የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎቹን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስረከበ - ኢዜአ አማርኛ
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎቹን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስረከበ
አዲስ አበባ፤ጥር 28/2018 (ኢዜአ)፡-የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ክልላዊና ሀገራዊ የምክክር አጀንዳዎቹን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስረክቧል።
የድርጅቱን አጀንዳዎች የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራሮች ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራር አባላት ጋር በአዲስ አበባ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርዓያ፣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራር አባላት ተሳትፈዋል።