አዲስ አዳጊዎቹ ጋሞ ጨንቻ እና ሃላባ ከተማ የከፍተኛ ሊግ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ - ኢዜአ አማርኛ
አዲስ አዳጊዎቹ ጋሞ ጨንቻ እና ሃላባ ከተማ የከፍተኛ ሊግ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2018 (ኢዜአ)፦ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደጉት ጋሞ ጨንቻ እና ሃላባ ከተማ የከፍተኛ የሊግ የፍጻሜ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ።
ጨዋታው ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።
ጋሞ ጨንቻ በምድብ ሀ በ41 ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።
በምድብ ለ የተጫወተው ሃላባ ከተማ በ41 ነጥብ አንደኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
ሁለቱም ክለቦች ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሲያድጉ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ቡድኖቹ ዓመቱን ሙሉ የተፋለሙበትን የከፍተኛ ሊግ ዋንጫ ለማንሳት ጠንካራ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተያያዘም የካ ክፍለ ከተማ እና ደሴ ከተማ ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ከቀኑ 6 ሰዓት ከ30 በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።