ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ጉባኤው የአህጉሪቱን እውነተኛ ገጽታ ለማስተዋወቅ ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው
May 7, 2026 23
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ) ፦ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ የአህጉሪቱን እውነተኛ ገጽታ ለማስተዋወቅና የለውጥ ትርክትን ለመገንባት ትልቅ መሠረት የሚጥል መሆኑን የጉባኤው ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡ የአፍሪካን እውነተኛ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅና የዲጂታል ትርክቱን በባለቤትነት ለመምራት ያለመው የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል። በጉባኤው ለመታደም ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 321 ሚሊዮን በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ያሏቸው 61 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ ከትመዋል። በተጨማሪም 150 ሚሊዮን ተከታዮች ያላቸው 120 ኢትዮጵያውያን የይዘት ፈጣሪዎች በጋራ በመሰባሰብ፣ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ አዲስ የዲጂታል ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅተዋል፡፡ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ /pulse of Africa/ ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ጉባዔ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" የሚል መሪ ሀሳብ ይዟል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ከአራቱም የአህጉሪቷ ማዕዘናት በመምጣት በውቧ አዲስ አበባ ከትመው የተለየዩ ሥራዎችን መጎብኘት ጀምረዋል፡፡ ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል ከኬንያ የመጣው ወጣቱ ሳሙኤል ማቦቴ፣ አዲስ አበባን "ውብና በእርግጥም የአፍሪካ ዋና ከተማ" በማለት ገልጾ፣ በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ በመሳተፉ የተሰማውን ኩራት ገልጿል። በመላው አፍሪካ የሚገኙ የይዘት ፈጣሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙበትን ይህን መድረክ ላዘጋጁት አካላት ምስጋናውን ያቀረበው ሳሙኤል፤ ማህበራዊ ሚዲያ የወደፊት ዕጣ ፈንታችን በመሆኑ፣ ወደዚህ ዘመናዊ ምዕራፍ መሸጋገር አለብን ብሏል፡፡ አፍሪካን ለመገንባትና ለመለወጥ ማህበራዊ ሚዲያን መጠቀም ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከመላው ዓለም ከመጡ የይዘት ፈጣሪዎች ጋር ለመገናኘትና ልምድ ለመለዋወጥ መዘጋጀቱን ጠቅሷል፡፡ አፍሪካን በአዲስ ተስፋ ለመገንባትና ለመለወጥ መሰል መድረኮች ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ጠቅሷል፡፡ ከካሜሩን የተገኘው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ ሞስቲክ ካሪስማቲክ በበኩሉ፤ ጉባኤው ድንቅ ሀሳብን የያዘ መሆኑን ገልጿል። እንዲሁም ከአፍሪካውያን ወንድም እና እህቶች ጋር ለመተዋወቅ ትልቅ እድልን የሚፈጥር መሆኑን ተናግሯል። ጉባኤው ሀሳቦችን በማጣራት ጠንካራ አፍሪካን ለመገንባትና ጠንካራ የወጣቶች ተፅዕኖ ለመፍጠር ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን አንስቷል፡፡ ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል ብራድሊ ማሮንጎ በአዲስ አበባ መገኘቱ በጣም እንዳስደሰተው ጠቅሷል፡፡ አዲስ አበባን በጣም ምርጥ ከተማ በማለት ያሞካሸው ወጣቱ የይዘት ፈጣሪው፣ አብሮ ለመስራትና ልምድ ለመለዋወጥ በሙሉ ፈቃደኝነት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።
በዞኑ በዘንድሮ የመኸር እርሻ ለውጭ ምንዛሬ እና ለኢንዱስትሪ ግብዓት ለሚውሉ ሰብሎች ትኩረት ተሰጥቷል
May 7, 2026 24
ገንዳ ውሃ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ በምዕራብ ጎንደር ዞን በዘንድሮ የመኸር እርሻ ለውጭ ምንዛሬ እና ለኢንዱስትሪ ግብዓት ለሚውሉ ሰብሎች ይበልጥ ትኩረት መሰጠቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። በምዕራብ ጎንደር ዞን የ2018/19 ዓ.ም የመኸር እርሻ የሰብል ልማት ንቅናቄ መድረክ ዛሬ በገንዳ ውኃ ከተማ ተካሄዷል። የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ በመድረኩ እንደገለጹት፤ በመጪው ክረምት በሚካሄደው የሰብል ልማት ሥራ ምርታማነትን ለማሳደግ በቂ ዝግጅት ተደርጓል። በዞኑ በምርት ዘመኑ በዘር ለመሸፈን ከታቀደው 530 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት ውስጥ ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው ለውጭ ምንዛሬና ለኢንዱስትሪ ግብዓት በሚውሉ ሰብሎች እንደሚለማም ተናግረዋል። እንደ ሰሊጥ፣ አኩሪ አተር፣ ማሾ፣ ጥጥ እና ሱፍ ያሉ ሰብሎችን በሜካናይዝድ እርሻ በማልማት በአጠቃላይ ከ12 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህ ዓመት 219 አዳዲስ ትራክተሮች ወደ ዞኑ እንደገቡ የገለጹት አቶ አንዳርጌ፣ በዚህም የሜካናይዝድ እርሻን በማስፋፋት የሚጠበቀውን ምርት ለማግኘት በትጋት ይሰራል ብለዋል። በየደረጃው ያለው የግብርና ባለሙያና አመራሩ ለአርሶ አደሩና በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ጠንካራ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሰራም አሳስበዋል። የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው ፤ በ2018/19 የመኸር እርሻ 154 ሺህ 817 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የማሳ ዝግጅትና የጽዳት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በአይነት፣ በብዛትና በጥራት ለማምረት ትኩረት መሰጠቱንም አመልክተዋል። የመተማ ወረዳ ዋና አስተሳዳዳሪ አቶ ግዛት ሰረፀ በበኩላቸው እንዳሉት፤ በወረዳው የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ አስፈላጊ ግብአቶች እንዲሟላ እየተደረገ ነው። በዞኑ ለግብርና ልማት የተሰጠው ትኩረት የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢንዱስትሪ ልማት መፋጠንና ለውጭ ገበያ የምረት አቅርቦት ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።
ታሪካችንን በራሳችን አንደበት የምንነግርበት ጊዜ አሁን ነው
May 7, 2026 38
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ ታሪካችንን በራሳችን አንደበት የምንነግርበት እና የምንሰንድበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡ የአፍሪካን እውነተኛ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅና የዲጂታል ትርክቱን በባለቤትነት ለመምራት ያለመው የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል። ጉባኤው አፍሪካውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በአንድ መድረክ በማገናኘት በአህጉራቸው የጋራ ትልሞች ላይ እንዲመክሩ የሚያስችል መድረክ ነው፡፡ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ከአራቱም የአህጉሪቷ ማዕዘናት በመምጣት በውቧ አዲስ አበባ ከትመው የተለየዩ የልማት ሥራዎችን መጎብኘት ጀምረዋል፡፡ ከደቡብ ሱዳን የመጣችው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ አዲት ሱዛን ሰዎች ብዙ ጊዜ የአፍሪካን መጥፎ ገፅታ እንጂ ያላትን አቅም፣ ጸጋና በረከት አይናገሩም ብላለች፡፡ አፍሪካ ከዓለም ማዕዘናት ሁሉም ሊጎበኟት የሚገባ ውብ አህጉር መሆኗን በመጥቀስ፤ ጉባኤው የአህጉሪቱ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ወደ አንድ ማምጣቱ ያጋራ ትስስርን እንደሚያጠናክር ገልጻለች፡፡ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ጉባዔ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎችን አንድ ማድረግ ያስችላል ብላለች፡፡ ማላዊያዊው ኬቨን ጉምቢ (KBG)፤ አፍሪካ ሁሉም ሀብቶች፣ የሚያምሩ ታሪኮች እና የውብ ጥበቦች አድባር የሆነች አህጉር መሆኗን ገልጿል፡፡ ብዙውን ታሪካችንን ሌሎች ሲነግሩን ቆይተዋል ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪው፤ ታሪካችንን በራሳችን አንደበት የምንነግርበትና የምንሰንድበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል፡፡ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ይዞት የመጣው ሀሳብ ግሩም መሆኑን የገለጸው ደግሞ ከዩጋንዳ የመጣው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ ሞሰስ ኬዩኔ ነው። አፍሪካውያን በዚህ መንገድ መገናኘታቸው እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ፣ ባህላቸውን እንዲጋሩ እና እንዲያሳድጉ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጿል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ እርስ በእርስ ለመማማር እና ልምድ ለመለዋወጥ ትልቅ እድል ይዞ መምጣቱን ተናግሯል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ የህልውና ጉዳይ ነው
May 7, 2026 49
ወልቂጤ፣ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ ምሁራን ገለጹ፡፡ ለኢዜአ አስተያየት የሰጡ ምሁራን እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የነበራትን የባህር በር መልሶ ለማግኘት በሚደረገው ጥረት የመንግስትን ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ በጥናትና በምርምር ለመደገፍ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተውታል። የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፋሪስ ደሊል (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ያለ ህዝብ ይሁንታ ለዘመናት ትጠቀምበትና ትታወቅበት የነበረውን የባሕር በር በሴራ ማጣቷን ነው የሚገልጹት፡፡ በመሆኑም የባሕር በር ጥያቄ ተገቢና ፍትሃዊ በመሆኑ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት የጀመረውን ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ምሁራን በጥናትና ምርምር የመደገፍ ስራችንን ማጠናከር ይጠበቅብናል ሲሉ አመልክተዋል፡፡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ልማት መምህርና ተመራማሪ ኢንጂነር ቀነኒ ኤልያስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ የትውልድ ቁጭት መሆኑን ጠቅሰው ህጋዊና ታሪካዊ መሰረት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የባህር በር አልባ መሆን ኢኮኖሚያዊና የደህንነት ህልውናን የሚፈትን በመሆኑ መንግስት ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ ለጀመረው ጥረት የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል፡ የኢትዮጵያውያን የህልውና ጉዳይ የሆነው የባህር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የሁሉንም የጋራ ጥረት ይጠይቃል ያሉት ደግሞ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ መምህርና ተመራማሪ ስለሺ ታመነ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የባህር በር ጥያቄው ምላሽ ማግኘት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ መገንባት እንድትችልና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም አስረድተዋል፡፡ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህንድስናና አገልግሎት መምህርና ተመራማሪ እድሜዓለም ተመስገን፤ ከህዝብ ቁጥር መጨመርና ከኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ ለኢትዮጵያ የባህር በር መሻት ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ጭምር ነው ብለዋል። የባህር በር ጉዳይ ከኢኮኖሚና ማህበራዊ ጠቀሜታውም ባሻገር የደህንነትና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ጥያቄው ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ጥያቄው ለውጤት እንዲበቃ አንድነትን በማጠናከር መንቀሳቀስ እንደሚገባ አመልክተው ምሁራንም በጥናትና ምርምር የተደገፈ አበርክቷችንን ማጎልበት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ዘርፍ አፍሪካን ከቀሪው ዓለም ጋር በማስተሳሰር ግንባር ቀደም ሚና እየተወጣ ነው
May 7, 2026 44
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ዘርፍ አፍሪካን ከቀሪው ዓለም ጋር በማስተሳሰር ግንባር ቀደም ሚና እየተወጣ መሆኑን የኤርባስ የአፍሪካ አየር መንገድ ኃላፊ ገለጹ። ምርትና አገልግሎትን ለዓለም ገበያ በማድረስም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንግድና ኢንቨስትመንትን እያፋጠነ መሆኑን የኢትዮጵያ ስጋ አምራችና ላኪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ከሊፋ ሁሴን ተናግረዋል። የኤርባስ የአፍሪካ አየር መንገድ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ዩፕ ኢለርስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የአቬሽን ኢንዱስትሪ የአህጉራትን ንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር በማሳለጥ ወሳኝ ሚና የሚወጣ ዘርፍ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ባለፉት 80 ዓመታት የበረራ አገልግሎት አፍሪካን ከቀሪው ዓለም እያስተሳሰረ የሚገኝ አንጋፋ አህጉራዊ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የአፍሪካን ምርትና አገልግሎቶች በዓለም ገበያ በማስተዋወቅ ንግድና ኢንቨስትመንትን እያበረታታ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የበረራ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱም የአፍሪካን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር በማሳለጥ ገንቢ ሚና እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጠው የእንግዳ ተቀባይነት መስተንግዶም የሚደነቅ መሆኑን አረጋግጠዋል። ከበረራ አገልግሎት ባሻገርም በአውሮፕላን ጥገና፣በትምህርትና ስልጠና የአፍሪካ የአቪዬሽን ዘርፍ ዕድገት መገለጫነቱን የሚያሳልጥ ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል። በቀጣይም ኤርባስ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያለውን ትብብር የበለጠ በማጠናከር በአቪዬሽን ስልጠና በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ስጋ አምራችና ላኪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ከሊፋ ሁሴን በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ዓለም አቀፍ ምልክት ነው ብለዋል። የአየር መንገዱ የበረራ አድማስ እየሰፋ መምጣትም ምርትና አገልግሎትን ለዓለም ገበያ በማቅረብ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብርን እያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል።
ፖለቲካ
ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ጉዞ አጠናክሮ ይቀጥላል
May 7, 2026 84
ቀብሪ ደሃር፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ በሶማሌ ክልል ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ጉዞ አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱራህማን አህመድ ገለጹ። የብልጽግና ፓርቲ በሶማሌ ክልል ቆረሃይ ዞን ቀብሪ ደሃር ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚያደርገውን የምርጫ ቅስቀሳ እና የማኒፌስቶ ማስተዋወቅ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት አካሄደ። በዝግጅቱ ላይ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላትና የከተማዋ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን፤ ፓርቲው በቀጣይ ዓመታት ይዞአቸው የተነሳቸውን የልማትና የፖለቲካ ግቦች ይፋ አድርጓል። በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱራህማን አህመድ ፤ በክልሉ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ የልማት ዕቅዶች በዋናነት ዘላቂ ሰላምን ለመገንባትና ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፓርቲው በሀገሪቱ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ይበልጥ በማዘመንና የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በማስቀጠል፣ ብልጽግናን በተጨባጭ እውን የሚያደርጉ ስልታዊ ዕቅዶችን ቀርጾ ወደ ተግባር ገብቷል ብለዋል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ያደረጉ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል። የቆረሃይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሻፊ ሙሁመድ በበኩላቸው፤ በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች በተከናወኑ የመሠረተ ልማት ሥራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሻሽሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዞኑ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የሚፈለገውን ጥራት ጠብቀው በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በፍጥነት እየተገነቡ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በከተማው በተካሄደው የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሃግብር ላይ የፓርቲው ደጋፊዎች፣ የከተማዋ ነዋሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በምርጫው ሂደት ለዜጎች ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ የድርሻችንን እየተወጣን ነው-የሴቶች ፌዴሬሽን እና ማህበራት
May 7, 2026 42
አምቦ ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ በምርጫው ሂደት ዜጎች በቂ ግንዛቤ ይዘው ድምፃቸውን ለመስጠት የሚያስችል ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን የአምቦ ከተማ የሴቶች ፌዴሬሽን እና የሴቶች ማህበር ገለጹ። የ7ኛው ጠቅላላ የምርጫ ሂደት ቀጥሎ ፓርቲዎች ራሳቸውን እያስተዋወቁና የምረጡኝ ቅስቀሳ እያካሄዱ ይገኛሉ። መራጮችም ከፓርቲዎቹ ፖሊሲና ስትራቴጂ በመነሳት ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል የሚሉትን ለመምረጥ በዝግጅት ላይ ናቸው። በመሆኑም ዜጎች የተሻለ ግንዛቤ አግኝተው በምርጫው በመሳተፍ መብታቸውን እንዲጠቀሙ በማስገንዘብ ረገድ የሲቪል ማህበራት ሚና የማይተካ ነው። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመራጮች ትምህርት ላይ ለሚሠማሩ 169 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዕውቅና መስጠቱ ይታወቃል። በአምቦ ከተማ በዚሁ ተግባር ላይ ከተሰማሩት ድርጅቶች መካከል የኢዜአ ሪፖርተር የሴቶች ፌዴሬሽን እና የሴቶች ማህበርን አነጋግሯል። የሲቪል ማህበራቱ ሃላፊዎችም በምርጫው ሂደት ዜጎች በቂ ግንዛቤ ይዘው ድምፃቸውን ለመስጠት የሚያስችል ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ የድርሻችንን እየተወጣን እንገኛለን ብለዋል። የአምቦ ከተማ የሴቶች ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ወይዘሮ ድንበሬ ጥበቡ፤ የፌዴሬሽኑ አባላት ለየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ባለመወገን በገለልተኝነት ለማገልገል ቃል ገብተው እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በምርጫ ሥነ-ምግባር ህጎች ዙሪያ ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር ለአባላቱ የተሟላ ስልጠና መሰጠቱን አስታውሰው ለምርጫው ሰላማዊ ሂደት ሚናቸውን ለመወጣት ዝግጁ ስለመሆናቸውም አረጋግጠዋል። የአምቦ ከተማ የሴቶች ማሕበር ሊቀመንበር ወይዘሮ ሶስና ዲበኩሉ በበኩላቸው፣ ማህበሩ ሴቶች በመምረጥ፣ በመመረጥና በምርጫ ታዛቢነት ሂደት በመሳተፍ ሚናቸውን እንዲወጡ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለምርጫው ሰላማዊ ሂደት ማህበሩ ከሌሎች የሲቪክ ማህበራት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር ሀገራዊ አደራውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማካሄድ በመርሃ ግብር መያዙ ይታወቃል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረኮች ለዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ጥሩ መሰረት እያኖሩ ነው
May 7, 2026 78
ሆሳዕና፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረኮችና አጠቃላይ የምርጫው ሂደት ለዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ጥሩ መሰረት እያኖሩ መሆኑን የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማካሄድ በተያዘው ቀነ ቀጠሮ መሰረት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው። የመራጮች የምዝገባ ሂደት ተጠናቅቆ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በመገናኛ ብዙሀን አማራጭ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ለህዝብ በማቅረብ የማስገንዘብ ሥራ እየሰሩ ነው። በጉዳዩ ላይ ኢዜአ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ያነጋገራቸው ምሁራን እንደገለጹት፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሀዊ፣ ተአማኒና ቅቡልነት ያለው እንዲሆን ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች የሚበረታቱና መቀጠል ያለባቸው ናቸው። በዩኒቨርሲቲው በሰላምና ደህንነት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑትና የፌዴራሊዝምና ህገ መንግስት ተመራማሪ ተመስገን ቶማስ (ዶ/ር)፤ ጠቅላላ ምርጫውን ተአማኒ፣ ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች እንደሆኑ ተናግረዋል። በተለይ ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የመራጮች ምዝገባን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትን በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ ማድረጉ ሂደቱን ከማቀላጠፍ ባለፈ ተአማኒነትን እና ተሳትፎን እንደሚያሳድግም አመልክተዋል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያየ መገናኛ ብዙሀን አማራጭ ሀሳቦችን በማቅረብ ክርክር ማድረጋቸው ህዝቡ ይሆነኛል ያለውን ፓርቲ ለመለየት ከማስቻል ባለፈ የዴሞክራሲ ሂደትን እንደሚያጠናክርም ተናግረዋል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተፈጠረውን ምቹ ምህዳር በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው የገለጹት ተመስገን (ዶ/ር)፣ ህዝብና ሀገርን ወደተሻለ ደረጃ የሚያሻግሩ አማራጭ ሀሳቦችን ይዘው ሊቀርቡ ይገባል ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር ሳምሶን ወልዴ በበኩላቸው፣ ለ7ኛ ጊዜ ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች የሚደነቁ ናቸው ብለዋል። ከምዝገባ ሂደት ጀምሮ ፓርቲዎች የሚያደርጉትን ክርክር ህዝብ አውቆ በምርጫው በንቃት እንዲሳተፍ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የሚዲያ ተቋማት እየሰሩት ያለውን ሥራ ለአብነት ጠቅሰዋል። 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሀዊና ተአማኒ ለማድረግ በገለልተኛነት የተሰየሙ ተቋማት እያከናወኑ ያለው ተግባር የዴሞክራሲ ሂደት አካል ስለመሆኑም መምህር ሳምሶን አንስተዋል። የዴሞክራሲ ምህዳርን በማስፋት ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ እኩል ተሳታፊና ውሳኔ ሰጪ እንዲሆኑ የተጀመረው ጥረት እንዲጠናከር የሁሉም ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አክለዋል።
በለውጡ ዓመታት የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ተጠናክሯል
May 6, 2026 179
ጂንካ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በለውጡ ዓመታት ወጣቶች በሀገር ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸው መጠናከሩን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አለማየሁ ባውዲ ገለፁ። የጂንካ ከተማ ወጣቶች ብልጽግና ፓርቲን የሚደግፍ ሰልፍ አካሂደዋል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ አለማየሁ ባውዲ እንደገለጹት፣ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ወጣቱ በማህበራዊ፣ በፖለቲካው እና በኢኮኖሚ ዘርፍ በንቃት በመሳተፍ ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ወጣቱ በተለያዩ የሥራ ሃላፊነቶች በመሳተፍ ሀገር የመምራት ዕድል እያገኘ መጥቷል ብለዋል፡፡ ወጣቱ በሀገረ መንግስት ግንባታ የሚያደርገውን ንቁ ተሳትፎ ማጠናከር እንዳለበት ገልፀው፣ በተለይ ብሔራዊ ጥቅምንና የሀገር ሉአላዊነትን በማስጠበቅ የወጣቱ አስተዋጽኦ ጉልህ መሆኑን አመልክተዋል። የሀገር ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ እንዲፋጠንም ወጣቱ ራሱን በቴክኖሎጂ ከማብቃት ባለፈ የሚያገኘውን እድል በአግባቡ መጠቀም አለበት ብለዋል። የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ በበኩላቸው፤ በወጣት የተገነባች ሀገር መሰረቷ ጽኑ እንደሆነ አንስተዋል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት ወጣቱ በልማት ሥራዎች ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆንበት ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል። በዚህም ወጣቱ በጥፋት ተግባር ከመሰማራት ይልቅ የልማት አርበኛ ሆኖ ለሀገራዊ ብልጽግና አሻራቸውን ማኖር መጀመሩን ገልጸዋል። በሰልፉ የታደመው ወጣት እስራኤል አዳሙ፣ መንግስት ለወጣቱ በሰጠው ትኩረት በሁለንተናዊ መስኮች ተሳትፎውና ተጠቃሚነቱ እያደገ መምጣቱን ተናግሯል። ወጣት አዲሴ ምስሌ በበኩሉ፣ በአካባቢያቸው በሥራ ዕድል ፈጠራ ለወጣቱ ቅድሚያ መሰጠቱ ተጠቃሚነቱን እንዳሳደገው ነው የገለጸው። በአሁኑ ወቅትም በርካታ ወጣቶች ሰርተው ሀብት ማፍራት እንደጀመሩ ጠቅሶ፣ ወጣቱ በሀገሩ ጉዳይ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን የተጀመሩ ሥራዎች መጠናከር አለባቸው ብሏል።
ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት የማስቀጠል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል
May 6, 2026 179
ጅማ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት የማስቀጠል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ነመራ ቡሊ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በዕጩ ተወዳዳሪነት በቀረቡበት በጅማ ዞን ጎማ ሁለት ምርጫ ክልል ብልጽግና ፓርቲ እጩዎችን አስተዋውቋል። በመርሀ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ነመራ ቡሊ፤ ብልጽግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት የማስቀጠል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በፓርቲው አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ለላቀ ውጤት እንደሚሰራ አመላክተዋል። ፓርቲው የበለፀገች ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል። የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር በበኩላቸው፤ በዞኑ በለውጡ አመታት ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን አንስተው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል ።
በከተማዋ በየዘርፉ የተሻለ ለውጥ እንዲመዘገብ በትጋት እንሰራለን- የብልጽግና ፓርቲ አባላት
May 6, 2026 159
ደብረ ብርሃን ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ መንግስት በደብረ ብርሃን ከተማ በየመስኩ በጀመራቸው የልማት ስራዎች የተሻለ ለውጥ እንዲመዘገብ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ገለፁ። “ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር'' በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ፓርቲ የጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ ግብር በደብረ ብርሃን ዛሬ ተካሄዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ወይዘሮ ብርሃኔ ስዩም እንደሚሉት፤ በደብረ ብርሃን ከተማ በመደመር እሳቤ የተከናወኑት የልማት ስራዎች ሁለንተናዊ ስኬት እንዲመዘገቡ ያደረጉ ናቸው። የተጀመሩ የልማት ስራዎች ይበልጥ አድገውና ዳብረው የህዝብን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡም ለፓርቲው የሚያደርጉትን ድጋፍና እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የተናገሩት። ፓርቲው በከተማዋ እያከናወነ የሚገኘው ሰላምን የማፅናትና ልማትን የማረጋገጥ ስራዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው ያሉት ደግሞ አቶ መዝገቡ ተመኙ ናቸው። መጪው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ የተናገሩት ደግሞ ሌላው የምርጫ ቅስቀሳው ተሳታፊ አቶ በለጠ ወልደማሪያም ናቸው። በተለይም በእጩዎችና በመራጮች ምዝገባ ወቅት የታየውን የነቃ ተሳትፎና እንቅስቃሴ በድምፅ አሰጣጡ ወቅትም እንዲቀጥል ተገቢውን እገዛ ለማድረግ እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ከተማዋ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ማዕከል እየሆነች መጥታለች ነው ያሉት። መንግስት የከተማዋን እድገትና ደረጃዎች የሚያፋጥኑ አዳዲስ የመንገድ እና የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በርካታ የልማት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል። እንዲሁም ወጣቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ በማድረግ ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል። ከተማዋን የኢንዱስትሪ፣ የኢንቨስትመንት እና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።
ዜጋ-ተኮር ዲፕሎማሲን በማጠናከር የዜጎችን መብትና ክብር ማስጠበቅ
May 6, 2026 156
መንግሥት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲው ማዕከል "ዜጋ-ተኮር ዲፕሎማሲ" ነው ፡፡ በማንኛውም የዓለም ጥግ የሚኖር ኢትዮጵያዊና ትውልደ-ኢትዮጵያዊ የሀገር ክብር መገለጫ ነው ። መንግሥት ዜጎች ለሥራ፣ ለትምህርትም ሆነ ለተለያዩ ጉዳዮች ድንበር አቋርጠው በሚሄዱበት ወቅት መብታቸው፣ ደኅንነታቸውና ሰብዓዊ ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ማድረግ ዋነኛ ተግባሩ እንደሆነ ይታወቃል ። ልዩነቶች ቢኖሩም እንኳ ለብዝሃ-ሀሳብ እውቅና በመስጠት፣ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች በሀገራዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ግንባታ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ የሚሆኑበትን ምቹ ምህዳር መፍጠር ዋነኛው ግብ መሆኑ ነው ። መንግሥት ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት የሰውን ልጅ ክብርና ጥቅም ማዕከል ያደረገ አሰራር ተከትሏል ። ይህም በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅርና ተቆርቋሪነት እንዲጨምር አድርጓል ። ዜጎች በሄዱበት ዓለም ሁሉ አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲንቀሳቀሱ የሚገጥሟቸውን እንግልቶች በሁለትዮሽ ስምምነቶችና በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ለመቅረፍ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች እያመጡ ነው ። በተለይም ከሳውዲ አረቢያ፣ ኳታር፣ ኩዌት፣ ጆርዳን፣ ባህሬን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ጣሊያንና ሮማኒያ ጋር የተፈረሙ የሁለትዮሽ የሥራ ስምሪት ስምምነቶች ዜጎች በክብር የሚሰሩበትን መንገድ አመቻችተዋል። ተቋማዊ አሰራርን ለማጠናከርም "የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት" ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱና መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሄደው ችግር የገጠማቸውን ዜጎች በክብር የመመለስ ስራ በትኩረት መከናወኑ ይታወቃል ። በተጨማሪም ዳያስፖራው ያለምንም እንግልት ወደ ሀገሩ እንዲገባና በኢንቨስትመንት እንዲሳተፍ የሚያስችሉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል ። በሀገራዊ ምክክር ሂደትም ዳያስፖራው አጀንዳ እንዲያቀርብና ድምፁ እንዲሰማ በዓለም ዙሪያ ሰፊ መድረኮች መመቻቸታቸው የመንግሥትን አካታችነት በተግባር አሳይቷል ። በ2017 ዓ.ም ብቻ ለ503 ሺህ 000 ዜጎች በውጭ ሀገራት ሕጋዊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ። ከዳያስፖራው የሚላከው ሐዋላ ወደ 7.17 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከፍ እንዲል በማድረግ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ትልቅ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል ። ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከሳውዲ አረቢያ፣ የመን፣ ኦማን፣ ሱዳንና ሌሎች ሀገራት ከ500 ሺህ በላይ ዜጎችን በክብር በመቀበል፣ የሥነ-ልቦና ድጋፍ በመስጠትና ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ የማድረግ ስራ ተከናውኗል ። ዳያስፖራው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በመመከት ረገድ ያሳየው ተሳትፎም የመንግሥት አካታች ፖሊሲ ውጤት እንደሆነ ይታመናል ። መንግሥት በቀጣይ ለተጨማሪ 800 ሺህ000 ዜጎች በውጭ ሀገር የሥራ ዕድል መፍጠር፣ ከዳያስፖራው የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ወደ 8 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማድረግና ዳያስፖራው በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በቱሪዝም እና በሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ላይ ያለ ምንም ቢሮክራሲ እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ውጥን ይዟል ። በተጨማሪም ከ500 በላይ የሚሆኑ የዳያስፖራ ማህበራትን በማስተባበር የሀገርን ገፅታ የሚገነቡና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስከብሩ ተዋንያን እንዲሆኑ የማድረግ እቅድ ተይዟል። የዜጋ-ተኮር ዲፕሎማሲ ጉዞውን ይበልጥ ማጠናከር የዳያስፖራውን ተሳትፎ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያግዛል ። የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶችን እንደ ውበት በመቀበል፣ ሁሉንም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ምክክርና በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ በእኩልነት እንዲሳተፉ እየተደረገ ይገኛል ። የመደመር መንግሥት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ግብ ኢትዮጵያ የልጆቿን መብትና ክብር በዓለም አቀፍ መድረክ የምታስከብር፣ ራሷን በምግብ የቻለችና ሉዓላዊነቷ የተከበረ ታላቅ ሀገር ማድረግ ነው።
ለሀገር እድገት የተሻለ ሀሳብ ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫውን ቀን እየተጠባበቅን ነው
May 6, 2026 154
ሚዛን አማን፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በምርጫ ካርዳቸው ለሀገር እድገት የተሻለ ሀሳብ ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ቀንን እየተጠባበቁ መሆናቸውን የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ በጠቅላላ ምርጫው ለሀገርና ለህዝብ የተሻለ ሀሳብ ያለውን ፓርቲ ለመለየት በመገናኛ ብዙሀን የሚቀርቡ የፓርቲዎችን ክርክር እየተከታተሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላ ሀገሪቱ ከ50 ሚሊዮን 514 ሺህ በላይ መራጮች ተመዝግበው ካርድ እንደወሰዱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጹ የሚታወስ ነው። የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሏቸውን የፖሊሲና የፕሮግራም አማራጮችን በመገናኛ ብዙሀን ከማቅረብ ባለፈ ቅስቀሳዎችን እያደረጉም ይገኛሉ። በምርጫው ላይ ኢዜአ በሚዛን አማን ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎችም በወሰዱት የምርጫ ካርድ ይሆነኛል ለሚሉት ፓርቲ ድምጻቸውን በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ዘላለም ዜና ምርጫ ዴሞክራሲን ከምንለማመድባቸው መንገዶች አንዱ በመሆኑ ይህን ዕድል ሳናባክን መጠቀም አለብን ብለዋል። በወሰድኩት የምርጫ ካርድ ድምጼን ለሀገር ልማትና ሰላም መጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ ያደርጋል ለምለው ፓርቲ ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ ያሉት ነዋሪው፣ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የአንድ ሰው ድምጽ ትልቅ ዋጋ ስላለው ሁሉም በንቃት መሳተፍ አለበት ብለዋል። እስካሁንም በመገናኛ ብዙሀን እየተካሄደ ያለው የፓርቲዎች የምርጫ ክርክርን ሲከታተሉ መቆየታቸውን ገልጸው፣ በምርጫው ቀንም ለሀገር እድገት የተሻለ ሀሳብ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቻያለሁ ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችን ፕሮግራም ከወዲሁ ለመለየት የፓርቲዎችን የክርክርና የቅስቀሳ መድረክ እየተከታተልን ነው፤ በምርጫው ቀንም ይሆነኛል ለምለው ፓርቲ ድምጼን እሰጣለሁ ያሉት ደግሞ አቶ ወልደሚካኤል ተሾመ ናቸው። በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የአንድ ሰው ድምጽ ዋጋ ስላላት በምርጫው ቀን የመምረጥ መብቴን በመጠቀም አሻራዬን ለማሳረፍ ተዘጋጅቻለሁ ብለዋል ። ወይዘሮ አፀደ አቱሞ የተባሉ ሌላዋ የከተማዋ ነዋሪ በበኩላቸው፤ በጠቅላላ ምርጫው ሀገር ለመምራትና ለማሻገር ብቁ ነው የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ለመሳተፍ ካርድ ወስዶ የምርጫውን እለት በጉጉት እየተጠባበቀ መሆኑን የተናገረው ደግሞ ወጣት አሻግሬ መቹል ነው። የሀገርን ልማት በማፋጠን ህዝብን ተጠቃሚ ያደርጋል ለሚለው የፖለቲካ ፓርቲ ድምጹን በመስጠት ኃላፊነቱን እንደሚወጣ ተናግሯል።

ማህበራዊ
ጉባኤው የአህጉሪቱን እውነተኛ ገጽታ ለማስተዋወቅ ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው
May 7, 2026 23
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ) ፦ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ የአህጉሪቱን እውነተኛ ገጽታ ለማስተዋወቅና የለውጥ ትርክትን ለመገንባት ትልቅ መሠረት የሚጥል መሆኑን የጉባኤው ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡ የአፍሪካን እውነተኛ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅና የዲጂታል ትርክቱን በባለቤትነት ለመምራት ያለመው የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል። በጉባኤው ለመታደም ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 321 ሚሊዮን በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ያሏቸው 61 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ ከትመዋል። በተጨማሪም 150 ሚሊዮን ተከታዮች ያላቸው 120 ኢትዮጵያውያን የይዘት ፈጣሪዎች በጋራ በመሰባሰብ፣ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ አዲስ የዲጂታል ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅተዋል፡፡ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ /pulse of Africa/ ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ጉባዔ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" የሚል መሪ ሀሳብ ይዟል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ከአራቱም የአህጉሪቷ ማዕዘናት በመምጣት በውቧ አዲስ አበባ ከትመው የተለየዩ ሥራዎችን መጎብኘት ጀምረዋል፡፡ ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል ከኬንያ የመጣው ወጣቱ ሳሙኤል ማቦቴ፣ አዲስ አበባን "ውብና በእርግጥም የአፍሪካ ዋና ከተማ" በማለት ገልጾ፣ በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ በመሳተፉ የተሰማውን ኩራት ገልጿል። በመላው አፍሪካ የሚገኙ የይዘት ፈጣሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙበትን ይህን መድረክ ላዘጋጁት አካላት ምስጋናውን ያቀረበው ሳሙኤል፤ ማህበራዊ ሚዲያ የወደፊት ዕጣ ፈንታችን በመሆኑ፣ ወደዚህ ዘመናዊ ምዕራፍ መሸጋገር አለብን ብሏል፡፡ አፍሪካን ለመገንባትና ለመለወጥ ማህበራዊ ሚዲያን መጠቀም ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከመላው ዓለም ከመጡ የይዘት ፈጣሪዎች ጋር ለመገናኘትና ልምድ ለመለዋወጥ መዘጋጀቱን ጠቅሷል፡፡ አፍሪካን በአዲስ ተስፋ ለመገንባትና ለመለወጥ መሰል መድረኮች ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸው ጠቅሷል፡፡ ከካሜሩን የተገኘው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ ሞስቲክ ካሪስማቲክ በበኩሉ፤ ጉባኤው ድንቅ ሀሳብን የያዘ መሆኑን ገልጿል። እንዲሁም ከአፍሪካውያን ወንድም እና እህቶች ጋር ለመተዋወቅ ትልቅ እድልን የሚፈጥር መሆኑን ተናግሯል። ጉባኤው ሀሳቦችን በማጣራት ጠንካራ አፍሪካን ለመገንባትና ጠንካራ የወጣቶች ተፅዕኖ ለመፍጠር ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን አንስቷል፡፡ ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል ብራድሊ ማሮንጎ በአዲስ አበባ መገኘቱ በጣም እንዳስደሰተው ጠቅሷል፡፡ አዲስ አበባን በጣም ምርጥ ከተማ በማለት ያሞካሸው ወጣቱ የይዘት ፈጣሪው፣ አብሮ ለመስራትና ልምድ ለመለዋወጥ በሙሉ ፈቃደኝነት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።
ታሪካችንን በራሳችን አንደበት የምንነግርበት ጊዜ አሁን ነው
May 7, 2026 38
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ ታሪካችንን በራሳችን አንደበት የምንነግርበት እና የምንሰንድበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ጉባኤ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡ የአፍሪካን እውነተኛ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅና የዲጂታል ትርክቱን በባለቤትነት ለመምራት ያለመው የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል። ጉባኤው አፍሪካውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በአንድ መድረክ በማገናኘት በአህጉራቸው የጋራ ትልሞች ላይ እንዲመክሩ የሚያስችል መድረክ ነው፡፡ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ከአራቱም የአህጉሪቷ ማዕዘናት በመምጣት በውቧ አዲስ አበባ ከትመው የተለየዩ የልማት ሥራዎችን መጎብኘት ጀምረዋል፡፡ ከደቡብ ሱዳን የመጣችው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ አዲት ሱዛን ሰዎች ብዙ ጊዜ የአፍሪካን መጥፎ ገፅታ እንጂ ያላትን አቅም፣ ጸጋና በረከት አይናገሩም ብላለች፡፡ አፍሪካ ከዓለም ማዕዘናት ሁሉም ሊጎበኟት የሚገባ ውብ አህጉር መሆኗን በመጥቀስ፤ ጉባኤው የአህጉሪቱ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ወደ አንድ ማምጣቱ ያጋራ ትስስርን እንደሚያጠናክር ገልጻለች፡፡ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ጉባዔ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎችን አንድ ማድረግ ያስችላል ብላለች፡፡ ማላዊያዊው ኬቨን ጉምቢ (KBG)፤ አፍሪካ ሁሉም ሀብቶች፣ የሚያምሩ ታሪኮች እና የውብ ጥበቦች አድባር የሆነች አህጉር መሆኗን ገልጿል፡፡ ብዙውን ታሪካችንን ሌሎች ሲነግሩን ቆይተዋል ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪው፤ ታሪካችንን በራሳችን አንደበት የምንነግርበትና የምንሰንድበት ጊዜ አሁን ነው ብሏል፡፡ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ይዞት የመጣው ሀሳብ ግሩም መሆኑን የገለጸው ደግሞ ከዩጋንዳ የመጣው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ ሞሰስ ኬዩኔ ነው። አፍሪካውያን በዚህ መንገድ መገናኘታቸው እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ፣ ባህላቸውን እንዲጋሩ እና እንዲያሳድጉ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጿል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ እርስ በእርስ ለመማማር እና ልምድ ለመለዋወጥ ትልቅ እድል ይዞ መምጣቱን ተናግሯል።
በአማራ ክልል የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግርን ለማቃለል የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
May 7, 2026 40
ባህር ዳር ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግርን ለማቃለል የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ገለፀ። የቢሮው ኃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ በክልሉ ከተሞች የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግር በተለያዩ አማራጮች የመፍታት ስራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም በማህበራት እና በጋራ የቤት ልማት የተደራጁትን ጨምሮ ሪል ስቴት ቤት ለመገንባት ለፈለጉ ዜጎች እንደየ ሁኔታው ታይቶ የግንባታ ቦታ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል። በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከ140 ሺህ ለሚልቁ ግለሰቦችና ማህበራት ቤት መስርያ ቦታ በመስጠት ወደ ቤት ልማት ስራ እንዲገቡ መደረጉን ገልፀዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራትም 51 ሺህ 460 የመኖሪያ ቤቶች በግል አልሚዎች፣ በማህበራት፣ በሪልስቴት እና በመንግስት መገንባታቸውን ነው የገለጹት። በዚህ በጀት ዓመትም ከ288 ሺህ በላይ ዜጎች በማህበር በመደራጀት ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል ቦታ መውሰድ እንዲችሉ ቅድመ ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል። አባላቱ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ መቆጠብ የቻሉ ሲሆን ከ5 ሺህ 600 ሄክታር በላይ መሬት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው ያመለከቱት። በአሁኑ ወቅትም ለአንድ ሺህ 12 ማህበራት የግንባታ ቦታ ማስረከብ የተቻለ መሆኑን ጠቁመው ቀሪ ማህበራትን ተጠቃሚ ለማድረግም የመረጃ ማጥራትን ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል። ማህበራቱ በጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ትኩረት እንዲያደርጉ እየተደረገ ሲሆን ይህም መሰረተ ልማት ለማሟላትም ሆነ የግንባታ ቁሳቁሶችን በቡድን ለመጠቀም ሰፊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት። በተለይም አዳዲስ በሚለሙ መንደሮች የመንገድ፣ የውሃ፣ የመብራት እና መሰል መሰረተ ልማት ፈጥነው እንዲሟሉም ትኩረት መደረጉን አብራርተዋል። የቤት ግንባታዎች የከተሞችን ዘላቂ እድገት መሰረት ባደረገ የግንባታ ፕላን መሰረት እንዲከናወኑም አስፈላጊ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ጨምረው አስታውቀዋል።
በደሴ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ ናቸው
May 7, 2026 69
ደሴ ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦በደሴ ከተማ የተመለከቷቸው የልማት ስራዎች ለህዝብ ጥያቄ ምላሽን ከመስጠት ባሻገር ቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለፁ። የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በደሴ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅትም የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮቹ እንደገለፁት፤ በደሴ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ ናቸው። "የሰላም ለኢትየጵያ ጥምር ፓርቲ" የምርጫና ፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊና የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ፕሬዚዳንት አቶ አላምረው ይርዳው፤ የኢትየጵያ ህዝብ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና አንድነት የሚረጋገጠው በሚገነቡ የልማት ስራዎች ትስስር ነው ብለዋል። በደሴ ከተማ የተመለከትነው የልማት ስራ ህብረተሰቡን በተግባር ተጠቃሚ ያደረገ፣ ለዘመናት የልማት ጥያቄ መልስ የሰጠና የቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ተገንዝበናል ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ ለመሰረተ ልማት ግንባታ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የኮሪደር ልማት፣ ስማርት ሲቲ፣ የአስፋልት መንገድና ሌሎች የልማት ስራዎች ልምድና ተሞክሮ ሊወሰድባቸው የሚገባ መሆናቸውን ተናግረዋል። የእኛ ህልም፣ ራዕይና ሀሳብ ህብረተሰቡ በልማትና በመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ሲሆን ማየት ነው ያሉት ደግሞ የወሎ ህዝቦች ዲሞክራሲ ፓርቲ የምርጫና ዴሞክራሲ ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ የሺበር ጌጡ ናቸው። በደሴ ከተማ የተመለከትነው የልማት ስራም አስደናቂና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ በመሆኑ ተደስተናል፣ በሌሎች አካባቢዎችም እንዲደገም እንፈልጋለን ብለዋል። የአንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የቦርድ አባል አቶ ዮሴፍ አሻግሬ በበኩላቸው፤ በደሴ ከተማ በተመለከትነው የልማት ስራ የአመራሩ፣ የባለሙያውና የህብረተሰቡ ቅንጅት ውጤት ነው ሲሉ ገልጸዋል። ይህም የዘመናት የልማት ጥያቄን ለመመለስ ውጤታማ የልማት ስራዎችን በማከናወን ከተማዋን ለቱሪዝም፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፣ የከተማውን ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ህብረተሰቡን በማስተባበር ሰፋፊ የልማት ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ቀርፏል ያሉት አቶ ሳሙኤል በኮሪደር ልማት፣ በአስፋልት መንገድና በስራ እድል ፈጠራ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል። ተፎካካሪ ፓርቲዎችም በከተማው የተሰሩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸው እየመጣ ያለውን ቀጣይነት ያለው ለውጥ ተገንዝበው ለልማት ያላቸውን ትብብር እንዲያጠናክሩ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። በጉብኝቱ ላይም የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የደሴ ከተማ አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ኢኮኖሚ
በዞኑ በዘንድሮ የመኸር እርሻ ለውጭ ምንዛሬ እና ለኢንዱስትሪ ግብዓት ለሚውሉ ሰብሎች ትኩረት ተሰጥቷል
May 7, 2026 24
ገንዳ ውሃ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ በምዕራብ ጎንደር ዞን በዘንድሮ የመኸር እርሻ ለውጭ ምንዛሬ እና ለኢንዱስትሪ ግብዓት ለሚውሉ ሰብሎች ይበልጥ ትኩረት መሰጠቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ። በምዕራብ ጎንደር ዞን የ2018/19 ዓ.ም የመኸር እርሻ የሰብል ልማት ንቅናቄ መድረክ ዛሬ በገንዳ ውኃ ከተማ ተካሄዷል። የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ በመድረኩ እንደገለጹት፤ በመጪው ክረምት በሚካሄደው የሰብል ልማት ሥራ ምርታማነትን ለማሳደግ በቂ ዝግጅት ተደርጓል። በዞኑ በምርት ዘመኑ በዘር ለመሸፈን ከታቀደው 530 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት ውስጥ ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው ለውጭ ምንዛሬና ለኢንዱስትሪ ግብዓት በሚውሉ ሰብሎች እንደሚለማም ተናግረዋል። እንደ ሰሊጥ፣ አኩሪ አተር፣ ማሾ፣ ጥጥ እና ሱፍ ያሉ ሰብሎችን በሜካናይዝድ እርሻ በማልማት በአጠቃላይ ከ12 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህ ዓመት 219 አዳዲስ ትራክተሮች ወደ ዞኑ እንደገቡ የገለጹት አቶ አንዳርጌ፣ በዚህም የሜካናይዝድ እርሻን በማስፋፋት የሚጠበቀውን ምርት ለማግኘት በትጋት ይሰራል ብለዋል። በየደረጃው ያለው የግብርና ባለሙያና አመራሩ ለአርሶ አደሩና በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ጠንካራ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሰራም አሳስበዋል። የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው ፤ በ2018/19 የመኸር እርሻ 154 ሺህ 817 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የማሳ ዝግጅትና የጽዳት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በአይነት፣ በብዛትና በጥራት ለማምረት ትኩረት መሰጠቱንም አመልክተዋል። የመተማ ወረዳ ዋና አስተሳዳዳሪ አቶ ግዛት ሰረፀ በበኩላቸው እንዳሉት፤ በወረዳው የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ አስፈላጊ ግብአቶች እንዲሟላ እየተደረገ ነው። በዞኑ ለግብርና ልማት የተሰጠው ትኩረት የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢንዱስትሪ ልማት መፋጠንና ለውጭ ገበያ የምረት አቅርቦት ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ የህልውና ጉዳይ ነው
May 7, 2026 49
ወልቂጤ፣ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ ምሁራን ገለጹ፡፡ ለኢዜአ አስተያየት የሰጡ ምሁራን እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የነበራትን የባህር በር መልሶ ለማግኘት በሚደረገው ጥረት የመንግስትን ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ በጥናትና በምርምር ለመደገፍ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑንም አፅንኦት ሰጥተውታል። የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፋሪስ ደሊል (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ያለ ህዝብ ይሁንታ ለዘመናት ትጠቀምበትና ትታወቅበት የነበረውን የባሕር በር በሴራ ማጣቷን ነው የሚገልጹት፡፡ በመሆኑም የባሕር በር ጥያቄ ተገቢና ፍትሃዊ በመሆኑ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት የጀመረውን ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ምሁራን በጥናትና ምርምር የመደገፍ ስራችንን ማጠናከር ይጠበቅብናል ሲሉ አመልክተዋል፡፡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ልማት መምህርና ተመራማሪ ኢንጂነር ቀነኒ ኤልያስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ የትውልድ ቁጭት መሆኑን ጠቅሰው ህጋዊና ታሪካዊ መሰረት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የባህር በር አልባ መሆን ኢኮኖሚያዊና የደህንነት ህልውናን የሚፈትን በመሆኑ መንግስት ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ ለጀመረው ጥረት የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል፡ የኢትዮጵያውያን የህልውና ጉዳይ የሆነው የባህር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የሁሉንም የጋራ ጥረት ይጠይቃል ያሉት ደግሞ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የጂኦግራፊ መምህርና ተመራማሪ ስለሺ ታመነ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የባህር በር ጥያቄው ምላሽ ማግኘት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ መገንባት እንድትችልና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም አስረድተዋል፡፡ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህንድስናና አገልግሎት መምህርና ተመራማሪ እድሜዓለም ተመስገን፤ ከህዝብ ቁጥር መጨመርና ከኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ ለኢትዮጵያ የባህር በር መሻት ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ጭምር ነው ብለዋል። የባህር በር ጉዳይ ከኢኮኖሚና ማህበራዊ ጠቀሜታውም ባሻገር የደህንነትና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ጥያቄው ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ጥያቄው ለውጤት እንዲበቃ አንድነትን በማጠናከር መንቀሳቀስ እንደሚገባ አመልክተው ምሁራንም በጥናትና ምርምር የተደገፈ አበርክቷችንን ማጎልበት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ዘርፍ አፍሪካን ከቀሪው ዓለም ጋር በማስተሳሰር ግንባር ቀደም ሚና እየተወጣ ነው
May 7, 2026 44
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቪዬሽን ዘርፍ አፍሪካን ከቀሪው ዓለም ጋር በማስተሳሰር ግንባር ቀደም ሚና እየተወጣ መሆኑን የኤርባስ የአፍሪካ አየር መንገድ ኃላፊ ገለጹ። ምርትና አገልግሎትን ለዓለም ገበያ በማድረስም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንግድና ኢንቨስትመንትን እያፋጠነ መሆኑን የኢትዮጵያ ስጋ አምራችና ላኪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ከሊፋ ሁሴን ተናግረዋል። የኤርባስ የአፍሪካ አየር መንገድ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ዩፕ ኢለርስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የአቬሽን ኢንዱስትሪ የአህጉራትን ንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር በማሳለጥ ወሳኝ ሚና የሚወጣ ዘርፍ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ባለፉት 80 ዓመታት የበረራ አገልግሎት አፍሪካን ከቀሪው ዓለም እያስተሳሰረ የሚገኝ አንጋፋ አህጉራዊ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የአፍሪካን ምርትና አገልግሎቶች በዓለም ገበያ በማስተዋወቅ ንግድና ኢንቨስትመንትን እያበረታታ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የበረራ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱም የአፍሪካን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር በማሳለጥ ገንቢ ሚና እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጠው የእንግዳ ተቀባይነት መስተንግዶም የሚደነቅ መሆኑን አረጋግጠዋል። ከበረራ አገልግሎት ባሻገርም በአውሮፕላን ጥገና፣በትምህርትና ስልጠና የአፍሪካ የአቪዬሽን ዘርፍ ዕድገት መገለጫነቱን የሚያሳልጥ ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል። በቀጣይም ኤርባስ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ያለውን ትብብር የበለጠ በማጠናከር በአቪዬሽን ስልጠና በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ስጋ አምራችና ላኪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ከሊፋ ሁሴን በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ዓለም አቀፍ ምልክት ነው ብለዋል። የአየር መንገዱ የበረራ አድማስ እየሰፋ መምጣትም ምርትና አገልግሎትን ለዓለም ገበያ በማቅረብ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብርን እያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል።
በምስራቅ ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ የለማ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያን ለማረጋጋት አግዟል
May 7, 2026 44
አዳማ ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ የለማ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ገበያን ለማረጋጋት ማገዙን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለፀ። የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ አብነት ዘገየ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ በዘንድሮ የበጋ ወቅት ባህላዊና ዘመናዊ መስኖን በመጠቀም ከ63 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ ለምቷል። የአዋሽ ወንዝን በመጥለፍና የከርሰ ምድር ውሃን በመጠቀም በስፋት ከለሙት አትክልቶች መካከል ቲማቲም፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ጥቅል ጎመን፣ ድንችና ሌሎችም የስራስር ምርቶች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል። ከፍራፍሬ ምርቶች መካከልም ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ እና ሀብሀብ ዋንኞቹ መሆናቸውን አመልክተዋል። በዚህም በመጀመሪያ ዙር ከለማው አትክልትና ፍራፍሬ ከ9 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን ተናግረዋል። የተሰበሰበው ምርት ገበያን በማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመው ለአርሶ አደሩም የገቢ ምንጭ ከመሆን ባለፈ ስርአተ ምግብን ለማሻሻል ማገዙን ገልጸዋል። እንዲሁም ዘርፉ ለስራ እድል ፈጠራ አይነተኛ ሚና መጫወቱን አመልክተዋል። በበጋ መስኖ ልማቱ ከ35 ሺህ በላይ ወጣቶችና አርሶ አደሮች መሳተፋቸውንም አስታውቀዋል። በዞኑ የገፀና ከርሰ ምድር የውኃ ሀብትን በመጠቀም 2ኛው ዙር የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ ልማት እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል ።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን እየጎበኙ ነው
May 7, 2026 79
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እየጎበኙ ነው፡፡ የአፍሪካን እውነተኛ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅና የዲጂታል ትርክቱን በባለቤትነት ለመምራት ያለመው የመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል። በጉባኤው ለመታደም ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 321 ሚሊዮን በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ያሏቸው 61 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ ከትመዋል። በተጨማሪም 150 ሚሊዮን ተከታዮች ያላቸው 120 ኢትዮጵያውያን የይዘት ፈጣሪዎች በጋራ በመሰባሰብ፣ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ አዲስ የዲጂታል ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅተዋል፡፡ በዚህም የጉባኤው አካል የሆነውን ጉብኝት የጀመሩ ሲሆን፤ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናነቷን የሚመጥነውን ሥራዎቿን ታስጎበኛለች፡፡ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ /pulse of Africa/ ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ጉባዔ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" የሚል መሪ ሀሳብ ይዟል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ ሀላፊነት የሚሰማቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት፣ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማጠናከር፣ ትብብርን ለመፍጠርና አዲስ አበባን የባህልና የዲጂታል ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው።
ዲጂታል አገልግሎት የአሰራር ዘመናዊነትን እና የምርታማነት እድገትን በተጨባጭ እያረጋገጠ ነው
May 7, 2026 76
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ የዲጂታል አገልግሎት አሰራርን በማዘመን፣ ብልሹ አሰራርን በመከላከልና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አስታወቀ። ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ-ግብሯ አማካኝነት ቴክኖሎጂን ለዘላቂ እድገት እንደ ዋና መነሻ በመጠቀም ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች። በዚህም ኢኮኖሚውን የሚያሳልጡ የዲጂታል ዘርፍ ስራዎች በስኬት እየተከናወኑ ነው። በተለይም እንደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ፋይዳ መታወቂያ እና ኢትዮ-ኮደርስ ያሉ መድረኮች መዘርጋታቸው እንዲሁም የኢንተርኔት ተደራሽነት መጨመሩ ለሀገራዊ ለውጡ ትልቅ ፋይዳ አለው። እነዚህ የቴክኖሎጂ ስኬቶች የሞባይል ክፍያና የኢ-ኮሜርስ ስርዓትን በማቀላጠፍ፣ የተገልጋዮችን ጊዜና ወጪ በመቆጠብ ረገድ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተብራርቷል። የአዲስ አበባ ከተማ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ቱሉ ጥላሁን (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ቴክኖሎጂ አሰራርን በማዘመን፣ ብልሹ አሰራርን በመከላከልና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና አለው፡፡ አዲስ አበባን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በተነደፈው የስምንት ዓመት ስትራቴጂክ ፕላን አማካኝነት በኮሪደር ልማትና በመዝናኛ ስፍራዎች ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውንም ጠቁመዋል። የስማርት ሲቲ ግንባታ ዋና ዓላማ ከተማዋን ለነዋሪዎችና ለእንግዶች ምቹና ሳቢ ማድረግ ሲሆን፣ ይህም የሚረጋገጠው አገልግሎቶችና መሰረተ ልማቶች በቴክኖሎጂ ሲደገፉ መሆኑን አብራርተዋል። በዚህም በከተማዋ የተከናወኑ ስኬታማ የቴክኖሎጂ ስራዎች ከንቲባ አዳነች አቤቤ እ.ኤ.አ በ2024 በደቡብ ኮሪያ ሴዑል በተካሄደው የዓለም አቀፍ ስማርት ሲቲ አመራር ውድድር አሸናፊ እንዲሆኑ ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ተግባራት መዲናዋ በኬኒያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ስማርት ሲቲ ፎረም ላይ ተገቢውን እውቅና እንድታገኝ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ነው ያሉት። የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት አገልግሎታቸውን በዲጂታል መንገድ እንዲያቀርቡ ለማስቻል፣ ቢሮው የቴክኖሎጂ ስርዓቶችን የማበልጸግ፣ የማቀናጀትና ደህንነታችውን የማስጠበቅ ስራዎችን ከፌዴራል ተቋማት ጋር በመተባበር እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የወረዳ ኔት መሠረተ ልማትን ወደ ሲቲ ኔት በማሳደግ በከተማዋ የሚገኙ ወረዳዎችንና ክፍለ ከተሞችን በቴክኖሎጂ ማስተሳሰር ተችሏል ብለዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለዜጎች በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን፣ ተአማኒ፣ ፍትሐዊና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡ አገልግሎቱ የተገልጋዮችን እንግልት በመቀነስና ግልጽነትን በመፍጠር፣ ህብረተሰቡ በዲጂታል አማራጮችን የመጠቀም ልምዱ እንዲዳብር ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል። በቀጣይም ወደ ዲጂታል ሥርዓት ያልገቡ አገልግሎቶችን የማዘመንና ወደ "መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት የማስገባት ሥራ ትኩረት እንደሚሰጠው አስታውቀዋል።
በከተማዋ ለባለይዞታዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የዲጂታል ካርታ እየተዘጋጀ ነው
May 7, 2026 56
ጎንደር ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦በጎንደር ከተማ ከ45 ሺህ በላይ የቤትና የቦታ ባለይዞታዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የዲጂታል ካርታ ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን የከተማዋ መሬት መምሪያ አስታወቀ። የዲጂታል ካርታው አሰራር በመሬት አስተዳደር ዙሪያ የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታትና ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን ያለመ እንደሆነም ተገልጿል። የከተማው መሬት መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ አዛናው መልካሙ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የዲጂታል ካርታው በዘርፉ የሚስተዋለውን የነዋሪዎች የመልካም አስተዳደር ቅሬታ ከመሠረቱ በሚፈታ መልኩ እየተከናወነ ነው። በስድስት ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የቤትና የቦታ ይዞታዎችን ወደ ዲጂታል የካርታ አሰራር ስርአት ለመቀየር መረጃን በመሰብሰብ፣ በማደራጀትና በማጣራት ወደ መረጃ ቋት የማስገባት ስራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከአራት ሺህ በላይ የከተማ ቦታና ቤት ባለይዞታዎችን በመመዝገብ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ባለይዞታዎች ዲጂታል ካርታ ማስረከብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ዲጂታል ካርታው ህጋዊነቱ የተረጋገጠ ይዞታ እንዲኖራቸው ከማድረግ ባለፈ ቀደም ሲል ይፈጸሙ የነበሩ በካርታ ላይ ካርታ የመስጠት፣ መረጃ የማጥፋትና የስርቆት ድርጊቶችን ለማስቀረት የሚያስችል ነው ብለዋል። ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከልና ውድ ሃብት የሆነውን መሬት በአግባቡ ይዞ ለሚፈለገው ልማት ለማዋል ጭምር ፋይዳው የጎላ መሆኑንም አስረድተዋል። የዲጂታል ካርታ ስርአቱን ከከተማው የስማርት ሲቲ ተግባራት ጋር በማቀናጀት በቅርቡ ከተጀመረው የዲጂታል የመኖሪያ ቤት መለያ ቁጥር አሰጣጥ ጋር በማስተሳሰር የሚፈጸም መሆኑን አብራርተዋል፡፡ መምሪያው በጥናት የተለዩትን የባለይዞታዎች መረጃን ወደ ዲጂታል የመረጃ ስርአት በመቀየር ዲጂታል ካርታን ተደራሽ የማድረግ ስራውን በሚቀጥለው ዓመት ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ዩኒቨርሲቲው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጉዞ የሚያፋጥኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል
May 6, 2026 121
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጉዞ የሚያፋጥኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ። "ትምህርትን በምርምር፣ በዲጂታላይዜሽን፣ በፈጠራና በኢንዱስትሪ ትብብር ማሳደግ" በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው የምርምር፣ የፈጠራና የአውደ-ርዕይ ሳምንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ተጀምሯል፡፡ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ አውደ-ርዕይ ላይ ሳይንሳዊ የፓናል ውይይቶች የሚካሄዱ ሲሆን፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና ግኝቶች ለጉብኝት ቀርበዋል። የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመክፈቻው ላይ እንደገለጹት፤ ተቋሙ በጥናትና ምርምር ዘርፍ ያለውን ሰፊ ተሞክሮ በመጠቀም ለሀገር ግንባታ የሚሰጠውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል። በትምህርት ዘርፉ የሚከናወኑ ማናቸውም ተግባራት የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያፋጥኑ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ምርምሮቻችን የሕዝባችንን ችግር ሊፈቱ ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ዩኒቨርሲቲው የሚያመነጫቸው እውቀቶችና የፈጠራ ሃሳቦች ወደ ተግባራዊ መፍትሄ እንዲቀየሩ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በዩኒቨርሲቲውና በኢንዱስትሪው መካከል ያለውን ቅንጅት በማጠናከር፣ የምርምር ውጤቶች በቀጥታ ለኢንዱስትሪው ግብዓት የሚሆኑበት ሥርዓት መዘርጋቱንም አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዲን የቆየአለም ደሴ (ዶ/ር)፤ አውደ-ርዕዩ በዋናነት በትምህርት፣ በምርምር፣ በዲጂታላይዜሽንና በኢንዱስትሪ ትብብር ላይ ያተኮረ መሆኑን አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ያለውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን አዳዲስ ግኝቶች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው የገለጹት ዲኑ፤ ትምህርት በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ እንዲሆን መስራት ዋነኛ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል። በተጨማሪም ትምህርት ከንድፈ-ሃሳብ ባለፈ የተማሪዎችንና የተመራማሪዎችን አቅም ወደ ተግባር የሚለውጥ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። ይህ አውደ-ርዕይ በምሁራን፣ በተማሪዎችና በባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ የልምድ ልውውጥ የሚደረግበትና የወደፊት የትብብር መድረክ የሚፈጠርበት ታላቅ አጋጣሚ እንደሚሆን ተገልጿል።
ስፖርት
አዲስ አዳጊዎቹ ጋሞ ጨንቻ እና ሃላባ ከተማ የከፍተኛ ሊግ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ
May 7, 2026 64
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደጉት ጋሞ ጨንቻ እና ሃላባ ከተማ የከፍተኛ የሊግ የፍጻሜ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ። ጨዋታው ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል። ጋሞ ጨንቻ በምድብ ሀ በ41 ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል። በምድብ ለ የተጫወተው ሃላባ ከተማ በ41 ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ሁለቱም ክለቦች ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሲያድጉ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ቡድኖቹ ዓመቱን ሙሉ የተፋለሙበትን የከፍተኛ ሊግ ዋንጫ ለማንሳት ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተያያዘም የካ ክፍለ ከተማ እና ደሴ ከተማ ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ከቀኑ 6 ሰዓት ከ30 በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ወደ ሞሮኮ ያመራል
May 6, 2026 143
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ 16ኛው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ከግንቦት 5 እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ። በአሜሪካዊው ቤንጃሚን ዚመር የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫው ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል። ቡድናችን አቋሙን ለመፈተሽ ከሀዋሳ ከተማ ጋር የልምምድ ጨዋታ አከናውኗል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳት አቶ ኢሳያስ ጅራ እና የሥራአስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በሜዳ በመገኝት ቡድኑን አበረታተዋል። የብሔራዊ ቡድኑ ልዑክ ዛሬ ከለሊቱ 10 ሰዓት ወደ አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ እንደሚያቀና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሕዳር ወር 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ሶስተኛ መውጣቱን ተከትሎ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ሞሮኮ፣ቱኒዚያ እና ግብጽ ጋር ተደልድላለች። በአፍሪካ ዋንጫው ከሚሳተፉ 16 ሀገራት መካከል የተሻለ ውጤት የሚያስመዘግቡ 10 ሀገራት በጥቅምት እና ህዳር ወር 2019 ዓ.ም በኳታር ለሚካሄደው 20ኛው የፊፋ ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ያልፋሉ።
ነገሌ አርሲ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
May 6, 2026 96
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ገብረመስቀል ዱባለ እና ኪቲካ ጅማ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ስምኦን ማሩ የወልዋሎን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ነገሌ አርሲ በ48 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። በሊጉም 12ኛ ድሉን አሳክቷል። በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ35 ነጥብ ከነበረበት 13ኛ ደረጃ ወደ 14ኛ ዝቅ ብሏል። ዛሬ አስቀድመው በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ መድን የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡና 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ባህር ዳር ከተማ ፋሲል ከነማን 2 ለ 0 ረቷል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ የ30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፍጻሜውን አግኝቷል። የ31ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በኢትዮጵያ መድን ተሸነፈ
May 6, 2026 124
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሳሙኤል ሳሊሶ በ83ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥሯል። በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና 55 ነጥብ ላይ ረግቷል። ከተከታዩ መቻል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማስፋት እድል መጠቀም አልቻለም። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም። በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ መድን በ37 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል። የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ መድን ከወራጅ ቀጠና አካባቢ በመጠኑ የራቀበትን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል። በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ፋሲል ከነማን 2 ለ 0 አሸንፏል። ብሩክ ሰሙ እና አማኑኤል ገብረሚካኤል ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ባህር ዳር ከተማ በ40 ነጥብ ከነበረበት 11ኛ ደረጃ ወደ 8ኛ ከፍ ብሏል። በሊጉ ስምንተኛ ድሉን አስመዝግቧል። በሊጉ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በ43 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።
አካባቢ ጥበቃ
በክልሉ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከ68 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ይሸፈናል
May 7, 2026 94
ቦንጋ፤ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከ68 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለመሸፈን ታቅዶ የችግኝ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሀገሪቱ ከፍተኛ የደን ሽፋንና የተፈጥሮ ሀብት ከሚገኝባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው። ክልሉ በየዓመቱ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚያከናውናቸው የችግኝ ተከላ ስራዎች፣ ነባር ደኖችን ከመጠበቅ ባለፈ የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ ለማልማትና የብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። የዘንድሮው የ68 ሺህ ሄክታር መሬት ሽፋን ዕቅድም ይህንን ክልላዊና ሀገራዊ የአየር ንብረት ለውጥ የመቋቋም ስትራቴጂ አካል ያደረገ ነው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው እንደገለጹት፤ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ለዚህም ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች የማዘጋጀትና በቴክኖሎጂ የታገዘ የተከላ ቦታ ልየታና መረጃ የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከ68 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በደንና በሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው ችግኞች ለመሸፈን የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግና የስራ እድል በመፍጠር የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያሳደገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የካፋ ዞን ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት መምሪያ ምክትል ሀላፊና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታሪኩ ወልደ ሚካኤል በበኩላቸው፣ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ዝግጅት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል። በዞኑ የፍራፍሬ፣ የሻይ፣ የቡናና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። ለዚህም በ539 የችግኝ ጣቢያዎች ዘር የማፍሰስና የችግኝ እንክብካቤ ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል። የተዘጋጁ ችግኞችም በ36 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የሚተከሉ ሲሆን ቦታ የመለየት እና መረጃ የማደራጀት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። አርሶ አደሮችም፣ ከዚህ ቀደም የተተከሉ ችግኞች ፀድቀው ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን ገልፀው፣ የመርሃግብሩ መጀመር ደንን በአግባቡ ለመጠበቅ ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሃግብር የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች ለመትከል መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል። የሚተከሉ ችግኞች ፀድቀው አገልግሎት እንዲሰጡ መንከባከብ አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት አርሶአደሮቹ ፣ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተጀመረ ወዲህ በርካታ ጥቅም እያገኙ እንደሆነም ገልፀዋል።
በጉጂ ዞን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ ነው
May 6, 2026 119
አዶላ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ በጉጂ ዞን ድርቅና የአካባቢ መራቆትን ለመቋቋም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ መጀመሩን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ ፡፡ በጽህፈት ቤቱ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ ወንዶ ሸርቦቴ እንዳሉት፤ በዞኑ ድርቅና የአካባቢ መራቆትን በዘላቂነት ለመቋቋም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ ተጀምሯል፡፡ በዞኑ ለደን፣ ለጥላ ዛፍ፣ ለፍራፍሬ ልማት፣ ለውበትና ለእንስሳት መኖ የሚውሉ ከ98 ሚሊዮን 800 ሺህ በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ ከተዘጋጁት ችግኞች ውስጥ እስካሁን 27 ነጥብ 8 ሚሊዮኑ የበልጉን ዝናብ በመጠቀም በ6 ሺህ 726 ሄክታር መሬት ላይ መተከላቸውን ገልጸዋል። በዞኑ እየተተከሉ ያሉት ችግኞች ድርቅና የአካባቢ መራቆትን ከመቋቋም አልፎ በፍራፍሬ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያግዙ ናቸው ብለዋል፡፡ ቀደም ብለው የተተከሉ ችግኞች የእንስሳት መኖና የከርሰና ገጸ ምድር ውሀ አቅርቦትን በማሻሻል የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውን ጠቅሰዋል። በዞኑ አዶላ ወረዳ የዳማ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ሙሉጌታ አሰፋ በበኩላቸው፤ በአካባቢያቸው የሚስተዋለውን የአካባቢ መራቆትና ድርቅ ለመከላከል በሚከናወኑ ተግባራት በንቃት መሳተፋቸውን አስታውሰዋል። ቀደም ብለው የለሙ አካባቢዎችን ከሰውና እንስሳት ንክኪ በመከለል ለመኖ አቅርቦትና ለንብ ማነብ ስራ ላይ በማዋል ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በዘንድሮ የበጋ ወራትም የማሳና የተራራ ላይ እርከን ስራ ላይ ከመሳተፍ ባለፈ በክረምቱ ወቅት የሚተከሉ ችግኞች ማፍላታቸውን ጠቁመዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የምድር መራቆትና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል በኩል ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው
May 6, 2026 191
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የምድር መራቆትና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል በኩል ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን የኢትዮጵያ ደን ልማት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የቴክኒክ ኮሚቴ ገለጸ። ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ያካሄደችው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር፣ በአካባቢ ጥበቃ በኩል ዓለምአቀፍ ትኩረትን የሳበ ለውጥ ማስመዝገብ ችላለች። እስካሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ልዩ ልዩ የችግኝ ዓይነቶችን በመትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ቀጥላለች። ይህም የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ ተጨባጭ ውጤት ያመጣ ሲሆን፤ የአፈር መሸርሸርን በመከላከል እና የውኃ ሀብትን በመጠበቅ ለግብርናው ዘርፍ ዕድገት ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል። መርኃ ግብሩ የፍራፍሬ ተከላን በማካተቱ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና ለዜጎች ሥርዓተ ምግብ መሻሻል የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተም ይገኛል። የኢትዮጵያ ደን ልማት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የምድር መራቆትና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል በኩል ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ምርትና ምርታማነትን በተጨባጭ እንዲጨምር ማድረጉን ጠቅሰው ቀደም ሲል በዓመት በሄክታር ይታጠብ የነበረን 130 ቶን አፈር፣ አሁን ወደ 54 ቶን ዝቅ ማለቱንም ገልጸዋል። በተለይም በበጋ ወቅት በሚከናወኑ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች የአፈር መሸርሸርን መከላከልና የውኃ ሀብቶችን መጠበቅ ተችሏል ነው ያሉት። በጥናት እንደተረጋገጠው የምርት እና ምርታማነት ማደጉን፣ የደን ሽፋን መጨመሩንና የአፈር መሸርሸር መቀነሱን የገለጹት አስተባባሪው፤ አረንጓዴ አካባቢዎችን በማስፋፋት ለኑሮ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ተናግረዋል። ቀደም ሲል ኢትዮጵያ በዓለም የምግብ ድርጅት እጅግ ውስን ፍራፍሬ ከሚያመርቱ ሀገራት መካከል ትመደብ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ግን ለምግብነትና ለአካባቢ ጥበቃ የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የችግኝ ጣቢያዎችን በማብዛትና ክትትልን በማጠናከር በመርኃ ግብሩ የሚተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች መጠንና ጥራት ላይ ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል። በተለይም በ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ዝግጅት በልዩ ትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝም ተናግረዋል። አምና 600 ሚየዮን የሚሆኑ የፍራፍሬ ችግኞች መተከላቸውን አውስተው ዘንድሮ ከዚህ በላይ እንደሚሆን አመልክተዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ፋይዳዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበቱ መምጣታቸውን ጠቁመው፤ የፍራፍሬ ምርቶችን ለውጭ ገበያ፣ ለአምራች ኢንዱስትሪዎችና ለገበያ ማዕከላት ማቅረብ የጀመሩ አርሶ አደሮች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል። እነዚህን መልካም ተሞክሮዎች ይበልጥ ለማስፋት የክትትልና ድጋፍ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል። በተጨማሪም የፍራፍሬ ምርቶች ማኅበረሰቡ አማራጭ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኝ በማድረግ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ጉልህ ሚና እያበረከቱ እንደሚገኙም አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የሚቲዎሮሎጂ ዘርፍን ለማዘምን ያከናወነቻቸው ተግባራት አርዓያ የሚሆኑ ናቸው
May 6, 2026 177
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የሚቲዎሮሎጂ ዘርፍን ለማዘመን ያከናወነቻቸው ውጤታማ ስራዎች የአፍሪካን አቅም የሚያሳድጉ መሆናቸውን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከአፍሪካ ሜቲዎሮሎጂ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር የመጀመሪያውን ሳይንቲፊክ ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ አካሂዷል። በኮንፍረንሱ የተሳተፉ ባለሙያዎች እንደገለጹት፤ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ በሚቲዎሮሎጂ እንዲሁም በሃይድሮሎጂ ምልከታዎች ዙሪያ በጋራ መሥራታቸው ወሳኝ ነው። ይህም የተፈጥሮ አደጋዎች ሳይከሰቱ አስቀድሞ ጥንቃቄ ማድረግ የሚያስችሉ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስልቶችን ለማጎልበት እንደሚረዳ አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በዘርፉ ላከናወነቻቸው የቴክኖሎጂና የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች አድናቆታቸውን ገልጸው፤ እነዚህ ኢንቨስትመንቶች ከኢትዮጵያ አልፈው ለአህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስርና የመቋቋም አቅምን ለመገንባት ትልቅ ድርሻ አላቸው ብለዋል፡፡ በተለይም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ፣ የታዳሽ ኃይልን ከማስፋፋት እና በሌሎች የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም በሚያስችሉ ተግባራት ዙሪያ ያሳየችው ውጤት የመንግስትን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚምባቡዌ የመጡት ፍሪዶ ሙካንጋ በሰጡት አስተያየት፤ በኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ዘርፍን ለማዘመንና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት እጅግ የሚያስደንቁና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተነሳሽነትን የሚፈጥሩ ናቸው፡፡ ኢንስቲትዩቱ በመረጃ አያያዝና በከፍተኛ አቅም በሚሰሩ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂዎች ላይ ያደረገው ኢንቨስትመንት መንግሥት ለዜጎቹ ሕይወት መታደግ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሥነ-ምሕዳርን ከመጠበቅ ባለፈ ለምግብነት የሚውሉ ተክሎች ላይ ትኩረት ማድረጉ፣ ለዜጎች የገቢ ምንጭ እንዲሆንና ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ማስቻሉን ገልጸዋል። በሃይድሮሎጂ ዘርፍ የሚደረጉ ምልከታዎችና ጥናቶችም ለኃይል ማመንጫ፣ ለመስኖ ልማትና ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገት የጀርባ አጥንት ለሆኑ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ መሆኑን መረዳታቸው ጠቅሰዋል፡፡ የታንዛንያው ተወካይ ዶክተር ፍሬድበሪት ኦዱንጋ በበኩላቸው፤ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን የመቋቋም አቅሟን ለማጎልበት ሀገራት በጋራ መሥራት፣ ግብዓቶችን መጋራት እና የተቀናጁ ስልቶችን መቅረጽ እንዳለባቸው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በውኃ አስተዳደር እና በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦች ግንባታ ላይ ያከናወነቻቸው ተግባራት ለአህጉራዊ የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት ዘርፍ እያከናወነች ያለችው ሰፊ ጥረት ለመላው አፍሪካ የመቋቋም አቅም መጎልበት ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ኬንያዊቷ ማሪያ ሎኪ ቻሬም በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በበለጠ ፍጥነትና ውጤታማነት ለመፍታት የአፍሪካ ሀገራት በጋራ መስራት እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ተሞክሮ ለሌሎች ሀገራት እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከኢትዮጵያ ልምድ በመነሳት የአፍሪካ ሀገራት ለአህጉሪቱ ስኬት መሥራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካት የአፍሪካ ሕብረትና አባል ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫ አሰናስሎ መምራት ይገባል
Apr 28, 2026 844
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካት የአፍሪካ ሕብረትና አባል ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫ አሰናስሎ መምራት እንደሚገባ የሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃጸም ይገመግማል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳ 2030 እና 2063 ጎን ለጎን የሚሄዱ ሳይሆን እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው። የአፍሪካ ሕብረት የሁለተኛውን የአሥር ዓመት የአጀንዳ 2063 የትግበራ ዕቅድን ሀገር በቀል በማድረግ አካታች ዕድገትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ሽግግርን የሚያፋጥን መሠረታዊ እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል። የሕብረቱ አባል ሀገራትም ብሔራዊ የልማት ዕቅዶችን ከአጀንዳው ጋር በማጣጣም የበጀት ድልድልና የፖሊሲ እርምጃዎችን ለአፍሪካ የትኩረት መስኮች ቅድሚያ እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካ አጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦች የበለጸገች አህጉርን እውን ለማድረግም የአባል ሀገራት ቅንጅትና ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። የአጀንዳ 2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን በማሳካት የተሳለጠ የለውጥ ሽግግርን ለመፍጠርም ጠንካራና የተሰናሰለ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ የፖሊሲ ፍሰት ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም የመንግሥታት፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች በወሳኝ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የሚኖራቸውን ትብብርና ቅንጅት የሚያበረታታ ምኅዳር መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የዑጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትርና ተሰናባቿ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ ቢሮ ሊቀ-መንበር ሮቢናህ ናባንጃ በበኩላቸው፤ የአፍሪካውያን ድምፅ በወሳኝ የዓለም መድረኮች ላይ መንፀባረቅ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ አፍሪካውያን በዓለም አቀፍ መድረኮች በከፍተኛ ደረጃ ከሚደረግ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ባለፈ በወሳኝ ስትራቴጂክ ሂደቶች ላይ በንቃት መሳተፍ ይገባቸዋል ብለዋል። የአፍሪካ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካትም ሎጂስቲክስ፣ ትራንስፖርትና መሰል የትኩረት ዘርፎች ላይ በስፋት በመሰማራት ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች ነው
Apr 28, 2026 459
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃፀም ይገመግማል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳ 2030 እና 2063 በትይዩ የሚሄዱ ሳይሆን እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው። በአፍሪካ አካታች ዕድገትና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ሽግግር ለመፍጠር ወሳኝ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት የሁለተኛውን የአሥር ዓመት የአጀንዳ 2063 የትግበራ ዕቅድ ሀገር በቀል እንዲሆን መሠረታዊ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል። የሕብረቱ አባል ሀገራት ብሔራዊ የልማት ዕቅዶቻቸው ከአጀንዳው ጋር እየተጣጣመ መምጣቱን በማንሳት፤ የበጀት ድልድልና ፖሊሲዎቻቸው ለአፍሪካ የትኩረት መስኮች ቅድሚያ የሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን በማሳካት የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ በሀገራት መካከል ያለው ቅንጅትና ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም አስገንዝበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
አፍሪካውያን የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የማዕድን ሀብታቸውን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ አለባቸው
Apr 27, 2026 481
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018 (ኢዜአ)፦ አፍሪካውያን የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የማዕድን ሀብታቸው ላይ እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከታንዛኒያ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የአፍሪካ ወሳኝ ማዕድናትን ለአረንጓዴ የኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ማዋል" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጁት የ12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ቅድመ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ ክላቨር ጋቴቴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ እንደ ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ግራናይት እና ሌሎች የከርሰ ምድር ሀብቶችን ጨምሮ የዓለምን 30 በመቶ ማዕድናትን ይዛለች፡፡ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብቻዋን የዓለምን ከፍተኛ የኮባልት ማዕድን የያዘች መሆኑን ገልጸው፤ ይሄውም አፍሪካን የዓለም አቀፍ የኃይል ሽግግር /Energy Transition/ ማዕከል ያደርጋታል ብለዋል፡፡ አፍሪካ ዩራኒዬምና ሌሎች የከርሰ ምድር የከበሩ ማዕድናት ባለቤት መሆኗን በመጥቀስ፤ ለዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል አቅርቦት አስተዋጽኦ ከማድረግ ባለፈ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ወደ ኒውክሌር ኃይል ልማት እያመሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ የከበሩ ማዕድናት ባለቤት ብትሆንም አብዛኛው በጥሬ እቃ መልክ ወደ ውጭ የሚላክ በመሆኑ የአህጉሪቱ የእርስ በእርስ ግብይት ከሁለት በመቶ እንዳማይዘል ተናግረዋል፡፡ በአህጉሪቱ የማዕድናት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን መገንባት ቢቻል በየዓመቱ ከ24 ቢሊየን ዶላር በላይ ተጨማሪ ገቢ ማግኘትና ለ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ይቻላል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ የማዕድን ፖሊሲ ለእሴት መጨመር፣ ኢንዱስትሪ ልማትና ሁሉን አቀፍ ልማት ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በአህጉሪቱ የተቀናጀ ቀጣናዊ ኢንዱስትሪ ለመገንባት ያለውን ፍላጎት በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ አህጉራዊ የማዕድን ሀብቶችን ወደ ዘላቂ ብልጽግና መለወጥ ይገባል ብለዋል፡፡ በዚህም የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቀጣናዊ እሴት ሰንሰለትን በማጠናከር የማዕድን ጸጋዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል በሚደረገው ጥረት ትብብሩን ማጠናከሩን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካዳሪ ሲንጎ በአፍሪካ ሁሉን አቀፍና አካታች ዕድገት ለማስመዝገብ የማዕድን ሀብቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አፍሪካውያን በተፈጥሮ ሀብታችን ላይ የሚኖረን ትብብርና ተሳትፎ ስትራቴጂያዊና መዳረሻ ግብ ያለው መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥና የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮት ሽግግርን ለመፈጠር በአቅም ግንባታ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ተምሳሌት ነበሩ
Apr 7, 2026 868
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ እሴት በተግባር ያሳዩ ታላቅ ዲፕሎማት ነበሩ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ስመጥር በሆኑት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደሯን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ፈር ቀዳጅ፣ ታላቅ ዲፕሎማት እና ህይወታቸውን ለሀገራቸውና ለአህጉሪቱ እድገት የሰጡ ጽኑ አፍሪካዊት ሲሉ አወድሰዋቸዋል። አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ለበርካታ አስርተ አመታት የዘለቀ አርአያነት ያለው ሙያዊ ስኬት ማስመዝገባቸውንና ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ሴት አምባሳደሮች አንዷ በመሆንም ለአፍሪካውያን ሴት ዲፕሎማቶች የብርሃን ፋና መሆናቸውን አመልክተዋል። የአፍሪካን ጥቅም ለማስከበርና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የነበራቸው የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለአህጉራዊ የጋራ ግቦች መሳካት የጎላ ሚና እንደነበረውም አውስተዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ቆንጂት በታማኝነት፣ በልዩ ብቃት እና ለጋራ የወደፊት እጣ ፈንታ የነበራቸው ጽኑ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ያላቸውን ጽኑ አቋም ያሳየ መሆኑንም ነው ያነሱት። የአምባሳደሯ የዲፕሎማሲ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ ዲፕሎማቶች፣በተለይም ለሴቶች፣በድፍረትና በዓላማ እንዲያገለግሉ ዘላቂ መነሳሳት ሆኖ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ስም ለአምባሳደር ቆንጂት ቤተሰቦች፣ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ፣ እንዲሁም ለሁሉም አፍሪካውያን ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ሐተታዎች
የአፍሪካዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣረ ዎዴ ማያ - በአዲስ አበባ
May 6, 2026 131
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ጉባኤ በአዲስ አበባ፣ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ይህ ጉባኤ ከሚያዚያ 29 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ አህጉራዊ መድረክ ነው። የአህጉሪቷ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎች እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት ይህ መድረክ፤ የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ አልሟል። ታዋቂው የአፍሪካዊ ዲጂታል ታሪክ ተራኪ ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) ጨምሮ የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) በዲጂታል መገናኛ ብዙኅን የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክትና ገፅታ ለዓለም የሚያስተዋውቅ ዓለም አቀፍ አንቱታን ያተረፈ የአህጉሪቷ የዘርፉ ፈርጥ ነው። ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያለው ጋናዊው ታዋቂ ዩቲዩበርና የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) አዲስ አበባ ገብቷል። በጉባኤው ላይ የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) መገኘትም የአፍሪካን የዲጂታል ገፅታ መቀየር የሚያስችል የአህጉራዊ ይዘት ፈጠራ ትብብርን ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ይጠበቃል። የአየር በረራ መሐንዲስ ስልጡኑ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የዲጂታል ታሪክ ተራኪነት ጉዞ በሀገረ ቻይና ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት ነበር የዩቱዩብ ይዘት ፈጠራን መሞከር የጀመረው። የመጀመሪያዎቹ የዲጂታል ይዘት ፈጠራ ሥራዎቹም አስቂኝ የነበሩ ቢሆንም ወላጅ አባቱ የአፍሪካን በጎ ገፅታ ለዓለም ማስተዋወቅ እንዳለበት የሰጡትን ምክር ተከትሎ ጉዞውን ቀይሯል። ባህላዊ ግንኙነትን ለማጠናከር የቻይንኛ ቋንቋ ቪዲዮዎችን ያዘጋጅ የነበረው ዎዴ ማያ፤ ወደ ጋና ተመልሶ በሰራቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራዎቹ የሚፈለገውን ያህል ዕውቅና አላስገኙለትም ነበር። መነሻውን በአዲስ አበባ በማድረግ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉዞ በማድረግ አህጉሪቷን ለማስተዋወቅ ከሰራቸው ይዘቶች ውስጥ በሩዋንዳ የሰራው ቪዲዮ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ዕውቅናው እንዲናኝ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በእርሱ አተራረክ ማዕከላዊ ስፍራ እንዳላት የሚናገረው ዎዴ ማያ፤ የአፍሪካን ያልተነገሩ ስኬቶችና የአፍሪካዊያን ፅናት በተከታታይ ለዓለም ማስተዋወቁን ተያይዞታል። አሁን ላይ የአፍሪካን ለውጥ፣ ተስፋና ዕድሎች ለዓለም ማህበረሰብ የሚያስተዋውቁ ዘጋቢ ፊልሞችን በመስራት የአህጉሪቷን ስሁት ትርክት በመቀየር ረገድ ጉልህ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሰዎች አንዱ ሆኗል። በሚሊዮን የሚቆጠር ዕይታ ያላቸውን ዘጋቢ ፊልሞቹና የጉዞ ታሪኮችም ጊዜ ያለፈባቸው ስሁት ትርክቶችን በመሞገት የአፍሪካን ተስፋና ዕድሎች ለዓለም በመግለጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኢትዮጵያን ዕድገትና ተስፋ ደጋግሞ የተረከው ዎዴ ማያ፤ በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) ወደ አዲስ አበባ መምጣቱም መድረኩን ተምሳሌታዊና ስልታዊ ያደርገዋል። ይህም የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የግል ጉዞ ከመሆኑም በላይ፤ ኢትዮጵያ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረክ ፈጠራና የታሪክ አተራረክ ለውጦች ማዕከላዊ ሚና በተግባር ያስመሰክራል። በዚህ ጉባኤ፤ እንደ ዎዴ ማያ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መሰባሰብ የአፍሪካን የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር በማጠናከር ይዘት ፈጣሪዎች የአህጉራቸውን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ጉልህ ፋይዳ አለው። ለኢትዮጵያም የዎዴ ማያ መገኘት ሀገሪቱ ለአፍሪካ ዲጂታልና ባህላዊ ሕዳሴ ያላትን ቁርጠኝነት የበለጠ በማሳደግ አዲስ አበባን የአፍሪካ የዲጂታል ገፅታ ግንባታ ሃሳቦች መነሻነት በተግባር ያረጋግጣል።
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች
May 3, 2026 346
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች በሙሴ መለሰ በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው የቴክኖሎጂ ለውጥ ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ምህዳር እያሸጋገራት ይገኛል።የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የመሰረተ ልማት እና የተቋማት ግንባታ ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ የሚጠቀሱ ዋንኛ ስራዎች ናቸው። ለውጡን ተከትሎ መንግስት "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን ስትራቴጂ በመቅረጽ የዲጂታላይዜሽን ስራውን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምሰሶ አድርጎታል። የለውጡ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ ቴክኖሎጂን እንደ አንድ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመቁጠር "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን አጠቃላይ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ተግባር ገባ።ይህ ስትራቴጂ የሀገሪቱን የዲጂታል ጉዞ ከመሰረቱ የለወጠ ሲሆን፣የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃም የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ነበር። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉ የሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ መግባትና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን የማዘመን ስራ የኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል።በተለይም የአምስተኛ ትውልድ (5G) ቴክኖሎጂ አገልግሎት መጀመር ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን አስችሏታል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ለውጡ የፋይናንስ ዘርፉ ላይ ውጤት አምጥቷል።እንደ ቴሌብር (telebirr) ያሉ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ ምንም የባንክ ሂሳብ በስልካቸው ብቻ ግብይት እንዲፈጽሙ በማድረግ፣ ሀገሪቱ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር ትልቅ መደላድል ፈጥረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ረገድ የተመዘገቡት ስኬቶችም የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ አድማስ ይበልጥ አስፍተውታል። የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ራዕይ ለዓለም ያሳየችበት አጋጣሚ ነው።ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት በጤናው ዘርፍ የካንሰር ህመምንና የሳምባ በሽታዎችን ቀድሞ መለየት የሚያስችሉ የኤአይ ውጤቶችን አበልጽጓል። በግብርናውም ረገድ የአፈርን ለምነትና የሰብል በሽታን በቴክኖሎጂ የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ይህም በምግብ ዋስትና ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ሌላው ትልቅ ስኬት የሀገር በቀል ቋንቋዎችን በዲጂታል ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተሰሩ የቋንቋ ፕሮሰሲንግ (NLP) ስራዎች ናቸው። ይህም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ውስጥ እንዲካተቱና ለተጠቃሚው ምቹ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የፋይዳ (Fayda) ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን መረጃ በአንድ ማዕከል በመሰብሰብ፣ ለባንክ፣ ለጤናና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች አስተማማኝ መሠረት ጥሏል። በአሁኑ ወቅት ዜጎች እንደ ፓስፖርት ማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ግብር መክፈል ያሉ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ማከናወን መቻላቸው የለውጡ ፍሬያማነት ማሳያ ነው።የሳይንስ ሙዚየምም የወጣቶችን የፈጠራ አቅም የሚያሳይና የሀገሪቱን ቴክኖሎጂ የሚደግፍ ትልቅ አቅም ሆኗል።የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቅርቡ መጠናቀቁ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2025 ስትራቴጂው መጠናቀቁን ተከትሎ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል።ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዲጂታል 2030ን ይፋ ሲያደርጉ የነበረው ትልቁ መልዕክት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዓለም ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊና መሪ ትሆናለች የሚል ነው። ስትራቴጂው በዋናነት"የፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያን ከሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት፣ ለዜጎች ቀልጣፋ አሰራርን መፍጠር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ስራ እድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት እና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) አድርጎ መገንባትን እንደ ዋነኛ ግብ አስቀምጧል። ይህም ሁሉን አቀፍ የኢንተርኔት ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ የመንግስት አገልግሎቶችን መቶ በመቶ ወረቀት አልባ በማድረግ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) በግብርና፣ በጤናና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በስፋት በመተግበር የምርታማነት አብዮት መፍጠርን ያለመ ነው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ስራ በአህጉራዊ ደረጃ ያለውን ተቀባይነትና የተሰጣትን ትልቅ ኃላፊነት የሚያሳይ ነው።ኢትዮጵያ አሁን ላይ የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ከፍታ፣ ሀገሪቱን በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ምንጭ እንድትሆንም እያደረጋት ይገኛል። በዚህ ረገድም የቀጣዩ ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬትም ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባና በቴክኖሎጂ የበለጸገች ሀገር የማድረግ ራዕይን ለማሳካት እና ለሀገራዊ ብልጽግና እንደ ቁልፍ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 3, 2026 220
ክልሎች፤ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች በወፍ በረር ሲቃኙ ይህንን ይመስላሉ!!! 👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል። እነዚህ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርባል። ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ፣ የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። 👉እንቁላልን ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት የማቆየት ልምምድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ፤ የዶሮ እንቁላል ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት ያህል ማቆየት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ወደ ተግባር ለማስገባት ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል። በዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ሕክምናና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ማስተዋል ብርሃን፤ ዩኒቨርሲቲው የእንቁላል ምርት ብክነትና ብልሽትን ለማስቀረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። በዚህም እንቁላልን እስከ ሁለት ዓመት ያለ ምንም ብልሽት ማቆየት የሚያስችለውን ቴክኖሎጂን የማላመድና የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ቴክኖሎጂው በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ 30 ግራም የኖራ አፈር ወይም ላይም ስቶን ጨምሮ በማዋሃድ እስከ 12 እንቁላሎችን ሳይበላሽ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ለአርሶ አደሩ ተመራጭ ነው ያሉት። ይህም እስካሁን ባለው አንድ ትኩስ እንቁላል ሳይበላሽ መቆየት የሚችለው እስከ ሁለት ሳምንት መሆኑን ጠቁመው ቴክኖሎጂው ይሄን ችግር በመሰረታዊነት የሚቀይር ነው።፡ ቴክኖሎጂውን በስፋት በማስተዋወቅና በማላመድ ረገድም ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን በመስጠት ችግር ፈቺነቱን የማሳየት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። 👉የአፋር ጥጥ ተስፋ ሰጪ ፀጋ! የአፋር ክልል የበርካታ የተፈጥሮ ፀጋዎች ባለቤት ነው፤ ሆኖም እነዚህን እምቅ ሀብቶች ወደ ልማት በመቀየር ከፀጋዎቹ ተቋዳሽ ለመሆን ሳይቻል ለረጅም ተቆይቷል። አሁን ግን ከፀጋዎቹ አንዱ የሆነውን ተፈጥሯዊ ጥጥ (Organic Cotton) ለማምረት ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በሰመራ በተካሄደ የውይይት መድረክም በግብርና ሚኒስቴር የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳምሶን አሰፋ፤ የአፋር ክልል ጥጥን በመስኖ ማልማት የሚቻልበት አቅም ያለው በመሆኑ ልማቱን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሀገራችን የጥጥ ልማትን ለማስፋፋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው፤ ባለፈው የምርት ዘመን እንደ ሀገር በስድስት ክልሎች 110 ሺህ ሄክታር መሬት በጥጥ መልማቱን ተናግረዋል።በዚህም 79 ሺህ ሜትሮክ ቶን የተዳመጠ ጥጥ በማምረት ለኢንደስትሪዎች ማቅረብ እንደተቻለ ነው የገለፁት። 👉የሸማቹ ሸክም ይቀላል! የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን “ወደ ቀበሌ መድረስ” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ስድስት ከተሞች ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም የንቅናቄ መድረክ ሲያካሄድ የህብረት ስራ ማህበራት ከእንግዲህ የሸማቹን ሸክም ሊያቀሉ ይገባል የሚል ሀሳብ ተነስቷል። በሀዋሳው በተካሔደው የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት በተለያዩ መስኮች የበለጸገችና ህብረ ብሔራዊት ሀገር ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን አንስተዋል። በተከናወኑ ተግባራትም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን አክለዋል። የመንግስትን፣ የግሉ ዘርፍንና የዜጎችን የካፒታል አቅምና ዕውቀትን ደምረው የያዙት የህብረት ስራ ማህበራት ግብርናውን በማሻገር የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት በመቀየር ረገድ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልፀው የፋይናንስ አቅርቦት ችግርን በመፍታትና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር የሸማቹን ህብረተሰብ ሸክም ያቀላሉ ተብሎ እንደሚታመንም አስረድተዋል። 👉ምርምር ለቀጣናዊ ትስስር በጅማ ዩኒቨርሲቲ "ቀጠናዊ ሰላምና ትብብር ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ባለችበት ቀጣና የሚታዩ ፍላጎቶችን ለማሟላትና ተግዳሮቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሩ ጥናቶች ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተነስቷል። በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጦሽኔ ቀጣናውን በልማት ለማስተሳሰር በሚደረግ ጥረት የትምህርት ተቋማቱ የጥናትና ምርምር ድጋፍ ከፍተኛ ሚና አለው ያሉ ሲሆን ለዚህም ተቋማቱ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያሳድጉ እና ማህበራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚያግዙ የፖሊሲ መነሻ ሀሳቦችን በጥናትና ምርምር እንዲያፈልቁ አሳስበዋል። የሚወጡ ጥናቶች በቀጣናው በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሊሆኑ እንደሚገባ የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን በመተግበር እያከናወነች ያለችው ተግባር በተመክሮነት ቀርቦ አድናቆትን አስገኝቶላታል። 👉ሻይ ቅጠል አሁን አሁን አርሶ አደሩ በተለያዩ ኢንሼቲቮች በሚከናወኑ የግብርና ልማት ትግበራዎች ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ ይገኛል። በርካታ አርሶ አደሮች በሻይ ቅጠል ልማት ኢንሼቲቭ በመሰማራት ገቢን ከማሳደግ ባለፈ ለሌሎችም ሰፊ የስራ ዕድል እየፈጠሩ ይገኛሉ። በጅማ ዞን የሻይ ቅጠል ልማትን ከማስፋፋት ባለፈ የበያ ትስስር የመፍጠርና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለፋብሪካ ለማቅረብ ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል። የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቲጃኒ ተማም፤ በዞኑ የሻይ ቅጠል ልማትን በኢኒሼቲቨን መልክ በመተግበር የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ ለበርካቶች የስራ ዕድል እየተፈጠረ ነው። ዘንድሮም ስራውን ለማስቀጠል በተመረጡ 6 ወረዳዎች በመጪው ክረምት የሚተከሉ 50 ሚሊዮን ችግኞች የተዘጋጁ ሲሆን ህዝብን በማሳተፍም ወደ 2 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬትን ለመሸፈንም ታስቧል። ጥቅሙ የገባቸው አርሶ አደሮችም የሰብል ልማቱን ለጊዜው ተወት በማድረግ በሻይ ቅጠል ልማት ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ይናገራሉ። በዞኑ የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አርሶ አደር ሲራጅ ሼክ ከድር በሻይ ቅጠል ልማት ላይ መሳተፍ ከጀመሩ ወዲህ ገቢያቸው መጨመሩን ተናግረዋል። አርሶ አደር ሱልጣን አባሞጋ በበኩላቸው ተሰማርተውበት ከነበረው የሰብል ልማት ወደ ሻይ ቅጠል ልማት በመሰማራት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል። የአካባቢ ፀጋን ተገንዝቦ ወደ ስራ መግባት ተጠቃሚነትን እንደሚያመጣ ማሳያ ሊሆን ይችላል። 👉ተስፋዎች ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በሆሳዕና ከተማ የተካሄደው የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ደረጃ ሽግግር እውቅና መርሃ ግብር ይጠቀሳል። "የኢንተርፕራይዞች ሽግግር ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሀሳብ የተከናወነው የዕውቅና መድረክ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት ነው የተካሄደው። እሳቸው እንደገለፁት፤ ኢንተርፕራይዞቹ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትና ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ከማምረት በተጨማሪ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠሩ ነው። በክልሉ በገጠርና በከተማ በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፍ ከ25 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ መስኮች መሰማራታቸው የተገለፀ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በጥቃቅንና በአነስተኛ ደረጃ የሚገኙ 4 ሺህ 948 ኢንተርፕራይዞችን የማሸጋገርና 495 ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን የመለየት ስራ መሰራቱም እንዲሁ። ከኢንተርፕራይዝ ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሸጋገሩ አምራቾች እንደተናገሩት ሽግግሩ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመከወን እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል። 👉ትምህርትና አርብቶ አደሩ የወፍ በረር ቅኝታችንን ስንቀጥል ጋምቤላ እንደርሳለን፤ በሳምንቱ በጋምቤላ ከተማ በተካሄደ መድረክም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውም ተመልክቷል። በለውጡ ዓመታት የአርብቶ አደሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገባቸውም እንዲሁ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና የገዘፈ መሆኑም በመድረኩ መገለፁን ቅኝታችን ዳሶታል። 👉ልወቅሽ ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ጠቅለል አድርጎ የዳሰሰው ቅኝታችን ደግሞ በስድስት ከተሞች ለማካሄድ ዕቅድ የተያዘለትና እስካሁን በጅማ፣ በሀዋሳና በደብረ ብርሃን ከተሞች የተካሄደው የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ታላቁ ሩጫ" ከተሞቹን ከማስተዋወቅ የዘለለ ፋይዳውን በመርሃ ግብሩ ላይ በተላለፉ መልዕክቶቹ አሳይቷል። ለአብነት በጅማ የተካሄደው ‘ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ’ የሚለውን የጤና ጉዳይን ያነሳ ነበር። በአዳማ ከተማ የተከናወነው ሁነት ደግሞ በመኪና ውድድር ታጅቦ የተከናወነና የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅን ታላሚ ያደረገ ነበር። ‘’ለሀዋሳ ከፍታ እንሮጣለን’’ በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ሁነትም ከጅማና አዳማው ሁነት የተለየ እሳቤንም ሆነ መልዕክትን አልያዘም። ሁሉም ሁነቶች ከዋነኞቹ አምስት ምጣኔ ሃብታዊ አምዶች መካከል አንዱ የሆነውን ቱሪዝም ልማት በማጠናከር የማህበረሰቡን የዘርፉ ተጠቃሚነት ማላቅን ታሳቢ ማድረጋቸውን መመልከት ተችሏል። ቅኝቶቻችን በወፍ በረር ይህንን ይመስላሉ!! የሳምንት ሰው ይበለን!!!
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
Apr 26, 2026 596
ክልሎች፤ሚያዝያ 18 /2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር የምንቃኝበት ነው። በዚህ ሳምንትም አንኳር የክልሎች ክንውኑን የሚያሳዩ መረጃዎች ቀርበዋል። የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ማህተም! ኢትዮጵያ የበጋ መስኖ ልማት ስራ መደባኛ ስራዋ ካደረገች ወዲህ አያሌ ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛሉ። ባለፉት ዓመታት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በእቅድ እና በቁርጠኝነት በመከናወኑ ከውጪ የሚገባ ስንዴ ቀርቷል፤ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጥረቱም ቀጥሏል። ከተረጂነት ወደ አምራችነት የሚደረገው ሽግግርም ዓመቱን ሙሉ በማልማት እየታጀበ ሲሆን የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሥራ ነው። በዚህ ውስጥ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል። በተያዘው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ወሬርሶ ማሊማ፣ በጂዳ ወረዳ ሲባ ሲርቲ እና ቂምቢቢት ወረዳ ሰገሌና ደርማሙሳ ቀበሌ በኩታ ገጠም የለማ እና በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ የስንዴ ቡቃያ አስቃኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፎቶ ጋር ያያዙት መልዕክትም ''ይህ የበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት በምግብ ራስን የመቻል እና የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ማህተማችን ነው'' ይላል። ብሪክስ -- ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በባህር ዳር ከተማ ''የብሪክስ አሁናዊ አቅሞች እና የኢትዮጵያ የልማት ትብብር ትኩረቶች'' በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ጉባኤ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ በመሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑ ይታወቃል። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር መሐመድራፊዕ አባራያ በመድረኩ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሳትፎዋን በማሳደግ በጥናት ላይ የተመሰረቱ የተደራጁ የመፍትሔ ሀሳቦችን በማቅረብ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅሙ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች። መድረኩም ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ የራሷን ድርሻ ለመወጣት የሚያስችላት የሁለትዮሽ ትብብር ጭምር የተካሄደበት፤ በብሪክስ ማዕቀፋ በተለይም በግብርና እና ስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና መሰል ዘርፎች ልምድ የተሰጠበትም መሆኑ ተመላክቷል። ማረም እና ማነጽ የማረሚያ ተቋማት የሰብዕና እና የክህሎት ግንባታ ማዕከል እንዲሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት መሰጠቱ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነው። የፌዴራልና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባኤ “የማረሚያ ተቋማት ለሀገር ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የማረሚያ ተቋማት የሰብዕና እና የክህሎት ግንባታ ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ እየተሰራ ነው ብለዋል። ከታራሚዎች የሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የመሰረታዊ ፍላጎት አቅርቦት፣ ከማረሚያ ቤት የሪፎርም ሥራዎች እንዲሁም ከማረም የማነጽ ተሃድሶ ልማት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ጉባኤው በልዩ ሁኔታ የመከረበት ነው። ኢትዮጵያ ማምረቷን ቀጥላለች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና የራስን አቅም የመገንባት ታሪካዊ ጉዞ እንደቀጠለ ነው። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል "ድሬ ታምርት ኢትዮጵያ ትበልፅግ" በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ በተዘጋጀ የአምራች ኢንዱስትሪ ኤክሲፖ ላይ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ በተደረገው ድጋፍና ክትትል እመርታዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል። በንቅናቄው የተዘጉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ በማድረግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በጥራትና በስፋት እየተተኩ ነው ብለዋል። ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት፣ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድም መሠረታዊ ውጤቶች ተገኝተዋል ነው ያሉት። ዘንድሮ ብቻ 13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገቡ የውጭ ሀገራት ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በዘርፉ ለመሰማራት መዘጋጀታቸውም ተገልጿል። ውኃ ይበላል፤ ውኃ ይጠጣል በኢትዮጵያ ቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ውኃ የህልውና ጉዳይ ነው። በእርግጥ ለፍጡራን ሁሉ ውኃ ህይወት ቢሆንም በእነዚህ አካባቢዎች ግን ውኃ ይበላል፤ ውኃ ይጠጣል። በሳምነቱም በአፋር ክልል ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የአይሳኢታ አፋምቦ የብዙሃን መንደር እና የአይሳኢታ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተከናወነው ልማት የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በተግባር ከመመለሱ በላይ፣ በየደረጃው ያለውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፤ መንግስት የውሃ ሽፋን አነስተኛ ለሆነባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በፕሮጀክቶች ታግዞ መስራት እንደሚገባ በጽኑ ያምናል፤ በተለይም የለውጡ መንግስት ለቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች በሰራው ስራ የውኃ ተደራሽነት በእጅጉ ማደጉን አንስተዋል። ልምድ ልውውጥ እና ተሞክሮ -ለምክር ቤቶች ሌላው ቅኝታችን በዚህ በተጠናቀቀው ሳምንት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤትና የዞን ምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ መካሄዱን የዳሰሰ ነው። የጋራ የምክክር መድረኩ ዓለማ የልምድ ልውውጥና የልማት ሥራዎችን በመመልከት ተሞክሮ መለዋወጫ ነው።የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፤ መንግስት ሕዝቡ የሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የምክር ቤቶችን አደረጃጀት ማጠናከርና የክልሉ ሕገ መንግስት ያስቀመጣቸውን ኃላፊነቶች መፈጸም ይገባል ብለዋል።የመንግስት የልማት ኢኒሼቲቮች የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችሉ በመሆናቸው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው መተግበር እንዲችሉ ምክር ቤቶች ያለሰለሰ ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተመልክቷል። የጤና ልማት ስራ እስከ አክሞ ማዳን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ በሚደረግ ጥረት የአጋር ድርጅቶች አስተዋጾ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም የተመለከተው በዚህ ሳምንት ነው። ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጋር በመሆን በአርባ ምንጭ ከተማ ያስገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ መሰል የጤና ዘርፍ የልማት ስራዎች መንግስት በዘርፉ የያዘውን ውጥን ከማሳካት አንጻር እገዛቸው ትልቅ መሆኑን አንስተዋል።ማዕከሉ ማህበረሰቡ በቅርበት ሕክምና እንዲያገኝ ከማስቻል ባለፈ ወደ ሌላ አካባቢ ሄዶ ሲታከም ሊያወጣ የሚችለውን ወጪ ያስቀራል። ማዕከሉ የኩላሊት እጥበት ማሽኖች፣ የመድሃኒት ቤት፣ መኝታ አልጋዎችና የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሟልቶ የተገነባ መሆኑም ታውቋል። የከተሞች ኮሪደር- ከቱሪዝም እስክ ኮንፍረንስ ማዕከልነት በኮሪደር ልማት እጅግ ከተዋቡ እና ከደመቁ የኢትዮጵያ ከተሞች መካከል ሀዋሳ አንዷ ናት። በሳምንቱ የከተማዋ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ ማጠናቀቂያ የምስጋናና ዕውቅና እንዲሁም የአራተኛ ዙር የኮሪደር ልማትና የሐይቅ ዳርቻ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄዷል፡፡ የሲዳማ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርቡ ቀጥሏል ብለዋል። በቀጣይ ለሚከናወነው የኮሪደር እና የሐይቅ ዳርቻ ልማት ስራዎች እንደሚቀጥሉ አንስተው የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑን ገልፀዋል። የከተማዋን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከልነት ለማጠናከር ሥራዎች በላቀ ፍጥነትና ጥራት መከናወናቸውን እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። ምርጫ -የዴሞክራሲ መሰረት ሳምንቱ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ከመጠናቀቁ በፊት መራጮች የምርጫ ካርድ ወስደው ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹበትም ነበር። ኢትዮጵያዊያን መጪውን ጊዜ የተሻለ የሚያደርግላቸውን መንግስት ለመመረጥ ዝግጅታቸውን በተግባር እያረጋገጡ ነው።
ትንታኔዎች
የ471 ሚሊዮን ተከታዮች ባለቤት የሆኑ የ30 ሀገራት ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የሚሳተፉበት ታሪካዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ
May 6, 2026 155
በመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) ላይ ለመሳተፍ፣ ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡና በአጠቃላይ 321 ሚሊዮን ተከታዮች ያሏቸው 61 ታዋቂ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። እነዚህንም 150 ሚሊዮን ተከታዮች ያሏቸው 120 ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ የይዘት ፈጣሪዎች ይቀላቀሏቸዋል። ታሪካዊው ጉባኤ ነገ እና ከነገ በስቲያ በአድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ጉባኤው በፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ እና በኤጂኤ ቴክ ኢንተርፕራይዝ የጋራ ትብብር የተዘጋጀም ነው። በአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል አዲስ አበባ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ የአፍሪካን ዲጂታል የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንደገና ለመቅረጽ ያለመ ነው። ጋናዊው ታዋቂ ዩቲዩበር እና የዲጂታል ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅበት ስም ነው) ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል። ሴራሊዮናዊው ቦይዜ ክሪሽ፣ ቤኒናዊቷ ሬጌ ቦይዘር፣ ሴኔጋላዊው ጃው ኬቹፕ እና ስዊዛላንዳዊው ጎጎ እስዋቲኒ ኤምኤም ሌሎች ለጉባኤው የገቡ የዲጂታል ሚዲያ ተጽእኖፐ ፈጣሪዎች ናቸው። የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎቹ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል። ጉባኤው በአፍሪካ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የሚሰባሰቡበት፣ ስለራሳቸውና ስለ አፍሪካ የሚናገሩበት፣ እንዲሁም ስለ ይዘት ፈጠራና ስለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች የሚወያዩበት መድረክ ነው። ይህም ተጽእኖ ፈጣሪዎቹን በአንድ መድረክ የማገናኘት ትልቅ አጋጣሚን ፈጥሯል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በመጠቀም የይዘት ፈጣሪነት የወደፊት ሁኔታ፣ የአፍሪካ አዎንታዊ ገጽታን መገንባት እና የዲጂታል ተጽዕኖን ከአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ ጋር ማጣጣም በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሶስት የከፍተኛ ደረጃ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ። ጉባኤው "በችግር ላይ የተመሰረተ" ዘገባን በእውነተኛ የአፍሪካ የዕድገት ታሪኮች ለመተካት የታለመ ስትራቴጂካዊ እርምጃ መሆኑም ተመልክቷል። የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ የኢትዮጵያን ቱሪዝም በከፍተኛ ሁኔታ የማስተዋወቅ እድሉ ሰፊ ነው። እነዚህ የይዘት ውጤቶች የአፍሪካን መልካም ገጽታ ለዓለም፣ የኢትዮጵያንም መልካም ገጽታ ለአፍሪካውያን ማሳየት የሚችሉ ናቸው። ጉባኤው ሐሙስ ዕለት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚጀመር ሲሆን፣ ከ470 ሚሊዮን በላይ የዲጂታል ተከታዮች አይኖች በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ላይ አርፈዋል። ይህም አፍሪካ የራሷን ታሪክ ራሷ መተረክ የጀመረችበት አዲስ ዘመን ማሳያ ሆኗል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 2, 2026 550
ከሚያዝያ 18 እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የጎበኙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው ብለዋል። በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ መሆኑን ገልጸው፣ ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድልም ፈጥሯል ነው ያሉት። በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጌጋዋት ዓመታዊ የማምረት ዐቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ ዐቅም ፈጥሯል ሲሉም ተናግረዋል። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን ተመልክቻለው ብለዋል በመልዕክታቸው። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአራዳ ፓርክን መመረቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት አራዳ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለንን ርዕይ በተግባር ያሳየንበት አንዱ ሥራችን ነው ብለዋል። ቀደም ሲል ተዘንግቶና ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው የአራዳ አካባቢ፤ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ አስደናቂ የከተማ አካል መሆን ችሏል ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጤናማ፣ ጽኑ፣ ለመጭው ትውልድ ተስፋን ከተጨባጭ ሀብት ጋር የምትሰጥ፣ በአፍሪካ መሪ፣ በዓለም መድረክ ደግሞ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር እየገነባን እንገኛለን ብለዋል። በየቀኑም ተስፋን ወደ እውነታ የመለወጥ ተግባራችንን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ሐሳባቸውን ያጋሩበት “የማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀውና በማኅበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የማኅበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም፤ ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች መሆኗን ገልጸው፤ ምንም እንኳ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩብንም ለማሻሻል ያልተሞከረ የማኅበራዊ ዘርፍ የለም ሲሉም አስረድተዋል። በየዘርፎች የታለመው ሁሉ በተግባር እንዲተረጎምና ተገቢውን ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ እንደማይችል ሁሉ፤ መንግሥት የሚጀምራቸውን ሥራዎች ሌላው የማኅበረሰብ ክፍል እንደ አንድ ባለ ድርሻ ኃላፊነት ወስዶ በጋራ መቆም እንዳለበት አስገንዝበዋል። • የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በክብር ተቀብለዋቸዋል። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ልማትና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጡ የሚችሉ ተጨባጭ ሥራዎችን ቅድሚያ የሰጠ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑንም አስረድተዋል። ከዚያም ባደረጉት ቆይታ ዘላቂ እና ተጨባጭ ለውጥ ለሚያመጣ አጋርነት መሠረት የጣለ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በስትራቴጂካዊ ዘርፎች ያለንን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩና የአሠራር ማዕቀፍ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የመግባቢያ ሠነዶችን ልውውጥ አካሂደናል ብለዋል። • የበጋ መስኖ እርሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የበጋ መስኖ እርሻ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሠረት የጣልንበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የውኃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እንደሚያሸጋግረን ጥርጥር የለውም ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ የሚገኘውን ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት ጎብኝተዋል። ጉብኝታቸውን ተከትሎም፤ ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ያሳተፈ የግብርና ሥራ እንዲስፋፋ ለሚደረገው ሥራ አንድ ማሳያ ነው ብለዋል። ይህ በግል ባለሀብት እየለማ ያለው የግብርና ሥራ እንደ ሶላር ያሉ የኃይል አማራጮችን እና የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም በመስኖ በማልማት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የግብርና ልማት እና የገጠር ሽግግር ሰፊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲሉም ገልጸዋል። በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግራናይት የሚያመርተውን የኦርላመንት (3ኤም) ማርብልና ቴራዞ ማኑፋክቸሪንግ የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት የግሉ ዘርፍ በማዕድን ልማት ላይ በስፋት እንዲሳተፍ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ፣ ማበረታቻና ድጋፍ እንዲህ ያሉ ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ ነው ብለዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከወርቅ እስከ ግራናይት በተፈጥሮ የታደለ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ፀጋ ለሀገር ብልጽግና ለማዋል የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ የፌደራል መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 25, 2026 647
ከሚያዝያ 11 እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ቀጣናችንን መልክ በሚያሲዙ እና የጋራ መፃኢ የልማት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል። በሁለቱ ሀገሮች በላቀ እድገትና ተጠቃሚነት ዙሪያ መረጃ የተለዋወጥን ሲሆን፤ የኢኮኖሚ ትስስርን በጠንካራ ትብብር እና በኢንቨስትመንት በመደገፍ እድሎችን የምናሰፋባቸውን የቀጣይ ስራዎች የተመለከተ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል ሲሉም ገልፀዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች አንዱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጆሴፍ ሲከላ ጋር መምከራቸው ነው። በዚሁ ወቅትም፤ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ስላለን የረጅም ጊዜ ትብብር መክረናል ብለዋል። በተመሳሳይም ከፕሬዚዳንት ኡመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት ይዘው ከመጡት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማር ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም በሀገሮቻችን መካከል ስላለው ትብብር ተወያይተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። እንዲሁም የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዣን ካሴያ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) በመሆን የተሰጠኝን አዲስ ኃላፊነት በሚመለከት በስፋት ተነጋግረናል ብለዋል። በጤናው ዘርፍ የሚገጥመንን ተለዋዋጭ ተግዳሮቶች ለመወጣት የሰው ሠራሽ አስተውሎትንና የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ዐቅም መጠቀም የጤና ሥርዓታችንን ለማጠናከር፣ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እና ለሕዝባችን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ያላትን ልምድ ለአህጉሩ ለማካፈል እንዲሁም በፍጥነት ከሚለዋወጠው የቴክኖሎጂው ዓለም ጋር ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመራመድ የሚያስችሉ ጠንካራ አጋርነቶችን ለመመሥረት ያላትን ቁርጠኝነት ዳግም ታረጋግጣለች ሲሉም አስታውቀዋል። • በኢትዮጵያ የበቆሎ መስኖ ውጤታማነት ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ትኩረት ሰጥተን እየሠራንባቸው ከሚገኙት ምርቶች አንዱ የሆነው የበቆሎ መስኖ ሥራ፤ ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል ማለታቸው ይታወሳል። የተገኘው ጅምር ውጤትም፤ ኢትዮጵያ የምግብ ዕርዳታ ከመቀበል ወጥታ ራሷን መመገብ የምትችል ሀገር የማድረግ ታላቁ ህልማችን ዕውን የሚሆንበት መንገድ ላይ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል። • መሶብ የሞባይል አገልግሎት መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመሶብ አገልግሎት የታየው ከፍተኛ የደንበኞች እርካታ የስራውን ውጤታማነት ያረጋገጠ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሰራሩን ይበልጥ መስፋፋት አስፈላጊነትም ገልጸዋል።ዜጎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የተቀናጁ አገልግሎቶችን ተደራሽ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ አንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ ዛሬ ሥራ የጀመረው የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። ለአገልግሎት የተደራጀው አውቶቡስ ሙሉ ቁሳቁስ የተሟላለትና ራሱን የቻለ የአገልግሎት ማዕከል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ቀልጣፋና አስተማማኝ አሠራርን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ሥርዓቶችን አቀናጅቶ የያዘ መሆኑን ገልጿል። አውቶቡሱ የአገልግሎት ፍሰቱን የሚያደራጅ የሰልፍ ማስተናገጃ ሥርዓት እንዳለውና የተለያዩ የክፍያ አማራጮች ማካተቱንም አመላክቷል። ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን ኃይል በከፊል ከ8 ኪሎ ዋት የፀሐይ ብርሃን የሚያገኝ ሲሆን፤ አስተማማኝ ኢንተርኔትም ተገጥሞለታል። በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጡን ደኅንነትና ግልፅነትን ለመከታተል ካሜራዎች ተገጥመውለታል፤ መፍትሔ አምጪ ሆኖ የተዘጋጀው የፈጠራ ውጤትና ተንቀሳቃሽ ክፍል፤ ከስምንት የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሚከተሉትን ወሳኝ አገልግሎቶች ይሰጣል፦ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መስጠት፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ማደስ፣ ለመንጃ ፈቃድ የሚያስፈልግ የሕክምና ምርመራ ማድረግ፣ የነዋሪነት መታወቂያ ማደስና የልደት ምዝገባ፣ የመንጃ ፈቃድ መስጠትና የተሽከርካሪ ታርጋ ማደስ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የመንገድ ፈንድ ክፍያን ማከናወን፣ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባና የመረጃ እርማት፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የሚሰጥ የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ይሰጣል። በአጠቃላይ ይህ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል። • የ100 ቀናትና የ9 ወራት የመንግሥት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት የሥራ ዘመኑ 3ኛ የ100 ቀናት የመንግሥት ሥራ አፈፃፀም ከዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም ጎን ለጎን መገምገሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በዚሁ ወቅትም፤ የቀየስነው አዲሱ የኢኮኖሚ አካሄድ በአጭር ጊዜ ትግበራ ጠንካራ ባለሁለት አሃዝ የዕድገት ሂደትን አስመዝግቧል ብለዋል። ጥረቶቻችን የበለጠ ጽኑ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለንን አቋም እና የመተግበር ዐቅም ያሳያሉ ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ስለ 3ኛው 100 ቀን አፈጻጸም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛው የ100 ቀን አፈጻጸም ሪፖርት ከፌደራል ተቋማት አመራሮች ጋር ተገምግሟል። በዚሁ ወቅትም አቶ ተመስገን፤ ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት፤ የሚገባትም ትልቅ ሥፍራ ነው፤ እኛ ደግሞ የዚህ ታሪክ ሠሪዎች የመሆን ዕድል በእጃችን ላይ ነው ሲሉ አዝገንዝበዋል። በኮሪደር ልማት፣ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችና በዲጂታል ኢትዮጵያ ዘርፍ የተካሄደው የመሠረተ-ልማት አብዮት የሀገራችንን እንዲሁም የከተሞቻችንን ገጽታና አገልግሎት ቀይሯል ብለዋል። በስንዴ ልማትና በሌማት ትሩፋት አማካኝነት የተረጅነትን ቀንበር ሰብረን ወደ ምግብ ሉዓላዊነት እየተጓዝን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዲፕሎማሲው መስክም ኢትዮጵያ ከእርዳታ ጠባቂነት ወደ ንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት በመሸጋገር፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ተደማጭነቷን ወደ ላቀ ምዕራፍ አሳድጋለች ብለዋል። • የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች ባሳለፍነው ሳምንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 54ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ፤ በሁለት የፋይናንስ ድጋፍና ብድር ስምምነቶች፣ በሀገራችን የዩሪያ ማዳበሪያ ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካን የሚመለከት የኢንቨስትመንት ማበረታቻና ጥበቃ ስምምነት፣ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ፣ በሥድስት ዓለም አቀፍ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ እሳት እና ሌሎች ቅጽበታዊ አደጋዎች አገልግሎት ማቋቋሚያ ደንብ ላይ መክሮ በማጽደቅ ውሳኔዎችን አሳልፏል። • ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች ብሎ ባጋራው መረጃ፤ በመሠረተ-ልማት (የ5G እና የ4G ሽፋን መስፋፋት)፣ በዲጂታል መሳሪያዎች (ስማርት ስልኮችን በሀገር ውስጥ መገጣጠም)፣ በዲጂታል መንግሥት (በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት መደራጀት፣ ዲጂታል ክፍያዎች፣ የፍትሕ ተደራሽ ስማርት ችሎት እና ዲጂታል ፖሊስ) የሚሉትን አንስቷል። በተጨማሪም በዲጂታል ክኅሎት (5 ሚሊየን ኮደሮች ስልጠና፣ ትምህርት ቤቶችን በኢንተርኔት (SchoolNet)፣ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ደረጃ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምርምር እና ስታርት አፖችን በዕውቀትና በፈጠራ ማብቃት፣ በተቋማት ግንባታ (ዲጂታል ስታቲስቲክስ እና ልማት አስተዳደር፣ AI ኢንስቲትዩት፣ AI ዩኒቨርሲቲ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር)፣ በሕግ ማዕቀፍ ተዓማኒነት (በፋይዳ መታወቂያ ከ40 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጋ ተካቷል፣ የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ተግባራዊነት) የሚሉት ጉዳዮችን ጠቅሷል። • የልማት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ኢንሼቲቮችን በመለየት መተግበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ የሀገሪቱ የደን ሽፋን 23 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን አስታውቋል። ሀገራዊ የስንዴ ልማትን በተመለከተም ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን እና ሉዓላዊነትን እያረጋገጠች ትገኛለች ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ አዳዲስ የግብርና ዕውቀቶች እየተስፋፉ፣ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ግብዓቶችን እያገኙ፣ ውድ የሆኑ የውጭ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የሥራ ዕድሎች እየሰፉና የአርሶ አደሮች ገቢ እየጨመረ ይገኛል ብሏል። ከሌማት ትሩፋት አንጻርም፤ የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት እና ምርታማነት እየጨመረ ነው፤ የተመጣጠነ ምግብ በቀላሉና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኝ ከማድረግ ባለፈ፣ አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡና አካባቢው ይበልጥ እንዲጠበቅ እያደረገ ይገኛል ሲል ገልጿል። ዲጂታል ኢትዮጵያን አስመልክቶም፤ የሕግ፣ የፋይናንስ እና የማንነት መታወቂያ (ID) ሥርዓቶች ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ነው። የኢንተርኔት ተደራሽነትና የኦንላይን አገልግሎቶች እየተስፋፉ፣ የሞባይል ክፍያ ሥርዓት እየተጠናከረ እንዲሁም የኢ-ኮሜርስ ንግድ የዜጎችን ጊዜና ገንዘብ እያተረፈ ነው ብሏል። የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማትም፤ የከተሞች መሠረተ-ልማት በአረንጓዴ ትራንስፖርት እየዘመነ ነው ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ ይህም የዜጎችን የኑሮ ጥራት እያሻሻለ፣ የአካባቢ ንግድን እያነቃቃ እንዲሁም በከተማና በገጠር መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከረ እንደሚገኝ አስታውቋል። ከኢትዮጵያ ታምርት አኳያም፤ የማምረት ዐቅምና የምርቶች እሴት የመጨመር ሂደት እየተሻሻለ ነው ብሏል። ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እያደገ፣ የግብዓት አቅርቦት እየተጠናከረና አዳዲስ የሥራ ዕድሎች እየተፈጠሩ ስለመሆኑም አመላክቷል። እያንዳንዱ ምሰሶ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር፣ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው ሲልም በአጽንዖት ገልጿል።
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል ጤና ከሀገር በቀል ስኬት ወደ አህጉራዊ መሪነት
Apr 23, 2026 596
(በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፍ እያከናወነች ያለችው ስራ ውጤታማ እንዲሆን ስትራቴጂካዊ የሆኑ ተቋማዊና የፖሊሲ መሰረቶች ተጥለዋል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መቋቋም ለሀገራዊ ችግሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ መፍትሄ ለማግኘት ትልቅ አቅም የፈጠረ ሲሆን፣ ብሄራዊ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ተቀርጾ መጽደቁ ደግሞ የዘርፉን ልማትና አጠቃቀም በተደራጀ መንገድ ለመምራት አስችሏል። እነዚህ እርምጃዎች ሀገሪቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እና 2030 ስትራቴጂ ውስጥ ቴክኖሎጂውን እንደ ቁልፍ የለውጥ አቅጣጫ እንድትጠቀም በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ዘላቂ ለማድረግም በሰው ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቷል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በኮዲንግ፣ በዳታ ሳይንስ እና በክህሎት ለማሰልጠን የተጀመረው ግዙፍ ፕሮግራም የለውጡ አንቀሳቃሽ ኃይል እየሆነ ነው። ከዚህም ባለፈ፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የኤአይ ዩኒቨርሲቲ እንዲገነባ መታቀዱና በዚህ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልነት ውስጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት እንዲሳተፍ መወሰኑ፣ ሀገሪቱ ቴክኖሎጂውን ለውሳኔ ጥራትና ለምርምር በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀመችበት መሆኑን ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ እንደገለጸው፣ ሹመቱ የተሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራር እና ኢትዮጵያ በአህጉሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ላለው የላቀ ሚና እውቅና ለመስጠት ነው። በሹመት ደብዳቤው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማስፋፋት ያደረጉት አመራር፣ AI ለአፍሪካ ሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአሳታፊ እድገት ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማስቻል ረገድ ትልቅ እገዛ ማድረጉ ተመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አክሎ እንደገለጸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልታዊ በሆነ መልኩ የቴክኖሎጂ ነጻነትን እና ዐቅምን ለመገንባት የሚያደርጉት ተከታታይ ቅስቀሳ፣ አህጉሩ በኃላፊነት እና በፍትሐዊነት በታጀበ የAI አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዲጂታል መሰረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል እና በፈጠራ ሥነ-ምህዳር ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ለሀገራዊ ለውጡ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ተግባራት መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ በዝርዝር አስፍሯል። በተጨማሪም ራሱን የቻለ የAI ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የተያዘው ሥራ ምርምርን፣ የክህሎት ልማትን እና አህጉራዊ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ተገልጿል። ይህ አህጉራዊ እውቅና በተለይ በጤናው ዘርፍ የታዩ ውጤቶችን ያካትታል። ኢትዮጵያ በኤአይ የታገዘ ዲጂታል ኤክስሬይን ለሳንባ ነቀርሳ ምርመራ ካዋሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። በተጨማሪም የ"HEP Assist" መተግበሪያን በሙከራ ደረጃ በማስጀመር፣ በገጠር የሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ውስብስብ ምልክቶችን ሲያዩ ሙያዊ የሕክምና ውሳኔ እንዲሰጡ ድጋፍ እየተደረገ ነው። እነዚህ የዲጂታል ጤና ስራዎች በ7 ክልሎችና በ15 ወረዳዎች ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸው፣ ቴክኖሎጂው በገጠርና በከተማ መካከል ያለውን የአገልግሎት ልዩነት ለማጥበብ ያለውን ፋይዳ ያሳያል። በአጠቃላይ፣ የኤአይ ቴክኖሎጂ በጤናው ዘርፍ ከሚሰጠው የጡት ካንሰር፣ የአንጎል እብጠትና የቆዳ በሽታዎች ምርመራ ባለፈ፣ በግብርና፣ በፋይናንስና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥም በስፋት እየገባ ይገኛል። በ2030 በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ሆስፒታሎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት ለመቀየር የተቀመጠው ግብ፣ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ነጻነትና የመሪነት ጉዞ ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሥርዓት በጤና፣ በግብርና እና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። በጤናው ዘርፍ እንደ ካንሰር እና ሳንባ ነቀርሳ ያሉ በሽታዎችን ቀድሞ በመለየት የህክምና ጥራትን ሲያሻሽል፣ በግብርናው ደግሞ የሰብል ተባዮችንና የቡና በሽታዎችን በመለየት ምርታማነትን እያሳደገ ነው። ከዚህ ባለፈም ቴክኖሎጂው በመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ እና በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ሰፊ የመረጃ ትንታኔዎችን በፍጥነት በማከናወን፣ የሥራ ፍጥነትን እና የውሳኔ አሰጣጥ ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ ይገኛል። የዘርፉ ፋይዳ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባለፈ የሀገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የሰው ኃይል አቅም በመገንባት ላይ ያተኩራል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በኮዲንግ እና በዳታ ሳይንስ በማሰልጠን እንዲሁም የፈጠራ ማዕከላትን (Startups) በመገንባት፣ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በሌሎች ላይ ጥገኛ ከመሆን ወጥታ የራሷን የዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት እየጣለች ትገኛለች። ይህም በአህጉር ደረጃ ለሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች እንደ አርአያ በመሆን፣ ቴክኖሎጂውን ለኢኮኖሚ እድገትና ለማህበራዊ ፍትሃዊነት የመጠቀም ጥቅል ፋይዳው የጎላ እንዲሆን አድርጎታል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ ያላትን የመሪነት ሚና ይበልጥ ያጎላል። በተጨማሪም ሹመቱ የኢትዮጵያ ተሞክሮ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ማግኘቱንና አፍሪካ በኃላፊነትና በፍትሐዊነት በታጀበ የኤአይ አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንድትሆን የመሪነት ሚናዋን እንድትወጣም ያደርጋታል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 4499
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2999
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8793
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 7276
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 801
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው። በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል። የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል። ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።
ፋሲካ -አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል
Apr 12, 2026 900
በኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ነው። የትንሳኤ በዓል የሚከበረው ከ55 ቀናት የጾም ወቅት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እነዚህን ቀናት ፈጣሪያቸውን በጾምና ጸሎት ከመለመን ባለፈ ከሥጋ፣ ከወተትና መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ታቅበው ነው የሚያሳልፉት። የትንሣኤ በዓል ከመድረሱ በፊት ያለው አንድ ሳምንት "ሰሞነ ሕማማት" በመባል ይታወቃል። የእምነቱ ተከታዮች በሰሞነ ሕማማት ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳለፈውን መከራና ስቃይ በማሰብ በቤተ ክርስቲያን በስግደት፣ በጸሎትና በጾም በተለየ ሁኔታ ያሳልፋሉ። ምእመናን በእለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን ብሎ በቀራኒዮ አደባባይ የከፈለውን መከራ፣ ግርፋትና ስቅላት በማሰብ በስግደት፣ በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ያሳልፋሉ። የትንሳኤ (የፋሲካ) በዓልም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትል ድል አድርጎ መነሳቱን ተከትሎ የሚከበር ነው። ትንሳኤው ይቅርታ፣ ለሰው ለጆች መዳን የተከፈለ ፍቅርና መስዋዕትነት ጎልቶ የሚታይበት ነው። በመሆኑም ፋሲካ ሞትን ድል በመንሳት በትንሳኤ የምስራች የተበሰረበት ታላቅ በዓል ነው ማለት ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በትንሳኤ የለወጠበት ለሰው ልጅም ፍቅርን በቤዛነት ተክቶ ያሳየበት ዕለት ነው። ዕለቱ ትንሳኤ ብርሀን የታየበት በመሆኑ በትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ምሽት ምዕመናን ነጭ ልብስ ለብሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች ያሳልፋሉ። የሌሊቱ ቅዳሴና ስርአተ ፀሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ምዕመናን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ጾም ይፈታሉ። ከቅባት ምግቦች ለሁለት ወራት በመቆጠብ ያሳለፉበት ወቅት በመሆኑም በትንሳኤ ሌሊት ዶሮ በመብላት ጾማቸውን ይፈስካሉ። በበዓሉ ቀንም በነጭ የሀበሻ ልብስ ደምቀው ይታያሉ። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ሥርአቱ ባለፈ የአብሮነት፣ የፍቅርንና የመተሳሰብ እሴት ያለው ነው። ዘመድ አዝማድ በመጠራራትና ከጎረቤት ጋር አብሮ በመብላትና በመጠጣት የሚያሳልፉት ነው። ቤት ያፈራውን በመቋደስ በዓሉን በአብሮነት በደስታ ያሳልፋሉ። የፋሲካ በዓል ማህበራዊ ትስስር የሚገለጥበትና አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል ነው። በተለይ በፋሲካ በዓል ለዶሮ ወጥ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ፋሲካና ዶሮ ወጥ ጥብቅ የሆነ ባህላዊ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ አንዱ የበዓሉ ማድመቂያ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በተጨማሪ የበሬ ቅርጫ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዳቦና ጠላ እንደየ አቅም በማዘጋጀት ይከበራል። በአንዳንዶች ዘንድም ከገብስ ብቻ የሚዘጋጅ "ኬኔቶ" የተሰኘ (ከአልኮል ነፃ የሆነ መጠጥ) በማዘጋጀት በአማራጭነት ይቀርባል።