ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተቀላጠፈ የዲጅታል አገልግሎትን ይበልጥ ለማስፋት አቅዶ እየሠራ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተቀላጠፈ የዲጅታል አገልግሎትን ይበልጥ ለማስፋት አቅዶ እየሠራ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተቀላጠፈ የዲጅታል አገልግሎትን ይበልጥ ለማስፋት አቅዶ እየሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጎብኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ በውስጡ 10 ተቋማት ይዞ 73 የሚሆኑ አገልግሎቶችን ለዜጎች በመስጠት ላይ ይገኛል።
አንድ ማዕከሉ ተገልጋዬችን የሚያስተናግዱ 96 ካውንተሮች እንዲኖሩት ተደርጎ የተደራጀ መሆኑንም ገልፀዋል ።
ማዕከሉ ስራ ከጀመረበት ስድስት ወራቶች ውስጥ በአጠቃላይ ከ23 ሺ በላይ ተገልጋዮችን ማስተናገዱንም ተናግረዋል፡፡
ከፍ ብሎ የተጀመረውን የተቀላጠፈ የዲጅታል አገልግሎት ይበልጥ ለማስፋት አቅዶም እየሠራ ነው ብለዋል።