በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ሃዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ታሪኳ ጴጥሮስ እና ብርቱካን ገብረክርስቶስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
የሃዋሳ ከተማዋ ብርቱካን ገብረክርስቶስ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጣለች።
በሊጉ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሃዋሳ ከተማ በ38 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ19 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።