በሰሜን ወሎ ዞን ለመጪው የመኸር ወቅት እርሻ ከሚያስፈልገው ማዳበሪያ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ዞኑ ደርሷል - ኢዜአ አማርኛ
በሰሜን ወሎ ዞን ለመጪው የመኸር ወቅት እርሻ ከሚያስፈልገው ማዳበሪያ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ዞኑ ደርሷል
ወልዲያ፤ መጋቢት 3/2018(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ለ2018/19 የመኸር እርሻ ከሚያስፈልገው ዘመናዊ ማዳበሪያ ከግማሽ በላይ የሚሆነው መግባቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
በመምሪያው የግብዓት አቅርቦት ባለሙያ ሳሙኤል ደሳለኝ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ በቀጣዩ መኸር ልማት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ወደ 211ሺህ ኩንታል የሚጠጋ ዘመናዊ ማዳበሪያ ለማስገባት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል።
እስካሁን በተደረገው ጥረትም ከ112ሺህ ኩንታል በላይ የሚሆነውን ዘመናዊ ማዳበሪያ ወደ ዞኑ ማዕከል ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል።
ቀሪውን ማዳበሪያ እስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው የገባውን ማዳበሪያ ወደ ወረዳዎች ማሰራጨት መጀመሩን አስረድተዋል።