም መካከል እስካሁን 16 ሺህ 700 የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው የምሥክር ወረቀት አግኝተዋል። በተያዘው ዓመትም የስልጠናው ሂደት ተጠናክሮ የቀጠለ በመሆኑ ተጨማሪ 63 ሺህ ዜጎችን የማሰልጠን እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የስልጠናው ዓላማ በዘርፉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ጊዜ ሳያባክኑ መመዝገብና መሰልጠን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። ሥልጠናውን ወስደው ሰርተፊኬት ከተቀበሉት መካከል የሲዝ ከተማ አስተዳደር ነዋሪው ወጣት ምናሉ ግዛቸው፤ በሥልጠናው ከዘመኑ ጋር ተወዳዳሪ እንድሆን የሚያስችለኝን እውቀት አግኝቻለሁ ብሏል። በወሰዳቸው አራት ኮርሶች ከመሠረታዊ የኮምፒዩተር እውቀት ጀምሮ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ እና ፕሮግራሚንግ ላይ በቂ ክህሎት ማግኘቱን ተናግሯል። የሥልጠና አሰጣጥ ሁኔታው ቀላልና ለመያዝ ምቹ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ጊዜ ብቻ ሰጥቶ ዕድሉን መጠቀም እንዳለበት ነው የተናገረው።
ሰልጣኞች በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀታቸው ዳብሯል
Dec 13, 2025 98
አርባምንጭ ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ):- የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የቴክኖሎጂ ዕውቀታቸውን እንዳዳበረው የአርባምንጭ ከተማ ሠልጣኞች ገለጹ። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የአርባ ምንጭ ከተማ የኢትዮ-ኮደርስ ሰልጣኞች መካከል ወጣት ሊዲያ ዳሾ፤በአንድሮይድ ደቨሎፕመንት፣ ዳታ አናሊስስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስና ፕሮግራሚንግ ዘርፎች ስልጠና በመከታተል በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋትን የምስክር ወረቀት መውሰዷን ገልጻለች። ወቅቱ የሚጠይቀውን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዕውቀት መያዝ አስገዳጅ በመሆኑ ለዚሁ ራሷን ማብቃቷን አስረድታለች። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የኦን ላይን ሥራዎችን ለመወዳደርና የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ምቹ ሁኔታ ያለው መሆኑንም ተናግራለች፡፡ ሌላኛው ሠልጣኝ ወጣት ኦሳ ፋንታ በበኩሉ፤ በፕሮግራሚንግ እና ኮዲንግ ዘርፎች ስልጠና በመውሰድ የምስክር ወረቀት አግኝቷል። ስልጠናው ወቅቱን የዋጀ የቴክኖሎጂ ክህሎት በማላበስ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን እንደሚጨምርለት ተናግሯል። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መንግስት ወጪውን መሸፈኑ ዜጎችን ለማብቃትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ የታለመ ትልቅ ዕድል ነው ብሏል። የምስክር ወረቀቱ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው መሆኑ በየትኛውም ሀገር የሥራ እድልን ለማግኘት መሰረት እንደሚጥል ገልጿል። የአርባምንጭ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ ሃላፊ አቶ በሃይሉ ካፒቴን ፤ መንግስት የዜጎችን የቴክኖሎጂ ዕውቀት ለማሳደግ የጀመረው የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል። በተለይ ለወጣቶች ዕውቀታቸውን በማሳደግ ለስራ ፈጠራ በማዋል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያሳድጉ የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡ የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና እንደ ሀገር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በአርባምንጭ ከተማ 4 ሺህ 455 ዜጎች ስልጠና ወስደው የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም 4 ሺህ ዜጎችን ለማሠልጠን ግብ ተይዞ እየተሰራ ሲሆን በእስካሁኑ 2 ሺህ 829 ዜጎች መሠልጠናቸውን ገልጸዋል።
አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር አቅም ይሆናል
Dec 13, 2025 87
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር አቅም እንደሚሆን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠንካራ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማትን በመገንባት በእውቀትና ክህሎት የበቃ የሰው ኃይል ማፍራት የሚያስችል አዲስ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ መዋሉ ይታወቃል። የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ አዲሱ ስትራቴጂ የአረንጓዴ የክህሎት ልማት የስልጠና ፕሮግራሞችን የያዘ እና ለታዳሽ ኃይል ትኩረት የሰጠ ነው። ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ በሚደረገው ሽግግር ብቃትና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ስትራቴጂው ብቃት ያለው እና ለአካባቢ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን የሚተገብርና ሃብትን በቁጠባ የሚጠቀም ትውልድ ለመገንባት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡ ሥርዓተ-ትምህርቶችን በአረንጓዴ የስራ መርሆዎችና አሠራሮች በማበልጸግ ተማሪዎች ከተቋማት ሲወጡ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ዘዴዎችንና መሣሪያዎችን እንዲጠቀሙ ያስችላል ብለዋል፡፡ አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር አቅም እንደሚሆንም ነው ሚኒስትር ዴዔታው የተናገሩት፡፡ በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ መሰረት የአረንጓዴ ቴክኒክና ሙያ ልጠና ፓኬጅ ተቀርጾ ወደ ስራ መግባቱን አመላክተዋል፡፡፡ ይህ ፓኬጅ ከብክለትና ከብክነት የጸዳ የሃይል አጠቃቀም እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡ በተቋማት ውስጥ ዘመናዊ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የማሰልጠኛ መሣሪያዎችን በማስገባት ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን በዘመናዊ አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ ልምምድ በማድረግ በሥራ ዓለም ውስጥ የአረንጓዴ ልምዶችን የመተግበር ብቃት እንዲኖራቸው እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ከዓለም አቀፍ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ አዳዲስ የስራ ዕድሎችን መጠቀም እንደሚያስችልም እንዲሁ፡፡
በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ አገልግሎት እያገኘን ነው - ተገልጋዮች
Dec 13, 2025 78
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 4/2018(ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እያገኘነው ያለው አገልግሎት ፈጣን እና እንግልትን የቀረፈ ነው ሲሉ ተገልጋዮች ገለጹ። በማዕከሉ አገልግሎት አግኝተው ሲመለሱ ኢዜአ ያነጋገራቸው ተገልጋዮች እንዳሉት፤ ነባሩ አገልግሎት አሰጣጥ ከአንዱ ወደ ሌላው ተቋም መመላለሱ ብሎም ቶሎ ጉዳይን ለመፈጸም አድካሚና የቅሬታ ምንጭ ነበር። አቶ ሙፍቲ መርቀኒ ለዓመታት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተቋማት ይመላለሱ እንደነበር አውስተው፤ ያኔ አገልግሎት አሰጣጡ ረጅም ጊዜ የሚወስድና ጉዳያቸውም ውሎ ያድር እንደነበር አስታውሰዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ከጀመረ ወዲህ አራት ጊዜ ለአገልገሎት መምጣታቸውንና በርካታ ተቋማት በአንድ ቦታ በመኖራቸው ጉዳያቸውን በቀላሉ መፈጸም መቻላቸውን ተናግረዋል። የንግድ ፈቃድ ለማውጣት ወደ ማዕከሉ መምጣታቸውን ጠቁመው፤ ከጠበቁት በተሻለ ፍጥነት በመስተናገዳቸው በአገልግሎቱ መርካታቸውን አስታውቀዋል። አክሲዮን ለማሻሻል፣ የንግድ ምዝገባ ለማከናወንና የንግድ መለያ ቁጥር ለማውጣት ወደ ማዕከሉ ያቀኑት ዝነኛው መዝገቡ በበኩላቸው፤ በ20 ደቂቃ ውስጥ ቀልጣፋ አገልግሎት በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። ዛሬን ጨምሮ በማዕከሉ ሁለት ጊዜ አገልግሎት ለማግኘት በማዕከሉ መገኘታቸውን ጠቁመው፤ አገልግሎት አሰጣጡ ምቹ እና ድካምን ያስቀረ ነው ብለዋል። ጽጌ ዳኛው በበኩላቸው ማኅበር ለማጸደቅና ስያሜ ለማውጣት ወደ ማዕከሉ መምጣታቸውን ጠቅሰው፤ በአምሥት ደቂቃ ውስጥ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ማዕከሉ ከመጀመሩ በፊት ግን የሲስተም ችግር፣ የተቋማት በተለያየ ቦታ መሆንና የወረፋ መብዛትን ተከትሎ መስተጓጎል ያጋጥም እንደነበር አውስተዋል። ለተለያዩ አገልግሎቶች በተደጋጋሚ ወደ ማዕከሉ መምጣታቸውን አንስተው፤ ከበር ጀምሮ እስከ መጨረሻ አገልግሎት አሰጣጥ ድረስ ጥሩ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ መስክረዋል። ከጠበቅነው ጊዜ በተሻለ ፍጥነት ተስተናግደናል ያሉት ተገልጋዮቹ፤ ወጪና ጊዜን በመቆጠብ ብሎም ከአንድ ወደ ሌላ ተቋም በመመላለስ የሚከሰት እንግልትን በማስቀረት በአጭር ጊዜ አገልግሎት አግኝተናል ብለዋል።
ስፖርት
በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ዛሬ በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች
Dec 13, 2025 18
አዲስ አበባ፤ታህሳሰ 4 /2018(ኢዜአ)፦በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ዛሬ በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች። 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ውድድር እየተካሄደ ነው:: ዛሬ በተደረጉ ውድድሮችም ኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች። በ1500 ሜትር ሴቶች ሀና ረጋሳ ውድድሯን በአንደኛነት በመፈፀም ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች። በተጨማሪም በ800ሜትር ሴቶች መርጋ ሀቃ የወርቅ ሜዳልያ አሸንፏል። ኢትዮጵያ በ5ሺ ሜትር እርምጃ ውድድር በህይወት አምባው አማካኝነት የውድድሩን 6ኛ የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች። በ3000ሺ ሜትር ወንዶች ጎይቶም መኮንን የነሀስ ሜዳልያ አሸንፏል።በመካከለኛ ሪሌይ የነሐስ ማዳልያ ተመዝግቧል። እንደ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ከ2ኛው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ወጣቶች ጨዋታዎች የተገኙ አትሌቶች በውድድሩ በአስገራሚ ውጤታማነታቸው ቀጥለዋል። #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
በፕሪሚየር ሊጉ ቼልሲ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል
Dec 13, 2025 62
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ጀምረዋል። በስታምፎርድ ብሪጅ በተካሄደው ጨዋታ ቼልሲ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸንፏል። ከጉዳት የተመለሰው ኮል ፓልመር እና ማሎ ጉስቶ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ቼልሲ በ28 ነጥብ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። ኤቨርተን በ24 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። በሌላኛው ጨዋታ ሊቨርፑል ብራይተንን 2 ለ 0 አሸንፏል። ሁጎ ኢኪቲኬ የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል በ26 ነጥብ ስድስተኛ፣ ብራይተን በ23 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የሊቨርፑል አጥቂ ሁጎ ኢኬቲኬ በ47ኛው ሴኮንድ ያስቆጠራት ጎል የውድድር ዓመቱ ፈጣን ጎል ተመዝግቧል። ምሽት 5 ሰዓት ላይ የሊጉ መሪ አርሰናል ከዎልቭስ በኤምሬትስ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል። ከዚያ አስቀድሞ በርንሌይ ከፉልሃም ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በኢትዮጵያ ዋንጫ ኢትዮጵያ መድን እና መቻል ለሩብ ፍጻሜ አለፉ
Dec 13, 2025 54
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ተከናውነዋል። በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ቢሾፍቱ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል። አማኑኤል ኤርቦ እና ዩጋንዳዊው አለን ካይዋ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ መቻል ድሬዳዋ ከተማን በመለያ ምት አሸንፏል። ጨዋታው በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ አጠናቋል። ዮዳሄ ዳዊት ለመቻል እና ጃፋር ሙደሲር ለድሬዳዋ ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። መቻል በመለያ ምት 5 ለ 4 ማሸነፍ ችሏል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን እና መቻል ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል። ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ነጌሌ አርሲ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማን፣ ቦዲቲ ከተማ ባህር ዳር ከተማን በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አልፈዋል። የኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር ጨዋታዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ይደረጋሉ።
ጤናማ እና አምራች ዜጋን በማፍራት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ልማድ ማድረግ ይገባል
Dec 13, 2025 67
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ ጤናማ እና አምራች የሰው ሀይልን በማፍራት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ልማድ ማድረግ እንደሚገባ ተመላከተ። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ያስገነባውን የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራ አስመርቋል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ስፖርት የሰዎችን ማህበራዊ መስተጋብር በማጠናከር አብሮ የመስራት ባህልን የሚያጎለብት ነው። ኢንዱስትሪዎች የተለያዩ ምርቶችን ለማምረት የሚሰሯቸውን ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ አምራች የሰው ሀይል የጀርባ አጥንት ነው ብለዋል። በመሆኑም የሰው ሀይላቸውን በአግባቡ ለመጠቀም፣ ውጤታማ ለማድረግና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጤንነቱ የተጠበቀ አምራች ዜጋ መገንባት ግድ መሆኑን አስገንዝበዋል። በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የተገነባው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራም የኢኮኖሚ ዞኑ ሰራተኞች እና የአካባቢው ማህበረሰብ የሚገለገልበት መሆኑን አስታውቀዋል። የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ዋና ሥራ አስኪያጅ ቶሎሳ በዳዳ በበኩላቸው፤ የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎቹ ሰራተኞቹ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ጤንነታቸውን እንዲጠብቁ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል። የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራው የእግር ኳስና የቅርጫት ኳስ ጨምሮ ሌሎች የስፖርት ዓይነቶችን ማከናወን የሚያስችሉ ስፍራዎችን ማካተታቸውን ጠቅሰዋል። የአዲስ አበባ የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አለምነህ ስዩም እንደ ሀገር ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራ መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
አካባቢ ጥበቃ
ኮፕ-32 ጉባኤን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ ባለሃብቶች ሚናቸውን መወጣት አለባቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Dec 12, 2025 172
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የምታስተናግደው 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት (ኮፕ-32) ጉባኤን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ ባለሃብቶች ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ /ኮፕ-32/ በተመለከተ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በአራዳ ፓርክ ተካሂዷል። በመርሀ ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን፣ የመዲናዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ ባለብቶች እንዲሁም አልሚዎች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የኮፕ-32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ የተመረጠችው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሳል የዲፕሎማሲ አመራር የተገኘ ስኬት ነው። ይህም ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል መሆኑን ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተናገሩት። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር፣ በከተሞች ልማትና ውበት የተመዘገቡ ውጤቶች ዓለም አቀፉን ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመራጭ አድርጓታል ብለዋል። ኢትዮጵያ ብሎም አዲስ አበባ የዓለም የስበት ማዕከል መሆናቸውን በመጥቀስ፣ መዲናዋ ባለፈው ዓመት በርካታ ዓለም አቀፍ፣ አሕጉራዊ እና ሀገራዊ ሁነቶችን ማስተናገድ መቻሏን ገልጸዋል። ኮፕ-32 የዓለማችን ትልቁ የትኩረት ማዕከል መሆኑንም ነው የተናገሩት። ጉባኤው ለኢትዮጵያውያን ብዙ ዕድል ይዞ ይመጣል ያሉት ከንቲባዋ፤ ለዚህ ደግሞ መንግሥት የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ባለድርሻ አካላት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ጉባኤው ኢትዮጵያ በቀጣይ ሌሎች ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማዘጋጀት ዕድል እንድታገኝ፣ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ለማሳየትና የስራ ዕድል ለመፍጠር ወሳኝ ነው ብለዋል። በመሆኑም ባለሀብቶች አልሚዎችና አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግሥት ጋር በመተባበር ጉባኤውን በስኬት ለማካሄድ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አስረድተዋል። ጉባኤውን በብቃት በማስተናገድ ለኢትዮጵያ ለውጥ መሰረት መጣል አለብን ያሉት ከንቲባዋ፤ ዛሬ የስራ ክፍፍል በማድረግና ዝግጅት በመጀመር ግባችንን ማሳካት አለብን ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ አቅሟ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ኮንፍረንሶችን በብቃት ማስተናገድ የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ገልጸው፤ ውጤቱም በጋራ ትብብር የተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸው ስኬቶች ለቀጣይ ስራዎቻችን መስፈንጠሪያ እንደሚሆኑ በመጥቀስ፤ ኮፕ-32 እንዲሁ የተገኘ አይደለም ብለዋል። ኢትዮጵያ የኮፕ-32 ጉባኤ አዘጋጅነትን ለማግኘት ዓለም አቀፋዊ ውድድር ማድረግ ነበረባት ያሉት ኃላፊዋ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በሌሎችም አረንጓዴ ልማት ስራዎች በተገኙ ውጤቶች መመረጧን በመግለጽ። ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት አምስት ወራት ከ105 በላይ ሁነቶችን ማዘጋጀቷን ገልጸው፤ እነዚህ ስኬቶች የኮፕ 32 ጉባኤ ዝግጅትን በድል እንደምንወጣ የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ባለሃብቶችና አልሚዎች በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ኮፕ-32 ለማስተናገድ መመረጧ ትልቅ ዕድል ይዞ ይመጣል ብለዋል፡፡ በጉባኤው የሚሳተፉ አካላት የውጭ ምንዛሪ ይዘው እንደሚመጡ በማንሳት፤ በቆይታቸው የአገልግሎት ዘርፉን ገቢ ለማሳደግ ገንቢ ሚና እንደሚኖራቸው ገልጸዋል፡፡ ኮፕ-32 የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲያ ስኬት ማሳያ እንዲሁም ለገጽታ ግንባታ የጎላ አበርክቶ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ጉባኤውን በስኬት ማስተናገድ እንድትችል ከመንግስት ጎን በመሆን አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡ በብራዚል ቤለም በተካሄደው 30ኛ ጉባኤ ላይ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሄደውን 32ኛ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ (COP-32) ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ መመረጧ ይታወቃል።
ኢትዮጵያ ኮፕ-32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ መመረጧ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ነው
Dec 12, 2025 108
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት(ኮፕ-32) ጉባኤን እንድታዘጋጅ መመረጥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሳል የዲፕሎማሲ አመራር የተገኘ ስኬት መሆኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ /ኮፕ-32/ በተመለከተ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በአራዳ ፓርክ ተካሂዷል። በመርሀ ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን፣ የመዲናዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ ባለሃብቶች እንዲሁም አልሚዎች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የኮፕ-32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ የተመረጠችው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሳል የዲፕሎማሲ አመራር የተገኘ ስኬት ነው። ይህም ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል መሆኑን ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተናገሩት። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር፣ በከተሞች ልማትና ውበት የተመዘገቡ ውጤቶች ዓለም አቀፉን ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመራጭ አድርጓታል ብለዋል። ኢትዮጵያ ብሎም አዲስ አበባ የዓለም የስበት ማዕከል መሆናቸውን በመጥቀስ፣ መዲናዋ ባለፈው ዓመት በርካታ ዓለም አቀፍ፣ አሕጉራዊ እና ሀገራዊ ሁነቶችን ማስተናገድ መቻሏን ገልጸዋል። ኮፕ-32 የዓለማችን ትልቁ የትኩረት ማዕከል መሆኑንም ነው የተናገሩት። ጉባኤው ለኢትዮጵያውያን ብዙ ዕድል ይዞ ይመጣል ያሉት ከንቲባዋ፤ ለዚህ ደግሞ መንግሥት የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ባለድርሻ አካላት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ጉባኤው ኢትዮጵያ በቀጣይ ሌሎች ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማዘጋጀት ዕድል እንድታገኝ፣ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ለማሳየትና የስራ ዕድል ለመፍጠር ወሳኝ ነው ብለዋል። በመሆኑም ባለሀብቶች አልሚዎችና አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግሥት ጋር በመተባበር ጉባኤውን በስኬት ለማካሄድ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አስረድተዋል። ጉባኤውን በብቃት በማስተናገድ ለኢትዮጵያ ለውጥ መሰረት መጣል አለብን ያሉት ከንቲባዋ፤ ዛሬ የስራ ክፍፍል በማድረግና ዝግጅት በመጀመር ግባችንን ማሳካት አለብን ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ አቅሟ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ኮንፍረንሶችን በብቃት ማስተናገድ የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ገልጸው፤ ውጤቱም በጋራ ትብብር የተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸው ስኬቶች ለቀጣይ ስራዎቻችን መስፈንጠሪያ እንደሚሆኑ በመጥቀስ፤ ኮፕ-32 እንዲሁ የተገኘ አይደለም ብለዋል። ኢትዮጵያ የኮፕ-32 ጉባኤ አዘጋጅነትን ለማግኘት ዓለም አቀፋዊ ውድድር ማድረግ ነበረባት ያሉት ኃላፊዋ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በሌሎችም አረንጓዴ ልማት ስራዎች በተገኙ ውጤቶች መመረጧን በመግለጽ። ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት አምስት ወራት ከ105 በላይ ሁነቶችን ማዘጋጀቷን ገልጸው፤ እነዚህ ስኬቶች የኮፕ 32 ጉባኤ ዝግጅትን በድል እንደምንወጣ የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። በብራዚል ቤለም በተካሄደው 30ኛው ጉባኤ ላይ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሄደውን 32ኛ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ(COP-32) ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ መመረጧ ይታወቃል።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ አንጻራዊ ጥንካሬ ይኖረዋል -የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
Dec 12, 2025 89
አዲስ አበባ ታህሳስ 3/2018 (ኢዜአ)፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት በሰሜን፣ ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡብ ደጋማ የአገሪቱ ክፍሎች የሌሌቱና የማለዳው ቅዝቃዜ አንጻራዊ ጥንካሬ እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢዜአ በላከው መግለጫ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ እንደሚስተዋል አስታውቋል። በሚቀጥሉት አስር ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት በመነሳት ወደ አገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል። በአንዳንድ አካባቢዎች ቅዝቃዜው ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየሽ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ አስታውቋል። በዚህም በሰሜን ፣ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡብ ደጋማ የአገሪቱ ክፍሎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ አንጻራዊ ጥንካሬ እንደሚኖረው ገልጿል። አልፎ አልፎ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ውርጭ የማስከተል ጥንካሬ እንደሚኖረውም ጠቁሟል። በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ጥቂት ቦታዎች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ብሏል። በተጨማሪም በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ ክፍሎች አልፎ አልፎ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ገልጿል። በዚሁ ወቅት አብዛኛው ተፋሰሶች ደረቅ የአየር ሁኔታ እንደሚስተዋል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል።
በክልሉ በመጪው ክረምት ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኝ እየተዘጋጀ ነው
Dec 12, 2025 103
ባህርዳር ፤ ታህሳስ 3/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በመጪው ክረምት ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑ ተመላከተ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ እንደሀገር በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተራቁቱ መሬትን መልሶ በደን በመሸፈን እና የከርሰ ምድርና ገጸ ምድር ውሀ ሀብትን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት እያተመዘገበ ይገኛል። ባለፉት አመታት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በትኩረት በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የክልሉን የደን ሽፋን ወደ 18 በመቶ ማሳደግ እንደተቻለም የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል። በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረት ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በተለያየ ምክንያት የተራቆተውን መሬት በደን መልሶ ለማልበስና የአየር ንብረት ሚዛኑን ለማስተካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል። ተግባሩን ለማስቀጠልም በመጪው ክረምት ለሚተከሉ ችግኞች በመንግስት፣ በተቋማት፣ በማህበራትና በግል ተቋማት እንዲሁም ከ75 ሺህ በሚበልጡ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ችግኞችን ለማዘጋጀት ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል። እስካሁንም በ65 ሺህ 694 የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ፣ ሀገር በቀልና የውጭ ዝርያ ችግኞችን ለማዘጋጀት የችግኝ መደቦችን በማዘጋጀት ዘር ማፍሰስ መቻሉን ገልጸዋል። ለአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተዘጋጁ ካሉት ችግኞችም 1 ነጥብ 7 ቢሊዮኑ በተራቆቱ፣ ለደን ተከላ በሚለዩና በበጋ ወራት የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ በሚከናወንባቸው ተፋሰሶች እንደሚተከሉም አስረድተዋል። በክልሉ ባለፈው የክረምት ወቅት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተተከለው ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መካከል በመጀመሪያ ዙር በተካሄደ ቆጠራ 86 ነጥብ 3 በመቶው ፀድቆ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ታውቋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የመጀመሪያው የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል
Dec 4, 2025 507
አዲስ አበባ፤ ህዳር 25/2018(ኢዜአ)፦ የመጀመሪያው የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ተከናውኗል። በዕውቅና መርሃ ገብሩ የኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትአለም መለሰ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ዘርፍ ሚኒስትሮችና ተወካዮች እንዲሁም የሚዲያ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ሽልማቱ ለአፍሪካ ጋዜጠኝነት፣ ብሮድካስት ሚዲያ፣ ዲጂታል ሚዲያ እና ዘገባዎች እውቅና የሰጠ ነው። በአፍሪካ ሚዲያ ምህዳርን በመቅረጽ ሚናቸውን የተወጡ ጋዜጠኞች ተሸልመዋል። ምርጥ የዜና ዘገባ፣ ምርጥ ቃለ መጠይቅ፣ ምርጥ ዶክመንተሪ፣ ምርጥ ወቅታዊ ፕሮግራም፣ ምርጥ አፍሪካ ተኮር የመዝናኛ ፕሮግራምና ምርጥ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ እና ሽልማት የተሰጠባቸው ዘርፎች ናቸው። አፍሪካ ተኮር ምርጥ የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ምርጥ የወቅታዊ ጉዳይ የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ እና ምርጥ አጭር የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ ምስል የማህበራዊ ሚዲያ ሽልማት የተሰጠባቸው ዘርፎች ናቸው። ሁሉም እጩዎች 2000 ዶላር ሽልማት ያገኙ ሲሆን በእያንዳንዱ ዘርፍ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች የስድስት ሺህ ዶላር ሽልማት አግኝተዋል። የምርጦች ምርጥ የይዘት ፈጣሪዎች አሸናፊም "The Golden Alkebulan" የተሰኘ ልዩ በወርቅ የተለበጠ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል። በሽልማቱ ላይ ከ40 ሀገራት በላይ የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ከ800 በላይ ስራዎችን ማቅረባቸውን ተገልጿል። የአፍሪካ ሕብረት ብሮድካስቲንግ፣ የፓትሪስ ሉሙምባ ፋውንዴሽን፣ የክዋሜ ንክሩማህ ፋውንዴሽን፣ የምዋሊሙ ኒዬሬሬ ፋውንዴሽን፣ የኬኔት ካውንዳ ሌጋሲ ፋውንዴሽን፣ የሲሱሉ ፋውንዴሽን ለማኅበራዊ ፍትህ፣ የፒኤልኦ ሉሙምባ ፋውንዴሽንና የሩስያው አር ቲ ሚዲያ የሽልማቱ አጋር ናቸው።
ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው - የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች
Dec 1, 2025 448
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው ሲሉየምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ገለጹ። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካን ትርክት በመቀየር ትልቅ ሚና የሚወጣ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንም ተናግረዋል። ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ መካሄዱ ይታወቃል። የሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ዛሬ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል። በሴት ጋዜጠኞች ዘርፍ አሸናፊ ከሆኑት መካከል ዩጋንዳዊቷ ጋዜጠኛ አይባሬ ሲንደሬላ ኢትዮጵያ በዜጎቿ አስተዋጽኦ ህዳሴ ግድብን ለመገንባት ያሳየችውን ቁርጠኝነት አድንቃለች። በበርካታ ሀገራት ዜጎች ከሚከፍሉት ታክስ ተጨባጭ ውጤቶችን እምብዛም ሲያዩ አይስተዋልም ያለችው ጋዜጠኛዋ ኢትዮጵያ በግልጽነትና በጠንካራ ራዕይ የህዝብን ሀብቶች አሻጋሪ ብሄራዊ ፕሮጀክት መቀየሯን ተናግራለች። የአፍሪካ መሪዎች ከሕዳሴ ግድብ ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ሊወስዱ ይገባል ብላለች። የኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አዘጋጅ አሻ ሃሚሲ አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግሮች ያለ ምንም ጣልቃ ገብነት መፍታት እንዳለባቸው ገልጻለች። ሕዳሴ ግድብ ዜጎች ለሀገራቸው መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ የሚያሳይ ፕሮጀክት ነው ያለችው አሻ ይህም በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለ መተማመንና ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ ላይ መስራት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላከት ነው ብላለች። ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ እንደሆነም ተናግራለች። በኢጋድ ሚዲያ ሽልማት በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ካሸነፉት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው ደቡብ ሱዳናዊው የፊልም ባለሙያ እና ተራኪ ጋብርኤል ጋትሉዋክ ዋል ኬት በበኩሉ ህዳሴ ግድብ አፍሪካ ያላትን አቅም በተግባር ያሳየ ነው ሲል ተናግሯል። ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የመሰለ ግዙፍ ፕሮጀክት ካሳካች ሌሎች ሀገራትም ይህን ፈለግ ተከትለው ትላልቅ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ ይችላሉ ብሏል። አፍሪካውያን ሀገራቸውን በራሳቸው መገንባት እንደሚችሉ ማመን አለባቸው ያለው ኬት የራሳቸውን ዕጣ ፈንታ ሌሎች እንዲወስኑላቸው መፍቀድ የለባቸውም ሲልም ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ለሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን እና በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የከፈሉትን መስዋዕትነት አንስተዋል። ሕዳሴ ግድ የአፍሪካ የስኬት ተምሳሌት ፕሮጀክት እንደሆነ ገልጸው ከግድቡ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። ይህም ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክርና የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ራዕይ የሆነውን የበለጸገች እና የተሳሰረች አፍሪካን የመፍጠር ራዕይን እንደሚደግፍም ተናግረዋል። ግድቡ የአፍሪካን ትርክት የመቀየር ትልቅ ኃይል ያለው ፕሮጀክት ነው ብለዋል አምባሳደሩ።
የአፍሪካን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል
Nov 21, 2025 798
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ገለጸ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዘጋጅነት የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ የልማት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችና የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦች ላይ የዌብናር ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት ወሳኔ ሰጪዎች፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የገንዘብ ተቋማት፣ ተመራማሪዎችና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የልማት ዕቅድ ክፍል ኃላፊ ኦዬባንኬ አበጂሪን፤ የምንፈልጋትን አፍሪካ ዕውን ለማድረግ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት የ2030 ዘላቂ የልማት አጀንዳና የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 አፈፃጸም ሂደትን የሚከታተል የሪፖርት ሥርዓት መኖሩንም ገልጸዋል። እ.ኤ.አ በ2017 የተጀመረው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርት ክትትል ሥርዓትም የአህጉሪቷን ዘላቂና ቁልፍ የልማት ማዕቀፎች አፈፃጸም የሚገመገምበትን መድረክ በማመቻቸት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። እ.ኤ.አ የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርት መድረክም የአህጉሪቷ ልማት በሳይንስና ማስረጃ የተመሰረቱ የመፍትሔ አፈፃጸሞችን ያመላከተ መሆኑን አስገንዝበዋል። ሪፖርቱም የአፍሪካ ዕድገት በጤና፣ በሥርዓተ ፆታ እኩልነት፣ በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በውቅያኖስ ጥበቃና ዓለም አቀፍ ሽርክና ጋር በአፍሪካ ሀገራት እ.ኤ.አ የ2030 ዘላቂ የልማት ግብና የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ወሳኝ አካል መሆኑን አስረድተዋል። የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ የትብብር ሥርዓትን በማጠናከር በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርትም ወሳኝ የአፈፃጸም ግኝቶችን በማረም የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦችን በሚገባ ለመተግበር አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል። በመድረኩም የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት ግቦችና አጀንዳዎች የአፈፃጸም ስኬት ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመቅረጽ የሚችል ተግባቦት መፈጠሩን አስገንዝበዋል። በቀጣይም የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካትም አዲስ ዓለም የፋይናንስ ድጋፍ ማዕቀፍ አስፈላጊነትን ታሳቢ በማድረግ በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። መድረኩም ብሔራዊና ቀጣናዊ የልማት ስኬት አፈፃጸም የአሰራር ስርዓቶችን በመፈተሽ ዕድሎችን በማስፋት የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት አጀንዳዎ ማሳካት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ የአጋርነት አድማሳቸውን ለማስፋት እንደሚሰሩ ገለጹ
Nov 20, 2025 689
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 11/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ በትምህርት እና ዲጂታል ዘርፍ ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በአፍሪካ ህብረት ዋና ኮሚሽን ዛሬ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህብረቱን የጎበኙ የመጀመሪያ ማሌዥያ መሪ ሆነዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት ማጠናከርን ያለመ ነው። ሊቀመንበሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የአፍሪካ እና ማሌዥያ ትብበር ውስጥ ታሪካዊና የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ ትብብር እንደሚያጠናክር አመልክተዋል። እ.አ.አ በ2024 የአፍሪካ እና ማሌዥያ የንግድ ልውወጥ መጠን 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መድረሱን ጠቅሰው፤ ይህም በዘርፉ ያለው ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ትምህርት የሁለቱ ወገኖች አጋርነት ዋነኛ ምሰሶ መሆኑንና ከእ.አ.አ 2012 አንስቶ ከ40 ሺህ በላይ አፍሪካውያን በማሌዥያ ትምህርታቸውን መከታተላቸውን ገልጸዋል። ማሌዥያ ቀጣይ የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት ሊቀ መንበር መሆኗ እና ብሪክስን ለመቀላቀል ያላት ፍላጎት ኢንቨስትመንትን ጨምሮ ከአፍሪካ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ነው ያሉት። ሁለቱ ወገኖች በዲጂታል ኢኖቬሽን፣ በግብርና ማቀነባበሪያ ልማት፣ በደቡብ ደቡብ ንግድ እና ትምህርት ዘርፍ ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ገልጸዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ ዓመታዊ ምክክር እ.አ.አ በ2026 እንዲካሄድ ሀሳብ አቅርበዋል። የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በበኩላቸው፤ ማሌዥያ እና አፍሪካ ንግድ፣ ግብርና እና ትምህርትን ጨምሮ በቁልፍ ጉዳዮች ትብብር እያደገ መምጣታቸውን አመልክተዋል። ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን የትብብር አድማስ በማስፋት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በውይይቱ ላይ የማሌዥያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሳትፈዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ማሌዥያ የአጋርነታቸውን አድማስ ለማስፋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል::
ሐተታዎች
መልካምነት ይከፍላል..!!!
Dec 11, 2025 204
መልካምነት ይከፍላል...!!! በማስረሻ ሀብታሙ (ኢዜአ-ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ) መልካም ስነ ምግባርና ባህሪ ከራስ ባለፈ ቤተሰብን ያኮራል፤ ከዚህ ከፍ ሲልም ለማህበረሰብ ግንባታና ለሀገር የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። ሌብነትና ሙስናን ለመከላከልም እንዲሁ አስተዋጾ አለው። በመልካም ስነምግባር ታንጾ ያደገ ሰው በላቡና በወዙ ጥሮ ግሮ ያፈራውን እንጂ የሌሎች የሆነን ሀብትና ንብረት አይመኝም። ዛሬ የራሱ ያልሆነውን ንብረት በሀሰት ምሎና ተገዝቶ ለመውሰድና ለመክበር የሚጥር ሰው በበዛበት በዚህ ዘመን ላይ ወድቆ ያገኙትን ንብረት ለባለቤቱ ለመመለስ "ገንዘብ የጣለ" እያለ በአደባባይ ባለቤቱን የሚያፈላለግ ሰው ሲገጥም ግርምትን ከማጫር ባለፈ እንዲህ አይነት ሰውም አለ ወይ? ያስብላል። ነገሩ የተከሰተው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ነው። በአካባቢው ባህልና እምነት የሰው ገንዘብም ሆነ ንብረት ያለአግባብ መውሰድ "ጎሜ" ወይም እንደ "ሀጥያት" ተደርጎ ይቆጠራል። በኮሻሌ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በዚህ ባህልና እምነት ውስጥ ያደጉ ቢሆንም በቤተሰባቸው በመልካም ስነ ምግባር ታንጸው ማደጋቸው አሁን ላላቸው ታማኝነትና ቅንነት ትልቁን ድርሻ ይይዛል። አርሶ አደሩ ታማኝነታቸውን በተግባር ጭምር በማሳየታቸው ከመንግስት ጭምር እውቅና ተችሯቸዋል። ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ቀን ገበያ ውለው ሲመለሱ በመንገዳቸው ላይ ተጠቅልሎ የታሰረ ነገር ይመለከታሉ። መሬት ወድቆ ያገኙት ነገር እስሩን ፈትው ሲያዩ በርከት ያለ የገንዘብ ኖት ነው። ለማመን እያቃታቸው ገንዘቡን መቁጠር ጀመሩ። በላስቲክ የተጠቀለለው ብር 30 ሺህ ነበር። የራሳቸው ያልሆነውን ገንዘብ ይዞ ወደ ቤት መግባት የህሊና እዳ መስሎ ስለታያቸው አማራጭ ያሉትን አደረጉ፡፡ የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት ከተገኘ በሚል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" እያሉ በአደባባይ ጽምጻቸውን ከፍ አድርገው መጠየቅ ጀመሩ። የሰማቸው ሁሉ ግራ ስለተጋባ ቀረብ ብሎ ሊጠይቃቸው ይቅርና ጤነኛ ሰውም አድርጎ አላያቸውም። የገንዘቡ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ትክክለኛ ሰውም ባለመገኘቱ ልፋታቸው ድካም ብቻ ሆነ። የያዙትን 30 ሺህ ብር ይዘው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተገደዱ። በአካባቢው የገበያ ቀን በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ነው። እናም የገንዘቡን ባለቤት ለማግኘት እስከ ሳምንት ድረስ መቆየት ግድ ሆኖባቸው። ባለቤቱ ይገኛል ወይስ አይገኝም በሚል ሀሳብ ሳምንቱን አሳለፉ። ቀጣይ የገበያ ቀን ሲደርስም ገንዘቡን እንጨት ላይ አስረው በማንጠልጠል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" አያሉ በገበያ ስፍራ በመዘዋወር ዳግም የጠፋበትን ሰው ማፈላለግ ጀመሩ። ገንዘቡ የእኔ ነው፤ ጠፍቶብኛል እያለ የሚመጣ ሰው ቢበዛም ትክክለኛውን የገንዘብ መጠንና ምልክቱን የሚጠራ ሰው አለመኖሩ ግን ፍለጋቸውን አድካሚ አድርጎታል። የገንዘቡን ባለቤት አግኝተው እስኪያስረክቡ ድረስ ተስፋ አልቆረጡም፤ “ገንዘብ የጠፋበት፣ ገንዘብ የጠፋበት...” እያሉ ገበያውን ከዳር ዳር ዞሩ። የኋላ ኋላ ግን ድካማቸው በከንቱ አልቀረም። በስተመጨረሻ ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን ከእነምልክቱ እና ቦታው የሚናገር አንድ ግለሰብ ተገኘ። ከገንዘቡ ባለቤት ጋር ከተወያዩ በኋላ ገንዘቡ ወድቆ ወዳገኙበት ስፍራ ይዘው በመሄድ የያዙትን ገንዘብ መሬት ላይ ጥለው ራሱ ባለቤቱ ምሎ እንዲያነሳ ያደርጋሉ። በእዚህ ሁኔታ ወደቆ ያገኙትን ገንዘብ በታማኝነት ያስረከቡት አቶ ሴዳ ለዚህ መልካም ተግባራቸው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ እውቅና ተችሯቸዋል። የእሳቸው መልካም ተግባር መረጃ የደረሰው ኮሚሽኑም የአርሶ አደሩን አርአያነት ለሌላው ለማስተማር አፈላልጎ ያገኛቸዋል፡፡ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ 22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ሲያከብር በማጠቃለያው ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ በተገኙበት የእውቅና ምስክር ወረቀትና የ15 ሺህ ብር ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡ የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አብደላ ከቤተሰብ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች በዜጎች ስነ ምግባር ላይ አበክሮ መስራት እንዲህ ያሉ ዜጎችን በብዛት ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት። ታማኝ የሆኑ ሰዎች ሲበራከቱ ደግሞ ሀገርና ህዝብን የሚጎዳውን ሙስና ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል፡ እንደ አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ የሚገነባው ከቤት ጀምሮ በሚሰራ ሥራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ኮሚሽኑ ትውልድን በስነ-ምግባር ለማነጽ የጀመረውን ስራ ለማጠናከር በሚሰራው ሥራ እንደ አርሶ አደሩ ያሉ ታማኞች ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ የተቋቋመው የጸረ ሙስና ግብረ ኃይልም በጸረ ሙስና ትግሉ ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡም ታማኝነትን ባህሉ ከማድረግ ባለፈ የጸረ ሙስና ትግሉን በመደገፍ ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣም ነው ያሳሰቡት። የአርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ መልካም ተግባርና ታማኝነትም ለብዙዎች ምሳሌ ይሆናል። በተለይ ያለፉበትን ለማግኘትና በአቋራጭ ለመክበር የሚሯሯጡ ሰዎች ከእሳቸው መልካም ተግባር ሊማሩ ይገባል። የሰው ሀብት ወስዶ ከመክበር ይልቅ በታማኝነት ከምናቆየው ንጹህ ህሊና ይበልጥ አትራፊ እንሆናለን። ለሰዎች መልካም መስራት ክብርና ዋጋ የሚያሰጥ መሆኑንም የእኚህ አርሶ አደሩ ተሞክሮ ያሳያልና እንደእሳቸው ለሰራነው መልካም ተግባር ዋጋ እንዲከፈለን ታማኝነትን የህይወታችን መርህ ማድረግ አለብን። መልካምነት ቢቆይም እንኳ በራሱ ይከፍላልና።
ለቀጣናዊ የጋዜጠኝነት ሙያዊ ልህቀት እውቅና የሚሰጠው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት
Nov 28, 2025 648
የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተጀመረው በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አማካኝነት ነው። ሽልማቱ የኢጋድ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ እና ተቋማዊ አቅምን የማጠናከር ጥረቶች አካል ነው። በኢጋድ ቀጣና በጋዜጠኝነት የላቀ ስራ ላከናወኑ የሚዲያ ባለሙያዎች በሽልማቱ እውቅና ይሳጣቸዋል። ሽልማቱ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ እና ሌሎችም ተጓዳኝ መድረኮችን የሚሸፍን ነው። የሚዲያ ስራው በቀጣናው በተለይም የድርቅ አይበገሬነት፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ልማት ያሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል። ዓመታዊው የኢጋድ ሽልማት የቀጣናዊ ተቋሙ አባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ በግላቸው የሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች እና የፎቶ ጋዜጠኞች ጨምሮ አጠቃላይ የሚዲያ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ነው። በተጨማሪም የቀጣናውን ጉዳይ የሚሸፍኑ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞችም ይሳተፉበታል። በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ስራቸውን በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ እና በኢጋድ አባል ሀገራት በሚገኙ ቋንቋዎች ያቀርባሉ። ከተለያዩ ሙያዎች የተወጣጡ የውሳኔ ሰጪ ወይም ገምጋሚ ቡድን ተቋቁሙ ስራዎቹን በመመዘን አሸናፊዎችን ይለያል። የመጀመሪያው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተካሄደው እ.አ.አ በ2023 በጅቡቲ ነበር። “የድርቅ ተጽእኖዎችን መቋቋም የሚያስችል ትብብር መፍጠር” የሽልማቱ መሪ ሀሳብ ነው። መሪ ሀሳቡ በድርቅ፣ አይበገሬ አቅም መገንባት፣ የውሃ አስተዳደር እና ቀጣናዊ ትብብር ያተኮረ ነው። ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመንት፣ ጦማር (ብሎግ) እና የፎቶ ጋዜጠኝነት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። በመጀመሪያው ሽልማት ላይ ከቀጣናው 105 ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን 14 ባለሙያዎች በዘርፎቹ ተመርጠው ተሸልመዋል። የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ተቋሙ ሚዲያን ለግንዛቤ መፍጠር እና ቀጣናዊ ትብብር እንደ መሳሪያ ለመጠቀም ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ በወቅቱ ገልጾ ነበር። በድርቅ እና በምግብ ዋስትና ላይ ያሉ የጋራ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚዲያ ሚና ወሳኝ እንደሆነም አመልክቷል። ሁለተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተካሄደው እ.አ.አ በ2024 በኬንያ ናይሮቢ ነው። “የተስፋ ትርክቶች፤ የቀጣናውን መጻኢ ጊዜ ሰላማዊ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ሁሉን አቃፊ ማድረግ” የሽልማቱ መሪ ሀሳብ ነው። ሽልማቱ በሰላም፣ ደህንነት፣ ሁሉን አሳታፊ የሆነ መጻኢ ጊዜን መፍጠር፣ ቀጣናዊ ትብብር እና መረጋጋት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የእድሜ ዘመን ተሻላሚ ከሽልማት ዘርፎቹ ውስጥ ናቸው። ለ2024ቱ ሽልማት 318 የሚዲያ ባለሙያዎች ስራቸውን ያቀረቡ ሲሆን 18 የሚዲያ ባለሙያዎች በዘርፎቹ ሽልማት አግኝተዋል። ሁለተኛው ሽልማት ከመጀመሪያው በዘርፎች እና በተሳታፊዎች ብዛት መሻሻል የታየበት ነበር። ይህም ሚዲያ በቀጣናዊ ሰላም፣ ደህንነት እና ቀጣናዊ ትስስር ላይ ያላቸውን ሚና የሚያሳይ ነው። ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ መጥቷል። ሽልማቱ ነገ ህዳር 20 እና 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። የሽልማት ስነ ስርዓቱ “ ውጤታማ የአየር ንብረት ዘገባ ደህንነቱ ለተረጋገጠ፣ ጠንካራ እና የተረጋጋ ቀጣና” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከናወን ነው። ኢጋድ ቀጣናዊ ሁነቱን ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ነው። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያና የአፍሪካ ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚም ባንክ) ለፕሮግራሙ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አስታውቋል። የዚህ ዓመት ሽልማት በአፍሪካ ቀንድ ውጤታማ የአየር ንብረት ትርክትን ለቀረጹ ጋዜጠኞች እና የፊልም ባለሙያዎች እውቅና የሚሰጥ ነው። የሁለት ቀን ሁነቱ የአየር ንብረት ጠንካራ ዘገባዎች እና ሀሳቦች የሚቀርቡበት እንዲሁም ቀጣናዊ ትብብር ጎልቶ የሚታይበት መሆኑን ኢጋድ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። የ2025 የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በ10 ዘርፎች የሚከናወን ነው። የህትመት ጋዜጠኝነት፣ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት፣ የቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ፎቶግራፈር፣ ሀገር በቀል ዘገባ፣ የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ/ የይዘት ቀራጭ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች እና የእድሜ ዘመን ሽልማት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። 400 የሚሆኑ የኢጋድ አባል ሀገራት ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ማስገባታቸውን ጠቁመው፤ ከዚህ ውስጥ 94 የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መሆናቸውን ኢጋድ አስታውቋል። ሽልማቱ በቀጣናው ገንቢ ሚና ያለው ጋዜጠኝነት እንዲጎለብት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም አመልክቷል። ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ አዋርድ ማስተናገዷም ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬቶች ዕውቅና የሚሰጥ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚዲያ ሽልማት ውድድሩ ላይ በርካታ የኢጋድ አባል ሀገራት የመገናኛ ብዙሃን ሙያተኞች እንደሚሳተፉም ገልጿል። የሽልማት ሥነ-ስርዓቱ በአዲስ አበባ መካሄዱም በፐብሊክ ዲፕሎማሲ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም ነው ሚኒስቴሩ ያመለከተው። የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ሙያዊ ደረጃውን የጠበቁ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ዘገባዎች እንዲጠናከሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር፣ የማህበረሰብን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ ብዝሃ ድምጾች እንዲሰሙ በማድረግ፣ ለዴሞክራሲ እሴቶች መጎልበት እና ዘላቂ ልማት የበኩሉን ሚና ይወጣል።
የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አዘጋጅነት
Nov 14, 2025 840
ለረጅም አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ምሰሶ ሆና ቆማለች። በሀገራት መካከል የግንኙነት ድልድል እና የአንድነት መልዕክተኛ መሆን ችለላች። ከምስረታው አንስቶ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ናት። የአፍሪካ መዲና በመባል የምትጠራው አዲስ አበባ በርካታ ድርድሮች፣ የሰላም ውይይቶች እና አህጉራዊ ውሳኔዎች የተላለፈባቸው ሁነቶች ተስተናግደውባታል። ውሳኔዎቹ የአፍሪካ ቀጣና ፖለቲካ እና የልማት ጉዞ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ ናቸው። የኢትዮጵያ የመሪነት ሚና ከዲፕሎማሲውም የተሻገረ ነው። ሀገሪቷ የገባችውን ቃል ከተግባር ጋር በማጣጣም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚለኩ ውጤቶችን እያስመዘገብች ትገኛለች። የተራቆቱ መሬቶች ወደ ነባር ይዞታቸው እንዲመለሱ በማድረግ እና የታዳሽ ኃይል አማራጮቿን በማስፋት ለአረንጓዴ ልማት እና እድገት ያላትን ቁርጠኝነት አሳይታለች። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው አረንጓዴ አሻራ ሚሊዮኖችን ከዳር እስከ ዳር በማነቃነቅ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ከችግር ተናገሪነት ወደ ተጨባጭ መፍትሄ አመንጪነት ሽግግር በማድረግ በአፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ምሳሌ የሚሆን ተግባር አከናውናለች። ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች በዓለም ደረጃ ያላትን ተአማኒነት እና ተቀባይነት እንዲያድግ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በከባቢ አየር ጥበቃ ቁርጠኝነት እና አቅምን በማጣመር ለውጥ አምጥታለች። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያገኘችው እምነት እና የመሪነት ሚና ውጤት የሚያሳይ ተጨማሪ ሃላፊነት ከሰሞኑ ከብራዚል የደን ከተማ ቤለም ተሰምቷል። 30ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30) በቤለም እየተካሄደ ይገኛል። የዓለም ሀገራት በአንገብጋቢ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች እና ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ እየመከሩ ይገኛል። በጉባኤው ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደውን 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ዓለም ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የገቡትን ቃል በተግባር ለመቀየር ቁርጠኝነት ባነሳቸው ወቅት ኢትዮጵያ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ተግባር መፈጸሟን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳላት ገልጸው የዳበረ የትራንስፖርት አገልግሎት ከብዙ የዲፕሎማሲ ተቋማት መቀመጫነት ጋር ሲደመር የዝግጁነት አቅሟን በላቀ ሁኔታ እንደሚያሳድገው አመልክተዋል። ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ ልምዱም አቅሙም እንዳላት ገልጸው፣ ሀገራት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። ናይጄሪያም ጉባኤውን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርባ ነበር። የኢትዮጵያ የኮፕ 32 የማስተናገድ ፍላጎት ከአፍሪካ ሀገራት ሙሉ ድጋፍ አግኝቷል። የወቅቱ የአፍሪካ የአየር ንብረት ተደራዳሪዎች ቡድን ሊቀመንበር የሆነችው ታንዛንያ የኢትዮጵያ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልጻለች። የአፍሪካውያን ውሳኔ ከቃል ባሻገር ኢትዮጵያ የአህጉሪቷን የአየር ንብረት የቅድሚያ ትኩረቶች የማራመድ እና የመወከል አቅም አላት ብለው ይሁንታ የሰጡበት ነው። ይህ ጠንካራ እምነት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ሁሉን አፍሪካውያን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግ እና አህጉሪቷን ያማከለ ውሳኔዎች በዓለም መድረክ እንዲተላለፍ እያደረገች ያለውን ጥረት ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግም ነው። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ አፍሪካውያን ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታስናግድ ድጋፍ በመስጠታቸው አመስግነው፤ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ አበክራ እንደምትሰራ ተናግረዋል። በቅርቡ በአዲስ አበባ የተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ መሰል አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በብቃት ማስተናገድ እንደምትችል የሚያመላክት ነው ብለዋል። አዲስ አበባ እንግዶቿን በሚመጥን ደረጃ ጉባዔውን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት አምባሳደሩ፥ ለኢትዮጵያ ጥያቄ ሌሎች ሀገራትም ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ የኮፕ 32ን ለማስተናገድ መመረጧ በድንገት የመጣ ጉዳይ አይደለም። በተግባር የተረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የመሪነት ሚና፣ አረንጓዴ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እያከናወነች ያለቻቸው ስራዎች እና የፖለቲካ ቁርጠኝነቷ፣ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ድምጽ እና ምልክት መሆኗ ከቃል ባለፈ በተጨበጠ ስራ መታየቱ፣ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ ውጤታማነቷ እና የዲፕሎማሲ ተሰሚነቷ ድምር ውጤቶች እንጂ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታስተናግድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጠን ክብር ይሰማናል ብለዋል። አፍሪካ በ2025 በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (COP 30) ላይ በብራዚል በአንድ ድምጽ ተናግራለች፤ ዓለምም አዳምጧል ብለዋል። እንዲሁም ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ በ2027 በአዲስ አበባ COP 32ን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ለደገፉ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች ምሥጋና አቅርበዋል። በሰው ልጆች ኑሮ በጣም አንገብጋቢ ከሆኑት ተግዳሮቶች መካከል አንዱን ለመቅረፍ እንዲቻል የጋራ ጥረቶችን ለመምራት ዕድሉን ስላገኘንም አመሥጋኞች ነን ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህን ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጠንም ክብር ይሰማናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ይህ ዕውቅና ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ላይ ያላትን ቁርጠኛ ርምጃ፣ አመራር ብሎም ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን የማስተናገድ የዳበረ ዐቅም ያሳያል ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የኮፕ 32 መድረክ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ ርምጃን የሚያበረታታ ጠንካራ እና ትርጉም ያለው ውጤት ለማምጣት ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ማዘጋጀቷ በዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ መድረኮች ኢትዮጵያ ያላትን የአየር ንብረት የመሪነት ሚና የበለጠ ያሳድጋል። የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ የሚያስፈልጋትን ፋይናንስ ለማግኘት እና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ለማጠናከር መልካም አጋጣሚን ይፈጥርላታል። በሺህዎች የሚቆጠሩ የጉባኤው ተሳታፊዎች የቱሪዝም መስህቧቿንና መዳረሻዎቿን ሲጎበኙ ከዘርፉ የሚያገኘው ገቢ ያድጋል ይህም ኢኮኖሚውን በመደገፍ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ተጽእኖ ፈጣሪን ጉባኤው በማስተናገድ በኩል ጉልህ አበርክቶ የሚኖረው ሲሆን ዘላቂ የሆነ የከባቢ አየር ትብብርን ለመፍጠር ያስችላል። ለኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ማስተናገድ ከክብር ባሻገር ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና ሰው ለሚኖርባት ምድር ጥበቃ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር የምታሳይበት ይሆናል። ኢትዮጵያ ጠንካራ የከባቢ አየር ጥበቃ ኢኒሼቲቮች፣ የማይበገር ዲፕሎማሲ እና የነገ አረንጓዴ እድገት ህልሟ ከጉባኤው ጋር ተዳምረው የተፈጥሮ ጠበቃነቷን እና የዓለም ትብብር ተምሳሌትና መሪነቷን የበለጠ ያሳድጉታል። ኢትዮጵያ እና ህዝቧቿ ከመቼውም ጊዜ በላይ የአየር ንብረት የረጅም ጊዜ ፈተናዎች እንዲፈቱ ከአፍሪካ ብሎም ከመላው ዓለም ጋር ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ እና ቁርጠኛ ናት።
" መሬት እና ፍትህ" - የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የእድገት ጉዞ
Nov 11, 2025 866
መሬት በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው። መሬት ከአፍሪካውያን የአኗኗር ዘይቤ፣ ማንነት፣ ባህል እና ማህበራዊ መስተጋብር ጋር የተቆራኘ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከቅኝ ግዛት ዘመን በፊት የአፍሪካ በርካታ ማህበረሰቦች መሬት በልማዳዊ እና ባህላዊ ስርዓት ያስተዳድሩ ነበር። የቤተሰብ ጎሳዎች ወይም ማህበረሰቦች መሬት የመጠቀም፣ የማስተዳደር እና ባህላዊ መንገዶች በሰጣቸው መብት ሲያስተላልፉ ቆይተዋል። በእንደዚህ አይነት ስርዓት ውስጥ መሬት ከሀብት ባለፈ ከማህበራዊ ግንኙነቶች፣ መንፈሳዊ መስተጋብሮች እና የተፈጥሮ ሀብቶችን በጋራ የማስተዳደር ኃላፊነት ጋር ትስስር አለው። በቅኝ ግዛት ዘመን የአውሮፓ ኃይሎች በስምምነቶች፣ በአዋጆች እና ኃይል በመጠቀም መሬት የቁጥጥር፣ የብዝበዛ እና ሀብትን የመንጠቂያ መሳሪያ አድርገውታል። መሬት ፖሊሲ ኃይልን ማጠናከሪያ እና የኢኮኖሚ ብዝበዛ መንገድ ሆኗል። አፍሪካውያን በልማዳዊ እና ባህላዊ መንገዶች የነበራቸውን የመሬት መብቶች በመንጠቅ ከአፍሪካ ውጪ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የሰፈራ ፕሮግራም ማካሄጃ እንዲሆኑ በር ከፍቷል። በዚህም ከፍተኛ የሆነ የአፍሪካ ሀብት ሲበዘበዝ ቆይቷል። ሀገር በቀል ማህበረሰቦች ከመሬታቸው የመፈናቀል እና የመገለል ሰለባ ሆነዋል። በቅኝ ገዢዎች የወጡ የመሬት ፖሊሲዎች፣ የመሬት ምዝገባ እና የመሬት አስተዳደር ስርዓት የአፍሪካ መሬት ተጠቃሚዎችን መብት የነፈገ ነበር። የቅኝ ግዛት የቀረጸው የመሬት አስተዳደር ስርዓት አፍሪካውያንን ህጋዊ የመሬት ባለቤትነትን ያሳጣ ነው። የአፍሪካ ሀገራት ከነጻነታቸው በኋላ እኩልነት ያልተረጋገጠባቸውን የመሬት መብቶች እና ስርዓቶች ወርሰዋል። ሀገራት የመሬት ፖሊሲዎቹን አሁን ያሉ የልማት ግቦችን፣ የፍትህ ፍላጎቶች እና ወቅታዊ የአስተዳደር ማዕቀፎች ባማከለ ሁኔታ የመቀየር ስራ በማከናወን ላይ ናቸው። በቅኝ ግዛት ዘመን የመሬት መብታቸውን ላጡ ዜጎች በተለይም ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተመለሰላቸው ይገኛል። ይሁንና የቅኝ ግዛት የመሬት ቅድሚያ መጥፎ፣ በሀገራት ብሄራዊ ህግ ውስጥ ያሉ የተደባለቁ የህግ ማዕቀፎች (ለምሳሌ ልማዳዊ ህጎች ከመደበኛ ህጎች ጋር መደባለቅ) እና የተቋማት የአስተዳደር ስርዓት አለመናከር በአፍሪካ ፍትሃዊ እና እኩልነት የመሬት ስርዓት የማስፈን ጉዞ ላይ ጋሬጣ ሆኗል። ዛሬ ላይ አፍሪካ አጀንዳ 2063 እና ዘላቂ ልማት ግቦች እየተገበረች ትገኛለች። የአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች አንኳር ምሰሶ ተደርገው ከሚጠቀሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ መሬት ነው። እኩል የመሬት መብት የምግብ ዋስትና እና ስርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ፣ ለከባቢ አየር ጥበቃ እና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ የአጀንዳ 2063 ሰነድ ያስረዳል። የአፍሪካ ህብረት ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በመተባበር በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ላይ ማዕቀፎች እና የህግ አሰራሮችን በመቅረጽ እያስተዋወቁ ይገኛሉ። የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የመሬት ህጎችን የተሰናነሰኑ እንዲሆኑና የተቋማት አቅምን እንዲያጠናክሩ ጥሪ በማቅረብ ላይ ነው። “የመሬት አስተዳደር፣ ፍትህ እና ካሳ ለአፍሪካውያን እና ለዘርዓ አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ ከህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ኮንፍረንሱን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) በጋራ በመተባበር ነው። ከአፍሪካ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ እና የአካባቢ ጉዳዮች ጋር የተጣጣሙ እና ለነባራዊ እውነታዎች ምላሽ የሚሰጡ የመሬት ፖሊሲ ምርጥ ተሞክሮዎች በኮንፍረንሱ ላይ እየቀረቡ ይገኛል። ህዳር 1 በነበረው የጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸኃፊ ክላቨር ጋቴቴ በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ጉዳይ ላይ የሚመክረው ስብሰባ በወሳኝ ወቅት የተዘጋጀ ነው ብለዋል። አፍሪካውያን ያላቸውን ሰፊ የመሬት ሀብት በቅኝ ግዛት አሰራሮች ሳቢያ በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላቸው በአፍሪካ መሬት ዛሬም የግጭትና የኢ-ፍትሐዊነት መገለጫ ሆኗል ብለዋል። በአፍሪካ የመሬት አስተዳደር በሴቶች፣ በወጣቶችና በዝቅተኛ አርሶ አደሮች ዘንድ ኢ-ፍትሐዊነትን በማንገስ ሰፊ የኢኮኖሚ ልዩነት መፍጠሩን ገልጸዋል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ስብሰባ ከአፍሪካ ሕብረት 2025 "የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካውያን" መሪ ሀሳብ ጋር የተጣጣመ መሆኑን አንስተው፤ ዓላማው አፍሪካውያን ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው ብለዋል። የአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የካሳ ጥያቄ ያለፈውን ማስመለስ ሳይሆን አሁን ባለው የዓለም የፋይናንስ ስርዓት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል። አፍሪካ 65 በመቶ ያልታረሰ መሬት፣ ከዓለም ኢንዱስትሪ ሁለት በመቶ ብቻ ድርሻ ያላት፣ ለአየር ንብረት ለውጭ ተፅዕኖ ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች የሆነ አህጉር መሆኗን አንስተዋል። በአፍሪካ የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን በማዘመን ፍትሐዊነትን ማስፈን ጊዜው አሁን ነው ያሉት ዋና ጸኃፊው፣ ሴቶችን ወጣቶችና ዝቅተኛ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ዘላቂ ሰላም ማስፈን እንደሚገባ ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዜጎችና ዳያስፖራ ዳይሬክተር አምር አልጆዋሊ የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ የአህጉሪቱን መፃኢ ጊዜ ለመቀየር ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካና ዘርዓ አፍሪካውያን ላይ የደረሰው በደል ዕውቅና ማግኘት እንዳለበት ገልጸው፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ለሕብረቱ መሪ ሀሳብ ትግበራ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። የመሬት አስተዳደር የፍትሐዊነት ምልክት መሆኑን በማንሳት፤ የመሬት ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መስፈን አለበት ብለዋል። የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 በማሳካት አካታች ብልፅግናና ሰላምን ለማረጋገጥ በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል። ሕብረቱ በመሬት አስተዳደር ዙሪያ ግልፅ አሰራር እንዲሰፍን ለአባል ሀገራት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዋል። ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ እስከ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። ውጤታማ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመሬት አስተዳደር ስርዓት መገንባት፣ ተቋማዊ አቅምን መፍጠር እና የቁጥጥርና ክትትልን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የቅኝ ግዛት አሻራዎች እና ወቅታዊ የኢ-ፍትሃዊነት ጉዳዮች በመሬት ባለቤትነት እና አስተዳደር ያሳደሯቸውን ተጽእኖዎች ለመፍታት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ይገልጻሉ። በመሬት ፖሊሲ ቀረጻ፣ ትግበራ እና ቁጥጥር አቅምን መገንባት፣ የእውቀት ሽግግርን ማሳደግ እና የፖሊሲ ቁርጠኝነትን ወደ ሚጨበጥ የተግባር ምላሽ የመቀየር ጉዳይም አጽንዖት የሚሰጣቸው አጀንዳዎች መሆናቸውን ህብረቱ ገልጿል። በአህጉራዊ ኮንፍረንሱ ላይ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት፣ የህብረቱ ተቋማት እና አደረጃጀቶች ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎች፣ የፖሊሲ ባለሙያዎች፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ትውልደ አፍሪካውያንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ሁነት ነው። የመሬት ፖሊሲ ጉባኤው አፍሪካውያን ፍትሃዊ እና ዘላቂ የመሬት አስተዳደርን ለማስፈን ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነታቸውን እያሳዩበት የሚገኝ መድረክ ነው። ጉባኤው አፍሪካውያን ከባለፈው ታሪክ በመማር ፖሊሲ፣ ጥናት እና የማህበረሰብ ድምጾችን በማቀናጀት ረገድ ያለው ፋይዳ ወሳኝ ነው። ጉባኤው የመሬት ፍትህን የማስፈን፣ አይበገሬነትን የመገንባት እና ለሁሉም አፍሪካውያን የጋራ ብልጽግና የማረጋገጥ የጋራ ራዕይ በመደገፍ ረገድ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
ትንታኔዎች
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ
Dec 8, 2025 336
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 2912
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ 7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 2852
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 3752
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 2228
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 1438
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7254
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 5742
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
በአረንጓዴ ልምላሜ ያጌጠው - የቤንቾች ቀዬ
Dec 3, 2025 672
በአረንጓዴ ልምላሜ ያጌጠው - የቤንቾች ቀዬ (በቀደሰ ተክሌ) -ከሚዛን ቅርንጫፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሚገኘው የቤንች ምድር የሰጡትን የሚያበቅል ክረምት ከበጋ የማይጠወልግ ልምላሜን የታደለ ክልል ነው። በቤንች ሸኮ ዞን ባሉ የተለያዩ ወረዳዎች ደን የሚመስልና በመኖሪያ መንደሮች የሚታየው አብዛኛው አረንጓዴ ስፍራ ለምግብነት የሚያገለግሉ ፍራፍሬዎች፣ ቅጠሎችና ስሮችን የያዘ ነው። የቤንቾች ቤት ዙሪያው በአረንጓዴ ተፈጥሮ ያጌጠ ነው። የቤታቸው ሞገስ፤ የምግብ ዋስትናቸውም ጭምር ነው። ከዚህ ከፍ ሲል ደግሞ ቤንቾች ነፋሻማ አየር እየማጉ የመኖር ልምድን ያጎናጸፋቸው ይኸው አፈር ቆፍረው ዘር ተክለው ያበቀሉትና የተንከባከቡት አረንጓዴ ሀብት ነው። ከአንድ አርሶ አደር ማሳ እንሰት፣ ሙዝ፣ ጎደሬ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ ብርቱካን እና ሌሎች ፍራፍሬዎች ማየት የተለመደ ነው። እግር ጥሎት ወደ ቀዬያቸው ያመራ እንግዳ ከፍራፍሬዎቹ የደረሰ ካለ ተቆርጦ ይሰጠዋል። በተጨማሪም ከብቶች፣ በጎችና ዶሮዎች የገቢ ምንጮቻቸው ናቸው። ወደ ቤታቸው ዘልቆ የገባ ሰው "ኪዥ" የተሰኘና የቤንች እናቶች ከወተት የሚያዘጋጁትን ''ጎደሬ'' ተብሎ ከሚጠራ የስራ ስር ምግብ ጋር ያጣጥማል። ቤንቾች በቆሎ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ባቄላ እንዲሁም ሌሎች የሰብል ዓይነቶችን ያለማሉ። ማር፣ ቡና፣ ኮረሪማ እና ሌሎች የተፈጥሮ ቅመማ ቅመሞችም ቤንቾች ከገበያ ገዝተው የሚያመጡት ሳይሆን ከማሳቸው የሚያፈሩት ነው። የተቀናጀ እርሻን ባህል ያደረጉት ብርቱ የቤንች አርሶ አደሮች ወደ ገበያ አውጥተው የሚሸጡት እንጂ የሚገዙት የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። የፋብሪካ ውጤቶችን ለመግዛትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግም ከጓዳቸው ሞልቶ የተረፈውን ወደ ገበያ አውጥተው በመሸጥ ገበያን ያረጋጋሉ። በጠንካራ የእርሻ ባህላቸውም ምክንያት ልጆቻቸው የበሰለ ምግብን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ፍራፍሬዎችንም ከጓሮና ከጫካ ቆርጠው ስለሚመገቡ ረሀብን አያውቁም። የቤንቾች ቤት ዙሪያ ውብና ጽዱ ነው። ለዚህ ደግሞ ሴቶቹ የቤታቸውን ግድግዳ በተፈጥሮ ቀለም ከማስዋብ ጀምሮ ይጠበቡበታል። በቤንቾች ዘንድ የአንድ አርሶ አደር ጉብዝና የሚለካው በቤቱ ነው። ይህም የቤቱ ዙሪያ ያለው ውበትና የቤቱ ጥንካሬ ብቻም ሳይሆን ገላጣ መሆን አለመሆኑም ጭምር ከግምት ውስጥ ይገባል። አባዎራው በማሳው ላይ የሰብል ስራውን ያከናውናል። ልጆችና እማውራዋ ደግሞ ይኮተኩታሉ ያርማሉ። ከዚህም በተጨማሪ የቤንች እናት ጎደሬና ሌሎች የጓሮ አትክልቶችን የማልማት ኃላፊነት አለባት። የቤታቸው ዙሪያና ቀዬው በሙሉ በአረንጓዴ ልምላሜ አጊጦ የሚታይበት ምስጢሩ ይሄው ነው። ከርቀት ደን መስሎ የሚታየው አረንጓዴው ቀዬአቸው የገቢ ምንጭም በመሆኑ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ነውም ማለት ይቻላል። የሌማት ትሩፋት እሳቤ ቀድሞ የገባቸው ቤንቾች ማር አይገዙም፤ ለእንቁላል ሸመታም ገበያ አይወጡም። ወተት ቢያምራቸው በትኩሱ፤ ከዛም አለፍ ሲል በባህላዊ መንገድ እርሾ ጨምረው የሚያዘጋጁት "ኪዥ" የተሰኘ የወተት ውጤትን እንደ አይብም እንደ እርጎም አደርገው ይጠቀሙታል። የትኛውንም መልክዓ ምድር በሚስማማው የሰብል ዓይነት መሸፈን ያውቁበታል። መሬቱ ረግረጋማ ከሆነ ለጎደሬ፤ ዳገታማ ሆኖ ለማረስ የሚያስቸግር ከሆነ ደግሞ ለሙዝ ልማት ያውሉታል። የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ ሥራ የሚሠራው በጓሮ ነው። ይህም ሁሉን ከአንድ ጓሮ ለማግኘት በመጣር የሚመጣ ነው። ይህም ካልሆነ ደግሞ አስተማማኝና ቋሚ ምርት ማሳ ላይ አልያም ጎተራው ላይ ማኖር ያስፈልጋል። እንደ ቤንቾች በቤተሰብ ደረጃ ምግብን በራስ አቅም ለመቻል የሚደረገው ጥረት እንደሀገር ሲጠናከር ለውጡ ቀጣይነት ባለው መልኩ ይፋጠናን። ሀገራችን ኢትዮጵያ ካላት የሕዝብ ቁጥር አብዛኛው አርሶ አደር ነው። ይሁን እንጂ ጾሙን የሚያድር ሰፊ መሬት እንዳለ መረጃዎች ያመለከታሉ። አንድም መሬት ጾም እንዳያድር በየአካባቢው ስራዎች ቢጀመረም ውጤቱ ቀሪ ሥራዎችን የሚጠይቅ ነው። ዛሬም በምርት እጥረት የኑሮ ውድነትና መሰል ችግሮች ይስተዋላሉ። በእነዚህ መሬቶች ላይ ሰርቶ ከመለወጥ ይልቅ ከተማ ቁጭ ማለትን የሚሻ ትውልድ ማየት የተለመደ ነው። የቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች እጃቸው ብርቱ በመሆኑ እነዚህ ችግሮች በስራ አሽንፈዋል። ይህም በምግብ ራሳቸውን ከመቻል ባለፈ በኢኮኖሚም እንዲረጋጉ አድርጓቸዋል። ለሀብት ምንጭ የሆነን ማሳ ለቆ ከተማ በመዋል የሚገኝ ነገር አይኖርም። በከተማም ሆነ በገጠር ለመለወጥ እንደ ቤንቾች ብርቱ እጆች ያስፈልጋሉ። ካልተሰራ ገቢ ሳይሆን ወጪ እያደገ ወዳልተገባ መንገድ ለመሄድ ምክንያት ይሆናል። ለችግርም ሆነ ሰርቶ የመለወጥ ዕድሉ የሚወሰነው በምርጫችንና ለሥራችን በምንሰጠው ትኩረት ነው። እንደ ቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች ሰርቶ ለመለወጥና ራስን ለመቻል በየአካባቢው ያለን የተፈጥሮ ሀብት ወደ ልማት ለመቀየር ተግቶ መስራት ያስፈልጋል ። ሰላም!
ብልህ ከችግር ይማራል!!
Dec 2, 2025 439
ብልህ ከደረሰበት ችግር ይማራል!! በማሙሽ ጋረደው ገራድ ተስፋዬ ተፈራ ትውልድና እድገታቸው በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ቃልሻ ቀበሌ ሲሆን በ1999 ዓ.ም በህገ ወጥ መንገድ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዘው እንደነበር ያስታውሳሉ። ገንዘብ ለማግኘትና የመለውጥ ህልማቸውን ለማሳካት በሚል ሩቅ አስበው የጀመሩት ህገ ወጥ ጉዞ መዳረሻውን እስር ቤት አደረገው። ይህም ሁኔታ ''ሩቅ አሳቢ-ቅርብ አዳሪ'' አደረጋቸው። በባዕድ አገር በነበራቸው የ2 ዓመት የእስር ቤት ቆይታም የምግብ እጦትን ጨምሮ አካላዊ ጥቃትና ጉልበት ብዝበዛ እንዲሁም የተለያዩ ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶችን እንዳስተናገዱ ይናገራሉ። ይህም አልበቃ ብሎ ከአካባቢው በህገወጥ መንገድ የሚሰደዱ ወጣቶችን ጉልበት በመጠቀም ሰፋፊ እርሻዎች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ የጉልበት ብዝበዛ ይፈፀምባቸው እንደነበርም ያስታውሳሉ። ብልህ ከደረሰበት ችግር ይማራል! የሚሉት ገራድ ተስፋዬ ሩቅ ሳይጓዙ፣ ገንዘብ ሳያወጡ ሰርተው መለወጥ የሚችሉበትን አካባቢያቸውን ፀጋ ሳያማትሩ ስደት መሄዳቸው ቁጭት ፈጥሮባቸው ነበር፡፡ ይህም በሀገራቸው እንኳንስ የለማን መሬት ይቅርና የተቦረቦረ መሬትን አልምቶ ጉልበትንና ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ለስኬት መብቃት እንደሚቻል ከእስር ቤት ቆይታቸው ተምረው ከእስር እንደተፈቱም ወዲያውኑ ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን ተናግረዋል። በ2001 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሱም በማህበር ተደራጅተው ከመንግሥት ባገኙት 70 ሺህ ብር ብድር በእንስሳት እርባታ ላይ ለመሰማራት 4 የወተት ከብቶችን ገዝተው የእርባታ ስራ መጀመራቸውን ይገልጻሉ፡፡ በዚህም የዞኑ አስተዳደር የሰጣቸውን መሬት አልምተው የእንስሳት እርባታውን አስፋፍተው መስራት ጀመሩ፡፡ አሁን ላይ የወተት ላሞቹን ቁጥር 37 በማድረስ የወተት ምርታማነታቸው አድጎ ከቤት ፍጆታ አልፎ ለሆሳዕና ከተማና አካባቢው በቀን ከ670 ሊትር በላይ ወተት እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ለ40 ወጣቶችም ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ከመፍጠራቸውም ባሻገር የተለያዩ የጭነትና የስራ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ማፍራት መቻላቸውን ይናገራሉ። የጀመሩትን ስራ በጥምር ግብርና የማስፋትና የሚያገኙትን ወተት በማቀነባበር ምርቱን በተለያየ መልኩ ለገበያ የማቅረብ ራዕይን ሰንቀው በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በህገወጥ ስደት ካጋጠማቸው ችግር ተነስተው በተግባር ያዩትን ለሌሎች በማስተማር የስደትን አስከፊነት ለአካባቢያቸው ወጣቶች እያስገነዘቡ መሆኑን ገልጸዋል። ወጣቶች የስደትን አማራጭ ከመመልከታቸው በፊት የአካባቢያቸውን ፀጋ እንዲቃኙና ራዕይ ሰንቀው ራሳቸውን ለማሻሻል እንዲሰሩም መክረዋል። መለወጥ በውጪ ሀገር ብቻ ያለ የሚመስላቸው የቤተሰብ ኃላፊዎችም ልጆቻቸው በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ በማመን ሊያግዟቸው እንደሚገባም አቶ ገራድ አስገንዝበዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትልና የእርሻና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለምይርጋ ወልደስላሴ፤ በክልሉ በርካታ ወጣቶች ያልተጨበጠ ተስፋ ሰንቀው ለህገወጥ ስደትና ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በሀገር ሰርቶ ለመለወጥ የሚያስችል አቅም በግብርናው ዘርፍ መኖሩን ጠቅሰው በዘርፉ የተሰማሩ ከስደት ተመላሾች በአካባቢያቸው ሰርተው ለስኬት እየበቁ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ከራሳቸው አልፈው ለበርካታ ስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ላይ የሚገኙና የእነዚህን አካላት ተሞክሮ በመውሰድ በሀገር ሰርቶ ለመለወጥ መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡