ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ዘላቂና አካታች ልማትን የሚያረጋግጡ ናቸው
Feb 6, 2026 49
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ዘላቂና አካታች ልማትን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ገለፁ። 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ተጠናቋል። በጉባኤው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ በጉባኤው ሃሳባቸውን የሰጡ የምክር ቤት አባላት እንደገለጹት፤ ባለፉት ስድስት ወራት በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ተግባራት በከተማዋ ዘላቂና አካታች ልማትን የሚያረጋግጡ ናቸው። እነዚህ ተግባራት የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን ለማስፈን ያለሙ መሆናቸውን አባላቱ አመልክተዋል። አስተዳደሩ ለኪነ-ጥበብ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሰፋፊ ሥራዎችን ያከናወነበትን ሂደት የምክር ቤት አባላቱ አድንቀዋል። በተለይም ዘመናዊ የኪነ-ጥበብ መድረኮች፣ የአምፊ-ቲአትሮችና ደረጃቸውን የጠበቁ የሲኒማ ቤቶች ግንባታ በተሻለ መልኩ መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። እነዚህ የጥበብ ማዕከላት ለከተማዋ የባህል ገጽታ ግንባታ፣ ለትውልድ ቀረጻ እንዲሁም ሀገራዊ አንድነትን ለሚያጠናክሩ የጋራ ትርክቶች መገንቢያ መሆናቸውንም አክለዋል። በመዲናዋ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እኩል የሚያገለግሉና አካታች የሆኑ ተቋማት መገንባታቸውን የጠቀሱት አባላቱ፤ እነዚህ ጅምር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል። ባለፉት ስድስት ወራት በፕሮጀክት አፈፃፀምና በገቢ አሰባሰብ የተገኙ ውጤቶች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ተግባራት የህዝብን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ማረጋገጥ ያስቻሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። የተከናወኑት የልማት ተግባራት ሁሉ ጥናትን መሰረት ያደረጉና ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚገቡ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው ብለዋል። ስራዎቹ አዲስ አበባ እንደ መዲናነቷ ሊኖራት የሚገባውን የከተማነት መስፈርትና ደረጃ የሚያሟሉ መሆናቸውንና በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። ግባችን ብልፅግናን ማረጋገጥ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ አዲስ አበባ የብልፅግና ማሳያና ማዕከል እንድትሆን በርብርብ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በመወያየት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። በተጨማሪም የ33 የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የሰባት የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት በሙሉ ድምፅ በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቋል።
ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ምክክሩን ስኬታማ የሚያደርጉና በአርዓያነት የሚጠቀሱ ተግባራትን አከናውኗል
Feb 6, 2026 66
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ምክክሩን ስኬታማ የሚያደርጉና በአርዓያነት የሚጠቀሱ መጠነ ሰፊ ተግባራት ማከናወኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ ገለጹ። ቋሚ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የሥራ አፈጻጸም እና የቀጣይ ዕቅዶችን ገምግሟል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ እውነቱ አለነ በወቅቱ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ ለዘመናት ስር ሰደው የቆዩ ውስብስብ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ስልጡን የፖለቲካ ባሕል በማስፈለጉ የምክክር ኮሚሽኑ ተቋቁሟል። ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ መጠነ ሰፊ ተግባራት ማከናወኑን ገልጸው የሂደቱ አሳታፊነትና አካታችነት ለሌሎች ሀገራት ጭምር ትልቅ ልምድ ሊሆን የሚችል መሆኑን ገልጸዋል። በሂደቱ ልዩነቶችን በኃይል የመፍታት አባዜ ቀርቶ፣ በምክክርና በሀሳብ የበላይነት ወደሚመራ ስልጡን የፖለቲካ ባህል መግባት መጀመሩ ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቅሰዋል። ኮሚሽኑ በብልሃትና በጥንቃቄ ባከናወናቸው ተግባራት እስካሁን በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የአጀንዳ ማሰባሰብና ለዋናው ጉባኤ የሚሳተፉ ሰዎችን የማስመረጥ ሥራ በስኬት ማከናወኑ ይበል የሚያሰኝ መሆኑንም አንስተዋል። ይህ ተግባር ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል ጠንካራ መሠረት እየጣለ መሆኑን ተናግረዋል። ሕዝቡ በምክክሩ ትልቅ ተስፋ መሰነቁን ጠቅሰው ቀሪ ሥራዎችን ለማሳካት ሁሉም ሚናውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል። በትግራይ ክልል የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን ማፋጠን እንደሚገባ ጠቅሰው፥ ባለድርሻ አካላትም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ሰብሳቢው ጥሪ አስተላልፈዋል። የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አዝመራው አንደሞ በበኩላቸው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አመርቂ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል። የምክክሩና የአጀንዳው ዋና ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን ጠቅሰው ሂደቱ የሁሉንም ሕዝብ ተሳትፎ በማረጋገጥ በኩል ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል። ወደ ዋናው የምክክር ጉባኤ ለመግባት አመቻቾችንና አወያዮችን በፍጥነት የማሰልጠን ሥራ በትኩረት ሊከናወን እንደሚገባ አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፥ የኮሚሽኑ የሥራ አፈጻጸም አካታችነትን በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል። እስካሁን ባለው ሂደት ከ1ሺህ 234 ወረዳዎች አጀንዳዎችን የማሰባሰብና ለዋናው ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮችን የማስመረጥ ሥራ በስኬት መከናወኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ከ38 የፌዴራል ተቋማት፣ ማኅበራት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎች ተሰብስበው የማደራጀት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ኮሚሽኑ የሥራ ሂደቱን ለማቀላጠፍ የአሠራር ሥርዓቱን በዲጂታል የታገዘ ማድረግ መቻሉንም ጠቁመዋል። ሀገራዊ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣ እጅግ መሠረታዊ የሚባሉ አጀንዳዎችን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ፣ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱን ማጠናቀቅ እና ዋናውን ሀገራዊ ጉባኤ ማካሄድ በቀጣይ በትኩረት የሚከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የምዘና እና ፈተና ሥርዓቱን ማዘመን ላይ ትኩረት ተደርጓል
Feb 6, 2026 54
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የምዘና እና የፈተና አሰጣጥ ሥርዓትን ለማዘመን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገለጹ። “ከተለዋዋጭ ዓለም ጋር የተጣጣመና ምላሽ የሚሰጥ የምዘና ሥርዓት መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ 3ኛው ሀገር አቀፍ ዓመታዊ የትምህርት ምዘናና ፈተና ጉባኤ የዘርፉ ተዋናዮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው። በጉባኤው በምዘናና ፈተና አተገባበር ዙሪያ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችንና ተግዳሮቶችን መፍታት የሚያስችሉ መፍትሄዎችን የሚያመላክቱ 25 ልዩ ልዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ይቀርባሉ። የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የምዘና ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ ማዘመን የሚያስችሉ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ በወቅቱ እንደገለጹት ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ብልጽግና ትምህርት ቁልፍ መሣሪያ ነው። በመሆኑም የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ የሕግ ማዕቀፎችንና አዳዲስ የትምህርት መርሃ ግብሮችን ተግባራዊ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። የትምህርት ዘርፉን ስብራት ለማከም መንግሥት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የፈተና አሰጣጥ ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ መደገፍና ማዘመን ቀዳሚው መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ የፈተናና ምዘና አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ጉባኤው በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን በጥናት ላይ ተመስርቶ ለመፍታትና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ለማጠናከር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ተቋሙ ለትምህርት ጥራት መሻሻል፣ ለምዘና ሥርዓቱ መዘመንና ብቁ ዜጋን ማፍራት የሚያስችሉ የምርምር ሥራዎች እንዲቀርቡ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል። ቀደም ባሉ ዓመታት የቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎባቸው፣ ለፖሊሲ አውጪዎችና ለትምህርት ዘርፉ ውጤታማነት በግብዓትነት እንዲያገለግሉ መደረጉን አመልክተዋል። በጉባኤው ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ(ዶ/ር) ዓለም የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ ለመድረስና በፍጥነት ለመራመድ የምዘና ሥርዓታችንን ዘመኑን የዋጀ ማድረግ የግድ እንደሚል ገልጸዋል። የጉባኤው ተሳታፊዎች ግሩም ታረቀ(ዶ/ር) እና ጀማል አብዱል ቃድር(ዶ/ር) በበኩላቸው መሰል ትምህርታዊ ጉባኤዎች ምሁራን ዕውቀታቸውንና የምርምር ግኝቶቻቸውን ለማካፈል እንደሚያስችሉ አንስተዋል፡፡
ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር የካቲት 1 ይጀመራል
Feb 6, 2026 50
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፦ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ ውድድሩን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ውድድሩ "የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ ይከናወናል። ሚኒስትር ዴኤታው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድሩን ለማከናወን አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። መንግስት የስፖርት ልማት ሥራዎችን ከስፖርት መሰረተ ልማት አንስቶ በታዳጊ ልማት እና በብሄራዊ ቡድን ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በያዘው እቅድ መሠረት ታዳጊዎችን በስልጠና ማዕከላትና በአካዳሚ መልሶ በማደራጀት የስልጠና አሰጣጥ ሂደትን የማዘመንና የመፈተሽ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ይህን መነሻ በማድረግ የዘንድሮው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር በአዳማ ከተማ ከየካቲት 1 እስከ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ግንባታ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ታዳጊዎችን በአንድ ማዕከል ላይ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ለማድረግ ውድድሩ የላቀ ድርሻ እንዳለው ተመላክቷል። ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር የአትሌቶች የስልጠና ሂደት የሚመዘንበት፣ ተሞክሮ የሚወሰድበት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ እንደሆነም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል። ተተኪ ስፖርተኞች የሚመለመሉበት ውድድር ከ15 ዓመት በታች አትሌቶች የሚወዳደሩበት መሆኑ ከባለፉት ዓመታት ለየት እንደሚያደርገው በመግለጫው ወቅት ተነስቷል። በዘንድሮው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ሶስት ሺህ የስፖርት ልዑካን እንደሚሳተፉና በ15 የስፖርት አይነቶች ውድድሩ እንደሚካሄድ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል። ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በውድድሩ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እያገዘ ነው
Feb 6, 2026 52
አጋሮ፤ ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እያገዘ መሆኑን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ(ዶ/ር) ገለጹ። የአጋሮ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዛሬ በይፋ ስራ ጀምሯል። በማስጀመሪያ መድረኩ የተገኙት ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ(ዶ/ር)፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በየአካባቢው ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊ እና ግልጽ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እያገዘ ነው ብለዋል። የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ የመልካም አስተዳደር ችግርን ትርጉም ባለው መልኩ መፍታት እያስቻለና በተለይም የህዝቡን እንግልት ለመቀነስና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ እንደሚጠናከር ገልጸዋል። በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ሕዝቡ ለረጅም ጊዜ ሲያነሳ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ ነው። ከእነዚህ ስራዎች መካከል አንዱ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰው እስካሁንም በሸገር፣ በአዳማ፣ በጅማ፣ በቢሾፍቱ እና በሻሸመኔ ከተሞች መጀመሩን አስታውሰዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀድሞ በተጀመረባቸው ከተሞች አገልግሎቱ የበለጠ እየሰፋ ወደ ክፍለ ከተሞችም እየወረደ መሆኑን ገልጸዋል። በአጋሮ ከተማ አስተዳደር የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ዘመናዊ እና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል። የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ስራ መጀመር በከተማ አስተዳደሩ ሲነሳ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያግዝ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአጋሮ ከተማ ከንቲባ ነዚፍ መሀመድ አሚን ናቸው። የአንድ ማዕከል አገልግሎቱን ወደ ስራ ለማስገባት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ፖለቲካ

ለዋናው ሀገራዊ ምክክር ግብዓት የሚሆኑ አጀንዳዎች ማሰባሰብ እና ልየታ ላይ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል
Feb 6, 2026 87
አዲስ አበባ፤ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፡-ለዋናው ሀገራዊ ምክክር ግብዓት የሚሆኑ አጀንዳዎች ማሰባሰብ እና ልየታ ላይ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቃባይ ጥበቡ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የሃሳብ ልዩነቶችና አለመግባባቶችን በምክክርና በሰለጠነ መንገድ በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡ ይህም ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠርና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ከፍተኛ አበርክቶ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ኮሚሽኑ ሁሉን አሳታፊና አካታች መርህን በመከተል የሁሉም ድምጽ የተሰማበት ውጤታማ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ማከናወኑን ገልጸዋል። በፌደራል ደረጃ፣በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከዳያስፖራው ማኀበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ መቻሉን አብራርተዋል። አጀንዳ ልየታ ላይም በተመሳሳይ ሰፋፊ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፥ በዋናው ምክክር ላይ የሚሳተፉ ተሳታፊዎችም መለየት መቻሉን አስረድተዋል። እንደ አቶ ጥበቡ ገለጻ፥ የምክክር ኮሚሽኑ እስከ አሁን በመጣበት ሂደትና በፈጠራቸው መድረኮች የምክክሩ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በነጻነት መግለጽ የሚችሉበት ምቹ አውድ ተፈጥሯል። የሀሳብ ልዩነቶችንና አለመግባባቶች መንስዔ የሆኑ ጉዳዮች በውይይትና በምክክር በመፍታት የተሻለች ሀገር መገንባት እንደሚቻል ትልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሻዕቢያ መንግስት የህዝብ ጠላት መሆኑን በተግባር አሳይቷል - የትግራይ ክልል ነዋሪዎች
Feb 6, 2026 135
መቀሌ፤ ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦ የሻዕቢያ መንግስት የህዝብ ጠላት መሆኑን በተግባር በሚገለጡ ድርጊቶች አሳይቷል ሲሉ በትግራይ ክልል ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከኤርትራ መንግስት ጋር የተፈጠረው አለመግባባት መነሻው በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሽሬን ሲቆጣጠር የኤርትራ ጦር ተከትሎ በመግባት የግለሰቦችን ቤቶች እና ፎቆች ማፍረስ ሲጀምር መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። በአድዋ እና በአዲግራት ከተሞችም ፋብሪካዎችን በመዝረፍና ነቃቅሎ በመጫን እንዲሁም በአክሱም በወጣቶች ላይ የፈጸመው ግድያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከፍተኛ ጸብ ውስጥ ሊያስገባው ችሏልም ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ በሽረ፣ በአክሱምና በመቀሌ ከተሞች የኢዜአ ሪፖርተር ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች፤ በሻዕቢያ የሚመራው የኤርትራ መንግስት የህዝብ ጠላት መሆኑን በተግባር በሚገለጡ ድርጊቶች አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል። የሽረ እንዳስላሴ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ራህዋ አለማየሁ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የሻዕቢያ ወታደሮች ከሸራሮ ከተማ እስከ መቀሌ ዙሪያ በንፁሀን ላይ ግድያና ዘረፋን ጨምሮ አረመኔያዊ ተግባር መፈፀማቸውን አስታውሰዋል። በተለይም በከተሞች ፋብሪካዎችንና የተለያዩ የህዝብ ሃብቶችን ነቃቅሎ በመጫን የሀገርና የህዝብን ሃብትና ንብረት በይፋ ዘርፈዋል ብለዋል። በመሆኑም የሻዕቢያ መንግስት የኢትዮጵያን እድገት የማይሻ የህዝብ ጠላት በመሆን ከሰላም ይልቅ አለመረጋጋትን፤ ከእድገት ይልቅ ድህነትን የሚሻ ስለመሆኑም አንስተዋል። የአክሱም ከተማ ነዋሪ መምህር አብርሀም ተመስገን፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ከተሞች በሰዎችና በንብረት ላይ አስነዋሪ ተግባራትን መፈፀማቸውን ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለምክር ቤት አባላት የሰጡት ማብራሪያም በተግባር ታይቶ ያለፈ እውነታ ነው ብለዋል። በመቀሌ ዙሪያ እንደርታ ወረዳ በመሰቦ የገጠር ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር መልአኩ በርኸ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ሰራዊት የቤት ንብረቶችን፣ ምርትና እንስሳትን ጭምር ዘርፈው ስለመውሰዳቸውም አስታውሰዋል። በዚህም በርካታ የአካባቢው አርሶ አደሮች ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጸው ለመከላከል ጥረት ያደረጉት ላይም ያለርህራሄ ግድያ ስለመፈፀማቸው አንስተዋል። በመሆኑም የኤርትራ መንግስት መቼም ቢሆን ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት መልካም የማያስብ የጥፋትና የውድቀት ዓላማ ሰንቆ የሚሰራ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
ሀገራዊ ምክክሩ አካል ጉዳተኞች በሀገራቸው ጉዳይ ተሳትፏቸውን ይበልጥ እንዲያሳድጉ መድረክ የፈጠረ ነው
Feb 6, 2026 130
አሶሳ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ምክክሩ አካል ጉዳተኞች በሀገራቸው ጉዳይ ተሳትፏቸውን ይበልጥ እንዲያሳድጉ መድረክ የፈጠረ መሆኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ የአካል ጉዳተኞች ተናገሩ። በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት የተቋቋመው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማህበረሰቡን በማወያየት የተሳታፊዎችና የአጀንዳ ልየታ ስራዎችን አከናውኗል። ስራውንም በማስቀጠል ሁሉንም አካላት በማሳተፍ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች ላይ በሳል ውይይት በማድረግ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት መሰረት እንደሚጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ማንሳታቸው ይታወሳል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ከተማ ነዋሪ የአካል ጉዳተኞችን አነጋግሯል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቀዳም ባሉት ግዜያት ባካሄዳቸው አካታችና አሳታፊ ምክክሮች በንቃት መሳተፋቸውንም ገልጸዋል። አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል የአሶሳ ከተማ ነዋሪ የሆነችው እስከዳር ጥበቡ የምክክር ኮሚሽኑ የአካል ጉዳተኞችና ሌሎች ድጋፍ የሚሹ ወገኖች በምክክሩ እንዲሳተፉ ማድረጉ አካታችነቱን ያረጋገጠ እንደሆነ ማሳያ ነው ብላለች። ኮሚሽኑ በሚያዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊ እንደነበረች አስታውሳ በምክክሩ የተለዩ አጀንዳዎችን በአግባቡ ምላሽ መስጠት እንደሚገባም ገልፃለች። ምክክሩ በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍንና ምቹ የመኖሪያ ካባቢ ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተናግራለች። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካል ጉዳተኞች ማህበር ሰብሳቢ አዳነች አስራት በበኩላቸው፤ በክልል ደረጃ በተካሄደው የምክክር መድረክ ከሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ አካል ጉዳተኞች መሳተፋቸውን ጠቁመዋል። የአካል ጉዳተኞች በምክክሩ መሳተፋቸው በህብረተሰቡ ዘንድ የነበረውን የተሳሳተ ግንዛቤ የቀየረ እና አካል ጉዳተኞች ሃሳብ እንዳላቸው እና ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ማድረጉን አብራርተዋል። ምክክሩ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት አስፈላጊነትን የሚያጠናክር እና ጦርነትን እንደ አማራጭ ለሚወስዱ አካላት ትምህርት የሚሰጥ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል።
በጠቅላላ ምርጫው የህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲጎለብት የድርሻችንን እንወጣለን - የምክር ቤት አባላት
Feb 6, 2026 116
ወልቂጤ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፡- በጠቅላላ ምርጫው የህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲጎለብትና ዴሞክራሲያዊ መብቱን እንዲጠቀም የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላት ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ሰላማዊ፣ አካታች እና ካለፈው ምርጫ የተሻለ እንዲሆን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ ጠቅላላ ምርጫውን አስመልክተው አስተያየታቸውን የሰጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላትም በምርጫው የህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲጎለብትና ዴሞክራሲያዊ መብቱን እንዲጠቀም የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። ከምክርቤቱ አባላት መካከል አቶ ሰላሙ ሱላሞ እንደገለፁት፤ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ማሳካት የሚቻለው የህግ የበላይነትን በማክበር፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ላይ መሳተፍ እና መተግበር ሲቻል ነው። በመሆኑም ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ምርጫ እንዲከናወን የድርሻቸውን እንደሚወጡ አብራርተዋል ። መራጩም የመምረጥ መብቱን ተጠቅሞ ይበጀኛል ያለውን ፖርቲ እንዲመርጥ በማስተማር ባገኙት አጋጣሚ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። ሌላኛው የምክር ቤቱ አባል ተፈራ ሞላ (ዶ/ር) ጠቅላላ ምርጫው ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ ባገኙት አጋጣሚ ለህዝቡ እያስገነዘቡ መሆኑን አስታውሰው ፤ ይህንንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ምርጫው ሰላማዊና ተአማኒነት ያለው ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ፓርቲዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች የሚጠበቅባቸውን ግዴታና ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚያከናውኑም አስረድተዋል። ምርጫው ለዴሞክራሲ፣ ለዘላቂ ሰላምና ለልማት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ የምክር ቤቱ አባል ወይዘሮ አሰለፈች ሃይሌ ናቸው። የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው
Feb 6, 2026 92
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል። በዚሁ ወቅትም፤ ምክር ቤቱ የ3ኛ ዙር የአዲስ አበባ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ-ጉባዔ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዢና ንብረት አሥተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ የዳኞች ሹመት ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ወቅትም የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ አጋማሽ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤት በማቅረብ ላይ ናቸው። በሪፖርታቸውም፤ ከለውጡ ወዲህ ግልጽ ከሆነ የብልጽግና እሳቤ በተቀዱ ስትራቴጂዎችና ፖሊሲዎች እየተመራች የምትገኘው አዲስ አበባ በርካታ ለውጦችን እያስመዘገበች መሆኗን ጠቅሰዋል። በዚህም በተከናወኑ በርካታ ተግባራት በዘመናት መካከል የተመላለስንበትን የኋላ ቀርነትና የድህነት ታሪክ እንዲሁም ጎስቋላ ገጽታን እየፋቅን፣ ከመጥፎ ጠረን እየራቅን፣ ከድንግዝግዙ እየተላቀቅን አሁን ወደምንገኝበት የተጨበጠና ወደሚታይ ብርሃናማ ምዕራፍ ተሸጋግረናል ብለዋል።
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎችን እያደረግን ነው - የፖለቲካ ፓርቲዎች
Feb 6, 2026 76
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎችን እያደረጉ መሆናቸውን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፤ የዘንድሮው ምርጫ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ልምዶች በተሻለ መልኩ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና አካታች እንዲሆን መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን መግለጻቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው መራጮች ለምርጫው እንደ ጡብ፣ ተሳታፊ ፓርቲዎች ደግሞ እንደ ማገር ናቸው በሚል የገለጹ ሲሆን፤ የምርጫ አውዱን ለማስፋት ልዩ ትኩረት መሰጠቱንም አረጋግጠዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤ ለምርጫው ስኬታማነት አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ፕሬዝዳንትና የሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት የምርጫና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አላምረው ይርዳው፤ ምርጫ የሕዝብ ሉዓላዊ ድምፅ የሚሰማበትና የሀገር የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወሰንበት ትልቅ መድረክ መሆኑን ጠቅሰዋል። ጥምረታቸው በአሁኑ ወቅት በበርካታ ክልሎች የዕጩዎች ምልመላና ምዝገባ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የድርጅታዊ መዋቅርን የማጠናከርና የምርጫ ማኒፌስቶን የማዘጋጀት ሥራዎች በትኩረት እየተሠሩ መሆኑን አስረድተዋል። ምርጫው ሰላማዊና ፍትሐዊ እንዲሆን ፓርቲያቸው የድርሻውን እንደሚወጣም አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ የጋሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀ-መንበርና የሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት ዋና አስፈጻሚ አቶ ዳሮት ጉምአ፤ ለዘንድሮው ምርጫ የሚመጥን ዝግጅት መጀመራቸውን አረጋግጠዋል። ምርጫው ዲሞክራሲያዊና ተዓማኒ እንዲሆን ከምርጫ ቦርድ ጋር በቅርበት እየሠሩ መሆኑን የገለጹት አቶ ዳሮት፤ ፓርቲያቸው በምርጫው ለመፎካከር የሚያስችሉ ስልቶችን ቀርጾ ወደ ሥራ መግባቱን ጠቁመዋል። በተለይም ከአባላትና ከደጋፊዎች ጋር ተከታታይ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት፣ በምርጫ ዝግጅትና ሂደት ላይ የጋራ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በሐረሪ ክልል በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
Feb 6, 2026 62
ሀረር፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፡-በሐረሪ ክልል በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ። በሐረሪ ክልል የመንግስትና የፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ። በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት፤ በግማሽ በጀት ዓመቱ በክልሉ አበረታች ተግባራትን ማከናወን ተችሏል። መድረኩም ትኩረት የሚያደርገው እቅድን መሰረት ያደረገ የመንግስትና የፓርቲ የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸምን በመገምገም ለቀጣይ ስራዎች ራስን ማዘጋጀት እንደሆነም አክለዋል። የግምገማ መድረኩም በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስፋት፣ የተስተዋሉ ውስንነቶችን በመሙላት የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስፋት ግብዓት የሚሰበሰብበት እንዲሁም ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት የሚደረግበትና ምቹ ሁኔታ የሚፈጠርበት መሆኑን ጠቁመዋል። በተለይም የፖለቲካና የአደረጃጀት ስራዎችን በአግባቡ ምልከታ በማድረግ የጋራ ግንዛቤና አረዳድ ሊኖር እንደሚገባም አክለዋል። የመንግስት ትልቁ ስራ ፈጣን የሆነ የኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥና የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ማሻሻል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በተለይም በክልሉ ገጠር እና ከተማ የህዝቡን ተጠቃሚነት ከማሻሻል አንጻር የተከናወኑ ስራዎችን መፈተሽ ይገባል ብለዋል። በዚህም ምርትና ምርታማነትን ከማጎልበት፣ የስራ እድልን ከማስፋት፣ የኑሮ ውድነትን ከመቀነስ፣ ኢንቨስትመንትን ከማበረታታትና ከሌሎች አንጻር የተከናወኑ ስራዎች ይገመገማሉ ብለዋል። የትምህርት ተሳትፎና ጥራት፣ ከጤና አገልግሎት እና ከሌሎች ማህበራዊ ዘርፍ እንዲሁም ከመሰረተ ልማት ግንባታ፣ ከማዘጋጃ ቤትና ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢን አሟጦ ከመሰብሰብ አንጻር የተከናወኑ ስራዎችም በጥልቀት ይታያሉ ብለዋል። የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመቅረፍና ብልሹ አሰራሮችን ከማስወገድ አኳያም የተከናወኑ ስራዎች በመድረኩ እንደሚገመገሙ ነው ያነሱት። በክልሉ ሰላምን ለማጽናትና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አንጻር እየተከናወኑ የሚገኙትን ተግባራት ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል ። በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ የክልሉ የመንግስትና የፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

ማህበራዊ
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የምዘና እና ፈተና ሥርዓቱን ማዘመን ላይ ትኩረት ተደርጓል
Feb 6, 2026 54
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የምዘና እና የፈተና አሰጣጥ ሥርዓትን ለማዘመን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገለጹ። “ከተለዋዋጭ ዓለም ጋር የተጣጣመና ምላሽ የሚሰጥ የምዘና ሥርዓት መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ 3ኛው ሀገር አቀፍ ዓመታዊ የትምህርት ምዘናና ፈተና ጉባኤ የዘርፉ ተዋናዮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው። በጉባኤው በምዘናና ፈተና አተገባበር ዙሪያ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችንና ተግዳሮቶችን መፍታት የሚያስችሉ መፍትሄዎችን የሚያመላክቱ 25 ልዩ ልዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ይቀርባሉ። የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የምዘና ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ ማዘመን የሚያስችሉ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ በወቅቱ እንደገለጹት ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ብልጽግና ትምህርት ቁልፍ መሣሪያ ነው። በመሆኑም የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ የሕግ ማዕቀፎችንና አዳዲስ የትምህርት መርሃ ግብሮችን ተግባራዊ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። የትምህርት ዘርፉን ስብራት ለማከም መንግሥት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የፈተና አሰጣጥ ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ መደገፍና ማዘመን ቀዳሚው መሆኑን ነው የገለጹት፡፡ የፈተናና ምዘና አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ጉባኤው በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን በጥናት ላይ ተመስርቶ ለመፍታትና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ለማጠናከር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ተቋሙ ለትምህርት ጥራት መሻሻል፣ ለምዘና ሥርዓቱ መዘመንና ብቁ ዜጋን ማፍራት የሚያስችሉ የምርምር ሥራዎች እንዲቀርቡ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል። ቀደም ባሉ ዓመታት የቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎባቸው፣ ለፖሊሲ አውጪዎችና ለትምህርት ዘርፉ ውጤታማነት በግብዓትነት እንዲያገለግሉ መደረጉን አመልክተዋል። በጉባኤው ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ(ዶ/ር) ዓለም የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ ለመድረስና በፍጥነት ለመራመድ የምዘና ሥርዓታችንን ዘመኑን የዋጀ ማድረግ የግድ እንደሚል ገልጸዋል። የጉባኤው ተሳታፊዎች ግሩም ታረቀ(ዶ/ር) እና ጀማል አብዱል ቃድር(ዶ/ር) በበኩላቸው መሰል ትምህርታዊ ጉባኤዎች ምሁራን ዕውቀታቸውንና የምርምር ግኝቶቻቸውን ለማካፈል እንደሚያስችሉ አንስተዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶችን ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ የማልማት፣ የመጠበቅና የመንከባከብ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል
Feb 6, 2026 66
አርባ ምንጭ፤ ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶችን ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ የማልማት፣ የመጠበቅና የመንከባከብ ተግባራት በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በግማሽ ዓመቱ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ኢዜአ ከቱሪዝም ቢሮ ሃላፊዋ ወይኒቱ መልኮ ጋር ቆይታ አድርጓል። የቢሮ ኃላፊዋ እንዳሉት በክልሉ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶችን ጨምሮ እምቅ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርሶችና ብሔራዊ ፓርኮች ይገኛሉ። እነዚህን የቱሪዝም ሀብቶች ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ የማልማት፣ የመጠበቅና የመንከባከብ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል በዚህም መስህቦቹን በማልማትና በማስተዋወቅ የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት። በግማሽ ዓመቱ 5 ሚሊየን 626 ሺህ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የክልሉን የመስህብ ስፍራዎች እንደጎበኙና ከዚህም ከ710 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል። በቱሪዝም ዘርፉ ባለፉት ስድስት ወራት ለ4ሺህ 658 ዜጎች በቀጥታ እንዲሁም ከ6 ሺህ በላይ ለሚሆኑት ደግሞ በተዘዋዋሪ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም አስረድተዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ አስጎብኚዎች መካከል በአርባ ምንጭ የሚገኘው የታሪክ ሪፍት ቫሊ ቱር ስራ ማኔጀር ወጣት ታሪኩ ቶሌራ የክልሉን የቱሪዝም ፀጋዎች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች ለማስተዋወቅ የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ገልጿል። በክልሉ እምቅ የቱሪዝም ፀጋዎችና አስተማማኝ ሰላም በመኖሩ እንዲሁም የማህበረሰቡ እንግዳ ተቀባይነት በርካታ ቱሪስቶች ወደ ስፍራው እንዲያቀኑ ምክንያት መሆኑንም ጠቅሷል። ለዚሁም እንግዶችን የሚያስተናግዱ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጆች፣ ሪዞርቶችና ሆቴሎች በስፋት መኖራቸውም የቱሪስቶችን ቆይታ ጊዜ እንዲጨምር አድርጓል ብሏል። በክልሉ ቱባ ባህል፣ መልክአ ምድሮች፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መስህቦች፣ አስደናቂ ታሪካዊ ስፍራዎች መኖራቸውን መመልከታቸውን የገለጹት ደግሞ ከጎብኚዎች መካከል አሜሪካዊቷ ኤልሳቤጥ አፈሳ ናቸው። በተመለከቱት ነገር መደሰታቸውን ጠቁመው ወደ አሜሪካ ሲመለሱ ሌሎች ቤተሰቦቼና ወዳጆቼ መጥተው እንዲጎበኙ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ወጣቶች በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና የጋራ ዕድገት ላይ ያላቸውን አበርክቶ እንዲያጎለብቱ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል
Feb 6, 2026 52
ድሬዳዋ፣ ጥር 28/2018 (ኢዜአ) ፡-ወጣቶች በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና የጋራ ዕድገት ላይ ያላቸውን አበርክቶ እንዲያጎለብቱ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። የአፍሪካ ቀንድ አገራት ወጣቶች በቀጣናው የጋራ ዕድገት እና ዘላቂ ሰላም ላይ የተቀናጀ አበርክቶ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችላቸው የድሬ-ፎረም ጉባኤ ነገ በድሬደዋ ከተማ መካሄድ ይጀምራል። የድሬ ፎረም ሁለተኛ ጉባኤን በማስመልከት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ለመገናኛ ብዘሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው ላይም ሁለተኛው የድሬ ፎረም ጉባኤ " የአፍሪካ ቀንድ አገራት ወጣቶች ለዘላቂ ሰላም እና አየር ንብረት ለውጥ ሚና " በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚካሄድ ተመላክቷል። በጉባኤው በሚነሱ ሐሳቦች ወጣቶች አሻጋሪ የሆኑ ሃሳቦችን በማመንጨት ለቀጠናው የጋራ ዕድገትና ተጠቃሚነት የድርሻቸውን ለመወጣት የሚስችላቸው መደላድል ይፈጥሯሉ ተብሏል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ተሳትፎና አደረጃጀት አቅም ግንባታ ኃላፊ አቶ አድነው አበራ፤ በወቅቱ እንዳሉት፣ ወጣቶች ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎም ወጣቱ ከሀገር ውስጥ ባለፈ በአፍሪካ አህጉርና በዓለም አደባባዮች የመሪነት ሚናውን እንዲያሳድግ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል። ወጣቶች ከሀገራቸው ባለፈ ለአህጉሪቱ አሻጋሪ ሃሳቦች በማመንጨት ሁለንተናዊ የጋራ ዕድገት እንዲመዘገብ የሚያስችሉ ተግባራትን እንዲያከናውኑ በየመስኩ የተመቻቸ ምህዳር ተፈጥሯል ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽነር ካሊድ መሐመድ በበኩላቸው፤ ነገ በሚጀመረው ጉባኤ ኢትየጵያ በአፍሪካ ቀንድና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰላም ማስከበር ስራ እያከናወነች ባለችው ስራና ቀጣይነት ላይ ውይይት ይደረጋል ብለዋል። በተጨማሪም በቀጠናው ዘላቂ እና የተቀናጀ ዕድገት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የከፍታ ሚና ወጣቶች ተቀናጅተው የድርሻቸውን እንዲወጡ መደላድል ለመፍጠር ጉባኤው ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል ። እንደ አገር የተጀመረውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ በሆነው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ እና ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ የማይጋለጥ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጉዞ ተሞክሮዎችን በማቅረብ በቀጠናው እንዲስፋፋ ፎረሙ ወሳኝ ሚና ያበረክታል ብለዋል። ወጣቱ በቀጣናው የተሻለ ሰላም፣ ዕድገት እና የጋራ ብልፅግንና ለማረጋገጥ አንዲችል የጋራ ፎረም አዘጋጅተን ጉዞ ጀምረናል ያለው ደግሞ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ምክር ቤት ሰብሳቢ ወጣት ሃሚድ አብደላ ነው። ነገ በሚጀመረው የድሬ ፎረም የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ወጣቶች ጉባኤ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጨምሮ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ የሁሉም ክልሎች የወጣት ተወካዮች ፣ ምሁራን እና ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተውጣጡ ወጣቶች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በክልሉ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር ማስተማር ስራን ለማሳካት ለመምህራን ልማት ትኩረት ተሰጥቷል
Feb 6, 2026 75
አርባ ምንጭ፣ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር ማስተማር ስራን ለማሳካት ለመምህራን ልማት ትኩረት መስጠቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ለሚያስተምሩ የአንደኛ ደረጃ መምህራን የክህሎት ስልጠና በአርባ ምንጭ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል። ስልጠናውን አስመልክተው የክልሉ ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራር ዘርፍ ሃላፊና የስልጠናው አስተባባሪ ታምራት ይገዙ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መከታተላቸው አካባቢያቸውንና የትምህርት ይዘቶችን በአግባቡ የሚረዱበትን እቅም ያሳድጋል። ይህን ለማሳካትም በአፍ መፍቻ የሚያስተምሩ መምህራን አቅም በማሳደግ የመማር ማስተማር ስራውን ለማሳለጥ እየተሰራ ነው ብለዋል። የአሁኑ ስልጠናም በዘርፉ ያለውን የመምህራን እጥረትን ለመፍታት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የተማሪ መጻሕፍትና የመምህሩ መምሪያ እጥረቶችን ለመፍታት መስራቱ ተጠቃሽ ነው ብለዋል። የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና የፈተና ስርዓትን በማዘመን የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን አስተባባሪው አስረድተዋል።
ኢኮኖሚ
በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ዘላቂና አካታች ልማትን የሚያረጋግጡ ናቸው
Feb 6, 2026 49
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ዘላቂና አካታች ልማትን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ገለፁ። 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ተጠናቋል። በጉባኤው ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ በጉባኤው ሃሳባቸውን የሰጡ የምክር ቤት አባላት እንደገለጹት፤ ባለፉት ስድስት ወራት በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ተግባራት በከተማዋ ዘላቂና አካታች ልማትን የሚያረጋግጡ ናቸው። እነዚህ ተግባራት የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን ለማስፈን ያለሙ መሆናቸውን አባላቱ አመልክተዋል። አስተዳደሩ ለኪነ-ጥበብ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሰፋፊ ሥራዎችን ያከናወነበትን ሂደት የምክር ቤት አባላቱ አድንቀዋል። በተለይም ዘመናዊ የኪነ-ጥበብ መድረኮች፣ የአምፊ-ቲአትሮችና ደረጃቸውን የጠበቁ የሲኒማ ቤቶች ግንባታ በተሻለ መልኩ መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። እነዚህ የጥበብ ማዕከላት ለከተማዋ የባህል ገጽታ ግንባታ፣ ለትውልድ ቀረጻ እንዲሁም ሀገራዊ አንድነትን ለሚያጠናክሩ የጋራ ትርክቶች መገንቢያ መሆናቸውንም አክለዋል። በመዲናዋ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች እኩል የሚያገለግሉና አካታች የሆኑ ተቋማት መገንባታቸውን የጠቀሱት አባላቱ፤ እነዚህ ጅምር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ብለዋል። ባለፉት ስድስት ወራት በፕሮጀክት አፈፃፀምና በገቢ አሰባሰብ የተገኙ ውጤቶች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ተግባራት የህዝብን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ማረጋገጥ ያስቻሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። የተከናወኑት የልማት ተግባራት ሁሉ ጥናትን መሰረት ያደረጉና ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚገቡ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው ብለዋል። ስራዎቹ አዲስ አበባ እንደ መዲናነቷ ሊኖራት የሚገባውን የከተማነት መስፈርትና ደረጃ የሚያሟሉ መሆናቸውንና በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። ግባችን ብልፅግናን ማረጋገጥ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ አዲስ አበባ የብልፅግና ማሳያና ማዕከል እንድትሆን በርብርብ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በመወያየት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። በተጨማሪም የ33 የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የሰባት የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት በሙሉ ድምፅ በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቋል።
የቀበሌ አደረጃጀቱ አገልግሎት በቅርበት ለማግኘትና የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እያስቻለ ነው
Feb 6, 2026 58
መቱ፣ጥር 29 (ኢዜአ)፡-በኢሉአባቦር ዞን ከዓመት በፊት ወደስራ በገባው የቀበሌ አደረጃጀት አገልግሎት በቅርበት ማግኘት ከማስቻል ባለፈ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እያስቻለ ነው ሲሉ በመቱ ወረዳ የእሁድ ገበያ ቀበሌ ነዋሪዎች ተናገሩ። በኢሉአባቦር ዞን 287 ቀበሌዎች በአዲስ መልክ ተዋቅረው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ቀበሌዎቹም ለህዝቡ በቅርበት እያገለገሉ መሆኑ ተመልክቷል። በዞኑ መቱ ወረዳ የእሁድ ገበያ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ታደሰ የቀበሌ አደረጃጀቱ ወደስራ ከገባ ወዲህ የሚፈልጉትን አገልግሎት በቅርበት እያገኙ ነው። ከዚህ በፊት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ወረዳ ማዕከል ለመሄድ ከሚያወጡት ወጪና ድካም መቅረቱን ገልጸው አሁን ላይ ግዜያቸውንም በአግባቡ ለልማት ስራ ማዋል እንደቻሉ ገልጸዋል። ከዚህም ባለፈ መንግስት ለልማት ጥያቄዎቻቸው ትኩረት እንዲሰጥ እድል መፈጠሩንም ተናግረዋል። አቶ ጀማል አብደላም የቀበሌ አደረጃጀቱ የሚፈልጉትን የመንግስት አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ የልማት ጥያቄዎቻቸው ምላሽ እንዲያገኙ እያገዘ ነው። በተለይ በወረዳ ደረጃ ይሰጥ የነበረው አገልግሎት ተገልጋዮች የሚበዙባቸው መሆኑን ተከትሎ ምልልስና ቀጠሮዎች ይበዙበት እንደነበር አስታወሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ በመንግሥት የሚቀረጹ የልማት ፕሮግራሞችና የስራ አቅጣጫዎች በወቅቱ ሕብረተሰቡ ጋር እንዲደርስ በማስቻል ለልማት እያነሳሳቸው መሆኑንም ገልጸዋል። በመቱ ወረዳ የእሁድ ገበያ ቀበሌ አስተዳዳሪ ወይዘሮ ፍጹም ባሕሩ እንደተናገሩት አዲሱ በቀሌ አደረጃጀት ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ ህብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ እያስቻለ ነው። በዚህም አገልግሎቱ ሕብረተሰቡ ጊዜውን በልማት ላይ በማዋል ረገድ ከፍተኛ ሚና ያለው ሲሆን ኑሮውን ለማሻሻል እያገዘ መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የኢሉአባቦር ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞሲሳ ለሜሳ ገልጸዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ በዞኑ 287 ቀበሌዎች ለሕብረተሰቡ በአዲሱ የቀበሌ አደረጃጀት እየተሰጠ የሚገኘው አገልግሎት ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሰፍን አግዟል ብለዋል።
የለውጡ መንግስት በአካባቢው ህዝብ ለረጅም ጊዜ ሲጠየቁ የነበሩ የልማት ጥያቄዎችን እየመለሰ ነው - የጉጂ አባ ገዳዎች
Feb 6, 2026 56
ሻኪሶ፤ ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦ የለውጡ መንግስት በአካባቢው ህዝብ ለረጅም ጊዜ ሲጠየቁ የነበሩ የልማት ጥያቄዎችን እየመለሰ መሆኑን የጉጂ አባ ገዳዎች ገለጹ። ሰሞኑን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት የሻኪሶ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል። በዚሁ ጊዜ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአካባቢው አባ ገዳዎች ቀደም ባሉት ዓመታት የጉጂ ህዝብ በርካታ የመሰረተ ልማት ችግሮች እንደነበሩበት አንስተዋል። በዚህ ምክንያት ህዝቡ አንገብጋቢ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመንግስት አካላት በተከታታይ ሲያቀርብ መቆየቱንም አስታውሰዋል። ከለውጡ ወዲህ ግን መንግስት የመሰረተ ልማት ጥያቄዎቻቸውን እየመለሰ፣ አካባቢውንም የልማት ማዕከል ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የጉጂ አባገዳ የሆኑት አባ ገዳ ገናሌ አጋ፣ በአካባቢያችን ሲጠየቅ የቆየው የልማት ጥያቄ ምላሽ እያገኘ በመሆኑ ተደስተናል ብለዋል፡፡ አካባቢው በወርቅና በሌሎች ማዕድናት እንዲሁም በቡና ሀብት የታደለ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህን ሀብት ለማልማት መሰረተ ልማት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል። የሻኪሶ አየር ማረፊያ ግንባታ መጀመር ለዘመናት ምላሽ ሳያገኙ የቆዩ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ተራ በተራ ምላሽ እያገኙ ስለመሆኑ ማሳያ መሆኑንም አክለዋል። እየተከናወነ ያለውን የልማት ሥራ እንዲሁም ሠላሙን አጠናክሮ ለማስቀጠል ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመቆም ድርሻውን እንዲወጣ የበኩላቸውን እንደሚወጡም አመልክተዋል። ሌላው የአካባቢው አባ ገዳ የሆኑት ገዳ ጉዬ በበኩላቸው የሻኪሶ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር እና ሌሎች በአካባቢው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች መንግስት አካባቢውን ለማልማት የሰጠውን ትኩረት ያመላክታል ብለዋል። የለውጡ መንግስት አካባቢውን ለማልማት የጀመረው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን ህብረተሰቡን በማስተባበር ሚናቸውን እንደሚወጡም አመልክተዋል። የአየር ማረፊያው ግንባታ ሲጠናቀቅም አካባቢውን በንግድና ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡
የፀሐይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Feb 6, 2026 85
ምእራብ አርሲ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ) ፡- በገጠራማ የሀገሪቱ አካባቢዎች የፀሐይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። በኦሮሚያ ክልል ምእራብ አርሲ ዞን ናንሰቦ ወረዳ የናንሰቦ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በይፋ ተመርቋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ኢንጅነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የነንሰቦ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ 824 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። በአሁኑ ወቅትም ገጠራማ የሀገሪቱ አካባቢዎች የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም እያደገ መምጣቱን ነው የሚናገሩት። በአሁኑ ወቅት መንግስት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የፀሐይ ኃይልን ጨምሮ ተግባራዊ የሚያደርጋቸው ፕሮጀክቶች በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰው ፕሮጀክቶቹ በዘላቂነት አገልግሎት እንዲሰጡ የአካባቢው ህዝብ ተገቢውን ጥበቃ ማድረግ አለበት ብለዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳይሬክተር ኢንጅነር ጥላሁን ብርሃኑ፤ አገልግሎቱ ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየሰራ ነው። በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት 8 ሺህ 400 በላይ ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል። ከዋናው ኤሌክትሪክ መስመር ርቀት ላይ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ደግሞ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን የማስፋፋት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል። በዚህም ከ 5 ሺህ 137 በላይ ደንበኞች የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል። የነንሰቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባሪሶ ባሜ በበኩላቸው፤ ከፍተኛ የልማት ፍላጎትና ሃብት ያለው የወረዳው ህዝብ የቆየ የኤሌክትሪክ ኃይል ጥያቄው እየተመለሰ ነው ብለዋል። የፌደራልና የክልል መንግስታት ቁርጠኛ አቋም በመያዝም የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እውን እንዲሆን ያከናወኑት ተግባራት ለአካባቢው እድገት ጉልህ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልጸዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አባገዳ ጣሂር ጎዳና በበኩላቸው፤ መንግስት የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመረው የፀሐይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የህዝቡን ህይወት መቀየሩን ገልጸዋል። በዚህም የለውጡ መንግስት ሊመሰገን ይገባል ያሉት አባገዳው የአካባቢው ህብረተሰብ የፀሐይ ኃይል ማመንጫው ዘላቂነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ ተገቢውን ጥበቃ እንደሚያደርግም ነው ያረጋገጡት።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እያገዘ ነው
Feb 6, 2026 52
አጋሮ፤ ጥር 29/2018(ኢዜአ)፦ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እያገዘ መሆኑን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ(ዶ/ር) ገለጹ። የአጋሮ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዛሬ በይፋ ስራ ጀምሯል። በማስጀመሪያ መድረኩ የተገኙት ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ(ዶ/ር)፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በየአካባቢው ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊ እና ግልጽ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እያገዘ ነው ብለዋል። የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ የመልካም አስተዳደር ችግርን ትርጉም ባለው መልኩ መፍታት እያስቻለና በተለይም የህዝቡን እንግልት ለመቀነስና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ እንደሚጠናከር ገልጸዋል። በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ሕዝቡ ለረጅም ጊዜ ሲያነሳ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ ነው። ከእነዚህ ስራዎች መካከል አንዱ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰው እስካሁንም በሸገር፣ በአዳማ፣ በጅማ፣ በቢሾፍቱ እና በሻሸመኔ ከተሞች መጀመሩን አስታውሰዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀድሞ በተጀመረባቸው ከተሞች አገልግሎቱ የበለጠ እየሰፋ ወደ ክፍለ ከተሞችም እየወረደ መሆኑን ገልጸዋል። በአጋሮ ከተማ አስተዳደር የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ዘመናዊ እና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል። የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ስራ መጀመር በከተማ አስተዳደሩ ሲነሳ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያግዝ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአጋሮ ከተማ ከንቲባ ነዚፍ መሀመድ አሚን ናቸው። የአንድ ማዕከል አገልግሎቱን ወደ ስራ ለማስገባት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና በብቁ ባለሙያዎች የታገዘ ቀልጣፋ የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት እየሰጠች ነው- የውጭ ሀገራት ዜጎች
Feb 6, 2026 97
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና በብቁ ባለሙያዎች የታገዘ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ቀልጣፋ የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት እየሰጠች መሆኑን ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች ገለጹ፡፡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በህግ የተሰጠውን የድንበር ቁጥጥር ለማከናወን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአየር ድንበር ቁጥጥር ሥራ ያከናውናል፡፡ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ዓለም አቀፍ ህግና አሰራርን ተከትለው በነጻነት መንቀሳቀስ የሚችሉበት የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል፤ ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እንግዶችን ለመቀበል ያደረገውን ዝግጅትም አስጎብኝቷል፡፡ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመዳረሻ ቪዛ ሲቀበሉ ያገኘናቸው ጋናዊቷ ማቪስ አኒማ ቦንሱ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት መስጫ መስኮቶች ጥቂት ተገልጋዮች ደግሞ ብዙ ነበሩ ብለዋል፡፡ በዚህ ምክንያት "ከአውሮፕላን እንደወረድኩ ሰልፍ ለመያዝ እየሮጥኩ ነበር የመጣሁት" ያሉት ማቪስ አኒማ ነገር ግን የጠበቃቸው በፈገግታ የሚያስተናግዱ ባለሙያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ስምጣ ስርዓቱ ሁሉ ተቀይሯል፤ የቪዛ አገልግሎቱ ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂና የላቀ አገልግሎት በሚሰጡ ባለሙያዎች ተሞልቷል ብለዋል፡፡ ለዚህ ስኬት ትልቅ አድናቆት እንዳላቸው የገለጹት ማቪስ አኒማ፤ ቀልጣፋ የመዳረሻ ቪዛ በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡ በኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመዳረሻ ቪዛ ሲወስድ ያገኘናቸው ብራዚላዊው ፔድሮ ላካዝ አማራል በኢትዮጵያውያን ፈጣን የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት አሰጣጥ ተድንቄያለሁ ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት ቪዛ እንዳልነበራቸው ገልጸው፤ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሱ ከአምስት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሁሉንም ዶክመንቶቻቸውን አረጋግጠው የመዳረሻ ቪዛ እንደሰጧቸው ተናግረዋል፡፡ "የተጠየኩት የግብዣ ደብዳቤና ፓስፖርቴን ነው፤ ባለሙያዎች በፈገግታ ነው የሚያስተናግዱ ቅንና መልካሞች ናቸው" ብለዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥራ ባለደረባና የሌሴቶ ዜግነት ያላቸው ማምዌላዝ ኮማ የኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን አገልግሎት አስደናቂ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የመጀመሪያቸው መሆኑን በመግለጽ፤ የተደረገልኝ አቀባበል ኢትዮጵያዊ እንደሆኑኩ ተሰምቶኛልና በተደጋጋሚ መምጣት እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡ የኢሚግሬሽን አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣንና ቀልጣፋ መሆኑን "የቢዝነስ ክላስ" እንደሚመስል በመግለጽ፤ ኢትዮጵያውያን ቀናኢና እንግዳ ተቀባዮች በመሆናቸው ሁሉም ሰው ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ እመክራለሁ ብለዋል፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ካናዳዊት ሂሩት አሰፋ፤ ኢትዮጵያ እንደዚህ ዓይነት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ስትሰጥ በማየቴ ኩራት ተሰምተኛል ብለዋል፡፡ የመዳረሻ ቪዛ አገልግሎት ለማግኘት መሰለፍ አይጠበቅብንም፤ ምክንያቱም በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት የሚሰጡ ብዙ ባለሙያዎች አሉ ብለዋል፡፡ ባለሙያዎች ፈጣኖች መሆናቸውን ገልጸው፤ ማንኛውንም ጫና ተቋቁመው ሰዎችን በብቃትና በፍጥነት ያስተናግዳሉ ብለዋል፡፡
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል
Feb 6, 2026 64
ጂንካ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፡-ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን የዘርፉ ምሁራን ገለፁ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት በጂንካ ዩኒቨርስቲ በኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ሌንጮ ደሳለኝ እንዳሉት በዲጂታል ኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓቱን ለማዘመንና ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎች እጅግ ውጤታማ ናቸው። ከተቋማት ለአብነት የጂንካ ዩኒቨርስቲን የጠቀሱት ተመራማሪው በዩኒቨርስቲው ባለፉት ዓመታት ሲተገበር የቆየው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የመማር ማስተማር ስራውን አንድ እርከን ማሳደጉን ጠቅሰዋል። በዩኒቨርስቲው በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር ማስተማር ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው ይህም ጥራቱን የጠበቀና በተግባር የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት አስችሏል ብለዋል። የፈተና አሰጣጡም በበይነ መረብ አማካኝነት መሆኑም ኩረጃና የፈተና ስርቆትን ለመከላከል እንዳስቻለ ጠቁመው የተማሪዎች የውጤት አያያዝም ከስህተት በፀዳ መልኩ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን አስችሏል። የዲጂታል ቴክኖሎጂው በተለይ የተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ለማሳደግ ትልቅ ሚናን እየተጫወተ እንደሚገኝም አንስተዋል። በዩኒቨርስቲው የኤሌክትሮንክስ የትምህርት ክፍል ዳይሬክተር እና የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ መምህርና ተመራማሪ እሸቱ ተስፋዬ በበኩላቸው፤ እንዳሉት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የተጀመረው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ኢንሼቲቭ ዘመናዊ የንግድና የገንዘብ ልውውጥ እንዲስፋፋ አድርጓል። በቴሌ ብር፣ በሞባይል ባንኪንግ እና በሌሎችም ፈጣን የዲጂታል የገንዘብ ልውውጦች እንዲኖሩ በማድረግ የንግድ ስርዓቱ እንዲዘምን አድርጓል ብለዋል። በተለይ የዲጂታል መታወቂያው ወንጀልን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ለዜጎች ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም ጠቁመዋል። ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር የተጣጣመ ማህበረሰብን ለመፍጠር የተጀመረው ስራና በተለይ በኢትዮ ኮደርስ የወጣቱን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ የተጀመረው ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ማስቻሉን ጠቁመው ሀገራችን ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወዳዳሪና ተፎካካሪ የምትሆንበትን መደላድል መፍጠሩንም አስታውቀዋል። በተለይ በኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርስቲ ለማቋቋም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረው ንቅናቄ በሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ልህቀት እንዲመጣ ያስችላል ብለዋል። የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በምርምር፣ በህክምና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በመከላከያ እና በሌሎች የስራ መስኮች የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።
ማዕከሉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ይደርስ የነበረውን መጉላላት አስቀርቷል
Feb 5, 2026 76
ባህር ዳር፤ ጥር 28/2018(ኢዜአ)፦ ባህርዳር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ቀደም ሲል ይደርስ የነበረውን መጉላላት እንዳስቀረላቸው ተገልጋዮች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትናንት በስቲያ በፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚሁ ጊዜ ከመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ጋር በተያያዘ በሰጡት ማብራርያ፣ አገልግሎቱ የተጀመረበት ጊዜ አጭር ቢሆንም በዘርፉ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለና በቀጣይም የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመር ቀደም ሲል ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት እንዳስቀረላቸው ገልጸዋል። ከማዕከሉ ተገልጋዮች መካከል አንዷለም ሞላ አንዱ ነው። እርሱ እንደሚለው፣ቀደም ሲል የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ክፍለ ከተማና ቀበሌ ሲሄድ ጉዳዩ ሳይፈጸም ተደጋጋሚ ቀጠሮ ብቻ ይሰጠው ነበር። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመር የሚፈልገውን አገልግሎት በፍጥነት ማግኘት እንዳስቻለው ገልጿል።። ሌላው የማዕከሉ ተገልጋይ አታለል ሙሴ በአንድ ቦታ ላይ በቴክኖሎጂ የታገዘ በርካታ አገልግሎቶችን በማግኘቱ ጊዜውንና ወጪውን እንደቆጠበለት ተናግሯል። አገልግሎቱ ቀደም ሲል ሲነሳ የነበረውን የመልካም አስተዳደርና የብልሹ አሰራር ችግሮችን በመፍታት ለተገልጋዩ እፎይታ የሰጠ መሆኑንም አመልክቷል። በማዕከሉ የሚፈልጉትን አገልግሎት በፍጥነት ማግኘታቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላዋ ተጋልጋይ አለሚቱ ንጉሴ ናቸው። እንዲህ አይነት አገልግሎቶች መጉላላትን በመቀነስ የህዝብን እርካታ የሚጨምሩ በመሆናቸው በሁሉም አካባቢዎች ሊሰፉ ይገባልም ብለዋል። የባህር ዳር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስተባባሪ ማስረሻ ፈንታ በበኩላቸው፤ በማዕከሉ የ12 ተቋማት 65 አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ ታግዘው እየተሰጡ መሆኑን ገልጸዋል። በማዕከሉ እየተሰጡ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል የባንክ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም፣ የትራንስፖርት፣ የመሬት ጉዳዮች፣ የንግድና የውሃና ፍሳሽ ይገኙበታል ብለዋል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሃላፊ ጤናው ምህረቱ፤ ቀደም ሲል ሕብረተሰቡ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በርካታ ቅሬታዎች ሲያነሳ እንደነበር አስታውሰዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ በፍጥነትና በጥራት መስጠት መጀመሩ የተገልጋዮችን እንግልት በማስቀረት ቅሬታውን ፈቷል ብለዋል። ማዕከሉ አሁን ለይ በቀን 325 ያህል ተገልጋዮችን እያስተናገደ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀጣይም አገልግሎቱን ለማስፋት ጥረት ይደረጋል ብለዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ተንቀሳቃሽ አገልግሎት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እተደረገ እንደሚገኝም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው ይታወሳል።
ስፖርት
ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር የካቲት 1 ይጀመራል
Feb 6, 2026 50
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፦ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ ውድድሩን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ውድድሩ "የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ ይከናወናል። ሚኒስትር ዴኤታው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድሩን ለማከናወን አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። መንግስት የስፖርት ልማት ሥራዎችን ከስፖርት መሰረተ ልማት አንስቶ በታዳጊ ልማት እና በብሄራዊ ቡድን ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በያዘው እቅድ መሠረት ታዳጊዎችን በስልጠና ማዕከላትና በአካዳሚ መልሶ በማደራጀት የስልጠና አሰጣጥ ሂደትን የማዘመንና የመፈተሽ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ይህን መነሻ በማድረግ የዘንድሮው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር በአዳማ ከተማ ከየካቲት 1 እስከ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ግንባታ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ታዳጊዎችን በአንድ ማዕከል ላይ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ለማድረግ ውድድሩ የላቀ ድርሻ እንዳለው ተመላክቷል። ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር የአትሌቶች የስልጠና ሂደት የሚመዘንበት፣ ተሞክሮ የሚወሰድበት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ እንደሆነም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል። ተተኪ ስፖርተኞች የሚመለመሉበት ውድድር ከ15 ዓመት በታች አትሌቶች የሚወዳደሩበት መሆኑ ከባለፉት ዓመታት ለየት እንደሚያደርገው በመግለጫው ወቅት ተነስቷል። በዘንድሮው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ሶስት ሺህ የስፖርት ልዑካን እንደሚሳተፉና በ15 የስፖርት አይነቶች ውድድሩ እንደሚካሄድ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል። ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በውድድሩ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ቡና የሊጉን የመጀመሪያ ዙር በድል አጠናቋል
Feb 6, 2026 58
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 አሸንፏል። በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የአማካይ ተጫዋቹ ኤርሚያስ ሹምበዛ በ14ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። አቡበከር አዳሙ ከኢትዮጵያ ቡና፣ መልካሙ ቦጋለ ከወላይታ ድቻ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል። ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮጵያ ቡና በ23 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 12ኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ድሉን አስመዝግቧል። በአንጻሩ በሊጉ ሰባተኛ ሽንፈትን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ በ16 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ወላይታ ድቻ ባለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም። ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ የ19ኛ ሳምንት ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ተጠናቋል። የፕሪሚየር ሊጉ የሁለተኛ ዙር መርሐ-ግብር የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀመር የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።
አርባምንጭ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ
Feb 6, 2026 52
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር አርባምንጭ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ታምራት እያሱ በ32ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል አርባምንጭ ከተማ መሪ ሆኗል። በ38ኛው ደቂቃ አቤል ነጋሽ የድሬዳዋ ከተማን የአቻነት ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ በ12 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዞ የመጀመሪያውን ዙር አጠናቋል። ቡድኑ በውድድር ዓመቱ ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ድሬዳዋ ከተማ በ24 ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል
Feb 6, 2026 142
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ በሊድስ ዩናይትድ እና ኖቲንግሃም ፎረስት መካከል ይካሄዳል። ጨዋታው ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በኢላንድ ሮድ ስታዲየም ይደረጋል። ሊድስ ዩናይትድ በ26 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል። ኖቲንግሃም ፎረስት በተመሳሳይ 26 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ11ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 10 ጨዋታዎች ሊድስ ዩናይትድ ሶስት ጊዜ ሲያሸንፍ ኖቲንግሃም ፎረስት በአራቱ አሸንፏል። በሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። በጨዋታዎቹ ላይ ሊድስ ዩናይትድ 14 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት 17 ጎሎችን አስቆጥሯል። ክለቦቹ ዘንድሮ በሊጉ የመጀመሪያ ዙር ባደረጉት ጨዋታ ኖቲንግሃም ፎረስት 3 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ሊድስ ዩናይትድ ከሁለት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። በ24ኛ ሳምንት በሊጉ መሪ አርሰናል 4 ለ 0 መሸነፉ አይዘነጋም ። በ24ኛ ሳምንት ከክሪስታል ፓላስ ጋር አንድ አቻ የተለያየው ኖቲንግሃም ፎረስት ማሸነፍ ወደ ድል መንገድ ይመልሰዋል። ሶስት ነጥብ ለሁለቱም ቡድኖች ከወራጅ ቀጠና ስጋት ለመራቅ ወሳኝ ነው። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር እስከ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
አካባቢ ጥበቃ
የተፋሰስ ልማት ስራ የአፈር ለምነትን በመጨመር ምርትና ምርታማነታችንን አሳድጎልናል- አርሶ አደሮች
Feb 6, 2026 59
ወላይታ ሶዶ ፤ ጥር 29/2018 (ኢዜአ)፡- የተፋሰስ ልማት ስራው የአፈር ለምነትን በመጨመር ምርትና ምርታማነታቸውን ማሳደጉን በደቡብ ኢትዮጵያ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ተናገሩ። በደቡብ ኢትዮጵያ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ እየተካሔደ ያለው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ የመሬት ለምነትን በመመለስ ምርታማነት ለማሳደግ እያስቻለ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ነዋሪ አቶ ተስፋዬ ሜጊሶ እና ማርታ አዋሾ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ መጀመሩ በጎርፍ እየተጠረገ ይወሰድ የነበረውን ለም አፈር ጥቅም ለይ ለማዋል አስችሎናል ይላሉ። በአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራው ሳቢያ የደረቁ ምንጮች ዳግም እንዲፈልቁ በማድረጉ የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲለሙ ማድረጉን አመልክተዋል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ምስራቅ ባድዋቾ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አበራሽ አቡቶ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሰራው የተራቆጡ አካባቢዎች ዳግም እንዲለሙ ማድረጉን ተናግረዋል ። በዚህም የተለያዩ የጓሮ አትክልት በማምረት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ጠቅሰው የተፋሰስ ልማት ስራን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው ያመለከቱት ። በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፋኖሴ መኮንን በበኩላቸው፤ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራው ምርታማነት በማሻሻል ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው። ባለፉት ዓመታት በተሰራው ስራ እንደ ሀገር አደጋ ላይ ከነበሩ 54 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ውስጥ 33 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ዳግም እንዲያገግም ለማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።። በተለይም የአፈር ለምነትን በመጨመር፣ የደረቁ ምንጮች ዳግም እንዲፈልቁ በማድረግ እና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ጉልህ ሚና መጫወቱንም ነው ያነሱት። የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራው እንደ ሀገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማሳካት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዘንድሮው ዓመትም 25 ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ በ23 ሺህ ተፋሰሶች ላይ 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው የተፋሰስ ልማት ስራ ላይ እየታየ ያለው የህብረተሰብ የተሳትፎ ባህል መጠናከር እንደሚገባውም አሳስበዋል።
የሐረማያ ሐይቅ የቱሪስት መዳረሻነት የማበልጸግ ስራ በተቀናጀ መንገድ በመከናወን ላይ ይገኛል
Feb 2, 2026 147
ሐረማያ ፤ጥር 25/2018 (ኢዜአ) ፡-የሐረማያ ሐይቅን የቱሪስት መዳረሻነቱን የማበልጸግ ስራ በተቀናጀ መልኩ እየተካሔደ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። በማያ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙት የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል የሐረማያ ሃይቅ እንዱ ነው። ለበርካታ ዓመታት ደርቆ የነበረው ሐይቁ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች ትኩረት ተደርጎ በመከናወናቸው ወደ ቀድሞው ይዞታው መመለስ ችሏል። የከተማ አስተዳደሩ እና የአካባቢው ማህበረሰብ ሃይቁን እያለማውና እየተንከባከበው በመሆኑም የጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲምቢሩ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ሐይቁ ከመዝናኛነቱ ባለፈ ለወጣቶች የስራ እድል እየፈጠረ የሚገኝ ሲሆን በዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የማጎልበት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። አካባቢው ትልልቅ እሴቶችና ጸጋዎች የሚገኙበትና በኪነ ጥበቡም ዘርፍ ስመ-ጥር አርቲስቶች የፈለቁበት መሆኑንም ይገልፃሉ። የአካባቢውን ባህል፣ ኪነ ጥበቡብና ቱሪዝሙ ዘርፉን እንደ አንድ ጸጋ በመጠቀምና ከቱሪዝም ጋር በማሰናሰል የዘርፉን ኢኮኖሚ ማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። የማያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢፍራህ ወዚር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በአፈርና ውሃ ጥበቃ እና በአረጓዴ አሻራ ስራ የተመለሰውን የሐረማያ ሃይቅ አጠቃቀምን የማስተካከል፣ የመጠበቅና የመንከባከብ ስራ እየተከናወነ ይገኛል። ሐይቁ ወደ ቀድሞ ቦታው መመለሱ ለጎብኚዎች እርካታን ከማጎናጸፉ ባለፈ ለአካባቢው ነዋሪዎችና ለወጣቶች የገቢ ምንጭ እየሆነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የሐረማያ ሐይቅ በተደረገለት እንክብካቤ ውብና ማራኪ የቱሪስት ቀልብ የሚስብ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ ለወጣቶችም የገቢ ምንጭ ማግኛ ሆኗል ያለው ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ባለሙያ ኦሊያድ በሪሶ ናቸው። በአካባቢው ባለሀብቶችን በመጋበዝ ሎጆችና ሪዞርቶች በማስፋፋት የተሻሉ ስራዎችን መስራት እንደሚቻልም ነው አቶ ኦሊያድ አስተያየታቸውን የሰጡት። በሐረማያ ሐይቅ ላይ የጀልባ አገልግሎት የሚሰጠው ወጣት ሙርቲ አህመድ፤ጎብኚዎችን በጀልባ ከማስጎብኘት ስራ በተጨማሪ በአሳ ልማት ስራም መሰማራቱን ይገልፃል።
በአማራ ክልል የበጋ ወራት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራዎች ምርታማነት እንዲጎለብት አግዘዋል
Feb 2, 2026 189
ባህር ዳር፤ጥር 25/2018 (ኢዜአ)፡- አማራ ክልል የበጋ ወራት የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች የአፈር ለምነትን በመጨመር ምርታማነት እንዲጎለብት እገዛ ማድረጋቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት፤ ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረት ለኢዜአ እንዳሉት በክልሉ የበጋ ወራት የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራዎች የአፈር ለምነትን በመጨመር ምርታማነት እንዲያድግ አግዘዋል። ስራውን በማስቀጠልም በያዝነው የበጋ ወራት በተለዩ ዘጠኝ ሺህ 206 ተፋሰሶች በ456 ሺህ 411 ሄክታር መሬት ላይ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ ለማከናወን ግብ ተይዞ ወደ ተግባር ተገብቷል። እስካሁን በተደረገ ጥረትም የዕቅዱን 37 በመቶ ማከናወን እንደተቻለ ጠቅሰው፤ በዚህም ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን ገልፀዋል። ከዚሁ በተጓዳኝም ለመጪው ክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የሚሆን ቦታ የመለየትና ለተከላ የሚውል ከ አንድ ነጥብ 7 ቢሊዮን በላይ ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን አንስተዋል። በተቀናጀ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ ላይ ከተሰማሩ አርሶ አደሮች መካከል በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ አርሶ አደር ዓለሙ መንጌ በበኩላቸው፤ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ከህልውና ጋር የተያያዘ መሆኑን በመረዳት ተግባሩን በማጠናከር በየዓመቱ በራሳቸው ተነሳሽነት እያከናወኑ መሆናችውን አንስተዋል። ዘንድሮም በቀበሌያቸው በተጀመረው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ ላይ በንቃት በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በቀበሌያቸው ያከናወኑት የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የመሬቱን ለምነት በመመለስ ለምርታማነት ማደግ አስተዋጽኦ እንዳበረከተላቸው የገለፁት ደግሞ ሌላኛው የዚሁ ወረዳ አርሶ አደር ካሳሁን መንግስት ናቸው። ቀደም ሲል የተሰራው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ግማሽ ሄክታር የእርሻ ማሳቸውን ለምነት በመመለሱ እስከ አምስት ኩንታል ተጨማሪ ምርት እንዲያገኙ ማስቻሉን ገልፀዋል። የልማት ስራው ተጠቃሚነታቸውን በተጨባጭ እያሳደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በበጋ ወራት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት የተከናወነ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራም የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባሻገር በግብርና ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ እንዳስቻለም ተመላክቷል።
የአረንጓዴ አሻራ፣ የተፋሰስ ልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች የውሃ አዘል መሬቶችን ከመጠበቅ አኳያ ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው
Feb 2, 2026 165
አዲስ አበባ፤ ጥር 25/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ አሻራ፣ የተፋሰስ ልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች የውሃ አዘል መሬቶችን ከመጠበቅ አኳያ ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ፡፡ ባለስልጣኑ የዘንድሮውን የዓለም የውሃ አዘል መሬቶች ቀን "የውሃ አዘል መሬት እና ሀገር በቀል እውቀት፤ የባህል ቅርሳችንን እናክብር" በሚል መሪ ቃል እያከበረ ይገኛል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የተለያዩ የውሃ አዘል መሬቶች እና የብዝሃ ህይወት ባለቤት ናት። እነዚህ ተፈጥሯዊ ጸጋዎች ተጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገሩም ሀገር በቀል እውቀት እና ባህላዊ የጥበቃ ስልቶች ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ መቆየታቸውን ገልጸዋል። የውሃ አዘል መሬቶች ከፍተኛ ጥቅም እያስገኙ መሆኑን ጠቁመው የተበከለ ውሃን በተፈጥሯዊ መንገድ ማጣራት፣ የጎርፍ አደጋን መከላከል እና የአፈር እርጥበትን መጠበቅ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እና የአካባቢን ሙቀት መቀነስን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡ በእነዚህ ወሳኝ የተፈጥሮ ሃብቶች ላይ የሚደርሱ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ዘመናዊውን ሳይንሳዊ እውቀት ከሀገር በቀል ጥበብ ጋር አቀናጅቶ መተግበር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበሩ ያሉ የአረንጓዴ አሻራ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች ለውሃ አዘል መሬቶች ደህንነት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን አረጋግጠዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአካባቢ ጥበቃና ደን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቴ ግጄ፤ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ውሃ አዘል መሬቶችን የመለየትና ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ተግባር በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የአማራ ክልል የአካባቢ ጥበቃና ደን ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ በልስቲ ፈጠነ በበኩላቸው፤ በክልሉ የሚገኙ የውሃ አዘል ስፍራዎችን በዘላቂነት ለማልማት ዘመናዊ ሳይንሳዊ ዕውቀቶችን ከባህላዊ ጥበቃ ዘዴዎች ጋር በማቀናጀት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ማህበረሰቡ ስለ እርጥብ መሬቶች ፋይዳ ያለውን ግንዛቤ እንዲያሳድግና ከሀብቱ በሥርዓት ተጠቃሚ እንዲሆን ሰፊ የትምህርትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የኦሮሚያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኢዳቲ ጠቁመዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ የምታስተናግዳቸው አህጉራዊ ሁነቶች
Feb 4, 2026 249
በሙሴ መለሰ የዓለም ስርዓት በፍጥነት እየተቀያየረ ይገኛል። አፍሪካ በዚህ ተለዋዋጭ ስርዓት ውስጥ የሚገባትን ቦታ የመያዝ ጉዳይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል። አፍሪካ በርካታ ወጣት የያዘች እና ብዝሃ የተፈጥሮ ፀጋዎች ያሏት አህጉር ናት። በአፍሪካ ተግባራዊ የተደረገው አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና በቀጣናው የንግድ ትስስርን በማሳለጥ እድገትን የማፋጠን ተስፋ ተጥሎበታል። አፍሪካ እድሎቿን በሚገባ ለመጠቀምና የሚስተዋሉ ፈተናዎቿን ለመሻገር ምላሽ የምትሰጥበት የልማት እና እድገት ጉዞዋን ከመበየን ባለፈ በዓለም መድረክ የሚኖራትን ሚናም ይወስናል። በአህጉር ደረጃ የተቀመጡ እንደ አጀንዳ 2063 እና የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ያሉ አህጉራዊ ማዕቀፎች እንዲሳኩ ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል። መንግስታት፣ የግሉ ዘርፍ እና የልማት አጋሮች ትብብራቸው ማጠናከር ይኖርባቸዋል። የተገቡ ቃልኪዳኖችን ወደ ሚለካ ውጤት ለመቀየር ዘላቂነት ያለው አመራር ሰጪነት፣ ኢንቨስትመንትን ማጠናከር እና ተከታታይነት ያለው ውይይቶችን ማድረግ ይገባል። ውሳኔ ሰጪዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኙ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ መድረኮች በአጀንዳዎች ላይ የተቀናጀ የተግበባር ምላሽ ለመስጠት ቁልፍ ሚና አላቸው። አፍሪካ እድሎቿን በመጠቀም እና ፈተናዎቿን በማለፍ መንገድ ላይ በሆነችበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ሁለት ወሳኝ አህጉራዊ ሁነቶችን ታስተናግዳለች። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል። የዘንድሮው መሪ ሀሳብ በአፍሪካ የውሃ ደህንነትና ንጽህና አጠባበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የመሪዎች ጉባኤ መሪ ሀሳብ ነው። ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓት ዘላቂ ልማት፣ አካታች እድገት፣ ጤናማ ማህበረሰብና ጠንካራ ስነ ምህዳር መገንባት፣ የተፈጥሮ ሀብት ዘላቂ አጠቃቀምና የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ከአጀንዳ 2063 ግቦች ጋር የተሳሰረ መሆኑ ተገልጿል። የመሪዎች ጉባኤው በመሪ ሀሳቡ በጥልቀት በመምከር የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦች ያስተላልፋል ተብሎም ይጠበቃል። ከመሪዎቹ ጉባኤ አስቀድሞ 48ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። 51ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች (PRC) ስብሰባ ከጥር 4 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በስብሰባው የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የሕብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል። ስብሰባው የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ መክሯል። ኮሚቴው በ2026 የአፍሪካ ህብረት መሪ ሀሳብ ላይ ምክረ ሀሳቦችን አቅርቧል። የኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብሰባ የሚያገለግል ነው። ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ማግስት ሌላኛው በኢትዮጵያ የሚካሄደው ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ነው። የቢዝነስ ፎረሙ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ኢሴኤ) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሁነቱን አዘጋጅተውታል። “የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ በፋይናንስ መደገፍ፤ ስራ እና ኢኖቬሽን ለዘላቂ ትራንስፎርሜሽን” የፎረሙ መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአፍሪካ የልማት እና የኢኮኖሚ እድገት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ በየዓመቱ የሚካሄድ ከፍተኛ አህጉራዊ የምክክር መድረክ መሆኑን የኢሲኤ መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ አጋርነትና የኢንቨስትመንት መጠንን ማሳደግ በተለይም የመንግስት እና የግል የተቀናጀ የፋይናንስ አቅርቦትን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይወያያል። የወጣቶችን የኢኖቬሽን ስራ ከፋይናንስ አቅርቦት ጋር የሚያስተሳስር የአፍሪካ የወጣቶች አይበገሬነትና ትራንስፎርሜሽን ማዕቀፍ ይፋ ይሆናል። በኢሲኤ የበለጸገውና የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ቃል ኪዳኖችን ትግበራ የሚከታታልና የሚቆጣጠር ስርዓትም በፎረሙ ይፋ ሆኖ ወደ ትግበራ ይገባል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሁነት ላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የምክክር መድረኮችና የባለሙያዎች ውይይቶች ይደረጋሉ። አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና የፈጣራ ባለሙያዎችን ከባለሀብቶች እና ፋይናንስ አቅራቢዎች ጋር የሚያገናኝ አውደ ርዕይም ይካሄዳል። ሁነቶቹ ቃል ኪዳኖችን ወደ ተጨበጡ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ለመቀየር አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል። ከአህጉራዊ ሁነቶቹ ባሻገር የባለብዙ ወገን መድረክ የሆነው የአፍሪካ እና ጣልያን ጉባኤ የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። ኢትዮጵያ አህጉራዊ ሁነቶቹን ማዘጋጀቷ በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ ጸንቶ የቆየውን የመሪነት ሚናዋን እንዲሁም የአህጉራዊ ምክክር፣ የባለብዙ ወገን ውይይቶችና ስትራቴጂካዊ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩባት ማዕከልነቷንም አጉልቶ የሚያሳይ ነው። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት እና በከተማ ማዘመን ስራ በፍጥነት እየተለወጠች ሲሆን የሁነቱ ተሳታፊዎች ከስብሰባው ባለፈ የመዲናዋን አዲስ መልክ የመመልከት እድል ያገኛሉ። የእነዚህ አህጉራዊ ስብሰባዎች ስኬት የሚለካው በአቋም መግለጫ ሳይሆን አጋርነትን በማጠናከር፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግና የሚጨበጥ ውጤት በአህጉሪቱ በማስመዝገብ ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያ የምታዘጋጃቸው አህጉራዊ ሁነቶች አህጉራዊ ትስስርን በማጠናከርና በዓለም ጉዳዮች ላይ የአፍሪካን ድምጽ ከፍ ለማድረግ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች። አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና የፈጣራ ባለሙያዎችን ከባለሀብቶች እና ፋይናንስ አቅራቢዎች ጋር የሚያገናኝ አውደ ርዕይም ይካሄዳል። ሁነቶቹ ቃል ኪዳኖችን ወደ ተጨበጡ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ለመቀየር አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል። ከአህጉራዊ ሁነቶቹ ባሻገር የባለብዙ ወገን መድረክ የሆነው የአፍሪካ እና ጣልያን ጉባኤ የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። ኢትዮጵያ አህጉራዊ ሁነቶቹን ማዘጋጀቷ በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ ጸንቶ የቆየውን የመሪነት ሚናዋን እንዲሁም የአህጉራዊ ምክክር፣ የባለብዙ ወገን ውይይቶችና ስትራቴጂካዊ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩባት ማዕከልነቷንም አጉልቶ የሚያሳይ ነው። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት እና በከተማ ማዘመን ስራ በፍጥነት እየተለወጠች ሲሆን የሁነቱ ተሳታፊዎች ከስብሰባው ባለፈ የመዲናዋን አዲስ መልክ የመመልከት እድል ያገኛሉ። የእነዚህ አህጉራዊ ስብሰባዎች ስኬት የሚለካው በአቋም መግለጫ ሳይሆን አጋርነትን በማጠናከር፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግና የሚጨበጥ ውጤት በአህጉሪቱ በማስመዝገብ ነው። በዚህ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያ የምታዘጋጃቸው አህጉራዊ ሁነቶች አህጉራዊ ትስስርን በማጠናከርና በዓለም ጉዳዮች ላይ የአፍሪካን ድምጽ ከፍ ለማድረግ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች።
በኒጀር በደረሰ ጥቃት መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው የአስካይ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ተጠግነው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ
Feb 3, 2026 140
አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2018(ኢዜአ)፦ በኒጀር ዋና ከተማ በደረሰ ጥቃት መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት የአስካይ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ተጠግነው በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ ፡፡ አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው ማብራሪያ ባለፈው ሐሙስ ጥር 21/ 2018 ዓ.ም ሌሊት በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው ጥቃት ሁለት የአስካይ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡ አውሮፕላኖቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋር የሆነው የአስካይ አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት ከአውሮፕላን አከራዮች የተከራያቸው እና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የተመዘገቡ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡ በአውሮፕላኖቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም የተላከው የቴክኒክ ቡድን ጉዳቱ መጠነኛ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን አውሮፕላኖቹ ተጠግነው በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡም ተገልጿል ::
የአፍሪካ ህብረት እና ዩናይትድ ኪንግደም አጋርነታቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Feb 2, 2026 131
አዲስ አበባ፤ጥር 25/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ዩናይትድ ኪንግደም ሰላምና ልማትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች አጋርነታቸውን ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር ጋር በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተወያይተዋል። ውይይቱ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ በቆየው የአፍሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም አጋርነት ያተኮረ ነው። ሁለቱ ወገኖች የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ እና ህግን መሰረት ያደረገ ዓለም አቀፍ ስርዓት ለመጠበቅ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ዩናይትድ ኪንግደም ከአፍሪካ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ትስስር ያደነቁ ሲሆን በዓለም ላይ ያላትን ገንቢ ሚና እና ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ጋር በጤና፣ ትምህርት፣ የአየር ንብረት ምላሽ እና ንግድ ያላትን ትብብር አንስተዋል። ሀገሪቷ ለአፍሪካ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) በአደጋ ጊዜ ዝግጁነት እና ምላሽ እንዲሁም በሶማሊያ ለአፍሪካ ህብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) ድጋፍ እያደረገች እንደምትገኝም አመልክተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር የአፍሪካ ህብረት በዓለም ዲፕሎማሲ፣ ቀጣናዊ ሰላም እና ልማት ያለውን ሚና አድንቀዋል። ሁለቱ ወገኖች የአፍሪካ ህብረት እና ዩናይትድ ኪንግደም በሱዳን፣ በሳሄል ቀጣና እና በሶማሊያ ያለውን የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሀገራት ለውኃ አቅርቦት፣ ጥራት እና ለንጽህና መሰረተ ልማቶች ቅድሚያ መስጠት ይጠበቅባቸዋል
Feb 1, 2026 250
አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፡- በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ሁሉም ሀገራት ለውኃ አቅርቦት፣ ለጥራት እና ለንጽህና መሰረተ ልማቶች ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው የአፍሪካ ሕብረት አስገነዘበ። በሕብረቱ የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና የዘላቂ አካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነር ሙሴ ቪላካቲ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ አህጉራዊው የግብርና ልማት ፕሮግራም ባለፉት 20 ዓመታት በአባል ሀገራት ዘንድ ጉልህ ለውጦች ማምጣቱን ገልጸዋል። ይህም አባል ሀገራት ጠንካራ የግብርና ዕቅድ ሥርዓት እንዲዘረጉ፣ ውጤታማ የኢንቨስትመንት ፕሮግራም ቀረፃ እንዲኖራቸው እና በምርትና ምርታማነት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ማገዙን አንስተዋል። ፕሮግራሙ ትኩረት የሚያደርገው በተለይም በምርት መጠንና በምርታማነት ዕድገት ላይ በመሆኑ፤ በአሁኑ ወቅት በበርካታ ሀገራት ውስጥ የሚታየው የምርት መጠን መጨመር የዚሁ ጥረት ውጤት ነው ብለዋል። ማንኛውም የልማት እንቅስቃሴ ከውኃ ጋር የተቆራኘ መሆኑን አስገንዝበው፤ ግብርናን፣ ኢነርጂን ወይም ጤናን ስናስብ ሁሉም ነገር ከውኃ ጋር የተያያዘ ነው፤ ስለዚህ ውኃ ለዘላቂ ልማት እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል። ለዚህም ነው “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የሚለው መሪ ሐሳብ ለ39ኛው የሕብረቱ መሪዎች ጉባዔ የተመረጠው ብለዋል። ኮሚሽነሩ ጉዳዩ በሕብረቱ አጀንዳነት የተያዘው በአህጉሪቱ ያለውን የውኃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል። በአህጉሪቱ ወደ 400 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች መሰረታዊ የውኃ አገልግሎት እንደማያገኙ ጠቁመው፤ ከ700 ሚሊየን የሚልቁትም ደኅንነቱ የተጠበቀ የጽዳት አገልግሎት የላቸውም ብለዋል። ይህ የአገልግሎት እጥረት በሰዎች የዕድገትና የአህጉሪቱ የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ትልቅ እንቅፋት መሆኑንም አመላክተዋል። ውኃን እንደ ትምህርት፣ ጤና እና ግብርና ትልቅ ትኩረት ሰጥተን ብንሠራበት ኖሮ ይህንን ችግር በቀላሉ መፍታት እንችል ነበር ያሉት ኮሚሽነሩ፤ አሁን ላይ ጉዳዩ ትኩረት በማግኘቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ዋነኛ ግብ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ መሆኑን ተናግረው፤ የአፍሪካ ግብርና ልማት ፕሮግራም 45 በመቶ የሚሆነውን የግብርና ምርት በአፍሪካ ለማምረት ግብ ይዞ እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። በተጨማሪ የአፍሪካን የውኃ አካላት ሀብት ወይም ብሉ ኢኮኖሚን ሙሉ በሙሉ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሆነ አንስተው፤ ይህ ዘርፍ ለአህጉሪቱ የሥራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ታምኖበታል ነው ያሉት። የአፍሪካን የሰብል ዝርያዎች መጠበቅ መቻል የአህጉሪቱ ኅልውና ጉዳይ መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸው፤ ለዚህም ጠንካራ የዘር ባንኮች ሊኖሩን ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።
ሐተታዎች
ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች
Jan 25, 2026 428
የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ ፍላጎት በመገንዘብ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች። ዶክተር አብዱራህማን ሮኔ ይባላሉ። ትውልድና ዕድገታቸው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልተሌ በተሰኘ አካባቢ ነው። የቀለም ትምህርት በሀገር ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ሀገረ አሜሪካ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው አድርገዋል። ለበርካታ ዓመታት ሕይወታቸውን በአሜሪካን ሀገር እየመሩ የሚገኙት ዶክተር አብዱራህማን ከሁለት ዓመታት በፊት ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ቦረና አቀኑ። የጉዟቸው ዓላማ ለዓመታት የናፈቋቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ብቻ እንደነበር ያስታውሳሉ። በቤተሰብ ጥየቃ ቆይታቸውም በቦረና ዞን ተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የሚጎበኙበት አጋጣሚ ተፈጠረ። ጉብኝታቸውም ሆስፒታሉ በኪነ-ሕንፃ የተዋበ መሆኑን ነገር ግን የህክምና ግብዓት እጥረት ያለበት ሆኖ ማግኘታቸውን ይናገራሉ። በተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ምልከታቸው በሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ታካሚዎች ሲቸገሩ ማየታቸው የወቅቱ አሳዛኝ ትውስታ እንደነበርና ይህን እጥረት ወደ አሜሪካን ሀገር ሲመለሱ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መወሰናቸውን አስታውሰዋል። ዶክተር አብዱረሃማን በተልተሌ አካባቢ ተወልደውና አድገው ለሕክምና ባለሙያነት ያበቃቸውን ትምህርት የቀሰሙ ሰው በመሆናቸው በሆስፒታሉ የተመለከቱት የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት የሺዎችን ሕይወት የሚታደግ ሰብዓዊ ፕሮጀክት የሚቀረጽበት ሃሳብ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። ከዚያም የራሳቸውን የሕክምና ሙያ ዕውቀትና በውጭ ያካበቱትን ግንኙነት በመጠቀም መነሻቸውን ባለፈው ዓመት ለተልተሌ እና ሜጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁስ በድጋፍ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ዓመትም የሞያሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ ለሶስት ትላልቅ የጤና ተቋማት ዘመናዊ ሕክምና መሳሪያዎችን አበርክተዋል። እነኚህ የሕክምና መሳሪያዎች አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያስታወሱበት በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ያስተማራቸውን ማህበረሰብ በማስታወስ መንግስት የዜጎችን የሕክምና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል። ሌላኛው በአሜሪካን ሀገር በሕክምና ሙያ የሚያገለግሉት ዶክተር ዋቆ ዳደቻ በበኩላቸው፤ ሁሉም ዜጋ በትብብር መስራት ከቻለ የማህበረሰብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል ይላሉ። ይህ የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ለማሟላት የሚደረገውን ተሳትፎ ሁሉም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ሊማሩበት የሚገባ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት የሕክምና ተቋማትን ጥራትና ደረጃ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ማሰብ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በውጭ የሚኖሩ የሕክምና ሙያተኞች የሚያደርጉት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በአርዓያነት የሚወሰድ ነው ብለዋል። በዶክተር አብዱራህማን መሪነት ለቦረና አካባቢ ሆስፒታሎች የተደረገው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍም የተቋማቱን የጤና አገልግሎት ጥራት በማስጠበቅ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በመግለጽ። በቀጣይም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህዝባቸውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማገዝ በኩል የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 766
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
አፍሪካውያን ሀገር በቀል አሰልጣኞች ጎልተው የታዩበት የአፍሪካ ዋንጫ !
Dec 28, 2025 716
35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው። በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ 24 ሀገራት 12ቱ በአፍሪካውያን የሚሰለጥኑ ናቸው። የአዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከዛው ከሀገራቸው ናቸው። የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሞሮኮን ለግማሽ ፍጻሜ አድርሰዋል።ሀገሪቷ በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከእ.አ.አ 2022 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እየመሩት የሚገኙት ሬግራጉዊ ሞሮኮን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቭዋር አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋች ኤመርሰን ፋኤ ነው። ፋኤ እ.አ.አ በ2023 በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን በመምራት ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል። በውድድሩ መሐል በውጤት ማጣት የተሰናበቱትን ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ ጂን-ሉዊስ ጋሴት በመተካት በጊዜያዊነት አሰልጣኝ የተሾመው ፋኤ ቡድኑን ለዋንጫ ማብቃቱ አስወድሶታል። በዘንድሮው ውድድር ዋንጫውን ለማንሳት የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ተርታ የተመደበችው ሴኔጋል አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፓፔ ታው ነው። ፓፔ ታው በተጫዋችነት ዘመኑ ለሴኔጋል ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። አሰልጣኙ ሴኔጋል ለ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እንድታልፍ አድርጓል። ከሶስት ዓመት በፊት በአልጄሪያ በተካሄደው የሰባተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) ሴኔጋል ዋንጫውን ስታነሳ የቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ መርቷል። የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ግብጽ የምትሰለጥነው በቀድሞ ኮከቧ ሆሳም ሀሰን ነው። በተጫዋችነት ዘመኑ በአፍሪካ ዋንጫ 11 ግቦችን አስቆጥሯል። በ177 ጨዋታዎች 69 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የብሄራዊ ቡድኑ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ሆሳም ሀሰን የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ በተጫዋችነት በማንሳት ስኬታማ አሰልጣኝ ነው። ሌላኛው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን አሰልጣኝ የ56 ዓመቱ ዴቪድ ፓጉ ነው። ካሜሮናዊው አሰልጣኝ የተሾሙት ከሰሞኑ ነው። ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን በመተካት ቡድኑን እንዲመሩ ኃላፊነት ተጠሎባቸዋል። በካሜሮን እግር ኳስ ባላቸው የታክቲክ መረዳት እና ብቃት የሚሞካሹት ፓጉ ቡድኑን አንድ በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጣሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል። ሌላኛው የውድድሩ ተሳታፊ ሀገር ዛምቢያ ናት።የ48 ዓመቱ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተከላካይ ሞሰስ ሲቾኔ የቡድኑ የወቅቱ ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2022 እስከ 2024 በጊዜያዊነት እና በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት ሲቾኔ በ2025 ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል። ምስራቅ አፍሪካን በውድድሩ ከሚወክሉ ሶስት ሀገራት መካከል አንዷ ሱዳና ናት። ጋናዊው ጀምስ ክዌሲ አፒያ የቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። አፒያ ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የጋቦን አሰልጣኝ ቲዬሪ ሞዩማ የብሄራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነበር። ለ11 ዓመታት ለጋቦን ተጫውተዋል። ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመሩ ይገኛል። የ44 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ሞሬና ራሞሬቦሊ የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2025 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛል። ሞሬና ከዚህ ቀደም የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነበሩ። የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን የአማካይ ተጫዋች ብራማ ትራኦሬ ነው። አሰልጣኙ ከእ.አ.አ ማርች 2024 አንስቶ ቡርኪናፋሶን እየመራ ይገኛል። ትራኦሬ ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የአንድ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ቱኒዚያ አሰልጣኝ የቀድሞ የቡድኑ የተከላከይ መስመር ተጫዋች ሳሚ ትራቤልሲ ናቸው። የ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ለቱኒዚያ ብሄራዊ ቡድን ለ10 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግሏል። ብሄራዊ ቡድኑን ከእ.አ.አ 2025 ቱኒዚያን እየመራ ይገኛል። በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ሞዛምቢክ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ፍራንቺስኮ ኩዌሪዮል ኮንዴ ጁኒየር (ቺኩዊኒዮ ኩንዴ) የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። የ60 ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሞዛምቢክ ለ15 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግለዋል። ለሀገራቸው በ43 ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኩንዴ ከእ.አ.አ 2021 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የናይጄሪያ አሰልጣኝ የሆነው ኤሪክ ቼሌ የኮትዲቭዋር፣ ማሊ እና ፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላቸው አሰልጣኝ ናቸው። ይሁንና ቼሌ የአፍሪካ የዘር ግንድ ቢኖራቸውም በፈረንሳይ መወለዳቸው የውጭ ሀገር ዜጋ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። የአፍሪካውያን አሰልጣኞች በአፍሪካ ዋንጫ የማሰልጠን ምጣኔ ከሌሎቹ ወቅቶች አንጻር የአሁኑ የተሻለ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ሀገር በቀል አሰልጣኞች እየተሰጣቸው ያለውን ትኩረት ያሳያል። 12 ሀገራት በውጭ ሀገር ዜጎች ይሰለጥናሉ። በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አፍሪካውያን የሚያሰለጥኗቸው ወይስ የውጭ ሀገር ዜጋዎች የሚመሯቸው ሀገራት ዋንጫውን ያነሳሉ? የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል።
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን
Dec 22, 2025 938
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ የተጀመረው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በወቅቱ የኤሌክትሮኒክ መሳሪዎችን ተጥቅሞ መረጃን በመተንተን እና መረጃን እንደ ልዩ ገጽታ በመጠቀም እና መለያ ቁጥር (ኮድ) በመስጠት አገልግሎት ላይ ይውል ነበር። ከዛ ጊዜ በኋላ በርካታ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞች እና ማሽኖች ተፈብርከው ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል። እ.አ.አ በ1946 በአሜሪካ የፔንሲሊቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ጥቅል አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያውን የኤሌክትሮኒክ ዲጂታል ኮምፒዩተር በመስራት የዲጂታል ዘመን ጅማሮን አበሰረ። ከእ.አ.አ 1943 እስከ 45 ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰራው ይህ ኮምፒዩተር ባለቤቶች ጆን ማውችሊ እና ጄ ፕሬስፐርት ኤከርት ናቸው። በ150 ኪሎ ዋት ኃይል የሚሰራው ኮምፒዩተር በሴኮንዶች ውስጥ በርካታ ስራዎችን ያከናውን ነበር። ኮምፒውተሩ በወቅቱ በነበሩ ባለሙያዎች ማርሽ ቀያሪ እና መሰረት ጣይ የሚል ስያሜ አግኝቷል። የዘመናዊ የዲጂታል ስርዓቶች ምሰሶ ነው የሚባለው ኢንተርኔት የተጀመረው እ.አ.አ በ1960ዎቹ መጀመሪያ ነበር። “አርፓኔት” የተሰኘ የአሜሪካ የጥናት ፕሮጀክት ኮምፒዩተሮችን ዘመኑ ከደረሰበት የኔትወርክ ስርዓቶች ጋር በማገናኘት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። እንግሊዛዊው የኮምፒዩተር ሳይንቲስት ቲም በርነርስ ሊ እ.አ.አ 1969 “ወርልድ ዋይድ ዌብ” (WWW) በመፍጠር ትስስርን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ አሸጋግሯል። ድረ ገጾችን በመፍጠር እና በህዝብ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሰፋ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ዲጂታል ቴክኖሎጂ ከኮምፒዩተር መሰራት ተነስቶ ወደ ዓለም አቀፍ የትስስር መሰረተ ልማትነት የተቀየረ ሲሆን በየዕለት ተዕለት የሰዎች ኑሮ፣ማህበራዊ መስተጋብር፣ ንግድ እና የመንግስታት አሰራር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ከማምጣት ባለፈ ዘርፎች በቴክኖሎጂ እንዲቃኙ አድርጓል። ዓለም ላይ አሁን ካለው ህዝብ 73 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። የዲጂታል ኢኮኖሚ የዓለምን ጥቅል ዓመታዊ ምርት (ጂዲፒ) የ15 በመቶ ድርሻን እንደሚያግዝ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ። ሞባይል ለኢንተርኔት መስፋፋት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ሀገራት እ.አ.አ 2025 በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ፣ ኔትወርኪንግ እና ለሌሎች ትራንስፎርሜሽ ስራዎች ያወጡት ኢንቨስትመንት ከአራት ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚልቅም ይገመታል። በአፍሪካ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ480 ሚሊዮን በላይ ተሻግሯል። ዲጂታል ስርዓቱን የሚያሳልጡ መሰረተ ልማቶች እና የዳታ ማዕከላት በአፍሪካ መንግስታት እና የልማት አጋሮች ትብብር እየተገነቡ ነው። ዲጂታል ኢኮኖሚ ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለትምህርት እና ክህሎት፣ ለመንግስት የአሰራር ውጤታማት፣ ለፋይናንስ አካታችነት እና ኮሙኒኬሽን ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 በፊት የዲጂታል ምህዳሯ የተገደበ ነው ማለት ይቻላል። ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት፣ ለቴሌኮም አገልግሎት ከፍተኛ ክፍያ ወጪ የሚወጣበት እና በቴሌኮም አገልግሎት የመንግስት ብቻ የበላይነት የሚታይበት ነበር። ከለውጡ በኋላ መንግስት የቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች አማካኝነት ዲጂታል ተጠቃሽ ነው። የዲጂታል ዘርፍ ከብዝሃ የኢኮኖሚ ምንጮች አንዱ ሆኖ ነው።ዲጂታላይዜሽን ለኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አካታች የሆነ የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ካስገባች ሰነባብታለች። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 አንስቶ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በማዘጋጀት ስተገብር ቆይታለች። ስትራቴጂው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን ዲጂታል የማድረግ አላማ ያደረገ ነው። በዚህም 900 ገደማ የሚሆኑ መንግስታዊ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ ሆነዋል።3000 የሚሆኑ የዲጂታል አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አግኝተዋል። የፋይዳ መታወቂያ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል። የሞባይል እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። የአራተኛ እና አምስተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰፋ መጥቷል።የዲጂታል ክህሎትም ተስፋ ሰጪ እድገት ታይቶበታል። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ክፍት እንዲሆን መንግስት ባስቀመጠው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት ሳፋሪኮም ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን “ምፔሳ” የተሰኘ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል። የመንግስት የዲጂታል ፖሊሲዎች እና የህግ ማዕቀፎች ለዘርፉ ምቹ ምህዳር በመፍጠር ትስስር እንዲሰፋ እና አገልግሎቶች እንዲዘምኑ አስችሏል። ኢትዮጵያ ከአምስት በፊት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በማቋቋም በርካታ ስራዎችን አከናውናለች። ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት በክረምት መርሃ ግብር (ሰመር ካፕም) ወጣቶች ሲማሩ እንደቆዩ አውስተው በዘርፉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያሳያል። ሁሉንም ዘርፍ የሚነካው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በግብርና፣ጤና፣ አገልግሎት እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በመግባት ስራን እያቀላጠፈ ይገኛል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የሚሰበሰቡ ዳታዎች ለመንግስት እና ግል ተቋማት አገልግሎት ላይ እየዋሉ እንደሚገኝም ተገልጿል። መንግስት ወጣቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ሀገርን አልፎም ዓለምን የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያቀርቡ የሚያደርገውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ቴሌብር፣ መሶብ እና ዘመንን ጨምሮ ያሉ የዲጂታል አገልግሎቶች የዘርፉን እድገት በማሳለጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የዲጂታል 2030ን ስትራቴጂ ይፋ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ መጠናቀቁን ገልጸዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ ያበሰሩ ሲሆን ተደራሽነትን ማስፋት፣ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን አመልክተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና አስተማማኝ የዲጂታል ምህዳር መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሦስት ቁልፍ ትልሞች እንዳሉት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህም ተደራሽነትን ማስፋት፤ እኩል እድል ማመቻቸትና በተቋማትና ህዝብ መካከል መተማመንን መፍጠር መሆናቸውን አብራርተዋል። ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፥ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው። ለአብነትም የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል ሲሉ አንስተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለው እንደገለጹት፥ አንድ ሺህ ሰላሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ሆነዋል ነው ያሉት። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ከተሞች ይደርሳል ብለዋል። በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሰራል ሲሉም አረጋግጠዋል።ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት፣ አካታችነት እና ማህበራዊ ለውጥ ቁልፍ ምሰሶ ነው። ስትራቴጂው በሚገባ ከተተገበረ፣ በቂ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ከተገነቡ እና ዜጎች በንቃት ከተሳተፉ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘመን ትሩፋቶች ተጠቅማ ትልሞቿን ማሳካት እንደምትችል አያጠራጥርም።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 775
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 1, 2026 747
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው። በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ
Dec 8, 2025 1342
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3651
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3311
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2152
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7960
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6448
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
"ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!!
Feb 6, 2026 75
"ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በያንተስራ ወጋየሁ -ዲላ ቀን ቀንን እየወለደ ጊዜ ሳያቋርጥ እንደ ዥረት መፍሰሱን አያቆምም። ትናንት አዲስ የነበረው አሮጌው የሚባልበት፣ ዛሬ አዲስ ሆኖ ነገ አሮጌ ለመባል ይሮጣል። ወቅቶች ይፈራረቃሉ፣ ይመሻል፣ ይነጋል፣ ትናንት ለዛሬ፣ ዛሬ ለነገ እንዲህ እንዲህ እየተቀባበሉ ዘመን ዘመንን እየተካ ዛሬ ላይ ተደርሷል። በጥምር ግብርናውና በቡናው የሚታወቀው ጌዴኦ ትናንትን ሸኝቶ ዛሬን እንደ አዲስ ለመቀበል ሽር ጉድ እያለ ነው። በክረምቱ የተዘራው ሰብል ተሰብስቦ ወደ ጎተራ እንዳስገባ ጌዴኦ አዲስ ዓመቱን ‹‹ዳራሮ››ን ይቀበላል። ዳራሮ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ቂም የያዘ ቂምና ቁርሾውን የሚተውበት፣ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ አዛውንቶች ወደ ሽምግልና የሚሸጋገሩበት እሴቶችን በውስጡ የያዘ ነው። "ያገኘሁትን ምርት ብቻዬን አልበላም" ብሎ የሚያምነው የጌዴኦ አርሶ አደር ካመረተው ምርት ለመሪው፣ ልጆች ለወላጆችና ለአሳዳጊዎቻቸው፣ አዲስ ተጋቢዎች ለአማቾቻቸው፣ ቂም የያዘ ሰው እንዲሁ የተቀየመውን ሰው ይቅርታ ለመጠየቅ ጉማታ ይዘው ይሄዳሉ። "ጉማታ" በጌዴኦ ዘመን መለወጫ ወቅት የሚፈጸም ስጦታ ነው። ጉማታ በቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ ወደ ታላላቆች ቤት ወይም ወደ ማኅበረሰቡ አደባባይ የሚወሰድ በመሆኑ፣ የግለሰብን ደስታ ወደ ማህበረሰባዊ ደስታ የሚቀይር ድልድይ ነው። በአጠቃላይ ጉማታ ከሌለ የዳራሮ በዓል ሙሉ አይሆንም። ጉማታ የጌዴኦን ሕዝብ አንድነት የሚያጸና፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ሀገር በቀል እሴት ነው። በዳራሮ በዓል አከባበር ውስጥ "ጉማታ" እጅግ አስፈላጊና ትልቅ ትርጉም ያለው ባህላዊ የክብር ስጦታ የመስጠት ሥርዓት ነው። "ጉማታ" ማለት በቀጥታ ትርጉሙ "ስጦታ" ማለት ቢሆንም፣ በጌዴኦ ባህል ግን ከስጦታ በላይ ነው። ምስጋናን፣ ፍቅርን፣ አክብሮትንና በረከትን የመጋራት መገለጫ ነው። የጌዴአ ባህላዊ የባሌ ስርዓት መሪ ሆነው የሚሰየሙት አባ ገዳ ለህዝብ ከመጸለይ፣ ከማስታረቅና ክፉን በማውገዝ ህዝቡ ተፈጥሮን እንዲንከባከብ ከማስተማር ውጭ አይዘሩም፣ አይነግዱም፣ አልፎም እንሳስትን አያረቡም፡፡ የዳራሮ በዓልን ተከትሎ ህዝቡ የሚያቀርብላቸውን "ጉማታ" በመቀበል ባህላዊ የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ ከመወጣት ውጪ። ኑሮው ከጥምር እርሻ ጋር የተቆራኘው የጌዴኦ ሕዝብ ዘርቶ ካጨደው፣ አርብቶ ካገኘው ከብት፣ አንቦ ከቆረጠው ማር፣ ከሁሉም በአይነት በአይነቱ ሸክፎ ዳራሮ ወደ ሚከበርበት ሶንጎ (አደባባይ) ይተማል። ለጉማታ ከሚቀርቡ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ስጦታዎች አንዱ ማር ነው። ማር በጌዴኦ ዘንድ የጣፋጭ ዘመንና የጤና ምልክት ተደርጎ ይወሰዳልና ዋናው ስጦታ ነው። ጌዶኦዎች ቡና፣ ቅቤና ባህላዊ ምግቦች፣ የቁም እንስሳት በግና ስንጋ እንዲሁም ገንዘብ በመያዝ በበዓሉ ውስጥ የጉማታ ስርዓት ሲደርስ ተሽቀዳድመው ለአባ ገዳው በመስጠት ምርቃት ይቀበላሉ። "ጉማታ" የተቀበለው ሰው የሚመርቀው ምርቃት በሰጪው ሕይወት ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይታመናልና ከስጦታው ይልቅ ምርቃቱ ትልቅ ዋጋ አለው። "ያገኘሁትን ምርት ብቻዬን አልበላም" ብሎ የሚያምነው ጌዴኦ በረከትን ማካፈል ለቀጣዩ ዓመት ተጨማሪ በረከት እንደሚያገኝ ስለሚያውቅ ጉማታ መስጠት የዘመናት ቅርሱ ነው። ጉማታ ከአባ ገዳና ከባህል ሽማግሌዎች ባለፈ አርሶ አደሩ ከማጋኖ (ከፈጣሪ) ያገኘውን በረከት ለሚወዳቸውና ለሚያከብራቸው ሰዎች የሚያቀርብበት መንገድ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ልጆች ለወላጆቻቸውና ለቤተሰብ አባላት ላሳደጓቸውና ለሰጧቸው ምርቃት ምስጋናቸውን ለመግለጽ ጉማታ ይዘው ይሄዳሉ። በቅርቡ ጋብቻ የመሠረቱ ወጣቶች ወደ አማቾቻቸው ቤት ጉማታ ይዞ በመሄድ ዝምድናቸውን ያጠናክራሉ። በዓመቱ ውስጥ ቅሬታ ወይም ቂም ካለ፣ በዳራሮ ወቅት ጉማታ ይዞ በመሄድ ይቅርታ ይጠየቃል። ጉማታ የሰውን ልብ ለማለስለስና አዲስ ዓመትን በሰላም ለመጀመር ያገለግላል ተብሎ ስለሚታመን። ጉማታ በቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ ወደ ታላላቆች ቤት ወይም ወደ ማህበረሰቡ አደባባይ የሚወሰድ በመሆኑ፣ የግለሰብን ደስታ ወደ ማህበረሰባዊ ደስታ የሚቀይር ድልድይ ስለመሆኑም ነው ዋና አስተዳዳሪው የጠቆሙት። በአጠቃላይ ጉማታ ከሌለ የዳራሮ በዓል ሙሉ አይሆንም። ጉማታ የጌዴኦን ሕዝብ አንድነት የሚያጸና፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ሀገር በቀል እሴት ነው። ይህም የመደጋገፍ እሴትን ከማጠናከር በተጓዳኝ ህዝቡ የመንግስት ገቢን እንዲሁም በማህበረሰብ ተሳትፎ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆን መሰረት የጣለ ነው ይላሉ። የዘንድሮው ዳራሮ ከቤት በተለይም ከአባ ገዳው መኖሪያ አንስቶ በሶንጎዎችና በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ጭምር እየተከበረ መሆኑን ያነሱት አስተዳዳሪው ጉማታም ዋናው የበዓሉ እሴት ሆኖ እየተከበረ ነው ብለዋል። ባህልና ማንነትን በማስጠበቅና በማዳበር፣ ባህሉ ወደ ወጣቶች እንዲተላለፍ በማበረታታት እንዲሁም የጌዴኦ ባህልን ለሌሎች ህዝቦች ለማስተዋወቅና የማህበረሰብ አንድነትና ባህላዊ እሴትን ለማጠናከር እያገለገለ ያለው የጌዴኦ ዘመን መለወጫ ዳራሮ ጥር 29 እና 30 በዲላ ከተማ ይከበራል። የዳራሮ በዓል የጌዴኦን ሕዝብ የሥራ ባህል፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ዕውቀትና የሰላም እሴት ለዓለም የሚያሳይ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ይህ በዓል በተለይ የጌዴኦ የባህላዊ መልክዓ ምድር (Cultural Landscape) በዩኔስኮ (UNESCO) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ተከትሎ፣ አሁን ላይ ከቤትና ከአደባባይ አልፎ ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እያገኘ ያለ ታላቅ እሴት ሆኗል። የዓመት ሰው ይበለን!!
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት
Jan 14, 2026 443
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት ብርቱዎች ነገን በማሰብ ሁሌም ታትረው ይሰራሉ፤ ይደክማሉ፤ ይጥራሉ…ለቀጣዩ ትውልድም ጥሪት በማስቀመጥ አሻራቸውን ያኖራሉ። አገር የምትገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው። “አባት ያበጀው፤ ለልጅ ይበጀው” እንደሚባለው ልጆች ከአባቶቻቸው ያገኙትን ጥሪት በአዲስ እውቀትና አሰራር ለአገር እድገት በሚበጅ መልኩ አጠናክረው መጠቀማቸው አይቀርም። “ዕድሜ ጸጋ ነው” የሚለው አባባል አንዳንዴ በዕድሜ ብንገፋም ጠንክረን ከሰራን ብዙ ነገር እናያለን ከሚለው ጋር የተያያዘ ነው። በሰቆጣ ከተማም እድሜ ሳይገድባቸው በልማት ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ለዚህ ማሳያ ናቸው። የከተማዋ ነዋሪ የ67 ዓመቱ አቶ ብርሃኑ አወቀ እና የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ዕድሜያቸው ቢገፋም ጠንክሮ ከተሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻልና ዕድሜ ጸጋ ሆኖ ብዙ ለውጥ ማየት እንደሚቻል ማሳያ ናቸው። ግለሰቦቹ ከዕድሜ ብዛት ጉልበቴ ደከመ፣ አይኔ ፈዘዘ፣ እጄም ተሳሰረ…ሳይሉ ጊዜያቸውን በደን፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራ በማሳለፍ ለወጣቶች የልማት አርአያነት ያለው ተግባር እየፈጸሙ ነው። አቶ ብርሃኑ አወቀ በሰቆጣ ከተማ ዳርቻ የሚገኝ አለቱ ያገጠጠና የተራቆተ አካባቢን ከሌላ አካባቢ ለም አፈር በማምጣትና በመደልደል አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ደን በማልማት ውጤታማ ስራ እያከናወኑ ነው። ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከወጣሁ ጀምሮ ጠንክሬ በመስራት የምለወጥበትን ሥራ ማሰብ ስነበረብኝ፤ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ ለዘመናት የቆየን ጭንጫ መሬት ጠርጌና ደልድዬ ማልማት ችያለሁ ይላሉ ወደኋላ መልስ ብለው የተነሱበትን ሁኔታ ሲያስታውሱ። ግማሽ ሄክታር በማይሞላ መሬት ላይ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ዘይቱና፣ ጌሾ፣ ቡና፣ ማንጎና አቮካዶ አልምተዋል። በተጨማሪም ቆስጣ፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመንና ሽንኩርት በማምረት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ጥሪት አፍርተዋል። ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ተግቶ መስራት ከተቻለ ሀብት ማፍራትና ህይወትንም መለወጥ እንደሚቻል የገለጹት አቶ ብርሀኑ፣ ወጣቱም ከእሳቸው የሥራ ትጋት በመማር በአካባቢው ያለውን ፀጋ ለይቶ በማልማት ሊጠቀም ይገባል ሲሉ ይመክራሉ። ሌላው የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ባለፉት 18 ዓመታት በተሰማሩበት የአትክልትና ደን ልማት ሥራ የአካባቢያቸውን ገጽታ ቀይረዋል። የዕድሜ ዘመናቸውን በውትድርናና በመንግስት ሠራተኝነት በማገልገል ሃገራዊ ግዳጃቸውን ሲወጡ ነው የቆዩት። ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከተገለሉ በኋላም ቤት ውስጥ መቀመጥን አልመረጡት። አካፋና ዶማቸውን ይዘው ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ ጌሾ፣ ዘይቱና እና ማንጎ በማልማት ምርቱን ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ሆነዋል። በአካባቢያችን ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ ለይተን ማልማት ከቻልን ድህነትን ማስወገድ የሚከብድ አይሆንም ያሉት አቶ ታደሰ፣ የተራቆተና በጎርፍ የተጎዳን መሬት በማልማት አካባቢውን ሳቢና ማራኪ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት። ወጣቱም ከእሳቸው አርአያነት ያለው ተግባር በመማር በአካባቢው እጁ ላይ ባለ ሀብት ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል በተግባር ማሳየት እንዳለበት መክረዋል። የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ ውሃ አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ ደሳለኝ አዳነ እንደገለጹት፤ በብሔረሰብ አስተዳደሩ 24ሺህ 847 አርሶ አደሮች በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተሰማርተዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል ዕድሜ ሳይገድባቸው ወደ ልማት የገቡ አረጋዊያን እያከናወኑት ያለው የግብርና ልማት ሥራ ለወጣቱ ትልቅ ትምህርት እንደሚሆንም ተናግረዋል። ከእነሱ ልምድ በመውሰድ በዞኑ ወጣቶች፣ ሴቶችና አረጋዊያን በጓሮና ባላቸው መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ይህም በዞኑ የሚስተዋለውን የስርዓተ ምግብ ችግር ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል።