ቀጥታ፡

ፋሲል ከነማ እና ምድረ ገነት ሽሬ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ፋሲል ከነማ እና ምድረ ገነት ሽሬ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በረከት ግዛው በ56ኛው ደቂቃ ፋሲል ከነማን መሪ ያደረገችው ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ዳንኤል ዳርጌ በ89ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ለምድረ ገነት ሽሬ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።

ፋሲል ከነማ በ34 ነጥብ ደረጃውን ከሰባተኛ ወደ ስድስተኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ምድረ ገነት ሽሬ በ27 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም።


 

በሌላኛው መርሐ-ግብር ባህርዳር ከተማ እና ነገሌ አርሲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ባህርዳር ከተማ በ28 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ነገሌ አርሲ በ38 ነጥብ ከነበረበት ሶስተኛ ደረጃ ወደ ሁለተኛ ከፍ ብሏል።

ነገሌ አርሲ ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ የማድረግ እድል አልተጠቀመበትም።

ኢትዮጵያ መድን ከሀድያ ሆሳዕና በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ  ስታዲየም፣ ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተመሳሳይ ከምሽቱ 12 ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም