ቀጥታ፡

ነገሌ አርሲ መቀሌ 70 እንደርታን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አደረገ 

አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ነገሌ አርሲ መቀሌ 70 እንደርታን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ርሆቦት ሰላሎ በ41ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

የመቀሌ 7ዐ እንደርታው ጋትሉዋክ ቱት በ62ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው  ነገሌ አርሲ በ35 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ 10ኛ ድሉን አሳክቷል።


 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቀሌ 70 እንደርታ በ18 ነጥብ 17ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ተገኝቷል።

ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ዛሬ በተደረጉ የ18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ባህር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት አቻ ሲለያዩ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቅቋል።

ኢትዮጵያ መድን እና ፋሲል ከነማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም