በፕሪሚየር ሊጉ ቼልሲ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ቼልሲ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 4/2018(ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ጀምረዋል።
በስታምፎርድ ብሪጅ በተካሄደው ጨዋታ ቼልሲ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ከጉዳት የተመለሰው ኮል ፓልመር እና ማሎ ጉስቶ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ቼልሲ በ28 ነጥብ ደረጃውን ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። ኤቨርተን በ24 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላኛው ጨዋታ ሊቨርፑል ብራይተንን 2 ለ 0 አሸንፏል። ሁጎ ኢኪቲኬ የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል በ26 ነጥብ ስድስተኛ፣ ብራይተን በ23 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
የሊቨርፑል አጥቂ ሁጎ ኢኬቲኬ በ47ኛው ሴኮንድ ያስቆጠራት ጎል የውድድር ዓመቱ ፈጣን ጎል ተመዝግቧል።
ምሽት 5 ሰዓት ላይ የሊጉ መሪ አርሰናል ከዎልቭስ በኤምሬትስ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል።
ከዚያ አስቀድሞ በርንሌይ ከፉልሃም ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።