ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ለአፍሪካ ሀገራት አቅም የሚሆን ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች ነው
Sep 4, 2026 8
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ለቀጣናው ብሎም ለአፍሪካ ሀገራት አቅም የሚሆን ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች መሆኗን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) ገለጹ። ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆየው የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት፣ የቀጣናውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስትራቴጂ በጋራ ለመቅረጽ ያለመ አውደ ጥናት መካሄድ ጀምሯል። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣን ዕድገት የዓለም ኢኮኖሚን፣ መንግሥታትንና የሰውን አቅም እየቀረጸ ይገኛል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ዘርፍ የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን በማፋጠን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ኃይል መሆኑንም ገልጸዋል። የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራትም የሰው ሰራሽ አስተውሎት የቴክኖሎጂ አማራጭን በአግባቡ በመጠቀም የኢኮኖሚ ውህደትን ማፋጠን እንዳለባቸው ተናግረዋል። ለዚህም የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም እና የመረጃ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ ከአባል ሀገራት ብሔራዊ የሕግ ማዕቀፎች ጋር የተጣጣመ ቀጣናዊ የጋራ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። አፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ተጠቃሚነት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑን አንስተው፤ ዘርፉ በፍጥነት ለውጥ እያስመዘገበ ያለ መሆኑን ተናግረዋል። ስለሆነም ሀገራት ይህ ተግባር የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ብሎም በአፍሪካ ደረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎትና ቴክኖሎጂ የተሻለ እየሰራች መሆኑንም ጠቁመዋል። ኤ አይ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ዘርፉን ለመምራት ኢንስቲትዩት በማቋቋም አበረታች ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅም መሆኑንም አብራርተዋል። የኢጋድ አባል ሀገራቱ የተናበበ ፖሊሲ እንዲኖራቸውና የተሻሉ ተሞክሮዎችን ለማስፋት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በቀጣይ ከቀጣናው የተውጣጡ ወጣቶችን የሚያሰለጥን የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢጋድ ጉዳዮች ዳይሬክተር ከተማ ኃይሌ በበኩላቸው፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የኢኮኖሚ እድገትን የሚያፋጥን ብዝኅ ምርታማነት አቅም መገንቢያ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። በዚህም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለቀጣናዊ ትብብር፣ ለጠንካራ የፖሊሲ ማዕቀፍ ዝግጅት፣ ለዲጂታል መሠረተ ልማት፣ እንዲሁም ለጥናትና ፈጠራ ኢንቨስትመንት መጠቀም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በሀገራዊ እና ቀጣናዊ ልማት ውስጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ሚና በመገንዘብ ከኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲም የኢጋድ አባል ሀገራትን እና አጠቃላይ አፍሪካን የሚጠቅም እንደሚሆን ገልጸዋል።
የሸገር ከተማ አስተዳደር የሕዝቡን ባህል፣ እሴትና ማንነት ለማሳደግ አልሞ እየሰራ ነው
Sep 4, 2026 33
ሸገር ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የሸገር ከተማ አስተዳደር የሕዝቡን ባህል፣ እሴትና ማንነት ለማሳደግ አልሞ እየሰራ እንደሚገኝ የከተማው ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) አስታወቁ። በኦሮሞ ባህል ዘንድ የክረምቱን መውጣትና የፀደይ መባቻን ለማብሰር ከሚከወኑት ባህላዊ ክዋኔዎች መካከል የጎቤና ሽኖዬ ጨዋታ አንዱ ነው። ጎቤ በወጣት ወንዶች የሚከወን፣ ጀግንነትን፣ ፍቅርን፣ ድልን እና የላቀ ተስፋን የሚያንጸባርቅ ባህላዊ ጨዋታ ሲሆን፤ ወጣቶቹ በቡድን ሆነው በድምቀትና በመስመር እርምጃ እየጨፈሩ የዘመኑን መለወጥ የሚያበስሩበት ነው። ሽኖዬ ደግሞ በወጣት ሴቶች የሚከወን፣ የዋህነትን፣ ውበትን፣ ሰላምን እና አዲስ ተስፋን የሚያበስር ውብ ባህላዊ ጨዋታ ሲሆን፤ ልጃገረዶቹ በባህላዊ አልባሳት አጊጠው፣ የሚከውኑት በደስታ እና በፈገግታ የታጀበ የውበት እና የህብረት ጨዋታ ነው። በሸገር ከተማ ደረጃ ላለፉት ሳምንታት ሲከወን የቆየው የጎቤና ሺኖዬ ጨዋታ የማጠናቀቂያ መርሃ ግብሩ በፌስቲቫል ትርኢት የሸገር ከተማ ክፍለ ከተሞች ወጣቶችን በማሳተፍ ዛሬ በሰበታ ክፍለ ከተማ ተካሄዷል። በመርሃ ግብሩ የተገኙት የከተማው ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)፤ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የኦሮሞን ባህል፣ እሴትና ማንነት ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ለኢኮኖሚ እድገትና ለአንድነት መጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል። ባለፉት ሶስት ዓመታት በከተማው በተከናወኑት ተግባራት የባህል ህዳሴን በማጠናከር ለቱሪዝም ምቹ ሁኔታን መፍጠር የተቻለ ሲሆን፣ በዚህም የሕዝቡን ባህል ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር ተችሏል ብለዋል። ወጣቶች በዚህ ፕሮግራም የሕዝቡን ባህልና ማንነት ለማሳየት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲሁም በኦሮሚያ ደረጃ የሚካሄደውን ትርኢት ስኬታማ ለማድረግ መስራት እንዳለባቸው ከንቲባው አሳስበዋል። የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ጉዮ ገልገሎ በበኩላቸው፤ ሸገር ከተማ የኦሮሞ ሕዝብ ባህል፣ እሴት፣ ማንነት ማሳያ ከተማ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ ጨዋታ ዘንድሮ አገራዊ ድሎች በተመዘገቡበት ወቅት መካሄዱ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል። በከተማው የኦሮሞን ሕዝብ ባህል፣ እሴትና ማንነት የበለጠ በማሳደግና በማስተዋወቅ ለቱሪዝም መስህብነት ለማሳደግ እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ጉዮ ገልጸዋል።
የሕብረተሰብን ጤና መጠበቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግና መሠረት ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Sep 4, 2026 35
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- የሕብረተሰብን ጤና መጠበቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግና መሠረት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ የሕብረተሰብ ጤና ድምር ውጤቱ በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ ውጤታማ ተግባር የሚከውን እና ለሀገሩ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚተጋ አምራች ሕብረተሰብ መገንባት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያን ላለፉት 100 ዓመታት ያገለገለውን፣ ታሪካዊ ወረት እና ዘመናዊ አቅምን ያጣመረውን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን የሥራ እንቅስቃሴ ዛሬ መመልከታቸውን ገልጸዋል። የሕብረተሰብን ጤና መጠበቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግና መሠረት ነው። ተቋሙም በወረርሽኝ ልየታ፣ በበሽታ ክትትልና ምላሽ፣ በላብራቶሪ፣ በምርምር፣ በዲጂታላይዜሽን እና በጤና ስጋት ዝግጁነት የሀገሪቱን የጤና ሥርዓት በጥንካሬ እየደገፈ ይገኛል ነው ያሉት። በክልሎች የድንገተኛ ሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከላትን ማቋቋሙና የሪፈራል ላብራቶሪዎችን ማስፋፋቱ የሀገሪቱን የጤና ዝግጁነት አቅም እያጠናከረ ያለ ወሳኝ ተግባር ነው ብለዋል። በቀጣይም የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና የልህቀት ማዕከል ለመሆን በከፍተኛ ትጋት እየሠራ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም የጤና ድርጅት የትብብር ማዕከል በመሆን ዓለም አቀፍ ሚናውን ለማጠናከር ብርቱ ጥረት እያደረገ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት የትላንትን ታሪክ ጠብቆ፣ ዛሬን በዘመናዊነት ዋጅቶ፣ ወደ ነገ የሚገሰግስ እንደዚህ ያለ ተቋምን መደገፍና ማጠናከር ለነገ የማንለው ተግባር ነው። ኢንስቲትዩቱ የሀገርን ብልፅግና ለማፋጠን ወሳኝ አቅም በመሆኑ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሥራን በእውቀትና በቴክኖሎጂ ታግዞ ለማከናወን አስችሎናል-ሰልጣኞች
Sep 4, 2026 48
ቦንጋ፣ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሥራቸውን በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ታግዘው ለማከናወን እንዳገዛቸው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግስት ሠራተኞች ገለፁ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቪ የሆነው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና ፕሮግራም የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር በማፋጠን ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል። በፕሮግራሙም በዋናነት በሶፍትዌር ልማት፣ በዳታ ትንተና፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ክህሎት እና መሰል የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በማተኮር ለዜጎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። ስልጠናውን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው በቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ የፊዚክስ መምህር ሲሳይ አብደላ፣ መንግስት ባመቻቸው የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በአራቱም ፕሮግራሞች ሰልጥናቸውን አጠናቀው የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ተናግረዋል። ይህም ሥራቸውን በቴክኖሎጂ አስደግፈው ለማከናወን ከማገዝ ባለፈ በኦንላይን የራሳቸውን ሥራ ለመስራት ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ጠቁመዋል። ሌላው የስልጠና ዕድሉ ተጠቃሚ የመንግስት ሠራተኛ ወጣት ጌጥዬ አለሙ በበኩሉ በነጻ በተሰጠው የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መሠረታዊ የዲጂታል እውቀቱን ማሳደጉ በስራው ተወዳዳሪ ለመሆን እንዳስቻለው ተናግሯል። በሶፍት ዌር ልማት፣ በዳታ ትንተና፣ በሞባይል አፕሊኬሽን ግንባታ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ሰልጥኖ ምስክር ወረቀት ማግኘቱ ሥራውን በተሻለ ጥራት ለማከናወን አስችሎታል። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ዜጎች በተለይ ወጣቶች ከቴክኖሎጂ ጋር እንዲተዋወቁና ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ትልቅ እገዛ እያደረገ ነው ያሉት ደግሞ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሒሳብ መምህር ሙሉጌታ አንዷለም ናቸው። በተለይ መምህራን ሥራቸውን ወቅቱ በደረሰበት የቴክኖሎጂ አውቀት ታግዘው እንዲያከናውኑ ያግዛቸዋል ብለዋል። በቀጣይ በዳታ ሳይንስ እና በአርቴፌሻል ኢንተለጀንስ ላይ ስፔሻላይዝ ለማድረግ ፍላጎት እንዳደረባቸውም ጠቁሟል ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ምክትል ሀላፊና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ አሰፋው ኢንሼቲቩ ዲጅታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማፋጠን ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። እንደሀገር የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢንሼቲቪ በቴክኖሎጂ የበቃ ተወዳዳሪ ዜጋ መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ስልጠናውን ለመውሰድ በክልሉ ከተመዘገቡት ውስጥ እስካሁን ድረስ ከ48 ሺህ በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው የምስክር ወረቀት ወስደዋል ብለዋል።
የህዳሴ ግድብን ያሳካው ትውልድ የባህር በር ጥያቄንም ማሳካቱ የማይቀር ነው
Sep 4, 2026 96
ሰቆጣ፤ ነሃሴ 29/2018(ኢዜአ) ፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በመገንባት ታሪክ የሰራው ትውልድ የባህር በር ባለቤትነትን ማሳካቱ የማይቀር ነው ሲሉ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ገለጹ። ኢትዮጵያዊያን በራሳቸው የፋይናንስ አቅምና ጉልበት ለዓመታት በጽናት የገነቡት የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ኃይል እያመነጨ፣ ዓሳ እየተመረተበት እና የአካባቢውን መልካዐ ምድር አስውቦ የቱሪስት መስህብ ጭምር ሆኗል። የዚህ ታሪካዊ ስኬት ባለቤት የሆነው የአሁኑ ትውልድ በሁሉም ረገድ የኢትዮጵያን ስኬት፣ ክብርና ልእልና ለማስጠበቅ በትጋት መስራቱን ቀጥሏል። በቅርበትም፣ በመልክዐ ምድርም ይሁን በታሪክ በቀይ ባህር ላይ የባህር በር ባለቤትነቷን እውን ማድረግ የትውልዱ ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ሻለቃ ባሻ ሞገስ የማነ ብርሃን፤ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትርቅ የተደረገበት ሴራ ስንቆጭበት የኖርንበት ጉዳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የወደቦች ባለቤት እንደነበረችና ገቢና ወጪ ምርቶችን በቀላሉ ታንቀሳቅስ እንደነበር በማስታወስ ለምን እንዳጣነው እስካሁንም ግልጽ አይደለም ብለዋል። የባህር በር ባለቤትና የባህር ሃይል የነበራት ኢትዮጵያ ለምን እንዳጣች ማንም የማያውቀውና ጉዳዩ እንዳይነሳ ተጽእኖ ይደረግ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ ግን የትውልድ ጥያቄ ሆኖ በመምጣቱ ኮርተናል ብለዋል። በመሆኑም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በመገንባት ታሪክ የሰራው ትውልድ የባህር በር ባለቤትነትን ማሳካቱ የማይቀር መሆኑን እርግጠኛ ነኝ ሲሉም ተናግረዋል። ሌላኛው የቀድሞ ሰራዊት አባል መቶ አለቃ አበባው ገብረእግዚአብሔር፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት በብዙ መልኩ እስካሁንም የተሻገረ ችግር የፈጠረባት መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም የሀገር ህልውና ጉዳይ እና የትውልዱ ጥያቄ ሆኖ መነሳቱና የባህር በር ባለቤትነት የግድ መሆኑ የሁላችንም ጽኑ አቋም ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያን ከአባይና ከቀይ ባህር ነጥሎ ማየት የማይታሰብ መሆኑን የገለጹት መቶ አለቃ አበባው፤ የባህር በር ባለቤትነታችን የማይቀር በመሆኑ ለዚህም በትብብርና በአብሮነት ለሀገራችን መስራታችን ይቀጥላል ብለዋል።
ፖለቲካ

በደብረ ብርሃን ከተማ ሰላምን አፅንቶ በማዝለቅ የልማት ስራው እንዲፋጠን የድርሻችንን እንወጣለን-ነጋዴዎች
Sep 4, 2026 53
ደብረ ብርሃን፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- በደብረ ብርሃን ከተማ የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት አጠናክሮ በማስቀጠል የተጀመሩ የልማት ተግባራት ተጠናከረው እንዲቀጥሉ የድርሻቸውን እንደሚወጡ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ። የአስተዳደሩ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ በወቅታዊ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ በከተማዋ ከሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር ዛሬ ውይይት አካሂዷል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ተስፋዬ እሸቴ እንደገለጹት፤ በከተማዋ እየተረጋገጠ የመጣውን ሰላም አፅንቶ ለማዝለቅ የሁሉንም ህብረተሰብ ርብርብ ይጠይቃል። በከተማዋ አሁን የተገኝው ሰላም ዘላቂ እንዲሆንና የልማት ጥያቄዎቻቸው ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ የድርሻቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል። ሌላዋ የመድረኩ ተሳታፊ ወይዘሮ ሰርካለም ተሾመ፤ የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥና ወንጀልን በጋራ ለመከላከል ከሚመለከተው አካል ጋር በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም አጥፊዎችን ተከታትሎ ለህግ አስከባሪ አካላት አጋልጦ በመስጠት ወንጀልን በጋራ ለመከላከል የተጀመረውን ስራ ከማገዝ አንፃር የበኩላቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል። በህብረተሰብ ተሳትፎ የብሎክ አደረጃጀትን መሰረት አድርጎ ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል በተጀመረው አሰራር ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላው የመድረኩ ተሳታፊ አቶ አውላቸው ለገሰ ናቸው። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ በበኩላቸው፤ የከተማዋን ሰላምና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የንግዱ ማህበረሰብ ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። ህዝቡ የሚያነሳውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በተገቢው መንገድ ለመመለስ በከተማዋ የመሰረተ ልማት፣ የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ልማቱን ለማፋጠን የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የፀጥታ ኃይሉ ወንጀልን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ የድርሻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። የከተማዋን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡና የፀጥታ ሀይሉ ተቀናጅተው ወንጀልን እየተከላከሉ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ገብረመስቀል ቦጋለ ናቸው። ከዚህ ውስጥም የንግዱ ማህበረሰብ በሆቴሎች አልጋ የሚይዙ እንግዶችን በአግባቡ በመመዝገብ ለፀጥታ ኃይሉ በማሳወቅ የጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። በተካሄደው የውይይት መድረክ ከከተማዋ የተውጣጡ የአገልግሎት ሰጪና የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ተሳትፈዋል።
የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ህዝብን መካስ ጀግንነትና የሀገር ወዳድነት መገለጫ ነው
Sep 4, 2026 184
መተማ፤ ነሐሴ29/2018(ኢዜአ) ፦ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ህዝብን መካስ ጀግንነትና የሀገር ወዳድነት መገለጫ ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ። በተለያዩ አካባቢዎች አሁንም በጫካ የሚገኙ የታጠቁ አካላት ለመንግስት የሰላም ጥሪ ፈጣን ምላሽ በመስጠት እድሉን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ መክረዋል። በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ትጥቅ ይዘው በየጫካው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ትጥቃቸውን በመፍታት ማህበረሰቡን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል። በተሳሳተ መንገድ በትጥቅ እንቅስቃሴ የነበሩ በርካታ ወጣቶች እውነታውን በመረዳት በህዝብ ላይ እገታና ዘረፋ አንፈፅምም በማለት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው እየመጡም ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የመንግስትን የሰላምን ጥሪ በመቀበል ከጥፋት መንገድ እየወጡ ያሉ ታጣቂዎች አርአያነት ያለው ተግባር እየፈፀሙ መሆኑን ገልጸው ሌሎችም ይህንኑ መልካም መንገድ እንዲከተሉ መክረዋል። የመንግሥትን የሰላም ጥረትና ቁርጠኝነት በማድነቅ የታጠቁ አካላት ይህንን መልካም እድል በመጠቀም ትጥቃቸውን በመፍታት ለሰላምና ልማት መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል። በምእራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ የሚኖሩት የኃይማኖት አባት ሊቀ ህሩያን እያሱ ገዳሙ እና መጋቤ ብርሃን ዘላለም አዲሱ፤ የመንግስት ሆደ ሰፊነትና ለሰላም የሚያደርገውን ተደጋጋሚ ጥረት አድንቀዋል። በዚህም መሰረት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከጥፋት መንገድ እየወጡ ያሉ ታጣቂዎች አርአያነት ያለው ተግባር እየፈፀሙ መሆኑን አንስተው ሌሎችም ይህንኑ ፈለግ እንዲከተሉ መክረዋል። በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች ተጨማሪ ህይወት ሳይጠፋና ንብረት ሳይወድም የተሰጠውን የሰላም እድል በመጠቀም ለህዝባቸው እፎይታን መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የሀገር ሽማግሌው አቶ ደርቤ ጫኔ፤ ለሰላም የሚደረግ ጥረት ጀግንነትና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው ለመንግስት ተደጋጋሚ የሰላም ጥረትና ሰላምን መርጠው እየመጡ ላሉ ታጣቂዎች አመስግነዋል። በመሆኑ በጫካ የቀሩ ታጣቂዎች የህዝቡን ፍላጎትና የመንግሥትን የሰላም ጥረት ትርጉም በመስጠት ከጥፋት ወጥተው ሰላምን መርጠው ህዝቡን እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል። በመሆኑም ይቅር ባይነትን በማስቀደም ወደ ሰላም መንገድ መመለስ እና ይህንን እድል መጠቀም ለህዝብና ለሀገር በማሰብ የሚፈፀም በመሆኑ የሰላም ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
Sep 3, 2026 371
ባህር ዳር ነሐሴ 28/2018;(ኢዜአ) ፦ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም በርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ። ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር የፍትህ ሙዚየም መገንባቱ የህዝቡን የፍትህ እሴትና በህግ የበላይነት ከማሳየት ባሻገር ተቋማት ለለውጥ ያላቸውን መነሳሳት የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል። በሀገሪቱ የፍትህ አስተዳደር ታሪክ ለጥናትና ምርምር የሚሆኑ ሰነዶችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን የያዘ በመሆኑም ለአዲሱ ትውልድ እሴትና ተደማሪ የእውቀት ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ይሆናል ብለዋል። በመሆኑም ይሄንን ታሪካዊ አሻራ ላስቀመጡና መረጃዎችን በማሰባሰብ ለምረቃ እንዲበቃ ላደረጉ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር)፤ የሙዚየሙ መገንባት በተለይም ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ትልቅ እሴት የሚሆን ነው ብለዋል። በካታሎግና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘውን የአገራችን የፍትህ ታሪክ ተማሪዎች በቀላሉ እንዲያውቁና ለምርምር ግባአት እንዲጠቀሙበት የሚያስችል መሆኑንም አንስተዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አለምአንተ አግደው፤ ሙዚየሙ ከባህላዊ እስከ ዘመናዊ አስተዳደር የነበሩ የፍትህ ታሪኮችን ሰንዶ በመያዝ የተደራጀ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ለህግ ማሻሻያ፣ ለፖሊሲና ስትራቴጂ ቀረጻና ለሌሎችም የጥናትና ምርምር ስራዎች ትልቅ አቅምና ግብአት ይሆናል ብለዋል። በሙዚየሙ ውስጥ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩና ሌላ ቦታ በቀላሉ ሊገኙ የማይችሉ ብርቅዬ የፍትህ ሰነዶች የሚገኙበት ነው ብለዋል። እነዚህን ታሪካዊ መረጃዎች ከተለያዩ ቦታዎች ለማሰባሰብ ክልል አቀፍ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሰፊ ስራ መሰራቱን አንስተው አጠቃላይ የሙዚየሙ ግንባታ አላማ የህዝቡን የፍትህ ስርዓት ታሪክ በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ መሆኑን ተናግረዋል። በፍትሕ ሙዚየም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ፅምዶ የጋራ ዓላማ የሌለውና የትም የማይደርስ ስብስብ ነው-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
Sep 3, 2026 418
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ፅምዶ የጋራ ዓላማ የሌለውና የትም የማይደርስ ስብስብ መሆኑን አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ በረጅም ታሪኳ በውስጥ ችግሮችም ሆነ በውጭ ጣልቃ ገብነቶች የተዳከመች ብትመስልም በጽናትና በአሸናፊነት ያለፈች ሀገር መሆኗን አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የማሳካት ጉዞዋ በየትኛውም የጥፋት ጥምረት ሊከሽፍ የማይችል ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ፅምዶ በሚል የጋራ ዓላማ በሌለው ተራ የጥፋት ኃይሎች ስብስብም ሆነ ለሌሎች ትላልቅ ኃይሎች ጫና የምትበገር ጠንካራ ሀገር አለመሆኗን ገልጸው፤ ይህ በታሪኳም ሆነ በአሁናዊ ጉዞዋ የታየ ተጨባጭ ሀቅ ነው ብለዋል። አሁን ፅምዶ በሚል የጥፋት ጥምረት የተሳሰቡት ኃይሎችም የጋራ ዓላማ የሌላቸውና አጭር ርቀት እንኳ አብረው መጓዝ የማይችሉና እርስ በርስ የሚጋጭ አጀንዳን ያነገቡ ተራ ስብስብ ናቸው ብለዋል። እነዚህ ኃይሎች ወጣቶችን በማስገደድ ለእልቂት እየዳረጉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ቆመንልሃል የሚሉትን ህዝብ ለመከራ መዳረጋቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያን ከጉዞዋ የሚያቆማት ኃይል የለም ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤እነዚህ ትናንሽና አቅመ ቢስ ቡድኖች የጀመሩት የጥፋት መንገድም የትም እንደማያደርሳቸው ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያን በውሃ ሃብቷ የመልማት መብት ግብጽ ልታከብር ይገባል - ቲቦር ናዥ
Sep 3, 2026 490
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያን በውሃ ሃብቷ የመልማት መብት ግብጽ ልታከብር ይገባል ሲሉ የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ገለጹ። ከቀይ ባህር ጋር ታሪካዊ ቁርኝት ያላት ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ ተገቢና ህጋዊ መሰረት ያለው መሆኑንም አመልክተዋል። ቲቦር ናዥ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ግብጽ በአባይ ተፋሰስ ላይ ምንም አይነት የውሃ ድርሻ ሳይኖራት ለዘመናት ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ስትጠቀም መቆየቷን አውስተዋል። ግብጽ የዓባይ ወንዝ ላይ ሙሉ ቁጥጥር ሊኖረኝ ይገባል በሚል የምትከተለው አካሄድ ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ ካለው የቀጣናው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ ጋር ፈጽሞ የማይጣጣም መሆኑንም ገልጸዋል። ግብፅ አዲሱን እውነታ መቀበል አለባት ያሉት የቀድሞው ዲፕሎማት፤ የኢትዮጵያን ፈጣን ዕድገትና በቀጣናው እየተቀየረ ያለውን የኃይል ሚዛንም አንስተዋል። የቀጣናው ፖለቲካዊ ገጽታ ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን የገለጹት ቲቦር ናዥ፣ ግብፅ በአሁኑ ሰዓት አዲስ የኃይል ሚዛን መፈጠሩንና ኢትዮጵያም እጅጉን ማደጓን ልትገነዘብ እንደሚገባ አስምረውበታል። ግብፅ የድርድር አቀራረቧን ዳግም በመመርመርና አዲስ እና አዎንታዊ አመለካከት ይዛ ወደ ንግግር ጠረጴዛው ከተመለሰች ዘላቂና ፍትሃዊ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚቻልም ነው ያነሱት። የሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሀብቶችን የመጠቀም መብት እውቅና መስጠት ላይ የተመሰረቱ ውይይቶች የጋራ መግባባት ሊፈጥሩ እንደሚችሉም ተናግረዋል። ቲቦር ናዥ የኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሃብት መጠቀም ራስ ወዳድነት ወይም በግብፅ ላይ የህልውና አደጋ ተደርጎ መታየት የለበትም ሲሉ አስገንዝበዋል። አገራት የራሳቸውን የተፈጥሮ ሃብት ይጠቀማሉ። ሁሉንም ነገር በእውነታው ላይ ቆመን እንመልከት ብለዋል። ቲቦር ናዥ አያይዘውም፤ ግብፅ ስለ ዓባይ ከምታነሳው አቋም በተቃራኒው፣ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር እንዳትደርስ የያዘቸውን አቋም ምክንያታዊነት የጎደለው መሆኑን አንስተዋል። ግብፅ የቀይ ባህር ዳርቻ ሀገራት ብቻ የባህር አስተዳደር ጉዳይ ይመለከታቸዋል የምትል ከሆነ፣ በአባይ ተፋሰስ መጠቀም ያለባቸው የውሃ ድርሻ ያላቸው ሀገራት ብቻ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። ከእውነታ ጋር የማይጣጣመውን ይህን የግብጽን አቋም የግብዝነት ድርጊት ሲሉ ተችተውታል። የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዠ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በተመለከተም ሀሳባቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የነበራትን የባህር ላይ ታሪክ በማስታወስ፣ ሀገሪቱ በወቅቱ የራሷ የባህር ኃይል (ኔቪ)፣ የባህር ኃይል ማዕከል እና በባህር ኃይል ውስጥ ያገለግሉ የነበሩ የኢትዮጵያ አድሚራሎች እንደነበሯትም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት እጅግ አሳዛኝ ክስተት እንደሆነ ጠቅሰው፣ ሀገሪቱ አሁን የምታደርገውን የባህር በር የማግኘት ጥረት ለቀይ ባህር ካላት ታሪካዊ ግንኙነት ጋር አያይዘውታል። የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ፍትሃዊና ሕጋዊ ጥያቄ መሆኑን የገለጹት ቲቦር ናዥ፣ የጎረቤት ሀገራት የኢትዮጵያን ፍላጎቶች በሚገባ መረዳት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን ለቀጣናው ኢኮኖሚያዊ እድገትና ዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው
Sep 3, 2026 426
ቦንጋ፤ ነሐሴ28/2018(ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ሀገራት የኢኮኖሚ እድገትና ደህንነት መረጋገጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ኢዜአ ያነጋገራቸው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ። የጥንታዊ ስልጣኔ መነሻና በአንድ ወቅት ስሟም ከሀያላን ሀገራት ተርታ የነበረችው ኢትዮጵያ በቀይ ባህር አካባቢ የነበራት ተሰሚነትና የወደብ ባለቤትነት ለገናናነቷ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ይሁን እንጂ በታሪክ አጋጣሚ የቀይ ባህር ባለቤት ከነበረችበት ከተነጠለች ጀምሮ የራሷ የባህር በር በማጣቷ ለበርካታ ችግሮች ተዳርጋ ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ያለቸው ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ቢኖራትም ወደብ አልባ መሆኗ በእድገቷና በኢኮኖሚዋ ላይ ተጽዕኖ አሳድሮባታል። ይህን ታሪክ በመቀየር ኢትዮጵያን በቀጣናው ሀገራት ወደነበረችበት ከፍታ ለመመለስ የባህር በር ባለቤትነትን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር ዘሪሁን ያሬድ፣ የባህር በር ባለቤትነት ለኢትዮጵያ ቅንጦት ሳይሆን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የደህንነት ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። የባህር በር ባለቤትነት ኢትዮጵያ በቀጣናውና በአሁጉሩ ያላትን ስትራቴጂካዊ ተሰሚነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚያሳድግ ነው። የአካባቢውን ሀገራት የህዝብ ለሕዝብ ትስስር በማጠናከር ቀጣናዊ ውሕደትን ለመፍጠር፣ ሰላምን ለማጽናትና የጋራ እድገትን ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል። የባህር በር መኖር ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት ለሀገር ልማት እንድታውል ያደርጋል ያሉት መምህሩ፣ የወጪና ገቢ ምርቶችን በቀላሉ በማሳለጥ የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነቷንም እንደሚያሳድግ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ለመሆን በዲፕሎማሲዊ መንገድ የጀመረችው ጥያቄ መልካዓ ምድራዊና ሕጋዊ መሠረት ያለው በመሆኑ የዜጎችን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑንም መምህሩ ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ሰለሞን ማሞ በበኩላቸው፣ ቀይ ባህር ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በዲፕሎማሲዊ መስክ ትልቅ ቁርኝት የነበረውና የሕልውናዋ መሠረት መሆኑንም ገልፀዋል። በወቅቱ ኢትዮጵያን በዓለም የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ዘርፎች ተፅዕኖ ፈጣሪ ከነበሩ አራት ሀገራት መካከል አንዷ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል፡፡ የባህር በር ማጣት በተዘጋ ቤት ውስጥ እንደመኖር መሆኑን የጠቀሱት መምህሩ፣ መልሶ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የሚደረገው ጥረት የመላው ኢትዮጵያውያን ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን በጋራ ተደጋግፎ ለማደግ ካለው ፋይዳ ባለፈ ለቀጣናው ሰላም መከበር ትልቅ ዋጋ እንዳለውና የኢትዮጵያም ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሳድግ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በሕገ-ወጡ ሕወሓት ቡድን የሚደርስብንን ግፍ ለማስቆም የጀመርነውን ትግል እናጠናክራለን - የትግራይ ክልል ተወላጆች
Sep 3, 2026 599
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ በትግራይ ክልል ሕገ-ወጡ ሕወሓት እያደረሰ ያለውን ግፍና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ለማስቆም በቡድኑ ላይ የጀመርነውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የክልሉ ተወላጆች ገለጹ። በአሁኑ ወቅት ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የክልሉን ወጣቶች ለሌላ አሳልፎ መሸጥን ጨምሮ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ በማካሄድ ከፍተኛ ግፍና መከራ እያደረሰ ይገኛል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የክልሉ ተወላጆች መካከል አቶ ኹሉፍ አጽአሊ እንደገለጹት፣ በትግራይ ክልል ወጣቶች ወደ ማይፈልጉት ጦርነት እንዲገቡ እየተገደዱ ነው። ወጣቶች ይህንን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በመሸሽ ከትውልድ ቀያቸው በመውጣት ወደ ባሕርና በረሃ እየገቡ መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም እኛ አንድነታችንን በማጠናከር ሕገ ወጡ ሕወሓት እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ማስቆም አለብን ሲሉ ተናግረዋል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ለምለም ሳሙኤል በበኩላቸው፤ በሕገ ወጡ ቡድን ምክንያት የትግራይ ክልል እናቶች በለቅሶና መከራ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ በጣም ኢ-ሰብአዊ መሆኑን በመግለጽ ሕገ ወጡን ቡድን ለማስወገድ የተጀመረውን ትግል ማጠናከር አለብን ያሉት ደግሞ ሌላኛው የክልሉ ተወላጅ ተካ ገብሩ ናቸው። ሰውን ያለፍላጎቱ ለጦርነት እንዲሰማራ ማድረግ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተካ፣ ኢትዮጵያውያን የሚታወቁበት የሰብዓዊነት እሴት በክልሉ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።

ማህበራዊ
የሸገር ከተማ አስተዳደር የሕዝቡን ባህል፣ እሴትና ማንነት ለማሳደግ አልሞ እየሰራ ነው
Sep 4, 2026 33
ሸገር ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የሸገር ከተማ አስተዳደር የሕዝቡን ባህል፣ እሴትና ማንነት ለማሳደግ አልሞ እየሰራ እንደሚገኝ የከተማው ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) አስታወቁ። በኦሮሞ ባህል ዘንድ የክረምቱን መውጣትና የፀደይ መባቻን ለማብሰር ከሚከወኑት ባህላዊ ክዋኔዎች መካከል የጎቤና ሽኖዬ ጨዋታ አንዱ ነው። ጎቤ በወጣት ወንዶች የሚከወን፣ ጀግንነትን፣ ፍቅርን፣ ድልን እና የላቀ ተስፋን የሚያንጸባርቅ ባህላዊ ጨዋታ ሲሆን፤ ወጣቶቹ በቡድን ሆነው በድምቀትና በመስመር እርምጃ እየጨፈሩ የዘመኑን መለወጥ የሚያበስሩበት ነው። ሽኖዬ ደግሞ በወጣት ሴቶች የሚከወን፣ የዋህነትን፣ ውበትን፣ ሰላምን እና አዲስ ተስፋን የሚያበስር ውብ ባህላዊ ጨዋታ ሲሆን፤ ልጃገረዶቹ በባህላዊ አልባሳት አጊጠው፣ የሚከውኑት በደስታ እና በፈገግታ የታጀበ የውበት እና የህብረት ጨዋታ ነው። በሸገር ከተማ ደረጃ ላለፉት ሳምንታት ሲከወን የቆየው የጎቤና ሺኖዬ ጨዋታ የማጠናቀቂያ መርሃ ግብሩ በፌስቲቫል ትርኢት የሸገር ከተማ ክፍለ ከተሞች ወጣቶችን በማሳተፍ ዛሬ በሰበታ ክፍለ ከተማ ተካሄዷል። በመርሃ ግብሩ የተገኙት የከተማው ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)፤ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የኦሮሞን ባህል፣ እሴትና ማንነት ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ለኢኮኖሚ እድገትና ለአንድነት መጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል። ባለፉት ሶስት ዓመታት በከተማው በተከናወኑት ተግባራት የባህል ህዳሴን በማጠናከር ለቱሪዝም ምቹ ሁኔታን መፍጠር የተቻለ ሲሆን፣ በዚህም የሕዝቡን ባህል ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር ተችሏል ብለዋል። ወጣቶች በዚህ ፕሮግራም የሕዝቡን ባህልና ማንነት ለማሳየት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲሁም በኦሮሚያ ደረጃ የሚካሄደውን ትርኢት ስኬታማ ለማድረግ መስራት እንዳለባቸው ከንቲባው አሳስበዋል። የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ጉዮ ገልገሎ በበኩላቸው፤ ሸገር ከተማ የኦሮሞ ሕዝብ ባህል፣ እሴት፣ ማንነት ማሳያ ከተማ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ ጨዋታ ዘንድሮ አገራዊ ድሎች በተመዘገቡበት ወቅት መካሄዱ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረዋል። በከተማው የኦሮሞን ሕዝብ ባህል፣ እሴትና ማንነት የበለጠ በማሳደግና በማስተዋወቅ ለቱሪዝም መስህብነት ለማሳደግ እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ጉዮ ገልጸዋል።
የሕብረተሰብን ጤና መጠበቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግና መሠረት ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Sep 4, 2026 35
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- የሕብረተሰብን ጤና መጠበቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግና መሠረት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ የሕብረተሰብ ጤና ድምር ውጤቱ በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ ውጤታማ ተግባር የሚከውን እና ለሀገሩ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚተጋ አምራች ሕብረተሰብ መገንባት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያን ላለፉት 100 ዓመታት ያገለገለውን፣ ታሪካዊ ወረት እና ዘመናዊ አቅምን ያጣመረውን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን የሥራ እንቅስቃሴ ዛሬ መመልከታቸውን ገልጸዋል። የሕብረተሰብን ጤና መጠበቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግና መሠረት ነው። ተቋሙም በወረርሽኝ ልየታ፣ በበሽታ ክትትልና ምላሽ፣ በላብራቶሪ፣ በምርምር፣ በዲጂታላይዜሽን እና በጤና ስጋት ዝግጁነት የሀገሪቱን የጤና ሥርዓት በጥንካሬ እየደገፈ ይገኛል ነው ያሉት። በክልሎች የድንገተኛ ሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከላትን ማቋቋሙና የሪፈራል ላብራቶሪዎችን ማስፋፋቱ የሀገሪቱን የጤና ዝግጁነት አቅም እያጠናከረ ያለ ወሳኝ ተግባር ነው ብለዋል። በቀጣይም የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና የልህቀት ማዕከል ለመሆን በከፍተኛ ትጋት እየሠራ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም የጤና ድርጅት የትብብር ማዕከል በመሆን ዓለም አቀፍ ሚናውን ለማጠናከር ብርቱ ጥረት እያደረገ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት የትላንትን ታሪክ ጠብቆ፣ ዛሬን በዘመናዊነት ዋጅቶ፣ ወደ ነገ የሚገሰግስ እንደዚህ ያለ ተቋምን መደገፍና ማጠናከር ለነገ የማንለው ተግባር ነው። ኢንስቲትዩቱ የሀገርን ብልፅግና ለማፋጠን ወሳኝ አቅም በመሆኑ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
በብሄረሰብ አስተዳደሩ የወባ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል የፀረ ወባ ኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ነው
Sep 4, 2026 46
ሰቆጣ፤ ነሃሴ 29/2018(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የወባ በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችል የፀረ ወባ ኬሚካል ርጭት እየተካሄደ እንደሚገኝ የአስተዳደሩ ጤና መምሪያ ገለፀ። በመምሪያው የወባና ሌሎች በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሞያ አቶ አበበ በለጠ ለኢዜአ እንዳሉት በብሄረሰብ አስተዳደሩ የወባ በሽታን ለመከላከል የተጠናከረ ስራ እየተከናወነ ነው። በተያዘው በጀት ዓመትም 125 ሺህ በላይ የመኝታ አጎበር ለህብረተሰቡ ከመሰራጨቱ በተጨማሪ በ38 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ላይም ፀረ ወባ የኬሚካል ርጭት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። የኬሚካል ርጭቱ የወባ በሽታ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ በሚስተዋልባቸው በሰሃላ፣ ሰየምትና አበርገሌ ወረዳዎች መሆኑን አስረድተዋል። ከከሚካል ርጭት በተጨማሪ ለትንኝ መራቢያ ምቹ የሆኑ ያቆረ ውሀን የማፋሰስ፣ የማደፈንና አካባቢውን ንፁህ የማድረግ ስራ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ እንዲቻል ህብረተሰቡን ያሳተፉ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል። በሰሃላ ወረዳ የመሸሀ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ የሺዓለም ሙላቴ እንዳሉት በክረምቱ በአካባቢያቸው ባጋጠመ የዝናብ መቆራረጥ የወባ ትንኝ እንዲራባ ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ ስጋት አድሮባቸው እንደነበር ገልፀዋል። አሁን ላይ በሚኖሩበት ቀበሌ የተካሄደው የቤት ለቤት የፀረ ትንኝ ኬሚካል ርጭት ስጋታቸውን በማስወገድ እፎይታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። ወባን ለመከላከል ለመራቢያ ምቹ የሆኑና ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማጽዳት፣ የማፋሰስና የማዳፈን ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ወይዘሮ አለም ፀሃይ ሽሙ ናቸው።
በሀረሪ ክልል የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የመደጋገፍ እሴት በማጎልበት የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየቀየረ ይገኛል - አቶ ጌቱ ዋዬሳ
Sep 4, 2026 62
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- በሐረሪ ክልል በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የመደጋገፍ እሴትን በማጎልበት የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየቀየረ ይገኛል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ዋዬሳ ገለጹ። በሀረሪ ክልል በክረምት በጎ ፍቃድ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። በመድረኩ ላይ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንደገለፁት ፣ በክልሉ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአብሮነትና መደጋገፍ እሴትን በማጎልበት የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየቀየረ ይገኛል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተደመረ አቅም ዜጎችን በማገዝና ሃብትን አቀናጅቶ በመምራት ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል። በተለይም በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ አቅመ ደካሞችንና አረጋውያንን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ስራዎች እውን ማድረግ መቻሉን አንስተዋል። በዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ 14 ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ እንደሚገኙ ነው የተናገሩት። በአሁኑ ወቅት የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት እድሳትና መልሶ ግንባታ፣ የአካባቢ ንጽህና ጥበቃ፣ ችግኝ ተከላ፣ ደም ልገሳ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና ሌሎች ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሆኑም አንስተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ማዕድ ማጋራት፣ አዳዲስና ነባር የመማሪያ ክፍል ግንባታ እና እድሳት ፣ የትምህርት ቤቶች የተማሪ ወንበሮች ጥገና፣ ጽዳትና ውበት ስራዎችን ጨምሮ የማጣቃሻ መጽሀፍት የማሰባሰብ ስራ በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ የትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ መደጋገፍ፣ የመተጋገዝና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ጠቁመው የዜጎችን እውቀት፣ ገንዘብ፣ ጉልበት እና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎችን በሚገባ መጠቀምና ከድህነት መላቀቅ እንደሚያስፈልግ ነው የጠቆሙት። ይህ የመተጋገዝና የአብሮነት ባህል ድህነትን ለማሸነፍ ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፣ አመራሩ የታቀዱትን ግቦች ወደ ሙሉ ተግባር ለመቀየር እያከናወነ የሚገኘውን ተግባራት ማጠናከር እንዳለበት አቶ ጌቱ አሳስበዋል። እንዲሁም በክልሉ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት የሚከናወኑ መርሃ-ግብሮች የተሳኩ እንዲሆኑ ሁሉም የመንግስት ተቋማት፣ በየደረጃ የሚገኝ አመራር፣ የመንግስት ሠራተኞችና መላው ሕዝቡ የሚጠበቅበትን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ የውሃ ሃብቶቿን ለኢነርጂ ልማት የማዋሉን ጉዞ አጠናክራ ትቀጥላለች - ኢንጂነር አሸብር ባልቻ
Sep 4, 2026 83
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የውሃ ሃብቶቿን ለኢነርጂ ልማት የማዋሉን ጉዞ አጠናክራ እንደምትቀጥል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ አስታወቁ። ግብፅ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሃብት ትብብርና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርህን ባለመቀበል በቅኝ ግዛት ዘመን የነበረውን የአባይን ወንዝን በብቸኝነት የመጠቀም ስሁት ትርክት ለመመለስ በራሷ ዓለም እየዳከረች እንደሚገኝ አንስተዋል። ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቶቿን በማልማት ሙሉ በሙሉ የመጠቀም መብት ያላት ሉዓላዊት ሀገር መሆኗን በሕዳሴ ግድብ በተግባር አስመስክራለች። ኢትዮጵያውያን ላለፉት አሥራ አራት ዓመታት ሕዳሴውን ለማደናቀፍ የተሸረቡ ሴራዎችን በመበጣጠስ በራሳቸው አቅም ገንብተው የዓባይ ትሩፋት ተቋዳሽ የሆኑበትን ዕድል እንደፈጠሩ ገልጸዋል። "ውሾች ይጮሃሉ ግመሏ ጉዞዋን ትቀጥላለች" እንዲሉም፤ ኢትዮጵያ ሕዳሴን እንዳሳካች ሁሉ የማንም ጩኸት ሳይገድባት እንደ ሕዳሴ ግድብ ሁሉ የውሃ ሃብቶቿን ለኢነርጂ ለማዋል ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም ለዓለም የገለጠ በሕብረ-ብሔራዊ አንድነት የተገነባ ሁነኛ የትዕምርት ፕሮጀክት መሆኑንም አንስተዋል። ሕዳሴ ግድብ መገንባቱ በታችኞቹ የተፋሰስ ሀገራት ላይ ምንም ዓይነት ጫና ሳይፈጥር ዓመቱን ሙሉ አስተማማኝ ውሃ የሚያገኙበትን ዕድል እንደፈጠረ አብራርተዋል። ግብፅም አስተማማኝ የውሃ ፍሰት እያገኘችና ግድቦቿም ሙሉ ሆነው ሳለ የምታስተጋባው ጩኸት ፍጹም ሐሰት መሆኑን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ አብሮ የማደግ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርና ትብብር መርህ በውሃ ሃብቶቿ ላይ የምታመነጨውን ኃይል ለጎረቤቶቿ በማቋደስ ተጠቃሚ እያደረገች መሆኗን ተናግረዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ማንም ስለጮኸ ሃብቶቿን አልምታ ከመጠቀም የሚያግዳት አካል የለም ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ግብጽ የምታሰራጨው የተዛባ መረጃም የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን በማልማት ዕድገትና ብልፅግናን እንዳናረጋግጥ የማድረግ ሴራ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫ ሌሎችን በመጉዳት ላይ የተመሠረተ አይደለም ያሉት ኢንጂነር አሸብር፤ በልማት ትሩፋቶች አብሮ በማደግ መርህ ለሌሎች በማቋደስ እየተንቀሳቀሰች ነው ብለዋል። አሁንም ወደፊትም ትልቁ የኃይል ምንጫችን ወንዞቻችን ናቸው ያሉት ኢንጂነር አሸብር፤ ወንዞቻችንን ወደ ልማት ለመቀየር ጥናትን መሰረት በማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ለመጪው አዲስ ዓመት የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶችን ለማቅረብ በቂ ዝግጅት ተደርጓል
Sep 4, 2026 193
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡-ለመጪው አዲስ ዓመት የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶችን በስፋት ለማቅረብ በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ገለጸ። ኮሚሽኑ የ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶችን የአቅርቦት ዝግጅት በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። ኮሚሽነር ሽታዬ መሐመድ እንደገለጹት፤ ህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማህበራት የሪፎርም ሥራዎች ተከናውነዋል። ከመጪው በዓላት ጋር ተያይዞ አስፈላጊ ግብዓቶችን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የሚያስችሉ የዋጋ ጥናቶችን በማድረግ የትስስር ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል። በዚህም ለአዲስ ዓመት፣ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ከፌዴራል ኅብረት ሥራ ኮሚሽንና ከክልሎች ማህበራት ጋር የአቅርቦት ትስስር መፈጠሩን ገልጸዋል። የጤፍ፣ የዱቄትና ሌሎች የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ ከአምራች ኢንዱስትሪዎችና ዩኒየኖች ጋር ትስስር መፈጠሩን ለአብነት ጠቅሰዋል። የእንቁላልና የዶሮ ምርቶች፣ የሽንኩርት እንዲሁም የዘይት አቅርቦትም ተደራሽ ለማድረግ ከአምራቾችና ከአስመጪዎች ጋር ትስስር መፈጠሩን አክለዋል። የስጋ አቅርቦትን በተመለከተም የሸማች ማህበራት ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡና የገበያ አማራጮችን የማስፋት ሥራዎች መከናወኑን ገልጸዋል። የገበያ አማራጮችን ለማስፋት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ለህብረተሰቡ በዩኒየን፣ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎችና በባዛሮች ምርቶች በስፋት መቅረባቸውንም አንስተዋል። በሁሉም ክፍለ ከተሞች ኤግዚቢሽንና ባዛር መዘጋጀታቸውንና ከ700 በላይ በሸማች ሱቆች፣ በ154 በመሰረታዊ ሸማች ማህበራት ምርቶች መቅረባቸውን ገልጸዋል። ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚከናወኑ የገበያዎችን ተደራሽነት የማስፋትና የማዘመን ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
በአማራ ክልል ከ 10 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ላይ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ ነው
Sep 4, 2026 86
ባህርዳር ፤ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረትን ለማቃለል በ10 ሺህ 456 ሄክታር መሬት ላይ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የምርጥ ዘር አቅርቦት ወሳኝ ድርሻ አለው። በአማራ ክልል ለሚያጋጥመው የምርጥ ዘር እጥረት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እና የአካባቢውን የስነ-ምህዳር ሁኔታ ያገናዘበ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ፣ የክልሉ ግብርና ቢሮ ትኩረቱን በሀገር ውስጥ የዘር ብዜት ላይ አድርጎ እየሰራ ይገኛል። ይህ በ10 ሺህ 456 ሄክታር መሬት ላይ የተጀመረው የዘር ብዜት ስራም የውጭ ዘር ጥገኝነትን ከመቀነስ ባለፈ፣ ለቀጣዩ ምርት ዘመን ገበሬው ጥራት ያለውና በሽታን የመቋቋም አቅሙ የጎለበተ የሰብል ዘር በቅርበትና በወቅቱ እንዲያገኝ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል። በክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ ነው። በዚህም ከምርምር የወጡ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በ2018/2019 የምርት ዘመን በኩታ ገጠም እርሻ ዘር የማባዛት ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በምርት ዘመኑ በ10 ሺህ 456 ሄክታር መሬት ላይ እየተባዙ ያሉት የበቆሎ፣ የስንዴ፣ የጤፍ፣ የሩዝ፣ የአኩሪ አተርና ሌሎች የተሻሻሉ የሰብል ዘሮች እንደሆኑም አመልክተዋል። የዘር ብዜት ስራው በአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ፣ በግል ዘር አባዥዎች፣ በዩኒየኖች፣ በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽንና ሌሎች ዘር አባዢ ድርጅቶች እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል። በምርት ዘመኑ 267 ሺህ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ምርጥ ዘር ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ ይህም የክልሉን የምርጥ ዘር እጥረት በማቃለል ረገድ የጎላ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የሚገኘው የዕድገት ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ በሪሁን እንዳሉት ዩኔየኑ በ360 ሄክታር መሬት ላይ የስንዴ፣ የበቆሎና ባቄላ ሰብሎች የምርጥ ዘር ብዜት ስራ እያከናወነ ነው። የዘር ብዜት ተግባሩን እያከናወነ ያለው ከ4 ሺህ 100 አርሶ አደሮች ጋር የኮንትራት እርሻ የውል ስምምነት በመፈፀም መሆኑንም ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል። ዩኔየኑ ባለፈው የምርት ዘመን አባዝቶ ከሰበሰበው ከሰባት ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ዘንድሮ የተሻለ ይሰበስባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ለአፍሪካ ሀገራት አቅም የሚሆን ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች ነው
Sep 4, 2026 8
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ለቀጣናው ብሎም ለአፍሪካ ሀገራት አቅም የሚሆን ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች መሆኗን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) ገለጹ። ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆየው የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት፣ የቀጣናውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስትራቴጂ በጋራ ለመቅረጽ ያለመ አውደ ጥናት መካሄድ ጀምሯል። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣን ዕድገት የዓለም ኢኮኖሚን፣ መንግሥታትንና የሰውን አቅም እየቀረጸ ይገኛል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ዘርፍ የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን በማፋጠን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ኃይል መሆኑንም ገልጸዋል። የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራትም የሰው ሰራሽ አስተውሎት የቴክኖሎጂ አማራጭን በአግባቡ በመጠቀም የኢኮኖሚ ውህደትን ማፋጠን እንዳለባቸው ተናግረዋል። ለዚህም የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም እና የመረጃ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ ከአባል ሀገራት ብሔራዊ የሕግ ማዕቀፎች ጋር የተጣጣመ ቀጣናዊ የጋራ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። አፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ተጠቃሚነት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑን አንስተው፤ ዘርፉ በፍጥነት ለውጥ እያስመዘገበ ያለ መሆኑን ተናግረዋል። ስለሆነም ሀገራት ይህ ተግባር የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ብሎም በአፍሪካ ደረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎትና ቴክኖሎጂ የተሻለ እየሰራች መሆኑንም ጠቁመዋል። ኤ አይ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ዘርፉን ለመምራት ኢንስቲትዩት በማቋቋም አበረታች ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅም መሆኑንም አብራርተዋል። የኢጋድ አባል ሀገራቱ የተናበበ ፖሊሲ እንዲኖራቸውና የተሻሉ ተሞክሮዎችን ለማስፋት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በቀጣይ ከቀጣናው የተውጣጡ ወጣቶችን የሚያሰለጥን የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢጋድ ጉዳዮች ዳይሬክተር ከተማ ኃይሌ በበኩላቸው፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የኢኮኖሚ እድገትን የሚያፋጥን ብዝኅ ምርታማነት አቅም መገንቢያ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። በዚህም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለቀጣናዊ ትብብር፣ ለጠንካራ የፖሊሲ ማዕቀፍ ዝግጅት፣ ለዲጂታል መሠረተ ልማት፣ እንዲሁም ለጥናትና ፈጠራ ኢንቨስትመንት መጠቀም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በሀገራዊ እና ቀጣናዊ ልማት ውስጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ሚና በመገንዘብ ከኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲም የኢጋድ አባል ሀገራትን እና አጠቃላይ አፍሪካን የሚጠቅም እንደሚሆን ገልጸዋል።
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሥራን በእውቀትና በቴክኖሎጂ ታግዞ ለማከናወን አስችሎናል-ሰልጣኞች
Sep 4, 2026 48
ቦንጋ፣ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሥራቸውን በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ታግዘው ለማከናወን እንዳገዛቸው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግስት ሠራተኞች ገለፁ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቪ የሆነው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና ፕሮግራም የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር በማፋጠን ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል። በፕሮግራሙም በዋናነት በሶፍትዌር ልማት፣ በዳታ ትንተና፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ክህሎት እና መሰል የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በማተኮር ለዜጎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። ስልጠናውን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው በቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ የፊዚክስ መምህር ሲሳይ አብደላ፣ መንግስት ባመቻቸው የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በአራቱም ፕሮግራሞች ሰልጥናቸውን አጠናቀው የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ተናግረዋል። ይህም ሥራቸውን በቴክኖሎጂ አስደግፈው ለማከናወን ከማገዝ ባለፈ በኦንላይን የራሳቸውን ሥራ ለመስራት ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ጠቁመዋል። ሌላው የስልጠና ዕድሉ ተጠቃሚ የመንግስት ሠራተኛ ወጣት ጌጥዬ አለሙ በበኩሉ በነጻ በተሰጠው የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መሠረታዊ የዲጂታል እውቀቱን ማሳደጉ በስራው ተወዳዳሪ ለመሆን እንዳስቻለው ተናግሯል። በሶፍት ዌር ልማት፣ በዳታ ትንተና፣ በሞባይል አፕሊኬሽን ግንባታ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ሰልጥኖ ምስክር ወረቀት ማግኘቱ ሥራውን በተሻለ ጥራት ለማከናወን አስችሎታል። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ዜጎች በተለይ ወጣቶች ከቴክኖሎጂ ጋር እንዲተዋወቁና ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ትልቅ እገዛ እያደረገ ነው ያሉት ደግሞ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሒሳብ መምህር ሙሉጌታ አንዷለም ናቸው። በተለይ መምህራን ሥራቸውን ወቅቱ በደረሰበት የቴክኖሎጂ አውቀት ታግዘው እንዲያከናውኑ ያግዛቸዋል ብለዋል። በቀጣይ በዳታ ሳይንስ እና በአርቴፌሻል ኢንተለጀንስ ላይ ስፔሻላይዝ ለማድረግ ፍላጎት እንዳደረባቸውም ጠቁሟል ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ምክትል ሀላፊና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ አሰፋው ኢንሼቲቩ ዲጅታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማፋጠን ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። እንደሀገር የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢንሼቲቪ በቴክኖሎጂ የበቃ ተወዳዳሪ ዜጋ መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ስልጠናውን ለመውሰድ በክልሉ ከተመዘገቡት ውስጥ እስካሁን ድረስ ከ48 ሺህ በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው የምስክር ወረቀት ወስደዋል ብለዋል።
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ክህሎታችንን በማሳደግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ አድርጎናል- ወጣቶች
Sep 4, 2026 47
ጎንደር፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ክህሎታችንን በማሳደግ ለስራ እድል ፈጠራ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ከፍተኛ እገዛ እያደረገልን ነው ሲሉ ሰልጣኞች ገለጹ። በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የጎንደር ከተማ ወጣቶች እንዳሉት፣ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ዘመኑ የሚጠይቀውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን እና ተወዳዳሪነታቸውን አሳድጓል። አስተያየታቸውን ከሰጡ ወጣቶች መካከል በውሃ ምሕንድስና ሁለተኛ ዲግሪውን ያጠናቀቀው ዮሐንስ መልኬ ፤ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የመረጃ ትንተና እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ክህሎቴን ለማሳደግ አስችሎኛል ነው የሚለው። በትምህርት ወቅት የምርምር ስራ በሚያካሒድበት ወቅት መረጃዎችን በቀላሉ ለማደራጀት የተሻለ ክሕሎት እንዲኖረው በማድረጉ በአራት ነጥብ ውጤት ለመመረቅ እንደረዳውም ነው የተናገረው። በተሰማራበት የስራ መስክም ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን፣ የጤና አጠባበቅ እና የምግብ ስርዓትን በቀላሉ በመገንዘብ ምርታማነትን ለማሳደግ ስልጠናው የላቀ ሚና እንዳበረከተለት ነው ያረጋገጠው። ወጣት ፍሬው ይግዛው በበኩሉ ከስልጠናው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ የፕሮግራሚንግ እና የመሰረታዊ ዳታ ሳይንስ እውቀትን በማግኘት በዲጂታል ቢዝነስ ዘርፍ ለመሰማራት እንደቻለ ነው የጠቀሰው። የኮደርስ ስልጠና በቴክኖሎጂው ዓለም አዳዲስ ግኝቶችን በቀላሉ ለመረዳት እና ከዓለም አቀፍ አሰራሮች ጋር አብሮ ለመራመድ የሚያስችሉ ዘመናዊ እሳቤዎችን ለመገንባት ትልቅ አቅም እንደፈጠረለትም ተናግሯል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት መምሪያ ተወካይ ኃላፊ አቶ አካሌ ፀጋይ እንደገለጹት፣ የኮደርስ ስልጠና በቴክኖሎጂ ዘርፍ እና በስራ እድል ፈጠራ የወጣቶችን ተጠቃሚነት እያሳደገ ይገኛል። የመንግስት ሰራተኞችን እና ወጣቶችን በስልጠናው በማሳተፍ የዲጂታል ክህሎታቸውን በማዳበር በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በመሆን ተጨማሪ የስራ እድል እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ 44 ሺህ 962 ዜጎች የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን ነው ያመለከቱት። በቀጣይም በከተማው የሚገኙ የመንግስት እና የግል ኮሌጆች የኮምፒውተር ክፍሎችን እና አሰልጣኝ መምህራንን በመጠቀም ስልጠናውን በስፋት ለማከናወን እንደሚሰራ አስረድተዋል።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀምን ከአባል ሀገራት ብሔራዊ የሕግ ማዕቀፎች ጋር የተጣጣመ ቀጣናዊ የጋራ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል-ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር)
Sep 4, 2026 96
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀምንና የመረጃ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከአባል ሀገራት ብሔራዊ የሕግ ማዕቀፎች ጋር የተጣጣመ ቀጣናዊ የጋራ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። ከዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆየውና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት፣ የቀጣናውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስትራቴጂ በጋራ ለመቅረጽ ያለመ አውደ ጥናት መካሄድ ጀምሯል። የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣን ዕድገት የዓለም ኢኮኖሚን፣ መንግሥታትንና የሰውን አቅም እየቀረጸ ይገኛል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ዘርፍ የቀጣናዊ ኢኮኖሚ ውህደትን በማፋጠን ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ኃይል መሆኑንም ገልጸዋል። የምሥራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል ሀገራትም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አማራጭን በአግባቡ በመጠቀም የኢኮኖሚ ውህደትን ማፋጠን እንዳለባቸው ተናግረዋል። ለዚህም የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም እና የመረጃ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ ከአባል ሀገራት ብሔራዊ የሕግ ማዕቀፎች ጋር የተጣጣመ ቀጣናዊ የጋራ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባ አሳስበዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢጋድ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ከተማ ኃይሌ በበኩላቸው፤ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያፋጥንና ብዝኅ ምርታማነት አቅም መገንቢያ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። በዚህም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለቀጣናዊ ትብብር፣ ለጠንካራ የፖሊሲ ማዕቀፍ ዝግጅት፣ ለዲጂታል መሠረተ ልማት፣ እንዲሁም ለጥናትና ፈጠራ ኢንቨስትመንት መጠቀም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በሀገራዊ እና ቀጠናዊ ልማት ውስጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችንና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ሚና በመገንዘብ ከኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗንም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲም የኢጋድ አባል ሀገራትን እና አጠቃላይ አፍሪካን የሚጠቅም እንደሚሆን ገልጸዋል።
ስፖርት
በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከአል ሂላል ጋር ይጫወታል
Sep 4, 2026 57
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ቅድመ ማጣሪያ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሱዳኑ አል ሂላል ጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል። ጨዋታው ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ በሩዋንዳ በሚገኘው ኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ይካሄዳል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአህጉራዊው መድረክ ለመሳተፍ የበቃው በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸንፎ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ ነው። ወልዋሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሲሳተፍ በክለቡ የ70 ዓመታት ታሪክ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመራው ወልዋሎ ለቅድመ ማጣሪያው ጨዋታው ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል። ካርሎስ ዳምጠው፣ በረከት ሳሙኤል፣ እዮብ አለማየሁ እና አህመድ ረሺድን ጨምሮ የተለያዩ ተጫዋቾችን በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት መስኮት በማስፈረም ስብስቡን አጠናክሯል። ክለቡ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች ባሻገር የጌቱ ኃይለማርያም እና አፈወርቅ ኃይሉን ጨምሮ የሌሎች ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ46 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ተጋጣሚው አል ሂላል በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሲሳተፍ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የሱዳኑ ክለብ ለመጨረሻ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተሳተፈው እ.አ.አ በ2022/23 የውድድር ዓመት እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። በአሰልጣኝ ናዲር ዛርግ አክላንድ የሚመራው አል ሂላል በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ የረጅም ጊዜ የተሳትፎ ልምድ አለው። እ.አ.አ በ1937 የተመሰረተው አል ሂላል አንጋፋ የሚባል ክለብ ነው። የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በሁለተኛ ዙር ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም እና ከሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል።
ሊቨርፑል በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ለማግኘት ከኤፕስዊች ታውን ጋር ይጫወታል
Sep 4, 2026 117
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል። ምሽት አራት ሰዓት ላይ ኤፕስዊች ታውን ከሊቨርፑል በፖርትማን ሮድ ስታዲየም ይጫወታሉ። ከሁለት የሊጉ ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ያገኘው ኤፕስዊች ታውን 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ተጋጣሚው ሊቨርፑል በሁለት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል። ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ13ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 12 ጨዋታዎች ሊቨርፑል ሰባት ጊዜ ሲያሸንፍ ኤፕስዊች ታውን ሁለት ጊዜ ድል ቀንቶታል። በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ሊቨርፑል በ12 ጨዋታዎች ላይ 26 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ኤፕስዊች ታውን ዘጠኝ ጎሎችን አስቆጥሯል። ክለቦቹ በፕሪሚየር ሊጉ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት እ.አ.አ ጃንዋሪ 2025 ሲሆን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊቨርፑል 4 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ባለሜዳው ኤፕስዊች ታውን በሁለተኛ ሳምንት በማንችስተር ዩናይትድ ካጋጠመው የ5 ለ 2 ሽንፈት አገግሞ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል። በሁለቱም የሊጉ ጨዋታዎች አቻ የወጣው ሊቨርፑል የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ መርሐ ግብር እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 የውድድር ዓመት ኮከቦች ሽልማት ሊያበረክት ነው
Sep 2, 2026 293
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 ዓ.ም የውድድር ዓመት ምርጦች ዕውቅና የመስጠት መርሐ ግብር ጳጉሜን 3 እንደሚያካሂድ አስታወቀ። በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ፣ የወንዶች ከፍተኛ ሊግ፣ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ፣ የሊግ አንድ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ አሰልጣኝ፣ ኮከብ ግብ ጠባቂ፣ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ እንዲሁም ምስጉን ዳኛ እና ረዳት ዳኞች ሽልማት ይበረከታል። የሽልማት ስነ ሥርዓቱ የሚካሄድበት ቦታ በቀጣይ እንደሚገለጽ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።
ማንችስተር ሲቲ የቼልሲውን ኤንዞ ፈርናንዴዝን ለማስፈረም ተስማማ
Sep 1, 2026 296
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦ ማንችስተር ሲቲ በዝውውር መስኮቱ ማብቂያ ቀን የቼልሲውን አማካይ ኤንዞ ፈርናንዴዝን በ125 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል። የ25 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አማካይ ከቤንፊካ በ107 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ቼልሲ የተቀላቀለው እ.አ.አ በ2023 ነበር። ተጫዋቹ ቼልሲ ከፉልሃም ጋር ባደረገው የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ የነበረ ቢሆንም፣ ከሉተን ጋር በካራባኦ ካፕ እንዲሁም ከብራይተን ጋር በተደረገው የሊጉ መርሐ ግብር አልተጫወተም። ይህ ዝውውር ሊቨርፑል ባለፈው ዓመት በክረምቱ የዝውውር መስኮት ማጠናቀቂያ ቀን የኒውካስትል ዩናይትዱን አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳክ ለማስፈረም ከከፈለው የእንግሊዝ ክብረ ወሰን ክፍያ እኩል መሆኑን ስካይ ስፖርትስ ዘግቧል። ፈርናንዴዝ ወደ ማንችስተር ሲቲ ማምራት እንደሚፈልግ ያሳወቀ ሲሆን፣ በኢትሃድ ከቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኙ ኤንዞ ማሬስካ ጋር እንደገና ይገናኛል። ተጫዋቹ በቀጣይ ሰዓታት ውስጥ የሕክምና ምርመራዎችን አድርጎ ዝውውሩን ሙሉ በሙሉ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል። ቼልሲ አርጀንቲናውን አማካይ የሚተካ ሌላ ተጫዋች ለማስፈረም እየሰሩ ይገኛሉ። ክለቡ የሮማውን ማኑ ኮኔ እና የሞናኮውን ላሚን ካማራን ለመግዛት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ የሚገኙ ሌሎች አማካዮችንም እየተመለከተ ይገኛል።
አካባቢ ጥበቃ
የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ ነው
Sep 2, 2026 330
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ መሆኑ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አባንግ ኩመዳን ገለጹ። ከመላው የሀገሪቱ የተውጣጣ የወጣቶች ቡድን በሦስት የአፍሪካ ሀገራት ነገ የሚጓዝ ይሆናል። የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አባንግ ኩመዳን እንደገለጹት፤ ወጣቶቹ የሚጓዙት ጋና፣ ዚምባብዌና ናይጄሪያ ነው። በዚህ የጉዞ መረሃ ግብር ሀያ አራት ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን፤ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን በመትከል ልምድ እንደሚያካፍሉም አስታውቀዋል። መርሃ ግብሩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም የብልጽግና ወጣት ክንፍ በፓኪስታን የችግኝ ተከላ ማካሔዳቸውን ገልጸዋል። የልዑካኑ ጉዞ የልምድ ልውውጥ ከማድረግ በተጨማሪ ወንድማማችነትን ለማጠናከር የሚያግዙ ተግባራትን እንደሚያከናውን አስታውቀዋል። በቀጣይም ወጣቶች ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሄድ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማከናወን የኢትዮጵያን ልምድ የማካፈል ተግባርን ያጠናክራል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በስኬታማነት እየተከናወነ ይገኛል። በዚህ ዓመት ብቻ ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በአንድ ጀምበር መተከላቸው ይታወሳል። ይህ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዓለም አቀፍ እውቅና እያገኘ ሲሆን የተለያዩ ሀገራትም ተሞክሮውን እየወሰዱት ይገኛሉ።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል
Sep 2, 2026 631
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ከነሃሴ 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜን አምስት ቀን 2018ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የሚኖረውን የአየር ፀባይ ሁኔታ በተመለከተ ለኢዜአ መግለጫ ልኳል። በመግለጫውም ነሀሴ ወር የክረምት የመጨረሻ ወቅት በመሆኑ በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የዝናብ መጠን እንደሚቀንስ በማመላከት ለረጅም ጊዜ ደረቅ ሆነው የሰነበቱት ደቡብና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸውን እንደሚያስተናግዱ ጠቁሟል። በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅና በመካከለኛው ኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚቀነስ ነገር ግን በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በስርጭትም በመጠንም የተሻለ ዝናብ እንደሚያገኙ በመግለጫው ተመላክቷል። በሚቀጥሉት አስር ቀናትም ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። ማኅበረሰቡም ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ የሚኖረውን የእርጥበት ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የግብርና ስራቹን እንዲያከናውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ከሚያስተናግዱ ቦታዎች መካከል ቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር የምዕራብ ፣መካከለኛ ፣ደቡብ እና ሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን፣ የምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ካማሺ፣ መተከል፣ አሶሳ ዞኖች እንደሚገኙበት ከመግለጫው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ሁሉም ሸዋ ዞኖች፣ አኝዋክ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ጉራጌ ፣አዲስ አበባ ፣ድሬዳዋ፣ የምዕራብ ፣የሰሜን ምዕራብ ፣መካከለኛው፣ ምሥራቅ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ፣የሲዳማ አብዛኛው የክልሉ ዞኖች ደግሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ከሚያስተናግዱ አካባቢዎች መካከል መሆናቸው ተጠቁሟል። ኢንስቲትዩቱ ቀላል፣መካከለኛ እና ከባድ እርጥበትን የሚያስተናግዱ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ፣ የመኸር ሰብል አብቃይ ፣ አርብቶ አድርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ይህን የአየር ሁኔታ ለግብርና ስራዎቻቸው እንዲያውሉ አስገንዝቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መካከለኛ እና ከባድ የዝናብ መጠን የሚያስተናግዱ አካባቢዎች ተደፋታማ ማሳዎች ላይ የተዘጉ የማፋሰሻና የማንጣፈፊያ ቦዮች ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሰብል በሽታን አረምን አስቀድሞ መከላከል ፣የአፈር መሸርሸር ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ማከናወን፣ እና አርሶ አደሮችም የማሳ ጉብኝት በየጊዜው በማድረግ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስቧል። ከቀላል እስከ መካከለኛ እርጥበት የሚያገኙ ቦታዎች ደግሞ የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል፣ የዝናብ ውሀን በማሰባሰብ በደረቅ ወቅቶች መጠቀም ፣የአፈር ውስጥ ትነትን መጠንን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን ፣የእንስሳት ግጦሽ ሳርን በአግባቡ መያዝ ተገቢ ነውም ተብሏል። ለተከታታይ አስር ቀናት የሚቆየው አየር ፀባይ ሁኔታም የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።
በአፍሪካ አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል
Sep 2, 2026 487
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ የአየር ንብረት መዛባትንና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ገቢራዊ ማድረግ እንደሚገባ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን የብሔራዊ የልማት ዕቅዷ አካል ማድረጓም ተገልጿል። የአፍሪካ ቀጣና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም ፎረም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። የቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 ይፋ የተደረገ ሲሆን እስከ 2027 እያንዳንዱን ሰው በአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና በተፈጥሮ አደጋዎች መጠበቅ የሚያስችል ኢንሼቲቭ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ከተመድ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቢሮና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የአፍሪካ የተቀናጀ አይነተ ብዙ አደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ እርምጃ ሥርዓት ተግባራዊ አድርጓል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሀና አበበ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፎረም ወቅታዊና ተገቢ ነው። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ መዛባት ድርቅ፣ ጎርፍ እና ሌሎችን አደጋዎችን በተደጋጋሚ እያስተናገደች መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ሴቶችና ህፃናት ጨምሮ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች የአደጋው ገፈት ቀማሽ እየሆኑ ነው ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የውስጥ የፋይናንስ አቅምን ማጎልበትና ተቋማዊ አንድነት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የአየር ንብረት መዛባትና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን የብሔራዊ የልማት ዕቅዷ አካል ማድረጓን ጠቅሰው፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በፋይናንስና ሌሎችም ተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል። ማንም ሀገር ብቻውን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስትራቴጂን ውጤታማ ማድረግ እንደማይችል ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራትና የተለያዩ አጋር አካላት ጋር በአይነተ ብዙ የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዘላቂ አካባቢና ብሉ ኢኮኖሚ ዳይሬክተር ሀርሰን ኒያምቤ፤ በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ማህበረሰቡን አደጋን የመቋቋም አቅም መገንባትና ከአደጋ መጠበቅ ይገባል ብለዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2027 እያንዳንዱን ሰው ከአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና መሰል አደጋዎች መጠበቅ የሚለውን ግብ ለማሳካት ውይይቱ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ጎርፍና የተራዘመ ደርቅ፣ በማህበረ-ኢኮኖሚ፣ እና በሌሎች አደጋዎች ተጋላጭነት ተባብሶ መቀጠሉን በመግለጽ፤ አፍሪካውያን ውስጣዊ ትብብራቸውን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል። አደጋ ድንበር የለውም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በአይነቱ ብዙ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የአባል ሀገራቱን አቅም ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ቢሮ ዳይሬክተር ኤግነስ ኪጃዚ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በአፍሪካ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የአመራር ቁርጠኝነት እያደገ በመምጣቱ መሻሻል እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች በፍጥነትና በተወሳሰበ ሁኔታ ተባብሰው ቀጥለዋል ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን ለመቆጣጠር የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በሀገራት የተቀናጀ አሰራር መምራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የ2027 ግብ ጠቃሚ መሰረት መሆኑን በመግለፅ፤ በአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ለቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ግንባታ ዘላቂና እምነት የሚጣልባቸው መሆን አለባቸው ብለዋል። በአፍሪካውያን መካከል ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ ተቋማትን መገንባት እንደሚገባ በመጥቀስ፤ የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የመጀመሪያው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ይካሄዳል - የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
Sep 1, 2026 227
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግርና ዘላቂ የኢንቨስትመንት እድል የሚያሰፋ የመጀመሪያው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አስታውቀ። የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ካሳሁን ማሞ፤ ምክር ቤቱ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀውን የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የኢትዮጵያን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትና ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚደረገውን ሽግግር ለማፋጠን ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ፎረምና ኤግዚቢሽኑም ፖሊሲ አውጪዎች፣ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና የአረንጓዴ ቢዝነስ ኩባንያዎችና አልሚዎች በተሳተፉበት ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማላቅ ዘላቂ ሥነ-ምህዳራዊ ዕይታን ያማከለ የቢዝነስና የኢንቨስትመንት እንዲጎለብት ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ረገድ ከጀርመን ዓለም አቀፍ የትብብር ድርጅት እና ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር የአረንጓዴ ልማትና ዘላቂነት ማዕከል ማቋቋሙን አመልክተዋል። የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽንም ጤናማ ሥነ-ምኅዳርን የተከተለ የታዳሽ ኃይልና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን በማጠናከር የዘርፉ ተዋናዮች ምርትና አገልግሎታቸውን እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል። መድረኩም በአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትንና ሥራ ፈጣሪዎችን በማገናኘት አዳዲስ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር በማፋጠን ዘላቂ ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋትና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማላቅም ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል። በኔዘርላንድ የልማት ድርጅት የሊዌይ የፕሮግራም ማኔጀር ሔለን ጌታው በበኩላቸው፤ መድረኩ ከአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው ብለዋል። ፎረሙም በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ አልሚዎችን የፋይናንስ፣ የገበያ፣ የቴክኖሎጂና የመረጃ ተግዳሮቶች በመለየት መፍትሔ የሚመላከትበት ጠቃሚ መድረክ እንደሚሆንም ገልጸዋል። በተጨማሪም ባለድርሻ አካላትን በማገናኘት የገበያ ትስስርና የድጋፍ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል አክለዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 118
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1570
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1225
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች። ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 1503
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሐተታዎች
የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች
Aug 28, 2026 323
አዲስ አበባ ነሀሴ 22/2018 (ኢዜአ) የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Homegrown Economic Reform) እቅዶችን በመተግበር በበርካታ ዘርፎች መሠረታዊ ለውጦችን እና ስኬቶችን ማስመዝገብ ተችሏል። በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል (አይሲቲ)፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ከማሳደግ ባሻገር የወደፊት ዘላቂ እድገት መሠረት ያኖሩ መሆኑን መናገር ይቻላል። በመሆኑም በአምስቱ ዋና ዋና ሴክተሮች የመጡ ውጤቶችና የተመዘገቡ ስኬቶችን በወፍ በረር እንቃኛለን። 1. በግብርና ዘርፍ የስንዴ ምርትና የውጭ ኤክስፖርት: የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መስፋፋት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት አስቀምጧል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ ሀገር መላክ የቻለችበትን እመርታዊ ስኬትም አሳይቶናል። የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭን በመተግበር በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና የማር ምርት እንዲሁም በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሩዝና ሻይ ልማትም ባለፉት አምስት አመታት እመርታዊ ለውጥ ተመዝግቧል። አርሶ አደሩ የመሬትና የውሃ ሀብቶችን አቃፊ በሆነ መንገድ በመጠቀም በዓመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችልበት አሰራር ተዘርግቷል። በዚህም የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሁነኛ የገቢ ምንጭ የሆነበትን እድል ፈጥሯል። ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የመቻል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል። በተለይም ደግሞ የቡና ምርታማነትና ጥራት በማደጉ ምክንያት በኤክስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማገኘት ተችሏል። በዘርፉ በቀጣይም የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሜካናይዜሽን በማስደገፍ ምርታማነትን የማሳደግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የዝናብ ጥገኝነትን ለመቀነስ መጣር እንዲሁም የግብርና ምርቶችን ጥራት በማሻሻልና በማቀነባበር ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ዋጋ ማሳደግ ተገቢ ይሆናል። 2. የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ንቅናቄ በመፍጠር ቀደም ሲል ተቆልፈው የነበሩና በዝቅተኛ አቅምያመርቱ የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። የሀገር ውስጥ የምርት ፍላጎትን በመሸፈን ለውጭ ሀገር ምርቶች ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪም መቀነስ አስችሏል። ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የህግና የአሰራር ሁኔታዎችን በመፍጠር በርካታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል። ከተገነቡት የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮች (IAIPs) ጋር አርሶ አደሩን በማስሳሰር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲጠናከር ተደርጓል። የአምራች ዘርፉ መስፋፋት ለብዙ ሺህ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር የታቸለበት ሆኗል። በቀጣይም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በኃይል፣ በሎጂስቲክስና በግብአት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በመደገፍ ኤክስፖርትን ማሳደግ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች 80% እና ከዚያ በላይ የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት፣ በህዝብና በግል አጋርነት (PPP) አማካኝነት በትልልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ላይ የግሉን ዘርፍ አሳትፎ ማስፋፋት ትኩረት የሚደረግበት ይሆናል። 3. የዲጂታል (አይሲቲ) ዘርፍ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስልት ስኬቶችን በማስቀጠል ወደ "ዲጂታል 2030" እቅድ መሸጋገር ተችሏል። በ"መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በሌሎች ፖርታሎች አማካኝነት ህዝባዊ አገልግሎቶችን በበይነ-መረብ (Online) የመስጠት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዜጎችን መረጃ ማዕከላዊ የሚያደርግና ለፋይናንስ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች መሠረት የሆነውን የፋይዳ መታወቂያ ፕሮጀክት በላቀ መልኩ ማሳካት ተችሏል። የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኮደር ስልጠናም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ ታላቅ ሀገራዊ የስልጠና መርሃ ግብር ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።የዲጂታል አገልግሎቶች መዘርጋታቸው የፊት ለፊት ግንኙነትን በመቀነስ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የኢንቨስትመንት ምህዳሩን አሳልጧል። የቴሌኮም ዘርፍ ውድድር: የቴሌኮም ዘርፉን ክፍት ማድረግን ተከትሎ የኢንተርኔትና የኔትወርክ ተዳራሽነትንና ጥራትን በየገጠሩ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን እና የባንክ አገልግሎቶችን ይበልጥ ዘመናዊና የተቀናጁ ማድረግም አስፈላጊ ይሆናል። የሀገሪቱን የዲጂታል መሠረተ ልማት ከሳይበር ጥቃቶች የመጠበቅ አቅምን ማጠናከር። 4. የማዕድን ዘርፍ በዘርፉ ይስተዋል የነበረውን ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ በመግታት ህጋዊ አሰራርና ቁጥጥር እንዲሰፍን ተደርጓል። የህግና መመሪያዎች ማሻሻያ በማድረግ የማዕድን ዘርፉን ለውጭና ሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ማራኪ የሚያደርጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የወርቅ፣ የከሰል ድንጋይ፣ የሲሚንቶ ግብአቶችና የከበሩ ድንጋዮች ምርትን በማሳደግ ዘርፉ የሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ እንዲሆን ተሰርቷል። በተለይም የከሰል ድንጋይ ምርትን በሀገር ውስጥ አምርቶ በመተካት ለፋብሪካዎች ግብአት ማቅረብ ተችሏል። 5. የቱሪዝም ዘርፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)አነሳሽነት የተጀመሩት "ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች በመላ ሀገሪቱ በርካታ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መገንባት ተችሏል። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶች የከተሞችን ውበትና ለኑሮ ምቹነት ከመጨመራቸው ባሻገር ለከተማ ቱሪዝም ትልቅ እድል ፈጥረዋል። አዲስ አበባ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፈረንሶችን ባካሄደችበት የዲፕሎማሲና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን አጠናክራለች። የሀገሪቱን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች የመጠበቅ፣ የማደስና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል። በድምሩ ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች ሀገሪቷን ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ማሸጋገር አስችለዋል። በመሆኑም እነዚህን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የታቀዱትን የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በተቀናጀ መልኩ መተግበር፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የግሉን ዘርፍ አሳታፊነት ማሳደግ በቀጣይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ዋነኛ የቤት ስራ ይሆናል።
የአረንጓዴ አሻራ ስኬት፦ኢትዮጵያን የአየር ንብረት ጥበቃ ሞዴል ያደረገ ኢኒሼቲቭ
Aug 23, 2026 521
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረው በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን ከ54 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እ.አ.አ በ2027 በኢትዮጵያ በሚካሄድበት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ብዛት 65 ቢሊዮን የማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ነው።ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ምርታማነትን በማሳደግ፣ የደን ሽፋንን በመጨመር፣ የተራቆተ መሬትን ወደ ነባር ይዞታው እንዲመለስ በማድረግ እና አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። በዚህም በ2011 ዓ.ም 17.2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው ሥራ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ ችሏል። ይህ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።በሁለተኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዋን ያስተዋወቀች ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራትም ለአህጉሪቱ ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እያከናወነች ላለው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠበት እና የሀገሪቱን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ውጤት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በመለገስ የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን በተግባር አሳይታለች።ይህም አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትንና አዎንታዊ የቀጣናዊ ትስስር ድልድይን እየገነባ ይገኛል። የድንበር ተሻጋሪ የወንዝ ተፋሰሶችን በመንከባከብ፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን ለጎረቤት ሀገራት በማዳረስ እና በጋራ ድንበሮች አካባቢ የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ እያከናወነችው ያለው ሥራ አህጉራዊ ሰላምና ትብብርን የሚያጎለብት አዲስ የዲፕሎማሲ መንገድ ከፍቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች የአህጉሪቱን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች ሆናለች። ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነገር ግን ለጉዳቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ የአፍሪካ ሀገራት ፍትሃዊ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኙ ድምፅ በመሆን አህጉራዊ መሪነቷን አስመስክራለች። ይህም አፍሪካውያን በራሳቸው ሀገር በቀል መፍትሔዎች የአየር ንብረት ጥበቃን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ለአካባቢ ጥበቃ አርአያ የሚሆን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ከመጠቀም፣የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ እና ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር አጣጥማ የምታካሂደው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ላይ እውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።
ረብጣ ገንዘብ ከወጣባቸው ዝውውሮች እስከ አነጋጋሪ የህግ ለውጦች ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ምን ይዞ መጣ?
Aug 21, 2026 518
በሙሴ መለሰ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቀው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሰኔ እና ሐምሌ ወራት የተካሄደውን የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተከትሎ፣ ለተጫዋቾች በቂ የእረፍት ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከተለመደው አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲጀምር ተደርጓል። የመክፈቻው ጨዋታ በኢምሬትስ ስታዲየም የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን አርሰናል እና ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ በተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህ አዲስ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ከ2.14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርገዋል። ይህ የወጪ መጠን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች የአውሮፓ አራት ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣልያን ጀርመንና ፈረንሳይ) በጥምረት ካወጡት የገንዘብ መጠን በላይ ሆኗል። ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በመዘዋወር የክረምቱ ውዱ ተጫዋች መሆን ችሏል። ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አምርቷል። በተጨማሪም ሳንድሮ ቶናሊ ከኒውካስል ወደ ቶተንሃም በ100 ሚሊዮን ፓውንድ፣ እንዲሁም ብሩኖ ጉማሬሽ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል በ75 ሚሊዮን ፓውንድ መዘዋወራቸው የክረምቱን የዝውውር ገበያ ከሚጠቀሱ ዝውውሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዝውውር ወጪው ባሻገር፣ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በአዳዲስ አሰልጣኞች የታጀበ ሆኗል። በሊጉ ታሪክ ከፍተኛው በተባለ ደረጃ ዘጠኝ ክለቦች ውድድሩን በአዲስ አሰልጣኞች ይጀምራሉ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን ላይ በሊጉ ረጅም ጊዜ (ሰባት ዓመታት) የቆየው አሰልጣኝ ሆኗል። የቼልሲው ዣቢ አሎንሶ፣ የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ እና የሊቨርፑሉ አንዶኒ ኢራኦላ ከአዳዲሶቹ አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳሉ። ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ በቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዓመታቸውን ይጀምራሉ። የሊጉ የተሳታፊዎች ስብጥርን በተመለከተ፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ከሃል ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ጋር በመሆን ከታችኛው ሊግ አድገው ሊጉን ተቀላቅለዋል። በተቃራኒው ዌስትሃም ዩናይትድ፣ በርንሌይ እና ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ባለፈው የውድድር ዘመን መውረዳቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም የእንግሊዝ ክለቦች ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ባሳዩት አስደናቂ ብቃት ምክንያት፣ በዚህ የውድድር ዘመን ክብረ ወሰን የሆነ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ። አርሰናል፣ አስቶንቪላ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ እና ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ብራይተን በኮንፈረንስ ሊግ አገራቸውን ይወክላሉ። የሊጉ አስተዳደር የክለቦችን የፋይናንስ ወጪ የሚቆጣጠር አዲስ የወጪ ገደብ (Squad Cost Ratio) መመሪያን ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም መሠረት ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ እና ለዝውውር የሚያወጡት ጠቅላላ ወጪ ከገቢያቸው 85 በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ህጉን የሚጥሱ ክለቦችም የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ይገጥማቸዋል። የጨዋታ ፍጥነትን ለመጨመርና ሰዓት ማባከንን ለመግታት በርካታ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች በይፋ ስራ ላይ ይውላሉ። በእጅ ውርወራ (Throw-in) እና በመልስ ምት (Goal-kick) ላይ ሰዓት ለሚያባክኑ ተጫዋቾች ዳኛው አምስት ሴኮንድ የሚቆጥር ሲሆን፣ ጊዜ ካለፈ እጅ ውርወራው ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣል፤ የመልስ ምት ላይ ከሆነ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ያገኛል። ሌላው ሰዓት ማባከንን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ተጫዋቾች ታክመው ከወጡ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ አንድ ደቂቃ ውጭ እንዲጠብቁ የሚያስገድደው ደንብ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሚቀየሩበት ወቅት ከሜዳ ለመውጣት የ10 ሴከንድ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ይሁንና ጊዜው ካለፈ ተቀያሪው መግባት የሚችለው ጨዋታው በሚቀጥለው ጊዜ ሲቆም ብቻ ይሆናል። በዚህ የውድድር ዘመን የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔዎችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አጠራጣሪ ከሆነ ቫር ጣልቃ የመግባት ስልጣን ተሰጥቶታል፤ እንዲሁም በጨዋታ ወቅት በቫር እና በሜዳ ላይ ዳኛው መካከል የሚደረጉ የድምፅ ውይይቶች በሊጉ የጨዋታ ማዕከል በኩል ለደጋፊዎች በቀጥታ ይፋ ይደረጋሉ። በአጠቃላይ፣ የዘንድሮው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከአዳዲስ የህግ ለውጦች፣ ከከፍተኛ የዝውውር ወጪዎች እና አዳዲስ የአሰልጣኞች ሹመት ጋር ተያይዞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን ስቧል። አርሰናል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ፣ ማንቸስተር ሲቲ ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችና ክለቦች ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ አስደሳች እና አጓጊ የእግር ኳስ ጊዜን እንደሚያሳልፉ አያጠራጥርም።
ቡሄ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ምስረታ ታሪካዊ ቁርኝት
Aug 19, 2026 716
በሙሴ መለሰ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን የቡሄ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ባለበት በዚህ ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አጀማመሩንና ምስረታውን ከዚህ በዓል ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚታወስበት ነው። የክለቡ ምስረታና የቡሄ በዓል (የሆያ ሆዬ ጨዋታ) ቀጥተኛና የማይነጠል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ክለቡ በመስረታው ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት ቀርፎ የመጀመሪያውን ማሊያ ለመግዛት የበቃው በዚህ ዕለት በተሰበሰበ የሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ነበር። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መጀመሪያ ሲጠነሰስ በጆርጅ ዱካስና በአየለ አትናሽ አማካኝነት የነበረ ቢሆንም፣ ክለቡን በይፋ አደራጅቶ ለማቋቋም ግን የግድ የፋይናንስ አቅም ወይም ገንዘብ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ግን በሃገር ፍቅር ስሜት የተነሱት ዘጠኙ ወጣቶች ማለትም አየለ አትናሽ፣ ጆርጅ ዱካስ፣ ዮሐንስ ጥላሁን፣ ገብረመድህን ተፈሪ፣ ተፈራ ገብረእግዚአብሔር፣ ዓለማየሁ እጅጉ፣ መኮንን ደምሴ፣ አስፋው ያዕቆብ እና ክልቱ አያኖ ክለቡን በሚመሰርቱበት ወቅት ቤሳ ቤስቲን እንኳ ኪሳቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተሰብስበው በሰፊው ተወያዩ። በዚህ የውይይት ወቅት ነው ገንዘብ ለማግኘትና የክለቡን መመስረት እውን ለማድረግ የቡሄ ቀን እጅግ መልካምና ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የተረዱት። ዘጠኙ ወጣቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተው በታሪካዊው የቡሄ ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 1927 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ቡሄ ጨፍረው (ሆያ ሆዬ ብለው) በሚያገኙት ማናቸውም ነገር የክለቡን የመጀመሪያ ማሊያ ለመግዛት ቁርጥ የሆነ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በዚያን ጊዜ የነበረው የባህል ልማድ አሁን ካለው የተለየ በመሆኑ፣ ቡሄ ሲጨፈር የሚሰጠው ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ዳቦ ነበር። በመሆኑም ዘጠኙ ተጫዋቾችና መስራቾች ቀደም ሲል ከሚጨፍሩበትና ለምደውት ከነበረው አካባቢ ራቅ ብለው በመንቀሳቀስ በየቤቱ በር እያንኳኩ በደመቀ ሁኔታ ጨፈሩ፤ በዚህም ጥረታቸው በርካታ ቁጥር ያለው የሙልሙል ዳቦ በአንድነት ማሰባሰብ ቻሉ ታሪካዊውን ስራ ሰሩ። ይሁን እንጂ የተሰበሰበውን ይህንን በርካታ ዳቦ ወደ ጥሬ ገንዘብ ለመቀየር አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ሰራተኛ ሰፈር ለሚገኙ ወዛደሮች ለመሸጥ ዳቦውን በከረጢት ይዘው ጉዟቸውን ጀመሩ። በዚህ የጉዞ መስመር ላይ ሳሉ ግን ያልተጠበቀ ፈተና ገጠማቸው፤ በመንገድ ላይ ያገኟቸው “ዱርዬዎች” ከተሰበሰበው ዳቦ ላይ የተወሰነውን ነጠቋቸው። ወጣቶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዟቸውን በመቀጠል የተረፈውን ዳቦ ለሰራተኛ ሰፈሩ ወዛደሮች በመሸጥ ማሊያ መግዣ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው አስገቡ። ከዳቦው ሽያጭ የተገኘችው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በወቅቱ መገበያያ በትክክል ሁለት ጠገራ ብር ነበረች። የክለባችው የመጀመሪያ መለያ ቡናና ነጭ ነበር። ቡናና ነጭ መሊያን የገዙት ግን ፈልገው አልነበረም በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው በሁለት ጠገራ ብር ከፒያሳ «ግሪካዊ አውግስታስ ዱስ» ከተባለ ሱቅ በርካሽ ስላገኙት ነበር። ይህ በቡሄ ዕለት የተጀመረው ታሪካዊ የማሊያ ግዢ በኋላ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም. በይፋ ተመሠረተ። ክለቡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ማዕረግንና ቀዳሚነትን ተቀዳጀ። በ1928 ዓ.ም. በይፋ የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ ያደረገው ከ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ነበር። በዚሁ ታሪካዊ የመጀመሪያ ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበረው የ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ ሲያመራ፣ አስቀድመው ከተመረጡትና ቡድኑን ካደራጁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ባልታወቀ ምክንያት ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ድንገተኛ መቅረት ምክንያት ቡድኑ በሰው ጎደሎ ለመጫወት በተገደደበት ወሳኝ ሰዓት፣ መስራቾቹ በሜዳው አቅራቢያ መንገድ ላይ ሲጫወት ያገኙትን አንድ ታዳጊ ወጣት ተመለከቱ። ይህ ታዳጊ በወቅቱ ገና የ14 ዓመት ዕድሜ የነበረውና በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የሆነው ይድነቃቸው ተሰማ ነበር። ወጣቶቹም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ቡድኑን እንዲሞላ ድንገት ጋበዙት፤ እርሱም የቀረበለትን ጥሪ በደስታ ተቀብሎ በአጋጣሚ ወደ ሜዳ ገባ። ያለ ምንም ልምምድና ዝግጅት በድንገት የተሰለፈው ይድነቃቸው ተሰማ፣ በሜዳ ላይ ያሳየው አስደናቂ ችሎታና ቅልጥፍና ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፣ ለክለቡ የመጀመሪያውን ድል ያስገኙትን ሁለቱንም ታሪካዊ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ይኸው መንገድ ላይ ተገኝቶ በድንገት የተሰለፈው ታዳጊ ይድነቃቸው ነበር። ይህ ብቃት ገና በታዳጊነቱ በክለቡ ውስጥ ያለውን የማይተካ ቦታ ከማረጋገጡም በላይ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን የድል ጉዞ በደመቀ ሁኔታ እንዲጀመር አድርጓል። ቡሄ በዓል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያላቸው ታሪካዊ ቁርኝት የክለቡን ጥልቅ ህዝባዊና ባህላዊ መሰረት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ ፋና ወጊ የሆነው ይህ ታላቅ ክለብ፣ በታሪካዊቷ የነሐሴ 13 ቀን የቡሄ ዕለት የመስራቾቹ የ"ሆያ ሆዬ" ጨዋታና ከተሰበሰበው ሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ባገኟት ሁለት ጠገራ ብር የመጀመሪያውን ቡኒና ነጭ ማሊያ መግዛቱ፣ ክለቡ ከህዝብ ማህፀን የወጣ የህዝብ ሀብት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ከባህልና ከትውፊት ጋር የተቆራኘ አስደናቂ አጀማመር፣ ከጊዜ በኋላ በ1928 ዓ.ም. ለይፋዊ ምስረታው በር ከፋች ከመሆኑም በላይ፣ በታሪካዊው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ታላላቅ መሪዎችና ድንቅ ተሰጥኦዎች እንዲፈጠሩ መሰረት የጣለ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።
ትንታኔዎች
ለኢትዮጵያ የቤት ልማት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ስምምነት
Sep 4, 2026 124
የኢትዮጵያ የከተሞች ዕድገት ፈጣን እየሆነ በመምጣቱ እና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመሄዱ፣የዜጎችን የቤት ባለቤትነትን ጥያቄ በዘላቂነት መመለስ የመንግሥት አንዱ ዋና የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል። ባለፉት ዓመታት የነበረው የቤት አቅርቦት በመንግሥት ትከሻ ላይ ብቻ የወደቀ በመሆኑ፣ ካለው ሰፊ የሕዝብ ፍላጎት ጋር አብሮ ለመሄድ ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል። ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት አዲስ የቤት ልማት ፖሊሲ ቀርጾ በካቢኔ ማጽደቁ ይታወቃል። ፖሊሲው የዕድገቱን ፍጥነት እና የከተሞችን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ ነው። በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የኮንስትራክሽንና የከተማ ልማት ሥራዎች ለዚህ ሰፊ ራዕይ ግልጽ ማሳያዎች ናቸው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ በመላ ሀገሪቱ 1.2 ሚሊዮን ቤቶችን መገንባት መቻሉን አስታውሰዋል። ይህንኑ ስኬት መሠረት በማድረግ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 1.5 ሚሊዮን አዳዲስ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት መንግሥት አጠቃላይ ዝግጅት አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። አሁን ላይ አዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂንና የረጅም ጊዜ የቤት ብድር ሥርዓትን በማስተዋወቅ የዜጎችን የቤት ባለቤትነት ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስ እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አዲሱ የቤት ልማት ፖሊሲ ተቀርጾ በካቢኔ መጽደቁንና በሁሉም ክልሎች የተቀናጀ ንቅናቄ መጀመሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ግንባታው በመንግሥት በጀት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ የግሉ ዘርፍ እንዲሁም የመንግሥትና የግል አጋርነት መዋቅሮችን በስፋት መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የዜጎችን የመግዛት አቅም ያገናዘበና ፍላጎታቸውን የሚያስተናግድ አዲስ የፋይናንስ አሠራር መፈጠሩን ጠቅሰው፤ሰዎች ቤት በቀጥታ መግዛት ካልቻሉ በመንግሥት በሚመቻቸው አዲስ የሞርጌጅ ሥርዓት አማካኝነት ከገቢያቸው ላይ እየከፈሉ በረጅም ጊዜ ሂደት የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ዕድል ይፈጠራል ብለዋል። ይህ ግብ የዜጎችን የቤት ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ የግሉን ዘርፍ በስፋት በማሳተፍ የሚሳካ መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል። የሞርጌጅ ሥርዓት የቤት ፍላጎትን ለማሟላት የቀረበ ሌላኛው አማራጭ ሆኗል። የቤት መግዣ ብድር ሥርዓት (ሞርጌጅ) ማለት አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከባንክ በብድር አግኝቶ፣ ያንን የተበደረውን ገንዘብ ከነወለዱ በረጅም ዓመታት መልሶ የሚከፍልበት የፋይናንስ አሠራር ነው። ይህ አሠራር አቅማቸው ውስን ለሆኑ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በወር በወር እየከፈሉ የቤት ባለቤት የመሆን ልዩ ዕድል ይፈጥራል። የከፍተኛ የቤት ኪራይ ወጪን በማስቀረት ዜጎች በየወሩ የሚከፍሉት ገንዘብ በራሳቸው ንብረት ላይ የሚደረግ ጠቃሚ ኢንቨስትመንት እንዲሆን ያደርጋል። ይህንን ታላቅ ራዕይ ከግብ ለማድረስ በዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መካከል በሀገሪቱ የመጀመሪያው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ተፈጽሟል። በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅዖ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፉ ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ገልጸዋል። ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት የተቀመጠውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን እንደምትቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማክታር ዲዮፕ በሰጡት አስተያየት፣ ይህ አጋርነት በኢትዮጵያ የከተሞች ልማት ላይ የግል ባለሀብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ትልቅ ምቹ ምህዳር እንደሚፈጥር ገልጸዋል። ጠንካራ የቤት ፋይናንስ ገበያ የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ቁልፍ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ እንዲጀመር እንዲሁም ሂደቱ ላይ ክትትል በማድረግ እያከናወኑት ላለው ሥራና አመራር ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዚህ የፋይናንስ ማዕቀፍ አማካኝነት ዜጎች ሙሉ የቤት መግዣ ገንዘብ እስኪኖራቸው ሳይጠብቁ በባንክ ብድር የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ይደረጋል።ግንባታው በመንግሥት በጀት ብቻ ሳይሆን በመንግሥት፣ በግል ዘርፍ፣ እንዲሁም በመንግሥትና በግል አጋርነት (PPP) ይከናወናል። የሞርጌጅ ፋይናንስ ሥርዓቱ የዜጎችን ማህበራዊ ዋስትና በማረጋገጥ የባለቤትነት ስሜት ከመፍጠር አኳያ ያለው ፋይዳ ቁልፍ የሚባል ነው። መንግሥት ብቻውን ሊያከናውነው የሚችለውን ግዙፍ የልማት ጫና፣የግሉን ዘርፍ እና ዓለም አቀፍ አጋሮችን በማስተባበር በጋራ መወጣት እንደሚቻል የዛሬው ስምምነት ግልጽ ማሳያ ነው። የ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ፈንድ እና የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ዕቅድ እውን መሆን፣ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ጉዞ የሚያፋጥንና ሁሉንም ዜጎች አካታች የልማት ባለቤት የሚያደርግ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
የኮሪደር ልማት እና የነገዋ ኢትዮጵያ
Sep 4, 2026 98
በኢትዮጵያ አሁን ላይ በተለያዩ መስኮች እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች መጻኢውን ጊዜ ብሩህ ለማድረግ መሰረት የሚጥሉ ናቸው። ከእነዚህ ስራዎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የሀገሪቱን ከተሞች ገጽታና የነዋሪዎቿን የኑሮ ዘይቤ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረ ያለው የኮሪደር ልማት መርሃ ግብር ነው። ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከተሞችን ለኑሮ ምቹ፣ ንጹህና ስልጡን በማድረግ ትልቅ ምዕራፍ ከፍቷል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበው ስኬትና የፈጠረው አርአያነት አሁን ላይ አዲስ አበባን አልፎ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ተግባራዊ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ የኮሪደር ልማት ከከተማ ውበትና ገጽታ ባለፈ የሀገሪቱን የዕድገት አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረ ያለ እና የነገዋን ሀገር ዛሬ ላይ የመቅረጽ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። በኮሪደር ልማቱ ለእግረኛ እና ለአካል ጉዳተኞች ፈታኝ የነበሩ መንገዶች ዛሬ ሰፊና ጥራት ባላቸው የኮንክሪት ንጣፎችና የብስክሌት መስመሮች ተተክተዋል። በከተሞች የሚገኙ የመዝናኛ ፓርኮች፣ የማረፊያ ስፍራዎች እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ቦታዎች የዜጎችን ማኅበራዊና ሰብአዊ ክብር ከፍ ያደረጉ ሲሆን፤ እነዚህ ጥራት ያላቸው መሠረተ-ልማቶች የነገውን ጤናማ እና ማህበራዊ ፍትሕ የሰፈነበት ማህበረሰብ ለመፍጠር የተጣሉ ጠንካራ መሠረቶች ናቸው። የኮሪደር ልማት የከተሞችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወደ ዘመናዊነት በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በዘመናዊ የጎዳና ላይ መብራቶችና የደህንነት ካሜራዎች የታገዙ ከተሞች በቀን ብቻ ሳይሆን በሌሊትም የንግድና የኢኮኖሚ ማዕከል እንዲሆኑ በር በመክፈታቸው፣ የ24 ሰዓት የስራ ባህልን በመፍጠር ለአያሌ ወጣቶችና አነስተኛ ነጋዴዎች አዲስ የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። በሌላ በኩል፣ ይህ ስትራቴጂካዊ ልማት ኢትዮጵያን ወደ ቋሚ የኮንፈረንስ፣ የንግድ እና የባህል ቱሪዝም መዳረሻነት እየቀየራትም ይገኛል። በተለይም የከተሞችን ማህበራዊ መስተጋብርና የሕዝቡን አንድነት በማጠናከር ረገድ የኮሪደር ልማቱ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ ነው። በልማቱ የተፈጠረው የጋራ ትስስር የነገዋን ጠንካራ፣ ሰላማዊና በአብሮነት የታነጸች ሀገር ለመገንባት እንደ ትልቅ ማህበራዊ መሰረት ያገለግላል። የነገዋ ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም ያደገችና አሰራሯ የዘመነ መሆኑን የሚያረጋግጥ ተግባራዊ እርምጃ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተሳስሮ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። ስራው ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በቅንጅት በማከናወን ዘመናዊ የትራፊክ ቁጥጥር ሥርዓቶች እና የስማርት ከተማ መተግበሪያዎች መሰረተ ልማት አብሮ እየተዘረጋ ይገኛል። በተጨማሪም ከኮሪደር ልማት ጋር እየተከናወነ ያለው መጠነ ሰፊ የአረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዞች ዳርቻ ልማቶች ከተሞች ከአየር ንብረት ለውጥ ስጋትና ሙቀት በመከላከል ለትውልዱ ንጹህና ጽዱ መኖሪያን አካባቢን ለማስረከብና ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት እያስቻለ ነው። በአጠቃላይ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከአንድ ከተማ ገጽታ ማሻሻል ባሻገር፣ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ በርካታ ክልል ከተሞች ላይ በመስፋፋት ሀገራዊ ለውጥ ፈጥሯል ማለት ያስችላል። የዚህ ዘርፈ ብዙ የልማት ፍሬ ዛሬ ላይ የኑሮ ዘይቤን እያሻሻለ እንደሚገኘው ሁሉ፣ ለወደፊቱ ትውልድም የኩራት ምንጭ የሆነ ዘላቂ ሀብት ሆኖ ይሸጋገራል። ዛሬ በጥራትና ውብ ሆነው እየተሰሩ ያሉ መንገዶች፣ ዘመናዊ መናፈሻዎች፣ የህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶች የነገዋ ኢትዮጵያ የበለጸገች፣ ስልጡንና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ራዕይን እውን የሚያደርጉ ናቸው።
የተኪ ምርት ስትራቴጂካዊ ሚና
Sep 3, 2026 129
የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እና የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን መዛባት በዘላቂነት ለመቅረፍ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ እያካሄደ ይገኛል። ይህ የተኪ ምርት ስራ ጅማሮ በዋናነት ያነጣጠረው በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬን በሀገር ውስጥ በማስቀረት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ላይ ነው። ቀደም ሲል የነበሩ የተበታተኑ የማምረት ሙከራዎችን ወደ ተቋማዊ አሰራር ለመቀየር ይፋዊ የተኪ ምርት ስትራቴጂ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ጸድቆ ወደ ስራ ገብቷል። ይህ ስትራቴጂ ለቀጣዮቹ አስር ዓመታት የሚቆይ ፍኖተ ካርታ ያስቀመጠ ሲሆን፣ ለትግበራው መፋጠን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ እንደ ትልቅ ሞተር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። ሀገራዊ ንቅናቄው በ2016 ዓ.ም ተግባራዊ መሆን ለጀመረው ብሔራዊ የተኪ ምርት ስትራቴጂ ትልቅ አቅም የፈጠረ ነው። የስትራቴጂው መውጣት እና ወደ ተግባር መግባት በሀገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ማስገኘት ጀምሯል። ትልቁ እና ዋነኛው ፋይዳም የውጭ ምንዛሬን ማዳን ሲሆን በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ በተመረቱ ተኪ ምርቶች ከ5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ አምራቾች በገበያ ላይ ያላቸው የምርት ድርሻ ወደ 45 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ የፋብሪካዎች አማካይ የማምረት አቅምም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ብሏል። ይህ መነቃቃት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ከመሆኑም በላይ የፋብሪካዎችን የጥሬ ዕቃ ፍላጎት ከሀገር ውስጥ የግብርና እና የማዕድን ምርቶች ጋር በማስተሳሰር የአቅርቦት ሰንሰለቱን አጠናክሮታል። ይህንኑ ሀገራዊ ጥረት እና የተመዘገቡ ስኬቶችን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ መድረኮች ላይ የዘርፉን ስልታዊ ጠቀሜታ በተደጋጋሚ አንስተዋል። በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የምግብ እና የማዳበሪያ አቅርቦት መስተጓጎል በመጥቀስ፣ የሀገር ውስጥ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት ኢትዮጵያን የምግብ እጥረት እንደታደጋት ገልጸዋል። ተኪ ምርት ለኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነት እና የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ቀደም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ይወጣባቸው የነበሩ የድንጋይ ከሰል እና የችፑድ ምርቶች አሁን ላይ በሀገር ውስጥ በስፋት እየተመረቱ መሆናቸውን አንስተዋል። የሀገር ውስጥ አምራቾች ጥራትን መሰረት አድርገው በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከተኪ ምርት ስራዎች ያገኘውን ስኬት ይበልጥ ለማስፋት እና ዘላቂ ለማድረግ አዳዲስ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን እና ግቦችን አስቀምጧል። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተያዘው አዲስ በጀት ዓመት የሀገር ውስጥ አምራቾችን የገበያ ድርሻ ወደ 49 ለማድረስ እና የውጭ ምንዛሬ ቁጠባውን ወደ 7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። ለዚህም ስኬት አምራቾች ጥሬ ዕቃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ እና ምርቶቻቸውን ያለ ደላላ ለገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችል የዲጂታል የገበያ ትስስር ፕላትፎርም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ይፋ ተደርጓል። ወደፊትም ከቀላል የሸማች ዕቃዎች ባለፈ እንደ ተሽከርካሪዎች፣ ኬሚካሎች እና ብረታብረት ያሉ አስራ አምስት ስልታዊ የከባድ ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ትኩረት የሚደረግ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመተካት ባለፈ የማኑፋክቸሪንግ ወጪ ንግድ ገቢን በማሳደግ ኢትዮጵያን በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ላይ ተወዳዳሪ የማድረግ ሰፊ ራዕይ ተሰንቋል። በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የተኪ ምርት ስራ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ መዋቅር ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሀገር ውስጥ ምርታማነት እያሸጋገረ የሚገኝ ስልታዊ እርምጃም ነው። በጥናት የተለዩት 96 ቁልፍ ስልታዊ ምርቶች በሙሉ አቅም ወደ ማምረት መሸጋገራቸው ለሀገር በቀል እውቀትና ለፈጠራ ስራዎች ሰፊ በር ከመክፈቱም በላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ላይ ያላትን የድርድር እና የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም በእጅጉ ያጠናክረዋል።
የቀይ ባህር ደህንነት እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ሚና
Aug 29, 2026 812
(በሙሴ መለሰ) በቀይ ባሕርና በኤደን ባሕረ-ሰላጤ ቀጣናዊ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ ኢትዮጵያ የሚኖራት ሚና ከፍተኛ ነው። የኢትዮጵያ አብዛኛው ወጪና ገቢ ሸቀጦች በባህር በር በኩል የሚተላለፉ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የሚከሰቱ የፀጥታ መደፍረሶች ወይም የሎጂስቲክስ መስተጓጎሎች በቀጥታ በሀገሪቱ ብሔራዊ ኢኮኖሚ ላይ የራሱን ተጽዕኖ ማሳረፉ የማይቀር ነው። በሆርሙዝ ሰርጥ የተከሰተውን የጸጥታ ቸግር ተከትሎ የተለያዩ የዓለም ሃገራት የቀይባህር መስመር ከባቤል ሜንደብ እስከ ስዊዝ ቦይ ድረስ ያለው ደህንነት አሳስቧቸዋል። ይሄንን ስጋት ለማቃለልም ሆነ የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን መነሻ በማድረግ አንዳንድ ሃገራት በቀጣናው ካሉ የባህር ተጋሪ መንግስታት ጋር በመሆን የመሰረቷቸውን የጦር ሰፈሮች ቢያጠናክሩም አሁንም ቀጣናው በባህር ላይ ውንብድና፣ በህገ-ወጥ ንግድና የሰዎች ዝውውር ወንጀል ለስጋት የተጋለጠ ሆኖ ይገኛል። የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ከቀይ ባህር ደህንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ መሆኑን በጽኑ የምታምነው ኢትዮጵያ፣ ድንበር ተሻጋሪ የፀጥታ ስጋቶችን ለመከላከል በሚደረጉ የባለብዙ ወገን ውይይቶች ላይ በመሳተፍ የበኩሏን አስተዋጽኦ ታበረክታለች። በተለይም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የጦር መሳሪያ እና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን እንዲሁም የባህር ላይ ወንጀሎችን በጋራ ለመመከት የቀጣናው ሀገራት የተቀናጀ ምላሽ እንዲኖራቸው ድጋፍ ታደርጋለች። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር ያላት መልክዐ ምድራዊ ትስስር እና የፀጥታ አጋርነት በቀይ ባህር ቀጣና መረጋጋት ውስጥ ወሳኝ ድርሻ አለው። በቀጣናው የሚከሰቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች እና የጸጥታ ችግሮች በቀጥታ በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የትብብር አማራጭን ተከትላ እየሰራች ትገኛለች። የአፍሪካ ቀንድና የቀይባሕር ደኅንነት ሊለያዩ የማይችሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛቷ፣ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋና በጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጧ በቀጣናው ትልቅ ድርሻ ያላት በመሆኑ፣ በሚደረጉ የማሪታይምና የደኅንነት ውይይቶች ላይ የምታደርገው ንቁ ተሳትፎ ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሰፊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚዊ ተጽዕኖ በመጠቀም፣ ስትራቴጂያዊ የንግድ መስመሮችን ከስጋት ነፃ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑ በቅርቡ በናይሮቢ በተካሄደው ዓለም አቀፍ መድረክ በግልጽ ታይቷል። በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው አምስተኛው የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ የባህር ላይ ህግ ማስከበር ውይይት (Maritime Law Enforcement Dialogue) ላይ፣ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አገራዊና ቀጣናዊ ጥቅሞችን የሚያስጠብቅ ተሳትፎ አድርጓል። ይህም ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና የኢኮኖሚ ትስስር ላይ ያላትን ሚና እና ባለቤትነት አሳይቷል። ለኢትዮጵያ የባህር በር ደህንነት የህልውና ጉዳይ ነው። በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ተወካይ ካፒቴን ክብሩ መስፍን እንደገለጹት፣ የባሕር ላይ ሰላም መደፍረስ በቀጥታ የአገሪቱን ብሔራዊ ኢኮኖሚ ይነካል። አብዛኛው የሀገሪቱ ወጪና ገቢ ንግድ በባህር ላይ የሚካሄድ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር ላይ የሚከሰቱ የባሕር ላይ ውንብድናዎችና ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች የንግድ ፍሰቱን እንዳያስተጓጉሉ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ካፒቴን ክብሩ አክለውም፣ የመርከቦች መድን ዋስትና መናርና የሸቀጦች መዘግየት የሀገሪቱን የንግድ ተወዳዳሪነት እንዳይፈታተኑ፣ ጠንካራና የተቀናጀ የባህር ላይ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህን ዓለም አቀፋዊ ስጋትን ለመመከት ኢትዮጵያ የጋራ መፍትሔዎችን በማቅረብ ረገድ ግንባር ቀደም ናት። በተለይም ከጎረቤት አገራት ጋር በመቀናጀት "ብሔራዊ የማሪታይም መረጃ ማዕከል" (National Maritime Information Centre) ለመመስረት ያቀደችው ስትራቴጂ፣ ሀገሪቱ ለቀጣናው መረጋጋት ያላትን የረጅም ጊዜ ራዕይ የሚያሳይ ነው። መረጃን በጋራ መለዋወጥና የተቀናጀ የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ለዚህ ስኬት ዋነኛው መሳሪያ እንደሆነ ኢትዮጵያ በጽኑ ታምናለች። በቀይ ባህርና በኤደን ባህረ-ሰላጤ የሚስተዋሉ እንደ ሕገ-ወጥ የሰዎችና የዕፅ ዝውውር እንዲሁም ሕገ-ወጥ አሳ ማጥመድ ያሉ ስጋቶች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ቀጣናዊ ኃይሎች ተሳትፎ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ትኩረት ስቧል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል ጉዳዮች ቢሮ (UNODC) የቀጣናው አስተባባሪ ሞስታፋ ኤልባና እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላት የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አስተማማኝና የተረጋጉ እንዲሆኑ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በቀይ ባህር ቀጣና ያላትን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ለማስጠበቅና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ዲፕሎማሲያዊና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል ጉዳዮች ቢሮ (UNODC)፣ ኢንተርፖል እና ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅርበት በመሥራት ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና ጸጥታ ላይ ያላትን የመሪነት ሚና በታሪካዊ ኃላፊነትና በሕግ አግባብ እያስጠበቀች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የባህር ኃሃይልን ጨምሮ በጥብቅ ዲሲፕሊኑ እና በመፈጸም አቅሙ የሚታወቅ ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ገንብታለች። ይሄ ሰራዊት በተለያየ ጊዜ ችግር ላጋጠማቸው ሃገራት ባሳየው የሰላም ማስከበር ሚናው በውጤታማነቱ የተመሰከረለትም ነው። የቀጣናውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሃይል አስፈላጊ ስለሆነም በቅርብም በሩቅም ያሉ ሃገራት የኢትዮጵያን የባህር ላይ ህልውና በበጎ ይመለከቱታል። ለዚህም በቅርቡ በአንድ የሃገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ የባብኤል ሜንደብን እና የቀጣናውን ሰላም ለማስጠበቅ ሃገራቸው በቂ አቅም ስለሌላት የሌሎች እገዛ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት የጅቡቲ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ፋይናስ ሚኒስትር ኢሊያስ ሙሳ ዳዋሌህ ገለጻ አንዱ ማሳያ ነው። እነዚህ ሁሉ ጉዳዮች አመላካች የሚሆኑት ያለ አግባብ ከባህሩ የተገፋችውና መብቷን የምትጠይቀው ኢትዮጵያ ያላት ዘርፈ ብዙ ዓቅም ለቀጣናውም ለራሷም ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ወሳኝ ሚና ያላት መሆኑን ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 12634
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 22114
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15147
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20888
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 959
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው። በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የአረቡ ዓለም ከግብፅ ምን አተረፈ?
Aug 19, 2026 811
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አካሄድ በታሪካዊ እውነታዎች እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ እየተመሠረተ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ጊዜ ያለፈባቸው የጂኦ ፖለቲካዊ የመጠላለፍ አካሄዶች ዋጋ ቢስነትና ጥቅም አልባነት በግልጽ እየታየ ይገኛል። ለብዙ አስርት ዓመታት ግብፅ የዓረብ ሊግን ለራሷ ጠባብ ፍላጎቶች እና ጂኦፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያነት በሰፊው ስትጠቀምበት ቆይታለች። ሆኖም ይህ ጥቅምና ጉዳትን ብቻ መሰረት ያደረገ ግንኙነት አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ የዓረቡ ዓለም ከግብፅ በምላሹ ያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ ምንም የሚል ነው ሲል “What Has the Arab World Gained from Egypt? Why Ethiopia Belongs in the Arab League?” ፀሐፊው እና በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት የሚተነትነው አስተያየት የሚሰጠው ጅብሪል ላሞ በኢዜአ እንግሊዘኛ ገጽ ባሳፈረው ሐተታ ላይ ፣ የግብጽ ፖሊሲዎች እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው አምባገነናዊ አስተዳደር የጋራ ጥንካሬን ከመፍጠር ይልቅ የቀጣናውን አለመረጋጋት ማባባሳቸውን ገልጿል። እነዚህ ፖሊሲዎች፣ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር አካባቢም ውጥረትን እያባባሱ እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካባቢዎች ለዓረቡ ዓለም የራቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ለዓረቡ ዓለም ደኅንነት፣ የባሕር ንግድ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ናቸው። የግብፅ ከፋፋይ ቀጣናዊ አካሄድ ከታዩባቸው ጉልህ ማሳያዎች አንዱ በኤርትራ ጉዳይ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ላይ የነበራት ታሪካዊ ጣልቃ ገብነት ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለመግታት በግብጽ ታስበው የተደራጁ ተገንጣይ ኃይሎችን እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ትደግፍ እንደነበረ ፀሐፊው አውስቷል። ከኢትዮጵያ የኤርትራ መገንጠል በምሥራቅ አፍሪካ ቀውስ የተሞላ ታሪክ ውስጥ አቢይ ክስተት ሲሆን፣ የውጭ ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች የሀገራትን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚያናጉ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዲፕሎማሲ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም ታስቦ የተዘረጋውን የኤርትራን የመገንጠል ፕሮጀክት በመደገፍና በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው። በተጨማሪም ግብጽ በደቡባዊ የቀይ ባህር ቀጣና የምታካሂደው ቀውስ የመፍጠር እንቅስቃሴ፣ ለዓለም አቀፍ የባህር ንግድና ለቀጣናው ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል። በባብ-ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ ውጥረቶችን በመቀስቀስ እና ተላላኪ ታጣቂ ቡድኖችን በማንቀሳቀስ፣ ወሳኝ የሆኑ የባህር መተላለፊያዎችን የጂኦፖለቲካዊ ግጭት መድረክ አድርጋዋለች። ይህም ለጠቅላላው የዓረብ ዓለም የኢነርጂና የምግብ አቅርቦት መሰረት የሆነውን የደህንነት መዋቅር አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ሲሉ ጅብሪል ላሞ ያብራራሉ። ጅብሪል ላሞ በጽሑፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ የግብፅ ግልጽ የራስ ወዳድነት እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን የሚፈጥሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ መቀላቀል ግን ለዓረቡ ዓለም እጅግ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ለውጥ አምጪ ዕድል ይዞ ይመጣል። በመደመር ፍልስፍና አሳታፊ ማዕቀፍ ሥር፣ ኢትዮጵያ ከማግለል ፖሊሲ ይልቅ የዓረቡን ዓለም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተሳሰር የሚያስችል የላቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት። በዚህም የአፍሪካ ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመቅረጽ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ታካፍላለች። የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ የመቀላቀል ጥረት ጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን፣ የተፈጥሮ የታሪክ ጥሪ ነው። ከ135 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጥልቅ የሥልጣኔ መሠረት ያላት ይህች የቀይ ባሕር ሀገር፣ አባልነቷ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያላት ቁርኝት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በጋራ ታሪክ፣ ባህል እና የደም ትስስር ላይ የተገነባ ነው። እንደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጥናቶች በታሪክ ደረጃ ከመካከለኛው እና ከቅርብ ምሥራቅ ታሪክ (Near Eastern Studies) ተመድቦ መጠናቱ፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከቀጣናው ጋር ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ውህደት የሚያረጋግጥ ሕያው ማሳያ ነው። የባብ-ኤል-ማንደብ የባህር ወሽመጥ በጭራሽ መሰናክል አልነበረም፤ ይልቁንም ንግድን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን በቀይ ባሕር በኩል ያገናኘ ዋንኛ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል። ከንጉሥ አብረሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች መካከል የጋራ የደም ትስስር እንደነበር የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የስነ ህይወት( ጄኔቲክስ) ጥናቶች፣ የዚህን ታሪካዊ ቁርኝት እውነተኛነት በግልጽ ያሳያሉ። በቋንቋና በባህል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው። የሀገሪቱ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ውርስ ከዓረብኛ፣ አራማይክና ዕብራይስጥ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በአረቢያ ልሳነ-ምድር መካከል ያለውን ጥልቅ የጋራ የሥልጣኔ ቁርኝት ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ተስደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ ማግኘታቸው የእስልምናን ህልውና የታደገ ታሪካዊ ክስተት ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱን ከዓረቡ ዓለም ጋር በጽኑ አስተሳስሯታል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዓረብ ሊግን በኢትዮጵያ ላይ እንደ ተቋማዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ መሣሪያ ግብጽ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ግብፅ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ዕድገት፣ የህዳሴውን ግድብም ሆነ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ሥጋት በሚያይ ጊዜ ያለፈበት ስሌት ላይ የተመሠረተ ነው። ግብፅ የራሷን የውሃ አቋም በሊጉ ላይ በመጫን፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጋለች። ጅብሪል ላሞ እንዳመለከተው፣ ከግብጽ የአግላይነት ፖሊሲ ይልቅ የዘመኑ ነባራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ትብብርን የሚጠይቁ ናቸው። በመደመር መርህ፣ ኢትዮጵያ ለዓረቡ ዓለም ለዘመናት ከቆዩ የጥላቻ መንገዶች በላቀ ሁኔታ የተሻሉ ጥቅሞችን ማቅረብ ትችላለች። እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ እና የአረንጓዴ ኃይል አቅሟ፣ ኢትዮጵያን ለቀይ ባህር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ አድርጓታል። የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የውሃ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ሥጋት በተጋረጠበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የውሃ ሀበት እና ለም መሬት ለቀጣናው ወሳኝ የግብርና-ኢንዱስትሪ አጋር ያደርጋታል። የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ብሔረተኝነት በመሻገር፣ የቀይ ባህርን ቀጣና የሥልጣኔ እውነታ መቀበል ይኖርባቸዋል። አረብ ሊግ እንደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ እና ሞሪታኒያ አባል ሀገራት መያዙ፣ ስብስቡ የተለያዩ ቀጣናዊ እውነታዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያሳያሉ። የዓረብ ሊግ ሙሉ አባልነት የኢትዮጵያን አፍሪካዊ ማንነት ሳይቀንሰው፣ አህጉሩን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የሚያገናኝ ዋነኛ ድልድይ የሚያደርጋት በመሆኑ፤ ሊጉ የኢትዮጵያን አጋርነት በመቀበል ለአዲስ አበባ ተገቢውንና ሕጋዊ ቦታዋን የሚሰጥበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ ጅብሪል ላሞ ፅሁፉን ቋጭቷል።