የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ-ግብር ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ-ግብር ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2018 (ኢዜአ)፦ ከመጋቢት 12 እስከ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ሊከናወኑ የነበሩ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገራቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
በአዲስ አበባ የሚደረገውን የውድድሩን ቀጣይ መርሐ ግብር በቅርቡ እንደሚያሳውቅም አመልክቷል።
ቦዲቲ ከተማ ከመቀሌ 70 እንደርታ፣ መቻል ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ቤንች ማጂ ቡና ከኢትዮጵያ መድን እና ነገሌ አርሲ ከሲዳማ ቡና በሩብ ፍጻሜው የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
በ1937 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ዋንጫ 81 ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ ውድድር ነው።