ቀጥታ፡

በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ዛሬ በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች

አዲስ አበባ፤ታህሳሰ 4 /2018(ኢዜአ)፦በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ዛሬ በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች።

4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ ውድድር እየተካሄደ ነው::

ዛሬ በተደረጉ ውድድሮችም ኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች።

በ1500 ሜትር ሴቶች ሀና ረጋሳ ውድድሯን በአንደኛነት በመፈፀም ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች።

በተጨማሪም በ800ሜትር ሴቶች መርጋ ሀቃ የወርቅ ሜዳልያ አሸንፏል።

ኢትዮጵያ በ5ሺ ሜትር እርምጃ ውድድር በህይወት አምባው አማካኝነት የውድድሩን 6ኛ የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች።

በ3000ሺ ሜትር ወንዶች ጎይቶም መኮንን የነሀስ ሜዳልያ አሸንፏል።በመካከለኛ ሪሌይ የነሐስ ማዳልያ ተመዝግቧል።

እንደ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ከ2ኛው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ወጣቶች ጨዋታዎች የተገኙ አትሌቶች በውድድሩ በአስገራሚ ውጤታማነታቸው ቀጥለዋል።

#ኢዜአ   #Ethiopian_News_Agency

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም