ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል አርባምንጭ ከተማን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መቻል አርባምንጭ ከተማን 5 ለ 0 ረቷል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ-ግብር ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መዲና ዐወል ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ሴናፍ ዋቁማ፣ ገነት ኃይሉ እና ቱፊት ካዲዮ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ሁለት ግቦችን ያስቆጠረችው መዲና ዐወል  የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

በውድድር ዓመቱ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ38 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 12ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም