ቀጥታ፡

በሕገ-ወጡ ሕወሓት ቡድን የሚደርስብንን ግፍ ለማስቆም የጀመርነውን ትግል እናጠናክራለን - የትግራይ ክልል ተወላጆች

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ በትግራይ ክልል ሕገ-ወጡ ሕወሓት እያደረሰ ያለውን ግፍና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ለማስቆም በቡድኑ ላይ የጀመርነውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የክልሉ ተወላጆች ገለጹ።

በአሁኑ ወቅት ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የክልሉን ወጣቶች ለሌላ አሳልፎ መሸጥን ጨምሮ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ በማካሄድ ከፍተኛ ግፍና መከራ እያደረሰ ይገኛል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የክልሉ ተወላጆች መካከል አቶ ኹሉፍ አጽአሊ እንደገለጹት፣ በትግራይ ክልል ወጣቶች ወደ ማይፈልጉት ጦርነት እንዲገቡ እየተገደዱ ነው።

ወጣቶች ይህንን -ሰብዓዊ ድርጊት በመሸሽ ከትውልድ ቀያቸው በመውጣት ወደ ባሕርና በረሃ እየገቡ መሆኑንም ገልጸዋል።

በመሆኑም እኛ አንድነታችንን በማጠናከር ሕገ ወጡ ሕወሓት እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ማስቆም አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ለምለም ሳሙኤል በበኩላቸው፤ በሕገ ወጡ ቡድን ምክንያት የትግራይ ክልል እናቶች በለቅሶና መከራ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ በጣም -ሰብአዊ መሆኑን በመግለጽ ሕገ ወጡን ቡድን ለማስወገድ የተጀመረውን ትግል ማጠናከር አለብን ያሉት ደግሞ ሌላኛው የክልሉ ተወላጅ ተካ ገብሩ ናቸው።

ሰውን ያለፍላጎቱ ለጦርነት እንዲሰማራ ማድረግ -ሰብዓዊ ድርጊት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተካ፣ ኢትዮጵያውያን የሚታወቁበት የሰብዓዊነት እሴት በክልሉ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም