ቀጥታ፡

ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት የማስቀጠል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል

ጅማ ፤ ሚያዝያ 28/2018 (ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት የማስቀጠል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ነመራ ቡሊ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በዕጩ ተወዳዳሪነት በቀረቡበት በጅማ ዞን ጎማ ሁለት ምርጫ ክልል ብልጽግና ፓርቲ እጩዎችን አስተዋውቋል።


 

በመርሀ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ነመራ ቡሊ፤ ብልጽግና ፓርቲ በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት የማስቀጠል ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በፓርቲው አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ለላቀ ውጤት እንደሚሰራ አመላክተዋል።


 

ፓርቲው የበለፀገች ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።


 

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር በበኩላቸው፤ በዞኑ በለውጡ አመታት ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን አንስተው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም