ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ አቻ ተለያዩ
Oct 10, 2026 30
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሪያን ምቤሞ በ73ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ዩናይትድ መሪ ሆኗል። ዶምኒክ ሶላንኪ በ92ኛው ደቂቃ ስፐርስን አቻ አድርጓል። የቶተንሃሙ አማካይ ሮድሪጎ ቤንታንኩር በ78ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። በመጀመሪያው አጋማሽ ስፐርስ፣ በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ዩናይትድ ብልጫ ነበራቸው። ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ በስድስት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ከድል ርቋል። ቶተንሃም በበኩሉ በሶስት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ ያላሸነፈ ሲሆን በውጤት ማጣት ጉዞው ቀጥሏል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር ሀገራዊ እድገትን እያፈጠነ ነው
Oct 10, 2026 66
ዲላ፣ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር ፈጣን እድገት እንዲመዘገብ ማስቻሉን የምጣኔ ሃብት ምሁራን ገለጹ። በዲላ ዩኒቨርሲቲ "ወቅታዊ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጉዳዮች እና እድገቶች" በሚል ርዕስ አውደ ጥናት ተካሂዷል። በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙ የዘርፉ ምሁራን እንዳሉት የተሟላ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ እውን መሆን ፈጣን ሁለንተናዊ እድገት እንዲመዘገብ አስችሏል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚ ትምህርት ክፍል ተመራማሪና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐና ለኢዜአ እንዳሉት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ብዝሃ ዘርፎችን በማነቃቃት የሀገሪቱን የእድገት ጉዞ እያፋጠነ ነው። በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ በዋጋ ንረት ሲከሰቱ የነበሩ ተግዳሮቶችን በመፍታት የተሟላ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ትግበራን ውጤታማ እያደረገው መምጣቱን ጠቁመዋል። የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያው እንዲመራ መደረጉም የዋጋ ግሽበትን በማረጋጋት የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ማሳደጉን ፕሮፌሰር ጣሰው አክለው ገልጸዋል። የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራን ተከትሎ የመጣውን የኢኮኖሚ እድገት በውጫዊ ተጽኖ አጣብቂኝ ውስጥ እንዳይገባ ማህበሩ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ የተለያዩ ጥናቶችን በማከናወን ለፖሊሲ ግብዓትነት እያዋለው ነው ብለዋል። የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ትግበራው የሀገርን ጸጋዎች በአግባቡ ለይቶ ለልማት በማዋል የነበሩ ክፍተቶችን የቀረፈ ነው ያሉት ደግሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢኮኖሚ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ታምራት በየነ (ዶ/ር ) ናቸው። በተለይ በራሳችን መንገድ ችግሮችን የመፍታት ባህልን በመገንባት በኩል የተሰሩ ሥራዎች ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የዋጋ ግሽበትንና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከማስተካከል ባለፈ በዲጀታል ፋይናንስ ከዓለም እኩል ለመራመድ ምቹ መደላድል መፍጠሩን የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ገልጸዋል። በዘርፉ የተስተዋለውን እድገትና የገጠመውን ተግዳሮት በምርምር በመለየት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙን ውጤታማነት አጠናክሮ ለማስቀጠል በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውንም ታምራት (ዶ/ር) አንስተዋል። በአውደ ጥናቱ ላይ ሦስት የምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበርና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአቅም ግንባታና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በጋራ መስራት የሚያስችላቸው የሦስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድም ተፈራርመዋል።
ከማዕድን ማውጣት እስከ ኢንዱስትሪ ሽግግር፤ የመደመር መንግሥት የማድረግ አቅም ማሳያ
Oct 10, 2026 95
በመንግሥቱ ዘውዴ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ኢትዮጵያ ካሏት ጸጋዎች መካከል የምድር ውስጥ ሃብቶች ይገኙበታል። ሃብቶቹ የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ግብዓት ናቸው። እጅግ የበለጸጉ የጂኦሎጂካል ማዕድናት ሀብት ያላት ኢትዮጵያ የማዕድን ሃብት በብዝኅ ኢኮኖሚ መርህ የዕድገት ሽግግርን የሚያፋጥን መሰረት እየጣለ ይገኛል። ኢትዮጵያ ወርቅን ጨምሮ ለኢንዱስትሪና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ በጥሬ ዕቃ ግብዓትነት የሚውሉ ውድና የከበሩ እንደ ታንታለም፣ ፖታሽና ሌሎች ማዕድናት በጉያዋ የታቀፈች ምድር ናት። ማዕድናት ለሥራ ዕድል ፈጠራም የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል አይደለም። በመደመር መንግሥት አምስት የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሮች መካከል የማዕድን ዘርፍ አንዱ እንዲሆን አድርጓል። ይህም የኢትዮጵያን የምድር ውስጥ እምቅ ሀብቶች ለኢኮኖሚ ዕድገት ማዋል እንደሚቻል ግልጸኝነትን የፈጠረ ወሳኝ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል። በዚህም ባለፉት ዓመታት በዘርፉ ያሉ ሀብቶችን በማልማት፣ እሴት ጨምሮ በማምረትና ለገበያ በማቅረብ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት በኩል አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካን ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፤ ሀብቶቻችንን ከኢንዱስትሪ አቅም ጋር በማስተሳሰር የወጪ ንግድ ገቢንና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ የጌጣጌጥ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍና ተወዳዳሪ የወርቅ እሴት ሰንሰለት ለመገንባት የመደመር መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው። የዚህ ሀገራዊ ጥረት አንድ አካል የሆነውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ሥራ የጀመረው የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካም የመደመር መንግሥት እምቅ የሀገር ሀብቶችን ለይቶ፣ አልምቶና አምርቶ ለውጤት ማብቃቱ አይነተኛ ምሳሌ ይሆናል። ይህ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ መካከል በተደረገ አጋርነት የተቋቋሙ የመደመር መንግሥት ከግሉ ዘርፍ ተዋንያን ጋር በጋራ በመሥራት የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳያል። የማዕድን ሀብቶችን በማልማትና እሴት ጨምሮ በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። ባለፉት ዓመታት በዘርፉ የተመዘገበውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ዕድገትም ሁነኛ አብነት ነው። ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካም በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም አለው። ፋብሪካው በሀገር ውስጥ ምርት ላይ እሴት በመጨመርና የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ በማጠናከር በውድ ማዕድናት ማጣሪያ ረገድ ኢትዮጵያን ቀጣናዊ ማዕከል የሚያደርግ ትልቅ ምዕራፍ ሆኗል። ከማዕድን ማውጣት እስከ ኢንዱስትሪ ሽግግር ድረስ በኢትዮጵያ የላቀ የእሴት ሰንሰለት እየፈጠረ ይገኛል። ይህ ፋብሪካም በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ርዕይ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ የሚወሰድ ተጨባጭ የልማት ውጤት መሆኑ እሙን ነው። የመደመር መንግሥት ኢንዱስትሪ ምርታማነትን ከማስፋፋት ባሻገር የማምረት አቅማቸው እንዲጎለብት የሰጠውን ትኩረት ያመላክታል። የማዕድን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቅድሚያ የሚሰጠው አምራች ዘርፍ እየሆነ መጥቷል። በተለይም የወርቅ ማዕድን ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱን ቀጥሏል። ይህ ሀገራዊ ተነሳሽነት ሀብቶችን ከሀገር ውስጥ ማቀነባበሪያ፣ ከኢንዱስትሪ አቅምና ከዘላቂ እሴት ፈጠራ ጋር ለማስተሳሰር የመደመር መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እንደሚያሳይም ያመላክታል። የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካውም የወርቅ ጥራትን በማስጠበቅ ለማንጠርና ለውጭ ገበያ ዝግጁ ወደሆኑ ንጹሕ ምርት በመቀየር የጥራት ደረጃዎችን ለማሟላት ሁነኛ አቅም ይሆናል። የመደመር መንግሥትም ኢትዮጵያ ያሏትን ሀብቶች በጥሬው ለገበያ ከማቅረብ ይልቅ እሴት በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ የያዘውን ትክክለኛ የልማት አቅጣጫ ተጨባጭ ያደርገዋል። ፋብሪካውም ኢትዮጵያ በሀብቶቿ ላይ እሴት ጨምራ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ በያዘችው የኢኮኖሚ አቅጣጫ መሰረት የተገነባው ነው። ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ መጀመሩ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ግልጽና ትልቅ ርዕይ ማንገቡን ያመላክታል። በተለይም ለማዕድን ልማትና ዕድገት የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የተመዘገበውን ውጤት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ይህ ውጤታማ ተግባር በሌሎች ዘርፎችም ተጠናክሮ ይቀጥላል። ትልቅ ሕዝብ ይዛ፣ ታላቅ ርዕይ የሰነቀችው ኢትዮጵያም የተፈጥሮ ሀብቶቿን በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በኢንዱስትሪ በማልማት ለሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ መሰረት እየጣለች ይገኛል። የብሔራዊ የከበሩ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ መጀመርም ሃብትን በጥሬው ከመሸጥ ወደ እሴት ጨምሮ ማምረት ከዚያም ከሀብት ወደ ምርት፣ ከምርት ወደ ውጭ ንግድ ተወዳዳሪነት የሚያሸጋግር ጉልህ እርምጃ ነው። በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተፈጠረውን ዕድል በማስፋት ማዕድንን ጨምሮ የብዝኅ ኢኮኖሚ አዕማዶችን በማሳደግ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የውጭ ምንዛሬ ገቢንና የሀገርን የምርት አቅም ማጠናከር የዚህ ርዕይ ዋነኛ መገለጫዎች ናቸው። በርግጥም ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገርነትን ከትልቅ ሕዝብ፣ ጸጋዎችን ከልማት በማሰናሰል አቅምን ወደ ውጤትና ርዕይንም ወደ ተጨባጭ የብልፅግና መሰረት እየቀየረች ይገኛል።
ቼልሲ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ድል አስመዘገበ
Oct 10, 2026 87
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019(ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል። በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ ቼልሲ ቦርንማውዝን 5 ለ 1 ረትቷል። ጆአኦ ፔድሮ እና ጆርዳን ሄንደርሰን በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥሩ ሞርጋን ሮጀርስ ቀሪዋን ጎል ለሰማያዊዎቹ ከመረብ ላይ አሳርፏል። ኢቫቢልሰን የቦርንማውዝን የማስተዛዘኛ ግብ አስቆጥሯል። ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ቼልሲ በ10 ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 5ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦርንማውዝ በሶስት ነጥብ ከነበረበት 17ኛ ደረጃ ወደ 18ኛ ዝቅ በማለት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ገብቷል። ቦርንማውዝ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም። በሌሎች መርሐ ግብሮች ብራይተን ሰንደርላንድን 2 ለ 0፣ ኤፕስዊች ታውን ፉልሃምን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። አስቶንቪላ ከብሬንትፎርድ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ፖለቲካ
ለሰላም ለአብሮነትና ለልማት መጠናከር የድርሻችንን እንወጣለን - የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች
Oct 10, 2026 132
ሀዋሳ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ) ፦ለህዝቦች ዘላቂ ሰላምና አብሮነት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ በማስቀጠል የመንግስት የልማት ዕቅዶች እንዲሳኩ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ። በተያዘው ሳምንት መጀመሪያ በተካሄደው የመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የመንግስት ዋና ዋና የልማት ትኩረቶች ለህዝብ ይፋ መደረጋቸው የሚታወስ ነው። በዚህም ሰላም ማጽናት፣ መዋቅራዊ ኢኮኖሚያዊ ሽግግሩን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ፣ መሰረተ ልማትን ማስፋፋትና ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልማቶችን ማስቀጠል ከመንግስት የትኩረት ግቦች ይጠቀሳሉ። በመንግስት ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት፤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እንዲሳኩ ዘላቂ ሰላምና የህዝቦች አብሮነትን ማጠናከር ወሳኝ ነው። የልማትና የእድገት ግቦቹ በህዝብ ዘንድ ተስፋን የሰነቁ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በመደመር መንግስት የተያዙ ሁለንተናዊ የልማት ግቦች እንዲሳኩ ለዘላቂ ሰላምና ለህዝቦች አብሮነት አበክረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። ከሲዳማ ሀገር ሽማግሌዎቹ መካከል አቶ ሻምበል በላይ እንደገለጹት፣ አዲስ የተመሰረተው መንግስት የህዝቦችን አንድነትና ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ ያስቀመጣቸው ግቦች የሚሳኩት በህዝብ ትብብር ሲሰራ ነው፡፡ በየአካባቢው የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች በስኬት እንዲጠናቀቁ ሰላም ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም ከመጠበቅ ባለፈ አብሮነቱን እንዲያጠናከር ሚናዬን እወጣለሁ ብለዋል። ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ አቶ ቦና ቦቆንቻ በበኩላቸው፤ የመደመር መንግስት አዳዲስ የልማት አቅጣጫዎችና ግቦች ህዝቡ ተስፋን እንዲሰንቅ የሚያደርጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት ሰላም፣ ልማትና የህዝቦችን አንድነት ለማጠናከር የተጀመሩ ሥራዎች ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን አስታውሰው፣ በመደመር መንግስትም እነዚህ ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። የተያዙ የልማት ግቦች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ሰላም አስፈላጊ በመሆኑ ባህላዊ የሰላም እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን አንድነት የማጠናከር ሃላፊነታቸውን በቁርጠኝነት እንደሚወጡ አስታውቀዋል። በሲዳማ ብሔር ባህላዊ የግጭት አፈታትና የዳኝነት ሥርአት አስታራቂ ሽማግሌ የሆኑት ሻለቃ ጨመረ ሻልኬ በበኩላቸው፣ በቀጣይ ሀገራዊ ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ አቅጣጫዎች በመንግስት መቀመጣቸው የሚደገፍ ነው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት በከተማና በገጠር የተመዘገቡ የልማት ውጤቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በቀጣይም እነዚህ እንዲጠናከሩ ከመንግስት ጎን ሆነው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። በተለይ በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት ተጠቅመው ህዝብን ለሰላምና ለልማት ለማስተባበር ዝግጁ መሆናቸውን ነው የገለጹት
የፍርድ ቤቶች በዲጂታል የታገዘ አሰራርን መከተል የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል
Oct 10, 2026 155
ባህር ዳር፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ) ፦ የፍርድ ቤቶች በዲጂታል የታገዘ አሰራርን መከተል ተቋማዊ ነጻነትን በማስጠበቅ ቀልጣፋና ተአማኒ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት ማስቻሉን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምሕረት ገለጹ። ባለፉት ሦስት ዓመታት በዲጂታል አሰራር ታግዞ በተተገበረው የፍርድ ቤቶች ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላይ የመከረ ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል። በጉባኤው ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት እንደገለጹት፣ የፍርድ ቤቶች የትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላለፉት ሦስት ዓመታት ተግባራዊ ሆኗል። ፎኖተ ካርታው ለዲጂታል አሰራር ትኩረት በመስጠቱ ፍርድ ቤቶች ተቋማዊ ነጻነታቸውን አስጠብቀው ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋና በህዝብ ዘንድ እርካታን የፈጠረ የፍትህ አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻሉን ተናግረዋል። ይህም የዳኝነት ሥርአቱን ከነበረበት ኋላ ቀር አሰራር በማውጣት ዘመኑን የሚመጥን የህግና የፍትህ አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠት አበረታች ውጤት እንዲመዘገብ አድርጓል ብለዋል። በቀጣይም በሁሉም ክልሎችና አካባቢዎች የዲጂታል ሥርአት ዝርጋታን በማፋጠን ተቀራራቢ የሕግ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል። የዛሬው ሀገራዊ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤም ባለፉት ዓመታት የመጡ ለውጦችን አሻሽሎ ለማስቀጠልና የተስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጎልበት ያለመ ነው ብለዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አለምአንተ አግደው በበኩላቸው እንዳሉት፣ የክልሉ የዳኝነት ሥርዓት ዘመኑን የሚመጥን ለማድረግ በዲጂታላይዜሽን አሰራር ላይ በማተኮር እየተሰራ ይገኛል። በዚህም ዜጎች ፍትህ ፍለጋ መንከራተት ሳያስፈልጋቸው እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሰጡ የፍትህ አገልግሎቶችን በአካባቢያቸው ሆነው የሚያገኙበት ሥርአት መዘርጋቱን አስታውቀዋል። ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤም ድንበር የለሽ የሕግ አገልግሎት ለመስጠትና አንድ የጋራ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት የተያዘውን ግብ ለማሳካት ያስችላል ብለዋል። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ከሌሎች አቻ የሀገሪቱ የፍትህ ተቋማት ጋር በቅንጅትና በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው መድረክ ከሁሉም ክልሎች የመጡ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች ተሳትፈዋል።
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት ተዘጋጅተዋል - ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን
Oct 10, 2026 208
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው በሰጡት መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መንግስት ወደ አዘጋጀላቸው ማዕከላት ለመግባት ጥሪውን እየተጠባበቁ ነው። ስለሆነም የተሃድሶ ኮሚሽኑ ታጣቂዎችን በመቀበል ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል። ታጣቂዎች ኮሚሽኑ ባዘጋጃቸው የቅበላ ማዕከላት በመምጣት ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲገቡ ጥሪ አቅርቧል። መንግስት በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የቅበላ ማዕከላትን ማዘጋጀቱን ጠቁመው፤ በደቡባዊ ዞን በማይጨው እና መሆኒ ከተሞች፤ በደቡብ ምስራቅ ዞን በመቀሌ ከተማ በሚገኙ ማዕከላት እንዲገቡ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ ጠይቀዋል። በምስራቃዊ ዞን በአዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች፤ በማዕከላዊ ዞን አድዋ፣ አክሱም እና አቢአዲ ከተሞች እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ ዞን ሸሬ ከተማ ወደ አሉት የቅበላ ማዕከላት እንዲገቡ ጥሪ አድርገዋል። በዚህም ታጣቂዎቹን የሚቀበሉ መዘጋጀታቸውን ጠቁመው ታጣቂዎች ይህንን ዕድል በመጠቀም ወደ ሰላማዊ ሕይወት በመምጣት እና ራሱን እንዲያድንም ጥሪ አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ጽንፈኛውን ቡድን እየተቃወመ መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁንም ታጣቂዎቹ ወደ ተዘጋጁት ማዕከላት በመግባት ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ከማድረግ አኳያ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ የተያዙ እቅዶች ለታለመው ግብ እንዲበቁ በተደመረ አቅም መስራትና ማሳካት ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
Oct 10, 2026 149
ወላይታ ሶዶ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፡- በሁሉም ዘርፎች የተያዙ እቅዶች ለታለመው ግብ እንዲበቁ በተደመረ አቅም መስራትና ማሳካት ይገባል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባው የመንግስት እና የፓርቲ የቀጣይ መቶ ቀናት ዕቅድን በማስመልከት እየመከረ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፤ እቅዶች በአግባቡ ወደ መሬት ወርደው በአፈጻጸምና በተጨባጭ ውጤት በህዝብ ግምገማ ጭምር ውጤታቸውና ትግበራቸው የሚለካ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በቀጣይ 100 ቀናት ለመተግበር የተያዙ እቅዶች በሁሉም የአስተዳደር ዕርከን በወጥነት ለታለመው ግብ ስኬት በተደመረ አቅም መስራትና ማሳካት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለህዝብ በተገባው ቃል መሰረት የመልካም አስተዳደር፣ የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ እና ሌሎችም ጥያቄዎችን ለመመለስ መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል። የክልሉን እምቅ ሃብት በማልማት ለዜጎች የሚታይና የሚጨበጥ ጥቅም እንዲሰጥ በየደረጃው ያለው አመራር በቁርጠኝነት መስራት የሚጠበቅበት መሆኑንም አስገንዝበዋል።
መንግሥት ያስቀመጣቸውን የሰላምና የልማት አቅጣጫዎች ለማሳካት የበኩላችንን እንወጣለን - አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች
Oct 10, 2026 206
ሸገር፣ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ) ፦ በመንግሥት የተቀመጡ የሰላምና የልማት አቅጣጫዎችን ለማሳካት በሚደረግ ጥረት የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሸገር ከተማ አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች ገለጹ። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች፤ መንግሥት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚጠበቅባቸውን ድርሻ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ከአባ ገዳዎች መካከል አባ ገዳ ቶሊ ኤግዱ እንደገለጹት፤ መንግሥት የሰላምና የልማት አቅጣጫዎችን ለማሳካት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ ናቸው። በተለይም በገዳ ሥርዓት እሴቶች መሠረት ለትውልዱ ፍቅርን፣ አንድነትንና ሰላምን በማስተማር ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ማኅበረሰቡም ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ ሀገሪቱን ወደ ተሻለ የልማትና የዕድገት ደረጃ ለማሸጋገር በጋራ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል። ሃደ ሲንቄ ካባ በያና በበኩላቸው፤ ሰላም የሁሉም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገቶች መሠረት መሆኑን ጠቁመው፣ "የጋራ ሀገር ስላለን ከመንግሥት ጎን በመሆን ሰላምን ማስፈንና ልማትን ማስቀጠል ይጠበቅብናል" ብለዋል። ሕዝቡ ሰላሙን በመጠበቅ ልማትን ለማፋጠን በሚያከናውናቸው ተግባራት የድርሻቸውን እንደሚወጡ አመልክተዋል። አባ ገዳ አብዮት ድሪባ በበኩላቸው፤ መንግሥት የያዛቸው የሰላምና የልማት እቅዶች እንዲሳኩ ህዝቡ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ በመምከርና በማስተማር ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ። መንግስት ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በሚያደርገው ጥረት ህዝቡ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ አመልክተዋል።
የሀገርን ልማት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ሁሉም ዜጋ በንቃት መሳተፍ አለበት
Oct 10, 2026 203
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠንና ሰላምን ለማጽናት በሚደረገው ጥረት ሁላችንም በተሰማራንበት የሙያ መስክ በንቃት መሳተፍ ይገባናል ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ሰባተኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ በምክር ቤቶቹ የጋራ መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላምና ተረጋግቶ የመኖርን ዋጋ በጥልቅ የሚያውቅ፣ የጦርነትን አጉዳይነት በጉልህ የሚረዳና የሚጠየፍ መሆኑን ጠቅሰዋል። የታላቅ ሀገርና የነባር ስልጣኔ ባለቤት የሆነ ህዝብ መገለጫ ሀገርን ማጽናት፣ ሉዓላዊነትን ማስከበርና ሰላምን መጠበቅ በመሆኑ የተጀመሩት የልማት ጉዞዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በስራና በትጋት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል። የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ የመንግስት ተግባር ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ ሀላፊነት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንኑ ጥረት ጠብቆ የማቆየት፣ የማስቀጠል እና የማሻሻል የጋራ ሀላፊነት መሆኑን አመልክተዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን በማንሳት የሚታዩ ተጨባጭ ለውጦች ለሀገር እድገት መሠረት እየጣሉ ናቸው። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ጉደታ ደንደነ፤ የልማት ሥራዎቹ ተጨባጭ ለውጦችን አሳይተዋል። በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ መሠረተ ልማቶች አዲስ አበባ በከፍተኛ የለውጥ ጎዳና ላይ መሆኗንም ነው የሚያንጸባርቁት። የቢሸፍቱ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ሁሉም ዜጋ ከመንግሥት ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባውም ጠቁመዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አድማሱ ዱላ መንግሥት በልማት ሥራዎች ላይ ውጤታማ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገልጸው፤ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሕብረተሰቡ ከመንግሥት ጋር በመተባበር መትጋት እንዳለበት ተናግረዋል። ለሀገር ዕድገት ልጆችን ከማስተማርና ከመምከር ጀምሮ በሁሉም ዘርፍ የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ራሔል መንገሻ ናቸው። ለተጀመሩ የልማት ሥራዎች መሳካት ከከተማ አስተዳደሩና ከመንግሥት ጎን በመቆም በጋራ መሥራት እንደሚገባም አብራርተዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ጥላሁን ዋቅጅራ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ በልማት ጉዞ ላይ ትገኛለች። በተለይም ቀደም ሲል በወንዝ ዳርቻ የልማት እጥረት የነበረባቸው አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት መልካቸውን ቀይረው መታየታቸው አበረታች ነው። ወይዘሮ ዛህራ ኑረዲን፤ በአሁኑ ወቅት እየተከናወነ በሚገኘው ልማት ላይ እያንዳንዱ ዜጋ ባለው አቅም መሳተፍ እንደሚጠበቅበት ጠቁመው፤ ለተጀመሩ ፕሮጀክቶች መፋጠን የጎላ ሚና ሊጫወት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ፖለቲካ
ለሰላም ለአብሮነትና ለልማት መጠናከር የድርሻችንን እንወጣለን - የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች
Oct 10, 2026 132
ሀዋሳ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ) ፦ለህዝቦች ዘላቂ ሰላምና አብሮነት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ በማስቀጠል የመንግስት የልማት ዕቅዶች እንዲሳኩ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ። በተያዘው ሳምንት መጀመሪያ በተካሄደው የመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የመንግስት ዋና ዋና የልማት ትኩረቶች ለህዝብ ይፋ መደረጋቸው የሚታወስ ነው። በዚህም ሰላም ማጽናት፣ መዋቅራዊ ኢኮኖሚያዊ ሽግግሩን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ፣ መሰረተ ልማትን ማስፋፋትና ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልማቶችን ማስቀጠል ከመንግስት የትኩረት ግቦች ይጠቀሳሉ። በመንግስት ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት፤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እንዲሳኩ ዘላቂ ሰላምና የህዝቦች አብሮነትን ማጠናከር ወሳኝ ነው። የልማትና የእድገት ግቦቹ በህዝብ ዘንድ ተስፋን የሰነቁ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በመደመር መንግስት የተያዙ ሁለንተናዊ የልማት ግቦች እንዲሳኩ ለዘላቂ ሰላምና ለህዝቦች አብሮነት አበክረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። ከሲዳማ ሀገር ሽማግሌዎቹ መካከል አቶ ሻምበል በላይ እንደገለጹት፣ አዲስ የተመሰረተው መንግስት የህዝቦችን አንድነትና ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ ያስቀመጣቸው ግቦች የሚሳኩት በህዝብ ትብብር ሲሰራ ነው፡፡ በየአካባቢው የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች በስኬት እንዲጠናቀቁ ሰላም ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም ከመጠበቅ ባለፈ አብሮነቱን እንዲያጠናከር ሚናዬን እወጣለሁ ብለዋል። ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ አቶ ቦና ቦቆንቻ በበኩላቸው፤ የመደመር መንግስት አዳዲስ የልማት አቅጣጫዎችና ግቦች ህዝቡ ተስፋን እንዲሰንቅ የሚያደርጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት ሰላም፣ ልማትና የህዝቦችን አንድነት ለማጠናከር የተጀመሩ ሥራዎች ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን አስታውሰው፣ በመደመር መንግስትም እነዚህ ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል። የተያዙ የልማት ግቦች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ሰላም አስፈላጊ በመሆኑ ባህላዊ የሰላም እሴቶችን በማጎልበት የህዝብን አንድነት የማጠናከር ሃላፊነታቸውን በቁርጠኝነት እንደሚወጡ አስታውቀዋል። በሲዳማ ብሔር ባህላዊ የግጭት አፈታትና የዳኝነት ሥርአት አስታራቂ ሽማግሌ የሆኑት ሻለቃ ጨመረ ሻልኬ በበኩላቸው፣ በቀጣይ ሀገራዊ ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ አቅጣጫዎች በመንግስት መቀመጣቸው የሚደገፍ ነው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት በከተማና በገጠር የተመዘገቡ የልማት ውጤቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በቀጣይም እነዚህ እንዲጠናከሩ ከመንግስት ጎን ሆነው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። በተለይ በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት ተጠቅመው ህዝብን ለሰላምና ለልማት ለማስተባበር ዝግጁ መሆናቸውን ነው የገለጹት
የፍርድ ቤቶች በዲጂታል የታገዘ አሰራርን መከተል የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል
Oct 10, 2026 155
ባህር ዳር፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ) ፦ የፍርድ ቤቶች በዲጂታል የታገዘ አሰራርን መከተል ተቋማዊ ነጻነትን በማስጠበቅ ቀልጣፋና ተአማኒ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት ማስቻሉን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምሕረት ገለጹ። ባለፉት ሦስት ዓመታት በዲጂታል አሰራር ታግዞ በተተገበረው የፍርድ ቤቶች ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላይ የመከረ ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል። በጉባኤው ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት እንደገለጹት፣ የፍርድ ቤቶች የትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላለፉት ሦስት ዓመታት ተግባራዊ ሆኗል። ፎኖተ ካርታው ለዲጂታል አሰራር ትኩረት በመስጠቱ ፍርድ ቤቶች ተቋማዊ ነጻነታቸውን አስጠብቀው ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋና በህዝብ ዘንድ እርካታን የፈጠረ የፍትህ አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻሉን ተናግረዋል። ይህም የዳኝነት ሥርአቱን ከነበረበት ኋላ ቀር አሰራር በማውጣት ዘመኑን የሚመጥን የህግና የፍትህ አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠት አበረታች ውጤት እንዲመዘገብ አድርጓል ብለዋል። በቀጣይም በሁሉም ክልሎችና አካባቢዎች የዲጂታል ሥርአት ዝርጋታን በማፋጠን ተቀራራቢ የሕግ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል። የዛሬው ሀገራዊ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤም ባለፉት ዓመታት የመጡ ለውጦችን አሻሽሎ ለማስቀጠልና የተስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጎልበት ያለመ ነው ብለዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አለምአንተ አግደው በበኩላቸው እንዳሉት፣ የክልሉ የዳኝነት ሥርዓት ዘመኑን የሚመጥን ለማድረግ በዲጂታላይዜሽን አሰራር ላይ በማተኮር እየተሰራ ይገኛል። በዚህም ዜጎች ፍትህ ፍለጋ መንከራተት ሳያስፈልጋቸው እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሰጡ የፍትህ አገልግሎቶችን በአካባቢያቸው ሆነው የሚያገኙበት ሥርአት መዘርጋቱን አስታውቀዋል። ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤም ድንበር የለሽ የሕግ አገልግሎት ለመስጠትና አንድ የጋራ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት የተያዘውን ግብ ለማሳካት ያስችላል ብለዋል። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ከሌሎች አቻ የሀገሪቱ የፍትህ ተቋማት ጋር በቅንጅትና በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው መድረክ ከሁሉም ክልሎች የመጡ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶች ተሳትፈዋል።
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት ተዘጋጅተዋል - ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን
Oct 10, 2026 208
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ መግባት እንዲችሉ በተለያዩ አካባቢዎች የቅበላ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ መኩሪያው በሰጡት መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መንግስት ወደ አዘጋጀላቸው ማዕከላት ለመግባት ጥሪውን እየተጠባበቁ ነው። ስለሆነም የተሃድሶ ኮሚሽኑ ታጣቂዎችን በመቀበል ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል። ታጣቂዎች ኮሚሽኑ ባዘጋጃቸው የቅበላ ማዕከላት በመምጣት ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲገቡ ጥሪ አቅርቧል። መንግስት በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የቅበላ ማዕከላትን ማዘጋጀቱን ጠቁመው፤ በደቡባዊ ዞን በማይጨው እና መሆኒ ከተሞች፤ በደቡብ ምስራቅ ዞን በመቀሌ ከተማ በሚገኙ ማዕከላት እንዲገቡ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴር ጄኔራል ደርቤ ጠይቀዋል። በምስራቃዊ ዞን በአዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች፤ በማዕከላዊ ዞን አድዋ፣ አክሱም እና አቢአዲ ከተሞች እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ ዞን ሸሬ ከተማ ወደ አሉት የቅበላ ማዕከላት እንዲገቡ ጥሪ አድርገዋል። በዚህም ታጣቂዎቹን የሚቀበሉ መዘጋጀታቸውን ጠቁመው ታጣቂዎች ይህንን ዕድል በመጠቀም ወደ ሰላማዊ ሕይወት በመምጣት እና ራሱን እንዲያድንም ጥሪ አቅርበዋል። በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ጽንፈኛውን ቡድን እየተቃወመ መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁንም ታጣቂዎቹ ወደ ተዘጋጁት ማዕከላት በመግባት ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ከማድረግ አኳያ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ የተያዙ እቅዶች ለታለመው ግብ እንዲበቁ በተደመረ አቅም መስራትና ማሳካት ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
Oct 10, 2026 149
ወላይታ ሶዶ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፡- በሁሉም ዘርፎች የተያዙ እቅዶች ለታለመው ግብ እንዲበቁ በተደመረ አቅም መስራትና ማሳካት ይገባል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባው የመንግስት እና የፓርቲ የቀጣይ መቶ ቀናት ዕቅድን በማስመልከት እየመከረ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፤ እቅዶች በአግባቡ ወደ መሬት ወርደው በአፈጻጸምና በተጨባጭ ውጤት በህዝብ ግምገማ ጭምር ውጤታቸውና ትግበራቸው የሚለካ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በቀጣይ 100 ቀናት ለመተግበር የተያዙ እቅዶች በሁሉም የአስተዳደር ዕርከን በወጥነት ለታለመው ግብ ስኬት በተደመረ አቅም መስራትና ማሳካት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለህዝብ በተገባው ቃል መሰረት የመልካም አስተዳደር፣ የመሠረተ ልማትና የኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ እና ሌሎችም ጥያቄዎችን ለመመለስ መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል። የክልሉን እምቅ ሃብት በማልማት ለዜጎች የሚታይና የሚጨበጥ ጥቅም እንዲሰጥ በየደረጃው ያለው አመራር በቁርጠኝነት መስራት የሚጠበቅበት መሆኑንም አስገንዝበዋል።
መንግሥት ያስቀመጣቸውን የሰላምና የልማት አቅጣጫዎች ለማሳካት የበኩላችንን እንወጣለን - አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች
Oct 10, 2026 206
ሸገር፣ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ) ፦ በመንግሥት የተቀመጡ የሰላምና የልማት አቅጣጫዎችን ለማሳካት በሚደረግ ጥረት የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሸገር ከተማ አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች ገለጹ። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች፤ መንግሥት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚጠበቅባቸውን ድርሻ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ከአባ ገዳዎች መካከል አባ ገዳ ቶሊ ኤግዱ እንደገለጹት፤ መንግሥት የሰላምና የልማት አቅጣጫዎችን ለማሳካት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ ናቸው። በተለይም በገዳ ሥርዓት እሴቶች መሠረት ለትውልዱ ፍቅርን፣ አንድነትንና ሰላምን በማስተማር ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ማኅበረሰቡም ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ ሀገሪቱን ወደ ተሻለ የልማትና የዕድገት ደረጃ ለማሸጋገር በጋራ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል። ሃደ ሲንቄ ካባ በያና በበኩላቸው፤ ሰላም የሁሉም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገቶች መሠረት መሆኑን ጠቁመው፣ "የጋራ ሀገር ስላለን ከመንግሥት ጎን በመሆን ሰላምን ማስፈንና ልማትን ማስቀጠል ይጠበቅብናል" ብለዋል። ሕዝቡ ሰላሙን በመጠበቅ ልማትን ለማፋጠን በሚያከናውናቸው ተግባራት የድርሻቸውን እንደሚወጡ አመልክተዋል። አባ ገዳ አብዮት ድሪባ በበኩላቸው፤ መንግሥት የያዛቸው የሰላምና የልማት እቅዶች እንዲሳኩ ህዝቡ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ በመምከርና በማስተማር ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ። መንግስት ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በሚያደርገው ጥረት ህዝቡ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ አመልክተዋል።
የሀገርን ልማት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ሁሉም ዜጋ በንቃት መሳተፍ አለበት
Oct 10, 2026 203
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠንና ሰላምን ለማጽናት በሚደረገው ጥረት ሁላችንም በተሰማራንበት የሙያ መስክ በንቃት መሳተፍ ይገባናል ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ሰባተኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ በምክር ቤቶቹ የጋራ መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላምና ተረጋግቶ የመኖርን ዋጋ በጥልቅ የሚያውቅ፣ የጦርነትን አጉዳይነት በጉልህ የሚረዳና የሚጠየፍ መሆኑን ጠቅሰዋል። የታላቅ ሀገርና የነባር ስልጣኔ ባለቤት የሆነ ህዝብ መገለጫ ሀገርን ማጽናት፣ ሉዓላዊነትን ማስከበርና ሰላምን መጠበቅ በመሆኑ የተጀመሩት የልማት ጉዞዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በስራና በትጋት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል። የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ የመንግስት ተግባር ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ ሀላፊነት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንኑ ጥረት ጠብቆ የማቆየት፣ የማስቀጠል እና የማሻሻል የጋራ ሀላፊነት መሆኑን አመልክተዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን በማንሳት የሚታዩ ተጨባጭ ለውጦች ለሀገር እድገት መሠረት እየጣሉ ናቸው። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ጉደታ ደንደነ፤ የልማት ሥራዎቹ ተጨባጭ ለውጦችን አሳይተዋል። በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ መሠረተ ልማቶች አዲስ አበባ በከፍተኛ የለውጥ ጎዳና ላይ መሆኗንም ነው የሚያንጸባርቁት። የቢሸፍቱ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ሁሉም ዜጋ ከመንግሥት ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባውም ጠቁመዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አድማሱ ዱላ መንግሥት በልማት ሥራዎች ላይ ውጤታማ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገልጸው፤ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሕብረተሰቡ ከመንግሥት ጋር በመተባበር መትጋት እንዳለበት ተናግረዋል። ለሀገር ዕድገት ልጆችን ከማስተማርና ከመምከር ጀምሮ በሁሉም ዘርፍ የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ራሔል መንገሻ ናቸው። ለተጀመሩ የልማት ሥራዎች መሳካት ከከተማ አስተዳደሩና ከመንግሥት ጎን በመቆም በጋራ መሥራት እንደሚገባም አብራርተዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ጥላሁን ዋቅጅራ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ በልማት ጉዞ ላይ ትገኛለች። በተለይም ቀደም ሲል በወንዝ ዳርቻ የልማት እጥረት የነበረባቸው አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት መልካቸውን ቀይረው መታየታቸው አበረታች ነው። ወይዘሮ ዛህራ ኑረዲን፤ በአሁኑ ወቅት እየተከናወነ በሚገኘው ልማት ላይ እያንዳንዱ ዜጋ ባለው አቅም መሳተፍ እንደሚጠበቅበት ጠቁመው፤ ለተጀመሩ ፕሮጀክቶች መፋጠን የጎላ ሚና ሊጫወት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ማህበራዊ
በአፋር ክልል ለአረጋዊያን የሚደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል
Oct 10, 2026 115
ሠመራ፤ መሰከረም 30/2019(ኢዜአ)፡-በአፋር ክልል የአገር ባለውለታ የሆኑ አረጋዊያንን የመደገፍና የመንከባከብ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ። "እንክብካቤና ዘላቂ ደህንነት ለአረጋውያን ሰላማዊ ሕይወት" በሚል መሪ ሐሳብ በአፋር ክልል ደረጃ የዓለም የአረጋውያን ቀን ዛሬ በሰመራ ሎጊያ ከተማ ተከብሯል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ወይዘሮ አሲያ ከማል እንዳሉት፣ አረጋውያን በጉብዝና ጊዜያቸው ለአገርና ለወገን ጠቃሚ ተግባራትን በማከናወን ሚናቸውን ተወጥተዋል። ዛሬ በእርጅና ጊዜያቸው የሁሉንም ድጋፍና እገዛ እንደሚሹ ገልጸው፣ በክልሉ ህብረተሰቡንና የተለያዩ አካላትን በማስተባበር ለአረጋውያን የሚደረገው ድጋፍና እንክብካቤ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ለዚህም ህብረተሰቡና ሌሎች አጋር አካላት የሚያደርጓቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አስገንዝበዋል። በዛሬው ዕለት በክልሉ በሚገኙ ከተሞች ከተውጣጡ የአረጋውያን ማህበራት ጋር በመሆን በዓሉ መከበሩን የገለፁት ደግሞ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የማህበራዊ ዘርፍ ምክትል ኀላፊ ወይዘሮ ነስሮ ኡዳ ናቸው። የአረጋዊያንን ቀን ምክንያት በማድረግ በአዋሽ ሰባት ከተማ ለሚገኘው "አቡነ አባቢ የአረጋውያን መርጃ ድርጅት" እና በአዋሽ አርባ ከተማ ለሚገኘው "አቡነ ዮናስ የአረጋውያንና ሕፃናት መርጃ ማዕከል" ለእያንዳንዳቸው 100 ሺህ ብር መለገሱን ገልጸዋል። በቀጣይም ለአረጋዊያን በተለያየ መልክ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥል ብለዋል። የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኀላፊ ወይዘሮ ራሩባ መሐመድ በበኩላቸው በዛሬው ዕለት በከተማው ቤት ለቤት በመሄድ አቅመ ደካማ አረጋዊያንን መደገፋቸውን አንስተዋል። በተመሳሳይ የዓለም የአረጋዊያን ቀን ከሰመራ ለጎጊያ ከተማ በተጨማሪ በክልሉ አሚበራ፣ አብአላ፣ ጎሊና፣ ደዌ እና ሲባቢ ወረዳዎችም ዛሬ ተከብሯል። ቀኑ የተከበረው በዓለም ለ36ኛ ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ35ኛ ጊዜ መሆኑም ታውቋል።
ለመልካም ሕይወት- የአእምሮ ጤንነት
Oct 10, 2026 101
አእምሮ የሰው ልጅ የሚያስብበት፣ ስሜቱን የሚረዳበት፣ በራስ ህይወትም ይሁን በተለያዩ አጋጣሚዎች በሌሎች ላይ የሚወስንበት በመሆኑ የአይምሮ ጤና ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይነገራል። የአእምሮ ጤና ሲጎዳ እነዚህና ተያያዥ ችግሮችን የሚያመጣ ብሎም የሥራ አፈጻጸም፣ የቤተሰብ ግንኙነት፣ የትምህርት ተሳትፎና የዕለት ተዕለት ኑሮ ሊነካ ይችላል። ስለዚህ ለአእምሮ ጤና የሚሰጠው ትኩረት እንደ አካላዊ ጤና ሁሉ ተመሳሳይ አስፈላጊነት ሊኖረው እንደሚገባ ይታመናል። በመሆኑም እ.ኤ.አ. በየዓመቱ ጥቅምት 10 የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ሆኖ ይከበራል። እለቱ የሚከበረው ለአእምሮ ጤና ተገቢውን ትኩረት ለመስጠት፣ ስለ ህመሙ በቂ ግንዛቤ እንዲኖር ለማድረግና ለታማሚዎች የድጋፍና እንክብካቤ ስራን ለማሳደግ መሆኑ ይነገራል። የአእምሮ ጤና ችግር ሲነሳ በአንዳንዶች ዘንድ የተሳሳቱ አመለካከቶችና ግንዛቤዎች ይስተዋላሉ። የችግሩን መንስኤ ከድክመት፣ ከግል ባህሪ ወይም ከፈቃደኝነት ጉድለት ጋር በማያያዝ የተሳሳተ ትርጉም የሚሰጥበት ሁኔታ እውነታውን አያመላክትም። የአእምሮ ጤና ችግር ከሥነ-ልቦናዊና ከማኅበራዊ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ሊከሰት የሚችልበት አጋጣሚም የሰፋ ነው። በውጥረትና የሕይወት ፈተናዎች ውስጥ ለረጅም ጊዜ መዝለቅ፣ የሚወዱትን ሰው በማጣት በሀዘን ውስጥ ለረጅም ጊዜ መዝለቅ፣ ግጭት፣ የኢኮኖሚ ችግርና ሌሎችም ምክንያቶች የህመሙ መንስኤዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ከመጠን በላይ ጭንቀትና ድብርት፣ ቀድሞ በደስታ ይሳተፍባቸው የነበሩ ነገሮች ላይ ፍላጎት ማጣት፣ የእንቅልፍ ለውጥ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም መጨመር፣ የትኩረት ችግርና የተስፋ መቁረጥ ስሜት በተደጋጋሚ ከታዩ ለአይምሮ ህመም ሊያጋልጡ ይችላሉ። የአእምሮ ጤና ችግር ውጤታማ የሆኑ የሥነ-ልቦና ሕክምናዎችና ሌሎች የሕክምና አማራጮች ያሉት ስለመሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት ይመክራል። የምክር አገልግሎት፣ የሥነ-ልቦና ሕክምና፣ በሀኪም ትእዛዝ መድኃኒት መውሰድና የማኅበራዊ ድጋፍ አገልገሎቶች መፍትሄዎች መሆናቸውንም ያመላክታል። በመሆኑም የአእምሮ ጤና ጉዳይ የጤና ተቋማት ብቻ ኃላፊነት ባለመሆኑ የቤተሰብ፣ የትምህርት ቤት፣ የሥራ ቦታ፣ የማህበራዊ ተቋማት፣ የሚዲያና ሌሎችም ተሳትፎ ማደግ እንዳለበት ይመከራል። በዚህ ችግር ውስጥ ያለን ሰው ስሜቱን ማክበር፣ ለባለሙያ እርዳታ እንዲያገኝ ማበረታታትና ከማኅበራዊ ግንኙነት እንዳይገለል ማድረግም አስፈላጊ ነው። የችግሩ ሰለባ የሆነን ሰው ማግለልና መሳለቅ ወይም ችግሩን በደካማነት መተርጎም ተገቢነት የለውም። በመሆኑም የዘንድሮው የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን የአእምሮ ጤና ችግር አጋጥሟቸው የነበሩ ሰዎችን ተሞክሮ ማጋራትና ለህመሙ ትኩረት በሚሰጥ መልኩ እየተከበረ ይገኛል። በኢትዮጵያም የአእምሮ ጤናን ለማሻሻል የግንዛቤ ማሳደግ፣ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋት፣ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን አቅም ማጠናከርና የማኅበረሰብ ድጋፍን ማሳደግ አስፈላጊ ይሆናል። በተለይም ከከተማ ርቀው በገጠር የሚኖሩ ህሙማን የአእምሮ ጤና ምርመራና የሕክምና አገልገሎት እንዲያገኙ መደገፍና ማበረታታት ይገባል። አእምሮን የመንከባከብ ጉዳይ በሕክምና ብቻ ባለመሆኑ በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ አዘውትሮ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጤናማ ምግብ መመገብ፣ ከቤተሰብና ከጓደኞች ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር፣ የዕረፍት ጊዜ መመደብና የውጥረት ምክንያቶችን በተቻለ መጠን መቀነስ እንደሚገባ ይመከራል። እነዚህ ልምዶች ግን በዘላቂነት የባለሙያ ሕክምናን የሚተኩ ባለመሆናቸው ተገቢውን ሕክምና ማድረግ የግድ ይላል። የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን በዓመት አንድ ቀን የሚዘከር ብቻ ሳይሆን በየዕለቱ በተግባር ሊተረጎም የሚገባ ማኅበራዊ ጉዳይ መሆን አለበት። ለአእምሮ ጤና ትኩረት መስጠት፣ ችግሮችን ቀድሞ ማወቅ፣ የሕክምና አገልግሎትን ማስፋት የተጎጂዎችን ክብር መጠበቅ እንደሚገባ ይመከራል።
በክልሉ በህገወጥ የመድኃኒት እና የምግብ ምርቶች ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ ይቀጥላል
Oct 10, 2026 78
ጂንካ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጥራትና ደህንነታቸውን የጠበቁ የምግብና የመድኃኒት ምርቶችን ለህብረተሰቡ ለማቅረብ የክትትልና የቁጥጥር ሥራን አጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የጤና ቢሮው ምክትል ኃላፊና የምግብ፣ መድኃኒት፣ ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ቁጥጥር ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ሶንቆ እንዳሉት፣ በክልሉ የቁጥጥር ስርዓትን በማጠናከር ጥራትና ደህንነታቸው የተጠበቀ የምግብና የመድኃኒት ምርቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን እየተሰራ ነው። ቢሮው የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መዲኃኒቶችና የተሻጉ ምግቦች፣ ባዕድ ነገር የተቀላቀለባቸው ምግቦች እንዲሁም ህጋዊ ምዝገባ ባልተደረገባቸው መድኋኒቶች ላይ የተጠናከረ የቁጥጥርና የክትትል ሥራ እንደሚያከናውን ገልጸዋል። በዚህም በክልሉ በሚገኙ ከ2ሺህ 300 በላይ የግል መድኃኒት ቤቶች ላይ በየጊዜው ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደረግ ተናግረዋል። በተያዘው በጀት ዓመቱ ያለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ቢሮው ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻና ቁጥጥር ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ህገ ወጥ የመድሀኒት ምርቶች እና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው የታሸጉ ምግቦች እንዲወገዱ ማድረጉን ገልፀዋል። ህገወጥ ድርጊቱን በፈጸሙ የግል መድሃኒት ቤቶች እንደጥፋት መጠናቸው የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የመስጠት፣ የማሸግ እና በህግ ተጠያቂ የማድረግ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም ዳይሬክተሩ አቶ ዮሴፍ አመልክተዋል። በህገወጥ የመድሃኒት ቁጥጥር ሥራው የህብረተሰቡ ተሳትፎ የላቀ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመው፣ በሦስት ወራት ውስጥ ብቻ 174 ጥቆማዎች ከሕብረተሰቡ መድረሱን ገልጸዋል፡፡ ፈዋሽነታቸውና ጤንነታቸው ያልተረጋገጡ የመድኃኒትና የምግብ ምርቶች በህብረተሰቡ እና በሕጻናት ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ መላው የክልሉ ህዝብ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
ኢኮኖሚ
የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር ሀገራዊ እድገትን እያፈጠነ ነው
Oct 10, 2026 66
ዲላ፣ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር ፈጣን እድገት እንዲመዘገብ ማስቻሉን የምጣኔ ሃብት ምሁራን ገለጹ። በዲላ ዩኒቨርሲቲ "ወቅታዊ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጉዳዮች እና እድገቶች" በሚል ርዕስ አውደ ጥናት ተካሂዷል። በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙ የዘርፉ ምሁራን እንዳሉት የተሟላ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ እውን መሆን ፈጣን ሁለንተናዊ እድገት እንዲመዘገብ አስችሏል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚ ትምህርት ክፍል ተመራማሪና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐና ለኢዜአ እንዳሉት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ብዝሃ ዘርፎችን በማነቃቃት የሀገሪቱን የእድገት ጉዞ እያፋጠነ ነው። በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ በዋጋ ንረት ሲከሰቱ የነበሩ ተግዳሮቶችን በመፍታት የተሟላ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ትግበራን ውጤታማ እያደረገው መምጣቱን ጠቁመዋል። የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያው እንዲመራ መደረጉም የዋጋ ግሽበትን በማረጋጋት የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ማሳደጉን ፕሮፌሰር ጣሰው አክለው ገልጸዋል። የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራን ተከትሎ የመጣውን የኢኮኖሚ እድገት በውጫዊ ተጽኖ አጣብቂኝ ውስጥ እንዳይገባ ማህበሩ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ የተለያዩ ጥናቶችን በማከናወን ለፖሊሲ ግብዓትነት እያዋለው ነው ብለዋል። የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ትግበራው የሀገርን ጸጋዎች በአግባቡ ለይቶ ለልማት በማዋል የነበሩ ክፍተቶችን የቀረፈ ነው ያሉት ደግሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢኮኖሚ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ታምራት በየነ (ዶ/ር ) ናቸው። በተለይ በራሳችን መንገድ ችግሮችን የመፍታት ባህልን በመገንባት በኩል የተሰሩ ሥራዎች ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የዋጋ ግሽበትንና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከማስተካከል ባለፈ በዲጀታል ፋይናንስ ከዓለም እኩል ለመራመድ ምቹ መደላድል መፍጠሩን የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ገልጸዋል። በዘርፉ የተስተዋለውን እድገትና የገጠመውን ተግዳሮት በምርምር በመለየት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙን ውጤታማነት አጠናክሮ ለማስቀጠል በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውንም ታምራት (ዶ/ር) አንስተዋል። በአውደ ጥናቱ ላይ ሦስት የምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበርና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአቅም ግንባታና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በጋራ መስራት የሚያስችላቸው የሦስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድም ተፈራርመዋል።
በኦሮሚያ ክልል በበጋ መስኖ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ይለማል
Oct 10, 2026 76
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮ የበጋ መስኖ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መግባቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ በሪሶ ፈይሳ ለኢዜአ እንደገለጹት ዘንድሮ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በስፋት ይካሄዳል። በክልሉ ዘንድሮ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ በበጋ መስኖ ስንዴ በማልማት ከ160 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል። ከታቀደው መሬት እስካሁን በተደረገ እንቅስቃሴ 400 ሺህ ሄክታር መዘጋጀቱን ጠቁመው ከዚህም ውስጥ 130 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የስንዴ ልማት ሥራዎች በሰፊው እና በተቀናጀ መልኩ ሲከናወኑ መቆየቱን ገልጸው ፣በዚህም አርሶ አደሩ ልምድና ክህሎት በማግኘት ከፍተኛ ተነሳሽነት እየጨመረ ነው ብለዋል። የመስኖ የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለውጪ ገበያ በማቅረብ የኢኮኖሚ አቅምን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው አቶ በሪሶ አብራርተዋል። ልማቱ የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል ባለፈ ለኢኮኖሚ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የመስኖ ልማቱ የሚከናወነው በገጽ እና በከርሰ ምድር የውሃ አማራጮች በመሆኑ፣ ለአርሶ አደሩ በርካታ የውሃ መሳቢያ ፓምፖች መቅረባቸውን አቶ በሪሶ አመልክተዋል ። ከስንዴ ልማት ጎን ለጎን በመደበኛ የመስኖ ልማት መርሃ ግብር ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ በማልማት ገበያን ለማረጋጋት ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል። ለልማቱ ስኬታማነት ለአርሶ አደሩ አስፈላጊው የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠና፣ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ጠቁመው ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በበቂ ሁኔታ መቅረቡን ገልጸዋል።
ማዕከሉ በምርምር ያወጣቸው የሩዝ ዝርያዎች የዝናብ እጥረትና በሽታን ተቋቁመው ከፍተኛ ምርት እያስገኙ ነው
Oct 10, 2026 91
ገንዳውኃ፣ መስከረም 30/2019(ኢዜአ)፡-የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር ያወጣቸው የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎች የዝናብ እጥረት እና በሽታን ተቋቁመው ከፍተኛ ምርት እያስገኙ መሆኑን በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ። የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል በመተማ ንዑስ ማዕከል እያካሄደ ያለውን የሩዝ ዘር ብዜትና የሰብል ልማት ለአርሶ አደሮች፣ አመራሮችና የግብርና ባለሙያዎች ዛሬ አስጎብኝቷል። በልማቱ እየተሳተፉ ያሉት የመተማ ወረዳ አርሶ አደር ጋሻው ሙሀመድ እንደገለጹት፤ ማዕከሉ ያወጣቸው "ፎገራ-1" እና "አዝመራ" የተባሉ የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎች ለአካባቢው ስነ ምህዳር ተስማሚ ናቸው። የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎቹ የዝናብ እጥረትን፣ በሽታን እና ሌሎች ችግሮችን ተቋቁመው ከፍተኛ ምርትየሚያስገኙ በመሆኑ የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። ሌላኛው አርሶ አደር አህመድ ይመር በበኩላቸው፣ የሩዝ ልማቱ ከቤት ውስጥ የምግብ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ሃብት ለመፍጠር እያስቻላቸው መሆኑን ተናግረዋል። በጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የመተማ ንዑስ ማዕከል አስተባባሪና ሰብል ተመራማሪ አቶ ግዛት አዱኛ፣ ማዕከሉ አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችና የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማስተዋወቅ ሥራ ላይ ማተኮሩን ገልጸዋል፡፡ በተለይም በአንድ ሄክታር እስከ 55 ኩንታል ምርት የሚሰጡት የፎገራ-1 እና አዝመራ የተባሉ የሩዝ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት በምግብ ራሱን ከመቻል ያለፈ ለገበያ በማቅረብ ትርፍ ምርት እንዲያመርት ለማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ጤናው ፈንታሁን በበኩላቸው እንዳሉት፣ በዞኑ የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎችን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ሥራ ውጤት አምጧል።
የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትና እና የገቢ ምንጭ በመሆን ኑሯችንን ለውጧል
Oct 10, 2026 93
ደብረ ብርሃን ፤መስከረም 30/ 2019 (ኢዜአ) ፡-የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የምግብ ዋስትና እና የገቢ ምንጭ በመሆን ኑሯችንን ለውጧል ሲሉ በደብረ ብርሃን በዘርፉ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ገለጹ። በመንግስት አዳዲስ ኢንሼቲቮች የሚደገፈው የግብርናው ዘርፍ በጥቂት ዓመታት ውስጥ የበርካታ አርሶና አርብቶ አደሮች ህይወት ላይ በተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ የሌማት ትሩፋት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ የእንስሳት እርባታ፣ የአረንጓዴ አሻራና ሌሎችም በመንግስት በትኩረት እየተሰሩና እየተደገፉ የሚገኙ የልማት ስራዎች ብዙዎችን ውጤታማ አድርገዋል። በመሆኑም በደብረ ብርሃን ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር እየተሳተፉ ያሉ አልሚዎች፤ የምግብ ዋስትና መሰረት ይዘናል የህይወት ለውጥም አምጥተናል ብለዋል። ከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎች መካከል አርሶ አደር ገብርየ ከበደ እና አርሶ አደር ጌታቸው ሸዋፈራ፤ በሌማት ትሩፋት ከቤተሰብ ፍጆታ አልፎ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። በእንስሳት እርባታና የወተት ልማት ድጋፍ ተደርጎላቸው ውጤታማ በመሆናቸው የገበያ ትስስር በመፍጠር በየእለቱ የገቢ ምንጭ እያገኙ ስለመሆኑም ተናግረዋል። የመስሪያ ቦታ፣ የብድር አቅርቦት ተመቻችቶላቸው በስልጠና ጭምር ታግዘው ለውጤት መብቃተቸውንም አልሚዎቹ አስታውሰዋል። ሌላው አርሶ አደር ምትኩ ጌታቸው፤ በመደበኛ እና በበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት በተከታታይ እያመረቱ በመሆኑ ከራሳቸው ፍጆታ ያለፈ ምረት እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም የበጋ መስኖ ልማት ስራቸውን አጠናክረው በመቀጠል የተሻለ ስኬት ለማስመዝገብ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። የደብረ በርሃን ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ መርሻ ዓይሳነው፤ በከተማዋና አካባቢው በሌማት ትሩፋትና የበጋ መስኖ ልማት የርካታ አርሶ አደሮች ህይወት እየተለወጠ መሆኑን ገልጸዋል። በእንስሳት ማድለብ፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተትና እንቁላል እንዲሁም የማር ምርት አበረታች ውጤት መጥቷል ብለዋል። የበጋ መስኖ የስንዴ ልማትም አሁን ላይ 4 ሺህ 200 ሄክታር መድረሱን ጠቁመው በቀጣይም የልማት ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰጠችው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ስራ ነው
Oct 9, 2026 134
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰጠችው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ገለጹ። ምክትል ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አድርገዋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በጉብኝቱ ወቅት ተቋሙ በአገልግሎት፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎች ዘርፎች የሰው ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ የምርምርና ልማት ስራዎች ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል። በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት እያከናወነ የሚገኘውን የቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ስራዎችን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል። የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ኢትዮጵያ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የሰጠችው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ስራ መሆኑን አመልክተዋል። የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት መጠናከር ለአፍሪካ የሚተርፍ ትሩፋት እንዳለው መግለጻቸውን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመለክታል።
ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት 1 ጀምሮ ለአንድ ወር ይከበራል
Oct 9, 2026 166
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማሳደግን ዓላማ ያደረገው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት 1 እስክ 30 ቀን 2019 ዓም እንደሚከበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቀ። ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) “ንቁ ዜጋ ደህንነቷ ለተጠበቀ ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ለቀጣይ አንድ ወር የሚከበረውን 7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወርን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በመግለጫቸው፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት በፍጥነት ማደጉን ተከትሎ በዜጎች፣ በተቋማትና ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ የሳይበር ጥቃት የሚጨምርበት ሁኔታ እንደሚታይ ገልጸዋል።በመሆኑም የሳይበር ደህንነት ወር የተቋማትንና የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ በማጎልበት ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል። ዘንድሮ በሚከበረው ወር የተቋማትን እና የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ በማጎልበት ለጉዳዩ ተገቢ ትኩረት እንዲሰጡና ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አጽንኦት ሰጥተዋል። የዘንድሮው የሳይበር ደህንነት ወር በህጻናት የበይነ-መረብ ጥበቃ ላይ ትኩረት ማድረጉን አመልክተው የህጻናት የበይነ-መረብ አጠቃቀምና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚከበር ተናግረዋል። በወሩ ታዳጊዎችና ወጣቶችን የሚያሳትፍ ውድድርና በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በሳይበር ደህንነት ላይ የውይይት መድረክ እንደሚካሄድም ገልጸዋል። ዋና ዳይሬክተሯ ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ ስራ ላይ ሁሉም በጋራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል። በመሆኑም የጥቅምት ወርን የመንግስትና የግል ተቋማት በዘርፉ የሰራተኞቻቸውን ግንዛቤ በሚያሳድጉ ተግባራት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል። ከጥቅምት 1 አስከ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ 7ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወርን በደመቀ ሁኔታ ማክበር የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል። የሳይበር ደህንነት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ23ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለሰባተኛ ጊዜ እንደሚከበርም ተመላክቷል።
የመደመር መንግስት ቀጣይ ዕቅዶች እንዲሳኩ በጥናትና ምርምር ለማገዝ ዝግጁ ነን- ምሁራን
Oct 9, 2026 128
ሀዋሳ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦የመደመር መንግስት በቀጣይ ለማከናወን ያቀዳቸውን ተግባራት ለማሳካት ብቁ ባለሙያ ከማፍራት ባሻገር በጥናትና ምርምር ሥራዎች ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። የመደመር መንግስት በቀጣይ ዓመታት ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመንግስት ምስረታ ወቅት ለምክር ቤት አባላት ባደረጉት ንግግር መግለጻቸው ይታወሳል። በተለይ የትምህርት፣ የጤና እና የማህበራዊ ጥበቃን ዘርፍ ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከል ያደረገ የልማት ሥራዎች እንደሚከናወኑም ተገልጿል። የመደመር መንግስት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በአግባቡ እንዲተገበሩና ስኬታማ እንዲሆኑ ከማድረግ አንጻር ብቁ ባለሙያ የማፍራትና የተለያዩ ችግር ፈቺ ምርምሮችን የማድረግ ሚናቸውን እንደሚወጡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገልፀዋል። የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት መምህርና ተመራማሪ ታፈሰ ማቲዮስ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት መንግስት ባከናወናቸው ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል። ዩኒቨርሲቲውም የመደመር መንግስት በቀጣይ ለማከናወን የያዛቸው ዕቅዶች እውን እንዲሆኑ የሰለጠነ ሰው ሀይል ከማፍራት ባለፈ በመንግስት የትኩረት መስኮች ላይ ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በመስራት የበኩሉን እንደሚወጣም ገልጸዋል። ልማት ስኬታማ እንዲሆን የዜጎች ሚናም ከፍተኛ እንደሆነ ያነሱት ታፈሰ (ዶ/ር)፣ ህብረተሰቡም ለሀገራዊ ዕቅዶቹ መሳካት የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አመልክተዋል። የዲጅታላይዜሽን ትግበራ የመንግስትና የግል አገልግሎቶችን ቀልጣፋ ከማድረግ ባሻገር ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረትም ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት መምህርና ተመራማሪ ሳሙኤል ጂሎ (ዶ/ር) ናቸው። መንግስት ያቀዳቸውን ተግባራት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የለውጥ ሥራዎች ውስጥ በማካተት በውጤታማነት እንዲተገበሩ የራሳቸውን አስተጽኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በግብርናው ዘርፍ የካበተ አቅምና ብቁ ተመራማሪዎች እንዳሉት ሳሙኤል (ዶ/ር) ገልጸው፣ ይህንን በመጠቀም መንግስት በግብርናው ዘርፍ የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ምርታማነትን የሚያሳድጉ ምርምሮችን በማድረግ ያግዛል ብለዋል። ምሁራኑ የመደመር መንግሥት የያዛቸው ግቦች እንዲሳኩ በምርምር፣ በመማር ማስተማርና በማህበረሰብ አገልግሎት የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
የመደመር መንግሥት የዲጂታላይዜሽን አቅጣጫ ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል
Oct 9, 2026 135
ጅማ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ የመደመር መንግሥት የዲጂታላይዜሽን አቅጣጫ ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅም እንደሚሆን ተገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት ምስረታ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ መንግሥት ከዚህ ቀደም ኢ-ኮደርስ ሥልጠና፣ዲጂታል መታወቂያን ጨምሮ የተለያዩ የዲጂታል ልማት ሥራዎችን ማከናወኑን አንስተዋል። በኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና የወሰዱ የጅማ ከተማ ወጣቶችም፣ የመንግሥት የዲጂታላይዜሽን አቅጣጫ በተለይ ለወጣቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል። አስተያየታቸውን ከሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል በግሉ በሶፍትዌር ማበልፀግ የተሰማራው ወጣት አደም ሰይድ እንዳለው በወሰደው የኢ-ኮደርስ ሥልጠና እውቀትና ክህሎቱን በማሳደግ ወደ ስራ እንዲገባ አድርጎታል። አዲስ የተመሰረተው መንግስትም የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን ለማስፋፋት የያዘው አቅጣጫ የወጣቶችን የስራ እድል እንደሚያሰፋው ተናግሯል። በመንግሥት አገልግሎቶቹን ዲጂታላይዝ በማድረግ የተገልጋይን ጊዜና ጉልበት ለመቆጠብ የተዘረጉ አሰራሮች ውጤት ማምጣታቸውን የገለጸችው ደግሞ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ባለሙያ የሆነችው ወጣት ሀናን አሙቲ ናት። በቀጣይም ሥራዎቹን ለማስፋፋት መንግስት የያዘው እቅድ ሀገራዊ እድገትን ለማፋጠን ተደማሪ አቅም እንደሚሆን ጠቅሳለች። በኢ-ኮደርስ ሥልጠና ራሷን በማብቃት ለህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዳስቻላት የጠቆመችው ደግሞ ሌላዋ የመሶብ አንድ ማዕከል ባለሙያ አሲያ አባፊራ ናት። መሰል የዲጂታል መሰረተ ልማት ሥራዎች የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት ለወጣቶች የበለጠ ተደራሽ በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ እንደሚያስችል ገልጻለች። ሌላው የጅማ ከተማ ነዋሪ መሀመድ ሀይደር በበኩላቸው እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን እቅዶች የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ ተግባራዊ የተደረጉ እንደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ያሉ ተቋማት አጋዥ ናቸው። በጅማ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ መሀመድ ሙንታዝ (ዶ/ር) ፤ የመንግስት የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ለወጣቶች ትልቅ የስራ እድል የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል። ተግባሩ በቴክኖሎጂ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ትልቅ አቅም በመፍጠር ተወዳዳሪነትን ለማስፋት እንደሚያስችል ገልጸዋል። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናና የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ስራዎች ወጣቶችን በዓለም የሥራ ገበያ ተወዳዳሪ እንደሚያደርጋቸው አብራርተዋል።
ስፖርት
ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ አቻ ተለያዩ
Oct 10, 2026 30
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሪያን ምቤሞ በ73ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ዩናይትድ መሪ ሆኗል። ዶምኒክ ሶላንኪ በ92ኛው ደቂቃ ስፐርስን አቻ አድርጓል። የቶተንሃሙ አማካይ ሮድሪጎ ቤንታንኩር በ78ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። በመጀመሪያው አጋማሽ ስፐርስ፣ በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ዩናይትድ ብልጫ ነበራቸው። ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ በስድስት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ከድል ርቋል። ቶተንሃም በበኩሉ በሶስት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ ያላሸነፈ ሲሆን በውጤት ማጣት ጉዞው ቀጥሏል።
ቼልሲ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ድል አስመዘገበ
Oct 10, 2026 87
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019(ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል። በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ ቼልሲ ቦርንማውዝን 5 ለ 1 ረትቷል። ጆአኦ ፔድሮ እና ጆርዳን ሄንደርሰን በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥሩ ሞርጋን ሮጀርስ ቀሪዋን ጎል ለሰማያዊዎቹ ከመረብ ላይ አሳርፏል። ኢቫቢልሰን የቦርንማውዝን የማስተዛዘኛ ግብ አስቆጥሯል። ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ቼልሲ በ10 ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 5ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦርንማውዝ በሶስት ነጥብ ከነበረበት 17ኛ ደረጃ ወደ 18ኛ ዝቅ በማለት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ገብቷል። ቦርንማውዝ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም። በሌሎች መርሐ ግብሮች ብራይተን ሰንደርላንድን 2 ለ 0፣ ኤፕስዊች ታውን ፉልሃምን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። አስቶንቪላ ከብሬንትፎርድ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
አትሌት መስከረም ማሞ በሊዝበን ማራቶን አሸነፈች
Oct 10, 2026 81
አዲስ አበባ፤መስከረም 30/2019(ኢዜአ)፦39ኛው የሊዝበን ማራቶን ዛሬ ተካሄዷል፡፡ በሴቶች አትሌት መስከረም ማሞ 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ አሸንፋለች። ጠጂቱ ስዩም እና በሻንኬ ኢሙሼ ሁለተኛና ሶስተኛ በመውጣት የኢትዮጵያን የበላይነት አረጋግጠዋል። በወንዶች ዩጋንዳዊው ማርቲን ናይቤይ ሙሳ አሸንፏል። ኢትዮጵያዊው አትሌት ደሳለኝ ይሌ አራተኛ ወጥቷል። አብዲ ዓሊ ሰባተኛ እና ደምሱ ገመዳ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። የሊዝበን ማራቶን ከእ.አ.አ 1986 አንስቶ እየተካሄደ የሚገኝ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ነው። የማራቶን ውድድሩ እውቅ አትሌቶች ከሚሳተፉባቸው ውድድሮች መካከል ይጠቀሳል።
አካባቢ ጥበቃ
አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት እያስገኘ ነው
Oct 9, 2026 169
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት እያስገኘ መሆኑን የኢትዮጵያ ደን ልማት ገለጸ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ተካሂዷል። በዚህም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተተከሉት 56 ቢሊዮን ችግኞች የተራቆቱ መሬቶችን በማገገም ጉልህ ፋይዳ እያስገኙ መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብሩም የግብርና ምርታማነትን በማገዝ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያስገኘ ዓለም አቀፍ ተነሳሽነት ነው። በኢትዮጵያ ደን ልማት የተፈጥሮ ደን መሪ ሥራ አስፈጻሚ ካብታሙ ግርማ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ደን የአካባቢ መራቆትና የሥነ-ምኅዳር ደህንነትን በመጠበቅ ለግብርና ምርታማነት ጉልህ ጠቀሜታ አለው። የደን ሽፋን ዕድገትም አየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቀነስ ብርቅዬ እንስሳትና የብዝኅ ሕይወት ደኅንነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልጸዋል። የመደመር መንግሥት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለደን ልማት የሰጠው ትኩረት የአካባቢ ተጽዕኖ ውጤታማነትን በማሻሻል ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም ዜጎች በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ተያያዥ የልማት መስኮች የሚሰማሩበትን ዕድል በመፍጠር ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ እያስገኘ መሆኑን አንስተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጭነት በ2011 ዓ.ም. የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራም 17 ነጥብ 2 በመቶ የነበረውን ደን ሽፋን ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደጉን አስታውሰዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የደን ጥበቃ ውጤታማነትን በማላቅ የተስተካከለ ሥነ-ምኅዳርና የብዝኅ ሕይወት እንዲፈጠር እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። በተለይም የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ በማድረግ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ እፅዋት ልማትን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሠረት እየጣለ መሆኑን አብራርተዋል። የህብረተሰቡን የደን ጥበቃና እንክብካቤ ባህል በማሻሻል የደን አስተዳደር ሥርዓት ውጤታማነትን ማሳደግ የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ደን ልማትም የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ፣ የደን ሀብት በዘላቂነት እንዲጠበቅና እንዲለማ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ አንስተዋል። በተጨማሪም የደን ውጤቶች ምርታማነትን በማሻሻል የደን ሀብት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጠቃሚነትን በማላቅ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ ሆኗል
Oct 7, 2026 187
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2019(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት ለሌሎች ሀገራት አርዓያ የሆነ ታላቅ ተግባር መሆኑን የዘርፉ ሙያተኞች ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ርዕይን አንግባ በትኩረት እየሰራችባቸው ከሚገኙ ውጤታማ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መካከል አረንጓዴ ዐሻራ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትን ለመከላከል፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ባለፉት ዓመታት በአርንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ተክላለች። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን መካሄዱ ይታወቃል። በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብርን ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን 56 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የተራቆቱ መሬቶችን አረንጓዴ ማልበስ ተችሏል። በተጨማሪም ይህ መርሀ ግብር የመሬት መሸርሸርን እንዲቀንስ፣ ስነ ምህዳራን መጠበቅ እንዳስቻለም መግለጻቸው ይታወሳል። በተባበሩት መንግስታት የደን ፎረም ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር ዶክተር ጁሊያት ቢያኦ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ የደን ሽፋንን ለመጨመር የሚከናወኑ ተግባራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እንደሚያበረክቱም ገልጸዋል። የደን መራቆትን ለመቅረፍና የመሬት ገጽታ ለመጠበቅ መንግስት ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ የዘርፉን ተዋንያን ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብርን ነድፎ ባለፉት ዓመታት በመተግበር የአረንጓዴ ሽፋንን ለማሳደግ ያከናወነው ተግባር ውጤት ማስመዝገቡንም አክለዋል። የአፍሪካ የደን ፎረም የደን ተመራማሪ የሆኑት ዶሪስ ሙታ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአካባቢ ስነ ምህዳርን ለመጠበቅና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራት የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ያከናወነቻቸው ውጤታማ ተግባራት ከደን ሽፋን መመናመን ጋር ተያይዞ የሚከሰት የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትን በመከላከል በኩል ጉልህ ሚና አለው ብለዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት በዘርፉ በትኩረት ከተሰራ ታሪክ መቀየር እንደሚቻል ለዓለም ጥሩ ምሳሌ እንደሚሆን ተናግረዋል። እንደ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አይነት ፕሮጀክት ነድፎ መተግበር ፋይዳው አካባቢን በደን ከመሸፈን በላይ መሆኑንም ነው የተናገሩት። በመሆኑም መሰል ምሳሌ የሚሆን ተግባር ሰዎች በምቹ ስነ ምህዳር እንዲኖሩ ዕድል የሚፈጥርና ምርታማነትን የሚያሳድግ አርዓያነት ያለው ተግባር እንደሆነም ነው ዶሪስ ሙታ ( ዶ/ር) የገለጹት።
በአማራ ክልል የግሪሳ ወፍ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ነው
Oct 7, 2026 173
ባህር ዳር፤ መስከረም 27/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የተከሰተው የግሪሳ ወፍ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል የኬሚካል ርጭት እየተካሔደ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ መንጋ በዘመናዊና ባህላዊ መንገድ የመከላከል ሥራ እየተሠራ ይገኛል። በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በሚገኙ 15 ወረዳዎች የተከሰተው የግሪሳ ወፍ መንጋ በደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በተቀናጀ አግባብ የመከላከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። መንጋው የማሽላ፣ የጤፍ፣ የስንዴ፣ የገብስ፣ የዳጉሳ፣ የሩዝ እና የመሳሰሉ ሰብሎችን በእሸትነት ደረጃ ፍሬውን በመብላትና በማራገፍ ጥፋት የሚያስከትል ነው። በዚህም 74 የግሪሳ ወፍ መንጋ ማደሪያ ቦታዎችን በመለየት ከመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት በማከናወን አብዛኛውን የግሪሳ ወፍ ማስወገድ ተችሏል። በተቀናጀ መንገድ በተካሄደ የመከላከል ሥራ ሰብሉን ሙሉ በሙሉ ከግሪሳ ወፍ ጉዳት መታደግ እንደተቻለ ነው ዳይሬክተሩ ያስገነዘቡት። አርሶ አደሩ በየእለቱ ሰብሉን አሰሳ በማድረግ ከግሪሳ ወፍ ጉዳት የመከላከል ሥራውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ደጀኔ ከበደ በበኩላቸው፤ መንጋው የተከሰተው በከሚሴ ከተማ አስተዳደር፣ በዳዋ ጨፋ፣ በአርጡማ ፉርሲ፣ በጅሌ እና ባቲ ወረዳዎች መሆኑን ተናግረዋል። መንጋውን በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ፈጥኖ በማከናወን የመከላከል ሥራ በመሠራቱ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነውን የግሪሳ ወፍ ማስወገድ መቻሉን ገልጸዋል። አሁንም መንጋውን የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተው፤ አርሶ አደሩም በባህላዊ መንገድ ድምፅ በማሰማት መንጋው በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ሳቢ በማድረግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Oct 3, 2026 294
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የሀገሪቱን የአረንጓዴ ልማት ግቦች ከማሳካት ባለፈ፣ ከተሞችን ለኑሮ ምቹ እና ተስማሚ እያደረገ እንደሚገኝ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የጀመረችው ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ትልቅ አርአያ መሆን ችሏል። በዚህ ግዙፍ ሀገራዊ ተነሳሽነት አማካኝነት ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ 56 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ተችሏል። በመርሃ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች ስነ-ምህዳርን ከማስጠበቅና ከተሞችን አረንጓዴ ከማላበስ ባለፈ ለምግብነት እና ለቱሪስት መዳረሻነት ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል። ይህ ሁሉን አቀፍ ጥረት ሀገሪቱ የተፈጥሮ ጸጋዎቿን ጠብቃ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ብሩህ ጉዞ ጠንካራ እና አዲስ መሰረት ጥሏል። በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናት ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ አማን አሰፋ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በከተሞች የሚካሄዱ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ስራዎች ከተሞች ለኑሮ ምቹ፣ ዘመናዊና ማራኪ አድርጓቸዋል። በከተሞች አካበቢ ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መኖር እና የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆናቸው ለከፍተኛ ካርቦን ልቀትና ብክለት ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። በመሆኑም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ይህንን ችግር በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም የሙቀት መጠንን በመቀነስ፣ የአካባቢ ስነ-ምህዳርን በመጠበቅ እና በከተሞች አካባቢ ጎርፍ እንዳይከሰት በመከላከል ለአየር ንብረት ለውጥ ትልቅ አዎንታዊ ድርሻ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት አዳዲስ የከተማ ፕላን አሠራር ላይ ማሻሻያ ማድረጉንም ተናግረዋል። በዚህም አዲስ የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት፣ 30 በመቶ ለመሠረተ ልማት እና 40 በመቶው ደግሞ ለመኖሪያነት እንዲውሉ የሚያስችል ሞዳሊቲ እንዲከተሉ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። በዚህ መሰረት የሚከናወኑ የከተማ ፕላን ዝግጅቶች የሀገሪቱን አረንጓዴ የልማት ግቦች ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ
Sep 21, 2026 1075
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 1130
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው። በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 1031
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 1205
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
ከማዕድን ማውጣት እስከ ኢንዱስትሪ ሽግግር፤ የመደመር መንግሥት የማድረግ አቅም ማሳያ
Oct 10, 2026 95
በመንግሥቱ ዘውዴ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ኢትዮጵያ ካሏት ጸጋዎች መካከል የምድር ውስጥ ሃብቶች ይገኙበታል። ሃብቶቹ የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ግብዓት ናቸው። እጅግ የበለጸጉ የጂኦሎጂካል ማዕድናት ሀብት ያላት ኢትዮጵያ የማዕድን ሃብት በብዝኅ ኢኮኖሚ መርህ የዕድገት ሽግግርን የሚያፋጥን መሰረት እየጣለ ይገኛል። ኢትዮጵያ ወርቅን ጨምሮ ለኢንዱስትሪና ለኮንስትራክሽን ዘርፍ በጥሬ ዕቃ ግብዓትነት የሚውሉ ውድና የከበሩ እንደ ታንታለም፣ ፖታሽና ሌሎች ማዕድናት በጉያዋ የታቀፈች ምድር ናት። ማዕድናት ለሥራ ዕድል ፈጠራም የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል አይደለም። በመደመር መንግሥት አምስት የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሮች መካከል የማዕድን ዘርፍ አንዱ እንዲሆን አድርጓል። ይህም የኢትዮጵያን የምድር ውስጥ እምቅ ሀብቶች ለኢኮኖሚ ዕድገት ማዋል እንደሚቻል ግልጸኝነትን የፈጠረ ወሳኝ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል። በዚህም ባለፉት ዓመታት በዘርፉ ያሉ ሀብቶችን በማልማት፣ እሴት ጨምሮ በማምረትና ለገበያ በማቅረብ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት በኩል አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካን ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፤ ሀብቶቻችንን ከኢንዱስትሪ አቅም ጋር በማስተሳሰር የወጪ ንግድ ገቢንና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ የጌጣጌጥ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍና ተወዳዳሪ የወርቅ እሴት ሰንሰለት ለመገንባት የመደመር መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው። የዚህ ሀገራዊ ጥረት አንድ አካል የሆነውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ሥራ የጀመረው የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካም የመደመር መንግሥት እምቅ የሀገር ሀብቶችን ለይቶ፣ አልምቶና አምርቶ ለውጤት ማብቃቱ አይነተኛ ምሳሌ ይሆናል። ይህ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ መካከል በተደረገ አጋርነት የተቋቋሙ የመደመር መንግሥት ከግሉ ዘርፍ ተዋንያን ጋር በጋራ በመሥራት የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳያል። የማዕድን ሀብቶችን በማልማትና እሴት ጨምሮ በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። ባለፉት ዓመታት በዘርፉ የተመዘገበውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ዕድገትም ሁነኛ አብነት ነው። ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካም በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም አለው። ፋብሪካው በሀገር ውስጥ ምርት ላይ እሴት በመጨመርና የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ በማጠናከር በውድ ማዕድናት ማጣሪያ ረገድ ኢትዮጵያን ቀጣናዊ ማዕከል የሚያደርግ ትልቅ ምዕራፍ ሆኗል። ከማዕድን ማውጣት እስከ ኢንዱስትሪ ሽግግር ድረስ በኢትዮጵያ የላቀ የእሴት ሰንሰለት እየፈጠረ ይገኛል። ይህ ፋብሪካም በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ርዕይ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ የሚወሰድ ተጨባጭ የልማት ውጤት መሆኑ እሙን ነው። የመደመር መንግሥት ኢንዱስትሪ ምርታማነትን ከማስፋፋት ባሻገር የማምረት አቅማቸው እንዲጎለብት የሰጠውን ትኩረት ያመላክታል። የማዕድን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቅድሚያ የሚሰጠው አምራች ዘርፍ እየሆነ መጥቷል። በተለይም የወርቅ ማዕድን ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱን ቀጥሏል። ይህ ሀገራዊ ተነሳሽነት ሀብቶችን ከሀገር ውስጥ ማቀነባበሪያ፣ ከኢንዱስትሪ አቅምና ከዘላቂ እሴት ፈጠራ ጋር ለማስተሳሰር የመደመር መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እንደሚያሳይም ያመላክታል። የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካውም የወርቅ ጥራትን በማስጠበቅ ለማንጠርና ለውጭ ገበያ ዝግጁ ወደሆኑ ንጹሕ ምርት በመቀየር የጥራት ደረጃዎችን ለማሟላት ሁነኛ አቅም ይሆናል። የመደመር መንግሥትም ኢትዮጵያ ያሏትን ሀብቶች በጥሬው ለገበያ ከማቅረብ ይልቅ እሴት በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ የያዘውን ትክክለኛ የልማት አቅጣጫ ተጨባጭ ያደርገዋል። ፋብሪካውም ኢትዮጵያ በሀብቶቿ ላይ እሴት ጨምራ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ በያዘችው የኢኮኖሚ አቅጣጫ መሰረት የተገነባው ነው። ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ መጀመሩ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ግልጽና ትልቅ ርዕይ ማንገቡን ያመላክታል። በተለይም ለማዕድን ልማትና ዕድገት የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የተመዘገበውን ውጤት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ይህ ውጤታማ ተግባር በሌሎች ዘርፎችም ተጠናክሮ ይቀጥላል። ትልቅ ሕዝብ ይዛ፣ ታላቅ ርዕይ የሰነቀችው ኢትዮጵያም የተፈጥሮ ሀብቶቿን በእውቀት፣ በቴክኖሎጂና በኢንዱስትሪ በማልማት ለሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ መሰረት እየጣለች ይገኛል። የብሔራዊ የከበሩ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ መጀመርም ሃብትን በጥሬው ከመሸጥ ወደ እሴት ጨምሮ ማምረት ከዚያም ከሀብት ወደ ምርት፣ ከምርት ወደ ውጭ ንግድ ተወዳዳሪነት የሚያሸጋግር ጉልህ እርምጃ ነው። በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተፈጠረውን ዕድል በማስፋት ማዕድንን ጨምሮ የብዝኅ ኢኮኖሚ አዕማዶችን በማሳደግ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የውጭ ምንዛሬ ገቢንና የሀገርን የምርት አቅም ማጠናከር የዚህ ርዕይ ዋነኛ መገለጫዎች ናቸው። በርግጥም ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገርነትን ከትልቅ ሕዝብ፣ ጸጋዎችን ከልማት በማሰናሰል አቅምን ወደ ውጤትና ርዕይንም ወደ ተጨባጭ የብልፅግና መሰረት እየቀየረች ይገኛል።
የህብረ ብሔራዊነት ማህተም
Oct 10, 2026 108
በብዙ ድል ታጅቦ የሚከበረው 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ እንደ ዓይን ብሌን በስስት ከሚጠበቁ የሀገር ካስማዎች መካከል ሰንደቅ ዓላማ አንዱና ዋነኛው ነው። አይነኬ የሀገር ምልክትም ነው፤ ሰንደቅ ዓላማ። ለሀገር ምልክት የማይከፈል ዋጋ የለም። የሀገር መከላከያና ሌሎች የጸጥታ አካላት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የደረሰ ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጁለት፤ የሀገር ምልክት የሆኑ አትሌቶችም ደከመኝ ሳይሉ፣ ሳይታክቱና ሕመማቸውን ዋጥ አድርገው በዓለም መድረክ ከፍ እንድትል የሞት ሽረት ትግል የሚያደርጉለት ነው ሰንደቅ ዓላማ። ሁሉም በየመስኩ ደፋ ቀና የሚልለት የሀገር ሰንደቅ ዓላማ ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዓሉን አስመልክቶ እንደገለጸው፣ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን የሚከበርበት ዋና ዓላማ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት ዜጎች የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያጠናክሩበት፣ በሀገራዊ አንድነትና በሕብረ ብሔራዊ መግባባት የሚፈጥሩበት ሀገራዊ በዓል ነው። ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በዋናነት የኢትዮጵያውያን የማንነት መገለጫና አርማ ነው። ሰንደቅ ዓላማ ለኢትዮጵያውያን የጽናታቸው፣ የሕብረታቸው፣ የሕልውናቸውና የሉዓላዊነታቸው ምልክት ነው። ሁለመናቸው ለሆነው ለዚህ ሰንደቅ ዓላማ ጸንቶ መዝለቅ ኢትዮጵያውያን የሚሰስቱት አንዳች ነገር የላቸውም። ታሪክ የሚነግረንም ይህንኑ ሀቅ ነው። የሀገር ሰንደቅ ዓላማ የሉዓላዊነት፣ የነጻነት፣ የሕዝቦች አንድነትና የክብር ምልክትም ጭምር ነው። ሰንደቅ ዓላማ የትውልዶች ታሪክ፣ የማንነት መገለጫ እንዲሁም የሀገር ሕልውና ምሰሶ መሆኑን የሚያረጋግጡ በርካታ ማሳያዎችን ማንሳት ይቻላል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳስታወቀው፣ 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሐሳብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኞ፣ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. በታላቅ ድምቀት ይከበራል። ይህ በምክር ቤቱ መሪነት የሚከበረው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በመላ ሀገሪቷ ወቅታዊ ሀገራዊና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ፣ በድምቀትና በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ይከበራል። ዘንድሮ የሚከበረው 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በበርካታ ሀገራዊ ድሎችና ውጤቶች የታጀበ ነው። ከእነዚህ ሀገራዊ ድሎች መካከል ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት አጠናቃ አዲሱን የመደመር መንግሥት መመሥረቷ የመጀመሪያው ጉዳይ ሲሆን፣ ሁለተኛው በአሳታፊነትና በአካታችነት ሂደት በስኬት የተጠናቀቀው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ነው። ለኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጸንቶ መቆየት በየትውልዱ ዜጎች የሕይወት መስዋዕትነትን ጨምሮ ውድ ዋጋ ከፍለዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ይህንን የሉዓላዊነት ምልክት ሳያጎድፉ፣ የሀገርን ዳር ድንበር ሳያስደፍሩና ነጻነትን አስከብረው ለዛሬው ትውልድ አስረክበዋል። የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ቀደምት የሀገር አለኝታዎች የከፈሉት መስዋዕትነት ለዚህ ትልቅ ምሳሌ ነው። የመከላከያ ሠራዊት ለሰንደቅ ዓላማው ጸንቶ መቆም ሲባል ሕይወቱን፣ ደሙንና አካሉን የገበረ የሀገር አለኝታ ስለመሆኑ ምስክር አያሻም። ለዚህ ነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀኑን አከባበር ሂደት በተመለከተ ባስታወቀበት መልዕክቱ፣ ይህ በዓል ኢትዮጵያውያን የሀገርን ዳር ድንበርና ክብሯን ለማስጠበቅ ደምና ላባቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ያስከበሩትን ሰንደቅ ዓላማ በጋራ የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር የመስጠትና የማክበር ኃላፊነትና ግዴታ አለበት ሲል ያስገነዘበው። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተከበረበት ወቅት፣ “የሰንደቅ ዓላማ ቀን ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ፍቅርና አንድነትን የሚያድሱበት፣ የነገ ተስፋቸውን የሚያጸኑበት ነው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርማ የሉዓላዊነት መገለጫ ማኅተም ነው” ሲሉ መግለጻቸው፣ ኢትዮጵያውያን ለሰንደቅ ዓላማ እስከ መስዋዕትነት የደረሰ ዝግጁነት ያላቸውን ቀናኢነት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ዘንድሮ የሚከበረው 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በብዙ ሀገራዊ ድሎችና ተስፋዎች ታጅቦ ነው። ኢትዮጵያ በኢኮኖሚያዊ፣ በማኅበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች በርካታ ስኬቶችን ባስመዘገበችበት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ውጤታማ በሆነችበትና የጀመረችውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አሳታፊና አካታች በሆነ መልኩ ባጠናቀቀችበት ወቅት የሚከበር ልዩ ቀን ነው። በተጨማሪም ሀገራችን በውጭም ሆነ በውስጥ የገጠሟትን ፈተናዎች በዲፕሎማሲያዊ መንገድና በአይበገሬነት መንፈሷ በጽናት እየመከተችና ውጤት እያስመዘገበች ባለችበት፣ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ግልጽ፣ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ በስኬት በማካሄድ አዲሱን የመደመር መንግሥት በመሠረተችበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ደግሞ እጅግ ልዩ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶቿን “የባንዲራ ፕሮጀክቶች” በማለት ሰይማለች። ለዚህ ምክንያቱ፣ ሰንደቅ ዓላማ የሀገር መለያ እንደሆነው ሁሉ፣ ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችም ሀገራዊ ውክልና ያላቸውና የክብር ምልክት በመሆናቸው የሀገሪቱን ታላቅነት፣ ዕድገትና የወደፊት ርዕይ ለዓለም የሚያሳዩ የልማት ውክልናዎች ናቸው። አንድ ሀገር ከነደፈቻቸው ዘመን ተሻጋሪ የልማት ዕቅዶች መካከል ግንባር ቀደም ሆነው የሚተገበሩ፣ ለሌሎች ፕሮጀክቶች አቅጣጫ የሚያሳዩና ስኬታቸው ለሌሎች መንገድ ጠራጊ የሚሆኑትም በመሆናቸው ጭምር ነው። እነዚህ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ በጀት፣ ሰፊ ሽፋንና የብዙ ዜጎችን ሕይወት የመቀየር አቅም ያላቸው በመሆናቸው፣ የስኬታማነታቸው ውጤት በጠቅላላው ሀገራዊ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ንቅናቄ ይፈጥራል። በባሕር ላይ ዋናዋ መርከብ ትኩረት እንደምትስበው ሁሉ፣ እነዚህ ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን መሪዎች፣ የመገናኛ ብዙኃንንና የሕዝቡን ከፍተኛ ትኩረት የሚስቡና ቅድሚያ የሚሰጠው የሀብት ድልድል የሚደረግላቸው ናቸው። ለዚህም ነው በዜጎችም ሆነ በመንግሥት ልዩ ጥበቃና ክትትል የሚደረግላቸው። ለአብነት ያህል፣ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች የሀገርን የልማት ቁርጠኝነት፣ አቅምና ርዕይ ለዓለም የሚገልጹ ናቸው። በሀገሪቱ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል በዜጎችም ሆነ በመንግሥት ተሳትፎና ትኩረት የሚስቡ በመሆናቸው “የባንዲራ ፕሮጀክት” ተብለው ይጠራሉ። የነጻነትና የጸረ-ኮሎኒያሊዝም ምሳሌ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለዜጎች ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጭምር የነጻነት ምልክት ነው። ይህ ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነጻነትና የጸረ-ኮሎኒያሊዝም ምሳሌ ሆኖ እንዲወሳ ያደረገው የመከላከያ ሠራዊቱና የሕዝቡ የጋራ ተጋድሎ ነው። በዓድዋ ጦርነት ወቅት በዘመናዊ መሣሪያ የተደራጀውን ወራሪውን የጣሊያን ሠራዊት በመመከት፣ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በነጻነት እንዲያውለበልብ የተደረገው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጀግኖች በከፈሉት መስዋዕትነት ጭምር ነው። ይህ የነጻነትና የጸረ-ኮሎኒያሊዝም ምልክት የሆነው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በትውልድ ቅብብሎሽ ተጠብቆ እዚህ ደርሷል፤ ይኸው ተጠናክሮ ቀጥሏል። ወደፊትም ይቀጥላል። ሀገር በውጭ ወራሪዎች በተፈተነችባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ፣ ሠራዊቱ የሰንደቅ ዓላማዋን ክብር ለማስጠበቅ ግንባሩን ለጥይት መስጠቱን አላቆመም። የሀገርን ድንበር ጥሶ ለመግባት የሚሞክር ወራሪ ኃይልን በመመከት፣ የሉዓላዊነት ምልክት የሆነችውን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ለሚያደርግ ሠራዊት ጽናትና ለሀገር ያለውን ጽኑ ፍቅር በግልጽ ይጠቁማል። የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለዘለዓለም በነጻነት ከፍ ብላ የምትውለበለበው በጀግኖች የመከላከያ ሠራዊት ውድ ዋጋና መስዋዕትነት ነው። ሠራዊቱ ለሰንደቅ ዓላማው መጽናት የከፈለውና እየከፈለው ያለው መስዋዕትነት የሀገርን ሕልውና የማስቀጠል፣ የሕዝቦችን ሰላም የማረጋገጥና ታሪካዊ ክብሯን የመጠበቅ ታላቅ ሀገራዊ አደራ ስላለበት ጭምር ነው። ይህንን መስዋዕትነት ማወቅ፣ ማክበርና ለሠራዊቱ የሚገባውን ምስጋና መስጠት ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው።
የሴቶች አካታችነት ምኅዳር መስፋት፤ ኢትዮጵያን የመገንባት ፍኖት
Oct 10, 2026 100
በየጸዳወርቅ ታደለ ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ርህራሔ፣ ጥንካሬ፣ ሕይወት፣ ፍቅርና ውበት የሀገርና ሴት መገለጫዎች ናቸው። በቋንቋ፣ በስያሜ፣ በታሪክና በተግባር ሲታዩ ሀገር እና ሴት አንድ የሚያደርጋቸውን ተመሳስሎሽ ያሳያሉ። ሴት የሕይወት መሠረት፣ የቤት ማዕዘንና የትውልድ አርበኛ ናት። ሴት ልጅ የተቸራት ሁለገብ ሙያ፣ ዕውቀት፣ ብልሃትና ብቃት የሀገር ግንባታ ድርሻዋን ጉልህ ያደርገዋል። ሀገር ስትጠራም በእናት ትመሰላለች። ይህ ስያሜ አባባል ብቻ አይደለም። የእናትነትን ታላቅ ባሕርይ ለሀገር የመስጠት ጥልቅ ፍቅር ነው። አንዲት ሴት ልጅን በእቅፏ እንደምታሳድግ ሁሉ፣ ሀገርም ዜጎቿን አስጠልላ የምታሳድግ ግዙፍ ጥላ ናት። ለዚህም ነው ሁለቱም የመጠለያና የደህንነት ተምሳሌቶች ናቸው የሚባሉት። ይህ ተፈጥሯዊ ሁኔታ ሴቶች በተሰማሩበት መስክ ስኬታማነታቸው የላቀ እንደሚሆኑ ያሳያል። ሴቶች ከቤታቸው አልፈው በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው። ለምሳሌ እርስ በርስ በመረዳዳት፣ በባህላዊ እሴቶችና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ሚና በመወጣት የሕብረተሰብ መስተጋብር ገመድ ናቸው። በኢኮኖሚ መስክም ለሀገር የልማት መርሃ ግብሮች ስኬት ከፍተኛ ዐሻራ አላቸው። የኢትዮጵያ ሴቶችም የርኅራሔ፣ የአብሮነት መሠረትና የትውልድ ግንባታ ተምሳሌት ናቸው። ጀግንነትም የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ነጻነት በማስከበር ሂደት በተግባር ተፈትሎ የሚያልፍበት መገለጫቸው ነው። ለዚህም ከዓድዋ ድል የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ሂደት ዐሻራቸው ሕያው ነው። ዛሬም የመደመር መንግሥት ሴቶችን በከፍተኛ የመንግሥት አመራርና በውሳኔ ሰጪነት በማሳተፍ፣ ያላቸውን ብቃትና አቅም ለሀገራዊ ሁለንተናዊ ለውጥ በማዋል የሴቶችን ሚና የበለጠ የሚያጎለብት ምኅዳር ፈጥሯል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጥ የወለደው የመደመር መንግሥት፣ ሴቶች ብቃታቸውን፣ ክህሎታቸውንና ተሰጧቸውን ለሀገር ግንባታ የሚያውሉበትን አስቻይ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምኅዳር ፈጥሯል። የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት አቅም ለማጎልበት አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል። ይህም በትምህርት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በተቋም ግንባታና በውሳኔ ሰጪነት ቦታዎች ላይ ሴቶች የማድረግ አቅማቸውን ማስመስከር ያስቻሉ ተግባራዊ ለውጦች እንዲመዘገቡ አድርጓል። በተለይም የመደመር መንግሥት የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማጎልበት የፈጠረው ልምምድ አሳታፊና አካታች ብልጽግናን ለማረጋገጥ በቁልፍ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አጀንዳነት የተያዘ ነው። እነዚህና መሰል ተግባራትም የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ምኅዳር እየፈጠረች መሆኗን ያመላክታሉ። የመደመር መንግሥት በፌዴራል፣ በክልልና በከተማ አስተዳደሮች የካቢኔ አወቃቀር ለሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ድርሻ መስጠቱ ሁለገብ ሙያዊ ክህሎታቸውን ለሀገር ግንባታ እንዲያውሉ እያስቻለ ይገኛል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅራቢነት በተዋቀረው አዲሱ ካቢኔ ውስጥ ከ22 የመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ውስጥ 9 ሴቶች ሹመት አግኝተዋል። ይህም ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካትና የሕዝብ አደራ በብቃት ለመወጣት የሚያስችል አካታች ሥርዓት የመገንባት መሰረት ነው። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ካቀረቧቸው 22 ዕጩዎች ሚኒስትሮች መካከል ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የገንዘብ ሚኒስትር፣ ሃና አርአያሥላሴ የፍትሕ ሚኒስትር፣ ያስሚን ወሃብረቢ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር፣ ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር፣ ዓይናለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስትር እና ሰላማዊት ካሳ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር በማድረግ ሹመት ሰጥቷል። እንዲሁም ዓለምጸሃይ ጳውሎስ የማዕድን ሚኒስትር፣ ሻዊት ሻንካ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ፍሬሕይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሲያደርጉ ሹመቱን ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ሚኒስትሮቹም ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ሕዝባዊ አደራና ኃላፊነት ተረክበዋል። ይህም ሴቶችን ከማሳተፍ በላይ የተሻገረ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም የመደመር መንግሥት አሳታፊና አካታችነት የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ማጠናከሩን የሚያሳይና እጅግ የሚያኮራ ውሳኔ መሆኑን አንስተዋል። በካቢኔ አወቃቀር ውስጥ በርካታ ሴቶች መካተታቸው ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ሀገራት ጭምር ተምሳሌት መሆኑን ነው ያመለከቱት። ከዚህ ቀደምም ኢትዮጵያ በፓርላማ፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድና በከንቲባነት ጭምር ሴቶችን በቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በመሾም አህጉራዊና ዓለም አቀፍ አርዓያነቷን ማሳየቷንም አስታውሰዋል። በቀጣይም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማጠናከር እንደሚሠራ አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፤ የሴቶችን የመፈጸም አቅምና ብቃት ለማረጋገጥ ብሎም ተጨማሪ ዕድል ለመስጠት የመደመር መንግሥት ዝግጁ ነው። የመደመር መንግሥት አካታች የዲሞክራሲ ሥርዓትን መገንባት ብቻ ሳይሆን እውን ማድረግ እንደቻለ ምስክር የሚሆኑ በርካታ ማሳያዎች አሉ። ሴቶችን በማብቃት፣ በማካተትና ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ የተወሰዱ ትልልቅ ውሳኔዎችና ስኬታማ ሥራዎች በመደመር መንግሥት የተጀመሩ ዛሬም ወደፊትም የሚቀጥሉ ናቸው። ሴቶች የበለጸገች ኢትዮጵያን በመቅረጽ ሂደት ውስጥ ያላቸው አበርክቶ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በእርግጥም ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ለሰነቀችው ኢትዮጵያ የሁሉንም ዜጎች አቅም፣ ዕውቀትና ተሰጥኦ ለሀገር ግንባታ ማሰለፍ ማለት ነው። ከዓድዋ ድል የነፃነት ተጋድሎ እስከ ዛሬው የልማትና የለውጥ ጉዞ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ያስመዘገቡት ጀግንነትና ሁለገብ ብቃት ለዚህ ታላቅ ርዕይ ወሳኝ መሰረት ነው። የመደመር መንግሥት ሴቶችን በከፍተኛ አመራርና ውሳኔ ሰጪነት በማሳተፍ የጀመረው እመርታም ይህንኑ አቅም ወደ ሀገራዊ ውጤት ለመቀየር የሚያስችል አካታች ምኅዳር ፈጥሯል። ስለሆነም ሴቶች በእኩልነት፣ በብቃትና በኃላፊነት የሚሳተፉባት፣ የሁሉንም ዜጎቿን አቅም የምታሰልፍና የጋራ ብልፅግናን የምታረጋግጥ ኢትዮጵያን መገንባት የዘመኑ ታሪካዊ ዐሻራ ነው። ትልቅ ሀገር የምትገነባው በትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይዋንም ወደ እውነት የምትቀይረው የሁሉንም ዜጎች አቅም በማካተት ነው።
የኢትዮጵያ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ - የመደመር መንግሥት እሳቤ ትሩፋቶች
Oct 9, 2026 157
ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ የመደመር መንግሥት እሳቤ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ የልማት አቅጣጫዎችን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ እያሸጋገረ ይገኛል። በዚህም በግብርና ዘርፍ ብቻ ተወስኖ የቆየውን የኢኮኖሚ መሰረት ወደ ባለብዙ ዘርፍ የኢኮኖሚ ልማት ለማስፋት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በዚህም በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድንና ቴክኖሎጂ ዘርፎች በተከናወኑ በርካታ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡ የመደመር መንግሥት ምሥረታና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ ሥርዓት፣ አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ የሰየመ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የሀገሪቱ የልማት ስኬቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። የበጋ መስኖ ልማትና የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብሮች የስንዴ፣ ሩዝ፣ ወተትና እንቁላል ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ እያሳኩ መሆኑን፤ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፣ በዲጂታሉም የፋይዳ ማንነት፣ የገበታ፣ የወንዝ ዳርና የማዕድን ልማት ፕሮጀክቶችም የምርትና አገልግሎት አሰጣጥ ባህልን ወደ ላቀ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገሩ ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር አንስተዋል። የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ትግበራና ስኬቶቹ የመደመር መንግሥት እሳቤ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ እና ውጤቶችም እንዲመዘገቡ እያስቻለ ይገኛል። በዚህም በግብርና ዘርፍ በዘመናዊ የመስኖ ልማት፣ በበጋ ስንዴ ምርት እና በኩታ-ገጠም የአስተራረስ ዘዴዎች የተገኙ ውጤቶች የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የውጭ ጥገኝነትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። በተጨማሪም በሌማት ትሩፋት፣ በከተማ ግብርና፣ በግብርና ምርቶች ላይ እሴት መጨመርና ሌሎች ውጤታማ ተግባራትም ተከናውነዋል። በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ በሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ለዜጎች በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን እየፈጠረ ይገኛል። በመደመር መንግሥት እሳቤ በመመራት በዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙት ውጤታማ ተግባራት ለውጭ ምንዛሬ ግኝትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ከማቅረብ አንጻርም አበርክቷቸው ከፍተኛ ሆኗል። ከሀገሪቱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ግብርና ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ በመሆኑ ይህን ዘርፍ ማዘመን፣ ሜካናይዜሽንን ማስፋፋትና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም የኢትዮጵያን የልማትና የዕድገት ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ ወሳኝ መንገድ ነው። በኢንዱስትሪው ዘርፍ ሀገራዊ የማምረት አቅምን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመቀነስ እና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ እና ለማዳን እንዲሁም ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ወሳኝ ሀገራዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። ለዚህ እንደጥሩ ምሳሌ የሚጠቀሰው በስፋት ተተግበሮ ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡበት የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ነው። ይህ ሀገራዊ ንቅናቄ በዘርፉ ለዓመታት ተግዳሮት ሆነው የቆዩ ጉዳዮችን በመፍታት ተጨባጭ ለውጦችን በማምጣት የሀገሪቱን የማምረት አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር አስችሏል። የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች አሁን ላይ የማምረት አቅማቸው ከ69 በመቶ በላይ ማደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሐመድ መግለጻቸው የንቅናቄውን ውጤታማነት በግልጽ የሚያመላክት ነው። ንቅናቄው ተዘግተው የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ፣ የሰው ኃይል እንዲሰባሰብና ምርታማነት እንዲያድግ በማድረግ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። ቀደም ሲል ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረትም በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ማዳን ተችሏል። ለዚህም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ማስፋፋትና ማጠናከር፣ ሀገር በቀል የመድኃኒት አምራቾች አቅም እንዲጎለብት በተሰራ ስራም እንዲሁ ከውጭ የሚገቡ መድኃኒቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ መደረጉ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። የመደመር መንግሥት በኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲመዘገብ ያስቀመጠውን አቅጣጫ ስኬታማ ለማድረግ በርካታ የፖሊሲ እና የአሰራር ማሻሻያዎችን አድርጓል። በዚህም የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን የሚጨምሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ እና የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ማሻሻያዎች ተደርገዋል። እነዚህ የተግባር እርምጃዎች የዘርፉን ምርታማነት በማሳደግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱ እንዲጨምርና ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ አስችለዋል። የመደመር መንግሥት ትኩረት ከሰጣቸው እና ውጤቶች ካስመዘገበባቸው ዘርፎች መካከል የዲጂታል ዘርፍ ተጠቃሽ ነው። ይህ ዘርፍ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ካለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አንጻር የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ተቀርጾ ተግባራዊ ተደርጓል። ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ ተደርጎ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገቡ ይታወቃል። በዚህም ዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ 2025 የኢትዮጵያን የልማትና የዕድገት ጉዞ በማፋጠን፣ ሀገሪቱን በቴክኖሎጂ ወደሚመራ ኢኮኖሚ ለማሸጋገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ አዲስ የዕድገት ሞተር ነው። ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማጠናቀቂያ እና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብር ላይ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ የተሳካ ነው" ሲሉ መግለጻቸው። ይህም ብቻ ሳይሆን ከአምሥት ዋና ዋና ዘርፎች መካከል አንዱ ስትራቴጂ መሆን አለበት ለኢትዮጵያ ብልጽግና አይተኬ ሚና አለው ነው ያሉት። ዲጂታል ቴክኖሎጂ የመደመር መንግሥት ለነደፋቸው ሌሎች ዋና ዋና ዘርፎች ውጤታማነትም አጋዥ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝና ለበርካታ ወጣቶች ሰፊ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ነው። በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘረፍ እየተገኙ ካሉ ውጤቶች መካከል የፋይናንስ ዘርፉን ቀልጣፋ እያደረገ መምጣቱ ተጠቃሽ ነው። በዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ዲጂታል የክፍያ ስርዓትን በመጠቀም ግብይት እየፈጸሙ መሆኑ ለውጤታማነቱ ጥሩ ማሳያ ነው። የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን መቀነስ፣ ሥራንና ንግድን ማቀላጠፍ እንዲሁም ሰዎች ገንዘብ በሚያስፈልጋቸው ጊዜና መጠን እንዲጠቀሙ እያስቻለ ይገኛል። ይህም ከባንክ ውጭ የሚዘዋወር የገንዘብ መጠንና የህትመት ወጪ እንዲቀንስና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲጨምር አስችሏል። ከዚህ አኳያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፉ እንዲመጣ የታቀደው ግብ እየተሳካ ነው። በፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያና መሶብ የአንድ ማዕከል የመንግሥት አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ለማስፋት በተሰራ ስራ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል። እነዚህ ወሳኝ የመንግስት ውሳኔዎች የተቀናጀ የመንግሥት አገልግሎት ምህዳርን በመፍጠር ዜጎች አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ግልጽ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲያገኙ እያስቻሉ ይገኛሉ። እነዚህ በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራር ስርዓቶች አገልግሎት ለማግኘት ይባክን የነበረውን ጊዜና ወጪ ከመቀነሳቸው ባለፈ ቢሮክራሲንና ብልሹ አሰራረን በመቀነስ በኩል ከለፍትኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። በመደመር መንግሥት እሳቤ ከተገለጡ የሀገር ሀብቶች መካከል ለቱሪዝም ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት የተገኙ አመርቂ ስኬቶች ይጠቀሳሉ። በዚህም አቧራ ለብሰው የቆዩ እና ለቱሪዝም መስህብነት ቢውሉ ከፍተኛ ጠቀሜታ የነበራቸውን ሀገራዊ ሀብቶች በመግለጥና በማልማት ወደ ወረት የተቀየሩበት አስደማሚ ስራዎች ለዚህ ትልቅ ማሳያዎች ናቸው። ይህ ውጤታማ ተግባራም ዘርፉ እንዲነቃቃ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲያድግ በር ከፍቷል። በዚህም ኢትዮጵያ በባለፈው 2018 በጀት ዓመት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች። በሌላ በኩል ለበርካታ ዜጎችን ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል። በመላ ሀገሪቱ ለመሠረተ ልማት መስፋፋት የተሰጠው ትኩረትም የከተሞች ውበትና መስህብነት እንዲያድግ ጉልህ ሚና ተጫውቷል። በዚህም የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎች ፍሰት ጨምሯል። ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ማደግም እንዲሁ አስተዋጽኦው የጎላ ነው። የየአካባቢዎቹ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተነቃቅተዋል። የኢትዮጵያም የቱሪዝም ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጎላ አስችሏል። የመደመር መንግሥት በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም ለማዕድን ልማት እንዲሁ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚያስችል ምህዳር ተፈጥሯል። ባለፉት አመታት ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል። ቀደም ሲል በጥሬው ወደ ውጭ ይላኩ የነበሩ የወርቅ፣ ድንጋይ ከሰል፣ ኦፓልና ሌሎች ማዕድናት ላይ እሴት ተጨምሮባቸው ለወጪ ንግድ እንዲውሉ ለማድረግ አዳዲስ አሰራሮች በመዘርጋታቸው ስኬቶች ተመዝግበዋል። ለአብነትም ከወርቅ ምርት የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ መጠን አድጓል። ለምሳሌ በ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከወርቅ ወጪ ንግድ ከ5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች። በሲሚንቶ፣ ድንጋይ ከሰል፣ ሴራሚክ ምርቶች ለኢንዱስትሪና ለግንባታ ዘርፍ ግብዓት በመሆን በርካታ ፋይዳዎች ተገኝተዋል። የማዕድን ዘርፍ ለሥራ ዕድል ፈጠራና የአካባቢ ኢኮኖሚ መነቃቃት እንዲሁም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በጥቅሉ የመደመር መንግሥት የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ የቱሪዝም እና የማዕድን ዘርፎች ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የየድርሻቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል የወሰዳቸው የፖሊሲ እና የስትራቴጂ እርምጃዎች ሀገሪቱ በአዲስ የዕድገት አቅጣጫ እንድትጓዝ እያስቻላት ይገኛል። ይህም ለወጭ ንግድ የሚሆኑ ምርቶች በስፋት እንዲመረቱ፣ ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ በዚህም የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግና ለማዳን እንዲሁም የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥና አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ከመፍጠር ባለፈ የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ ስራዓት በማዘመን፣ ሀገሪቱ ዘላቂና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ብልጽግና እንድታስመዘግብ ጠንካራ መሠረት ጥሏል።
ትንታኔዎች
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Oct 10, 2026 144
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት እጩ የካቢኔ አባላትን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ሹመታቸውን አጸድቀዋል። የካቢኔ አባላቱ ሹመት ህዝብን የማገልገል አቅምና ፍላጎት፤ የትምህርት ዝግጁነት፣ የስራ ልምድና አጠቃላይ ውጤታማነትን መሰረት ያደረገ ነው። እንደ አጠቃላይ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የከፍታ ምዕራፍ የማሸጋገር አደራና ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። በቀጣይ በላቀ የስራ አፈፃፀም የሀገርን እድገት የማስቀጠልና በዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት በሚታይ ለውጥ ለማምጣት መትጋትም ይጠበቅባቸዋል። በተቋማት ቀጣይነት፣ በሥርዓት ግንባታና በሕዝብ አገልግሎት ውጤታማነት ላይ በመመሥረት የሀገር ግንባታን ሂደት ማስቀጠል የመደመር መንግስት አበይት ትኩረቱ አድርጎ እንደሚሰራም ይጠበቃል። የተቋማት ስኬት የሚለካው ለሕዝብ በሚሰጡት ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሁም ውጤታማ አገልግሎት በመሆኑ ሚኒስትሮቹ በዚሁ ልክ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል። የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የህዝብ እውነተኛ አገልጋይ ለመሆን የሚተጉ መሆን ይኖርባቸዋል። የመደመር መንግስት የካቢኔ አባላት እጩዎችም የመፈጸም አቅምና ፍላጎት፣ የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት እንደ መሠረታዊ መስፈርቶች ተወስደው የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የህዝብ እውነተኛ አገልጋይ ለመሆን በመዘጋጀት መሆኑን እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል። የመንግስት ሹመት “የሚዝናኑበት ሳይሆን የሚሰሩበት” ከፍተኛ የሕዝብ አደራ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የካቢኔ አባላት ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል እንዲተጉም አሳስበዋል። የመደመር መንግስት ሀገር የመምራት እድልም የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን የማስቀጠል፣ የተቋማትን ግንባታ የማጠናከር፣ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማስቀጠል ይሆናል።
ካለመችው ሸብረክ የማትል ኢትዮጵያ፤ ወጥቶ መግቢያ በሯን ታስከብራለች!!
Oct 9, 2026 136
በቤተልሔም ባህሩ ኢትዮጵያ የክንደ ብርቱዎች ምድርና የነጻነት ተምሳሌት መሆኗን ታሪክ ደጋግሞ ከትቦታል። በየዘመናቱ የተጎናጸፈቻቸው አኩሪ ገድልም የአፍሪካ ቀንዲልነቷን ደጋግማ እንድታረጋግጥ አስችለዋታል። ፈተናን ወደ ድል ተግዳሮትን ወደ ዕድል የምትቀይር በሕብርና ትብብር የተሸመነ አይበገሬ ሀገር መሆኗንም ታሪክ መዝግቧል፤ እየመዘገበም ይገኛል። ቅድመ አያቶቻችን በዓድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች ላይ ባበሩት የነጻነት ጮራ የፈነጠቀው የድል ችቦ ለጭቁን የዓለም ሕዝቦች የነጻነት ተስፋን አብስሯል። ከዚያ የድል ታሪክ የተሸጋገረው የኢትዮጵያውያን አርበኝነትም በዚያ የሚያበቃ አይደለም። በእያንዳንዱ የትውልድ ምዕራፍ አዲስ የታሪክ ገጽ እየተጻፈ ቀጥሏል። ከጉሊት ነጋዴ እናት እስከ ሀገር ጠባቂ ሰራዊት፣ ከጎልማሳ እስከ ታዳጊ፣ ከሀገር ውስጥ እስከ የተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋትና ተሳትፎ የሀገራቸውን የልማት ሕልም እውን ለማድረግ የሚደርጉት ጥረት የዚህ ትውልድ አይበገሬነት መገለጫ ነው። በዚህ የጋራ ጥረት ውስጥ በጉባ ተራሮች ግርጌ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሕዝብ ትብብርና የብሔራዊ ቁርጠኝነት ተጨባጭ ተምሳሌት ሆኗል። በጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም የተመረቀው ሕዳሴም የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ የሚያሳልጥ አቅም ፈጥሯል። ለአፍሪካውያኑም በራሳቸው አቅም ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማሳካት እንደሚችሉ የሚያመለክት የፓን አፍሪካኒዝም ሐውልት ሆኗል። የመደመር መንግሥት የልማት ፕሮጀክቶችን ለማሳካት የሚያደርገው ጥረትና የሚያሳየው ቁርጠኝነትም ኢትዮጵያ ህልሟን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ያላትን ጽኑ ፍላጎት ያመላክታል። በሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ወቅት የሕዳሴ ግድብ የዘመናችን ትውልድ የአይበገሬነት ማሕተም መሆኑ መገለጹም ይህንኑ ያረጋግጣል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ ወቅት ድጋሚ በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሰየማቸውን ተከትሎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ካለመችው ትልም ሸብረክ ሳትል ዕድገቷን የምታስቀጥል ሀገር መሆኗን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታትም በርካታ ፈተናዎችን በማለፍ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያፋጥኑ መሰረቶችን በመጣል ሀገርን የሚቀይሩ የልማት ትሩፋቶች መፍጠር መቻሉንም አብራርተዋል። ለአብነትም ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የቸራትን የውሃ ሀብት በራሷ ጥረት ለማልማትና ለመጠቀም ያጋጠሟትን ፈተናዎች በመሻገር ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ መቻሏን አንስተዋል። የግድቡ ስኬት የሀገሪቱን የኃይል ምርት አቅም ከማሳደግ ባሻገር ከጎረቤት ሀገራት ጋር በኃይልና በቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያሳልጥ ዕድል ይፈጥራል። ይህም የመደመር መንግሥት በጋራ ተጠቃሚነትና በትብብር ላይ የተመሰረተ የውጭ ግንኙነት አቅጣጫን እመርታዊ ጉዞ ያመለክታል። ከሕዳሴ ግድብ ተሞክሮ በመነሳት ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መሻቷንም በሰላማዊ የዲፕሎማሲ ድርድርና በጋራ ጥቅም መርህ ለማሳካት ጥረት እየተደረገ ነው። ለኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ከኢኮኖሚያዊ ፍላጎትና ቀጣናዊ ትስስር ጋር የተቆራኘ ስትራቴጂክ የሕልውና ጉዳይ ነው። ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት ምሥረታ ወቅት ካነሷቸው ዐበይት የልማትና የዕድገት ጉዳዮች አንዱ የባህር በር ጉዳይ ነው። ጎረቤቶቻችን በተፈጥሮ ያገኘናቸው ወዳጆቻችን ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ከሁሉም ጎረቤቶች ጋር በሰላም ፣ በጋራ ጥቅምና በትብብር የመስራት መርሃችንን እንገፋበታለን ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል። ነገር ግን የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልምና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን ሲሉ አስምረውበታል። በዚህም የኢትዮጵያን ታላቅነት፣ የዓለምና የአካባቢያችን ወቅታዊ ሁኔታ ብሎም የወደፊቱን የዓለም አካሄድ ያገናዘበ የመከላከያ ኃይል በመገንባት በቀጣናው የአየር የበላይነት ለመፍጠር የሚያስችል አቅም እንደሚገነባ አስታውቀዋል። የሚኖረን መከላከያ ዘመናዊ፣ ፈጣሪ፣ ሁሌም ዝግጁ ብቁና ንቁ በየአውዶቹ የመሰማራት አቅምና ቁመና ያለው እንደሚሆን በመጠቆም፤ ችግሮች ሳይፈጠሩ በፊት አስቀድሞ ማወቅና መግታት ከመጡም መከላከል ከባሰም እንደ አባቶቹ እንደልማዱ ማሸነፍ የሚችል ኃይል ሆኖ ይገነባል ብለዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ውጭ ግንኙነት ማዕከላዊ መርህ ብሔራዊ ጥቅምና የዜጎች ክብር መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አቅጣጫ ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ቀራጭነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት እንዲሸጋገር የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ምርጫዎችን ማጠናከር እንደሚገባም አብራርተዋል። በድንበር ተሻጋሪ ሀብቶች ላይ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና ኢትዮጵያ አስተማማኝ የባሕር በር የማግኘት መሻቷን በሰላማዊ መንገድ ማሳካት የውጭ ግንኙነቷ ትኩረት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መንግሥት በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቶቿን በፍትሐዊነት የመጠቀም መብቷን እንድታረጋግጥና የባሕር በር ጥያቄዋን በጋራ ጥቅምና በሰላማዊ ድርድር እንደምታሳካ ገልጸዋል። ይህ አቋም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ከጋራ ሰላምና ደኅንነት ጋር በማጣጣም በትብብርና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ያለውን ፍላጎት ያመለክታል። የዓባይን ውሃ በፍትሐዊነት የመጠቀም ቀጣይ መሻት፣ አስተማማኝ የባሕር በር የማግኘት ጥረት፣ ብሔራዊ ደኅንነትን ማረጋገጥና የዜጎችን ክብር የማስቀጠል ጥረት በሕዝብ ተሳትፎ፣ በመንግሥት ተቋማዊና በዜጎች አንድነት የሚጠናከሩ የጋራ ግቦች ናቸው። በመሆኑም የሕዝብ ትጋትና የመንግሥት ጥረት የኢትዮጵያን ትልቅ ሀገርነት፣ የሕዝቧን ታላቅነትና የሰነቀችውን ታላቅ ርዕይ እውን የሚያደርጉ ዋነኛ መሠረቶች ናቸው። የጠንካራ ሀገር መንግሥት ግንባታ ሂደት የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የዜጎችን ተሳትፎ፣ የተቋማትን ብቃት፣ የሕዝብን ትጋትና የትውልድን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ የጋራ ጉዞ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያውያን አንድነታችንን በማጎልበትና በብሔራዊ ጥቅም ዙሪያ በመተባበር የሀገራችንን ክብርና ጥቅም ለማስጠበቅ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት መወጣት ግድ ይለናል። የዘመኑ አርበኛ ትውልድም ከቀደሙት አያቶች የወረሰውን የነጻነትና የክብር ታሪክ በእውቀት፣ በሥራና በልማት በማላቅ ብሔራዊ ጥቅምና የዜጎችን ክብር ለማስከበር የሚጠይቀውን የጋራ ጥረትና ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል። ኢትዮጵያም የትናንትን መሰረት አጽንታ፣ የዛሬን አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ለተሻለ ነገ ትሰራለች። ምክንያቱም የትልቅ ሀገር ታላቅነት የሚረጋገጠው ከታሪክ ባሻገር በሕዝብ የጋራ ትጋት፣ በመንግሥት ተቋማዊ ጥረትና በትውልዱ የጋራ ቁርጠኝነት በሚገነባው የወደፊት ስኬትም ጭምር ነው። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብና ታላቅ ርዕይ የሰነቀችው ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መሻቷንም በሕዝብና በመንግሥት የተቀናጀ ጥረት ታሳካለች። የዘመኑ አርበኛ ትውልድ ብሔራዊ ጥቅሙንና ክብሩን ለማስጠበቅ መትጋት ይጠበቅበታል።
ሀገራዊ ብልፅግናን ከውጭ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ጋር የሚያስተሳስር አዲስ ምዕራፍ
Oct 9, 2026 104
የመደመር መንግሥት- ሀገራዊ ብልፅግናን ከውጭ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ጋር የሚያስተሳስር አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ኢትዮጵያ ዛሬ የምትገኝበት ምዕራፍ በታሪኳ ውስጥ ልዩ ቦታ የሚይዝ ነው። በአንድ ወቅት በፖለቲካዊ ውጥረት፣ በኢኮኖሚያዊ ጫና፣ በማኅበራዊ መለያየት እና በተለያዩ ሀገራዊ ፈተናዎች የተከበበች ሀገር፣ ዛሬ በራሷ አቅም እና በራሷ እሳቤ በመመራት የዕድገትና ብልፅግና ግስጋሴ ላይ ትገኛለች። ይህ ስኬት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በሕዝብ ፈቃድ ወደ ሥልጣን የመጣው አመራር በሀገር በቀል የመደመር እሳቤ ላይ ተመስርቶ ያከናወነው ጉዞ ውጤት ነው። የመደመር ፍልስፍና እንደ ፖለቲካ መርህ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ሀገር ግንባታ ስትራቴጂ ተቀርጾ የተተገበረ ነው። የዚህ እሳቤ አፍላቂ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ወቅቶች የተደቀኑ ውስብስብ ፈተናዎችን በመሻገር፣ ሀገሪቱን ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች ወደ መረጋጋት፣ ከመቆም ወደ መንቀሳቀስ፣ ከጥርጣሬ ወደ ተስፋ እና ከተግዳሮት ወደ ዕድል የመቀየር ቁርጠኛ አመራር አሳይተዋል። ዛሬ ኢትዮጵያ የምትናገረው ስለ ሕልውና ጥያቄ ሳይሆን፣ ስለ ብልፅግና፣ ስለ ከፍታ እና ስለ ቀጣይ ትውልድ ዕጣ ፈንታ ነው። ይህን ለውጥ የሚመሰክሩ ተጨባጭ ውጤቶችም በስምንቱ ዓመታት ጉዞ በስፋት ተመዝግበዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሀገራዊ ሕልም ወደ ተጨባጭ እውነት በመቀየር የኢትዮጵያን የልማት ፍላጎት እና የሕዝቧን ጽናት ለዓለም አስመስክሯል። የገበታ ለሸገር፣ የገበታ ለሀገር እና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ደግሞ የቱሪዝም ሀብቶችን ከጥላ ወደ ብርሃን በማምጣት፣ ተፈጥሮን፣ ታሪክን እና ልማትን አስተሳስረው ኢትዮጵያን አዲስ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን መሠረት ጥለዋል። በተመሳሳይ ጊዜ ሀገሪቱ ከአንድ ዘርፍ ተመርኩዞ ከሚጓዝ ኢኮኖሚ ወደ ብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ የመሸጋገር ጉዞ ጀምራለች። በቱሪዝም ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች፣ በማዕድን ዘርፍ የተፋጠነ እንቅስቃሴ፣ በግብርና የተመዘገበው የምርታማነት ዕድገት፣ በማኑፋክቸሪንግ የተፈጠሩ አዳዲስ አቅሞች፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ እና በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ የተመዘገቡ ለውጦች ኢኮኖሚውን የበለጠ ተወዳዳሪ እና ዘመናዊ እያደረጉት ነው። ዲጂታል ኢትዮጵያ፣ የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርሞች፣ የኢንቨስትመንት መስክ ማሻሻያዎች እና የአምራች ኢንዱስትሪ ማስፋፊያዎች የሕዝብን ተጠቃሚነት በማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ወደ ተጨባጭ ውጤት የቀየሩ ናቸው። በከተማ ልማት የተመዘገቡ ለውጦችም የመደመር መንግሥት እሳቤን ከቃል ወደ ተግባር የቀየሩ ግልጽ ማሳያዎች ናቸው። በተለይም የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ከተሞችን ዘመናዊ፣ ማራኪ እና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ምቹ በማድረግ የከተማ አኗኗር ዘይቤን በአዲስ መልክ እያሻሻሉ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ልማት ማለት የሕዝብን አኗኗር ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ማስፋት እና የሀገርን ገጽታ መቀየር መሆኑን ያሳያል። እነዚህ ተጨባጭ ውጤቶች በመሆናቸው ነው ሕዝቡ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በማሰብ ውሳኔ የሰጠው። የተጀመሩት ለውጦች እንዲቀጥሉ፣ የተገኙት ስኬቶች እንዲጠናከሩ እና የብልፅግና ጉዞው ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር በማመን ሕዝቡ የብልፅግና ፓርቲን በመምረጥ አዲሱ የመደመር መንግሥት እንዲመሠረት አድርጓል። ይህም ምርጫ የፖለቲካ ሂደት ብቻ ሳይሆን፣ ሕዝብ በተጨባጭ ውጤቶች ላይ የሰጠው እምነት እና ድጋፍ ነበር። በመሆኑም የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ የተመሠረተው አዲሱ የመደመር መንግሥት የአዲስ ካቢኔ ምሥረታ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ የከፍታ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት ታሪካዊ መድረክ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመንግሥት ምሥረታ ወቅት በምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው አንኳር ሀገራዊ ጉዳዮችም ይህንን እውነታ ያረጋግጣል። ኢኮኖሚያዊ ለውጥ፣ የከተማ ልማት፣ የግብርና ምርታማነት፣ የስልጣኔ ግንባታ እና የተቋማት ጥንካሬ እንደ ዋና ዋና የልማት ምሰሶዎች ቀርበዋል። በተለይም የሀገር ብልፅግና የሚገነባው በጠንካራ ኢኮኖሚ፣ በምርታማ ዜጎች፣ በዘመናዊ ከተሞች እና በጠንካራ ተቋማት መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል። ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመታት የምትከተለውን የልማት አቅጣጫም በግልጽ አመላክተዋል። ይህም በመደመር እሳቤ ላይ ተመስርቶ ልዩነቶችን ወደ ጥንካሬ፣ ችግሮችን ወደ ዕድል እና ሀብቶችን ወደ ብልፅግና የመቀየር መንገድ ያመላከተ ሆኗል። አዲሱ የመደመር መንግሥት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች ጠንካራ መሠረት እንዳለውም አረጋግጧል። ኢትዮጵያ በቀጣናው የምትጫወተውን ሚና ማጠናከር፣ የዲፕሎማሲ ተፅዕኖዋን ማሳደግ፣ የኢኮኖሚ ጥቅሞቿን ማስከበር እና የባህር በር ባለቤት የመሆን ጽኑ ፍላጎቷን በሰላማዊ እና በተቀናጀ መንገድ ለማሳካት ጠንካራ የውስጥ አቅም ያስፈልጋል። ያለ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ፣ ያለ ተቋማዊ ብቃት እና ያለ ሀገራዊ አንድነት ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስከበር አይቻልም። ስለዚህ የመደመር መንግሥት ምሥረታ የውስጥ ብልፅግናን ከውጭ ተፅዕኖ ፈጣሪነት ጋር የሚያስተሳስር ታሪካዊ እርምጃ ነው። በመሆኑም የመደመር መንግሥት ምሥረታ የፖለቲካ ክስተት ብቻ ሳይሆን፣ ከፈተና ወደ ዕድል፣ ከለውጥ ወደ ብልፅግና እና ከብልፅግና ወደ ከፍታ የሚወስደውን ሀገራዊ ጉዞ የሚያጠናክር አዲስ ታሪካዊ ውል ነው። ዛሬ የተጀመረው ጉዞ የአንድ መንግሥት ወይም የአንድ ትውልድ ጉዞ ብቻ አይደለም፤ የበለጸገች፣ የተረጋጋች፣ በቀጣናው ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ብሔራዊ ጥቅሞቿን በሙሉ ማስከበር የምትችል ኢትዮጵያ የመገንባት ታሪካዊ ሂደት ነው።
የላቀች ኢትዮጵያ - የመደመር መንግስት
Oct 8, 2026 443
የመደመር መንግስት ምስረታን ተከትሎ ሀገሪቱ ወደ አዲስ የፖለቲካና የዕድገት ምዕራፍ የሚያሸጋግራትን መንገድ ጀምራለች። ይህ ታሪካዊ ምዕራፍ አዲስ መንግስት ከመመስረት ባለፈ አዲስ አቅጣጫና ተስፋን ይዞ መጥቷል። ይህ ጉዞ ሀገሪቱ ካለፉት ውስብስብ ፈተናዎች ወጥታ ወደ ላቀ የስልጣኔ ማማ፣ ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለመሻገር ያላትን ፅኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። አዲሱ መንግሥት ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በነፃና በዴሞክራሲያዊ መንገድ በሰጡት ድምፅ ላይ የቆመ መሆኑ፣ ከሕዝብ ጋር ያለውን ማህበራዊ ውል በአዲስ መልክ ያደሰበት የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ተደርጎም ይወሰዳል። ይህ አዲስ አቅጣጫ የሕዝብን የነገ ብሩህ ተስፋ በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት እንዲሁም የልማትና እድገት ስኬቶችን በላቀ የውጤታማነት ደረጃ ለማስቀጠል የተቀረፀ ታላቅ ራዕይ ነው። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሰላምና ጸጥታን ይበልጥ ማጽናት፣ የባህር በር ባለቤት መሆን፣ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግሩን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ፣ የማህበራዊ ልማትና ጥበቃ ሥራዎችን ማጠናከር እንዲሁም መሠረተ ልማትን ማስፋፋት የመንግሥት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው። የተያዙት እቅዶች በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን ይበልጥ ለማጠናከር፣ ተቋማዊ አቅምን ለማጎልበት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ ምቹ መደላድል የሚፈጥሩ ናቸው። አዲሱ መንግሥት ለገበያ መረጋጋት፣ ለቤት አቅርቦት እና ለሀገራዊ ሁለንተናዊ ዕድገት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ተመልክቷል። የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጠርባቸውን መስኮች በማስፋፋት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ ትልቁ የቤት ሥራ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመታቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ጠንካራና አይበገሬ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ስርዓት እየገነባች ያለች ሀገር መሆኗን ገልጸዋል። ማንኛውም የውስጥና የውጭ ፈተና የሀገሪቱን የሥልጣኔና የብልጽግና ጉዞ ሊያቆመው አይችልም ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የያዘቻቸውን ታላላቅ እቅዶች እውን ለማድረግ የመንግሥትና የሕዝብ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይሄንን ታላቅ ርዕይ እውን ለማድረግ ያስችላቸው ዘንድ በህዝብ ድምጽ የተመረጠውና አደራንም የተረከበውን መንግስት ካቢኔ በአዲስ መልክ አደራጅተዋል። የሃገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስቀድሙ ለህዝብ ተጠቃሚነት ያለድካም በትኩረት የሚሰሩና በጥብቅ ዲሲፕሊን የተመረጡ አባላትን በማደራጀትና ሹመታቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማስጸደቅ ስራ ጀምረዋል። ከአመራሩ ባለፈ ደግሞ ዜጎችም በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ተመልካች ብቻ ሳይሆኑ የለውጡ ባለቤት በመሆን፣ የላቀች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም ይጠበቃል። መሆንም አለበት። ይህ አዲሱ የመንግሥት ምሥረታና ግዙፍ ሀገራዊ ትልሞች፣ ኢትዮጵያን ወደ ላቀ የሥልጣኔና የብልጽግና ምዕራፍ ለማሻገር መሰረት ናቸው።
ልዩ ዘገባዎች
ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር
Oct 9, 2026 118
ነጋሪ መጽሔት የዓባይ ውሃ አጠቃቀምና የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት በስፋት ተንትናለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ፣ “የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም” በማለት ሀገሪቱ የባሕር መዳረሻ እንድታገኝ በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ይህ ጥረት በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ተጠቃሚነትና በ“ሰጥቶ መቀበል” መርሕ እንደሚመራ በማስገንዘብ፣ ጉዳዩን ከአፍሪካ ቀንድ፣ ከቀይ ባሕርና ከመካከለኛው ምሥራቅ እየተለወጡ ካሉ የጂኦፖለቲካና የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ጋር አያይዘው አቅርበዋል። መጽሔቷም በመስከረም 2019 ዓ.ም. እትሟ “የኢትዮጵያ የትንሳኤ መንገድ፡ ከዓባይ እስከ ቀይ ባሕር ፖለቲካ የዘለቀው ፍጥጫ” በሚል ርዕስ ባቀረበችው ትንታኔ፣ የውሃ ሀብት፣ የባሕር መዳረሻ፣ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችና የቀጣናዊ ደኅንነት ጉዳዮች በሀገራት መካከል ባለው የኃይል አሰላለፍ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ዳስሳለች። እንደ መጽሔቷ ትንታኔ፣ ዓባይና ቀይ ባሕር በተፈጥሮ የተለያዩ የውሃ አካላት ቢሆኑም፣ በዘመናዊው የጂኦፖለቲካ ስሌት ውስጥ በውሃ አጠቃቀም፣ በኢኮኖሚያዊ ጥቅም፣ በባሕር መዳረሻና በደኅንነት ጉዳዮች የተሳሰሩ ናቸው። የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያና ለተፋሰሱ ሀገራት ለኃይልና የልማት ጥቅም ሲኖረው፣ ቀይ ባሕር ደግሞ አፍሪካን፣ እስያንና አውሮፓን የሚያገናኝ ወሳኝ የዓለም አቀፍ የንግድና የባሕር መተላለፊያ ነው። በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የዓባይ ውሃን በፍትሐዊነትና በጋራ ተጠቃሚነት የማስተዳደር ጥያቄና የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በቀጣናው የፖለቲካና የደኅንነት ስሌቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ መጽሔቷ በስፋት ተንትናለች። የ1929 እና የ1959 የውሃ ስምምነቶች የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም በበቂ ሁኔታ እንዳልተካተቱ በመግለጽ፣ የወንዙ ውሃ አጠቃቀም በፍትሐዊነት፣ በትብብርና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ ማዕቀፍ መመራት እንዳለበት አመልክታለች። ኢትዮጵያ በ1993 ዓ.ም በኋላ የባሕር በር መዳረሻዋን ማጣቷን ተከትሎ፣ ጉዳዩ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ ከብሔራዊ ደኅንነትና ከረጅም ጊዜ የልማት ፍላጎት ጋር እንደተያያዘ መጽሔቷ አትታለች። የባሕር በር መዳረሻ ማግኘት የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ የወደብ አማራጮችን ለማስፋትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ወሳኝ መሆኑንም አብራርታለች። በሌላ በኩል፣ ቀይ ባሕር ከእስያ፣ ከአፍሪካና ከአውሮፓ የንግድ መስመሮችን የሚያገናኝ ስትራቴጂካዊ የባሕር መተላለፊያ በመሆኑ፣ በአካባቢው ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከአካባቢያዊ ግንኙነቶች ባለፈ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ፍሰትን ይነካል። መጽሔቷ የቀይ ባሕር የጂኦፖለቲካ አስፈላጊነት ከስዊዝ ቦይና ከባብ-ኤል መንደብ የባሕር መተላለፊያ ጋር በማያያዝ የዳሰሰች ሲሆን፣ በአካባቢው የሚካሄዱ የኃይል ፉክክሮች የንግድና የደኅንነት ስጋቶችን እንደሚያባብሱ ተንትናለች። መጽሔቷ በትንታኔዋ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ከቀጣናው ሀገራት የፖለቲካ አቋሞች ጋር በማያያዝ የተለያዩ ትንታኔዎችን አቅርባለች። ሆኖም እነዚህ በመጽሔቷ የቀረቡ የፖለቲካ ትንታኔዎች ሲሆኑ፣ የተጠቀሱ አቋሞችንና ክሶችን ከተረጋገጡ እውነታዎች መለየት ያስፈልጋል። መጽሔቷ በዓባይ ውሃ አጠቃቀምና በባሕር መዳረሻ ጉዳይ ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶች በግጭት ሳይሆን በውይይት፣ በድርድርና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ መፍትሔ ማግኘት እንዳለባቸው አጉልታለች። የውሃ ሀብትን በፍትሐዊነት ማስተዳደርና የባሕር መዳረሻ ጉዳይን በሰላማዊ ስምምነት መፍታት ለቀጣናዊ መረጋጋት፣ ለኢኮኖሚ ትብብርና ለዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆናቸውን በትንታኔዋ አመልክታለች። የመጽሔቱ ሊንክ https://www.ena.et/web/negari/w/negari_9696604
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 322
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 209
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 214
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
መጣጥፍ
የከተሞች ትንሳኤ ምሥጢር - የመደመር መንግሥት
Oct 9, 2026 137
በታዬ ለማ 👉አዲስ አበባ ዳግም አብባለች ጎህ ሲቀድ በአዲስ አበባ ላይ የሚወጣው ፀሐይ ዛሬ ሌላ ከተማ ያበራል። ሰፋፊ መንገዶቿ ላይ ብርሃን ሲያርፍ፣ በእግረኛ መንገዶቿ ላይ የማለዳ ተጓዦች ሲተላለፉ፣ በወንዞቿ ዳርቻ የተሠሩ ፓርኮች አረንጓዴ ሲለብሱ ማየት ይቻላል። ይህች ከተማ እንደ ስሟ አዲስ ሆናለች። ይህ ለውጥ ግን ድንገት የመጣ አይደለም፤ በትልቅ ቁጭት የተገነባ የትውልድ ተሻጋሪ አሻራ ነው፡፡ 👉አገር እየተቀየረች ነው የመደመር መንግሥት ባለፉት ዓመታት አገርን የሚቀይሩና ኢትዮጵያን ወደ ፊት ያራመዱ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል። በኢኮኖሚው ዘርፍ ታሪካዊ ውጤት ተመዝግቧል። ኢትዮጵያ ስንዴን ከውጭ የምታስገባ አገር መሆኗ ቀርቶ ዛሬ ወደ ውጭ የምትልክ ሆናለች። በኢንዱስትሪው ዘርፍም ትልቅ ድል ተገኝቷል፤ ቀደም ሲል ብዙ የውጭ ምንዛሬ ያስወጡ የነበሩ ምርቶች አሁን እዚሁ ይመረታሉ፤ በዚህም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል። በማዕድን ዘርፍ እስከ ዛሬ ታይቶ በማያውቅ መንገድ የኢትዮጵያ ማዕድናት እንዲወጡ እየተደረገ ነው፤ አገሪቱም ከዚህ ሀብቷ ተጠቃሚ እየሆነች ነው። በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሠሩት ሥራዎች አስደናቂ ናቸው፤ መንግሥት በቴክኖሎጂ የተገነባች የነገዋን ኢትዮጵያ ለመፍጠር ምን ያህል ርቀት እንደተጓዘ ያሳያሉ። በቱሪዝም ዘርፍ ደግሞ «ገበታ ለሀገር»፣ «ገበታ ለሸገር» እና «ገበታ ለትውልድ» በተሰኙ ማዕቀፎች አስደናቂ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል። በዚህ ሳቢያ አብዛኞቹ የአገሪቱ ክፍሎች በአስደናቂ ሁኔታ ተቀይረዋል። ታሪካቸው ተለውጦ አዲስ መልክ የያዙት እነዚህ ስፍራዎች ለዜጎቻቸው ኑሮ የተመቹ ከመሆናቸውም በላይ የውጭ አገር ዜጎች ጭምር ሊጎበኟቸው የሚናፍቋቸው ከተሞች እየሆኑ ነው። ከእነዚህ ሁሉ መካከል እንደ ስሟ በመደመር መንግሥት ዘመን አዲስ መሆን የቻለችው አዲስ አበባ ጎልታ ትታያለች። 👉«ውብ አበባ» የተባለችው አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛው የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ይህንኑ እውነታ አንስተዋል። ከተሞቻችን የዘመናዊ ከተማ መልክ ለመያዝ በጀመሩት ጥረት ለመኖሪያ የተመቹ፣ ለንግድና ለኮንፈረንስ የተስማሙ፣ ተምሳሌት ተደርገው የሚጠቀሱም እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል። «ዛሬ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ውብ አበባ ተብላ ብትጠራ እውነት እንጂ ባዶ ምኞት ተደርጎ አይወሰድም» ብለዋል። አያይዘውም የአዲስ አበባ ለውጥ የዓለም ጎብኚዎችን «ኑ ወደ እኔ» እያለ የሚጣራ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት እውነት ነው። 👉ትናንት የነበረችው አዲስ አበባ ይህ ጥሪ ምን ያህል ትልቅ ለውጥ እንደሆነ ለመረዳት ወደ ኋላ መለስ ብሎ ማየት ያስፈልጋል። አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መዲና፣ የአፍሪካም የዲፕሎማሲ ማዕከል ሆና ለዘመናት በአገሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ቦታ ይዛ ኖራለች። ይሁን እንጂ እድገቷ ከደረጃዋ ጋር ፈጽሞ አይጣጣምም ነበር። በአብዛኞቹ የከተማዋ ክፍሎች ደረጃውን የጠበቀና ከተሽከርካሪ መንገድ የተለየ የእግረኛ መንገድ አልነበረም። እግረኛው ከመኪና ጋር እየተጋፋ ይጓዝ ነበር፤ መንገዶቿም ለትራፊክ አደጋና ለእግረኞች እንግልት ዋና ምክንያት ነበሩ። የመንገድ ዳር መብራቶች ካሉበት ቦታ ይልቅ የሌሉበት አካባቢዎች በርከት ይሉ ነበር፤ በርካታ አደባባዮችና መንገዶችም ከፍተኛ ጥገና ይፈልጉ ነበር። ዘመናዊና አማራጭ የትራንስፖርት ዘዴዎችን የሚያበረታቱ መንገዶች ደግሞ ጨርሶ የሚታሰቡ አልነበሩም። ሌላው ጎልቶ የሚታይ ክፍተት የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች እጥረት ነበር። ነዋሪው ነፃ ጊዜውን የሚያሳልፍበት ሰፊ ቦታ አልነበረውም። በከተማዋ ውስጥ አቋርጠው የሚያልፉ በርካታ ወንዞችና የወንዝ ዳርቻዎችም ተንከባካቢ በማጣታቸው በቆሻሻ ተሞልተው የአካባቢ ጥበቃ ሥጋት ሆነው፣ የበሽታ ምንጭና የደህንነት ስጋትም ነበሩ፡፡ እንደ ካዛንቺስና አራት ኪሎ ባሉ የከተማዋ እምብርት ሰፈሮች ውስጥ በአንድ ወቅት ተደራርበው የቆሙ አሮጌ የጭቃ ቤቶች፣ ጠባብ ጥጋጥጎች እና የታጨቁ መንደሮች የተለመደ ገጽታ ነበሩ። የዘመናት ታሪክ የተሸከሙ ሕንፃዎችና መኖሪያዎች ተገቢውን እድሳትና እንክብካቤ ሳያገኙ በጊዜ ሲሸረሸሩ ኖረዋል። ከተማዋ ወጥ የሆነ የውበትና የቀለም መመሪያ ስላልነበራት ገጽታዋ የተበታተነ ነበር፤ የታሪካዊ ስፍራዎችና የሐውልቶች ዙሪያም በቂ ጽዳትና ብርሃን አላገኘም ነበር። ዛሬ ግን ያ ገጽታ ወደ ታሪክነት እየተሸጋገረ ነው። እነዚሁ ሰፈሮች በዘመናዊ ዕቅድ ተቃኝተው፣ ታሪካዊ ሕንፃዎቻቸው ታድሰውና ተጠብቀው፣ በተዋሃደ የቀለምና የዲዛይን ቅንብር አዲስ መልክ እየያዙ ነው። ሐውልቶችና ታሪካዊ ስፍራዎች በጽዳትና በምሽት ብርሃን ተውበው፣ ለነዋሪው ኩራት ለጎብኚውም መስህብ ሆነው ይታያሉ። 👉ትንሳኤ ዛሬ ግን ታሪኩ ተቀይሯል። አዲስ አበባ የትናንት ገጽታዋን በማይታመን ሁኔታ እየቀየረች ነው። ነዋሪው ለውጡን እያጣጣመው ነው፤ ዓለምም አድናቆቱን እየገለጸ ነው። ትናንት የነበረችው አዲስ አበባ ላትመለስ ተሰናብታለች። መዓዛዋ ተቀይሯል፤ ደስ የማይል ገጽታዋና ሽታዋም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተወግዷል። አዲስ አበባ በእርግጥም አዲስ ሆናለች። 👉የመደመር መንግሥት ለአዲስ አበባ ትንሳኤ ሆኗታል። ዛሬ እንደ ስሟ አዲስ ሆና ተገንብታለች። በኮሪደር ልማቷ፣ በስማርት ሲቲ ግንባታዋና በሰው ተኮር ልማቶቿ ለዜጎቿ ምቹ እየሆነች፣ የአፍሪካ መዲናነቷንም በትክክል እያረጋገጠች ትገኛለች። የኮሪደር ልማት አዲስ አበባን ከጊዜው ጋር የሚመጥንና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሠረተ ልማት ባለቤት ያደረገ ትልቅ የለውጥ ምዕራፍ ነው። ፕሮጀክቱ መንገድን ከማሻሻል ባለፈ የከተማዋን ሁለንተናዊ ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይሯል። 👉ከመንገድ እስከ እግረኛ የከተማዋ ዋና ዋና አውታሮች ሰፊና ደረጃቸውን የጠበቁ ሆነው እንደገና ተገንብተዋል። ተሽከርካሪዎች ቀልጣፋ ፍሰት አግኝተዋል፤ የትራፊክ እንግልትም በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ቀሏል። ቀደም ሲል ትኩረት ተነፍጎት የነበረው እግረኛ አሁን ትክክለኛውን የመራመጃ ቦታ አግኝቷል። የእግረኛ መንገዶች ተስፋፍተዋል፤ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መተላለፊያዎች፣ ንጹሕና ውብ የእግረኛ መንገዶች እንዲሁም የብስክሌት መጋለቢያ መስመሮች ተካተዋል። ዜጎች ደኅንነታቸው በተጠበቀ፣ ምቹ በሆነ አካባቢ መንቀሳቀስ ጀምረዋል። ምሽት ሲመጣም ከተማዋ አትደበዝዝም። ዘመናዊና ኃይል ቆጣቢ የመብራት ሥርዓቶች፣ የዲጂታል መረጃ መስጫ ሰሌዳዎችና ውብ የመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማቶች ውበቷንና ደኅንነቷን ይጨምራሉ። ይህ የተቀናጀ ልማት አዲስ አበባን የነዋሪዎቿን ፍላጎት የምታሟላ፣ ለኑሮና ለሥራ ምቹ፣ የአፍሪካ መዲናነቷንም በሥራ ያረጋገጠች ዘመናዊ ከተማ አድርጓታል። 👉ወንዞችና አረንጓዴ ስፍራዎች በአንድ ወቅት የቆሻሻ መጣያና የከተማዋ ሥጋት የነበሩት የወንዝ ዳርቻዎችና ክፍት ቦታዎች ዛሬ የከተማዋ ዋነኛ የመስህብ ሀብትና የጽዳት ማዕከል ሆነዋል። በከተማዋ ማዕከልና አካባቢ የሚያልፉ ጥንታዊ ወንዞች ከቆሻሻ ተነጥለው የተፈጥሮ ፍሰታቸውን ጠብቀው እንዲፈሱ ተደርገዋል። ዳርቻዎቻቸው በድንጋይና በኮንክሪት ግድግዳዎች ተጠብቀው ከጎርፍ ሥጋት ነፃ ሆነዋል። በወንዝ ዳርቻዎች ላይ የተገነቡት ውብ ፓርኮች፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎችና የስፖርት ማዕከላት ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ሁለንተናዊ የዕረፍትና የመዝናኛ አማራጭ ፈጥረዋል። የዛፎችና አረንጓዴ ተክሎች መብዛት የከተማዋን የአየር ጥራት አሻሽሏል፤ የሙቀት መጠኑን አመጣጥኖ የተፈጥሮ ሥነ ምኅዳሩ እንደገና እንዲያንሰራራ አድርጓል። በዚህም አዲስ አበባ አረንጓዴ፣ ንጹሕና ለኑሮ እጅግ ተስማሚ ሆናለች። 👉ሰላምና ደኅንነት የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበትና ገጽታ ብቻ አልቀየረም፤ ወንጀልን በመከላከልም ትልቅ ሚና እየተወጣ ነው። ፍትሕ ሚኒስቴር «የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በወንጀል መከላከልና ደኅንነት ማረጋገጥ ላይ ያለው ሚና» በሚል ርዕስ ባካሄደው ጥናት ይህንኑ አመልክቷል። በተለይ ለጎዳና ወንጀል ምቹ የነበሩ ስፍራዎች እንዲጠፉ በማድረግ አስተማማኝ ሰላምና ደኅንነት እንዲረጋገጥ ዕድል መፍጠሩን ጥናቱ ያሳያል። 👉ጉዞው ይቀጥላል ታላቅ ሕዝብን የሚመጥን ርዕይ የሰነቀችው ኢትዮጵያ፣ ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን ይበልጥ የማደስ ተግባሯን አጠናክራ ትቀጥላለች። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማዋን ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለመምራት በተመረጡበት ወቅት ያረጋገጡትም ይህንኑ ነው። በቀጣዮቹ ዓመታት አዲስ አበባን ይበልጥ ጽዱ፣ ሳቢ፣ ምቹና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ የማድረጉ የሪፎርም ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው በማለት አፅንኦት ሰጥታዋል። ትናንት የነበረችው አዲስ አበባ ተሰናብታለች። ዛሬ የምትታየው አዲስ አበባ ደግሞ ገና ጅማሬዋ ላይ ናት። 👉አዲስ አበባ የለኮሰችው የልማት ችቦ በሁሉም ይበራል ከአዲስ አበባ የተነሳው የልማት ብርሃን በዚያው አልተወሰነም፤ ወደ ሁሉም የአገሪቱ ማዕዘናት እየተሰራጨ ነው። በመዲናዋ የተጀመረው የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ፓርኮችና የከተማ እድሳት ልምድ ወደ ሌሎች ከተሞች ተሸጋግሮ፣ ዛሬ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያሉ ከተሞች አዲስ መልክ እየያዙ ይገኛሉ። የመደመር መንግሥት የሚያከናውነው ልማት ማንንም ወደ ኋላ የማይተው፣ ሁሉንም አካባቢዎች በእኩል ዓይን የሚያይና ያቀፈ ነው። በ«ገበታ ለሀገር»፣ «ገበታ ለሸገር» እና «ገበታ ለትውልድ» ማዕቀፎች በተለያዩ ክልሎች የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ በየከተማው የሚታዩ ዘመናዊ መንገዶችና የመዝናኛ ስፍራዎች፣ እንዲሁም በገጠር የሚካሄዱ የግብርና እና የመሠረተ ልማት ሥራዎች አንድ እውነት ይናገራሉ፤ ልማቱ የአንድ ከተማ ሳይሆን የመላው አገር መሆኑን። አዲስ አበባ ለሌሎች ከተሞች አርአያ ሆና ስትቆም፣ ሌሎች ከተሞችም በየፊናቸው አብበው የአገሪቱን ውበት እያበዙ ነው። በዚህም ኢትዮጵያ በአንድ ማዕከል ብቻ የምታደምቅ ሳትሆን፣ በሁሉም ማዕዘኗ የምታበራ፣ ዜጎቿም በየትኛውም ቦታ የልማቱ ተካፋይና ተጠቃሚ የሆኑባት አገር እየሆነች ነው።
ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ
Oct 7, 2026 241
ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል።የመደመር መንግሥት ከትናንት በስትያ በይፋ በተመሠረተበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርላማ ያቀረቡት ንግግር የመንግሥቱን አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን የወደፊት ራዕይ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የንግግራቸው ማዕከላዊ ጭብጥም ኢትዮጵያ ዘላቂ ችግሮቿን የምትፈታው በራሷ የሥልጣኔ መንገድ ስትጓዝ ብቻ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የብዝሃ ሥልጣኔ ሀገር መሆኗን አንስተዋል። ለዘመናት የታሪክ፣ የባህል፣ የእምነት እና የማንነት መገናኛ ሆና ቆይታለች። ለብዙ ሕዝቦች መነሻ፣ ለብዙ ትውልዶች መነቃቃት ምንጭ የሆኑ ታሪኮችን በውስጧ ይዛለች። ሆኖም ይህን ታላቅ ቅርስ ወደ ዘላቂ ልማትና ዕድገት በመቀየር ረገድ ፈተናዎች በተደጋጋሚ ያጋጥማሉ። የጀመርነውን ማስቀጠል፣ የተገነባውን ማስጠበቅ እና በትውልድ መካከል ቀጣይነትን ማረጋገጥ ትልቁ ፈተና መሆኑንም አስገንዝበዋል።አንድ ትውልድ የገነባውን ሌላው ትውልድ እያፈረሰ የሚሄድበት ሁኔታ ሥልጣኔን እንደማይፈጥር ፣ ሀገርንም እንደማያበለጽግ አብራርተዋል። በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ በብዙ ዘርፎች ያላትን አቅም ሙሉ በሙሉ መጠቀም አልቻለችም። ሀሳብን በውይይት ከመፍታት ይልቅ በኃይል ለማስፈጸም የተደረጉ ጥረቶች ሀገሪቱን ወደ ኋላ ጎትተዋል። በመሆኑም የመደመር መንግሥት መልዕክት ግልጽ ነው፤ የኢትዮጵያ ችግሮች መፍትሔ የሚገኘው በግጭት ሳይሆን በመግባባት፣ በመደመር እና በጋራ ግብ ዙሪያ በመሰባሰብ ነው። አዲሱ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማለት የመከባበር ባህልን መገንባት፣ ሕግን ማክበር፣ ልዩነቶችን እንደ ጥንካሬ መቀበል እና የጋራ ሀገራዊ ራዕይ መፍጠር ነው። ይህ ደግሞ ስሜትን በማሸነፍ፣ ጥላቻን በመተው እና አቅምን በጋራ በማሰባሰብ የሚሳካ ታላቅ ሀገራዊ ርዕይ ነው። በዚህ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር የመንግሥት ቀዳሚው አጀንዳው ነው። ከሁሉም የዓለም ሀገራት ጋር የሚደረገው ግንኙነት የኢትዮጵያን ጥቅም እና ተጽዕኖ የሚያሳድግ መሆን አለበት ብለዋል። ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያ በሌሎች ፍላጎት የምትመራ ሳይሆን በራሷ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ተመስርታ የምትወስን ጠንካራ ሀገር መሆኗን ነው። በቀጣናውም ኢትዮጵያ የመረጋጋት እና የትብብር ማዕከል ሆና ትቀጥላለች። ጎረቤቶቿ በተፈጥሮ ያገኘቻቸው አጋሮቿ በመሆናቸው የጋራ ጥቅም፣ የሰላም እና የትብብር መርሆዎች የውጭ ግንኙነቷ መሠረት እንደሚቀጥሉ አጽንዖት ሰጥተዋል። በዚህም ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም በማስከበር እና በጋራ ጥቅም መርህ ላይ ተመስርታ የቀጣናው ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር ለመሆን ትሰራለች። በመሆኑም የመደመር መንግሥት ምሥረታ የአስተሳሰብ ለውጥ፣ የሥልጣኔ ግንባታ ጥሪ እና ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ አዲስ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ ነው። ይህ ጉዞ ስኬታማ የሚሆነው ደግሞ መንግሥት፣ ፓርላማ፣ ተቋማት እና ሕዝብ በአንድ ራዕይ ሲተባበሩ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ያላትን ታሪካዊ ቅርስ ወደ ዘመናዊ ሥልጣኔ በመቀየር፣ ብሔራዊ ጥቅሟን በማስከበር እና በቀጣናው የሰላም አርበኛ ሆና በመቆም አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅታለች። የኢትዮጵያ ዘላቂ ብልጽግና፣ የሕዝቦቿ አንድነት እና የቀጣናው ደህንነት የሚረጋገጠው አዲስ ኢትዮጵያዊ ሥልጣኔ በሚገነባበት መጠን ነው።