ቀጥታ፡

በክልሉ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ ነው

ባህር ዳር፤ የካቲት 30 /2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች በመራጭነት፣ በተመራጭነትና በታዛቢነት የሚያደርጉትን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የምርጫ ካርዳችንን ወስደናል - የምርጫ ካርድ የወሰዱ ነዋሪዎች

የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ ብርቱካን ሲሳይ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የክልሉ ሴቶች በምርጫው ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑና የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ የማንቃት ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ሴቶች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅማቸውን የሚያስከብርና ፍላጎታቸውን የሚያሟላ የፖለቲካ ፓርቲን ለይተው እንዲመርጡ ለማስቻል ግንዛቤያቸውን የማሳደግ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።


 

በተመራጭነት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግም ውጤታማና ሞዴል የሆኑ ሴቶች በፈለጉት ፓርቲ ተመልምለው እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውንም አመልክተዋል።

ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሴቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ በቢሮው በኩል ይህንኑ ታሳቢ ያደረጉ የተለያዩ የንቅናቄ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

ዕድሜያቸው ለመምረጥ የደረሱ ሁሉም ሴቶች የምርጫ ካርዳቸውን በመውሰድ የሚፈልጉትን በመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም