ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ መድን እና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር  ኢትዮጵያ መድን እና ፋሲል ከነማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ተደርጓል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ መድን በ20 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 15ኛ ከፍ አድርጓል።  የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።

ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ ከነበረበት አራተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ከፍ ብሏል። ቡድኑ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ አልቻለም።

ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በነጥብ እኩል መሆን የሚችልበትን እድልም አልተጠቀመም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም