ቀጥታ፡

የኮሪደር ልማት ዘመናዊ ከተሜነትን በማስፋፋት ከተሞችን የብልጽግና ማዕከል እያደረገ ነው

 አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ከተሞች የኮሪደር ልማት ዘመናዊ ከተሜነትን በማስፋፋት ከተሞችን የብልጽግና ማዕከል እያደረገ መሆኑን የከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደአክራ የሚያደርገው የቀጥታ በረራ የንግድ ትብብርን በማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት የተደራሽነት አድማሱን በማስፋት አሁን ላይ በ75 ከተሞችና በርካታ የገጠር አካባቢዎች በስፋት እየተሰራበት ነው።

የኢትዮጵያ ከተሞች የኮሪደር ልማት መርሃ ግብርም የአካባቢና የወንዞችን ሥነ-ምኅዳር ጤናማነትን በማረጋገጥ ነዋሪዎችን ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ እያጎናጸፈ ይገኛል።


 

የከተሞችንና የመንግስት ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመን ተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገኙበትን ምቹ ምኅዳርም ፈጥሯል።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ደጀን ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ከተሞች የኮሪደር ልማት፤ ብክለትን በማስወገድ ማራኪ የከተሜነት ምኅዳር እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።


 

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት የተደራሽነት አድማሱን በማስፋት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል።

በሰባ አምስት ከተሞች ተግባራዊ የተደረገው የኮሪደር ልማትም ከተሞችን የብልፅግና ማዕከል በማድረግ ስሉጥ የከተሜነት ምኅዳር በመገንባት ወሳኝ መሰረት እየጣለ መሆኑን አብራርተዋል።

የወንዝና የአካባቢ ብክለትን በመቀነስም የኢትዮጵያ ከተሞችን ውብ ገጽታ በማላበስ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን እያሳደገ እንደሚገኝ አሰገንዝበዋል።


 

ከ10 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ከተሞች ከ1ሺህ የማይበልጡ እንደነበር አውስተው፤ አሁን ላይ ከእጥፍ በላይ ተስፋፍቶ 2 ሺህ 500 መድረሱን ገልጸዋል።

የከተሞች ኮሪደር ልማትም የከተሞችን የመሰረተ ልማት ፍላጎት ምላሽ በመስጠት ለቀጣዩ ትውልድ ስሉጥ ከተሞችን ለማስተላለፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም