ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል
አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፍጹም ጥላሁን በ13ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪ ሆኗል። ይሁንና መሪነቱ የቆየው ለተወሰኑ ደቂቃዎች ነው።
የቅዱስ ጊዮርጊሱ ጥዑመልሳን ኃይለሚካኤል በ16ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ የወልዋሎን የአቻነት ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ፍሬው ሰለሞን ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ60ኛው ደቂቃ ላይ ያገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር አልቻለም።
ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ24 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
የ16 ጊዜ የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ17 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ማግኘት አልቻለም።
በአሁኑ ሰዓት ነገሌ አርሲ ከመቀሌ 70 እንደርታ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው።