ቀጥታ፡

አራት ግቦች የተቆጠሩበት የባህር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ባህር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ግርማ ዲሳሳ እና ወንድወሰን በለጠ ለባህር ዳር ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሁዘይፋ ሻፊ እና ዩጋንዳዊው ሳይመን ፒተር ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በሊጉ ለ12ኛ ጊዜ አቻ የወጣው ባህር ዳር ከተማ በ24 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

ባህር ዳር ከተማ በሊጉ በርካታ የአቻ ውጤቶችን ያስመዘገበ ቡድን ነው። ባለፉት አምስት ጨዋታዎችም አቻ ወጥቷል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ21 ነጥብ ከነበረበት 14ተኛ ደረጃ ወደ 12ተኛ ከፍ ብሏል። ቡድኑ  ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም