ቀጥታ፡

የሰላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጉባኤ መሪዎቹን በመምረጥ በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2018(ኢዜአ)፦ የሰላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በአምስተኛ መደበኛ ጉባዔው የቀጣይ አምስት ዓመታት የተቋሙን መሪዎች በመምረጥ በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

ሚኒስቴሩ በየደረጃው ተቋሙን ለመምራት ኃላፊነትን ከተረከቡት የዕምነቱ አባቶች ጋር በመቀራረብ እንደሚሰራም አስታውቋል።


 

ካውንስሉ በሰላም፣ በማኅበራዊ ልማት እና በሀገር ግንባታ ዙሪያ የጀመረውን በጎ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያለውን ተስፋም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ካውንስሉ በጉባኤው ሌሎች አመራሮችን ጨምሮ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስልን እንዲመሩ ቄስ ደረጄ ጀምበሩን በፕሬዝደንትነት መምረጡ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም