ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የህዝቦችን አብሮነትና ወንድማማችነትን የሚያጎለብቱ እሴቶችን በጥናትና ምርምር ማልማትና መጠቀም ይገባል
Jan 11, 2026 12
ሲዝ፣ ጥር 3/2018 (ኢዜአ)፡- የህዝቦችን አብሮነትና ወንድማማችነትን የሚያጎለብቱ ባህላዊ እሴቶችን በጥናትና ምርምር ማልማትና መጠቀም እንደሚገባ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን ገለጹ። የቤንች ዘመን መለወጫ "ቢስት ባር"ን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የፓናል ወይይት በዞኑ ሲዝ ከተማ ተካሄዷል። በመድረኩ ላይ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን እንደገለጹት "ቢስት ባር" በቤንቾች መንደር የጋራ ደስታ የሚጎላበት እና የደረሰ አዝመራን ሰብስበው ፈጣሪን የሚያመሰግኑበት ባህላዊ ኩነት ነው፡፡ በዓሉ ዘመን ከመለወጥ ባሻገር የደረሰን እህል ከጎረቤት ጋር በአንድነት በመቅመስ የሚከበር መሆኑ የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴቱ ጎልቶ የሚንጸባረቅበት እንደሆነም ገልጸዋል። እነዚህ እሴቶች ለአካባቢውና ለሀገር ልማት መጎልበት ያላቸውን ፋይዳ በጥናትና ምርምር በማስደገፍ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሠራ አመልክተዋል። የሼይ ቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክፍሌ ጎበዜ በበኩላቸው በዓሉ የያዛቸውን ቱባ ባህሎች ከአካባቢው መስህብ ስፍራዎች ጋር በማስተሳሰር የቱሪዝም ሀብት እንዲሆን ለማስቻል ትኩረት ተደርጓል ብለዋል። ከአባቶቻችን የመጣውን አብሮ ሰርቶ አብሮ የማደግና የመተባበር ልምድ ወጣቱ አውቆት በመተግበር ለሀገር እድገት ሚናውን እንዲወጣ ማስቻል አለብን ሲሉም ገልጸዋል። የ"ቢስት ባር" ፓናል ውይይት ላይ "ኢኮኖሚያዊ ሥርዓትና የቢስት ባር ባህላዊ መሠረቶች" በሚል ርዕስ ጽሑፍ ያቀረቡት ካሳሁን ሙላት(ዶ/ር) በዓሉ ከምርት ጋር የተገናኘ በዓል በመሆኑ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍ እንደሚል ተናግረዋል። በተለይም ከ"ቢስት ባር" ማግስት ለቀጣዩ ዓመት ሰፊ የግብርና ሥራ ለማከናወን ቤንቾች ወደ ማሳቸው የሚዘምቱበት መሆኑ ዘላቂና አስተማማኝ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋገጥ ዕሴቱ ጉልህ እንደሆነ አብራርተዋል። እነዚህን ባህላዊ ሥርዓቶች ከዘመናዊ እውቀት ጋር በማስተሳሰር የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን አመልክተዋል። የፓናል ውይይቱ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በዓሉ ጥር 4 እና 5 ቀን 2018ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት በሼይ ቤንች ወረዳና ሚዛን አማን ከተማ ይከበራል።
በክልሉ ከታችኛው እርከን ጀምሮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቷል
Jan 11, 2026 35
ባህርዳር፤ ጥር 3/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ገለፁ። በባህርዳር ከተማ በ28 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ የመስከረም16 የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ተመርቋል። በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት ላይ ግብ ተይዞ እየተሰራ ነው። ለዚህም በሁሉም ቀበሌዎች አንድ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ለመገንባት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናገረዋል። ከፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በባህር ዳር ከተማ በመስከረም 16 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሞዴል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ መጠናቀቁ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል። ወደፊትም ባለሃብቶችን፣ ህብረተሰቡንና አጋር አካላትን በማስተባበር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን የመገንባቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በበኩላቸው ትምህርት ለአንድ ሀገር ዕድገትና ብልፅግና መሰረት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። በዚህም ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ ሁኔታ የመፍጠሩ ተግባር ተጠናከሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። በባህርዳር ከተማ በ28 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የመስከረም16 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ለሌሎች ሞዴል ነው ያሉት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሙሏለም አቤ (ዶ/ር) ናቸው። ትምህርት ቤቱ 14 የመማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር ቢሮዎችና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች ያሉትና የውስጥ ቁሳቁስ የተሟላለት መሆኑን ተናግረዋል ። የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቱ 760 ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ አቅም ያለው መሆኑንም አመልክተዋል። የፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ቴሬንስ ሂላቢ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የትምህርትን ተደራሽነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በሰላምና በልማት ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ የበደልነውን ህዝብ ለመካስ ተዘጋጅተናል
Jan 11, 2026 40
ደብረብርሃን፤ጥር 3/2018 (ኢዜአ)፡-በሰላምና ልማት ሥራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የበደልነውን ህዝብና መንግስት ለመካስ ተዘጋጅተናል ሲሉ በሰሜን ሸዋ ዞንና በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሰላም አማራጭን የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች ገለጹ። በአማራ ክልል በርካታ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪን ተቀብለው ወደ ቀደመ ህይወታቸው እየተመለሱ መሆኑም ተመላክቷል። በሰሜን ሸዋ ዞንና በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የቀድሞ ታጣቂዎች በደብረ ብርሃን የስልጠና ማዕከል ዛሬ የተሀድሶ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል። ከተመላሾቹ መካከል ከምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የመጣው ፈለቀ ሰጤ በተሳሳተ መንገድ በመጓዝ በህዝብ ላይ ባደረሰው በደልና ጥፋት መጸጸቱን ተናግሯል። ትግሉ የህዝብን ሃብትና ንብረት በመዝረፍ ለመበልጸግ ያለመ መሆኑን በመገንዘቤ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብዬ ወደሰላም ተመልሻለሁ ብሏል። ስንፈጽመው በነበረው የጥፋት ተግባር ህብረተሰቡን ከመበደል ባለፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው በመስተጓጎሉ ለጸጸት መዳረጉን ገልጾ፣ ከተሀድሶ ስልጠና በኋላ ህዝቡን ለመካስ እንደሚሰራ ተናግሯል። ከባሶና ወራና ወረዳ የመጣው ተስፋዬ ጌታቸው በበኩሉ፥ የህብረተሰቡን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በማወክ ባደረስኩት በደል በመጸጸትና የመንግስትን ጥሪ በመቀበል ተመልሻለሁ ብለዋል። አሁንም ጫካ ቀርተው በጥፋት ተግባራቸው የቀጠሉት ትምህርት እንዲቋረጥ፣ንጹሀን እንዲገደሉ በማድረግ የሚመለስ የፖለቲካ ጥያቄ እንደሌለ ተገንዝበው ወደሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል። በቀጣይ በየአካባቢው በሚከናወኑ የሰላምና የልማት ሥራዎች ላይ ጉልህ አስተዋጾ በማድረግ የበደሉትን ህዝብና መንግስት ለመካስ ዝግጁነታቸውንም አረጋግጠዋል። ከቡልጋ ከተማ አስተዳደር የመጣው ሙሉቀን መስፍን በበኩሉ፥ ትግሉ የአማራን ህዝብ ጥያቄ የሚያስመልስ ሳይሆን የጥቂቶች ሀብት ማከማቻ እየሆነ መምጣቱን በመገንዘብ የመንግስትን የሰላም አማራጭ መቀበሉን ተናግሯል። የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ደጀኔ ልመንህ እንዳሉት፥ ሰላምን በዘላቂነት ለማጽናት ከህዝብ ጋር የተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች ውጤት እያስገኙ ናቸው። በአሁኑ ወቅት በክልሉ በርካታ ታጣቂዎች የሰላምን ጥሪ ተቀብለው ወደ ቀደመ ህይወታቸው እየተመለሱ መሆኑን ጠቁመው፣ ለተመላሾቹ የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት በፈለጉት የሙያ ዘርፍ እንዲሰማሩ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። አሁንም በጫካ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በሀይል የሚመለስ ምንም አይነት ጥያቄ እንደማይኖር በመረዳትና የጥፋት ተግባራቸውን በመተው የሰላምን አማራጭ እንዲቀበሉ አስገንዝብዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ ዓለማየሁ በበኩላቸው፥ በዞኑ የሰፈነው ሰላም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንዲሻሻል መልካም እድል ፈጥሯል ብለዋል። መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተመለሱ ወንድሞች አሁንም ሳይመለሱ በጫካ ያሉ ታጣቂዎችን መክረው ወደሰላም እንዲመለሱና የበደሉትን ህዝብ እንዲክሱ የድርሻቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል። በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደርና በዙሪያው እየሰፈነ ያለው ሰላም ለኢንዱስትሪና ለንግድ ሥራዎች መስፋፋት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የተናገሩት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ናቸው። ወደሰላም የመጡ የቀድሞ ታጣቂዎችን በቀጣይ በሚፈልጉት የሥራ ዘርፍ ለማሰማራት በአስተዳደሩ በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።
የስፖርት ቱሪዝም መጠናከር ለኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መነቃቃት ፋይዳው የጎላ ነው
Jan 11, 2026 38
ደብረብርሃን ፤ጥር 3/2018 (ኢዜአ) ፡- ስፖርት ጤናማና አምራች ዜጋን በመፍጠር የአካባቢውን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ምርታማነት ለማሳደግ የጎላ ፋይዳ አለው ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በደሉ ውብሸት ገለጹ። የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 2018 የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች ዛሬ በደብረብርሃን ከተማ ተካሂደዋል። ውድድሮቹም የ6 ኪሎ ሜትር የሴቶችና ወንዶች ሩጫ እና የ22 ኪሎ ሜትር የዱላ ቅብብልን ያካተተ ነው። የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በእለቱ እንደገለጹት ስፖርት ጤናማና አምራች ዜጋን በመፍጠር ለአካባቢው ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ምርታማነት እድገት የጎላ ፋይዳ አለው። በተጨማሪም ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ስፖርተኞችንና ተመልካቾችን በማገናኘት ለማህበራዊ ትስስር መጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። በደብረ ብርሃን የተካሄደው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያም የከተማዋን እድገት፣ የመስህብ ስፍራዎችና ጸጋዎችን ለማስተዋወቅ መልካም እድል የሚፈጥር በመሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ቡድን መሪ አቶ አክሊል ጌታቸው እንዳሉት ከተማዋ ያላት የአየር ንብረት ለስፖርታዊ ውድድሮች አመቺ ነው። ዛሬ የተካሄደው የስፖርት ውድድርም ወንድማማችነትን ለማጠናከርና ያሉ የተፈጥሮ ፀጋዎችን ለማስተዋወቅ የሚያግዝ በመሆኑ አዘጋጆቹን አመስግነዋል። የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ሀላፊ ወይዘሮ ሃና ገብረስላሴ በበኩላቸው ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ ህፃናትን፣ ወጣቶችንና ታዋቂ አትሌቶችን ያሳተፈ ውድድር መካሄዱን ገልጸዋልⵆ ውድድሩም የ6 ኪሎ ሜትር የሴቶችና ወንዶች ሩጫ እና የ22 ኪሎ ሜትር የዱላ ቅብብልን ያካተተ እንደነበር አንስተዋል። በ6 ኪሎ ሜትር የወንዶች ሩጫ ውድድር 1ኛ የወጣው ስጦታው ሰማኸኝ እንዳለው እንደዚህ ያለ ውድድር ያልታወቁ አትሌቶች የሚታዩበት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
በአፋር ክልል ከለውጡ ዓመታት ወዲህ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የክልሉን የመልማት አቅምን ያሳዩ ናቸው
Jan 11, 2026 94
ሰመራ፣ጥር 3/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል ከለውጡ ዓመታት ወዲህ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የክልሉን የመልማት አቅም ማሳየት የቻሉ መሆናቸውን በብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ተናገሩ። በብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ አመራሮች በክልሉ በሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደርና በዱብቲ ወረዳ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በወቅቱ እንዳሉት፥ በአፋር ክልል ከለውጡ ዓመታት ወዲህ በርካታ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል። የልማት ስራዎቹ የክልሉን የመልማት አቅም ያሳዩ መሆናቸውን አመልክተዋል። የአዋሽ ወንዝን ለመስኖ አገልግሎት እንዲውል በማድረግ ሰፋፊ እርሻዎች መሠራታቸውን መመልከታቸውን ገልጸው፤ በተለይም በዱብቲ ወረዳ እየለማ ያለው የስንዴና የሱፍ ምርት አስደናቂ መሆኑን ተናግረዋል። በሌማት ትሩፋት መርሃግብር በተለይም በዶሮ፣እንቁላል፣ በዘመናዊ ከብት እርባታ ረገድ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልፀዋል። ክልሉ የብልፅግና ተስፋ የሚታይበት መሆኑን የገለፁት አቶ ፍቃዱ፤በሠመራ ከተማ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማትም የህብረተሰቡን ባህልና እሴት መሠረት ያደረገ፣ከተሜነትን ያዋሃደና ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልፀዋል። በብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኀላፊ ወይዘሮ ማርታ ወይቤ በበኩላቸው፥ በክልሉ የተሰሩ ስራዎች ከዚህ ቀደም ስለ በረሃ የነበረውን አመለካከት ጭምር የቀየሩ ናቸው ብለዋል። በተለይም የሠመራ ከተማ ኮሪደር ልማት ባህላዊ ይዘቱን የጠበቀ፣ማራኪና ከተማዋን እያንሰራሩ ከሚገኙ ከተሞች ተርታ እንድትመደብ የሚያደርጋት መሆኑን አመልክተዋል። በክልሉ በለውጡ ዓመታት የታዩ ተግባራት የሀገሪቷን ማንሰራራትና እመርታዎችን ያንፀባረቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ በበኩላቸው፥ በአፋር ክልል ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም የብልፅግናን መንገድ የሚያግዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። የህዝብ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረጉ ስራዎች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ እየተሰሩ መሆናቸውን ተመልክተናል ብለዋል። "ጠንካራ አደረጃጀት ለጠንካራ ፓርቲ" በሚል መሪ ሀሳብ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ መድረክ ትናንት በሰመራ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል።
ፖለቲካ

በክልሉ በሰፈነው ሠላም ልማትን የማጠናከር ሥራ ይቀጥላል
Jan 11, 2026 87
አሶሳ፤ጥር 3/2018 (ኢዜአ)፦በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰፈነውን ሠላም በመጠቀም ልማትን የማጎልበት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ። የቤኒሻንጉል ብሔረሰብ ምክር ቤት ከመንጌ ወረዳ መስተዳድር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት "የህዝብ ለህዝብ ትስስር መድረክ" በመንጌ ወረዳ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፤ በክልሉ የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። የህዝበ ለህዝብ ትስስር መድረኩ በክልሉ የሰፈነውን ሠላም ለማጽናትና አብሮነትን ለማጠናከር የሚያግዝ ነው ብለዋል። ክልሉ የተፈጥሮ ሀብትን ወደ ልማት በመቀየር የዜጎችን ተጠቃሚነት በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ህብረተሰቡን ያሳተፈ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡ በልማት ስራዎች ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ በማጠናከር ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ መትጋት ይጠበቅበታል ሲሉም ተናግረዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አስካለች አልቦሮ በበኩላቸው፤ የህዝቦችን ትስስር ማጠናከር ለጋራ ዓላማ እንዲቆሙ የሚያደርግ እና የዜጎችን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ የሚያሳድግ ነው ብለዋል። በቀጣይም ተመሳሳይ መድረኮችን በማዘጋጀት ህብረተሰቡ ክልላዊ እና ሀገራዊ የልማት አጀንዳዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዝ ይደረጋል ነው ያሉት። የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር ለዘላቂ ሠላም እና አብሮነት የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ያሉት ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር ናቸው። የመደመር መንግስት ከህብረተሰቡ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎችን በማድመጥ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ተናግረው ህብረተሰቡ የልማት ስራዎች ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። በመድረኩ ላይ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የመንጌ ወረዳ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ርዕይ አቅጣጫ ይሰጣል። መደመር ጥንካሬን ያጎናፅፋል። እነዚህ ተደምረው ነገን ይገነባሉ።
Jan 10, 2026 177
ርዕይ አቅጣጫ ይሰጣል። መደመር ጥንካሬን ያጎናፅፋል። እነዚህ ተደምረው ነገን ይገነባሉ። #PMOEthiopia የቢሾፍቱ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ይሆናል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቢሾፍቱ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በይፋ አስጀመሩ
በኢትዮጵያ በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎች ለትውልድ ምንዳ ማውረስ የሚያስችሉ ናቸው -ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)
Jan 10, 2026 112
ባህር ዳር፤ ጥር 2/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት አመታት በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎች ለትውልድ ምንዳ ማውረስ የሚያስችሉ ናቸው ሲሉ በብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) ተናገሩ። ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ አመራሮች በተገኙበት የ6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)፤ በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት አመታት በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎች ለትውልድ ምንዳ ማውረስ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል። ለዚህም ብልጽግና ፓርቲ ትናንትን፣ ከዛሬና ነገ ጋር አሰናስሎና አስተሳስሮ ለትውልድ ምንዳ ለማውረስ የሚያስችሉ ስኬታማ ስራዎችን አከናውኗል ብለዋል። ፓርቲው በተለይም ባለፉት ዓመታት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የዲፕሎማሲ ድሎችን ማስመዝገቡን አንስተው ከተረጅነት የመውጣት ጥረትም ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል። በግብርና ልማት፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪ እና ሌሎችም ብዝሃ ኢኮኖሚ ዘርፎች የላቀ ስኬት ተመዝግቧል ብለዋል። በግንቦት ወር የሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲከናወን ብልጽግና የድርሻውን ለመወጣት ከወዲሁ ዝግጅት ማድረጉንም ተናግረዋል። በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፤ በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር በመቀልበስ ወደ ዘላቂ ሰላምና የተሟላ ልማት መገባት መቻሉን ገልጸዋል። በክልሉ በተለይም ለሰላም አማራጭ ትኩረት በመስጠት ስኬታማ ስራ መሰራቱን አንስተው የሰላምን አማራጭ በሚገፋ የጥፋት ቡድን ላይም የተጠናከረ ህግ የማስከበር እርምጃ መወሰዱን አንስተዋል። ለሁለት ቀናት የሚካሄደው መድረክ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ተገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ውይይት የሚደረግ መሆኑ ታውቋል።
የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ በሁሉም መስኮች የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተገኘባቸው ነው
Jan 10, 2026 131
ሰመራ፤ ጥር 2/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ በሁሉም መስኮች የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ ተናገሩ። "ጠንካራ አደረጃጀት ለጠንካራ ፓርቲ" በሚል መሪ ሀሳብ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ መድረክ በሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው። መድረኩን ያስጀመሩት የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ እንዳሉት ፓርቲው የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያረጋግጡ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ስራዎችም የብልፅግና አይቀሬነት እየተረጋገጠ መምጣቱን ጠቅሰው ከዚህ ውስጥ አንዱ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሆኑን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመትም ሀገርን ወደ ከፍታ ያሸጋገሩ ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶች የተፈጸሙበት እና ይፋ የተደረጉበት መሆኑንም ገልጸዋል። ለከተሞች ዕድገት ወሳኝ የሆኑ አንፀባራቂ ስራዎች በተለያዩ ከተሞች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው ይኼም ከተጠቃሚነት አኳያ የህብረተሰብን ጥያቄዎች መመለስ የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ በሁሉም መስኮች የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን ነው ያብራሩት። በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ መሐመድ ሁሴን በበኩላቸው ፓርቲው ባለፉት ዓመታት ሁሉንም አኩል ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን አንስተዋል። በክልሉም ከዚህ በፊት ያልተለመዱ ሰፋፊ የግብርና ልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው በሰመራ ከተማም የተከናወነው የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋን ለነዋሪው ጽዱ እና ምቹ ማድረግ አስችሏል ብለዋል። በክልሉ በተለይም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚደረገው ጉዞ ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወልኦ አይትሌ ናቸው።
አዲሱ የቀበሌ አደረጃጀት ነዋሪዎች መንግስታዊ አገልግሎቶችን በቅርበት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል
Jan 9, 2026 376
ሮቤ ፤ጥር 1/2018 (ኢዜአ):-በኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ የቀበሌ አደረጃጀት መንግስታዊ አገልግሎቶችን በቅርበት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን በባሌ ዞን የሀረና ቡሉቅ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ። የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ በ189 ቀበሌዎች የተዋቀረው አደረጃጀት ለነዋሪዎች አገልግሎት በቅርበት ለመስጠት ከማስቻሉ ባለፈ ጊዜና ወጪን በመቆጠብ በልማት ሥራዎች ላይ እንዲያተኩሩ ማድረጉን ገልጿል። አዲሱን የቀበሌ አደረጃጀት በማስመልከት አስተያየታቸውን ከሰጡ የሀረና ቡሉቅ የቁምቢ ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል አቶ ሀሰን አህመድ እንዳሉት፣ አደረጃጀቱ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎቶች በቅርበት ለማግኘት አስችሏቸዋል። ከዚህ በፊት መንግስታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ወረዳና ከተማ አስተዳደር የሚያደርጉት ምልልስ ጊዜና ድካም እንደነበረው አስታውሰው "አዲሱ የቀበሌ አደረጃጀት ይህንን በማቃለል ተጠቃሚ አድርጎናል" ብለዋል። ሌላኛው ተገልጋይ አቶ አህመድ መሐመድ በበኩላቸው እንዳሉት የቀበሌ አደረጃጀቱ የህዝብን የልማት ተሳትፎ በማሳደግ ከዚህ በፊት የነበሩት የመሰረተ ልማት ችግሮች በህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲፈቱ ዕድል ፈጥሯል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ከተከናወኑ የልማት ሥራዎች መካከል ድልድይና ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን ለአብነት ጠቅሰዋል። የሀረና ቡሉቅ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ሀሰን በበኩላቸው አዲሱ አደረጃጀት የወረዳውን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በቅርበት ለመመለስ እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል። የባሌ ዞን አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ብርሃኑ አርፋሳ በበኩላቸው በዞኑ የሚገኙ 189 ቀበሌዎች በአዲሱ አደረጃጀት ተዋቅረው ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግሯል። በቀበሌ አደረጃጀቶችም አመራሮች ተመድበው ህብረተሰቡን በቅርበት እንዲያገለግሉ መደረጉን ገልጸዋል። እንደ አቶ ብርሀኑ ገለጻ በአዲሱ የቀበሌ አደረጃጀት እየተሰጠ ያለው የህዝብ አገልግሎት ከዚህ በፊት ወደ ዞንና ወረዳዎች በተደጋጋሚ ይመጡ የነበሩ ቅሬታዎችን እየቀነሰና የህዝብ እርካታን እየጨመረ መጥቷል። በቀበሌዎቹ የተመደቡ አመራሮችና በለሙያዎች ህብረተሰቡን በተሻለ እንዲያገለግሉ የአቅም ግንባታ ሥልጠናና የድጋፍና ክትትል ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቅርበት ለመፍታት አዲስ የቀበሌ አደረጃጀት ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል። አደረጃጀቱ ህዝቡ በልማት ተጠቃሚ እንዲሆንና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎቹም በህዝብ ተሳትፎ መፍትሄ እንዲያገኙ ያለመ መሆኑ እንዲሁ።
ኢትዮጵያ እና ቻይና በዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታቸውን በይበልጥ ለማጠናከር ተወያዩ
Jan 8, 2026 233
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 30/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እና ቻይና በተለያዩ በርካታ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታቸውን በይበልጥ አጠናክረው ማስቀጠል በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን ተቀብዬ በጽናት በሚጓዘው የኢትዮጵያ እና ቻይና የመንግሥት እና ሕዝብ ግንኙነት ላይ ተነጋግረናል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀበሉ ኢትዮጵያ እና ቻይና ለአስርት ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸውም ገልጸዋል። ይኽ ግንኙነት በቅርቡ ወደ በሁኔታዎች የማይለዋወጥ የስትራቴጂክ ትብብር ማደጉንም አስታውቀዋል። በተለያዩ የልማት ትብብር ርዕሰ ጉዳዮችን ለማከናወን ያለንን ጽኑ አቋም በማስቀጠል ላይ ውይይት አድርገናልም ነው ያሉት። በኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ መሠረተ ልማት፣ የኃይል አቅርቦት እና ትራንስፖርት ብሎም አዲስ በመፈጠር ላይ ባሉ እንደኢ-ኮሜርስ፣ ዲጂታል ኢኮኖሚ፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና አረንጓዴ ኃይል ልማት ላይ ትብብራችንን ለማጠናከር ተወያይተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀበሉ
Jan 8, 2026 211
አዲስ አበባ ፤ ታኅሣስ 30/2018(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ዛሬ መቀበላቸውንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። ጉብኝቱ የወል ፍላጎት በሆኑ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን ያካትታል ተብሎ እንደሚጠበቅም አመልክቷል።

ማህበራዊ
የህዝቦችን አብሮነትና ወንድማማችነትን የሚያጎለብቱ እሴቶችን በጥናትና ምርምር ማልማትና መጠቀም ይገባል
Jan 11, 2026 12
ሲዝ፣ ጥር 3/2018 (ኢዜአ)፡- የህዝቦችን አብሮነትና ወንድማማችነትን የሚያጎለብቱ ባህላዊ እሴቶችን በጥናትና ምርምር ማልማትና መጠቀም እንደሚገባ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን ገለጹ። የቤንች ዘመን መለወጫ "ቢስት ባር"ን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የፓናል ወይይት በዞኑ ሲዝ ከተማ ተካሄዷል። በመድረኩ ላይ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን እንደገለጹት "ቢስት ባር" በቤንቾች መንደር የጋራ ደስታ የሚጎላበት እና የደረሰ አዝመራን ሰብስበው ፈጣሪን የሚያመሰግኑበት ባህላዊ ኩነት ነው፡፡ በዓሉ ዘመን ከመለወጥ ባሻገር የደረሰን እህል ከጎረቤት ጋር በአንድነት በመቅመስ የሚከበር መሆኑ የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴቱ ጎልቶ የሚንጸባረቅበት እንደሆነም ገልጸዋል። እነዚህ እሴቶች ለአካባቢውና ለሀገር ልማት መጎልበት ያላቸውን ፋይዳ በጥናትና ምርምር በማስደገፍ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሠራ አመልክተዋል። የሼይ ቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክፍሌ ጎበዜ በበኩላቸው በዓሉ የያዛቸውን ቱባ ባህሎች ከአካባቢው መስህብ ስፍራዎች ጋር በማስተሳሰር የቱሪዝም ሀብት እንዲሆን ለማስቻል ትኩረት ተደርጓል ብለዋል። ከአባቶቻችን የመጣውን አብሮ ሰርቶ አብሮ የማደግና የመተባበር ልምድ ወጣቱ አውቆት በመተግበር ለሀገር እድገት ሚናውን እንዲወጣ ማስቻል አለብን ሲሉም ገልጸዋል። የ"ቢስት ባር" ፓናል ውይይት ላይ "ኢኮኖሚያዊ ሥርዓትና የቢስት ባር ባህላዊ መሠረቶች" በሚል ርዕስ ጽሑፍ ያቀረቡት ካሳሁን ሙላት(ዶ/ር) በዓሉ ከምርት ጋር የተገናኘ በዓል በመሆኑ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍ እንደሚል ተናግረዋል። በተለይም ከ"ቢስት ባር" ማግስት ለቀጣዩ ዓመት ሰፊ የግብርና ሥራ ለማከናወን ቤንቾች ወደ ማሳቸው የሚዘምቱበት መሆኑ ዘላቂና አስተማማኝ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋገጥ ዕሴቱ ጉልህ እንደሆነ አብራርተዋል። እነዚህን ባህላዊ ሥርዓቶች ከዘመናዊ እውቀት ጋር በማስተሳሰር የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን አመልክተዋል። የፓናል ውይይቱ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በዓሉ ጥር 4 እና 5 ቀን 2018ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት በሼይ ቤንች ወረዳና ሚዛን አማን ከተማ ይከበራል።
በክልሉ ከታችኛው እርከን ጀምሮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቷል
Jan 11, 2026 35
ባህርዳር፤ ጥር 3/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ገለፁ። በባህርዳር ከተማ በ28 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ የመስከረም16 የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ተመርቋል። በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት ላይ ግብ ተይዞ እየተሰራ ነው። ለዚህም በሁሉም ቀበሌዎች አንድ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ለመገንባት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናገረዋል። ከፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በባህር ዳር ከተማ በመስከረም 16 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሞዴል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ መጠናቀቁ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል። ወደፊትም ባለሃብቶችን፣ ህብረተሰቡንና አጋር አካላትን በማስተባበር የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን የመገንባቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በበኩላቸው ትምህርት ለአንድ ሀገር ዕድገትና ብልፅግና መሰረት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። በዚህም ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ ሁኔታ የመፍጠሩ ተግባር ተጠናከሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። በባህርዳር ከተማ በ28 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የመስከረም16 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ለሌሎች ሞዴል ነው ያሉት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሙሏለም አቤ (ዶ/ር) ናቸው። ትምህርት ቤቱ 14 የመማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር ቢሮዎችና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች ያሉትና የውስጥ ቁሳቁስ የተሟላለት መሆኑን ተናግረዋል ። የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቱ 760 ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ አቅም ያለው መሆኑንም አመልክተዋል። የፓርትነርስ ኢን ኢዱኬሽን ኢትዮጵያ ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ቴሬንስ ሂላቢ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የትምህርትን ተደራሽነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በሀላባ ዘመን መለወጫ በዓል ያሉትን የአብሮነትና የእርስ በርስ ትስስር እሴቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
Jan 11, 2026 89
ቁሊቶ፣ ጥር 3/2018 (ኢዜአ)፡-የሀላባ ዘመን መለወጫ በዓል "ሴራ" ሲከበር ያሉትን የአብሮነት፣ የመረዳዳትና የእርስ በርስ ትስስር እሴቶችን በሚያጠናክር መልኩ መሆን እንዳለበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ "ሴራ በዓላችን በህብረት የመቻል አቅም ማሳያችን" በሚል መሪ ሀሳብ የሀላባ የዘመን መለወጫ በዓል "ሴራ" በተለያዩ ክዋኔዎች ዛሬ በሀላባ ስታዲየም ተከብሯል፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዓሉ ሲከበር ያሉትን የእርስ በርስ ትስስርና የአብሮነት እሴቶችን በሚያጠናክር መልኩ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል። የ"ሴራ" በዓል ከልዩነት ይልቅ አብሮነትና እርስ በርስ መደጋገፍን ለማጠናከር የሚያግዙ እሴቶች እንዳሉት ጠቅሰው፣ በዓሉ ከሃላባዎች ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ጋር የተሳሳረ መሆኑንም አመልክተዋል። የህዝቦችን አብሮነት በማጠናከር የጋራ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ሥራዎች እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ በበዓሉ ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ነፊሳ አልመሀዲ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር የሚረዱ በርካታ እሴቶች እንዳሉ አንስተዋል፡፡ የሀላባ የዘመን መለወጫ በዓል "ሴራ" የአብሮነት፣ የመረዳዳትና የመተሳሰብ እሴት ጎልቶ ከሚንፀባረቅባቸው ባህሎች አንደኛው መሆኑን ጠቅሰው፣ የበዓሉ መከበር እነዚህን ማህበራዊ እሴቶች አጠናክሮ ላማስቀጠል ጠቀሜታ አለው ብለዋል። የቤተሰብ ኃላፊነትንና የሥራ ድርሻን በአግባቡ መወጣት ጭምር የሚያስተምር በመሆኑ ለልማታዊ እንቅስቃሴ አበርክቶው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል። የበዓሉን እሴቶች ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍና ለማጎልበት በሚደረገው ጥረት ሚኒስቴሩ የሚጠበቅበትን ሚና እየተወጣ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን በበኩላቸው ሀላባ የራሱ የሆነ ቋንቋ፣ ባህልና የተለያዩ ባህላዊ እሴቶች እንዳሉት አንስተዋል። የዘመን መለወጫ "ሴራ" በዓል በታህሳስ ወር መጠናቀቂያ እና በወርሃ ጥር መግቢያ እንደሚከበርም ነው የተናገሩት። በዓሉ በሃላባዎች ዘንድ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ መሆኑን ጠቁመው፣ ለአቅመ አዳም የደረሱ ወጣቶች ራሳቸውን ለማስተዳደር ወደ ድርብ ኃላፊነት የሚሸጋገሩበት መሆኑንም አመልክተዋል። "ሀላባ ተከባብሮና ተደማምጦ በጋራ ለመልማት የሚረዱ በርካታ እሴቶች አሉት" ያሉት ደግም የበዓሉ ታዳሚ ወይዘሮ አሚና ኢሳ ናቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ አንዱ የሆነው የሀላባ ዘመን መለወጫ በዓል የአብሮነት እሴት የሚጎላበት በዓል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዓሉን ከሌሎች ወንድምና እህት ህዝብች ጋር በአብሮነት በማክበራቸው ደስተኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በበዓሉ አከባበር ሥነ ስርዓት ላይ ከፌዴራልና ከክልሉ የመጡ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡
ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በሥርዓተ-ትምህርት በማካተት ለሀብት ፈጠራና ለሀገር ዕድገት የማዋል ቅድመ ዝግጅት ተጀምሯል
Jan 11, 2026 87
አዲስ አበባ፤ጥር 3 / 2018 (ኢዜአ)፦ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በሥርዓተ-ትምህርት በማካተት ለሀብት ፈጠራና ለሀገር ዕድገት የማዋል ቅድመ ዝግጅት መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢትዮጵያዊያን ሀገር በቀል ዕሴቶች፣ ዕውቀቶች፣ ባህሎችና የአኗኗር ዘይቤዎች ለዜጎች አብሮነት፣ ለሀገር ልማትና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ወሰን ተሻጋሪ ፋይዳ እንዳላቸው ይጠቀሳል። የዜጎችን ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ዕሴቶች ለዘላቂ ልማትና አብሮነት ግንባታ የሚያበረክቱትን ጉልህ አስተዋትኦ በመንከባከብና በማጥናት ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ይነሳል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ሀገር በቀል ዕውቀቶች የዜጎች የሁለንተናዊ የማንነት መነሻና መሠረት ናቸው። የኢትዮጵያዊያን ዕምቅ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለዜጎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማዋል በተበታተነ አግባብ የተደረጉ ጥናቶች የሚፈለገውን ያክል ውጤት እንዳላመጡ ገልጸዋል። የዘርፉ ተመራማሪዎችና ሥራ ፈጣሪዎች በማሳተፍ የኢትዮጵያዊንን ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በተደራጀ ጥናትና ምርምር ለሀገር ዕድገትና ብልጽግና ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ሀገር በቀል ዕውቀቶች በሥርዓተ ትምህርት ማካተት የሚያስችል ፕሮጀክት በመቅረጽ በተደራጀ ጥናትና ምርምር ሰንዶ በመለየት ለሀገር ዕድገት ለማዋል ወደ ሥራ መገባቱን አንስተዋል። ሀገር በቀል ዕውቀቶችንም ለሥርዓተ ትምህርት፣ ለፖሊሲ፣ ለልማትና ልዩ ልዩ የሀገር ልማት ግብዓትነት ለማዋል የልየታ ውሳኔ ማሳለፍ የሚያስችል ጥናት ለማካሄድ ዝግጅት መጀመሩን አስታውቀዋል። ከፍተኛ የትምህርትና የምርምር ተቋማት ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በሚያጠኑበት ወቅት ማህበረሰቡ የአካባቢ የሀገር በቀል ዕውቀት መረጃዎችን በአግባቡ በመስጠት ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት የሀገር በቀል ዕውቀት የመሰነድ ጅማሮ አስተባባሪ ፕሮፌሰር ምርጊሳ ካባ፤ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በመሰነድ በትምህርት ሥርዓቱ ማካተት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ነው ብለዋል። በቀጣይም ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በሳይንሳዊ የጥናትና ምርምር ሥርዓት በማበልጸግ ለሀገር ሁለንተናዊ ልማት እንዲውሉ ለማስቻል በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በባሕር-ዳር ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ህይወት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደስታው ዳምጤ (ዶ/ር)፤ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚደረጉ የምርምር ሥራዎች የኢትዮጵያን የዕውቀት ምንጭነት የሚገልጡ ናቸው ብለዋል። ለሀገር ዕድገትና ለዜጎች ዘላቂ ሰላም ግንባታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸውን ሀገር በቀል ዕውቀቶች መለየት የሚያስችል ጥናትና ምርምር እያካሄዱ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
በአፋር ክልል ከለውጡ ዓመታት ወዲህ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የክልሉን የመልማት አቅምን ያሳዩ ናቸው
Jan 11, 2026 94
ሰመራ፣ጥር 3/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል ከለውጡ ዓመታት ወዲህ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የክልሉን የመልማት አቅም ማሳየት የቻሉ መሆናቸውን በብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ተናገሩ። በብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ አመራሮች በክልሉ በሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደርና በዱብቲ ወረዳ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በወቅቱ እንዳሉት፥ በአፋር ክልል ከለውጡ ዓመታት ወዲህ በርካታ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል። የልማት ስራዎቹ የክልሉን የመልማት አቅም ያሳዩ መሆናቸውን አመልክተዋል። የአዋሽ ወንዝን ለመስኖ አገልግሎት እንዲውል በማድረግ ሰፋፊ እርሻዎች መሠራታቸውን መመልከታቸውን ገልጸው፤ በተለይም በዱብቲ ወረዳ እየለማ ያለው የስንዴና የሱፍ ምርት አስደናቂ መሆኑን ተናግረዋል። በሌማት ትሩፋት መርሃግብር በተለይም በዶሮ፣እንቁላል፣ በዘመናዊ ከብት እርባታ ረገድ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችም የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልፀዋል። ክልሉ የብልፅግና ተስፋ የሚታይበት መሆኑን የገለፁት አቶ ፍቃዱ፤በሠመራ ከተማ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማትም የህብረተሰቡን ባህልና እሴት መሠረት ያደረገ፣ከተሜነትን ያዋሃደና ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልፀዋል። በብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኀላፊ ወይዘሮ ማርታ ወይቤ በበኩላቸው፥ በክልሉ የተሰሩ ስራዎች ከዚህ ቀደም ስለ በረሃ የነበረውን አመለካከት ጭምር የቀየሩ ናቸው ብለዋል። በተለይም የሠመራ ከተማ ኮሪደር ልማት ባህላዊ ይዘቱን የጠበቀ፣ማራኪና ከተማዋን እያንሰራሩ ከሚገኙ ከተሞች ተርታ እንድትመደብ የሚያደርጋት መሆኑን አመልክተዋል። በክልሉ በለውጡ ዓመታት የታዩ ተግባራት የሀገሪቷን ማንሰራራትና እመርታዎችን ያንፀባረቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ በበኩላቸው፥ በአፋር ክልል ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም የብልፅግናን መንገድ የሚያግዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። የህዝብ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረጉ ስራዎች በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ እየተሰሩ መሆናቸውን ተመልክተናል ብለዋል። "ጠንካራ አደረጃጀት ለጠንካራ ፓርቲ" በሚል መሪ ሀሳብ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ መድረክ ትናንት በሰመራ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል።
የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ለማረጋገጥ የባህር በር ወሳኝ ነው-የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች
Jan 11, 2026 47
አዲስ አበባ፣ጥር 3/2018(ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ለማረጋገጥ የባህር በር ማግኘት ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት ገለጹ። የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት የመላው ኢትዮጵያውያንን ልብ ያደማ የማይረሳ ጠባሳ መሆኑን አመራር አባላቱ ተናግረዋል፡፡ የባህር በር ባለቤትነት የረጅም ዓመታት ስትራቴጂካዊ ዕቅድን፣የትውልድንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ከፍታ ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑንም ጠቁመዋል። ጉዳዩን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማስገንዘብ የተጀመሩ የዲፕሎማሲ ሥራዎች ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት ጠቅሰዋል፡፡ የአገው ለፍትህና ለዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ አዲሱ መኮንን (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ በፖለቲካ ሴራ የባህር በር ያጣችበት ሂደት የሚያስቆጭ መሆኑን ገልጸዋል። የባህር በር ለአገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑን አንስተው፤ኢትዮጵያ የባህር በር ማጣቷ በኢኮኖሚ ዕድገቷ ላይ ከፍተኛ ተግዳሮት መፍጠሩን ተናግረዋል። የባህር በር ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለስኬቱ በጋራ እየተረባረበ መሆኑን አመልክተዋል። የራያ ራዩማ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ከበደ በበኩላቸው እንደገለጹት፤የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ለማረጋገጥ የባህር በር ማግኘት ዋነኛ መሰረት ነው ብለዋል፡፡ የባህር በር ጉዳይን ዓለም አቀፍ አጀንዳ በማድረግ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የሚደነቁና የሚደገፉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያ ህዝብ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማስተናገድ የባህር በር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አሰፉ ተረፈ በበኩላቸው፤ የባህር በር ጉዳይ የሁላችንም ጥያቄ በመሆኑ በጋራ እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል። በዚህ ረገድ መንግስት የጀመረው ጥረት ግቡን እንዲመታ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሚና ወሳኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ሊቀ መንበር ዘሪሁን ገብረእግዚአብሄር፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት የኢትዮጵያውያንን ልብ በእጅጉ ያደማ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የራሷን የባህር በር ያጣችበት ሂደት ኢ-ፍትሃዊ መሆኑን አንስተው፥ አሁን ላይ ጉዳዩ ብሔራዊ አጀንዳ ሆኖ ሁሉም የበኩሉን ማድረጉ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የትውልዱ አጀንዳ ነው
Jan 11, 2026 70
ሀዋሳ፤ጥር 3/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የትውልዱ አጀንዳ ሆኖ የሚቀጥልና የሀገር የህልውና ጉዳይ መሆኑን የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ፡፡ ለብዙ ዘመናት የባህር በር ባለቤት የነበረችው ኢትዮጵያ ምክንያቱ በግልጽ በማይታወቅ መልኩ ለዓመታት የባህር መግቢያና መውጫ የተቆለፈባት ሀገር ሆናለች። በአሁኑ ወቅት ከ120 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ህዝብ ላላት ሀገር የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከገቢና ወጪ ንግድ ባለፈ የሀገርን ህልውና የሚወስን የትውልድ ጥያቄም ጭምር ሆኖ በስፋት እየተነሳ ይገኛል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የትውልዱ አጀንዳ ሆኖ የሚቀጥል የሀገር ህልውና ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ደምሴ ሱካሬ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት ሁኔታ ለህዝብ ግልጽ ያልሆነና ቁጭት ፈጥሮ የቆየ ጉዳይ መሆኑን አስታውሰዋል። የነበራትን የባህር በር አጥታ በዝምታ ዓመታት አልፈው በአሁኑ ወቅት ትውልዱ ጥያቄውን በይፋ እያነሳና ተገቢ ምላሽ የሚጠብቅ ሀገራዊ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከምጣኔ ሀብት፣ከፖለቲካ፣ ከዲፕሎማሲና ቀጣናዊ የልማት ትስስር ባለፈ ብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ በመሆኑ ምላሽ ሊሰጠው ግድ ይላል ብለዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና በህልውናዋ ጉዳይ በተቃራኒ ሊቆም የሚችል ዜጋ መኖር እንደሌለበት አንስተው፥ ፓርቲያቸው በዚህ ረገድ የጸና አቋም ያለው መሆኑን አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ በለጠ ሲጌቦ፤ የባህር በር ጉዳይ በአደባባይ ከመነሳቱ ባለፈ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጭምር እንዲገነዘበው መደረጉ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል። ጥያቄው ተገቢ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የትውልዱ ጥያቄ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ተስፋዬ ኤርሚያስ፤ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የሀገር ህልውና ጉዳይ በመሆኑ ምላሽ እንዲያገኝ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የባህር በር ጥያቄ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን እያደገ የመጣውን ህዝቧን ለመመገብ፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ለመሆንና ብሔራዊ ደህንነቷን ለማስጠበቅ ጭምር መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ ምላሽ ሊያገኝ ግድ ይላል ብለዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተቆልፎባት መኖር የማትችል መሆኑን ዓለም እንዲገነዘበው መደረጉን አንስተው፥ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ጥረቱ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
በክልሉ የተለያዩ ከተሞች 100 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ ነው
Jan 11, 2026 82
ባህር ዳር፤ ጥር 3/2018(ኢዜአ):-በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች 100 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው አማካሪ አቶ ሽቤ ክንዴ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የኮሪደር ልማት ሥራው የከተሞችን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለኑሮ ምቹና ተወዳዳሪነታቸው ከፍ እንዲል እያደረገ ነው። ባለፉት ጊዜያት የተገኙ ተሞክሮዎችን በማስፋት በዚህ ዓመት በስምንት ዋና ዋና ከተሞችና በ20 መካከለኛና አነስተኛ ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። እስካሁን በተደረገ ጥረትም ከ24 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር በላይ የአስፋልት መንገድን ጨምሮ የእግረኛ፣ የብስክሌትና ሌሎችን መሰረተልማቶችን ያካተተ የኮሪደር ልማት ለማከናወን ተችሏል። በተጨማሪም በከተሞች ልማቱ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የአረንጓዴ ቦታዎች፣ የህፃናት መጫዎቻ፣ አደባባዮችና ሌሎች የመዝናኛ ስፍራዎችን አካቶ እየተከናወነ መሆኑን ነው ያስታወቁት። ለልማት ስራው ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1ነጥብ 8 ቢሊዮን የሚሆነው ከህብረተሰቡ በድጋፍ የተገኘ መሆኑን አንስተዋል። በልማት ሥራው አንድ ሚሊዮን ለሚጠጉ ወገኖች የሥራ እድል በመፍጠር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም ጠቁመዋል። በባህር ዳር ከተማ ሦስተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ መጀመሩን እና በሌሎች ዋና ዋና ከተሞችም አንደኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ ተጠናቆ ሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። የኮሪደር ልማት ሥራው ቀደም ሲል በልማት ወደኋላ ቀርተው የነበሩ ከተሞችን ደረጃቸውን በጠበቀ አግባብ እንዲገነቡ ለማድረግ ማስቻሉንም አስገንዝበዋል። ለአረንጓዴ ቦታና ለመዝናኛ ስፍራ ትኩረት ሰጥቶ እየተከናወነ በመሆኑ የከተሞች ገጽታ እየተቀየረ መምጣቱንም ተናግረዋል። ከተሞች በፕላን እንዲመሩ፣ ለኑሮ የተመቹ እንዲሆኑ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ የቱሪዝም ሳቢነታቸውን በማሳደግ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስችሏል ብለዋል። የኮሪደር ልማት ሥራው በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተመራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ልማቱ የህብረተሰቡን የሥራ ባህል በማዳበር ኑሮውን በማሻሻል ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም አንስተዋል። በቀሪ ወራትም ዕቅዱን በተሟላ መንገድ ለማከናወን የአመራሩም ሆነ የባለሙያ እገዛ ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል። ልማቱን ወደ ሌሎች ከተሞች የማስፋት ሥራ እንደሚከናወን አንስተው፤ ለዚህም የዲዛይን፣ መሬትን ከሦስተኛ ወገን ነፃ የማድረግና ሃብት የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። በክልሉ ባለፈው ዓመት በሰባት ከተሞች 35 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ በተሻለ ጥራትና ፍጥነት ማከናወን እንደተቻለም አቶ ሽቤ ጨምረው አስታውሰዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተከናወኑ ተግባራት ሀገር ወደተሻለ ከፍታ እንድታመራ መሰረት ጥለዋል
Jan 11, 2026 73
ወልቂጤ፤ ጥር 3/2018 (ኢዜአ)፡-በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተከናወኑ ተግባራት ሀገሪቱ ወደተሻለ ከፍታ እንድታመራ መሰረት የጣሉ መሆናቸውን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ። ስትራቴጂው በቅርቡ ይፋ የተደረገውን ዲጂታል 2030 ትግበራን ለማሳካት ትልቅ ግብዓት እንደሚሆንም ምሁራኑ ጠቁመዋል። መንግስት የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ በየዘርፉ የጀመራቸውን ሥራዎች ይበልጥ ለማዘመንና ለማሳለጥ በቅርቡ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ትግበራን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ምሁራኑ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተተገበሩ ቴክኖሎጂዎች ሀገሪቱ ወደተሻለ ከፍታ እንድታመራ መሰረት የጣሉ ናቸው። ዲጂታል ቴክኖሎጂው በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርትና በፋይናንስ ዘርፎች ያመጣው ተጨባጭ ለውጥና ያስገኘው ጥቅም እያደገ መሆኑን የተናገሩት በዩኒቨርሲቲው የሶፍት ዌር ኢንጂነሪንግ መምህር በላይ አለምነህ ናቸው። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬቶች በዘርፉ ልምድና ተሞክሮ የተቀሰመበት መሆኑን ገልጸው፣ በስትራቴጂው በተዘረጉ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች በተለያዩ ተቋማት ከወረቀት ነጻ የሆነ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲውም የትምህርት መርሃ ግብሮችና በሥራ ክፍሎች የመረጃ ልውውጥ ሥራው ከወረቀት ነጻ በሆነ መንገድ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዞ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በመደረጉ ተማሪዎች ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው ትምህርታቸውን በኦንላይን መከታተል መቻላቸውን ጠቁመዋል። ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች ጋር የሚያደርገው ግንኙነትና የተማሪዎች ውጤትም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደራሽ መደረጋቸውንም ነው ያመለከቱት። የመማር ማስተማር ሂደቱን በማዘመንና የፈተና አሰጣጥ ሥርአቱን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የፈተናን ደህንነት ለማስጠበቅ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም አስረድተዋል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራት በቅርቡ ይፋ ለተደረገው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ትግበራ መሰረትና ግብአት መሆናቸውን ተናግረዋል። የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኔትዎርኪንግ ሳይበር ደህንነት መምህር ወንድወሰን ዝና በበኩላቸው ለተማሪዎች በሳይበር መረጃ ደህንነት አጠባበቅ ላይ በተግባር የተደገፈ ትምህርት ለመስጠትና በቂ ዕውቀት ለማስጨበጥ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 አበርክቶ ላቅ ያለ መሆኑን ተናግረዋል። በየደረጃው ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ይበልጥ መረጋገጥ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸው፣ "ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠል በዲጂታል ቴክኖሎጂ ያሉ አማራጮችን በአግባቡ ልንጠቀምባቸው ይገባል" ብለዋል። ስትራቴጂው ዜጎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮች ታግዘው ባሉበት ቦታ ትምህርታቸውን መከታተል የሚችሉበት ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም ጠቁመዋል። እንደ መምህሩ ገለጻ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መሆን እንደሀገር ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ከመከላከል ባለፈ የተለያዩ ማጭበርበሮችን ለማስቀረትም እያገዘ ነው። ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ አካታችና ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ በሁሉም ዘርፍ ተግባራትና የሚሰጡ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የታገዙና ቀልጣፋ እንዲሆኑ የተጀመሩ ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸውም መምህሩ ገልጸዋል።
በከተማው ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች የዲጂታል እውቀት የማሳደግ ስራ ይከናወናል
Jan 11, 2026 80
ጎንደር ፤ጥር 3/2018(ኢዜአ)፡- በስራ ፈጠራ የሚሰማሩ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች የዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት ለማጎልበት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጎንደር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና "ኦርቢት ኢኖቬሽን ሀብ" የተባለ ድርጅት በጋራ በመሆን በስራ ፈጠራ ክህሎት ላሰለጠኗቸው 45 ወጣቶች ዛሬ የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል። የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኋላ ለሰልጣኞቹ እንደገለጹት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት ልዩ የስራ ፈጠራ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ተሳትፎ ማሳደግ ይገባል። የከተማ አስተዳደሩ ልዩ የስራ ፈጠራ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ተቋማዊ የአሰራር ስርአቶችን በመዘርጋት ውጤታማና እንዲሆኑ ሁለተናዊ ድጋፍ በማድረግ ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡ የዲጂታል ቴክኖሎጂ በሀገራችን ለተዘመገቡ ኢኮኖሚያዊ እድገቶች አዎንታዊ ሚና እንደነበረው ጠቁመው የሰራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በከተማው በማደራጀት ተሰጥዋቸውን ለሀገር ልማትና እድገት የሚያውሉበት ምቹ አውድ እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡ የጎንደር ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ተስፋሁን መኮንን እንደገለጹት የስራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች የዲጂታል ክህሎትና እውቀታቸው እንዲዳብር ኮሌጁ ተገቢውን የሙያ ስልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል፡፡ የስራ ፈጠራ ሃሳብ ተወዳዳሪነትን፣ ብቃትንና ዘመኑን የዋጀ መሆን እንዳለበት ጠቁመው ለስልጠናው የተመረጡ ወጣቶችም መስፈርቱን ያሟሉ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡ "የኦርቢት ኢኖቬሽን ሀብ" የኮሚኒቲ ዴቨሎፕመንት ፕሮግራም ማኔጀር ቅኔል ሃይሉ በበኩላቸው በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የስራ ፈጣሪ ወጣቶችን ራእይ ለማሳካት የዲጂታል ክህሎት ስልጠና የሚያገኙበት አሰራርን በመዘርጋት አየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ድርጅቱ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመተባበር በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎቸ በ6 ዙር የስራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በማወዳደር የቴክኖሎጂ ስልጠና እንዲያገኙ እየደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በጎንደር ከተማም 218 የስራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በማወዳደር ከዚህ ውስጥ መመዘኛውን ያለፉ 45 ወጣቶች ለሶስት ተከታታይ ወራት የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸቱን አስረድተዋል፡፡ ከሰልጣኞቹ መካከል የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ዶክተር አዲሱ ወርቄ ስልጠናው በዲጂታል አለም ውስጥ የስራ ፈጠራ ሃሳቦቻችንን አንዴት ማሳካት እንደምንችል እውቀትና ክህሎት መጨበጥ እንድንችል አግዞናል ብለዋል፡፡ የሳይካትሪስት ባለሙያ የሆነችው ቤተልሄም ጌታቸው በበኩሏ የስራ ፈጠራ ሃሳቦቼን እንዴት ወደ መሬት ማውረድና ገበያ ላይ ማውጣት አንደምችል ስልጠናው የተሟላ እውቀትና ግንዛቤ ፈጥሮልኛል ብላለች። በስነ ስርአቱ ላይ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችን ጨምሮ ስልጠናውን የተከታተሉ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ተሳታፊ ናቸው፡፡
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዲጂታላይዝ የሆነ አሰራሩን ማጠናከር ይገባዋል
Jan 10, 2026 127
አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2018(ኢዜአ)፦የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን የሪፎርም ስራዎችን በመተግበር አሰራሩን ዲጂታላይዝ በማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስገነዘበ። የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢዎች እና ከምክር ቤቱ ሴቶች ኮከስ አመራር አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል። ውይይቱም የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን እያከናወናቸው በሚገኙ የሪፎርም እና የዲጂታል ስራዎች፣ የግዥና ንብረት የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም ወደፊት በትኩረት ሊሰራባቸው በታቀዱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ ፤ ባለስልጣኑ ሪፎርም ስራዎችን በመተግበር አሰራሩን ዲጂታላይዝ በማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ማጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል። ባለስልጣኑ በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በመንግስት ግዥና ንብረት ዲጂታላይዜሽን፣ ከዘለቄታዊነት የግዥና ንብረት አስተዳደር ሥርዓት በማጎልበት ከመንግስት ግዥና ንብረት አገልግሎት እና መረጃ ጥራትና ሽፋን ለማሳደግ ያከናወነው ስራ ለሌሎችም ተቋማት በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸዋል። ተቋሙ እየተገበረ በሚገኘው ዘመናዊ አሰራር ከሀገር አልፎ ለሌሎች ሀገራትም ልምድ እያካፈለ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። በመንግስት ግዥ ውጤታማ እንዲሆንና ግልጸኝነት ያለው አገልግሎት እንዲሳለጥ በማድረግ በኩል እያከናወነ ያለውን ተግባር ሊያጠናክር እንደሚገባ ገልጸዋል። የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሰረት መስቀሌ በበኩላቸው፤ ተቋሙ በዘመናዊ አሰራር በመታገዝ የግዥ ስርዓቱን ለማዘመንና የቁጥጥር ስርዓቱን ከማጠናከር አኳያ በርካታ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ከግዥ ጋር ተያይዞ ያለውን ግልጸኝነት ከማረጋገጥ እና ህገ-ወጥነት ለመከላከል የሚያስችሉ የተለያዩ ዘመናዊ ስርዓቶችን መዘርጋቱን አብራርተዋል። ባለስልጣኑ የአሰራር ስርዓቱን ጥራትና ቅልጥፍና ለማሳደግ አዋጁን፣ መመሪያዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ በማድረጉ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል። ለተገልጋዮች እና ለባለድርሻ አካላት ተከታታይ ሥልጠና መስጠቱንም ገልጸዋል። በተለይ የመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥን (e-GP) ከፌዴራል ተቋማት አልፎ ወደ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የማውረድ ስራዎች ማከናወኑን ጠቁመዋል። በውይይት የተሳተፉና አስተያየታቸውን የሰጡት የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች በበኩላቸው፤ ተቋሙ አሰራሩን ዘመናዊ እና ግልጸኝነት በማስፈን እያከናወነ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል። በምክር ቤቱ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰለሞን ላሌ እንደገለጹት፤ ተቋሙ አሰራሩን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያከናውናቸው ተግባራት የሚበረታቱ ናቸው። የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የመንግስት ግዥ ስርዓት ግልጽና ፍትሃዊ እንዲሆን እየተደረገ ያለው የመቆጣጠር ስራ የሚበረታታ መሆኑን ነው የገለጹት። ተቋሙ ከራሱ አልፎ ሌሎች ተቋማትን በዘመናዊ አሰራር ለማዘመን እያደረገ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል። የመንግስት ልማት ድርጅት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ መለሰ መና በበኩላቸው፤ ባለስልጣኑ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ያደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል። የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እጸገነት መንግስቱ በበኩላቸው፤ ባለስልጣኑ በምክር ቤቱ የወጡ አዋጆችን በአግባቡ በመተግበር ለሌሎችም ተቋማት ምሳሌ መሆኑን ገልጸዋል። ባለስልጣኑ የጀመረውን ተግባር በማጠናከር ለወደፊት የላቁ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባው አሳስበዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለጉምሩክ አገልግሎት መቀላጠፍ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል
Jan 8, 2026 230
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018(ኢዜአ)፦ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ቀልጣፋ የጉምሩክ አገልግሎትን ለማጠናከር ትልቅ ዕድል ይዞ መምጣቱን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል ዕድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና በተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ዋነኛ ዓላማዎቹ ናቸው። የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሙሉ ወርቅ ደረሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ኮሚሽኑ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ትግበራ ወቅት የንግድ እንቅስቃሴን የሚያሳልጡ፣ ኮንትሮባንድን ለመቆጣጠር የሚያስችሉና በአጠቃላይ የኮሚሽኑን ስራዎች የሚያሻሽሉ ቴክኖሎጂዎች ወደ ሥራ አስገብቷል። ቴክኖሎጂዎቹ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን ክትትል ለማጠናከር፣ የሰው ንክኪና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንዲሁም ደንበኞች ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል። በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ደግሞ በጉምሩክ ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማዘመን እና ለማቀላጠፍ ትልቅ እድል ይዞ መምጣቱን ጠቅሰዋል። ስትራቴጂውን ስኬታማ ለማድረግ የተቋማት ቅንጅት እንደ ዋነኛ የድጋፍ ማዕቀፍ መሆኑን በማንሳት፥ ኮሚሽኑ የበከሉን ይወጣል ብለዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ አሰራር ተግባራዊ መደረጉን ገልጸው፤ በሂደት ላይም ያሉ ቴክኖሎጂዎች በቀጣይ ወደ ስራ ይገባሉ ብለዋል። ምክትል ኮሚሽነሯ እንደገለጹት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የጉምሩክ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማድረግ ሰራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
ስፖርት
የስፖርት ቱሪዝም መጠናከር ለኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መነቃቃት ፋይዳው የጎላ ነው
Jan 11, 2026 38
ደብረብርሃን ፤ጥር 3/2018 (ኢዜአ) ፡- ስፖርት ጤናማና አምራች ዜጋን በመፍጠር የአካባቢውን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ምርታማነት ለማሳደግ የጎላ ፋይዳ አለው ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በደሉ ውብሸት ገለጹ። የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 2018 የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች ዛሬ በደብረብርሃን ከተማ ተካሂደዋል። ውድድሮቹም የ6 ኪሎ ሜትር የሴቶችና ወንዶች ሩጫ እና የ22 ኪሎ ሜትር የዱላ ቅብብልን ያካተተ ነው። የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በእለቱ እንደገለጹት ስፖርት ጤናማና አምራች ዜጋን በመፍጠር ለአካባቢው ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ምርታማነት እድገት የጎላ ፋይዳ አለው። በተጨማሪም ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ስፖርተኞችንና ተመልካቾችን በማገናኘት ለማህበራዊ ትስስር መጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። በደብረ ብርሃን የተካሄደው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያም የከተማዋን እድገት፣ የመስህብ ስፍራዎችና ጸጋዎችን ለማስተዋወቅ መልካም እድል የሚፈጥር በመሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ቡድን መሪ አቶ አክሊል ጌታቸው እንዳሉት ከተማዋ ያላት የአየር ንብረት ለስፖርታዊ ውድድሮች አመቺ ነው። ዛሬ የተካሄደው የስፖርት ውድድርም ወንድማማችነትን ለማጠናከርና ያሉ የተፈጥሮ ፀጋዎችን ለማስተዋወቅ የሚያግዝ በመሆኑ አዘጋጆቹን አመስግነዋል። የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ሀላፊ ወይዘሮ ሃና ገብረስላሴ በበኩላቸው ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ ህፃናትን፣ ወጣቶችንና ታዋቂ አትሌቶችን ያሳተፈ ውድድር መካሄዱን ገልጸዋልⵆ ውድድሩም የ6 ኪሎ ሜትር የሴቶችና ወንዶች ሩጫ እና የ22 ኪሎ ሜትር የዱላ ቅብብልን ያካተተ እንደነበር አንስተዋል። በ6 ኪሎ ሜትር የወንዶች ሩጫ ውድድር 1ኛ የወጣው ስጦታው ሰማኸኝ እንዳለው እንደዚህ ያለ ውድድር ያልታወቁ አትሌቶች የሚታዩበት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የኤፍኤ ካፕ ባለ ብዙ ክብሩ አርሰናል ከፖርትስማውዝ ይጫወታል
Jan 11, 2026 60
አዲስ አበባ፤ ጥር 3/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል። ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በፍራተን ፓርክ ስታዲየም ፖርትስማውዝ ከአርሰናል ይጫወታሉ። በእንግሊዝ ሁለተኛ ዲቪዚዮን (ሻምፒዮንሺፕ) የሚጫወተው ፖርትስማውዝ የሁለት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ነው። አርሰናል 14 ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት የውድድሩ ስኬታማ ክለብ ነው። ሁለቱ ክለቦች በኤፍኤ ካፕ ሲገናኙ የአሁኑ ለአምስተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው አራት ጨዋታዎች አርሰናል ሶስት ጊዜ ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ አቻ ተለያይተዋል። አርሰናል ጨዋታውን የማሸነፍ ሰፊ ግምት አግኝቷል። በሌላኛው መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከብራይተን ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ በኦልትራፎርድ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ዩናይትድ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን 13 ጊዜ አንስቷል። የብራይተን ትልቁ ውጤት እ.አ.አ በ1982/83 ለፍጻሜ ደርሶ በዛሬ ተጋጣሚው ተሸንፎ ዋንጫ ያጣበት አጋጣሚ ነው። ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀደም ሶስት ጊዜ በውድድሩ ተገናኝተው ማንችስተር ዩናይትድ ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ በቀሪው አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል። ብራይተን በዩናይትድ ላይ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። ዌስትሃም ዩናይትድ ከኪውፒአር፣ ደርቢ ካውንቲ ከሊድስ ዩናይትድ እና ስዋንሲ ሲቲ ከዌስትብሮም ዛሬ ከሚደረጉ የኤፍኤ ካፕ ጨዋታዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ኤፍኤ ካፕ እ.አ.አ በ1871 መጀመሩን መረጃዎች ያመለክታሉ። 155 ዓመታትን ያስቆጠረው ኤፍኤ ካፕ የዓለም አንጋፋው የክለቦች ውድድር ነው።
ተጠባቂው የኤል ክሊሳኮ ደርቢ በስፔን አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ፍጻሜ
Jan 11, 2026 55
አዲስ አበባ፤ጥር 3 / 2018 (ኢዜአ)፦በስፔን የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ዛሬ የሚያደርጉት የፍጻሜ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከምሽቱ 4 ሰዓት በሳዑዲ አረቢያ ኪንግ አብዱላህ ስፖርትስ ሲቲ ስታዲየም ይካሄዳል። ባርሴሎና በግማሽ ፍጻሜው አትሌቲኮ ቢልባኦን 5 ለ 0 እንዲሁም ሪያል ማድሪድ አትሌቲኮ ማድሪድን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። የባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ታሪካዊ ተቀናቃኝነት ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ነው። ሁለቱ ክለቦች እ.አ.አ በ1902 ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ባርሴሎና 3 ለ 1 አሸንፏል። ቡድኖቹ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ጨምሮ እስከ አሁን 303 ጊዜ እርስ በእርስ ተገናኝተዋል። ባርሴሎና 128 ጊዜ ሲያሸንፍ ሪያል ማድሪድ 111 ጊዜ ድል ቀንቶታል። 64 ጊዜ አቻ ወጥተዋል። ሁለቱ ክለቦች በስፔን የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ለፍጻሜ ሲገናኙ የዛሬው ለ18ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 16 ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ ዘጠኝ ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል።ባርሴሎና ስድስት ጊዜ ባለድል ሆኗል። ሁለት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥተዋል (ውድድሩ የደርሶ መልስ ጨዋታ ፎርማት በነበረው ወቅት)። አምና ሁለቱ ክለቦች በፍጻሜው ተገናኝተው ባርሴሎና 3 ለ 2 በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት መሆኑ የሚታወስ ነው። ቡድኖች የስፔን አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን ለበርካታ ጊዜ ያነሱ ክለቦች ናቸው። ባርሴሎና 15 ጊዜ በማንሳት ቀዳሚነቱን ሲይዝ ሪያል ማድሪድ 13 ጊዜ አሸንፏል። በጉዳይ ላይ የሚገኘው የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ኪሊያን እምባፔ በቡድኑ ስብስብ ውስ መካከቱ ለለሎስ ብላኮንሶቹ መልካም ዜና ሆኗል። የ42 ዓመቱ ሆዜ ሉዊስ ሞንቴሮ የሁለቱን ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል። የስፔን የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ በስፔን ላሊጋ እና በስፔን ጥሎ ማለፍ ዋንጫ በተመሳሳይ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን የያዙ ክለቦች የሚሳተፉበት ውድድር ነው።
ግብጽ የወቅቱን የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት ኮትዲቯር በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
Jan 11, 2026 95
አዲስ አበባ፤ ጥር 2 /2018 (ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር ግብጽ ኮትዲቯርን 3 ለ 2 አሸንፋለች። ማምሻውን በአጋዲር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኦማር ማርሙሽ፣ ራሚ ራቢያ እና መሐመድ ሳላህ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ጉዌላ ዱዌ እና የግብጹ አህመድ አቡ ኤል ፎቱህ በራሱ ላይ ለኮትዲቯር ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በጨዋታው ግብጽ ግልጽ የግብ እድሎችን በመፍጠር፣ ኮትዲቯር በኳስ ቁጥጥር የተሻሉ ነበሩ። ኮትዲቯር በጨዋታው ማብቂያ ላይ ተጭና ብትጫወትም ግብ ማስቆጠር አልቻለችም። የግብጹ መሐመድ ሳላህ በውድድሩ ላይ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ አራት ከፍ አድርጓል። ድሉን ተከትሎ ግብጽ ግማሽ ፍጻሜ የገባች የመጨረሻዋ ሀገር ሆናለች። በግማሽ ፍጻሜው ከሴኔጋል ጋር የምታደርገው ጨዋታ ከወዲሁ ትኩረትን ስቧል። የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ኮትዲቯር የአፍሪካ ዋንጫ ክብሯን የመጠበቅ ጉዞዋ ሩብ ፍጻሜው ላይ ተገቷል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር ናይጄሪያ ከአዘጋጇ ሞሮኮ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ረቡዕ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።
አካባቢ ጥበቃ
በድሬደዋ አስተዳደር የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራ ተጀመረ
Jan 11, 2026 100
ድሬደዋ፣ጥር 3/2018(ኢዜአ) ፡-በድሬደዋ አስተዳደር 38ቱ የገጠር ቀበሌዎች የበጋ ወራት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ዛሬ መካሄድ ጀመረ። በአስተዳደሩ አራቱ የገጠር ክላስተሮች ዛሬ በተጀመረውና ለአንድ ወር በሚዘልቀው የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ሥራ 5ሺህ 550 ሄክታር የሚሸፍን የተፋሰስ ልማት እንደሚከናወን ታውቋል። በአሰሊሶ ገጠር ክላስተር ገንደ ሪጌ ቀበሌ ተገኝተው የተፋሰስ ልማቱን ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የአስተዳደሩ ምክርቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ከሪማ አሊ ናቸው። የድሬደዋ አስተዳደር ምክርቤት አፈጉባኤ አቶ አብዲ ሙክታር፣ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬደዋ አስተዳደር ምክርቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተቀሩት ክላስተሮች ተገኝተው የተፋሰስ ልማቱን አስጀምረዋል። "የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት፤ ለግብርና ሽግግር ስኬት" በሚል መሪ ሃሳብ በተጀመረው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ ላይ የተለያዩ የአፈርና የውሃ ሃብትን በዘላቂነት መጠበቅና ማበልፀግ የሚያስችሉ ተግባራት እንደሚካሄዱም በወቅቱ ተገልጿል። ለአንድ ወር በሚካሄደው የተፋሰስ ልማት ስራው ከ37ሺህ 900 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉም ታውቋል።
በዞኑ በልዩ ትኩረት ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ ነው
Jan 10, 2026 92
መቱ፤ ጥር 2/2018 (ኢዜአ)፡- በኢሉአባቦር ዞን በልዩ ትኩረት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን የዞኑ የግብርና ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አወል መሐመድ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በያዝነው የበጋ ወራት በዋናነት የተቀናጀ የአፈርና ውኃ ጥበቃን ጨምሮ ችግኝ የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ ነው። በዚህም መሠረት 131 ሺህ ሔክታር መሬት የሚሸፍን የተፋሰስ ልማት ሥራ ሕብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል። የተፋሰስ ልማት በተሠራባቸው አካባቢዎች የሚተከሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው በርካታ ችግኞች እየተዘጋጁ መሆናቸውንም ጠቁመዋል። ችግኞቹ ለምግብነት፣ ለደን ልማት፣ ለከብቶች መኖና ለውበት የሚውሉ መሆናቸውንም ነው ያብራሩት። የችግኝ ዝግጅቱ በመንግሥት ችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች እና በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ መካሄዱንም አስረድተዋል። በመጪው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች ከአካባቢ ጥበቃ ፋይዳ ባለፈ በችግኝ ማፍላት ለሚሳተፉ ወገኖች የሥራ እድል እንደፈጠሩመ አክለዋል። በችግኝ ማፍላት ሥራው የሥራ እድል ከተፈጠረላችው መካከል ሽብሩ አምቢሳ እንዳሉት፤ በችግኝ ጣቢያዎች ተቀጥረው ከሚያገኙት ገቢ ባሻገር በሥራው ያገኙትን ልምድ በግል ማሳቸው ላይ ለማስፋት ማቀዳቸውን ተናግረዋል። ችግኞችን ከማዘጋጀት ሥራ ጎን ለጎን ባለፈው ክረምት የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ሥራም እያከናወኑ መሆናቸውን ነው የተናገሩት። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር መተግበር ከጀመረ ወዲህ ችግኝ በማዘጋጀት ገቢ እያገኙበት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ አበራ ገለታ ናቸው።
በሐረሪ ክልል በተፋሰስ ልማት የተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ምርትና ምርታማነትን አሳድጓል
Jan 10, 2026 78
ሐረር፤ ጥር 2/2018(ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል ባለፉት ዓመታት በተፋሰስ ልማት የተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ምርትና ምርታማነት ማሳደጉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር ገለጹ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ሮዛ ኡመር፤ የዘንድሮውን የክልሉን የተፋሰስ ልማት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በዛሬው እለት አስጀምረዋል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት የተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ተጨባጭ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አንስተው ዘንድሮም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በተለይም የከርሰ ምድር ውሃን በማጎልበትና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል። የክልሉ የተፈጥሮ ሀብት ልማት አጠቃቀም እና ጥበቃ ዳይሬክተር አራርሶ አደም፤ በክልሉ በዘንድሮ በጋ ወራት 9 ተፋሰሶች ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እንደሚከናወን ተናግረዋል። በዚህም 300 ሄክታር በሚሆን መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራው እንደሚከናወን ጠቁመው በተፋሰስ ልማት ስራው ከ11 ሺህ በላይ ሰዎች ይሳተፋሉ ብለዋል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የለሙ ተፋሰሶች የጎርፍ ተጋላጭነትን ከመቀነስ ባለፈ ለወጣቶች የስራ ዕድል እንደፈጠረም ገልጸዋል።
የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራን በብቃት በማከናወን ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት ማድረግ ተችሏል
Jan 10, 2026 96
አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2018 (ኢዜአ)፦ የመዲናዋን ወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ በብቃትና በልቀት በማከናወን ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት ማድረግ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ እየተገነቡ ከሚገኙ ስምንት የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች መካከል የቀበና እና የግንፍሌ ወንዞችን የመስክ ምልከታ በማድረግ የሥራ ሂደቱን ገምግመዋል። ከንቲባዋ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት፤ የከተማዋ የወንዝ ዳርቻዎች ቀደም ሲል በቆሻሻ ክምችት የተሞሉ፣ በከባድ ጠረን ምክንያት ለመጠጋት የማይቻልበት ስፍራዎች ነበሩ። ሆኖም አሁን ላይ ይሄ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ተቀይሮ አካባቢው ውበት ተጎናፅፎ ለከተማችን ትልቅ የቱሪስት መዳረሻ ሆኗል ብለዋል። ነዋሪዎች ንጹህ አየር የሚያገኙበት እና የሚዝናኑበት ምቹ አካባቢ መፈጠሩን አክለው ተናግረዋል። ቀደም ሲል ለሕገ-ወጥ ተግባራት መሸሸጊያ የነበሩ ስፍራዎች አሁን ላይ ወደ ልማት በመቀየራቸው የነዋሪዎች ደህንነት መረጋገጡን ጠቁመዋል። የወንዝ ዳርቻ ልማቱ በኢትዮጵያ አዲስ የልማት አይነት መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባዋ፤ ሥራው በብቃትና በልቀት እየተከናወነ ነው ብለዋል። ፕሮጀክቱ ለበርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠሩን የጠቀሱት ከንቲባዋ፤ የአፈር መሸርሸርን በመከላከል እና አካባቢን በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ነው ያሉት። ደርቀው የነበሩ ምንጮች ዳግም መፍለቅ መጀመራቸውን አንስተው ልማቱ ተጨባጭ ውጤት እየታየበት መሆኑ ከንቲባዋ ጠቅሰዋል። የወንዝ ዳርቻ ልማት ለሀገራችን አዲስ ተሞክሮ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እጅግ አስደናቂና ለውጥ አምጭ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። የወንዝ ዳርቻ ልማቱን ተከትሎ ባለሀብቶች በአካባቢው የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን እንዲያከናውኑ ጥሪ አቅርበዋል። የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የቀበና ግንፍሌ ፒኮክ ፓርክ ወንዝ ዳርቻ ልማት የሚያስተባብሩት አቶ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው፤ አካባቢው ለረጅም ጊዜ በተለያየ መልኩ ሳይጠቅም የባከነና ትኩረት ተነፍጎት የቆየ እንደነበር አስታውሰዋል። ሆኖም አሁን ላይ በተከናወነው የተቀናጀ የጽዳትና የውበት ስራ ስፍራው ዳግም ህይወት ዘርቶ ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት እንደሆነ ገልጸዋል። ይህም በቆሻሻ ተሸፍኖ የነበረውን እምቅ አቅም እንዴት ወደ ትልቅ ተስፋ መቀየር እንደሚቻል በተግባር የታየበት መሆኑን ተናግረዋል። ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለጎብኚዎች ማራኪ የመዝናኛ ስፍራ መሆኑን በማንሳት ለከተማዋ ደግሞ አዲስ የኢኮኖሚና የውበት ምንጭ እንደሆነ ገልፀዋል። ይህ ስራ የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮችን በትጋትና በቅንጅት ወደ ትልቅ ውጤት መቀየር እንደሚቻል ትልቅ ትምህርት የሰጠ መሆኑንም ነው አቶ ሞገስ የገለጹት።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የቻይና አፍሪካ ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል
Jan 8, 2026 122
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር ውይይት አካሄዱ። ውይይቱ እያደገ የመጣው የቻይና አፍሪካ ትብብርን ማጠናከር ላይ ያለመ ነው ተብሏል። ቻይና የአፍሪካ እውነተኛ አጋር መሆኗን የገለፁት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረው ፖሊሲ ጠንካራ ወዳጅነት እንዲፈጠር ማድረጉን ገልፀዋል። የቻይና አፍሪካ ግንኙነት በተለያዩ የትብብር ማዕቀፎች እያደገ መምጣቱንም ተናግረዋል። ከውይይቱ በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ ሁለቱ ወገኖች የዓለም ደቡባዊ ቀጣና (Global South) ሀገራትን መብትና ጥቅም ለማስከበር፣ የሉዓላዊነትን ክብር ለመጠበቅ እና ዓለም አቀፍ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በጋራ ለመሥራት መስማታቸውን አስታውቀዋል። በውይይቱ ወቅት የቻይናን የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ ከአፍሪካ ኅብረት የ2063 አጀንዳ ሁለተኛው የዐሥር ዓመት ትግበራ ጋር በማጣጣም ዘመናዊነትን ለማምጣት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ምክክር መደረጉ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነቶችን ጨምሮ፣ ቻይና ያቀረበቻቸውን ዓለም አቀፍ የደኅንነትና የልማት ተነሳሽነቶች በጋራ ለመደገፍ ከስምምነት መድረሳቸውን ኢቢሲ ዘግቧል። በተጨማሪም የተፈረሙ የትብብር ስምምነቶችን በተግባር በመተርጎም እና የንግድ ልውውጥን በማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት በጋራ መግለጫቸው አረጋግጠዋል።
51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ በቀጣዩ ሳምንት ይጀመራል
Jan 8, 2026 126
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018(ኢዜአ)፦ 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ(PRC) መደበኛ ስብሰባው ከጥር 4 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም የህብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል። ስብሰባው "ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል የአፍሪካ ህብረት ባዘጋጀው የ2026 መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ነው። የዘንድሮው መሪ ሀሳብ ጭብጥ በአፍሪካ የውሃ ደህንነትና ንጽህና አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ነው። በስብሰባው የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የሕብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንደሚሳተፉበት ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ስብሰባው የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትን የአፈጻጸም እንዲሁም ሕብረቱ እ.አ.አ በ2025 ያካሄዳቸውን ስብሰባዎች የተመለከቱ ሪፖርቶችን ያደምጣል። ሰላም እና ደህንነት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣናን ጨምሮ የኢኮኖሚ ትስስር፣ የተቋማዊ ሪፎርሞች እና የበጀት እቅዶችን የተመለከቱ የቴክኒክ ሰነዶችንም ያዘጋጃል። ኮሚቴው በ2026 የአፍሪካ ህብረት መሪ ሀሳብ ላይ ምክረ ሀሳቦችን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። የኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብሰባ የሚያገለግል ነው። የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ የሕብረቱን ቋሚ ተወካዮችና የአባል ሀገራቱን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ያቀፈ ነው።
ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓት፤ የአፍሪካ ህብረት የ2026 መሪ ሀሳብ ዋና የትኩረት አጀንዳ
Dec 26, 2025 624
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 14 እና 15 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል። “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የ2026 የአፍሪካ ህብረት መሪ ቃል ነው። መሪ ሀሳቡን ያረቀቀው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽን ነው። የዘንድሮው መሪ ሀሳብ ጭብጥ በአፍሪካ የውሃ ደህንነትና ንጽህና አጠባበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የዘንድሮው መሪ ቃል ከአጀንዳ 2063 ጋር የተቆራኘ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓት ዘላቂ ልማት፣ አካታች እድገት፣ ጤናማ ማህበረሰብና ጠንካራ ስነ ምህዳር መገንባት፣ የተፈጥሮ ሀብት ዘላቂ አጠቃቀምና የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ከአጀንዳ 2063 ግቦች ጋር የተሳሰረ መሆኑ ተገልጿል። ሁሉም አፍሪካዊ ንጹህ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና በቂ ውሃ ለመጠጥ፣ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪ እና ለሌሎች ፍላጎቶቹ እንዲያገኝ የማድረግ ራዕይን ለማስተዋወቅ እድል እንደሚፈጥርም ታምኖበታል። ህብረቱ የውሃ ደህንነት እንደ አህጉር የተያዙ ስትራቴጂካዊ ግቦችን ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን በማዕቀፎቹ አስቀምጧል። ውሃ እና ንጽህና የኢኮኖሚ እድሎችን በማስፋት፣ የስራ አጥነት ምጣኔን በመቀነስ፣ የስደቶችና ተፈናቃዮችን ጫና ለማቃለል እንዲሁም ለሰላምና ደህንነት መስፈን አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተመላክቷል። የ2026 የአፍሪካ ህብረት መሪ ሀሳብ ህብረቱ ውሃ እና ንጽህና ለጤና፣ ለኢኮኖሚ እድገት፣ የምግብ ዋስትና መረጋገጥና ዘላቂ የአካባቢ ምህዳር ለመፍጠር መሰረት መሆኑን የበለጠ እውቅና እንደተሰጠው አመልክቷል። ሁሉን አቀፍ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይገበር የውሃ ደህንነትን የማረጋገጥ አላማ ካለው የአፍሪካ የውሃ ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ ነው። የዘንድሮው መሪ ቃል የአፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ያስተሳሰረ ድልድይ ሆኗል። በዘላቂ ልማት ግቦች ውስጥ ያለው ግብ ስድስት ከውሃ እና ንጽህና ጋር የተያያዘ ነው። ይህ ግብ እ.አ.አ በ2030 ለሁሌም ዜጋ ደህንነቱ የተረጋገጠ ውሃ አቅርቦትና የንጽህና አጠባበቅን ተደራሽ የማድረግ አላማ አለው። የአየር ንብረት ለውጥ፣ የህዝብ እድገት፣ የከተሜነት በፍጥነት መስፋፋትና ውሃ በአግባቡ አለመጠቀም የውሃ ደህንነት እና ዘላቂ አቅርቦት ላይ ተጽእኖ አሳድሯል። የንጽህና አጠባበቅ የአፍሪካ አንዱ ፈተና ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች መሰረታዊ የሚባል የንጽህና መጠበቂያ መሰረተ ልማቶችን አያገኙም። ይህም እንደ ኮሌራ ላሉ የውሃ ወለድ በሽታዎች መስፋፋት ምክንያት ሆኗል። የተቀናጀ የውሃ አስተዳደር ስርዓት፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብር፣ ለዘላቂ መሰረተ ልማት የሚፈሰወን መዋዕለ ንዋይን ማሳደግ፣ ውሃ በድጋሚ አጣርቶ መጠቀም፣ የውሃ ሀብቶችን መጠበቅ፣ ዘላቂ የውሃ ሀብት አስተዳደር እና ለውሃ ደህንነት ትኩረት የሚሰጡ ፖሊሲዎችና ማዕቀፎችን በውጤታማነት መተግበር ያሉትን እድሎች በዘላቂነት ለመፍታትና ፈተናዎችን ለመቅረፍ ያስችላል። ደህንነቱ የተረጋገጠ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት ላይ ያለፈውን ኢንቨስትመንት ማሳደግ፣ የቆሸሸ ውሃ በአግባቡ ማከም፣ የንጽህና አጠባበቅ ማስፋትና የግንዛቤ ፈጠራ ስራን በስፋት ማከናወን፣ ማህበረሰብ መር የንጽህና አጠባበቅ ኢኒሼቲቮችን ትግበራ ማስፋት፣ ጠንካራ የፖሊሲ ማዕቀፎችና ሀገር በቀል አቅምን መገንባት ደህንነቱ የተረጋገጠ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓትን መፍጠር ያስችላል። “ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የ2026 የአፍሪካ ህብረት መሪ ቃል ለአፍሪካ ዘላቂ ልማት፣ የኢኮኖሚ እድገት እና ጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ ያላቸውን ቁልፍ ሚና የሚያሳይ ነው። የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የንጽህና አጠባበቅን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ማድረግ መሰረታዊ መብቶች እንዲጠበቁ ከማድረግ ባለፈ ለማህበረሰብ ደህንነትና የተሻለ የኑሮ ዘይቤ፣ ለአካባቢ ጥበቃና ለአፍሪካ ብልጽግና መረጋገጥ ስትራቴካዊ አቅም ናቸው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 14 እና 15 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ በሚካሄድበት ወቅት በመሪ ሀሳቡ በጥልቀት በመምከር የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦች ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል። ከመሪዎቹ ጉባኤ አስቀድሞ 48ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የካቲት 11 እና 12 ቀን 2018 ዓ.ም እና 51ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኞች ስብሰባ ከጥር 4 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳሉ። ኢትዮጵያ 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና የአፍሪካ ጣሊያን ስብሰባን ለማዘጋጀት ብሄራዊ የዝግጅት ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በኤርትራ መንግሥት እየደረሰብን ላለው መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብቶችና የዘር ማጥፋት ወንጀል ላቀረብነው ክስ ምላሽ እየተጠባበቀን ነው - የቀይ ባሕር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
Dec 24, 2025 535
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በኤርትራ መንግሥት እየደረሰብን ላለው መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብቶችና የዘር ማጥፋት ወንጀል በተመለከተ ለአፍሪካ የሰብዓዊ እና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን ላቀረብነው ክስ ምላሽ እየተጠባበቅን ነው ሲል የቀይ ባሕር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ገለጸ። የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በኤርትራ መንግሥት አገዛዝ ደረሰብን ያለውን መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ጋምቢያ(ባንጁል) የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ላቀረበው ክስ የኤርትራ መንግስት ምላሽ እንዲሰጥ ክሱን መላኩን አድንቋል። በኤርትራ መንግስት ላይ የቀረቡትን ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ክስ ተቀብሎ በመዝገብ ቁጥር 868/25 መመዝገቡን፣ የክሱ ፍሬ ነገር እና ይዘት ተቀባይነት ያለው መሆኑን እውቅና በመስጠት የኤርትራ መንግስት እንዲመልስ ክሱን መላኩን ኮሚሽኑ ማስታወቁን ገልጿል። የድርጅቱ ሊቀ-መንበር ኢብራሂም ሀሩን በመግለጫቸው እንደተናገሩት፤ የኤርትራው መንግሥት በደናክል አካባቢ በቀይ ባህር አፋር ህዝቦች እየፈፀመ ያለው መጠነ ሰፊ፣ ስልታዊ፣ መንግስታዊ መር እና ቀጣይነት ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መጥቷል። በአሁኑ ወቅት እየደረሱ ነው ካሏቸው የመብት ጥሰቶች መካከልም ከህግ እና ከፍርድ ውጭ ግድያዎች እና ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ማካሄድ፣ ያለ ፍርድ ማሰር እና ማሰቃየት፣ በሺዎች የሚቆጠሩትን መሰወር፣ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ማከናወን መሆናቸውን ለአብነት ጠቅሰው፤ በተለይም ከ300ሺህ በላይ የቀይ ባህር አፋር ህዝብን ማፈናቀል እና ፆታዊ ጥቃትን የአገዛዙ የአፈና መሳሪያ አድርጎ መጠቀሙን ጠቅሰዋል። በተጨማሪም ከሀገሪቱ ፖለቲካዊ አስተዳደር ማግለል፣ የቀይ ባህር አፋር ህዝብን ማንነትና ባህል ማጥፋትና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን መጣስ ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም ድርጅቱ የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ከ1993 ጀምሮ በኤርትራ መንግሥት እየደረሰባቸው ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ክስ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። እኤአ ጁን 04 ቀን 2025 በ122 ገጽ የተደራጀ ክስ ማስገባታቸውን ጠቁመው፤ ኮሚሽኑ የኤርትራ መንግስት በ60 ቀናት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ ክሱን መላኩን እንደገለጸላቸው ጠቁመዋል። ለክሱም ከተጠቀሙት ማስረጃዎች መካከል በድርጅቱ የተከናወነ የሰብዓዊ መብት ምርመራ ግኝት፣ በተባበሩት መንግስታት እና በአፍሪካ የሰብዓዊና ሕዝባዊ መብቶች በኤርትራ ላይ የተደረጉ ምርመራዎች፣ ግኝቶችና ማስረጃዎች፣ የመብት ጥሰት የደረሰባቸው የቀይ ባሕር አፋር ተጎጂ ወገኖች እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የተገኙ የሰብዓዊ መብት ምርመራዎችን መቅረቡን ተናግረዋል። ድርጅቱ የአፋር ህዝብ ከሚደርስበት መከራ ለማዳን፣ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ድምፅ እንዲሆኑት፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት ትኩረት እንዲሰጡንና የኢሳያስ መንግስት ላይ ህጋዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ሰብዓዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንዲሁም ተፅዕኖ እንዲያሳድሩ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ሐተታዎች
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 463
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
አፍሪካውያን ሀገር በቀል አሰልጣኞች ጎልተው የታዩበት የአፍሪካ ዋንጫ !
Dec 28, 2025 435
35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው። በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ 24 ሀገራት 12ቱ በአፍሪካውያን የሚሰለጥኑ ናቸው። የአዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከዛው ከሀገራቸው ናቸው። የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሞሮኮን ለግማሽ ፍጻሜ አድርሰዋል።ሀገሪቷ በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከእ.አ.አ 2022 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እየመሩት የሚገኙት ሬግራጉዊ ሞሮኮን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቭዋር አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋች ኤመርሰን ፋኤ ነው። ፋኤ እ.አ.አ በ2023 በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን በመምራት ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል። በውድድሩ መሐል በውጤት ማጣት የተሰናበቱትን ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ ጂን-ሉዊስ ጋሴት በመተካት በጊዜያዊነት አሰልጣኝ የተሾመው ፋኤ ቡድኑን ለዋንጫ ማብቃቱ አስወድሶታል። በዘንድሮው ውድድር ዋንጫውን ለማንሳት የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ተርታ የተመደበችው ሴኔጋል አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፓፔ ታው ነው። ፓፔ ታው በተጫዋችነት ዘመኑ ለሴኔጋል ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። አሰልጣኙ ሴኔጋል ለ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እንድታልፍ አድርጓል። ከሶስት ዓመት በፊት በአልጄሪያ በተካሄደው የሰባተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) ሴኔጋል ዋንጫውን ስታነሳ የቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ መርቷል። የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ግብጽ የምትሰለጥነው በቀድሞ ኮከቧ ሆሳም ሀሰን ነው። በተጫዋችነት ዘመኑ በአፍሪካ ዋንጫ 11 ግቦችን አስቆጥሯል። በ177 ጨዋታዎች 69 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የብሄራዊ ቡድኑ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ሆሳም ሀሰን የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ በተጫዋችነት በማንሳት ስኬታማ አሰልጣኝ ነው። ሌላኛው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን አሰልጣኝ የ56 ዓመቱ ዴቪድ ፓጉ ነው። ካሜሮናዊው አሰልጣኝ የተሾሙት ከሰሞኑ ነው። ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን በመተካት ቡድኑን እንዲመሩ ኃላፊነት ተጠሎባቸዋል። በካሜሮን እግር ኳስ ባላቸው የታክቲክ መረዳት እና ብቃት የሚሞካሹት ፓጉ ቡድኑን አንድ በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጣሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል። ሌላኛው የውድድሩ ተሳታፊ ሀገር ዛምቢያ ናት።የ48 ዓመቱ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተከላካይ ሞሰስ ሲቾኔ የቡድኑ የወቅቱ ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2022 እስከ 2024 በጊዜያዊነት እና በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት ሲቾኔ በ2025 ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል። ምስራቅ አፍሪካን በውድድሩ ከሚወክሉ ሶስት ሀገራት መካከል አንዷ ሱዳና ናት። ጋናዊው ጀምስ ክዌሲ አፒያ የቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። አፒያ ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የጋቦን አሰልጣኝ ቲዬሪ ሞዩማ የብሄራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነበር። ለ11 ዓመታት ለጋቦን ተጫውተዋል። ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመሩ ይገኛል። የ44 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ሞሬና ራሞሬቦሊ የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2025 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛል። ሞሬና ከዚህ ቀደም የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነበሩ። የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን የአማካይ ተጫዋች ብራማ ትራኦሬ ነው። አሰልጣኙ ከእ.አ.አ ማርች 2024 አንስቶ ቡርኪናፋሶን እየመራ ይገኛል። ትራኦሬ ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የአንድ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ቱኒዚያ አሰልጣኝ የቀድሞ የቡድኑ የተከላከይ መስመር ተጫዋች ሳሚ ትራቤልሲ ናቸው። የ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ለቱኒዚያ ብሄራዊ ቡድን ለ10 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግሏል። ብሄራዊ ቡድኑን ከእ.አ.አ 2025 ቱኒዚያን እየመራ ይገኛል። በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ሞዛምቢክ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ፍራንቺስኮ ኩዌሪዮል ኮንዴ ጁኒየር (ቺኩዊኒዮ ኩንዴ) የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። የ60 ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሞዛምቢክ ለ15 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግለዋል። ለሀገራቸው በ43 ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኩንዴ ከእ.አ.አ 2021 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የናይጄሪያ አሰልጣኝ የሆነው ኤሪክ ቼሌ የኮትዲቭዋር፣ ማሊ እና ፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላቸው አሰልጣኝ ናቸው። ይሁንና ቼሌ የአፍሪካ የዘር ግንድ ቢኖራቸውም በፈረንሳይ መወለዳቸው የውጭ ሀገር ዜጋ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። የአፍሪካውያን አሰልጣኞች በአፍሪካ ዋንጫ የማሰልጠን ምጣኔ ከሌሎቹ ወቅቶች አንጻር የአሁኑ የተሻለ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ሀገር በቀል አሰልጣኞች እየተሰጣቸው ያለውን ትኩረት ያሳያል። 12 ሀገራት በውጭ ሀገር ዜጎች ይሰለጥናሉ። በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አፍሪካውያን የሚያሰለጥኗቸው ወይስ የውጭ ሀገር ዜጋዎች የሚመሯቸው ሀገራት ዋንጫውን ያነሳሉ? የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል።
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን
Dec 22, 2025 654
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ የተጀመረው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በወቅቱ የኤሌክትሮኒክ መሳሪዎችን ተጥቅሞ መረጃን በመተንተን እና መረጃን እንደ ልዩ ገጽታ በመጠቀም እና መለያ ቁጥር (ኮድ) በመስጠት አገልግሎት ላይ ይውል ነበር። ከዛ ጊዜ በኋላ በርካታ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞች እና ማሽኖች ተፈብርከው ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል። እ.አ.አ በ1946 በአሜሪካ የፔንሲሊቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ጥቅል አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያውን የኤሌክትሮኒክ ዲጂታል ኮምፒዩተር በመስራት የዲጂታል ዘመን ጅማሮን አበሰረ። ከእ.አ.አ 1943 እስከ 45 ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰራው ይህ ኮምፒዩተር ባለቤቶች ጆን ማውችሊ እና ጄ ፕሬስፐርት ኤከርት ናቸው። በ150 ኪሎ ዋት ኃይል የሚሰራው ኮምፒዩተር በሴኮንዶች ውስጥ በርካታ ስራዎችን ያከናውን ነበር። ኮምፒውተሩ በወቅቱ በነበሩ ባለሙያዎች ማርሽ ቀያሪ እና መሰረት ጣይ የሚል ስያሜ አግኝቷል። የዘመናዊ የዲጂታል ስርዓቶች ምሰሶ ነው የሚባለው ኢንተርኔት የተጀመረው እ.አ.አ በ1960ዎቹ መጀመሪያ ነበር። “አርፓኔት” የተሰኘ የአሜሪካ የጥናት ፕሮጀክት ኮምፒዩተሮችን ዘመኑ ከደረሰበት የኔትወርክ ስርዓቶች ጋር በማገናኘት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። እንግሊዛዊው የኮምፒዩተር ሳይንቲስት ቲም በርነርስ ሊ እ.አ.አ 1969 “ወርልድ ዋይድ ዌብ” (WWW) በመፍጠር ትስስርን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ አሸጋግሯል። ድረ ገጾችን በመፍጠር እና በህዝብ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሰፋ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ዲጂታል ቴክኖሎጂ ከኮምፒዩተር መሰራት ተነስቶ ወደ ዓለም አቀፍ የትስስር መሰረተ ልማትነት የተቀየረ ሲሆን በየዕለት ተዕለት የሰዎች ኑሮ፣ማህበራዊ መስተጋብር፣ ንግድ እና የመንግስታት አሰራር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ከማምጣት ባለፈ ዘርፎች በቴክኖሎጂ እንዲቃኙ አድርጓል። ዓለም ላይ አሁን ካለው ህዝብ 73 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። የዲጂታል ኢኮኖሚ የዓለምን ጥቅል ዓመታዊ ምርት (ጂዲፒ) የ15 በመቶ ድርሻን እንደሚያግዝ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ። ሞባይል ለኢንተርኔት መስፋፋት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ሀገራት እ.አ.አ 2025 በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ፣ ኔትወርኪንግ እና ለሌሎች ትራንስፎርሜሽ ስራዎች ያወጡት ኢንቨስትመንት ከአራት ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚልቅም ይገመታል። በአፍሪካ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ480 ሚሊዮን በላይ ተሻግሯል። ዲጂታል ስርዓቱን የሚያሳልጡ መሰረተ ልማቶች እና የዳታ ማዕከላት በአፍሪካ መንግስታት እና የልማት አጋሮች ትብብር እየተገነቡ ነው። ዲጂታል ኢኮኖሚ ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለትምህርት እና ክህሎት፣ ለመንግስት የአሰራር ውጤታማት፣ ለፋይናንስ አካታችነት እና ኮሙኒኬሽን ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 በፊት የዲጂታል ምህዳሯ የተገደበ ነው ማለት ይቻላል። ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት፣ ለቴሌኮም አገልግሎት ከፍተኛ ክፍያ ወጪ የሚወጣበት እና በቴሌኮም አገልግሎት የመንግስት ብቻ የበላይነት የሚታይበት ነበር። ከለውጡ በኋላ መንግስት የቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች አማካኝነት ዲጂታል ተጠቃሽ ነው። የዲጂታል ዘርፍ ከብዝሃ የኢኮኖሚ ምንጮች አንዱ ሆኖ ነው።ዲጂታላይዜሽን ለኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አካታች የሆነ የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ካስገባች ሰነባብታለች። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 አንስቶ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በማዘጋጀት ስተገብር ቆይታለች። ስትራቴጂው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን ዲጂታል የማድረግ አላማ ያደረገ ነው። በዚህም 900 ገደማ የሚሆኑ መንግስታዊ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ ሆነዋል።3000 የሚሆኑ የዲጂታል አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አግኝተዋል። የፋይዳ መታወቂያ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል። የሞባይል እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። የአራተኛ እና አምስተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰፋ መጥቷል።የዲጂታል ክህሎትም ተስፋ ሰጪ እድገት ታይቶበታል። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ክፍት እንዲሆን መንግስት ባስቀመጠው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት ሳፋሪኮም ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን “ምፔሳ” የተሰኘ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል። የመንግስት የዲጂታል ፖሊሲዎች እና የህግ ማዕቀፎች ለዘርፉ ምቹ ምህዳር በመፍጠር ትስስር እንዲሰፋ እና አገልግሎቶች እንዲዘምኑ አስችሏል። ኢትዮጵያ ከአምስት በፊት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በማቋቋም በርካታ ስራዎችን አከናውናለች። ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት በክረምት መርሃ ግብር (ሰመር ካፕም) ወጣቶች ሲማሩ እንደቆዩ አውስተው በዘርፉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያሳያል። ሁሉንም ዘርፍ የሚነካው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በግብርና፣ጤና፣ አገልግሎት እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በመግባት ስራን እያቀላጠፈ ይገኛል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የሚሰበሰቡ ዳታዎች ለመንግስት እና ግል ተቋማት አገልግሎት ላይ እየዋሉ እንደሚገኝም ተገልጿል። መንግስት ወጣቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ሀገርን አልፎም ዓለምን የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያቀርቡ የሚያደርገውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ቴሌብር፣ መሶብ እና ዘመንን ጨምሮ ያሉ የዲጂታል አገልግሎቶች የዘርፉን እድገት በማሳለጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የዲጂታል 2030ን ስትራቴጂ ይፋ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ መጠናቀቁን ገልጸዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ ያበሰሩ ሲሆን ተደራሽነትን ማስፋት፣ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን አመልክተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና አስተማማኝ የዲጂታል ምህዳር መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሦስት ቁልፍ ትልሞች እንዳሉት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህም ተደራሽነትን ማስፋት፤ እኩል እድል ማመቻቸትና በተቋማትና ህዝብ መካከል መተማመንን መፍጠር መሆናቸውን አብራርተዋል። ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፥ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው። ለአብነትም የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል ሲሉ አንስተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለው እንደገለጹት፥ አንድ ሺህ ሰላሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ሆነዋል ነው ያሉት። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ከተሞች ይደርሳል ብለዋል። በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሰራል ሲሉም አረጋግጠዋል።ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት፣ አካታችነት እና ማህበራዊ ለውጥ ቁልፍ ምሰሶ ነው። ስትራቴጂው በሚገባ ከተተገበረ፣ በቂ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ከተገነቡ እና ዜጎች በንቃት ከተሳተፉ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘመን ትሩፋቶች ተጠቅማ ትልሞቿን ማሳካት እንደምትችል አያጠራጥርም።
መልካምነት ይከፍላል..!!!
Dec 11, 2025 809
መልካምነት ይከፍላል...!!! በማስረሻ ሀብታሙ (ኢዜአ-ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ) መልካም ስነ ምግባርና ባህሪ ከራስ ባለፈ ቤተሰብን ያኮራል፤ ከዚህ ከፍ ሲልም ለማህበረሰብ ግንባታና ለሀገር የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። ሌብነትና ሙስናን ለመከላከልም እንዲሁ አስተዋጾ አለው። በመልካም ስነምግባር ታንጾ ያደገ ሰው በላቡና በወዙ ጥሮ ግሮ ያፈራውን እንጂ የሌሎች የሆነን ሀብትና ንብረት አይመኝም። ዛሬ የራሱ ያልሆነውን ንብረት በሀሰት ምሎና ተገዝቶ ለመውሰድና ለመክበር የሚጥር ሰው በበዛበት በዚህ ዘመን ላይ ወድቆ ያገኙትን ንብረት ለባለቤቱ ለመመለስ "ገንዘብ የጣለ" እያለ በአደባባይ ባለቤቱን የሚያፈላለግ ሰው ሲገጥም ግርምትን ከማጫር ባለፈ እንዲህ አይነት ሰውም አለ ወይ? ያስብላል። ነገሩ የተከሰተው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ነው። በአካባቢው ባህልና እምነት የሰው ገንዘብም ሆነ ንብረት ያለአግባብ መውሰድ "ጎሜ" ወይም እንደ "ሀጥያት" ተደርጎ ይቆጠራል። በኮሻሌ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በዚህ ባህልና እምነት ውስጥ ያደጉ ቢሆንም በቤተሰባቸው በመልካም ስነ ምግባር ታንጸው ማደጋቸው አሁን ላላቸው ታማኝነትና ቅንነት ትልቁን ድርሻ ይይዛል። አርሶ አደሩ ታማኝነታቸውን በተግባር ጭምር በማሳየታቸው ከመንግስት ጭምር እውቅና ተችሯቸዋል። ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ቀን ገበያ ውለው ሲመለሱ በመንገዳቸው ላይ ተጠቅልሎ የታሰረ ነገር ይመለከታሉ። መሬት ወድቆ ያገኙት ነገር እስሩን ፈትው ሲያዩ በርከት ያለ የገንዘብ ኖት ነው። ለማመን እያቃታቸው ገንዘቡን መቁጠር ጀመሩ። በላስቲክ የተጠቀለለው ብር 30 ሺህ ነበር። የራሳቸው ያልሆነውን ገንዘብ ይዞ ወደ ቤት መግባት የህሊና እዳ መስሎ ስለታያቸው አማራጭ ያሉትን አደረጉ፡፡ የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት ከተገኘ በሚል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" እያሉ በአደባባይ ጽምጻቸውን ከፍ አድርገው መጠየቅ ጀመሩ። የሰማቸው ሁሉ ግራ ስለተጋባ ቀረብ ብሎ ሊጠይቃቸው ይቅርና ጤነኛ ሰውም አድርጎ አላያቸውም። የገንዘቡ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ትክክለኛ ሰውም ባለመገኘቱ ልፋታቸው ድካም ብቻ ሆነ። የያዙትን 30 ሺህ ብር ይዘው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተገደዱ። በአካባቢው የገበያ ቀን በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ነው። እናም የገንዘቡን ባለቤት ለማግኘት እስከ ሳምንት ድረስ መቆየት ግድ ሆኖባቸው። ባለቤቱ ይገኛል ወይስ አይገኝም በሚል ሀሳብ ሳምንቱን አሳለፉ። ቀጣይ የገበያ ቀን ሲደርስም ገንዘቡን እንጨት ላይ አስረው በማንጠልጠል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" አያሉ በገበያ ስፍራ በመዘዋወር ዳግም የጠፋበትን ሰው ማፈላለግ ጀመሩ። ገንዘቡ የእኔ ነው፤ ጠፍቶብኛል እያለ የሚመጣ ሰው ቢበዛም ትክክለኛውን የገንዘብ መጠንና ምልክቱን የሚጠራ ሰው አለመኖሩ ግን ፍለጋቸውን አድካሚ አድርጎታል። የገንዘቡን ባለቤት አግኝተው እስኪያስረክቡ ድረስ ተስፋ አልቆረጡም፤ “ገንዘብ የጠፋበት፣ ገንዘብ የጠፋበት...” እያሉ ገበያውን ከዳር ዳር ዞሩ። የኋላ ኋላ ግን ድካማቸው በከንቱ አልቀረም። በስተመጨረሻ ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን ከእነምልክቱ እና ቦታው የሚናገር አንድ ግለሰብ ተገኘ። ከገንዘቡ ባለቤት ጋር ከተወያዩ በኋላ ገንዘቡ ወድቆ ወዳገኙበት ስፍራ ይዘው በመሄድ የያዙትን ገንዘብ መሬት ላይ ጥለው ራሱ ባለቤቱ ምሎ እንዲያነሳ ያደርጋሉ። በእዚህ ሁኔታ ወደቆ ያገኙትን ገንዘብ በታማኝነት ያስረከቡት አቶ ሴዳ ለዚህ መልካም ተግባራቸው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ እውቅና ተችሯቸዋል። የእሳቸው መልካም ተግባር መረጃ የደረሰው ኮሚሽኑም የአርሶ አደሩን አርአያነት ለሌላው ለማስተማር አፈላልጎ ያገኛቸዋል፡፡ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ 22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ሲያከብር በማጠቃለያው ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ በተገኙበት የእውቅና ምስክር ወረቀትና የ15 ሺህ ብር ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡ የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አብደላ ከቤተሰብ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች በዜጎች ስነ ምግባር ላይ አበክሮ መስራት እንዲህ ያሉ ዜጎችን በብዛት ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት። ታማኝ የሆኑ ሰዎች ሲበራከቱ ደግሞ ሀገርና ህዝብን የሚጎዳውን ሙስና ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል፡ እንደ አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ የሚገነባው ከቤት ጀምሮ በሚሰራ ሥራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ኮሚሽኑ ትውልድን በስነ-ምግባር ለማነጽ የጀመረውን ስራ ለማጠናከር በሚሰራው ሥራ እንደ አርሶ አደሩ ያሉ ታማኞች ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ የተቋቋመው የጸረ ሙስና ግብረ ኃይልም በጸረ ሙስና ትግሉ ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡም ታማኝነትን ባህሉ ከማድረግ ባለፈ የጸረ ሙስና ትግሉን በመደገፍ ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣም ነው ያሳሰቡት። የአርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ መልካም ተግባርና ታማኝነትም ለብዙዎች ምሳሌ ይሆናል። በተለይ ያለፉበትን ለማግኘትና በአቋራጭ ለመክበር የሚሯሯጡ ሰዎች ከእሳቸው መልካም ተግባር ሊማሩ ይገባል። የሰው ሀብት ወስዶ ከመክበር ይልቅ በታማኝነት ከምናቆየው ንጹህ ህሊና ይበልጥ አትራፊ እንሆናለን። ለሰዎች መልካም መስራት ክብርና ዋጋ የሚያሰጥ መሆኑንም የእኚህ አርሶ አደሩ ተሞክሮ ያሳያልና እንደእሳቸው ለሰራነው መልካም ተግባር ዋጋ እንዲከፈለን ታማኝነትን የህይወታችን መርህ ማድረግ አለብን። መልካምነት ቢቆይም እንኳ በራሱ ይከፍላልና።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 429
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 1, 2026 393
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው። በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ
Dec 8, 2025 1053
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3392
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 2998
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 1905
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7723
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6203
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
አማድ ዲያሎ - የአፍሪካ እግር ኳስ ብሩህ ተስፋ
Jan 9, 2026 198
ተጫዋቹ አዲሱ ሳሙኤል ኤቶ የሚል ስያሜ እየተሰጠው ይገኛል። ፍጥነቱን ከዲዲየር ድሮግባ ጋር ያነጻጽሩታል። ለተጋጣሚ ተጫዋቾች የራስ ምታት እና ፈተና የሆነውን ግራ እግሩን ከሌላኛው የግራ እግር ምትሃተኛ ሪያድ ማህሬዝ ጋር የሚያወዳድሩም አልጠፉም። በዚህ አካሄዱ ከቀጠለ ያለ ምንም ጥርጥር ወደፊት በእግር ኳስ ከምንመለከታቸው ኮከቦች አንዱ ሊሆን ይችላል እየተባለለት ይገኛል። ይህ ተጫዋች በማንችስተር ዩናይትድ የ147 ዓመታት ታሪክ ሀትሪክ የሰራ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ተጫዋች ነው። እያወራን የምንገኘው የማንችስተር ዩናይትድ 16 ቁጥር ማልያ ለባሽ አማድ ዲያሎ ነው። የ23 ዓመቱ ኮትዲቯራዊ ተስፈኛ ተጫዋች በቀያዮቹ ሴጣኖች እያሳየ ያለው ብቃት ከብዙዎች ዘንድ ሙገሳ አስችሮታል፣ አድናቆት እንዲጎርፍለት አድርጓል። ወደ ኋላ መለስ እንበልና የአማድ ዲያሎን መነሻ እንመልከት። ካሜሮን ከአዘጋጇ ሞሮኮ ለግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው አማድ የተወለደው እ.አ.አ ጁላይ 11 2002 በኮትዲቭዋር መዲና አቢጃን ነው። ተጫዋቹ በአፍሪካ ምድር ቢወለድም ገና በህጻንነት እድሜው ነበር ወደ ጣልያን የተሰደደው። የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው እ.አ.አ በ2014 በጣልያን ሬጂዮ ኢሚሊያ ግዛት በሚገኘው ቦካ ባርኮ የታዳጊ ቡድን ነው። ቡድኑን በተቀላቀለበት ዓመት የገና በዓል (ክሪስማስን) በማስመልከት በተካሄደ ውድድር ላይ በ12 ዓመቱ ኮከብ ግብ አግቢ ሲሆን ያሳየው አስደማሚ ብቃት የብዙዎችን ቀልብ ሳበ። ይህ የገና በዓል ውድድር አማድን እ.አ.አ በ2015 በቦካ ባርኮ ቡድን እንዲመዘገብ አደረገው። ተጫዋቹ በቡድኑ ብዙም አልቆየም። የበርካታ የጣልያን ሴሪአ ክለቦች አይን አረፈበት። ብዙም ሳይቆይ በዛው በ2015 ወደ ጣልያኑ አትላንታ አመራ። አማድ ከእ.አ.አ 2015 እስከ 2019 ለአትላንታ ታዳጊ ቡድን የተጫወተ ሲሆን እ.አ.አ 2019 እና 20 ለዋናው ቡድን ተጫውቷል። ለዋናው ቡድን አራት ጨዋታዎችን አድርጎ ማስቆጠር የቻለው አንድ ግብ ብቻ ነው። የእንግሊዙ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹ በጣልያኑ ክለብ ባሳየው ብቃት በ18 ዓመት እድሜው እ.አ.አ ጃንዋሪ ወር 2021 በአምስት ዓመት ኮንትራት በ37 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዩሮ አስፈርሞታል። ተጫዋቹ ወደ ማንችተር ሲመጣ ቀጥታ ወደ ዋናው ቡድኑ አልተቀላቀለም። በቡድኑ ከ23 ዓመት በታች ጨዋታውን ማድረግ ጀመረ። አማድ የመጀመሪያ ጨዋታውን ለማንችስተር ያደረገው እ.አ.አ ፌብሩዋሪ 18 2021 ቡድኑ ከሪያል ሶሲዬዳድ ጋር ባደረገው የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ነው። በዛው ዓመት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ላይ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። ዲያሎ ከእ.አ.አ 2022-2023 ባለው ጊዜ ሬንጀርስ እና ሰንደርላንድ በውሰት የተጫወተ ሲሆን በቡድኖቹ ባደረጋቸው 47 ጨዋታዎች 16 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። እ.አ.አ በ2023/24 አማድ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ በመመለስ በድጋሚ መጫወት ጀምሯል። በክለቡም ድንቅ ብቃቱን እያሳየ መምጣት ጀመረ። እ.አ.አ ጥር 17 2025 ማንችስተር ዩናይትድ ከሊጉ ከወረደው ሳውዝሃምፐን ጋር በነበረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር በ12 ደቂቃ ውስጥ ሶስት ግቦችን አስቆጥሮ ሀትሪክ በመስራት ቡድኑ 3 ለ 1 አንዲያሸንፍ ያደረገበት መንገድ አድናቆት አስችሮታል። በዚህም አማድ በማንችስተር ዩናይትድ የ147 ታሪክ የመጀመሪያ ሀትሪክ የሰራ አፍሪካ ተጫዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ጽፏል። አማድ በቀያዮቹ ሴጣኖች ማልያ እስከ አሁን ባደረጋቸው 53 ጨዋታዎች 11 ግቦችን አስቆጥሯል። ተጫዋቹ ከክለቡ በተጨማሪ ለኮትዲቯር ብሄራዊ ቡድን በመጫወት ላይ ይገኛል። እ.አ.አ 2021 ኮትዲቯር ከኒጀር ጋር ባደረገችው ጨዋታ በ86ኛው ደቂቃ ተቀይሮ በመግባት ለብሄራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። ለሀገሩ እስከ አሁን ባደረጋቸው 15 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። የመጀመሪያ ጎሉን ኮትዲቯር በ2021 በወዳጅነት ጨዋታ ቡርኪናፋሶን 2 ለ 1 ስታሸነፍ ነበር ያስቆጠረው። አማድ ዲያሎ ዘንድሮ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ድንቅ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል። አማድ በውድድሩ ላይ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሶስት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን አንድ ለግብ የሚሆን ግብ አመቻችቶ አቀብሏል። ኮትዲቯር ከሞዛምቢክ፣ ካሜሮን እና ቡርኪናፋሶ ጋር ባደረገቻቸው ጨዋታዎች የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተምርጧል። የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቯር ሩብ ፍጻሜ እንድትደርስ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ኮትዲቯር ከግብጽ በሩብ ፍጻሜው ነገ ከግብጽ ጋር ምሽት አራት ሰዓት ላይ በአጋዲር ስታዲየም የምታደርገው ጨዋታ በጉጉጉት ይጠበቃል። ሀገሩ በጠዋታው ላይ ከአማድ ብዙ ትጠብቃለች። ወደ ክለብ እንቅስቃሴው ስንመለስ አማድ በማንችስተር ዩናይትድ ስብስብ ውስጥ ቁልፍ የሚባል ተጫዋች ነው። ፈጣን ኳስን የማንከበላል ክህሎቱ፣ ፍጥነቱ ፣ የቴክኒክ አቅሙ፣ ጨዋታን የማንበብ ብቃቱ እና ሁለቱንም እግሩን የመጠቀም አቅሙ አልፎም ተጫዋቾችን በቄንጥ የሚያልፍበት መንገድ ተጫዋቹን እያስወደሰው ነው። አማድ ዲያሎ ከክንፍ ተጫዋችነቱ ባሻገር የአጥቂ አማካይ ሆኖ መጫወትም ይችላል። እ.አ.አ በ2020 የ18 ዓመት ልደቱን ተከትሎ ተጫዋቹ ስሙን ከአማድ ትራኦሬ ወደ አማድ ዲያሎ አስቀይሯል። አማድ ካለው ድንቅ ብቃት አንጻር ወደፊት በክለብ እና ብሄራዊ ቡድን ደረጃ ድንቅ ጊዜን ካሳለፉ ታዋቂ የአፍሪካ ተጫዋቾች ተርታ የመሰለፉ ጉዳይ አያጠራጥርም።
በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ብዙ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ያቀበሉ ተጫዋቾች
Jan 5, 2026 224
በእግር ኳስ ጨዋታ ከግብ አስቆጣሪዎች ጀርባ ኳስን ፍትፍት አርገው ጨርሰው የሚያቀብሉ ተጫዋቾች አሉ። አንድ ተጫዋች ግብ ሲያገባ ከማግባቱ ባልተናነሰ ማን ኳሱን አቀበለው? የሚለው ጥያቄ በተመልካቾች ይነሳል። በእግር ኳስ እድገት ውስጥ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለጎል ኳስ አመቻችተው የሚያቀብሉ ተጫዋቾች ትልቅ ዋጋ ይሰጣቸዋል። ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን አሰናበተ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ። የ33 ዓመቱ የሴኔጋል አምበል ሳዲዮ ማኔ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ካስቆጠረው አንድ ግብ በተጨማሪ ሶስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዟል። ማኔ ሴኔጋል ለሩብ ፍጻሜ እንድታልፍ ያበረከተው አስተዋጽኦ ትልቅ የሚባል ነው። ስምንት ተጫዋቾች በተመሳሳይ ሁለት ለግብ የሚሆኑ ግቦችን አመቻችተው አቀብለዋል። ናይጄሪያውያኑ አዴሞላ ሉክማን እና አሌክስ ኢዎቢ፣ የሞሮኮው አዝዲን ኡናሂ፣ የአልጄሪያው አኒስ ሃጂ-ሙሳ፣ የቡርኪናፋሶው ዳንጎ ኡታራ፣ የቱኒዚያው ሃኒባል ሜጅብሪ፣ የደቡብ አፍሪካው ላይል ፎስተር እና የታንዛንያ ኖቫቱስ ሞሮሺ በሁለት ግቦች ላይ እጃቸው ያለበት ተጫዋቾች ናቸው። የናይጄሪያው የክንፍ የመስመር ተጫዋች አዴሞላ ሉክማን ሁለት ግቦችን በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አስቆጥሯል። የኮትዲቯሩ ክርስቶፈር ኦፔሪ እና የናይጄሪያው ሳሙኤል ቹኩዌዜ በተመሳሳይ አንድ አንድ ግቦች ከመረብ ላይ እንዲቆጠሩ የቀጥታ ተሳትፎ አድርገዋል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬን (ካፍ) የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ምርጫ ላይ ካስቀመጣቸው መመዘኛ መስፈርቶች አንዱ ማን ብዙ ለጎል የሚሆን አቀበለ? የሚለው ይገኝበታል። 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እስከ ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የግብ አግቢዎችና የኳስ አቀባዮቹ ፉክክር በያዘው ግለት ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።