ቀጥታ፡

ዜጋ-ተኮር ዲፕሎማሲን በማጠናከር የዜጎችን መብትና ክብር ማስጠበቅ

መንግሥት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲው ማዕከል "ዜጋ-ተኮር ዲፕሎማሲ" ነው ፡፡ በማንኛውም የዓለም ጥግ የሚኖር ኢትዮጵያዊና ትውልደ-ኢትዮጵያዊ የሀገር ክብር መገለጫ ነው መንግሥት ዜጎች ለሥራ፣ ለትምህርትም ሆነ ለተለያዩ ጉዳዮች ድንበር አቋርጠው በሚሄዱበት ወቅት መብታቸው፣ ደኅንነታቸውና ሰብዓዊ ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ማድረግ ዋነኛ  ተግባሩ እንደሆነ ይታወቃል

ልዩነቶች ቢኖሩም እንኳ ለብዝሃ-ሀሳብ እውቅና በመስጠት፣ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች በሀገራዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ግንባታ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ የሚሆኑበትን ምቹ ምህዳር መፍጠር ዋነኛው ግብ መሆኑ ነው

መንግሥት ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት የሰውን ልጅ ክብርና ጥቅም ማዕከል ያደረገ አሰራር ተከትሏል ይህም በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅርና ተቆርቋሪነት እንዲጨምር አድርጓል ዜጎች በሄዱበት ዓለም ሁሉ አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲንቀሳቀሱ የሚገጥሟቸውን እንግልቶች በሁለትዮሽ ስምምነቶችና በጠንካራ  ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ለመቅረፍ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች እያመጡ ነው በተለይም ከሳውዲ አረቢያ፣ ኳታር፣ ኩዌት፣ ጆርዳን፣ ባህሬን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ጣሊያንና ሮማኒያ ጋር የተፈረሙ የሁለትዮሽ የሥራ ስምሪት ስምምነቶች ዜጎች በክብር የሚሰሩበትን መንገድ አመቻችተዋል።


 

ተቋማዊ አሰራርን ለማጠናከርም "የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት" ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱና መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሄደው ችግር የገጠማቸውን ዜጎች በክብር የመመለስ ስራ በትኩረት መከናወኑ ይታወቃል በተጨማሪም ዳያስፖራው ያለምንም እንግልት ወደ ሀገሩ እንዲገባና በኢንቨስትመንት እንዲሳተፍ የሚያስችሉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል በሀገራዊ ምክክር ሂደትም ዳያስፖራው አጀንዳ እንዲያቀርብና ድምፁ እንዲሰማ በዓለም ዙሪያ ሰፊ መድረኮች መመቻቸታቸው የመንግሥትን አካታችነት በተግባር አሳይቷል

2017 . ብቻ 503 ሺህ 000 ዜጎች በውጭ ሀገራት ሕጋዊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ከዳያስፖራው የሚላከው ሐዋላ  ወደ 7.17 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከፍ እንዲል በማድረግ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ትልቅ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከሳውዲ አረቢያ፣ የመን፣ ኦማን፣ ሱዳንና ሌሎች ሀገራት 500 ሺህ በላይ ዜጎችን በክብር በመቀበል፣ የሥነ-ልቦና ድጋፍ በመስጠትና ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ የማድረግ ስራ ተከናውኗል ዳያስፖራው በታላቁ የኢትዮጵያ  ህዳሴ ግድብ ግንባታና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በመመከት ረገድ ያሳየው ተሳትፎም የመንግሥት አካታች ፖሊሲ ውጤት እንደሆነ ይታመናል

መንግሥት በቀጣይ ለተጨማሪ 800 ሺህ000 ዜጎች በውጭ ሀገር የሥራ ዕድል መፍጠር፣ ከዳያስፖራው የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ወደ 8 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማድረግና ዳያስፖራው በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በቱሪዝም እና በሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ላይ ያለ ምንም ቢሮክራሲ እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ውጥን ይዟል በተጨማሪም 500 በላይ የሚሆኑ የዳያስፖራ ማህበራትን በማስተባበር የሀገርን ገፅታ የሚገነቡና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስከብሩ ተዋንያን እንዲሆኑ የማድረግ እቅድ ተይዟል።

የዜጋ-ተኮር ዲፕሎማሲ ጉዞውን ይበልጥ ማጠናከር የዳያስፖራውን ተሳትፎ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር  ያግዛል የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶችን እንደ ውበት በመቀበል፣ ሁሉንም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ምክክርና በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ በእኩልነት እንዲሳተፉ እየተደረገ ይገኛል

የመደመር መንግሥት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ  ግብ ኢትዮጵያ የልጆቿን መብትና ክብር በዓለም አቀፍ መድረክ የምታስከብር፣ ራሷን በምግብ የቻለችና ሉዓላዊነቷ የተከበረ ታላቅ ሀገር ማድረግ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም