ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
Sep 3, 2026 69
ባህር ዳር ነሐሴ 28/2018;(ኢዜአ) ፦ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም በርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ። ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር የፍትህ ሙዚየም መገንባቱ የህዝቡን የፍትህ እሴትና በህግ የበላይነት ከማሳየት ባሻገር ተቋማት ለለውጥ ያላቸውን መነሳሳት የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል። በሀገሪቱ የፍትህ አስተዳደር ታሪክ ለጥናትና ምርምር የሚሆኑ ሰነዶችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን የያዘ በመሆኑም ለአዲሱ ትውልድ እሴትና ተደማሪ የእውቀት ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ይሆናል ብለዋል። በመሆኑም ይሄንን ታሪካዊ አሻራ ላስቀመጡና መረጃዎችን በማሰባሰብ ለምረቃ እንዲበቃ ላደረጉ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።   የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር)፤ የሙዚየሙ መገንባት በተለይም ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ትልቅ እሴት የሚሆን ነው ብለዋል። በካታሎግና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘውን የአገራችን የፍትህ ታሪክ ተማሪዎች በቀላሉ እንዲያውቁና ለምርምር ግባአት እንዲጠቀሙበት የሚያስችል መሆኑንም አንስተዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አለምአንተ አግደው፤ ሙዚየሙ ከባህላዊ እስከ ዘመናዊ አስተዳደር የነበሩ የፍትህ ታሪኮችን ሰንዶ በመያዝ የተደራጀ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ለህግ ማሻሻያ፣ ለፖሊሲና ስትራቴጂ ቀረጻና ለሌሎችም የጥናትና ምርምር ስራዎች ትልቅ አቅምና ግብአት ይሆናል ብለዋል። በሙዚየሙ ውስጥ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩና ሌላ ቦታ በቀላሉ ሊገኙ የማይችሉ ብርቅዬ የፍትህ ሰነዶች የሚገኙበት ነው ብለዋል። እነዚህን ታሪካዊ መረጃዎች ከተለያዩ ቦታዎች ለማሰባሰብ ክልል አቀፍ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሰፊ ስራ መሰራቱን አንስተው አጠቃላይ የሙዚየሙ ግንባታ አላማ የህዝቡን የፍትህ ስርዓት ታሪክ በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ መሆኑን ተናግረዋል። በፍትሕ ሙዚየም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በሲዳማ ክልል የህዝብን የልማት ጥያቄ የመመለሱ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
Sep 3, 2026 72
ሀዋሳ፣ ነሀሴ 28/2018 (ኢዜአ) በሲዳማ ክልል የሕዝቡን የልማት ጥያቄ የሚመልሱ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ። በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ቡድን በምስራቃዊና ማዕከላዊ ሲዳማ ዞኖች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል። ርዕሰ መስተዳድሩ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ በክልሉ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ዳዬ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ ከተማዋን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ እና ተመራጭ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል። የኮሪደር ልማት ሥራው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃም አክለዋል። ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ታስቦ እየተገነባ የሚገኘውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ለማጠናቀቅም ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።   የልኡካን ቡድኑ የአርቤጎና እና የቡራ ወረዳዎችን የሚያገናኘውና በሎጊታ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የባሬ ድልድይ እንዲሁም የቡራ ወረዳ የአስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሕንፃ ግንባታ በዚሁ ወቅት ከጎበኙዋቸው የልማት ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የክልሉ መንግሥት የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና የልማት ጥያቄዎችን የሚመልሱ ፕሮጀክቶችን እውን የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በቡራ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘው የአስተዳደር ሕንፃም የመንግሥት አገልግሎትን ምቹና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለመስጠት እንደሚያስችል ነው ያመለከቱት። በቡራ ወረዳ ዳለቻ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ባንጫ ባዲሶ በበኩላቸው፣ የአርቤጎና እና ቡራ ወረዳዎችን የሚያገናኘው የባሬ ድልድይ መሠራቱ ቀደም ሲል ወንዙን ለመሻገር ይገጥም የነበረውን ችግር እንዳስቀረላቸው ተናግረዋል።   ወንዙ በሚሞላበት ወቅት በርካቶች ለመሻገር ሲሞክሩ በደራሽ ውኃ ይወሰዱ እንደነበር አስታውሰው፣ የድልድዩ ግንባታ ትልቅ እፎይታ እንደሰጣቸው ገልጸዋል። ሌላው የአርቤጎና ወረዳ ሚቂቾ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ፌኦ ሲዱ በበኩላቸው፣ የድልድዩ መገንባት ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ለማውጣትና የሚፈልጉትን ሸምተው ለመመለስ ይገጥማቸው የነበረውን ችግር እንደፈታላቸው ገልጸዋል። በጉብኝቱ ላይ የክልሉ፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ፅምዶ የጋራ ዓላማ የሌለውና የትም የማይደርስ ስብስብ ነው-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
Sep 3, 2026 71
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ፅምዶ የጋራ ዓላማ የሌለውና የትም የማይደርስ ስብስብ መሆኑን አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ በረጅም ታሪኳ በውስጥ ችግሮችም ሆነ በውጭ ጣልቃ ገብነቶች የተዳከመች ብትመስልም በጽናትና በአሸናፊነት ያለፈች ሀገር መሆኗን አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የማሳካት ጉዞዋ በየትኛውም የጥፋት ጥምረት ሊከሽፍ የማይችል ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ፅምዶ በሚል የጋራ ዓላማ በሌለው ተራ የጥፋት ኃይሎች ስብስብም ሆነ ለሌሎች ትላልቅ ኃይሎች ጫና የምትበገር ጠንካራ ሀገር አለመሆኗን ገልጸው፤ ይህ በታሪኳም ሆነ በአሁናዊ ጉዞዋ የታየ ተጨባጭ ሀቅ ነው ብለዋል። አሁን ፅምዶ በሚል የጥፋት ጥምረት የተሳሰቡት ኃይሎችም የጋራ ዓላማ የሌላቸውና አጭር ርቀት እንኳ አብረው መጓዝ የማይችሉና እርስ በርስ የሚጋጭ አጀንዳን ያነገቡ ተራ ስብስብ ናቸው ብለዋል። እነዚህ ኃይሎች ወጣቶችን በማስገደድ ለእልቂት እየዳረጉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ቆመንልሃል የሚሉትን ህዝብ ለመከራ መዳረጋቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያን ከጉዞዋ የሚያቆማት ኃይል የለም ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤እነዚህ ትናንሽና አቅመ ቢስ ቡድኖች የጀመሩት የጥፋት መንገድም የትም እንደማያደርሳቸው ጠቅሰዋል።
በትምህርት ቤቶች የተጀመሩ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Sep 3, 2026 115
ሰመራ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስና ለመቋቋም በትምህርት ቤቶች የተጀመሩ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። በአየር ንብረት ለውጥና በአካባቢ ጥበቃ ሥራ ላይ የትምህርት ቤቶችን ሚና ለማሳደግ ያለመ የውይይት መድረክ ዛሬ በሰመራ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሳ አደም እንዳሉት የአካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ሥራ ዓለም አቀፍ ትኩረት ያለው ነው። በዚህም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስና ለመቋቋም እንደ ሀገር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነሰና ለመቋቋም በክልሉ በትምህርት ቤቶች የተጀመሩ ሥራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በተለይም በክልሉ በረሃማ አካባቢዎች ለሚሰሩ የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ሥራዎች ትምህርት ቤቶች ላይ ያተኮረ ስራ በስፋት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመከላከል በትምህርት ቤቶች ከአረንጓዴ አሻራ ልማት ሥራዎች በተጨማሪ የጓሮ እርሻ ሥራዎች በቅንጅት እየተከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል። በትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ እንዲላበሱ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል። በክልሉ ከዚህ ቀደም ብዙም ያልተለመደው የጓሮ እርሻ ልማትም በአሁኑ ወቅት እየተስፋፋና በ35 ትምህርት ቤቶችም ልማቱ እየተከናወነ መሆኑን በአብነት ጠቅሰዋል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት ማሻሻል መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዮሐንሰ ወጋሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት፣ ትምህርት ቤቶች ከንድፈ ሀሳብ በተጨማሪ ተግባራዊ የመማማሪያ መስክ እንዲሆኑ ካለፉት ስድስት ዓመታት ጀምሮ በትኩረት እየተሰራ ነው። ቅድመ መደበኛን ጨምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ56 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ጠቅሰው፣ ከነዚህ ውስጥ በ24 ሺህ ትምህርት ቤቶች የጓሮ እርሻ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። የጓሮ እርሻ ማልማት የጀመሩና የተለያየ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞችን የተከሉ ትምህርት ቤቶች ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል አዎንታዊ ሚና እየተጫወቱ ናቸው ብለዋል። በመርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአይሳኢታ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ባለሙያ አቶ ፈንታው ካሳ በትምህርት ቤቶች ውስጥ በተሰሩ ሥራዎች ለውጥ መጥቷል። በትምህርት ቤቶች ባዶ በነበረ ቦታ ላይ የተለያዩ ቋሚ ተክሎችን በመተከላቸው የአካባቢው ሞቃታማ የአየር ፀባይ እየተለወጠ መምጣቱን ገልጸዋል።
የጳጉሜን ቀናት የመደመር መንግሥት ባስመዘገባቸው ውጤቶች በመታገዝ ለሌላ ስኬት በሚያዘጋጅ መልኩ ይከበራሉ - ከንቲባ ከድር ጁሃር
Sep 3, 2026 63
ድሬዳዋ ፤ ነሐሴ 28/2018(ኢዜአ) ፦ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ። ከንቲባው በጳጉሜን አምስት ቀናት በሚከናወኑ መርሃ ግብሮች፣ እቅዶችና ዝግጅቶች ዙሪያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ቀናቱ የመደመር መንግሥት ባስመዘገባቸው ውጤቶች በመታገዝ ለሌላ ስኬት በሚያዘጋጅ መልኩ በተለያዩ ተግባራት ይከበራሉ ብለዋል። በዚሁ መሠረት በጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን እስካሁን የተከናወኑ ውጤታማ ሥራዎችን በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ሁነቶች እንደሚካሔዱ ነው የገለጹት። እስካሁን የተገኙ ድሎችን በተባበረ ቅንጅት ለማስቀጠልና ቀጣይነታቸውን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ መርሃ ግብሮች የሚከበረው ደግሞ ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን ነው ብለዋል። ጳጉሜን 3 የሚከበረው የጽናት ቀን የሀገርን አንድነትና ልማት ለማጽናት ለሚተጉ የሀገር መከላከያ፣ የጸጥታና የፍትሕ ተቋማት ያለንን ደጀንነትና ድጋፍ በማረጋገጥ እንደሆነም ነው ያመለከቱት ። ጳጉሜን 4 የህብር ቀን የድሬዳዋን የመደጋገፍ፣ የመረዳዳትና ሰው ተኮር ልማቶች በሚያስቀጥሉ እንዲሁም ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ይከበራል ብለዋል። ጳጉሜን 5 የነገ ቀን ደግሞ የአዲሱ ዓመት ዋዜማ እንደመሆኑ መጠን ሀገራችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያስመዘገበች የምትገኘውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ በሚያጠናክሩ ሁነቶች እንደሚከበር ከንቲባው አስረድተዋል።
የሚታይ

መንግሥት የዜጎችን ኑሮ ማሻሻልና ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው አድርጓል - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Sep 3, 2026 87
አዲስ አበባ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ መንግሥት የዜጎችን ኑሮ ማሻሻልና ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው ማድረጉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። አገልግሎቱ መንግሥት ሃገራዊ ሪፎርሞችን በመተግበር የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገባውን ቃል ወደ ተግባር እየለወጠ ይገኛል ብሏል። ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥና የዜጎቿን ሕይወት ከፍ ለማድረግ በምታደርገው ያልተቋረጠ ርብርብ፣ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ የሚያበስሩ ታሪካዊ ምዕራፎች እውን እየሆኑ ይገኛሉ ብሏል። መንግሥት ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስልታዊ ፖሊሲዎችን በመንደፍና በመተግበር በኢኮኖሚውና በማኅበራዊው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጦችን በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ ይፋ የተደረገው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል የተደረሰው ታሪካዊ ስምምነት የዚህ አበይት ርዕይ አንዱ ማሳያ ነው ሲልም አገልግሎቱ አብራርቷል። በ100 ቢሊየን ብር ካፒታል የሚቋቋመውና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ያካተተው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ፣ በባንክ ዘርፍ ያለውን የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን በመቅረፍ ለዜጎች አስተማማኝ የፋይናንስ አቅርቦት ይፈጥራል ብሏል። አገልግሎቱ ይህ ታሪካዊ ስምምነት መንግሥት በተመጣጣኝ ዋጋ የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊየን ቤቶችን ለማቅረብ ያስቀመጠውን ግብ በግንባር ቀደምትነት የሚያሳካ መሆኑን ገልጿል። ስምምነቱ የዜጎችን የቤት ባለቤትነት ፍላጎት እውን በማድረግ ረገድ የሚታዩ ማነቆዎችን በመስበር፣ የበርካቶችን የዕለት ተዕለት ሕይወትና ማኅበራዊ ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያሻሽል የመንግሥት ቁርጠኝነትን ያረጋገጠ ቁልፍ ርምጃ መሆኑንም ጠቅሷል። ይህ ስኬት ብቻውን የቆመ አይደለም፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በሜጋ ፕሮጀክቶች የተመዘገቡት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ድሎች ቀጣይ ምዕራፍ አካል ነው። የመደመር መንግሥት የግል ዘርፉን ተሳትፎ በስፋት በማካተትና የገበያ ሥርዓቱን በማዘመን አገራዊ የኢኮኖሚ አቅምን ማጠናከር የልማት ጉዞው መሠረት አድርጎ ቀጥሏል። እንደ ሀገር እየተመዘገበ ካለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ በሚፈጠር የዋጋ ግሽበት አነስተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርሰውን ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ መንግሥት በቢሊዮኖች የሚቆጠር በጀት በመመደብ በነዳጅ፣ በመሠረታዊ ፍጆታዎች እና በግብርና ግብአቶች ላይ ከፍተኛ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል። ከዚህ የዕለት ኑሮ ማቃለያ ሥራ ባሻገር የዜጎችን ኑሮ በዘላቂነት ማሻሻልና ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎል። በዚህም ቃል በተግባር እየተለወጠ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ የመገንባት ጽኑ ፍላጎቱ በሁሉም መስክ በተግባር እየተፈጸመ ቀጥሏል ብሏል።
የመደመር መንግሥት ​የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሰሶዎች መካከል አንዱ የሆነው የቱሪዝም ዘርፍ ስኬቶች በሀረሪ ክልል
Sep 3, 2026 109
የመደመር መንግሥት ​የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሰሶዎች መካከል አንዱ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል። በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭና ትውልድን የሚሻገሩ ድሎች ማስመስገብ ከተቻለባቸው አካባቢዎች መካከል የሀረሪ ክልል ተጠቃሽ ነው። ​የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት በሰጡት ልዩ ትኩረት ዛሬን ተሻግሮ ለነገዋ ኢትዮጵያ ብልፅግና መሰረት የሚሆኑ ስራዎች ተከናውነዋል።   ከመደመር ትውልድ መፅሐፍ ሽያጭ በተገኘና የሀረሪ ክልል መንግሥት በመደበው ተጨማሪ በጀት በሀረር ከተማ እውን የተደረገው የሀረር ኢኮ ቱሪዝም ፖርክም ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው። የፓርኩ መገንባት ከዚህ ቀደም የህዝብና የጎብኚዎችን ደህንነት ባልጠበቀና የጅቦች ምቾት ባልጠበቀ መልኩ በየመንደሩ ሲካሄድ የቆየው የጅብ ትርኢት አሁን ላይ በዘመናዊ መልኩ እንዲደረግ ያስቻለ ሆኗል። ​ፓርኩ የጅብ ትርዒቱን በተደራጀ መልኩ በአንድ ማዕከል እንዲካሄድ ከማድረግም ባሻገር አገር በቀልና መድኃኒትነት ያላቸው እፅዋቶችን ጨምሮ በክልሉ እየተመናመኑ የሚገኙ አትክልቶችን አልምቶ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ የሚያስችል ነው።   የዕደ ጥበብ መሸጫ ማዕከላት፣ የመዝናኛ እና የስብሰባ አዳራሾችን በውስጡ ያካተተው የሀረር ኢኮ ቱሪዝም ፓርክ በአካባቢው ለተሰማሩ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚነት እንዲጨምር አድርጓል። ፓርኩ ከተገነባ ወዲህ ወደ ክልሉ የሚመጡ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥር ትርጉም ባለው መልኩ እንዲጨምር ከማድረጉም በተጨማሪ የጎብኚዎችን ቆይታና ከዘርፉ የሚገኘው ገቢ ማሳደግ አስችሏል። የሀረር ቀደምት የግንባታ ኪነህንፃ ጥበብን በጠበቀና አምስቱ የሀረር ጁገል መግቢያ በሮችን በሚያሳይ መልኩ እውን ተደርጓል።   ሀረር ላይ ጅብን መመገብ ለበርካታ አመታት የዘለቀ ቢሆንም የሀረር ኢኮ ቱሪዝም ፓርክ ግን ትርዒቱ በአዲስ ምዕራፍና በላቀ ምቾት እየተካሄደ የጎብኚዎች የሀሴት ምንጭና የዘርፉ ተጨማሪ አቅም ሆኗል።
በአማራ ክልል የቴክኖሎጂውን ዘርፍ ቁልፍ የእድገት መሳሪያ ለማድረግ እየተሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
Sep 3, 2026 127
ባህርዳር ፤ ነሃሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል የቴክኖሎጂውን ዘርፍ ቁልፍ የእድገትና የመወዳደሪያ መሳሪያ አድርጎ ለመጠቀም በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ። በክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ "የኤሌክትሮኒክስ መንግስት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሰረት ነው" በሚል መሪ ቃል የፓናል የውይይት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። ርዕሰ መስተዳደሩ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ በክልሉ ፈጠራና ቴክኖሎጂን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳለጫ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል። በአማራ ክልል "ዲጂታል አማራ" በሚል በ25 ዓመቱ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላይ ቴክኖሎጂ እንደ ልማት መዳረሻ መፍጠሪያ ተደርጎ ተይዟል ብለዋል። በ25 ዓመቱ ስትራቴጂክ ግብ ላይ በ2042 የአማራ ክልል ዋነኛ ሀብት፤ የአገልግሎት መስጫ እና የኢኮኖሚ የዕድገት ምንጭ ቴክኖሎጂ እንዲሆን ይሠራል ነው ያሉት። በዚህም ዘርፉን የሚመራውን ተቋም በአዲስ በማደራጀት፣ አሰራሮችን በመዘርጋትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን አስረድተዋል። በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን የታገዘ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት ያስቻለ ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል። በቀጣይም ተቋማት ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የማምረትና አገልግሎት የመስጠት ተግባር ላይ አተኩረው እንዲሰሩ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አስገንዝበዋል። የኢፌዴሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶር) በበኩላቸው፣ በቴክኖሎጂና ፈጠራ ላይ በትኩረት በመስራት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን ማሳካት ተችሏል ብለዋል። ባለፈው አፈጻጻም የተገኘውን ተሞክሮ በመቀመርም አሁን ላይ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትን በማሟላት የዲጂታል ግብይት፣ ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆነ የመንግስት አገልግሎትና ጉልበት የቀነሰ አመራረት እውን በማድረግ ለውጥ መመዝገቡንም አስረድተዋል። ይህም የሰው ኃይሉን በኢትዮ ኮደርስ በማሰልጠን ጭምር በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ሁሉ ውጤታማና በዓለም አቀፍ ጭምር ተወዳዳሪ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በአገራችን የሚገኘው ወጣት ኃይል ራሱን በቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት በማነጽ እየመጣ ያለውን ዓለም አቀፍ ውድድር ለማሸነፍ መዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል። በፓናል ውይይቱ ላይ የፌዴራልና የክልል የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በእለቱም የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ያዘጋጀው የቴክኖሎጂ ውጤቶች አውደ ርዕይ ለእይታ ክፍት ተደርጓል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና የዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል
Sep 3, 2026 147
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና የዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ ቴሌኮም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።   ኩባንያው ባለፈው የ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገበውን ስኬት መነሻ በማድረግ፣ በ2019 ዓ.ም የደንበኞቹን ቁጥር ለማሳደግ፣ ገቢውን ለማሳደግ እና የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማስፋፋት በርካታ ግቦችን ማቀዱን አስታውቋል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በመግለጫው እንደተናገሩት በ2019 በጀት ዓመት የቴሌኮም መሰረተ ልማትን ይበልጥ ለማዘመን የ5G እና 4G የኔትወርክ ተደራሽነትን ለማሳደግ ታቅዷል። ተቋሙ ባለፈው አንድ ዓመት የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና የዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት አበረታች ውጤቶች ማስመዝገቡን ገልጸዋል። በ2019 በጀት ዓመት የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ይበልጥ የሚያንቀሳቅሱ አዳዲስ አሰራሮችና አገልግሎቶች እንደሚተገበሩ ተናግረው፤ 295 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ገልጸዋል። በ2019 ዕቅድ የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። በበጀት ዓመቱ 1ሺህ 628 ተጨማሪ አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች የሚገነቡ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 605 ያህሉ በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎችና የቴሌኮም አገልግሎት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች መሆኑን አብራርተዋል። የ4G አገልግሎት ለተጨማሪ 300 ከተሞች ተደራሽ የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም የአገልግሎቱን ተደራሽነት 95 በመቶ ያደርሰዋል ብለዋል። የ5G አገልግሎት ለተጨማሪ 40 ከተሞች እንደሚዳረስና በአጠቃላይ የ5G ተጠቃሚ ከተሞች ቁጥር ወደ 83 ከፍ ይላል ብለዋል። ተቋሙ ባደረገው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 20 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ የሚያስችል የገመድ አልባ ሞባይል ኔትወርክ አቅም በመፍጠር፣ አጠቃላይ የማስተናገድ አቅሙን ወደ 135 ነጥብ 7 ሚሊዮን ያሳድጋል ብለዋል። በፊክስድ ብሮድባንድ አገልግሎት ላይ የሚታዩ የአገልግሎት መቋረጦችን ለማስወገድና የአገልግሎት ጥራትን ከፍ ለማድረግ ተጨማሪ 150 ሺህ ደንበኞችን የተሻለ የፋይበር ቴክኖሎጂ የማዛወር ስራ እንደሚከናወን አብራርተዋል። በከተሞች የሚገኘውን የፋይበር መስመር በመጨመር 300 ኪሎ ሜትር በማስፋፋት አጠቃላይ አቅሙን ከ15 ሺህ ኪሎሜትር በላይ ከፍ ለማድረግ ማቀዱን አስታውቀዋል። ኢትዮ ቴሌኮም ያስቀመጣቸውን እነዚህን ግቦች ለማሳካት የቴክኖሎጂ አጋርነቱን እንደሚያጠናክር እና በሰው ሃይል ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
Sep 3, 2026 69
ባህር ዳር ነሐሴ 28/2018;(ኢዜአ) ፦ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገነባው የፍትሕ ሙዚየም በርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ። ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር የፍትህ ሙዚየም መገንባቱ የህዝቡን የፍትህ እሴትና በህግ የበላይነት ከማሳየት ባሻገር ተቋማት ለለውጥ ያላቸውን መነሳሳት የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል። በሀገሪቱ የፍትህ አስተዳደር ታሪክ ለጥናትና ምርምር የሚሆኑ ሰነዶችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን የያዘ በመሆኑም ለአዲሱ ትውልድ እሴትና ተደማሪ የእውቀት ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ይሆናል ብለዋል። በመሆኑም ይሄንን ታሪካዊ አሻራ ላስቀመጡና መረጃዎችን በማሰባሰብ ለምረቃ እንዲበቃ ላደረጉ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።   የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር)፤ የሙዚየሙ መገንባት በተለይም ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ትልቅ እሴት የሚሆን ነው ብለዋል። በካታሎግና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘውን የአገራችን የፍትህ ታሪክ ተማሪዎች በቀላሉ እንዲያውቁና ለምርምር ግባአት እንዲጠቀሙበት የሚያስችል መሆኑንም አንስተዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አለምአንተ አግደው፤ ሙዚየሙ ከባህላዊ እስከ ዘመናዊ አስተዳደር የነበሩ የፍትህ ታሪኮችን ሰንዶ በመያዝ የተደራጀ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ለህግ ማሻሻያ፣ ለፖሊሲና ስትራቴጂ ቀረጻና ለሌሎችም የጥናትና ምርምር ስራዎች ትልቅ አቅምና ግብአት ይሆናል ብለዋል። በሙዚየሙ ውስጥ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩና ሌላ ቦታ በቀላሉ ሊገኙ የማይችሉ ብርቅዬ የፍትህ ሰነዶች የሚገኙበት ነው ብለዋል። እነዚህን ታሪካዊ መረጃዎች ከተለያዩ ቦታዎች ለማሰባሰብ ክልል አቀፍ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሰፊ ስራ መሰራቱን አንስተው አጠቃላይ የሙዚየሙ ግንባታ አላማ የህዝቡን የፍትህ ስርዓት ታሪክ በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ መሆኑን ተናግረዋል። በፍትሕ ሙዚየም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ፅምዶ የጋራ ዓላማ የሌለውና የትም የማይደርስ ስብስብ ነው-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
Sep 3, 2026 71
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ፅምዶ የጋራ ዓላማ የሌለውና የትም የማይደርስ ስብስብ መሆኑን አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለኢዜአ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ በረጅም ታሪኳ በውስጥ ችግሮችም ሆነ በውጭ ጣልቃ ገብነቶች የተዳከመች ብትመስልም በጽናትና በአሸናፊነት ያለፈች ሀገር መሆኗን አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የማሳካት ጉዞዋ በየትኛውም የጥፋት ጥምረት ሊከሽፍ የማይችል ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ፅምዶ በሚል የጋራ ዓላማ በሌለው ተራ የጥፋት ኃይሎች ስብስብም ሆነ ለሌሎች ትላልቅ ኃይሎች ጫና የምትበገር ጠንካራ ሀገር አለመሆኗን ገልጸው፤ ይህ በታሪኳም ሆነ በአሁናዊ ጉዞዋ የታየ ተጨባጭ ሀቅ ነው ብለዋል። አሁን ፅምዶ በሚል የጥፋት ጥምረት የተሳሰቡት ኃይሎችም የጋራ ዓላማ የሌላቸውና አጭር ርቀት እንኳ አብረው መጓዝ የማይችሉና እርስ በርስ የሚጋጭ አጀንዳን ያነገቡ ተራ ስብስብ ናቸው ብለዋል። እነዚህ ኃይሎች ወጣቶችን በማስገደድ ለእልቂት እየዳረጉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ቆመንልሃል የሚሉትን ህዝብ ለመከራ መዳረጋቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያን ከጉዞዋ የሚያቆማት ኃይል የለም ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤እነዚህ ትናንሽና አቅመ ቢስ ቡድኖች የጀመሩት የጥፋት መንገድም የትም እንደማያደርሳቸው ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያን በውሃ ሃብቷ የመልማት መብት ግብጽ ልታከብር ይገባል - ቲቦር ናዥ
Sep 3, 2026 223
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያን በውሃ ሃብቷ የመልማት መብት ግብጽ ልታከብር ይገባል ሲሉ የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ገለጹ። ከቀይ ባህር ጋር ታሪካዊ ቁርኝት ያላት ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ ተገቢና ህጋዊ መሰረት ያለው መሆኑንም አመልክተዋል። ቲቦር ናዥ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ግብጽ በአባይ ተፋሰስ ላይ ምንም አይነት የውሃ ድርሻ ሳይኖራት ለዘመናት ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ስትጠቀም መቆየቷን አውስተዋል። ግብጽ የዓባይ ወንዝ ላይ ሙሉ ቁጥጥር ሊኖረኝ ይገባል በሚል የምትከተለው አካሄድ ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ ካለው የቀጣናው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ ጋር ፈጽሞ የማይጣጣም መሆኑንም ገልጸዋል። ግብፅ አዲሱን እውነታ መቀበል አለባት ያሉት የቀድሞው ዲፕሎማት፤ የኢትዮጵያን ፈጣን ዕድገትና በቀጣናው እየተቀየረ ያለውን የኃይል ሚዛንም አንስተዋል። የቀጣናው ፖለቲካዊ ገጽታ ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን የገለጹት ቲቦር ናዥ፣ ግብፅ በአሁኑ ሰዓት አዲስ የኃይል ሚዛን መፈጠሩንና ኢትዮጵያም እጅጉን ማደጓን ልትገነዘብ እንደሚገባ አስምረውበታል። ግብፅ የድርድር አቀራረቧን ዳግም በመመርመርና አዲስ እና አዎንታዊ አመለካከት ይዛ ወደ ንግግር ጠረጴዛው ከተመለሰች ዘላቂና ፍትሃዊ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚቻልም ነው ያነሱት። የሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሀብቶችን የመጠቀም መብት እውቅና መስጠት ላይ የተመሰረቱ ውይይቶች የጋራ መግባባት ሊፈጥሩ እንደሚችሉም ተናግረዋል። ቲቦር ናዥ የኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሃብት መጠቀም ራስ ወዳድነት ወይም በግብፅ ላይ የህልውና አደጋ ተደርጎ መታየት የለበትም ሲሉ አስገንዝበዋል። አገራት የራሳቸውን የተፈጥሮ ሃብት ይጠቀማሉ። ሁሉንም ነገር በእውነታው ላይ ቆመን እንመልከት ብለዋል። ቲቦር ናዥ አያይዘውም፤ ግብፅ ስለ ዓባይ ከምታነሳው አቋም በተቃራኒው፣ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር እንዳትደርስ የያዘቸውን አቋም ምክንያታዊነት የጎደለው መሆኑን አንስተዋል። ግብፅ የቀይ ባህር ዳርቻ ሀገራት ብቻ የባህር አስተዳደር ጉዳይ ይመለከታቸዋል የምትል ከሆነ፣ በአባይ ተፋሰስ መጠቀም ያለባቸው የውሃ ድርሻ ያላቸው ሀገራት ብቻ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። ከእውነታ ጋር የማይጣጣመውን ይህን የግብጽን አቋም የግብዝነት ድርጊት ሲሉ ተችተውታል። የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዠ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በተመለከተም ሀሳባቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የነበራትን የባህር ላይ ታሪክ በማስታወስ፣ ሀገሪቱ በወቅቱ የራሷ የባህር ኃይል (ኔቪ)፣ የባህር ኃይል ማዕከል እና በባህር ኃይል ውስጥ ያገለግሉ የነበሩ የኢትዮጵያ አድሚራሎች እንደነበሯትም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ማጣት እጅግ አሳዛኝ ክስተት እንደሆነ ጠቅሰው፣ ሀገሪቱ አሁን የምታደርገውን የባህር በር የማግኘት ጥረት ለቀይ ባህር ካላት ታሪካዊ ግንኙነት ጋር አያይዘውታል። የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ፍትሃዊና ሕጋዊ ጥያቄ መሆኑን የገለጹት ቲቦር ናዥ፣ የጎረቤት ሀገራት የኢትዮጵያን ፍላጎቶች በሚገባ መረዳት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን ለቀጣናው ኢኮኖሚያዊ እድገትና ዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው
Sep 3, 2026 165
ቦንጋ፤ ነሐሴ28/2018(ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ሀገራት የኢኮኖሚ እድገትና ደህንነት መረጋገጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ኢዜአ ያነጋገራቸው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ። የጥንታዊ ስልጣኔ መነሻና በአንድ ወቅት ስሟም ከሀያላን ሀገራት ተርታ የነበረችው ኢትዮጵያ በቀይ ባህር አካባቢ የነበራት ተሰሚነትና የወደብ ባለቤትነት ለገናናነቷ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ይሁን እንጂ በታሪክ አጋጣሚ የቀይ ባህር ባለቤት ከነበረችበት ከተነጠለች ጀምሮ የራሷ የባህር በር በማጣቷ ለበርካታ ችግሮች ተዳርጋ ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ያለቸው ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ቢኖራትም ወደብ አልባ መሆኗ በእድገቷና በኢኮኖሚዋ ላይ ተጽዕኖ አሳድሮባታል። ይህን ታሪክ በመቀየር ኢትዮጵያን በቀጣናው ሀገራት ወደነበረችበት ከፍታ ለመመለስ የባህር በር ባለቤትነትን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር ዘሪሁን ያሬድ፣ የባህር በር ባለቤትነት ለኢትዮጵያ ቅንጦት ሳይሆን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የደህንነት ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። የባህር በር ባለቤትነት ኢትዮጵያ በቀጣናውና በአሁጉሩ ያላትን ስትራቴጂካዊ ተሰሚነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚያሳድግ ነው። የአካባቢውን ሀገራት የህዝብ ለሕዝብ ትስስር በማጠናከር ቀጣናዊ ውሕደትን ለመፍጠር፣ ሰላምን ለማጽናትና የጋራ እድገትን ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል። የባህር በር መኖር ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት ለሀገር ልማት እንድታውል ያደርጋል ያሉት መምህሩ፣ የወጪና ገቢ ምርቶችን በቀላሉ በማሳለጥ የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነቷንም እንደሚያሳድግ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ለመሆን በዲፕሎማሲዊ መንገድ የጀመረችው ጥያቄ መልካዓ ምድራዊና ሕጋዊ መሠረት ያለው በመሆኑ የዜጎችን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑንም መምህሩ ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ሰለሞን ማሞ በበኩላቸው፣ ቀይ ባህር ከአክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በዲፕሎማሲዊ መስክ ትልቅ ቁርኝት የነበረውና የሕልውናዋ መሠረት መሆኑንም ገልፀዋል። በወቅቱ ኢትዮጵያን በዓለም የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ዘርፎች ተፅዕኖ ፈጣሪ ከነበሩ አራት ሀገራት መካከል አንዷ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል፡፡ የባህር በር ማጣት በተዘጋ ቤት ውስጥ እንደመኖር መሆኑን የጠቀሱት መምህሩ፣ መልሶ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የሚደረገው ጥረት የመላው ኢትዮጵያውያን ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን በጋራ ተደጋግፎ ለማደግ ካለው ፋይዳ ባለፈ ለቀጣናው ሰላም መከበር ትልቅ ዋጋ እንዳለውና የኢትዮጵያም ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሳድግ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በሕገ-ወጡ ሕወሓት ቡድን የሚደርስብንን ግፍ ለማስቆም የጀመርነውን ትግል እናጠናክራለን - የትግራይ ክልል ተወላጆች
Sep 3, 2026 202
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ በትግራይ ክልል ሕገ-ወጡ ሕወሓት እያደረሰ ያለውን ግፍና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ለማስቆም በቡድኑ ላይ የጀመርነውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የክልሉ ተወላጆች ገለጹ። በአሁኑ ወቅት ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የክልሉን ወጣቶች ለሌላ አሳልፎ መሸጥን ጨምሮ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ በማካሄድ ከፍተኛ ግፍና መከራ እያደረሰ ይገኛል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የክልሉ ተወላጆች መካከል አቶ ኹሉፍ አጽአሊ እንደገለጹት፣ በትግራይ ክልል ወጣቶች ወደ ማይፈልጉት ጦርነት እንዲገቡ እየተገደዱ ነው። ወጣቶች ይህንን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በመሸሽ ከትውልድ ቀያቸው በመውጣት ወደ ባሕርና በረሃ እየገቡ መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም እኛ አንድነታችንን በማጠናከር ሕገ ወጡ ሕወሓት እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ማስቆም አለብን ሲሉ ተናግረዋል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ለምለም ሳሙኤል በበኩላቸው፤ በሕገ ወጡ ቡድን ምክንያት የትግራይ ክልል እናቶች በለቅሶና መከራ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ በጣም ኢ-ሰብአዊ መሆኑን በመግለጽ ሕገ ወጡን ቡድን ለማስወገድ የተጀመረውን ትግል ማጠናከር አለብን ያሉት ደግሞ ሌላኛው የክልሉ ተወላጅ ተካ ገብሩ ናቸው። ሰውን ያለፍላጎቱ ለጦርነት እንዲሰማራ ማድረግ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተካ፣ ኢትዮጵያውያን የሚታወቁበት የሰብዓዊነት እሴት በክልሉ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።
ዲፕሎማሲ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ግንባታ ያለው ፋይዳ ላይ ያተኮረው የአሰፋ አብዩ (ዶ/ር) መጽሐፍ ተመረቀ
Sep 2, 2026 402
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አሰፋ አብዩ(ዶ/ር) የዲፕሎማሲ ሥራ በአፍሪካ ቀንድ ለሚካሄደው የሰላም ግንባታ ሂደት ያለውን ቁልፍ ሚና አስመልክቶ የጻፉት አዲስ መጽሐፍ ተመርቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ በተካሄደው የመጽሐፉ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ማኅበረሰብ፣የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት እንዲሁም ምሁራን ተገኝተዋል። ዲፕሎማሲ ለሰላም ግንባታ ስትራቴጂ በአፍሪካ ቀንድ ያለው ተሞክሮና ፈተናዎቹ (Diplomacy As A Peace Building Strategy:-Approaches and challenges in the Horn Africa) የተመረቀው መጽሐፍ ርዕስ ነው። የመጽሐፉን ዳሰሳ ያቀረቡት የብሔራዊ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እንደገለጹት፤ የመጽሐፉ ዋነኛ ዓላማ ዲፕሎማሲ ለሰላም ግንባታ ያለውን ፋይዳ አጉልቶ ማሳየት ነው፡፡ ፀሐፊው በዳበረ ሙያዊ ልምድ፣ የአመራርነት ክህሎት፣ በትምህርት ባገኙት እውቀትና ጥልቅ ጥናት ታግዘው ያዘጋጁት መጽሐፍ መሆኑን ከንባባቸው መገንዘባቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ ዲፕሎማሲ ከሰላም ግንባታ ባሻገር ብሔራዊ ጥቅምና ደኀንነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ማሣሪያ መሆኑ በትኩረት እንደተተነተነ ጠቁመዋል፡፡ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ግጭቶችንና ጦርነቶችን መፍታት ብቻ ሳይሆን፤ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ቁልፍ መሣሪያ መሆኑ በመጽሐፉ በሚገባ መብራራቱ የጥንካሬው ማሳያ ነው ብለዋል። ሌላኛው የመጽሐፍ ዳሰሳ አቅራቢ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም-አቀፍ ግንኙነት መምህር ባዩልኝ ዘመድአገኘሁ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መጽሐፉ የአፍሪካ ቀንድ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታን አጉልቶ ማሳየቱ ጠንካራ ጎኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሰላም ጉዳዮችንና የዲፕሎማሲ ፅንሰ-ሐሳቦችን አስተሳስሮ በማንሳት መፍትሔ እንደሚጠቁም አብራርተዋል። መጽሐፉ ወቅታዊ የሆኑ አህጉራዊና ዓለም-አቀፋዊ ክስተቶችና ግጭቶችን በማጣቀስ በአፍሪካ ቀንድ የሚስተዋሉ ችግሮች በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ፖሊሲ አውጪዎች 21 ምክረ-ሐሳቦችን በግብዓትነት ማቅረቡ የይዘት ጥንካሬውን አጉልቶ እንደሚያሳይ ዶክተር ባዩልኝ አመልክተዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳሰሳ ያቀረቡት አምባሳደር ሽብሩ ማሞ፤ መጽሐፉ ሰላም፣ዲፕሎማሲና ደኀንነት ከድንበር ግጭት ጋር ያላቸውን ትስስር በሚገባ የሚያነሳ መሆኑን ጠቁመዋል። የሀገራችን ዲፕሎማቶች፣የፀጥታና ደኀንነት አባላት፣ ጥናትና ምርምር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ግንባታ ጥረቶች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ እንደሚያደርግ ጠቅሰዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ቀነአ ያደታ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መጽሐፉ ወሳኝ የሆኑ የሰላም፣ ግጭትና ዲፕሎማሲ ጽንሰ-ሐሳቦችን በሚገባ እንዳነሳ ጠቅሰዋል፡፡ በአፍሪካ በተለያዩ ሀገራት የሚታዩ የድንበር ወሰን ችግሮች የፀጥታና ደኅንነት ስጋት እንደሚፈጥሩ በመግለጽ፤ መጽሐፉ ለባለድርሻ አካለት ግብዓት እንደሚሆን አመልክተዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ድንበሮች ጥናት ግብረ-ኃይል አስተባባሪ አምባሳደር ኢብራሂም አድሪስ በበኩላቸው፤ መጽሐፉ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ክፍተት በሆኑት የድንበር ግጭት ፣ ሰላምና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መሆኑ ጠቅሰው፤ በዲፕሎማሲ ፣ፀጥታና ደኀንነት ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎችና አመራሮች ጠቃሚ ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል። በቀጣይ በዲፕሎማሲና የሰላም ግንባታ ዘርፎች የካበተ ሥራ ልምድና ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያዎችም መጽሐፍ ለመጻፍ እንዲነሳሱ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አሰፋ አብዩ (ዶ/ር) በፀጥታና ደኅንነት ተቋማት እንዲሁም በዲፕሎማሲ የተልዕኮ ሥምሪት ያገኙት ልምድና ተሞክሮ እንዲሁም የፒኤችዲ ድግሪ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ያዘጋጁት ጥናታዊ ጽሑፍ መጽሐፉን ለማዘጋጀት መነሻ እንደሆናቸው ጠቁመዋል። ከዝግጅት እስከ ሕትመት ባለው ሂደት ተሳትፎ ላደረጉት አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከመጽሐፉ ሽያጭ ከሚገኝ ገቢ 100 ሺህ ብር ለኢትዮጵያ ሰላምና ደኅንነት መስዕዋትነት ለሚከፍለው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም 100 ሺህ ብር ደግሞ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በስምሪት ላይ እያሉ ጉዳት ለደረሰባቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት እንደሚያበረክቱ በመድረኩ ላይ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ከአገልግሎቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የህዳሴ ግድብ ግንባታን ያሳካ ታሪካዊ ትውልድ የባህር በር ጥያቄንም ያሳካል
Sep 2, 2026 395
ደሴ ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የህዳሴ ግድብ ግንባታን በማሳካት ታሪክ የሰራው ይህ ትውልድ የባህር በር ባለቤትነትንም እውን በማድረግ ለሌላ ታሪክ መትጋት አለበት ሲሉ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ገለጹ። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለረጅም ዘመናት የቀይ ባህር ዳርቻዎችና ወደቦች ባለቤት ሆና የቆየች ቢሆንም፣ በየጊዜው በነበሩ የታሪክ አጋጣሚዎችና ጂኦፖለቲካዊ ሁነቶች ምክንያት የባህር በር አልባ እንድትሆን መደረጓ ይታወቃል። ይሁን እንጂ የሀገሪቱ የህዝብ ብዛት፣ እያደገ የመጣው ኢኮኖሚ እና የመልክዐ ምድራዊ አካባቢዋ ተፈጥሯዊ ቁርኝት ተፈጥሯዊና ታሪካዊ የባህር በር መብቷን እንደገና እንድታስከብር የሚያስገድድ መሆኑም ይታወቃል። የአርበኞች ማህበር አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የቀድሞ የሰራዊት አባላት፣ ለሀገር ተቆርቋሪ ምሁራንና ሌሎችም ይህ ታሪካዊና ህጋዊ እውነት በትውልዶች መካከል ሳይደበዝዝ እንዲቀጥል የነበራቸውን ድርሻ ሲያሳስቡ ቆይተዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የደቡብ ወሎ ዞን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ጽህፈት ቤት አባላት፤ በቀይ ባህር ቅርብ እርቀት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የባህር በር ማጣቷ የሚያስቆጭ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትርቅ መደረጉ በሴራ የተፈፀመ የባንዳነት ተግባር መሆኑን ያነሱት አርበኞቹ አሁን ላይ ይህንን የቆየ ስብራት ለመጠገን በመደመር መንግስትና በህዝቡ የተጀመረው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል። የጽሕፈት ቤቱ ፀሐፊ ተተኪ አርበኛ አየለ ወልደ ጊዮርጊስ፤ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትርቅ የተደረገበት ምክንያት እስካሁን ለማንም ግልጽ ያልሆነና የምንቆጭበት ነው ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም የህዳሴ ግድብ ግንባታን በማሳካት ታሪክ የሰራው ይህ ትውልድ የባህር በር ባለቤትነትንም እውን በማድረግ ለሌላ ታሪክ መትጋት እንዳለበት አንስተዋል። በዚህ ረገድ የተጀመሩ ጥረቶች የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸው ለስኬቱም የሁላችንም ሀገራዊ አደራ እና ሃላፊነት አለብን ብለዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተዘግቶባት መዝለቅ የማትችልና የህልውናዋ ጉዳይ በመሆኑ ጥያቄው መልስ ሊያገኝ እንደሚገባም ገልጸዋል። የማህበሩ አባል አቶ ማሞ አያሌው እና ሃምሳ አለቃ አለማየሁ አበበ፤ ለኢትዮጵያ የባህር በር ቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን የትውልዱ መረዳት አስደናቂነት አንስተው ለተግባራዊነቱ በጋራ መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል። የኢትዮጵያ እና የቀይ ባህር መልክዓ ምድራዊ ቁርኝት ከጥንት ጀምሮ ዘመናትን የተሻገረ መሆኑን አንስተው በዚህ ዘመን የባህር በር የምትነፈግበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይችልም ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያና ቀይ ባህርን ለመነጠል የተሄደበት ርቀት የሴራ ፖለቲካ ውጤት መሆኑን ያነሱት ሌላኛው የማህበሩ አባል ሃምሳ አለቃ ባለሟል መለሰ፤ ኢትዮጵያ ታሪኳን አድሳ የባህር በር ባለቤት የምትሆንበት ጊዜ ብዙም እሩቅ ሊሆን አይችልም ብለዋል። በወቅቱ የነበሩ ፖለቲከኞች የሰሩት ታሪካዊ ስህተት ኢትዮጵያን አሁን ላይ ብዙ ዋጋ እያስከፈላት መሆኑን የሚናገሩት ሃምሳ አለቃ ባለሟል መለሰ፤ የባህር በር ባለቤትነቷ እውን እንዲሆን በመስራት ታራካችንን የምናድስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በታሪክ፣ በመልክዐ ምድርና በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ምላሽ ሊሰጠው የሚገባ ተገቢ ጥያቄ መሆኑም ተናግረዋል።
በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ጊዜ ሳያባክኑ እድሉን ሊጠቀሙበት ይገባል
Sep 2, 2026 532
ጎንደር ፤ ነሐሴ 27/2018(ኢዜአ) ፦ በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ጊዜ ሳያባክኑ እድሉን ሊጠቀሙበት ይገባል ሲሉ በአማራ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች ተናገሩ። በጽንፈኛ ቡድኖች የህዝብ ትግል እየተባለ የሚነሳውም ዓላማው ዘረፋና ሃብት የማካበት ጉዳይ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባልም ብለዋል። በአማራ ክልል በተሳሳተ መንገድ ትጥቅ በማንሳት ጫካ ገብተው የነበሩ ወገኖች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል በይቅርታ ወደ ህዝባቸው ገብተዋል፤ እየገቡም ይገኛሉ። በጎንደርና አካባቢው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩና የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ልማት ከገቡ የቀድሞ ታጣቂዎች መካከል አቶ አበበ ሽፈራው፤ ለህዝብ እንታገላለን የሚል ሽፋን በመያዝ የሚደረግ እንቅስቃሴ ዓላማው ዘረፋ መሆኑን ተረድተናል ብለዋል። በመሆኑም እራሳቸውና በእርሳቸው ስር የነበሩ ከ50 በላይ የቀድሞ ታጣቂዎችን በመያዝ የመንግስትን ጥሪ በመቀበል ሰላምን መርጠው መምጣታቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ አሁን ላይ የትኛውም የፖለቲካ ጥያቄ በንግግርና በመግባባት እንደሚፈታ እናምናለን፤ ለዚህም ምቹ እድሎች አሉ የሚሉት አቶ አበበ፤ የትኛውም ታጣቂ ጊዜውን በጫካ ሳያባክን የሰላም እድሉን በአግባቡ ሊጠቀም ይገባዋል ብለዋል። የአማራ ክልል ህዝብ ከለውጡ በፊት ሆን ተብሎ ብዙ በደሎች ይፈፀሙበት እንደነበር አስታውሰው የመደመር መንግስት ግን የጋራ እሳቤዎችን በመሰነቅ ለሀገር ልማትና ለህዝብ ተጠቃሚነት እየሰራ መሆኑን ቆይተንም ቢሆን ተገንዝበናል ሲሉ ተናግረዋል። ሌላኛው የቀድሞ ታጣቂ አቶ ተረፈ እንየው፤ በኢትዮጵያ አሁን ላይ የትኛውም የትጥቅ ትግል አማራጭ መፍትሄ የማያመጣና የተሳሳተ ስሌት ስለመሆኑ ተናግረዋል። በጦርነት የሚፈታ የፖለቲካ ጥያቄም ሆነ የሚገነባ ሀገር እንደሌለ ገልጸው በተሳሳተ ቅስቀሳ ወደ ጫካ የገቡ ወገኖቻችን ዛሬ ነገ ሳይሉ የሰላምን አማራጭ በመቀበል ወደ ልማታቸው ሊመለሱ ይገባል ሲሉ መክረዋል። በኢትዮጵያ የጠመንጃ ጊዜ አብቅቶ የምክክር ጊዜ እውን መሆኑን በተግባር አይተናል ያሉት የቀድሞ ታጣቂው ከቅራኔ እና ግጭት በመውጣት በልማት ሀገራችንን ለመገንባት መትጋት አለብን ብለዋል። ሌላኛው የቀድሞ ታጣቂ አቶ ዮሐንስ አዲስ፤ የትጥቅ ትግል ልማትን ከማደናቀፍና ዜጎችን ከማጎሳቆል በስተቀር ሌላ አላማ የሌለውና ውጤት የማያመጣ መሆኑን በትክክል መናገር እችላለሁ ሲሉ ተናግረዋል። በአማራ ክልል ባለፉት ሶስት ዓመታት የተመለከትነው የባእዳንን ተልእኮ ለማሳካት በባንዳነት በመሰለፍ የህዝብን ሃብት መዝረፍና ማውደም ነው ብለዋል ። በመሆኑም በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች ሁሉ በጥፋታቸው በመጸጸት የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል መጥተው ማህበረሰባቸውን መቀላቀልና ወደ ልማት መግባት እንዳለባቸው የቀድሞ ታጣቂዎቹ መክረዋል።

ማህበራዊ
በትምህርት ቤቶች የተጀመሩ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Sep 3, 2026 115
ሰመራ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስና ለመቋቋም በትምህርት ቤቶች የተጀመሩ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። በአየር ንብረት ለውጥና በአካባቢ ጥበቃ ሥራ ላይ የትምህርት ቤቶችን ሚና ለማሳደግ ያለመ የውይይት መድረክ ዛሬ በሰመራ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሳ አደም እንዳሉት የአካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ ጥበቃ ሥራ ዓለም አቀፍ ትኩረት ያለው ነው። በዚህም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስና ለመቋቋም እንደ ሀገር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አንስተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነሰና ለመቋቋም በክልሉ በትምህርት ቤቶች የተጀመሩ ሥራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በተለይም በክልሉ በረሃማ አካባቢዎች ለሚሰሩ የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ሥራዎች ትምህርት ቤቶች ላይ ያተኮረ ስራ በስፋት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመከላከል በትምህርት ቤቶች ከአረንጓዴ አሻራ ልማት ሥራዎች በተጨማሪ የጓሮ እርሻ ሥራዎች በቅንጅት እየተከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል። በትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ እንዲላበሱ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል። በክልሉ ከዚህ ቀደም ብዙም ያልተለመደው የጓሮ እርሻ ልማትም በአሁኑ ወቅት እየተስፋፋና በ35 ትምህርት ቤቶችም ልማቱ እየተከናወነ መሆኑን በአብነት ጠቅሰዋል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት ማሻሻል መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዮሐንሰ ወጋሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት፣ ትምህርት ቤቶች ከንድፈ ሀሳብ በተጨማሪ ተግባራዊ የመማማሪያ መስክ እንዲሆኑ ካለፉት ስድስት ዓመታት ጀምሮ በትኩረት እየተሰራ ነው። ቅድመ መደበኛን ጨምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ56 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ጠቅሰው፣ ከነዚህ ውስጥ በ24 ሺህ ትምህርት ቤቶች የጓሮ እርሻ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። የጓሮ እርሻ ማልማት የጀመሩና የተለያየ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞችን የተከሉ ትምህርት ቤቶች ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል አዎንታዊ ሚና እየተጫወቱ ናቸው ብለዋል። በመርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአይሳኢታ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ባለሙያ አቶ ፈንታው ካሳ በትምህርት ቤቶች ውስጥ በተሰሩ ሥራዎች ለውጥ መጥቷል። በትምህርት ቤቶች ባዶ በነበረ ቦታ ላይ የተለያዩ ቋሚ ተክሎችን በመተከላቸው የአካባቢው ሞቃታማ የአየር ፀባይ እየተለወጠ መምጣቱን ገልጸዋል።
የጳጉሜን ቀናት የመደመር መንግሥት ባስመዘገባቸው ውጤቶች በመታገዝ ለሌላ ስኬት በሚያዘጋጅ መልኩ ይከበራሉ - ከንቲባ ከድር ጁሃር
Sep 3, 2026 63
ድሬዳዋ ፤ ነሐሴ 28/2018(ኢዜአ) ፦ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ። ከንቲባው በጳጉሜን አምስት ቀናት በሚከናወኑ መርሃ ግብሮች፣ እቅዶችና ዝግጅቶች ዙሪያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ቀናቱ የመደመር መንግሥት ባስመዘገባቸው ውጤቶች በመታገዝ ለሌላ ስኬት በሚያዘጋጅ መልኩ በተለያዩ ተግባራት ይከበራሉ ብለዋል። በዚሁ መሠረት በጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን እስካሁን የተከናወኑ ውጤታማ ሥራዎችን በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ሁነቶች እንደሚካሔዱ ነው የገለጹት። እስካሁን የተገኙ ድሎችን በተባበረ ቅንጅት ለማስቀጠልና ቀጣይነታቸውን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ መርሃ ግብሮች የሚከበረው ደግሞ ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን ነው ብለዋል። ጳጉሜን 3 የሚከበረው የጽናት ቀን የሀገርን አንድነትና ልማት ለማጽናት ለሚተጉ የሀገር መከላከያ፣ የጸጥታና የፍትሕ ተቋማት ያለንን ደጀንነትና ድጋፍ በማረጋገጥ እንደሆነም ነው ያመለከቱት ። ጳጉሜን 4 የህብር ቀን የድሬዳዋን የመደጋገፍ፣ የመረዳዳትና ሰው ተኮር ልማቶች በሚያስቀጥሉ እንዲሁም ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ይከበራል ብለዋል። ጳጉሜን 5 የነገ ቀን ደግሞ የአዲሱ ዓመት ዋዜማ እንደመሆኑ መጠን ሀገራችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያስመዘገበች የምትገኘውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ በሚያጠናክሩ ሁነቶች እንደሚከበር ከንቲባው አስረድተዋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን የሰፈነው ሰላም የልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ አስችሏል
Sep 3, 2026 67
ጊምቢ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ በዞኑ የሰፈነው ሰላም የልማት ሥራዎችን በቅንጅት ለመስራትና በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ማስቻሉን የምዕራብ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተረፈ ገለጹ። በዞኑ ዪብዶ ወረዳ በ148 ሚሊዮን ብር የተገነቡ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ከበቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ ሁለተኛው ትውልድ ጤና ኬላ፣ የሀር ትል ማባዣ ማዕከል፣ የወረዳው የስብሰባ አዳራሽ፣ የመንገድ እና ሌሎች የልማት ሥራዎች ይገኙበታል ። በፕሮጀክቶቹ ምረቃ ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እንደተናገሩት፣ በዞኑ በህብረተሰቡ ተሳትፎ እና በፀጥታ አካላት ቅንጅት ሰላምን በማስፈን የልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ተገንብተው ለአገልግሎት እንዲበቁ እየተደረገ ነው።   በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ470 በላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአገልግሎት ለማብቃት መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ሕብረተሰቡ የሰላም ግንባታና የልማት ሥራዎች ላይ ተሳትፎውን ይበልጥ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የብልፅግና ጉዞን ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የዪብዶ ወረዳ አስተዳደር አቶ ደጋጋ ሞሐመድ ናቸው።   በአካባቢው የሰፈነው ሰላም የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የተናገሩት ደግሞ የዩብዶ ወረዳ ነዋሪ መምህር ተክሉ ተሾመ ናቸው። ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት የበቁት መሠረተ ልማቶችም ረጅም ዕድሜ እንዲያገለግሉ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። በወረዳው የብዙ ጊዜ የልማት ጥያቄያቸው ምላሽ ማግኘቱ የሚበረታታ መሆኑንና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለጹት ደግሞ ወይዘሮ ክብቱ ጋዲሳ የተባሉ ነዋሪ ናቸው።   የአካባቢው የፀጥታ ችግር መፈታቱ በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ተጠቃሚ እንዳደረጋቸውም ገልጸዋል። በቀጣይም የልማት ሥራዎች በሚፈለገው ልክ እንዲከናወኑ ለአካባቢያቸው ዘላቂ ሰላም ዘብ በመቆም የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።
የዜጎች የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የመንግስት አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ ነው- ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
Sep 3, 2026 104
ባሕር ዳር ፤ ነሐሴ 28/2018(ኢዜአ) ፦የዜጎች የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ዘመናዊ የምዝገባ ስርአት የመንግስት አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ። የክልሉ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ምዝገባ ሲስተም የሚያስተዋውቅ መርሃ ግብር በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድሩ የዜጎች መረጃ ዘላቂነትና ታማኝነትን በሚያረጋግጥ መልኩ የተደራጀ የምዝገባ ሥርዓት ጠቀሜታው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል። የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን በተጨባጭ መረጃ ላይ መሰረት አድርጎ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን አንስተው ምዝገባው ለፖሊሲ አውጪዎችና ሌሎች አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ይጠቅማልም ብለዋል። በቴክኖሎጂ የታገዘ የምዝገባ ስርአት ጊዜን፣ ጉልበትንና ወጪን ከመቆጠብም ባለፈ የመንግሥትና የህዝብን አስተዳደራዊ ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም ከአገልግሎቱ የሚገኘው መረጃ የስራ ቅልጥፍናንና የህዝብን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ለላቀ ውጤታማነት ሁሉም ተባብሮ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል። የክልሉ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ኃላፊ ወይዘሪት መዓዛ በዛብህ፤ አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ ታግዞ ተደራሽ መደረጉ ፈጣንና ደህንነቱ የተረጋገጠ ትክክለኛ መረጃን ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሚረዳ ተናግረዋል። በተጨማሪም ብልሹ አሰራርን፣ ሀሰተኛና ህገ-ወጥ ሰነዶችን ከመከላከል ባለፈ በትክክለኛና ተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን ያስችላል ብለዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም በ761 የምዝገባ ጣቢያዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኩነቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል። በቀጣይም የዘርፉን የዲጂታል 2030 እቅድ እውን የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፣ ለዚህ ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት ትብብርና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል። በመድረኩ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን፣ በ2018 በጀት ዓመት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም እውቅና ተሰጥቷል።
ኢኮኖሚ
በሲዳማ ክልል የህዝብን የልማት ጥያቄ የመመለሱ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
Sep 3, 2026 72
ሀዋሳ፣ ነሀሴ 28/2018 (ኢዜአ) በሲዳማ ክልል የሕዝቡን የልማት ጥያቄ የሚመልሱ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ። በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ቡድን በምስራቃዊና ማዕከላዊ ሲዳማ ዞኖች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል። ርዕሰ መስተዳድሩ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ በክልሉ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ዳዬ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ ከተማዋን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ እና ተመራጭ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል። የኮሪደር ልማት ሥራው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃም አክለዋል። ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ታስቦ እየተገነባ የሚገኘውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ለማጠናቀቅም ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።   የልኡካን ቡድኑ የአርቤጎና እና የቡራ ወረዳዎችን የሚያገናኘውና በሎጊታ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የባሬ ድልድይ እንዲሁም የቡራ ወረዳ የአስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሕንፃ ግንባታ በዚሁ ወቅት ከጎበኙዋቸው የልማት ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የክልሉ መንግሥት የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና የልማት ጥያቄዎችን የሚመልሱ ፕሮጀክቶችን እውን የማድረጉ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በቡራ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘው የአስተዳደር ሕንፃም የመንግሥት አገልግሎትን ምቹና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለመስጠት እንደሚያስችል ነው ያመለከቱት። በቡራ ወረዳ ዳለቻ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ባንጫ ባዲሶ በበኩላቸው፣ የአርቤጎና እና ቡራ ወረዳዎችን የሚያገናኘው የባሬ ድልድይ መሠራቱ ቀደም ሲል ወንዙን ለመሻገር ይገጥም የነበረውን ችግር እንዳስቀረላቸው ተናግረዋል።   ወንዙ በሚሞላበት ወቅት በርካቶች ለመሻገር ሲሞክሩ በደራሽ ውኃ ይወሰዱ እንደነበር አስታውሰው፣ የድልድዩ ግንባታ ትልቅ እፎይታ እንደሰጣቸው ገልጸዋል። ሌላው የአርቤጎና ወረዳ ሚቂቾ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ፌኦ ሲዱ በበኩላቸው፣ የድልድዩ መገንባት ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ለማውጣትና የሚፈልጉትን ሸምተው ለመመለስ ይገጥማቸው የነበረውን ችግር እንደፈታላቸው ገልጸዋል። በጉብኝቱ ላይ የክልሉ፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
መንግሥት የዜጎችን ኑሮ ማሻሻልና ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው አድርጓል - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Sep 3, 2026 87
አዲስ አበባ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ መንግሥት የዜጎችን ኑሮ ማሻሻልና ዘላቂ ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው ማድረጉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። አገልግሎቱ መንግሥት ሃገራዊ ሪፎርሞችን በመተግበር የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገባውን ቃል ወደ ተግባር እየለወጠ ይገኛል ብሏል። ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥና የዜጎቿን ሕይወት ከፍ ለማድረግ በምታደርገው ያልተቋረጠ ርብርብ፣ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ የሚያበስሩ ታሪካዊ ምዕራፎች እውን እየሆኑ ይገኛሉ ብሏል። መንግሥት ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስልታዊ ፖሊሲዎችን በመንደፍና በመተግበር በኢኮኖሚውና በማኅበራዊው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጦችን በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ ይፋ የተደረገው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል የተደረሰው ታሪካዊ ስምምነት የዚህ አበይት ርዕይ አንዱ ማሳያ ነው ሲልም አገልግሎቱ አብራርቷል። በ100 ቢሊየን ብር ካፒታል የሚቋቋመውና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ያካተተው የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ፣ በባንክ ዘርፍ ያለውን የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን በመቅረፍ ለዜጎች አስተማማኝ የፋይናንስ አቅርቦት ይፈጥራል ብሏል። አገልግሎቱ ይህ ታሪካዊ ስምምነት መንግሥት በተመጣጣኝ ዋጋ የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊየን ቤቶችን ለማቅረብ ያስቀመጠውን ግብ በግንባር ቀደምትነት የሚያሳካ መሆኑን ገልጿል። ስምምነቱ የዜጎችን የቤት ባለቤትነት ፍላጎት እውን በማድረግ ረገድ የሚታዩ ማነቆዎችን በመስበር፣ የበርካቶችን የዕለት ተዕለት ሕይወትና ማኅበራዊ ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያሻሽል የመንግሥት ቁርጠኝነትን ያረጋገጠ ቁልፍ ርምጃ መሆኑንም ጠቅሷል። ይህ ስኬት ብቻውን የቆመ አይደለም፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በሜጋ ፕሮጀክቶች የተመዘገቡት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ድሎች ቀጣይ ምዕራፍ አካል ነው። የመደመር መንግሥት የግል ዘርፉን ተሳትፎ በስፋት በማካተትና የገበያ ሥርዓቱን በማዘመን አገራዊ የኢኮኖሚ አቅምን ማጠናከር የልማት ጉዞው መሠረት አድርጎ ቀጥሏል። እንደ ሀገር እየተመዘገበ ካለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ በሚፈጠር የዋጋ ግሽበት አነስተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርሰውን ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ መንግሥት በቢሊዮኖች የሚቆጠር በጀት በመመደብ በነዳጅ፣ በመሠረታዊ ፍጆታዎች እና በግብርና ግብአቶች ላይ ከፍተኛ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል። ከዚህ የዕለት ኑሮ ማቃለያ ሥራ ባሻገር የዜጎችን ኑሮ በዘላቂነት ማሻሻልና ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳው አድርጎል። በዚህም ቃል በተግባር እየተለወጠ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ የመገንባት ጽኑ ፍላጎቱ በሁሉም መስክ በተግባር እየተፈጸመ ቀጥሏል ብሏል።
የሸገር ከተማ አስተዳደር አርሶ አደሮችን ማዕከል ያደረገ ዘመናዊ ከተማ ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወነ ነው
Sep 3, 2026 92
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- የሸገር ከተማ አስተዳደር ዘመናዊና ውጤታማ ከተማ ለመገንባት በሚያደርገው እንቅስቃሴ አርሶ አደሮችን ማዕከል ያደረጉ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የከተማዋ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ገለጹ። በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች ሲከበር የቆየው የሸገር ከተማ አስተዳዳር የአርሶ አደሮችን ቀን ዛሬ በፓናል ውይይትና የከተማዋ ግንባር ቀደም አርሶ አደሮችን እውቅና በመስጠት ዛሬ ተጠናቋል።   ዛሬ በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ የፓናል ውይይት "የመደመር መንግሥት እይታ እና የአርሶአደሮች ተጠቃሚነት" በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ ለሞዴል አርሶ አደሮችም የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል። የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ፤ በከተማዋ ባለፉት ዓመታት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ አሳታፊ ልማትን ለማስፈንና ውጤታማ የኢኮኖሚ ሽግግር ለማምጣት በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለይም ጠንካራ ከተማን ለመገንባት አርሶ አደሩን ማሰልጠን፣ የከተማ ግብርናን ማዘመንና አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ ለሀገር ኢኮኖሚ መሰረት ስለሆነ ጠንካራ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። የከተማዋን የኢኮኖሚ ዕድገትና ግንባታ እውን ለማድረግ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ላይ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።   የሸገር ከተማ በአዲስ መልኩ ከመደራጀቱ በፊት በክረምት ወቅት ይለማ የነበረው 50 ሺሕ ሄክታር መሬት ብቻ እንደነበር ያስታወሱት ከንቲባው፣ በአሁኑ ወቅት የማልማት አቅሙን ወደ 95 ሺሕ ሄክታር ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል። በተጨማሪም ቀደም ሲል ከአንድ ሄክታር መሬት በሽያጭ ወይም በምርት ደረጃ በሰፊው ይገኝ የነበረው 37 ኩንታል አማካይ ምርት፣ በአሁኑ ወቅት ወደ 45 ኩንታል ማደጉን ገልጸዋል። ለአርሶ አደሩ የሚሰጡ ሥልጠናዎችን፣ የግብዓት አቅርቦትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ግብርናውን ከባህላዊ ወደ ዘመናዊ ማሸጋገር ተችሏል ያሉት ከንቲባው፤ ይህም ምርትና ምርታማነትን ከመጨመር ባለፈ አርሶ አደሮች ለገበያ በማቅረብ ሀብት እንዲያፈሩ ማስቻሉን ገልጸዋል። በሌማት ትሩፋትና በቤተሰብ ብልጽግና ረገድም ተጨባጭ ውጤት መገኘቱን የጠቀሱት ከንቲባው፤ በተለይም የግብርና ሥርዓቱን ወደ እንስሳት እርባታ በማሸጋገር አርሶ አደሩ ይበልጥ ተጠቃሚ እየሆነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። አክለውም ሸገር ከተማ ከተመሠረተ ወዲህ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገበያ ትስስርን የሚያጠናክሩ የማዕከላዊ ገበያዎችና የመሠረተ ልማት ዝርግታዎች በመከናወናቸው የሕዝቡ ተጠቃሚነት እየተረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል። ዛሬ እውቅና ከተሰጣቸው አርሶ አደሮች መካከል የፉሪ ክፍለ ከተማ ነዋሪው አቶ በቀለ ደሜ፣ ሸገር ከተማ እንደ አዲስ ከመደራጀቱ በፊት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ያመርቱ እንደነበርገልጸዋል።   ባለፉት ሦስት ዓመታት በተደረገላቸው የስልጠና፣ የቴክኖሎጂና የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ በእንስሳት እርባታና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተሰማርተው ኑሯቸውን ከማሻሻል ባሻገር ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን አስታውቀዋል። አርሶ አደር እንግዳ አርጋው በበኩላቸው፣ በተለይም የመስኖ ድንችና ስንዴን በስፋት በማምረት ከፍተኛ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። አስተዳደሩ ከጎናቸው በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረጉ ውጤታማ መሆን መቻላቸውንም አስታውቀዋል። አርሶ አደሮቹ አክለውም፣ በቀጣይ በግብርናው ዘርፍ ተግተው በመስራት ወደ ኢንቨስትመንት ለመሸጋገር ዕቅድ እንዳላቸው በመጠቆም፣ በዚህም ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ የራሳቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።    
በጋምቤላ ክልል የሰብአዊ ድጋፎችን በእራስ አቅም ለመሸፈን ለተያዘው ግብ መሳካት  የባለድርሻ አካላት ትብብር ይጠናከራል  
Sep 3, 2026 145
‎ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፡-በጋምቤላ ክልል ሰብአዊ ድጋፎችን በራስ አቅም ለመሸፈን ለተያዘው ግብ መሳካት የባለድርሻ አካላት ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ገለጹ። ተረጅነትን ለማስቀረት እየተከናወኑ ባሉት ስራዎችና በቀጣይ የበጋ መስኖ የግብርና ልማት ዙሪያ ያተኮረ የንቅናቄ ውይይት መድረክ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተካሄዷል።   ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ ለሚከሰቱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ሰብአዊ ድጋፎችን በራስ አቅም ለመሸፈን ባለድርሻ አካላትን ያሳተፉ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በክልሉ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተቀየሱ እቅዶችን ውጤታማ ለማድረግ ያለውን ሰፊ የመሬትና የውሃ ሀብት ካለው የሰው ኃይል ጋር አቀናጅቶ ለመጠቀም እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት። በዚህም ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ ለሚያጋጥሙ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች በራስ አቅም ሰብአዊ ድጋፍ ለመስጠት የመጠባበቂያ የሰብል ምርትና የበጀት ፈንድ ላይ ትኩረት መሰጠቱን አስረድተዋል። ምርታማነትን ከማሳደግ ጎን ለጎን ወቅት ጠብቆ ከማምረት ለመውጣት ለተነደፈው የበጋ ወራት የመስኖ ልማት ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል። ለዘርፉ ስኬታማነት በጋራ መረባረብ የሚገባ ሲሆን የግብአትና የባለሙያ ድጋፍ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ከመቼውም ጊዜ በላይ መስራት እንደሚገባ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው ገልጸዋል። በክልሉ ሰብአዊ ድጋፎችን በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት የ400 ሚሊዮን ብር የመጠባበቂያ ፈንድ እቅድ ተነድፎ ንቅናቄ መጀመሩንም አስረድተዋል።   በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸኔ አስቲን በበኩላቸው፣ እንደ ሀገር ከተረጅነት ለመውጣት እየተተገበረ ላለው ኢኒሼቲቭ ውጤታማነት የመንግስትም ሆነ የድርጅቱ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል። በተለይ ሕብረተሰቡ ምርታማነቱን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንዲችል ያልተቆጠበ የድጋፍና የክትትል ስራዎችን ማከናወን የግድ እንደሚለው ነው የተናገሩት። በንቅናቄ የውይይት መድረኩ ላይ የመንግስትና የድርጅት አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።  
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የአዳማ ከተማ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝ አድርጓል
Sep 3, 2026 94
አዳማ ፤ነሐሴ 28/2018(ኢዜአ )፡-የአዳማ ከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ ማድረጉን የአስተዳደሩ ከንቲባ ሃይሉ ጀልዴ ገለፁ። በከተማዋ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ ባለሃብቶች የተሳተፉበት ፎረም ተካሄዷል ።   የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ እንደገለፁት፣ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በስፋት ለማሳደግ ከተማ አስተዳደሩ በዋናነት ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል። የሕዝብ ወይም የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ዘመናዊ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ ለማድረግ ዋናው ትኩረት የተደረገው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ላይ ነው ብለዋል። በዚህም በከተማዋ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ እንዲሁም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።   የአዳማ ከተማ ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሐሲያ ኢሳ በበኩላቸው፤ በከተማዋ ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ምርቶችን ለውጭ ገበያ ለማቅረብና የተኪ ምርቶችን ለማሳደግ በተደረገው እንቅስቃሴ አበረታች ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል። በዚህም ዘርፉ የግንባታና የፍጆታ ምርቶችን በማምረት ገበያውን ለማረጋጋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የጎላ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የአዳማ ከተማ የኢንቨስተሮች ፎረም አስተባባሪ አቶ ፈይሳ አራርሳ በበኩላቸው፤ ፎረሙ በባለሀብቶችና በአስተዳሩ መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር የመሠረተ ልማትና የመሬት አቅርቦት ጥያቄዎችን በትብብር ለመፍታት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም የከተማዋን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳለጥና የባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል። ከፎረሙ ተሳታፊዎች መካከል የኩሩፍቱ የወረቀት ፋብሪካ ተወካይ አቶ ሲሳይ ጌታቸው፤ መንግሥት ባለሀብቶች በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማስቻል የኢንቨስትመንት መሬትና የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን በወቅቱ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።    
በአማራ ክልል የቴክኖሎጂውን ዘርፍ ቁልፍ የእድገት መሳሪያ ለማድረግ እየተሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
Sep 3, 2026 127
ባህርዳር ፤ ነሃሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል የቴክኖሎጂውን ዘርፍ ቁልፍ የእድገትና የመወዳደሪያ መሳሪያ አድርጎ ለመጠቀም በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ። በክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ "የኤሌክትሮኒክስ መንግስት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሰረት ነው" በሚል መሪ ቃል የፓናል የውይይት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። ርዕሰ መስተዳደሩ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ በክልሉ ፈጠራና ቴክኖሎጂን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳለጫ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል። በአማራ ክልል "ዲጂታል አማራ" በሚል በ25 ዓመቱ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላይ ቴክኖሎጂ እንደ ልማት መዳረሻ መፍጠሪያ ተደርጎ ተይዟል ብለዋል። በ25 ዓመቱ ስትራቴጂክ ግብ ላይ በ2042 የአማራ ክልል ዋነኛ ሀብት፤ የአገልግሎት መስጫ እና የኢኮኖሚ የዕድገት ምንጭ ቴክኖሎጂ እንዲሆን ይሠራል ነው ያሉት። በዚህም ዘርፉን የሚመራውን ተቋም በአዲስ በማደራጀት፣ አሰራሮችን በመዘርጋትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን አስረድተዋል። በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን የታገዘ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት ያስቻለ ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል። በቀጣይም ተቋማት ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የማምረትና አገልግሎት የመስጠት ተግባር ላይ አተኩረው እንዲሰሩ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አስገንዝበዋል። የኢፌዴሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶር) በበኩላቸው፣ በቴክኖሎጂና ፈጠራ ላይ በትኩረት በመስራት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን ማሳካት ተችሏል ብለዋል። ባለፈው አፈጻጻም የተገኘውን ተሞክሮ በመቀመርም አሁን ላይ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትን በማሟላት የዲጂታል ግብይት፣ ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆነ የመንግስት አገልግሎትና ጉልበት የቀነሰ አመራረት እውን በማድረግ ለውጥ መመዝገቡንም አስረድተዋል። ይህም የሰው ኃይሉን በኢትዮ ኮደርስ በማሰልጠን ጭምር በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ሁሉ ውጤታማና በዓለም አቀፍ ጭምር ተወዳዳሪ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በአገራችን የሚገኘው ወጣት ኃይል ራሱን በቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት በማነጽ እየመጣ ያለውን ዓለም አቀፍ ውድድር ለማሸነፍ መዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል። በፓናል ውይይቱ ላይ የፌዴራልና የክልል የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በእለቱም የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ያዘጋጀው የቴክኖሎጂ ውጤቶች አውደ ርዕይ ለእይታ ክፍት ተደርጓል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና የዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል
Sep 3, 2026 147
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና የዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት ተጨባጭ ውጤቶች መገኘታቸውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ ቴሌኮም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።   ኩባንያው ባለፈው የ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገበውን ስኬት መነሻ በማድረግ፣ በ2019 ዓ.ም የደንበኞቹን ቁጥር ለማሳደግ፣ ገቢውን ለማሳደግ እና የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማስፋፋት በርካታ ግቦችን ማቀዱን አስታውቋል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በመግለጫው እንደተናገሩት በ2019 በጀት ዓመት የቴሌኮም መሰረተ ልማትን ይበልጥ ለማዘመን የ5G እና 4G የኔትወርክ ተደራሽነትን ለማሳደግ ታቅዷል። ተቋሙ ባለፈው አንድ ዓመት የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና የዲጂታል አገልግሎቶችን በማስፋፋት አበረታች ውጤቶች ማስመዝገቡን ገልጸዋል። በ2019 በጀት ዓመት የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ይበልጥ የሚያንቀሳቅሱ አዳዲስ አሰራሮችና አገልግሎቶች እንደሚተገበሩ ተናግረው፤ 295 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ገልጸዋል። በ2019 ዕቅድ የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታውቀዋል። በበጀት ዓመቱ 1ሺህ 628 ተጨማሪ አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች የሚገነቡ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 605 ያህሉ በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎችና የቴሌኮም አገልግሎት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች መሆኑን አብራርተዋል። የ4G አገልግሎት ለተጨማሪ 300 ከተሞች ተደራሽ የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም የአገልግሎቱን ተደራሽነት 95 በመቶ ያደርሰዋል ብለዋል። የ5G አገልግሎት ለተጨማሪ 40 ከተሞች እንደሚዳረስና በአጠቃላይ የ5G ተጠቃሚ ከተሞች ቁጥር ወደ 83 ከፍ ይላል ብለዋል። ተቋሙ ባደረገው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተጨማሪ 20 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ የሚያስችል የገመድ አልባ ሞባይል ኔትወርክ አቅም በመፍጠር፣ አጠቃላይ የማስተናገድ አቅሙን ወደ 135 ነጥብ 7 ሚሊዮን ያሳድጋል ብለዋል። በፊክስድ ብሮድባንድ አገልግሎት ላይ የሚታዩ የአገልግሎት መቋረጦችን ለማስወገድና የአገልግሎት ጥራትን ከፍ ለማድረግ ተጨማሪ 150 ሺህ ደንበኞችን የተሻለ የፋይበር ቴክኖሎጂ የማዛወር ስራ እንደሚከናወን አብራርተዋል። በከተሞች የሚገኘውን የፋይበር መስመር በመጨመር 300 ኪሎ ሜትር በማስፋፋት አጠቃላይ አቅሙን ከ15 ሺህ ኪሎሜትር በላይ ከፍ ለማድረግ ማቀዱን አስታውቀዋል። ኢትዮ ቴሌኮም ያስቀመጣቸውን እነዚህን ግቦች ለማሳካት የቴክኖሎጂ አጋርነቱን እንደሚያጠናክር እና በሰው ሃይል ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።
በአማራ ክልል ዲጂታል 2030ን በተሳካ መልኩ እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው
Sep 3, 2026 105
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ዲጂታል 2030ን በተሳካ መልኩ እውን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለፀ። በባሕር ዳር ከተማ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ ተከፍቷል።   በአውደ ርዕዩ የመክፈቻ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው እንደገለጹት፤ የኤግዚቢሽኑ ዋና ዓላማ በክልሉ ዲጂታል 2030 ን እውን ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ማሳየትና ማስተዋወቅ ነው። አውደ ርዕዩ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የፈጠራ ሥራዎቻቸውንና የቴክኖሎጂ ውጤቶቻቸውን ለሕዝብና ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡበት ዕድል እንደሚፈጥርላቸው አብራርተዋል። ይህም የቴክኖሎጂ ፈጠራን በማስፋፋት የተያዘውን ሀገራዊና ክልላዊ የዲጂታላይዜሽን ግብ ለማሳካት እየተሠራ መሆኑን የሚያመላክት ነው ብለዋል። በተጨማሪም በኤግዚቢሽኑ በተለያዩ ተቋማት የለሙ 35 የተለያዩ ዲጂታል ሥርዓቶች (Digital Systems) በይፋ ተመርቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ አስታውቀዋል።
ስፖርት
ማንችስተር ሲቲ የቼልሲውን ኤንዞ ፈርናንዴዝን ለማስፈረም ተስማማ
Sep 1, 2026 267
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦ ማንችስተር ሲቲ በዝውውር መስኮቱ ማብቂያ ቀን የቼልሲውን አማካይ ኤንዞ ፈርናንዴዝን በ125 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል። የ25 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አማካይ ከቤንፊካ በ107 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ቼልሲ የተቀላቀለው እ.አ.አ በ2023 ነበር። ተጫዋቹ ቼልሲ ከፉልሃም ጋር ባደረገው የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ የነበረ ቢሆንም፣ ከሉተን ጋር በካራባኦ ካፕ እንዲሁም ከብራይተን ጋር በተደረገው የሊጉ መርሐ ግብር አልተጫወተም። ይህ ዝውውር ሊቨርፑል ባለፈው ዓመት በክረምቱ የዝውውር መስኮት ማጠናቀቂያ ቀን የኒውካስትል ዩናይትዱን አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳክ ለማስፈረም ከከፈለው የእንግሊዝ ክብረ ወሰን ክፍያ እኩል መሆኑን ስካይ ስፖርትስ ዘግቧል። ፈርናንዴዝ ወደ ማንችስተር ሲቲ ማምራት እንደሚፈልግ ያሳወቀ ሲሆን፣ በኢትሃድ ከቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኙ ኤንዞ ማሬስካ ጋር እንደገና ይገናኛል። ተጫዋቹ በቀጣይ ሰዓታት ውስጥ የሕክምና ምርመራዎችን አድርጎ ዝውውሩን ሙሉ በሙሉ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል። ቼልሲ አርጀንቲናውን አማካይ የሚተካ ሌላ ተጫዋች ለማስፈረም እየሰሩ ይገኛሉ። ክለቡ የሮማውን ማኑ ኮኔ እና የሞናኮውን ላሚን ካማራን ለመግዛት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ የሚገኙ ሌሎች አማካዮችንም እየተመለከተ ይገኛል።
አርሰናል ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
Sep 1, 2026 305
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል አስቶንቪላ 1 ለ ዐ አሸንፏል። ማምሻውን በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቡካዮ ሳካ በ59ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል። የ24 ዓመቱ የክንፍ መስመር ተጫዋች በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል። እምብዛም ግልጽ የግብ እድሎች ባልተፈጠሩበት ጨዋታ አርሰናል ያገኘውን የግብ እድል በሚገባ ተጠቅሟል። አስቶንቪላ ወደ አርሰናል የግብ ክልል በተደጋጋሚ ጊዜ ቢደርስም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ ተስኖታል። በ75 ሚሊዮን ፓውንድ ከኒውካስትል ዩናይትድ ወደ አርሰናል የተዘዋወረው ብሩኖ ጉማራይሽ ተቀይሮ በመግባት የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል ተከታታይ ድሉን አግኝቷል። በአንጻሩ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በርካታ ቁልፍ ተጫዋቾቹን ያጣው አስቶንቪላ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል። አስቶንቪላ በሁለቱ የሊግ ጨዋታዎች ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ አልቻለም። በሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አስቶንቪላ ከአዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ ጋር ይጫወታል። በለንደን ደርቢ አርሰናል ከቼልሲ የሚያደርገው ጨዋታ ከወዲሁ ተጠባቂ ነው። የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።
አካባቢ ጥበቃ
‎የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ ነው
Sep 2, 2026 288
‎አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ መሆኑ ‎የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አባንግ ኩመዳን ገለጹ። ከመላው የሀገሪቱ የተውጣጣ የወጣቶች ቡድን በሦስት የአፍሪካ ሀገራት ነገ የሚጓዝ ይሆናል። ‎የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አባንግ ኩመዳን እንደገለጹት፤ ወጣቶቹ የሚጓዙት ጋና፣ ዚምባብዌና ናይጄሪያ ነው። በዚህ የጉዞ መረሃ ግብር ሀያ አራት ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን፤ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን በመትከል ልምድ እንደሚያካፍሉም አስታውቀዋል። ‎መርሃ ግብሩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም የብልጽግና ወጣት ክንፍ በፓኪስታን የችግኝ ተከላ ማካሔዳቸውን ገልጸዋል። ‎የልዑካኑ ጉዞ የልምድ ልውውጥ ከማድረግ በተጨማሪ ወንድማማችነትን ለማጠናከር የሚያግዙ ተግባራትን እንደሚያከናውን አስታውቀዋል። ‎በቀጣይም ወጣቶች ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሄድ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማከናወን የኢትዮጵያን ልምድ የማካፈል ተግባርን ያጠናክራል ብለዋል። ‎በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በስኬታማነት እየተከናወነ ይገኛል። ‎በዚህ ዓመት ብቻ ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በአንድ ጀምበር መተከላቸው ይታወሳል። ‎ይህ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዓለም አቀፍ እውቅና እያገኘ ሲሆን የተለያዩ ሀገራትም ተሞክሮውን እየወሰዱት ይገኛሉ።  
በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል
Sep 2, 2026 588
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ከነሃሴ 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜን አምስት ቀን 2018ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የሚኖረውን የአየር ፀባይ ሁኔታ በተመለከተ ለኢዜአ መግለጫ ልኳል። በመግለጫውም ነሀሴ ወር የክረምት የመጨረሻ ወቅት በመሆኑ በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የዝናብ መጠን እንደሚቀንስ በማመላከት ለረጅም ጊዜ ደረቅ ሆነው የሰነበቱት ደቡብና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸውን እንደሚያስተናግዱ ጠቁሟል። በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅና በመካከለኛው ኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚቀነስ ነገር ግን በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በስርጭትም በመጠንም የተሻለ ዝናብ እንደሚያገኙ በመግለጫው ተመላክቷል። በሚቀጥሉት አስር ቀናትም ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። ማኅበረሰቡም ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ የሚኖረውን የእርጥበት ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የግብርና ስራቹን እንዲያከናውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ከሚያስተናግዱ ቦታዎች መካከል ቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር የምዕራብ ፣መካከለኛ ፣ደቡብ እና ሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን፣ የምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ካማሺ፣ መተከል፣ አሶሳ ዞኖች እንደሚገኙበት ከመግለጫው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ሁሉም ሸዋ ዞኖች፣ አኝዋክ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ጉራጌ ፣አዲስ አበባ ፣ድሬዳዋ፣ የምዕራብ ፣የሰሜን ምዕራብ ፣መካከለኛው፣ ምሥራቅ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ፣የሲዳማ አብዛኛው የክልሉ ዞኖች ደግሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ከሚያስተናግዱ አካባቢዎች መካከል መሆናቸው ተጠቁሟል። ኢንስቲትዩቱ ቀላል፣መካከለኛ እና ከባድ እርጥበትን የሚያስተናግዱ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ፣ የመኸር ሰብል አብቃይ ፣ አርብቶ አድርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ይህን የአየር ሁኔታ ለግብርና ስራዎቻቸው እንዲያውሉ አስገንዝቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መካከለኛ እና ከባድ የዝናብ መጠን የሚያስተናግዱ አካባቢዎች ተደፋታማ ማሳዎች ላይ የተዘጉ የማፋሰሻና የማንጣፈፊያ ቦዮች ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሰብል በሽታን አረምን አስቀድሞ መከላከል ፣የአፈር መሸርሸር ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ማከናወን፣ እና አርሶ አደሮችም የማሳ ጉብኝት በየጊዜው በማድረግ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስቧል። ከቀላል እስከ መካከለኛ እርጥበት የሚያገኙ ቦታዎች ደግሞ የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል፣ የዝናብ ውሀን በማሰባሰብ በደረቅ ወቅቶች መጠቀም ፣የአፈር ውስጥ ትነትን መጠንን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን ፣የእንስሳት ግጦሽ ሳርን በአግባቡ መያዝ ተገቢ ነውም ተብሏል። ለተከታታይ አስር ቀናት የሚቆየው አየር ፀባይ ሁኔታም የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።
በአፍሪካ አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል
Sep 2, 2026 455
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ የአየር ንብረት መዛባትንና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ገቢራዊ ማድረግ እንደሚገባ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን የብሔራዊ የልማት ዕቅዷ አካል ማድረጓም ተገልጿል። የአፍሪካ ቀጣና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም ፎረም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። የቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 ይፋ የተደረገ ሲሆን እስከ 2027 እያንዳንዱን ሰው በአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና በተፈጥሮ አደጋዎች መጠበቅ የሚያስችል ኢንሼቲቭ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ከተመድ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቢሮና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የአፍሪካ የተቀናጀ አይነተ ብዙ አደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ እርምጃ ሥርዓት ተግባራዊ አድርጓል።   የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሀና አበበ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፎረም ወቅታዊና ተገቢ ነው። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ መዛባት ድርቅ፣ ጎርፍ እና ሌሎችን አደጋዎችን በተደጋጋሚ እያስተናገደች መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ሴቶችና ህፃናት ጨምሮ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች የአደጋው ገፈት ቀማሽ እየሆኑ ነው ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የውስጥ የፋይናንስ አቅምን ማጎልበትና ተቋማዊ አንድነት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የአየር ንብረት መዛባትና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን የብሔራዊ የልማት ዕቅዷ አካል ማድረጓን ጠቅሰው፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በፋይናንስና ሌሎችም ተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል። ማንም ሀገር ብቻውን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስትራቴጂን ውጤታማ ማድረግ እንደማይችል ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራትና የተለያዩ አጋር አካላት ጋር በአይነተ ብዙ የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።   በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዘላቂ አካባቢና ብሉ ኢኮኖሚ ዳይሬክተር ሀርሰን ኒያምቤ፤ በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ማህበረሰቡን አደጋን የመቋቋም አቅም መገንባትና ከአደጋ መጠበቅ ይገባል ብለዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2027 እያንዳንዱን ሰው ከአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና መሰል አደጋዎች መጠበቅ የሚለውን ግብ ለማሳካት ውይይቱ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ጎርፍና የተራዘመ ደርቅ፣ በማህበረ-ኢኮኖሚ፣ እና በሌሎች አደጋዎች ተጋላጭነት ተባብሶ መቀጠሉን በመግለጽ፤ አፍሪካውያን ውስጣዊ ትብብራቸውን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል። አደጋ ድንበር የለውም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በአይነቱ ብዙ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የአባል ሀገራቱን አቅም ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።   በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ቢሮ ዳይሬክተር ኤግነስ ኪጃዚ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በአፍሪካ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የአመራር ቁርጠኝነት እያደገ በመምጣቱ መሻሻል እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች በፍጥነትና በተወሳሰበ ሁኔታ ተባብሰው ቀጥለዋል ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን ለመቆጣጠር የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በሀገራት የተቀናጀ አሰራር መምራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የ2027 ግብ ጠቃሚ መሰረት መሆኑን በመግለፅ፤ በአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ለቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ግንባታ ዘላቂና እምነት የሚጣልባቸው መሆን አለባቸው ብለዋል። በአፍሪካውያን መካከል ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ ተቋማትን መገንባት እንደሚገባ በመጥቀስ፤ የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የመጀመሪያው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ይካሄዳል - የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
Sep 1, 2026 197
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግርና ዘላቂ የኢንቨስትመንት እድል የሚያሰፋ የመጀመሪያው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አስታውቀ። የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ካሳሁን ማሞ፤ ምክር ቤቱ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀውን የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የኢትዮጵያን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትና ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚደረገውን ሽግግር ለማፋጠን ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ፎረምና ኤግዚቢሽኑም ፖሊሲ አውጪዎች፣ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና የአረንጓዴ ቢዝነስ ኩባንያዎችና አልሚዎች በተሳተፉበት ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማላቅ ዘላቂ ሥነ-ምህዳራዊ ዕይታን ያማከለ የቢዝነስና የኢንቨስትመንት እንዲጎለብት ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ረገድ ከጀርመን ዓለም አቀፍ የትብብር ድርጅት እና ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር የአረንጓዴ ልማትና ዘላቂነት ማዕከል ማቋቋሙን አመልክተዋል። የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽንም ጤናማ ሥነ-ምኅዳርን የተከተለ የታዳሽ ኃይልና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን በማጠናከር የዘርፉ ተዋናዮች ምርትና አገልግሎታቸውን እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል። መድረኩም በአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትንና ሥራ ፈጣሪዎችን በማገናኘት አዳዲስ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር በማፋጠን ዘላቂ ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋትና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማላቅም ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል።   በኔዘርላንድ የልማት ድርጅት የሊዌይ የፕሮግራም ማኔጀር ሔለን ጌታው በበኩላቸው፤ መድረኩ ከአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው ብለዋል። ፎረሙም በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ አልሚዎችን የፋይናንስ፣ የገበያ፣ የቴክኖሎጂና የመረጃ ተግዳሮቶች በመለየት መፍትሔ የሚመላከትበት ጠቃሚ መድረክ እንደሚሆንም ገልጸዋል። በተጨማሪም ባለድርሻ አካላትን በማገናኘት የገበያ ትስስርና የድጋፍ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል አክለዋል።  
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1544
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1207
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች።   ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 1485
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል - አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና
Jul 29, 2026 2081
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርጉ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው እና የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ምክር ቤቱ አጀንዳ 2063 እና የህብረቱ መሪ ሀሳብን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የእርስ በእርስ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያሳዩት ፍላጎት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ በበጎ ፈቃደኝነት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይፋ ማድረጋቸው የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት የኢትዮጵያንና የኬንያን ፈለግ በመከተል ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራት የገቧቸውን ቃል ኪዳኖችና ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መተግበር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ለሚኒስትሮችና ሌሎች ልዑካን ላደረገችው አቀባበልም አመስግነዋል።
ሐተታዎች
የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች
Aug 28, 2026 290
አዲስ አበባ ነሀሴ 22/2018 (ኢዜአ) የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Homegrown Economic Reform) እቅዶችን በመተግበር በበርካታ ዘርፎች መሠረታዊ ለውጦችን እና ስኬቶችን ማስመዝገብ ተችሏል። በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል (አይሲቲ)፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ከማሳደግ ባሻገር የወደፊት ዘላቂ እድገት መሠረት ያኖሩ መሆኑን መናገር ይቻላል። በመሆኑም በአምስቱ ዋና ዋና ሴክተሮች የመጡ ውጤቶችና የተመዘገቡ ስኬቶችን በወፍ በረር እንቃኛለን። 1. በግብርና ዘርፍ የስንዴ ምርትና የውጭ ኤክስፖርት: የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መስፋፋት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት አስቀምጧል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ ሀገር መላክ የቻለችበትን እመርታዊ ስኬትም አሳይቶናል። የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭን በመተግበር በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና የማር ምርት እንዲሁም በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሩዝና ሻይ ልማትም ባለፉት አምስት አመታት እመርታዊ ለውጥ ተመዝግቧል። አርሶ አደሩ የመሬትና የውሃ ሀብቶችን አቃፊ በሆነ መንገድ በመጠቀም በዓመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችልበት አሰራር ተዘርግቷል። በዚህም የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሁነኛ የገቢ ምንጭ የሆነበትን እድል ፈጥሯል። ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የመቻል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል። በተለይም ደግሞ የቡና ምርታማነትና ጥራት በማደጉ ምክንያት በኤክስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማገኘት ተችሏል።   በዘርፉ በቀጣይም የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሜካናይዜሽን በማስደገፍ ምርታማነትን የማሳደግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የዝናብ ጥገኝነትን ለመቀነስ መጣር እንዲሁም የግብርና ምርቶችን ጥራት በማሻሻልና በማቀነባበር ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ዋጋ ማሳደግ ተገቢ ይሆናል። 2. የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ንቅናቄ በመፍጠር ቀደም ሲል ተቆልፈው የነበሩና በዝቅተኛ አቅምያመርቱ የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። የሀገር ውስጥ የምርት ፍላጎትን በመሸፈን ለውጭ ሀገር ምርቶች ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪም መቀነስ አስችሏል። ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የህግና የአሰራር ሁኔታዎችን በመፍጠር በርካታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል። ከተገነቡት የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮች (IAIPs) ጋር አርሶ አደሩን በማስሳሰር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲጠናከር ተደርጓል። የአምራች ዘርፉ መስፋፋት ለብዙ ሺህ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር የታቸለበት ሆኗል። በቀጣይም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በኃይል፣ በሎጂስቲክስና በግብአት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በመደገፍ ኤክስፖርትን ማሳደግ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች 80% እና ከዚያ በላይ የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት፣ በህዝብና በግል አጋርነት (PPP) አማካኝነት በትልልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ላይ የግሉን ዘርፍ አሳትፎ ማስፋፋት ትኩረት የሚደረግበት ይሆናል።   3. የዲጂታል (አይሲቲ) ዘርፍ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስልት ስኬቶችን በማስቀጠል ወደ "ዲጂታል 2030" እቅድ መሸጋገር ተችሏል። በ"መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በሌሎች ፖርታሎች አማካኝነት ህዝባዊ አገልግሎቶችን በበይነ-መረብ (Online) የመስጠት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዜጎችን መረጃ ማዕከላዊ የሚያደርግና ለፋይናንስ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች መሠረት የሆነውን የፋይዳ መታወቂያ ፕሮጀክት በላቀ መልኩ ማሳካት ተችሏል። የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኮደር ስልጠናም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ ታላቅ ሀገራዊ የስልጠና መርሃ ግብር ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።የዲጂታል አገልግሎቶች መዘርጋታቸው የፊት ለፊት ግንኙነትን በመቀነስ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የኢንቨስትመንት ምህዳሩን አሳልጧል። የቴሌኮም ዘርፍ ውድድር: የቴሌኮም ዘርፉን ክፍት ማድረግን ተከትሎ የኢንተርኔትና የኔትወርክ ተዳራሽነትንና ጥራትን በየገጠሩ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን እና የባንክ አገልግሎቶችን ይበልጥ ዘመናዊና የተቀናጁ ማድረግም አስፈላጊ ይሆናል። የሀገሪቱን የዲጂታል መሠረተ ልማት ከሳይበር ጥቃቶች የመጠበቅ አቅምን ማጠናከር። 4. የማዕድን ዘርፍ በዘርፉ ይስተዋል የነበረውን ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ በመግታት ህጋዊ አሰራርና ቁጥጥር እንዲሰፍን ተደርጓል። የህግና መመሪያዎች ማሻሻያ በማድረግ የማዕድን ዘርፉን ለውጭና ሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ማራኪ የሚያደርጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የወርቅ፣ የከሰል ድንጋይ፣ የሲሚንቶ ግብአቶችና የከበሩ ድንጋዮች ምርትን በማሳደግ ዘርፉ የሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ እንዲሆን ተሰርቷል። በተለይም የከሰል ድንጋይ ምርትን በሀገር ውስጥ አምርቶ በመተካት ለፋብሪካዎች ግብአት ማቅረብ ተችሏል። 5. የቱሪዝም ዘርፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)አነሳሽነት የተጀመሩት "ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች በመላ ሀገሪቱ በርካታ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መገንባት ተችሏል። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶች የከተሞችን ውበትና ለኑሮ ምቹነት ከመጨመራቸው ባሻገር ለከተማ ቱሪዝም ትልቅ እድል ፈጥረዋል። አዲስ አበባ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፈረንሶችን ባካሄደችበት የዲፕሎማሲና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን አጠናክራለች።   የሀገሪቱን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች የመጠበቅ፣ የማደስና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል። በድምሩ ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች ሀገሪቷን ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ማሸጋገር አስችለዋል። በመሆኑም እነዚህን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የታቀዱትን የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በተቀናጀ መልኩ መተግበር፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የግሉን ዘርፍ አሳታፊነት ማሳደግ በቀጣይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ዋነኛ የቤት ስራ ይሆናል።  
የአረንጓዴ አሻራ ስኬት፦ኢትዮጵያን የአየር ንብረት ጥበቃ ሞዴል ያደረገ ኢኒሼቲቭ
Aug 23, 2026 502
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረው በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን ከ54 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እ.አ.አ በ2027 በኢትዮጵያ በሚካሄድበት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ብዛት 65 ቢሊዮን የማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ነው።ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ምርታማነትን በማሳደግ፣ የደን ሽፋንን በመጨመር፣ የተራቆተ መሬትን ወደ ነባር ይዞታው እንዲመለስ በማድረግ እና አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። በዚህም በ2011 ዓ.ም 17.2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው ሥራ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ ችሏል።   ይህ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።በሁለተኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዋን ያስተዋወቀች ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራትም ለአህጉሪቱ ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እያከናወነች ላለው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠበት እና የሀገሪቱን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ውጤት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በመለገስ የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን በተግባር አሳይታለች።ይህም አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትንና አዎንታዊ የቀጣናዊ ትስስር ድልድይን እየገነባ ይገኛል። የድንበር ተሻጋሪ የወንዝ ተፋሰሶችን በመንከባከብ፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን ለጎረቤት ሀገራት በማዳረስ እና በጋራ ድንበሮች አካባቢ የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ እያከናወነችው ያለው ሥራ አህጉራዊ ሰላምና ትብብርን የሚያጎለብት አዲስ የዲፕሎማሲ መንገድ ከፍቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች የአህጉሪቱን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች ሆናለች።   ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነገር ግን ለጉዳቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ የአፍሪካ ሀገራት ፍትሃዊ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኙ ድምፅ በመሆን አህጉራዊ መሪነቷን አስመስክራለች። ይህም አፍሪካውያን በራሳቸው ሀገር በቀል መፍትሔዎች የአየር ንብረት ጥበቃን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ለአካባቢ ጥበቃ አርአያ የሚሆን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲሉ አድንቀውታል።   ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ከመጠቀም፣የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ እና ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር አጣጥማ የምታካሂደው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ላይ እውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።
ረብጣ ገንዘብ ከወጣባቸው ዝውውሮች እስከ አነጋጋሪ የህግ ለውጦች ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ምን ይዞ መጣ?
Aug 21, 2026 500
በሙሴ መለሰ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቀው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሰኔ እና ሐምሌ ወራት የተካሄደውን የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተከትሎ፣ ለተጫዋቾች በቂ የእረፍት ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከተለመደው አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲጀምር ተደርጓል። የመክፈቻው ጨዋታ በኢምሬትስ ስታዲየም የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን አርሰናል እና ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ በተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህ አዲስ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ከ2.14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርገዋል። ይህ የወጪ መጠን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች የአውሮፓ አራት ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣልያን ጀርመንና ፈረንሳይ) በጥምረት ካወጡት የገንዘብ መጠን በላይ ሆኗል። ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በመዘዋወር የክረምቱ ውዱ ተጫዋች መሆን ችሏል። ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አምርቷል። በተጨማሪም ሳንድሮ ቶናሊ ከኒውካስል ወደ ቶተንሃም በ100 ሚሊዮን ፓውንድ፣ እንዲሁም ብሩኖ ጉማሬሽ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል በ75 ሚሊዮን ፓውንድ መዘዋወራቸው የክረምቱን የዝውውር ገበያ ከሚጠቀሱ ዝውውሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዝውውር ወጪው ባሻገር፣ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በአዳዲስ አሰልጣኞች የታጀበ ሆኗል። በሊጉ ታሪክ ከፍተኛው በተባለ ደረጃ ዘጠኝ ክለቦች ውድድሩን በአዲስ አሰልጣኞች ይጀምራሉ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን ላይ በሊጉ ረጅም ጊዜ (ሰባት ዓመታት) የቆየው አሰልጣኝ ሆኗል። የቼልሲው ዣቢ አሎንሶ፣ የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ እና የሊቨርፑሉ አንዶኒ ኢራኦላ ከአዳዲሶቹ አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳሉ። ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ በቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዓመታቸውን ይጀምራሉ። የሊጉ የተሳታፊዎች ስብጥርን በተመለከተ፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ከሃል ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ጋር በመሆን ከታችኛው ሊግ አድገው ሊጉን ተቀላቅለዋል። በተቃራኒው ዌስትሃም ዩናይትድ፣ በርንሌይ እና ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ባለፈው የውድድር ዘመን መውረዳቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም የእንግሊዝ ክለቦች ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ባሳዩት አስደናቂ ብቃት ምክንያት፣ በዚህ የውድድር ዘመን ክብረ ወሰን የሆነ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ። አርሰናል፣ አስቶንቪላ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ እና ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ብራይተን በኮንፈረንስ ሊግ አገራቸውን ይወክላሉ። የሊጉ አስተዳደር የክለቦችን የፋይናንስ ወጪ የሚቆጣጠር አዲስ የወጪ ገደብ (Squad Cost Ratio) መመሪያን ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም መሠረት ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ እና ለዝውውር የሚያወጡት ጠቅላላ ወጪ ከገቢያቸው 85 በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ህጉን የሚጥሱ ክለቦችም የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ይገጥማቸዋል። የጨዋታ ፍጥነትን ለመጨመርና ሰዓት ማባከንን ለመግታት በርካታ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች በይፋ ስራ ላይ ይውላሉ። በእጅ ውርወራ (Throw-in) እና በመልስ ምት (Goal-kick) ላይ ሰዓት ለሚያባክኑ ተጫዋቾች ዳኛው አምስት ሴኮንድ የሚቆጥር ሲሆን፣ ጊዜ ካለፈ እጅ ውርወራው ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣል፤ የመልስ ምት ላይ ከሆነ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ያገኛል። ሌላው ሰዓት ማባከንን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ተጫዋቾች ታክመው ከወጡ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ አንድ ደቂቃ ውጭ እንዲጠብቁ የሚያስገድደው ደንብ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሚቀየሩበት ወቅት ከሜዳ ለመውጣት የ10 ሴከንድ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ይሁንና ጊዜው ካለፈ ተቀያሪው መግባት የሚችለው ጨዋታው በሚቀጥለው ጊዜ ሲቆም ብቻ ይሆናል። በዚህ የውድድር ዘመን የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔዎችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አጠራጣሪ ከሆነ ቫር ጣልቃ የመግባት ስልጣን ተሰጥቶታል፤ እንዲሁም በጨዋታ ወቅት በቫር እና በሜዳ ላይ ዳኛው መካከል የሚደረጉ የድምፅ ውይይቶች በሊጉ የጨዋታ ማዕከል በኩል ለደጋፊዎች በቀጥታ ይፋ ይደረጋሉ። በአጠቃላይ፣ የዘንድሮው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከአዳዲስ የህግ ለውጦች፣ ከከፍተኛ የዝውውር ወጪዎች እና አዳዲስ የአሰልጣኞች ሹመት ጋር ተያይዞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን ስቧል። አርሰናል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ፣ ማንቸስተር ሲቲ ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችና ክለቦች ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ አስደሳች እና አጓጊ የእግር ኳስ ጊዜን እንደሚያሳልፉ አያጠራጥርም።
ቡሄ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ምስረታ ታሪካዊ ቁርኝት
Aug 19, 2026 699
በሙሴ መለሰ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን የቡሄ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ባለበት በዚህ ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አጀማመሩንና ምስረታውን ከዚህ በዓል ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚታወስበት ነው። የክለቡ ምስረታና የቡሄ በዓል (የሆያ ሆዬ ጨዋታ) ቀጥተኛና የማይነጠል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ክለቡ በመስረታው ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት ቀርፎ የመጀመሪያውን ማሊያ ለመግዛት የበቃው በዚህ ዕለት በተሰበሰበ የሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ነበር። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መጀመሪያ ሲጠነሰስ በጆርጅ ዱካስና በአየለ አትናሽ አማካኝነት የነበረ ቢሆንም፣ ክለቡን በይፋ አደራጅቶ ለማቋቋም ግን የግድ የፋይናንስ አቅም ወይም ገንዘብ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ግን በሃገር ፍቅር ስሜት የተነሱት ዘጠኙ ወጣቶች ማለትም አየለ አትናሽ፣ ጆርጅ ዱካስ፣ ዮሐንስ ጥላሁን፣ ገብረመድህን ተፈሪ፣ ተፈራ ገብረእግዚአብሔር፣ ዓለማየሁ እጅጉ፣ መኮንን ደምሴ፣ አስፋው ያዕቆብ እና ክልቱ አያኖ ክለቡን በሚመሰርቱበት ወቅት ቤሳ ቤስቲን እንኳ ኪሳቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተሰብስበው በሰፊው ተወያዩ። በዚህ የውይይት ወቅት ነው ገንዘብ ለማግኘትና የክለቡን መመስረት እውን ለማድረግ የቡሄ ቀን እጅግ መልካምና ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የተረዱት። ዘጠኙ ወጣቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተው በታሪካዊው የቡሄ ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 1927 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ቡሄ ጨፍረው (ሆያ ሆዬ ብለው) በሚያገኙት ማናቸውም ነገር የክለቡን የመጀመሪያ ማሊያ ለመግዛት ቁርጥ የሆነ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በዚያን ጊዜ የነበረው የባህል ልማድ አሁን ካለው የተለየ በመሆኑ፣ ቡሄ ሲጨፈር የሚሰጠው ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ዳቦ ነበር። በመሆኑም ዘጠኙ ተጫዋቾችና መስራቾች ቀደም ሲል ከሚጨፍሩበትና ለምደውት ከነበረው አካባቢ ራቅ ብለው በመንቀሳቀስ በየቤቱ በር እያንኳኩ በደመቀ ሁኔታ ጨፈሩ፤ በዚህም ጥረታቸው በርካታ ቁጥር ያለው የሙልሙል ዳቦ በአንድነት ማሰባሰብ ቻሉ ታሪካዊውን ስራ ሰሩ። ይሁን እንጂ የተሰበሰበውን ይህንን በርካታ ዳቦ ወደ ጥሬ ገንዘብ ለመቀየር አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ሰራተኛ ሰፈር ለሚገኙ ወዛደሮች ለመሸጥ ዳቦውን በከረጢት ይዘው ጉዟቸውን ጀመሩ። በዚህ የጉዞ መስመር ላይ ሳሉ ግን ያልተጠበቀ ፈተና ገጠማቸው፤ በመንገድ ላይ ያገኟቸው “ዱርዬዎች” ከተሰበሰበው ዳቦ ላይ የተወሰነውን ነጠቋቸው። ወጣቶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዟቸውን በመቀጠል የተረፈውን ዳቦ ለሰራተኛ ሰፈሩ ወዛደሮች በመሸጥ ማሊያ መግዣ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው አስገቡ። ከዳቦው ሽያጭ የተገኘችው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በወቅቱ መገበያያ በትክክል ሁለት ጠገራ ብር ነበረች። የክለባችው የመጀመሪያ መለያ ቡናና ነጭ ነበር። ቡናና ነጭ መሊያን የገዙት ግን ፈልገው አልነበረም በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው በሁለት ጠገራ ብር ከፒያሳ «ግሪካዊ አውግስታስ ዱስ» ከተባለ ሱቅ በርካሽ ስላገኙት ነበር። ይህ በቡሄ ዕለት የተጀመረው ታሪካዊ የማሊያ ግዢ በኋላ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም. በይፋ ተመሠረተ። ክለቡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ማዕረግንና ቀዳሚነትን ተቀዳጀ። በ1928 ዓ.ም. በይፋ የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ ያደረገው ከ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ነበር። በዚሁ ታሪካዊ የመጀመሪያ ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበረው የ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ ሲያመራ፣ አስቀድመው ከተመረጡትና ቡድኑን ካደራጁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ባልታወቀ ምክንያት ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ድንገተኛ መቅረት ምክንያት ቡድኑ በሰው ጎደሎ ለመጫወት በተገደደበት ወሳኝ ሰዓት፣ መስራቾቹ በሜዳው አቅራቢያ መንገድ ላይ ሲጫወት ያገኙትን አንድ ታዳጊ ወጣት ተመለከቱ። ይህ ታዳጊ በወቅቱ ገና የ14 ዓመት ዕድሜ የነበረውና በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የሆነው ይድነቃቸው ተሰማ ነበር። ወጣቶቹም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ቡድኑን እንዲሞላ ድንገት ጋበዙት፤ እርሱም የቀረበለትን ጥሪ በደስታ ተቀብሎ በአጋጣሚ ወደ ሜዳ ገባ። ያለ ምንም ልምምድና ዝግጅት በድንገት የተሰለፈው ይድነቃቸው ተሰማ፣ በሜዳ ላይ ያሳየው አስደናቂ ችሎታና ቅልጥፍና ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፣ ለክለቡ የመጀመሪያውን ድል ያስገኙትን ሁለቱንም ታሪካዊ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ይኸው መንገድ ላይ ተገኝቶ በድንገት የተሰለፈው ታዳጊ ይድነቃቸው ነበር። ይህ ብቃት ገና በታዳጊነቱ በክለቡ ውስጥ ያለውን የማይተካ ቦታ ከማረጋገጡም በላይ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን የድል ጉዞ በደመቀ ሁኔታ እንዲጀመር አድርጓል። ቡሄ በዓል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያላቸው ታሪካዊ ቁርኝት የክለቡን ጥልቅ ህዝባዊና ባህላዊ መሰረት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ ፋና ወጊ የሆነው ይህ ታላቅ ክለብ፣ በታሪካዊቷ የነሐሴ 13 ቀን የቡሄ ዕለት የመስራቾቹ የ"ሆያ ሆዬ" ጨዋታና ከተሰበሰበው ሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ባገኟት ሁለት ጠገራ ብር የመጀመሪያውን ቡኒና ነጭ ማሊያ መግዛቱ፣ ክለቡ ከህዝብ ማህፀን የወጣ የህዝብ ሀብት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ከባህልና ከትውፊት ጋር የተቆራኘ አስደናቂ አጀማመር፣ ከጊዜ በኋላ በ1928 ዓ.ም. ለይፋዊ ምስረታው በር ከፋች ከመሆኑም በላይ፣ በታሪካዊው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ታላላቅ መሪዎችና ድንቅ ተሰጥኦዎች እንዲፈጠሩ መሰረት የጣለ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።
ትንታኔዎች
የተኪ ምርት ስትራቴጂካዊ ሚና
Sep 3, 2026 93
የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እና የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን መዛባት በዘላቂነት ለመቅረፍ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ እያካሄደ ይገኛል። ይህ የተኪ ምርት ስራ ጅማሮ በዋናነት ያነጣጠረው በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬን በሀገር ውስጥ በማስቀረት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ላይ ነው። ቀደም ሲል የነበሩ የተበታተኑ የማምረት ሙከራዎችን ወደ ተቋማዊ አሰራር ለመቀየር ይፋዊ የተኪ ምርት ስትራቴጂ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ጸድቆ ወደ ስራ ገብቷል። ይህ ስትራቴጂ ለቀጣዮቹ አስር ዓመታት የሚቆይ ፍኖተ ካርታ ያስቀመጠ ሲሆን፣ ለትግበራው መፋጠን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ እንደ ትልቅ ሞተር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።   ሀገራዊ ንቅናቄው በ2016 ዓ.ም ተግባራዊ መሆን ለጀመረው ብሔራዊ የተኪ ምርት ስትራቴጂ ትልቅ አቅም የፈጠረ ነው። የስትራቴጂው መውጣት እና ወደ ተግባር መግባት በሀገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ማስገኘት ጀምሯል። ትልቁ እና ዋነኛው ፋይዳም የውጭ ምንዛሬን ማዳን ሲሆን በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በሀገር ውስጥ በተመረቱ ተኪ ምርቶች ከ5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ አምራቾች በገበያ ላይ ያላቸው የምርት ድርሻ ወደ 45 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ የፋብሪካዎች አማካይ የማምረት አቅምም ከነበረበት 47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ብሏል። ይህ መነቃቃት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ከመሆኑም በላይ የፋብሪካዎችን የጥሬ ዕቃ ፍላጎት ከሀገር ውስጥ የግብርና እና የማዕድን ምርቶች ጋር በማስተሳሰር የአቅርቦት ሰንሰለቱን አጠናክሮታል። ይህንኑ ሀገራዊ ጥረት እና የተመዘገቡ ስኬቶችን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ መድረኮች ላይ የዘርፉን ስልታዊ ጠቀሜታ በተደጋጋሚ አንስተዋል። በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የምግብ እና የማዳበሪያ አቅርቦት መስተጓጎል በመጥቀስ፣ የሀገር ውስጥ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት ኢትዮጵያን የምግብ እጥረት እንደታደጋት ገልጸዋል። ተኪ ምርት ለኢትዮጵያ የብሔራዊ ደህንነት እና የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ቀደም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ይወጣባቸው የነበሩ የድንጋይ ከሰል እና የችፑድ ምርቶች አሁን ላይ በሀገር ውስጥ በስፋት እየተመረቱ መሆናቸውን አንስተዋል። የሀገር ውስጥ አምራቾች ጥራትን መሰረት አድርገው በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከተኪ ምርት ስራዎች ያገኘውን ስኬት ይበልጥ ለማስፋት እና ዘላቂ ለማድረግ አዳዲስ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን እና ግቦችን አስቀምጧል።   የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተያዘው አዲስ በጀት ዓመት የሀገር ውስጥ አምራቾችን የገበያ ድርሻ ወደ 49 ለማድረስ እና የውጭ ምንዛሬ ቁጠባውን ወደ 7 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። ለዚህም ስኬት አምራቾች ጥሬ ዕቃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ እና ምርቶቻቸውን ያለ ደላላ ለገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችል የዲጂታል የገበያ ትስስር ፕላትፎርም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ይፋ ተደርጓል። ወደፊትም ከቀላል የሸማች ዕቃዎች ባለፈ እንደ ተሽከርካሪዎች፣ ኬሚካሎች እና ብረታብረት ያሉ አስራ አምስት ስልታዊ የከባድ ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ትኩረት የሚደረግ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመተካት ባለፈ የማኑፋክቸሪንግ ወጪ ንግድ ገቢን በማሳደግ ኢትዮጵያን በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ላይ ተወዳዳሪ የማድረግ ሰፊ ራዕይ ተሰንቋል። በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የተኪ ምርት ስራ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ መዋቅር ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሀገር ውስጥ ምርታማነት እያሸጋገረ የሚገኝ ስልታዊ እርምጃም ነው። በጥናት የተለዩት 96 ቁልፍ ስልታዊ ምርቶች በሙሉ አቅም ወደ ማምረት መሸጋገራቸው ለሀገር በቀል እውቀትና ለፈጠራ ስራዎች ሰፊ በር ከመክፈቱም በላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ላይ ያላትን የድርድር እና የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም በእጅጉ ያጠናክረዋል።
የቀይ ባህር ደህንነት እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ሚና
Aug 29, 2026 792
(በሙሴ መለሰ) በቀይ ባሕርና በኤደን ባሕረ-ሰላጤ ቀጣናዊ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ ኢትዮጵያ የሚኖራት ሚና ከፍተኛ ነው። የኢትዮጵያ አብዛኛው ወጪና ገቢ ሸቀጦች በባህር በር በኩል የሚተላለፉ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የሚከሰቱ የፀጥታ መደፍረሶች ወይም የሎጂስቲክስ መስተጓጎሎች በቀጥታ በሀገሪቱ ብሔራዊ ኢኮኖሚ ላይ የራሱን ተጽዕኖ ማሳረፉ የማይቀር ነው። በሆርሙዝ ሰርጥ የተከሰተውን የጸጥታ ቸግር ተከትሎ የተለያዩ የዓለም ሃገራት የቀይባህር መስመር ከባቤል ሜንደብ እስከ ስዊዝ ቦይ ድረስ ያለው ደህንነት አሳስቧቸዋል። ይሄንን ስጋት ለማቃለልም ሆነ የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን መነሻ በማድረግ አንዳንድ ሃገራት በቀጣናው ካሉ የባህር ተጋሪ መንግስታት ጋር በመሆን የመሰረቷቸውን የጦር ሰፈሮች ቢያጠናክሩም አሁንም ቀጣናው በባህር ላይ ውንብድና፣ በህገ-ወጥ ንግድና የሰዎች ዝውውር ወንጀል ለስጋት የተጋለጠ ሆኖ ይገኛል። የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ከቀይ ባህር ደህንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ መሆኑን በጽኑ የምታምነው ኢትዮጵያ፣ ድንበር ተሻጋሪ የፀጥታ ስጋቶችን ለመከላከል በሚደረጉ የባለብዙ ወገን ውይይቶች ላይ በመሳተፍ የበኩሏን አስተዋጽኦ ታበረክታለች። በተለይም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የጦር መሳሪያ እና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን እንዲሁም የባህር ላይ ወንጀሎችን በጋራ ለመመከት የቀጣናው ሀገራት የተቀናጀ ምላሽ እንዲኖራቸው ድጋፍ ታደርጋለች። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር ያላት መልክዐ ምድራዊ ትስስር እና የፀጥታ አጋርነት በቀይ ባህር ቀጣና መረጋጋት ውስጥ ወሳኝ ድርሻ አለው። በቀጣናው የሚከሰቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች እና የጸጥታ ችግሮች በቀጥታ በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የትብብር አማራጭን ተከትላ እየሰራች ትገኛለች። የአፍሪካ ቀንድና የቀይባሕር ደኅንነት ሊለያዩ የማይችሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛቷ፣ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋና በጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጧ በቀጣናው ትልቅ ድርሻ ያላት በመሆኑ፣ በሚደረጉ የማሪታይምና የደኅንነት ውይይቶች ላይ የምታደርገው ንቁ ተሳትፎ ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሰፊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚዊ ተጽዕኖ በመጠቀም፣ ስትራቴጂያዊ የንግድ መስመሮችን ከስጋት ነፃ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑ በቅርቡ በናይሮቢ በተካሄደው ዓለም አቀፍ መድረክ በግልጽ ታይቷል። በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው አምስተኛው የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ የባህር ላይ ህግ ማስከበር ውይይት (Maritime Law Enforcement Dialogue) ላይ፣ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አገራዊና ቀጣናዊ ጥቅሞችን የሚያስጠብቅ ተሳትፎ አድርጓል። ይህም ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና የኢኮኖሚ ትስስር ላይ ያላትን ሚና እና ባለቤትነት አሳይቷል። ለኢትዮጵያ የባህር በር ደህንነት የህልውና ጉዳይ ነው። በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ተወካይ ካፒቴን ክብሩ መስፍን እንደገለጹት፣ የባሕር ላይ ሰላም መደፍረስ በቀጥታ የአገሪቱን ብሔራዊ ኢኮኖሚ ይነካል። አብዛኛው የሀገሪቱ ወጪና ገቢ ንግድ በባህር ላይ የሚካሄድ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር ላይ የሚከሰቱ የባሕር ላይ ውንብድናዎችና ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች የንግድ ፍሰቱን እንዳያስተጓጉሉ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ካፒቴን ክብሩ አክለውም፣ የመርከቦች መድን ዋስትና መናርና የሸቀጦች መዘግየት የሀገሪቱን የንግድ ተወዳዳሪነት እንዳይፈታተኑ፣ ጠንካራና የተቀናጀ የባህር ላይ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህን ዓለም አቀፋዊ ስጋትን ለመመከት ኢትዮጵያ የጋራ መፍትሔዎችን በማቅረብ ረገድ ግንባር ቀደም ናት። በተለይም ከጎረቤት አገራት ጋር በመቀናጀት "ብሔራዊ የማሪታይም መረጃ ማዕከል" (National Maritime Information Centre) ለመመስረት ያቀደችው ስትራቴጂ፣ ሀገሪቱ ለቀጣናው መረጋጋት ያላትን የረጅም ጊዜ ራዕይ የሚያሳይ ነው። መረጃን በጋራ መለዋወጥና የተቀናጀ የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ለዚህ ስኬት ዋነኛው መሳሪያ እንደሆነ ኢትዮጵያ በጽኑ ታምናለች። በቀይ ባህርና በኤደን ባህረ-ሰላጤ የሚስተዋሉ እንደ ሕገ-ወጥ የሰዎችና የዕፅ ዝውውር እንዲሁም ሕገ-ወጥ አሳ ማጥመድ ያሉ ስጋቶች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ቀጣናዊ ኃይሎች ተሳትፎ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ትኩረት ስቧል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል ጉዳዮች ቢሮ (UNODC) የቀጣናው አስተባባሪ ሞስታፋ ኤልባና እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላት የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አስተማማኝና የተረጋጉ እንዲሆኑ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በቀይ ባህር ቀጣና ያላትን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ለማስጠበቅና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ዲፕሎማሲያዊና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል ጉዳዮች ቢሮ (UNODC)፣ ኢንተርፖል እና ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅርበት በመሥራት ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና ጸጥታ ላይ ያላትን የመሪነት ሚና በታሪካዊ ኃላፊነትና በሕግ አግባብ እያስጠበቀች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የባህር ኃሃይልን ጨምሮ በጥብቅ ዲሲፕሊኑ እና በመፈጸም አቅሙ የሚታወቅ ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ገንብታለች። ይሄ ሰራዊት በተለያየ ጊዜ ችግር ላጋጠማቸው ሃገራት ባሳየው የሰላም ማስከበር ሚናው በውጤታማነቱ የተመሰከረለትም ነው። የቀጣናውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሃይል አስፈላጊ ስለሆነም በቅርብም በሩቅም ያሉ ሃገራት የኢትዮጵያን የባህር ላይ ህልውና በበጎ ይመለከቱታል። ለዚህም በቅርቡ በአንድ የሃገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ የባብኤል ሜንደብን እና የቀጣናውን ሰላም ለማስጠበቅ ሃገራቸው በቂ አቅም ስለሌላት የሌሎች እገዛ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት የጅቡቲ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ፋይናስ ሚኒስትር ኢሊያስ ሙሳ ዳዋሌህ ገለጻ አንዱ ማሳያ ነው። እነዚህ ሁሉ ጉዳዮች አመላካች የሚሆኑት ያለ አግባብ ከባህሩ የተገፋችውና መብቷን የምትጠይቀው ኢትዮጵያ ያላት ዘርፈ ብዙ ዓቅም ለቀጣናውም ለራሷም ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ወሳኝ ሚና ያላት መሆኑን ነው።
የኢትዮጵያ አዲሱ የቱሪዝም ከፍታ!
Aug 29, 2026 244
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ከሀገሪቷ ልዩ ፀጋዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ሀገሪቱ ያሏት ጉምቱ ታሪክ፣ ብዝሃ ባህል እና ልዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለአፍሪካ ስልጣኔ ያላትን ታላቅ ድርሻ የሚያመላክቱ ናቸው። ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንስቶ እስከ አክሱም ሀውልትና የጁገል ግንብ ድረስ ያሉት ቅርሶች የኢትዮጵያን የታሪክ ጥልቀት እና የባህል ትሩፋቶች በግልጽ ያሳያሉ። እነዚህ ታሪካዊ ሀብቶች በአሁኑ ወቅትም የውጭ ጎብኚዎች፣ ተመራማሪዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቀልብ መሳባቸውን ቀጥለዋል። ከታሪክ ሀብቶቿ ባለፈም ማራኪው የመልክዓ ምድር አቀማመጥ፣ ብቅ ያሉ የዱር እንስሳቶች እና የዜጎች እንግዳ ተቀባይነት የአኗኗር ዘይቤ ለዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። መንግስት ቱሪዝምን እንደ አንድ ዋነኛ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመውሰድ ስትራቴጂካዊ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተቀረጹት የ"ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ከማውጣት ባለፈ የገቢ መጠንን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ለውጥ እያስመዘገቡ ነው። ከዚህም መካከል በሶማሌ ክልል በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በዋቢ ሸበሌ ወንዝ ዳርቻ ተገንብቶ በቅርቡ የተመረቀው እና የ"ገበታ ለትውልድ" አካል የሆነው የሸበሌ ሪዞርት አንዱ ማሳያ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃቱ ወቅት እንደገለጹት፣ ሪዞርቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጠ የምስራቁ የሀገራችን ክፍል ትልቅ ማሳያ ሥራ ነው። ይህ ስራ በታችኛው የዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ አካባቢ ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል የፈጠረና የክልሉን የቱሪዝም ገጽታ የቀየረ ነው። በተጨማሪም በመዲናዋ አዲስ አበባ የተገነቡት የወዳጅነት አደባባይ፣ አንድነት ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚየም እና አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት አዳዲስና ተመራጭ የከተማ ቱሪዝም (Urban Tourism) መዳረሻዎች ሆነዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዋና ከተማዋ የተከናወነው ሰፊው የኮሪደር ልማት ሥራ የአዲስ አበባን መልክ በአዲስ ሁኔታ በመግለጥ፣ ከተማዋን ለሰው ልጅ ምቹ፣ ውብ እና የጎብኚዎች ዓይን ይበልጥ የሚያርፍባት የቱሪስት ማዕከል አድርጓታል። ከታሪካዊ ቅርሶች ጥበቃ አንጻርም እድሳት የተደረገላቸው ብሔራዊ ቤተ መንግስት (ኢዮቤልዩ)፣ የጎንደር የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስታት፣ የጅማ አባጅፋር ቤተመንግስት እና የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ለዘርፉ መነቃቃት የጎላ አበርክቶ እያበረከቱ ይገኛሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ በቅርቡ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እና የባልካሌ ውብ ተፈጥሮአዊ ጥንታዊ ቅርሶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ካርታ ይበልጥ አበልጽገውታል። ይህ ዓለም አቀፋዊ እውቅና የሀገሪቱን የባህል እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጥረት ማሳደጉ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ እነዚህ አካባቢዎች የሚመጡ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ የቱሪዝም ገቢን ለማሳደግ አስችሏል። በሌላ በኩል፣ የቱሪዝም ዘርፉን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ የአቪዬሽን እና የእንግዳ ተቀባይነት (Hospitality) አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ መሆናቸው ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መዳረሻ ማብዛት፣ የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ (e-Visa) አሰጣጥ መዘመኑ እና ወደ ተለያዩ የመዳረሻ አካባቢዎች የሚደረጉ የትራንስፖርት አማራጮች መቃናታቸው ጎብኚዎች ያለ ምንም እንግልት ሀገሪቱን እንዲጎበኙ መንገድ ከፍቷል። ይህም ሀገሪቱ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ለአፍሪካ እና ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ተፈላጊ ማዕከል እንድትሆን አስችሏታል። በተጨማሪም የዲጂታል ቱሪዝም ፕሮሞሽን እና የቅርሶች ጥበቃ ስራዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መደገፋቸው ለዘርፉ አዲስ ምዕራፍ አጎናጽፎታል። በማህበራዊ ሚዲያ እና በዲጂታል አማራጮች የሚሰሩ ማስተዋወቂያዎች የኢትዮጵያን ገጽታ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በአዲስ መልክ አስተዋውቀዋል። እነዚህ የተቀናጁ የልማት፣ የጥበቃ እና የማስተዋወቅ ስራዎች ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በመላው አህጉር ቀዳሚ የቱሪዝም መዳረሻ የመሆን ራዕይዋን በተግባር እያረጋገጡት ይገኛሉ። ይህንን የመንግስት ጥረት ተከትሎም ከባለሀብቶች እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የዘርፉ ተዋንያን የሚመጣው ተሳትፎና የኢንቨስትመንት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል። በአጠቃላይ እነዚህ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች፣ የታሪካዊ ቅርሶች ጥገና እና የተፈጥሮ መስህቦች ጥምረት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ ለኢኮኖሚ እድገት እና ለዘላቂ ልማት ያለውን ድርሻ ወደ ላቀ ደረጃ እያሳደጉት ይገኛል።
የኢትዮጵያውያን የወል እውነት- ሀገራዊ ምክክር
Aug 28, 2026 584
በሙሴ መለስ ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የጋራ መኖሪያ እና የብዝሃነት ውበት ደምቆ የሚታይባት ሀገር ናት ። ዛሬ ላይ ለመድረስም በርካታ ውጣ ውረዶችን፣ እና የታሪክ ምዕራፎችን ተሻግራለች። በነዚህ ምዕራፎች ውስጥም በአብሮነትና በጋራ ሃገራዊ እሳቤ ከተገነቡት የጋራ ማንነቶች ባልተናነሰ መልኩ ያጋጠሙ የታሪክ ስብራቶች የልዩነት እና ያለመግባባት መንስኤ የሚሆኑበትን አጋጣሚም አስተናግዳለች። ልዩነቶችን በጉልበት ወይም በኃይል ሳይሆን፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር እና ከነጣይ ትርክት ይልቅ ወደ ሃገራዊ መግባባትና የጋራ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣትም ሃገራዊ ምክክሩ የራሱን ቁልፍ ሚና በመወጣት በሃገራችን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑ ይታወቃል። ከአራት ዓመታት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ የህብረተሰቡን አጀንዳዎች በባለቤትነት የማሰባሰብ ሂደቱን በስኬት አከናውኗል። የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ምሁራን፣ ዳያስፖራዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በአንድ መድረክ የተሳተፉበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ለ46 ቀናት ተካሄዶ በስኬት መጠናቀቁ ተበስሯል። ይህ ጉባኤ ዜጎች ሃሳባቸውን በነፃነት የገለጹበት፣ የጋራ መግባባት ላይ የደረሱበት በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥም የጠመንጃ የበላይነትን በማስቀረት፣ የሀሳብ የበላይነትና የሰላማዊ የውይይት ባህልን ለማስፈን ምቹ ምህዳር የፈጠረ አካታች አካሄድ ነው። ከጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሐሳቦችና የተገኙት ልምዶች ወደ ተግባር እየተሸጋገሩ፣ በየደረጃው በሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ውይይቱ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍትም ነው። የጋራ ትርክት ህዝቦች በታሪካቸው፣ በአሁኑ ሁኔታቸው እና በወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ላይ ያላቸው የጋራ መረዳትና ስምምነት ሲሆን ይህም አብሮነትን ለማጎልበት ጠንካራ መሰረት ይጥላል። ለዘመናት በጦርነት፣ በኃይልና በፖለቲካ ሽኩቻ ሲንከባለሉ የቆዩ የትርክት ስብራቶችም ከጠመንጃ ይልቅ በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ክርክር ለመፍታት ስለመቻሉም ትልቅ ማሳያ ነው። በምክክሩ ላይ በመላው ሃገሪቱ አሉን የሚሏቸውን ጥያቄዎችና ቅሬታዎች በኃይል በጦር መሳሪያ ለመፍታት ነፍጥ አንግበው ሲታገሉ የነበሩ አካላት ሁሉ እንዲሳተፉ መደረጉም የሒደቱን ስኬታማነት ለዓለም ማህበረሰብ ያሳየ ነው። ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች፣የፖለቲካ አመለካከቶችና የኅብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ አራት ሺህ ተመካካሪዎች የየራሳቸውን የተናጠል ፍላጎት ብቻ ከማንጸባረቅ ተቆጥበው በተለዩ ስምንቱ አበይት አጀንዳዎች ላይ በጋራ መስማማታቸውም የወል ትርክት ግንባታን የውጤታማነት ጉዞ ስኬት በተግባር የገለጠ ነው። ይህ ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሳይሆን ለሀገር ህልውና እና ለጋራ ዕድገት ቅድሚያ የመስጠት ትልቅ የፖለቲካ ብስለትም ነው። ይህ ሂደት እያንዳንዱ ዜጋ በሀገሩ ላይ ሙሉ ባለቤትነትና ደህንነት እንዲሰማው የሚያደርግ ሲሆን የጋራ አገርና የጋራ ዕድል አለን የሚለውን እሳቤ በማጉላትም የወል ትርክትን በጽኑ መሠረት ላይ ይገነባል። ምክክሩ በጥቂት የፖለቲካ ልሂቃን (Elites) መካከል ብቻ የተደረገ ውይይት ሳይሆን እስከ ወረዳ ድረስ ያሉትን የታችኛውን የህብረተሰብ ክፍሎች፣ አርሶ አደሮችን፣ አርብቶ አደሮችንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ መሆኑም ትልቅ ትርጉም አለው። ከሕዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ የፈለቁት ምክረ ሀሳቦች ለሀገራዊ ትርክት መጠንከር ወሳኝ ሚና ከመጫወት ባለፈ ሂደቱ በህዝቡ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ያደርገዋል። ምክክሩ ያረጋገጠው ትልቁ እውነት የኢትዮጵያውያን ዕጣ ፈንታ የተሳሰረ መሆኑንና የወል ትርክት ግንባታ የሀገር ህልውና ዋስትናነቱን ነው። ልዩነቶችን ውበት፣ ውይይትን ደግሞ መሳሪያ በማድረግ የተጀመረው ይህ ጉዞ ኢትዮጵያ በቀደመ ታሪኳ የገጠሟትን የታሪክ ስብራቶች በመጠገን ወደ ዘላቂ ብልጽግና፣ ዲሞክራሲና እውነተኛ አንድነት እንድትሸጋገር ያስችላታል።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና 
Jun 17, 2026 12599
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል።   የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።   የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 22093
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15129
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20868
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 105626
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 80086
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 58432
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 56039
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 40008
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 39919
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 39384
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 37865
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 105626
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 80086
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 58432
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 56039
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 924
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።   በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው።   በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የአረቡ ዓለም ከግብፅ ምን አተረፈ?
Aug 19, 2026 793
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አካሄድ በታሪካዊ እውነታዎች እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ እየተመሠረተ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ጊዜ ያለፈባቸው የጂኦ ፖለቲካዊ የመጠላለፍ አካሄዶች ዋጋ ቢስነትና ጥቅም አልባነት በግልጽ እየታየ ይገኛል። ለብዙ አስርት ዓመታት ግብፅ የዓረብ ሊግን ለራሷ ጠባብ ፍላጎቶች እና ጂኦፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያነት በሰፊው ስትጠቀምበት ቆይታለች። ሆኖም ይህ ጥቅምና ጉዳትን ብቻ መሰረት ያደረገ ግንኙነት አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ የዓረቡ ዓለም ከግብፅ በምላሹ ያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ ምንም የሚል ነው ሲል “What Has the Arab World Gained from Egypt? Why Ethiopia Belongs in the Arab League?” ፀሐፊው እና በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት የሚተነትነው አስተያየት የሚሰጠው ጅብሪል ላሞ በኢዜአ እንግሊዘኛ ገጽ ባሳፈረው ሐተታ ላይ ፣ የግብጽ ፖሊሲዎች እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው አምባገነናዊ አስተዳደር የጋራ ጥንካሬን ከመፍጠር ይልቅ የቀጣናውን አለመረጋጋት ማባባሳቸውን ገልጿል። እነዚህ ፖሊሲዎች፣ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር አካባቢም ውጥረትን እያባባሱ እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካባቢዎች ለዓረቡ ዓለም የራቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ለዓረቡ ዓለም ደኅንነት፣ የባሕር ንግድ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ናቸው። የግብፅ ከፋፋይ ቀጣናዊ አካሄድ ከታዩባቸው ጉልህ ማሳያዎች አንዱ በኤርትራ ጉዳይ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ላይ የነበራት ታሪካዊ ጣልቃ ገብነት ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለመግታት በግብጽ ታስበው የተደራጁ ተገንጣይ ኃይሎችን እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ትደግፍ እንደነበረ ፀሐፊው አውስቷል። ከኢትዮጵያ የኤርትራ መገንጠል በምሥራቅ አፍሪካ ቀውስ የተሞላ ታሪክ ውስጥ አቢይ ክስተት ሲሆን፣ የውጭ ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች የሀገራትን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚያናጉ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዲፕሎማሲ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም ታስቦ የተዘረጋውን የኤርትራን የመገንጠል ፕሮጀክት በመደገፍና በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው። በተጨማሪም ግብጽ በደቡባዊ የቀይ ባህር ቀጣና የምታካሂደው ቀውስ የመፍጠር እንቅስቃሴ፣ ለዓለም አቀፍ የባህር ንግድና ለቀጣናው ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል። በባብ-ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ ውጥረቶችን በመቀስቀስ እና ተላላኪ ታጣቂ ቡድኖችን በማንቀሳቀስ፣ ወሳኝ የሆኑ የባህር መተላለፊያዎችን የጂኦፖለቲካዊ ግጭት መድረክ አድርጋዋለች። ይህም ለጠቅላላው የዓረብ ዓለም የኢነርጂና የምግብ አቅርቦት መሰረት የሆነውን የደህንነት መዋቅር አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ሲሉ ጅብሪል ላሞ ያብራራሉ። ጅብሪል ላሞ በጽሑፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ የግብፅ ግልጽ የራስ ወዳድነት እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን የሚፈጥሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ መቀላቀል ግን ለዓረቡ ዓለም እጅግ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ለውጥ አምጪ ዕድል ይዞ ይመጣል። በመደመር ፍልስፍና አሳታፊ ማዕቀፍ ሥር፣ ኢትዮጵያ ከማግለል ፖሊሲ ይልቅ የዓረቡን ዓለም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተሳሰር የሚያስችል የላቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት። በዚህም የአፍሪካ ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመቅረጽ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ታካፍላለች። የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ የመቀላቀል ጥረት ጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን፣ የተፈጥሮ የታሪክ ጥሪ ነው። ከ135 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጥልቅ የሥልጣኔ መሠረት ያላት ይህች የቀይ ባሕር ሀገር፣ አባልነቷ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያላት ቁርኝት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በጋራ ታሪክ፣ ባህል እና የደም ትስስር ላይ የተገነባ ነው። እንደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጥናቶች በታሪክ ደረጃ ከመካከለኛው እና ከቅርብ ምሥራቅ ታሪክ (Near Eastern Studies) ተመድቦ መጠናቱ፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከቀጣናው ጋር ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ውህደት የሚያረጋግጥ ሕያው ማሳያ ነው። የባብ-ኤል-ማንደብ የባህር ወሽመጥ በጭራሽ መሰናክል አልነበረም፤ ይልቁንም ንግድን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን በቀይ ባሕር በኩል ያገናኘ ዋንኛ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል። ከንጉሥ አብረሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች መካከል የጋራ የደም ትስስር እንደነበር የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የስነ ህይወት( ጄኔቲክስ) ጥናቶች፣ የዚህን ታሪካዊ ቁርኝት እውነተኛነት በግልጽ ያሳያሉ። በቋንቋና በባህል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው። የሀገሪቱ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ውርስ ከዓረብኛ፣ አራማይክና ዕብራይስጥ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በአረቢያ ልሳነ-ምድር መካከል ያለውን ጥልቅ የጋራ የሥልጣኔ ቁርኝት ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ተስደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ ማግኘታቸው የእስልምናን ህልውና የታደገ ታሪካዊ ክስተት ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱን ከዓረቡ ዓለም ጋር በጽኑ አስተሳስሯታል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዓረብ ሊግን በኢትዮጵያ ላይ እንደ ተቋማዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ መሣሪያ ግብጽ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ግብፅ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ዕድገት፣ የህዳሴውን ግድብም ሆነ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ሥጋት በሚያይ ጊዜ ያለፈበት ስሌት ላይ የተመሠረተ ነው። ግብፅ የራሷን የውሃ አቋም በሊጉ ላይ በመጫን፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጋለች። ጅብሪል ላሞ እንዳመለከተው፣ ከግብጽ የአግላይነት ፖሊሲ ይልቅ የዘመኑ ነባራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ትብብርን የሚጠይቁ ናቸው። በመደመር መርህ፣ ኢትዮጵያ ለዓረቡ ዓለም ለዘመናት ከቆዩ የጥላቻ መንገዶች በላቀ ሁኔታ የተሻሉ ጥቅሞችን ማቅረብ ትችላለች። እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ እና የአረንጓዴ ኃይል አቅሟ፣ ኢትዮጵያን ለቀይ ባህር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ አድርጓታል። የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የውሃ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ሥጋት በተጋረጠበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የውሃ ሀበት እና ለም መሬት ለቀጣናው ወሳኝ የግብርና-ኢንዱስትሪ አጋር ያደርጋታል። የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ብሔረተኝነት በመሻገር፣ የቀይ ባህርን ቀጣና የሥልጣኔ እውነታ መቀበል ይኖርባቸዋል። አረብ ሊግ እንደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ እና ሞሪታኒያ አባል ሀገራት መያዙ፣ ስብስቡ የተለያዩ ቀጣናዊ እውነታዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያሳያሉ። የዓረብ ሊግ ሙሉ አባልነት የኢትዮጵያን አፍሪካዊ ማንነት ሳይቀንሰው፣ አህጉሩን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የሚያገናኝ ዋነኛ ድልድይ የሚያደርጋት በመሆኑ፤ ሊጉ የኢትዮጵያን አጋርነት በመቀበል ለአዲስ አበባ ተገቢውንና ሕጋዊ ቦታዋን የሚሰጥበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ ጅብሪል ላሞ ፅሁፉን ቋጭቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም