በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሲዳማ ቡና ባህር ዳር ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ምርትነሽ ዮሐንስ በ30ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥራለች።
የሲዳማ ቡናዋ ባንቺዓየሁ ደመላሽ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ ሰባተኛ ድሉን ያሳካው ሲዳማ ቡና በ24 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ለ14ኛ ጊዜ የተሸነፈው ባህር ዳር ከነማ በ10 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዛሬ በተደረጉ የ18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መቻል አርባምንጭ ከተማን 5 ለ 0፣ ሃዋሳ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ 18ኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የ19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከመጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።