ቀጥታ፡

ዛሬ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ ታድመናል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ ዛሬ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ መታደማቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ አስታወቁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንደገለፁት የፍቅር፣ የእዝነትና የበጎነት ወር በሆነው የረመዳን ወር ከተለያዩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ከተቋሙ ሠራተኞች እና ጥሪ ከተደረገላቸው የእምነቱ ተከታዮች በጋራ በመሆን ዛሬ አፍጥረናል ብለዋል።


 

በዚህ የጾም ወቅት በፍቅር አብረን እየኖርን፣ በጋራ ለትውልድ የምትሆን ሀገርን እየገነባን፣ እንደተለመደው የመረዳዳት ባህላችንን እየጠበቅን፣ አብሮ ተካፍሎ በመብላት እና በመተሳሰብ አብረን ማሳለፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።



 
የሁሉም እምነት፣ ባህልና ሥርዓት የሚከበርባት ኢትዮጵያን መገንባት፣ የመደመር መንግሥት ተልዕኮ ነው  ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋሜ ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የረመዳን ጾም ጊዜ እንዲሆን እመኛለሁ! ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም