የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 የውድድር ዓመት ኮከቦች ሽልማት ሊያበረክት ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 የውድድር ዓመት ኮከቦች ሽልማት ሊያበረክት ነው
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 ዓ.ም የውድድር ዓመት ምርጦች ዕውቅና የመስጠት መርሐ ግብር ጳጉሜን 3 እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ፣ የወንዶች ከፍተኛ ሊግ፣ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ፣ የሊግ አንድ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ አሰልጣኝ፣ ኮከብ ግብ ጠባቂ፣ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ እንዲሁም ምስጉን ዳኛ እና ረዳት ዳኞች ሽልማት ይበረከታል።
የሽልማት ስነ ሥርዓቱ የሚካሄድበት ቦታ በቀጣይ እንደሚገለጽ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።