ቀጥታ፡

የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ የምታስተናግዳቸው አህጉራዊ ሁነቶች

በሙሴ መለሰ 

የዓለም ስርዓት በፍጥነት እየተቀያየረ ይገኛል። አፍሪካ በዚህ ተለዋዋጭ ስርዓት ውስጥ የሚገባትን ቦታ የመያዝ ጉዳይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከሆነ ሰነባብቷል።

አፍሪካ በርካታ ወጣት የያዘች እና ብዝሃ የተፈጥሮ ፀጋዎች ያሏት አህጉር ናት። በአፍሪካ ተግባራዊ የተደረገው አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና በቀጣናው የንግድ ትስስርን በማሳለጥ እድገትን የማፋጠን ተስፋ ተጥሎበታል።

አፍሪካ እድሎቿን በሚገባ ለመጠቀምና የሚስተዋሉ ፈተናዎቿን ለመሻገር ምላሽ የምትሰጥበት የልማት እና እድገት ጉዞዋን ከመበየን ባለፈ በዓለም መድረክ የሚኖራትን ሚናም ይወስናል።

በአህጉር ደረጃ የተቀመጡ እንደ አጀንዳ 2063 እና የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ያሉ አህጉራዊ ማዕቀፎች እንዲሳኩ ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል። መንግስታት፣ የግሉ ዘርፍ እና የልማት አጋሮች ትብብራቸው ማጠናከር ይኖርባቸዋል።

የተገቡ ቃልኪዳኖችን ወደ ሚለካ ውጤት ለመቀየር ዘላቂነት ያለው አመራር ሰጪነት፣ ኢንቨስትመንትን ማጠናከር እና ተከታታይነት ያለው ውይይቶችን ማድረግ ይገባል። 

ውሳኔ ሰጪዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኙ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ መድረኮች በአጀንዳዎች ላይ የተቀናጀ የተግበባር ምላሽ ለመስጠት ቁልፍ ሚና አላቸው።

አፍሪካ እድሎቿን በመጠቀም እና ፈተናዎቿን በማለፍ መንገድ ላይ በሆነችበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ሁለት ወሳኝ አህጉራዊ ሁነቶችን ታስተናግዳለች።

39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል።

የዘንድሮው መሪ ሀሳብ በአፍሪካ የውሃ ደህንነትና ንጽህና አጠባበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የመሪዎች ጉባኤ መሪ ሀሳብ ነው።

ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተረጋገጠ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓት ዘላቂ ልማት፣ አካታች እድገት፣ ጤናማ ማህበረሰብና ጠንካራ ስነ ምህዳር መገንባት፣ የተፈጥሮ ሀብት ዘላቂ አጠቃቀምና የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ከአጀንዳ 2063 ግቦች ጋር የተሳሰረ መሆኑ ተገልጿል።

የመሪዎች ጉባኤው በመሪ ሀሳቡ በጥልቀት በመምከር የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦች ያስተላልፋል ተብሎም ይጠበቃል።

ከመሪዎቹ ጉባኤ አስቀድሞ 48ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

51ኛው የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች (PRC) ስብሰባ ከጥር 4 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በስብሰባው የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የሕብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል።

ስብሰባው የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ መክሯል።

ኮሚቴው በ2026 የአፍሪካ ህብረት መሪ ሀሳብ ላይ ምክረ ሀሳቦችን አቅርቧል። የኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብሰባ የሚያገለግል ነው።

ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ማግስት ሌላኛው በኢትዮጵያ የሚካሄደው ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ነው።

የቢዝነስ ፎረሙ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ኢሴኤ) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሁነቱን አዘጋጅተውታል።

“የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ በፋይናንስ መደገፍ፤ ስራ እና ኢኖቬሽን ለዘላቂ ትራንስፎርሜሽን” የፎረሙ መሪ ሀሳብ ነው።

የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአፍሪካ የልማት እና የኢኮኖሚ እድገት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ በየዓመቱ የሚካሄድ ከፍተኛ አህጉራዊ የምክክር መድረክ መሆኑን የኢሲኤ መረጃ ያመለክታል።

በፎረሙ ላይ አጋርነትና የኢንቨስትመንት መጠንን ማሳደግ በተለይም የመንግስት እና የግል የተቀናጀ የፋይናንስ አቅርቦትን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይወያያል።

የወጣቶችን የኢኖቬሽን ስራ ከፋይናንስ አቅርቦት ጋር የሚያስተሳስር የአፍሪካ የወጣቶች አይበገሬነትና ትራንስፎርሜሽን ማዕቀፍ ይፋ ይሆናል።

በኢሲኤ የበለጸገውና የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ቃል ኪዳኖችን ትግበራ የሚከታታልና የሚቆጣጠር ስርዓትም በፎረሙ ይፋ ሆኖ ወደ ትግበራ ይገባል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሁነት ላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የምክክር መድረኮችና የባለሙያዎች ውይይቶች ይደረጋሉ።

አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና የፈጣራ ባለሙያዎችን ከባለሀብቶች እና ፋይናንስ አቅራቢዎች ጋር የሚያገናኝ አውደ ርዕይም ይካሄዳል።

ሁነቶቹ ቃል ኪዳኖችን ወደ ተጨበጡ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ለመቀየር አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል።

ከአህጉራዊ ሁነቶቹ ባሻገር የባለብዙ ወገን መድረክ የሆነው የአፍሪካ እና ጣልያን ጉባኤ የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል።

ኢትዮጵያ አህጉራዊ ሁነቶቹን ማዘጋጀቷ በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ ጸንቶ የቆየውን የመሪነት ሚናዋን እንዲሁም የአህጉራዊ ምክክር፣ የባለብዙ ወገን ውይይቶችና ስትራቴጂካዊ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩባት ማዕከልነቷንም አጉልቶ የሚያሳይ ነው።

የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት እና በከተማ ማዘመን ስራ በፍጥነት እየተለወጠች ሲሆን የሁነቱ ተሳታፊዎች ከስብሰባው ባለፈ የመዲናዋን አዲስ መልክ የመመልከት እድል ያገኛሉ።

የእነዚህ አህጉራዊ ስብሰባዎች ስኬት የሚለካው በአቋም መግለጫ ሳይሆን አጋርነትን በማጠናከር፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግና የሚጨበጥ ውጤት በአህጉሪቱ በማስመዝገብ ነው።

በዚህ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያ የምታዘጋጃቸው አህጉራዊ ሁነቶች አህጉራዊ ትስስርን በማጠናከርና በዓለም ጉዳዮች ላይ የአፍሪካን ድምጽ ከፍ ለማድረግ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል።

ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም