ቀጥታ፡

በክልሉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ልማት ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል

ወላይታ ሶዶ ፤ የካቲት 30 /2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ልማት ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑ ተገለጸ።

በክልሉ ኮንትሮባንድ እና ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን በመከላከል ጤናማ የገበያ ሥርአት ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቷል

የክልሉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አፀደ አይዛ በነገው እለት የሚካሄደውን የኢንቨስትመንት ፎረም አስመልክተው ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በክልሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ ለማቅረብ በመቻሉ በርካታ ባለሃብቶችን ለመሳብ እየተቻለ መሆኑን አብራርተዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት 10 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 226 ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወሰደው ወደ ሥራ ገብተዋል ነው ያሉት።

ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ እየተካሔደ ያለው የድጋፍና የክትትል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ኮሚሽነሯ የገለጹት።

በአሁኑ ወቅትም ለኢንቨስትመንት መሬት ተረክበው ወደልማት ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በተለዩ 81 ፕሮጀክቶች ላይ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን 13 ሺህ 600 ሄክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ ለማስገባት መቻሉን አስታውቀዋል።

በነገው እለት የሚካሔደው የኢንቨስትመንት ፎረም  ከባለሀብቶች ጋር ውይይቶችን በማድረግ በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያግዝ መሆኑን አመልክተዋል።

በመሆኑም ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ በመጠቀም በኢንዱስትሪ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ላይ በመሰማራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም