ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ፤ አዲሲቷ የዘመን ተሻጋሪ ዲጂታል ክህሎት የተስፋ አድማስ!!
Aug 7, 2026 23
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በወፍ በረር “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ ተጠናቋል። በዛሬው ዕለትም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን በይፋ አስጀምረናል። ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል ዕድል መፍጠር፣ እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሠረታዊ ትልሞች ናቸው። እነዚህ ትልሞች እንዲሳኩም በተለይ የሕዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማትን ማስፋት ላይ ትልቅ ሥራ የሚከናወን ሲሆን፣ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ሥራዎች የመደመር መንግሥት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ ናቸው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ዲጅታላይዜሽን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚመራ ብሔራዊ የልማትና ዕድገት ፕሮግራም ነው። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2020 በዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ማዕቀፍ ይፋ የተደረገው ብሔራዊ አጀንዳ በዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂም ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ ተይዟል። ግቡም ሁሉንም ተቋማት በኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ በማስተሳሰር በኢትዮጵያ ፈጣን የዲጅታል ኢኮኖሚ ሽግግር መፍጠር ነው። ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት፣ የኢንተርኔትና የዲጅታል ትስስርን ማስፋፋት፣ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎትን ማላቅ፣ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ የጤና አጠባበቅና የትምህርት ሥርዓትን ማሻሻል፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የዲጅታል ኢኮኖሚ መገንባት፣ በኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም በኢኖቬሽን የሥራ ዕድል መፍጠር እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን መደገፍ የዲጅታላይዜሽን መሠረቶች ናቸው። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የዲጅታል ኢኮኖሚ መሠረት ጥሏል። በመንግሥት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን በዲጅታል ቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል፤ ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋትም ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የሚያስችል መሠረት ጥሏል። የዲጅታል ማንነትን በማስፋፋት ዜጎች አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ማግኘት እንዲችሉ ያስቻለ ሲሆን፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን፣ ቅንጅትንና ተደራሽነትንም አሳድጓል። ቀደም ሲል ዜጎች ዲጅታል ማንነት መጠቀም በማይችሉበት ወቅት በርካታ የወረቀት ሰነዶችን ከማቅረብ ጀምሮ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትን በመዳረስ ረጅም ጊዜና ጉልበት ያጠፉ ነበር። አሁን ግን ሁኔታው ተለውጧል። በወረቀት አልባ ሥርዓት ፈጣንና ፍትሐዊ የመንግሥት አገልግሎት ማግኘት የሚቻልበት የዲጅታል ምህዳር ተፈጥሯል፤ የዜጎች እንግልት ቀንሷል፤ ወረፋና ጥበቃም ተረት ሆኗል። የዲጅታል ክፍያ ሥርዓትም በኢትዮጵያውያን ዘንድ እንደዕለት ተዕለት አጠቃቀም ቀላልና የተለመደ እየሆነ መጥቷል። የቴሌኮም መሠረተ ልማትን የማስፋፋት ሥራም ተጠናክሯል፤ የዲጅታል ክህሎት በተለይም በወጣቶች ዘንድ አዲስ የእውቀትና የተወዳዳሪነት መሣሪያ ሆኗል። ለዲጅታል መሠረተ ልማት መስፋፋት ቁልፍ የሆኑ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፎችም ተፈጥረዋል። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ለኢትዮጵያ የዲጅታል ኢኮኖሚ ሽግግር መሠረት ጥሏል፤ የኢትዮጵያን መጪ ጊዜ በተስፋ መመልከት የሚያስችል አጉሊ መነጽር አቅርቧል። በዲጅታል ክፍያዎች የታገዘ የጥሬ ገንዘብ አልባ ግብይትም የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እያዘመነ ይገኛል። ጥሬ ገንዘብ በእጅ የመያዝ ልማድ መቀነሱ የገንዘብ ማተሚያና ማጓጓዣ ወጪን ቀንሷል፤ የገንዘብ ዝውውርን ግልጽና ፈጣን በማድረግም ሕገወጥ አሠራሮችንና ሙስናን ለመከላከል አስችሏል። ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ከተደረገለት የፋይናንስ ሥርዓት ጋር ሲቀናጅም፣ ሕዝቡ በዲጅታል ክፍያዎች ላይ ያለው መተማመን እንዲጎለብት ያደርጋል፤ የሀገሪቱንም የዲጅታል ሽግግር ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል። ይህም ለዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መሠረት ጥሏል። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030፤ የሽግግሩ ቀጣይ ምዕራፍ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነትን በማጠናከር፣ የኤሌክትሮኒክ የመንግሥት አገልግሎቶችን ፍጥነት፣ ተደራሽነትና ግልጽነት ለማሳደግ ያለመ ነው። ይህም የመንግሥትን ወጪ ለመቀነስና የአገልግሎት ብቃትን ለማሳደግ ዕድል ይፈጥራል። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬትም በኢኮኖሚ፣ በትምህርትና በአገልግሎት ዘርፎች አዎንታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል። የሀገሪቱ የዲጅታል ሽግግር በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ በተመሠረተው የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ የተቃኘ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በስትራቴጂ ማስጀመሪያው ወቅት፦ ስትራቴጂው በከተማም ሆነ በገጠር የዲጅታል ሥርዓትን በማስረጽ የዲጅታል ኢኮኖሚን እውን የምናደርግበት ነው ብለዋል። ቁሳዊ ዕድገት የሚጀምረው የሰው ኃይል አቅምን በመገንባት እንደሆነ ጠቅሰው፣ ወጣቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ የፈጠራ ባለቤቶችና ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ በዲጅታል ክህሎት ማስታጠቅ እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል። የዲጅታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ግቦች ኢትዮጵያ የብሮድባንድና ኢንተርኔት ተደራሽነትን በመላ ሀገሪቱ በመዘርጋት፣ የዜጎችና ተቋማትን የዲጅታል ክህሎት በማሳደግ፣ እንደ ግብርና፣ ቱሪዝም፣ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ስታርትአፖችን በቴክኖሎጂ በማዘመን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትና ንግድን መሳብ፣ እንዲሁም አካታች የዲጅታል ኢኮኖሚ መገንባት ናቸው። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የመንግሥት የዲጅታል አገልግሎት ማስፋፊያ፣ የቴሌኮም ሪፎርም፣ ዲጅታል ክፍያ፣ ብሔራዊ የዲጅታል መታወቂያ/ፋይዳ፣ እንዲሁም በሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ ዲጅታል የሕዝብ መሠረተ ልማት፣ የሳይበር ደህንነትና ብሔራዊ የዲጅታል አካታችነትን መርህ ያደረገውን የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አዋልዷል። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጅታል ሽግግር ስትራቴጂ ነው። ከዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬት የተቀዳ ታላቅ የመሆን ህልም ሥጋ ለብሶ የታየበት ግልጽ ፍኖተ ካርታም ነው። የዲጅታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2030 ቀልጣፋ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ፣ የአስተዳደር ሥርዓትን በማጠናከር አገልግሎትን ማሻሻል፣ በዲጅታል ቴክኖሎጂ የበቃ ማኅበረሰብ በመፍጠር ሀገርን ማበልጸግ፣ ለነገ ዛሬ የሚኖር አደራና ዛሬ የነገ ስንቅ ሆኖ በግልጽ ሰፍሯል። የኢትዮጵያ የዲጅታል ሽግግር ግብ አንድ ነው፤ አካታችና ዘላቂ ዲጅታል ኢኮኖሚ መገንባት፣ በዋጋ ተመጣጣኝና ተደራሽ የኢንተርኔትና የኮሙኒኬሽን አገልግሎትን ማስፋት፣ በዲጅታል ኢኮኖሚ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የመረጃ አስተዳደርና የሳይበር ደህንነት ጥበቃን ሕልው ማድረግ፣ የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትን መጨመር፣ ዲጅታል ክህሎትና ኢኖቬሽንን ማሳለጥ ነው። ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ /ፋይዳ/፤ የዲጅታል ሽግግር መልህቅ ''በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ ዲጅታል ማንነት ተስፋ ሰጪ ከሆነው ፈጠራ ወደ ዲጅታል ሽግግር መሠረታዊ ምሰሶ ተሻሽሏል። ከአሁን በኋላ አማራጭ ሳይሆን፣ ሰዎችን ከአገልግሎቶች፣ ከማኅበረሰቦች፣ ከተቋማት እና ከመንግሥታት ጋር የሚያገናኝ አስፈላጊ መሠረተ ልማት ነው። ፋይዳ ካርድ ብቻ አይደለም። የግለሰቦችን የግል መረጃ ምሥጢራዊነት በመጠበቅና አስፈላጊ የሆነውን መረጃ ብቻ በማጋራት ማንነትን የሚያረጋግጥ ልዩ መለያ ቁጥር ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ /ፋይዳ/፤ የዲጅታል ሽግግር መልህቅ የዲጅታል ብሔራዊ መታወቂያ /ፋይዳ/ (National Digital ID) በኢትዮጵያ ሥራ የጀመረው እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2023 ነበር። ምንም እንኳን የፕሮጀክቱ ዝግጅትና ሕጋዊ መሠረት ቀደም ብሎ የተጀመረ ቢሆንም፣ በአዋጅ ቁጥር 1284/2015 በሕግ ተቋቁሟል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር ከ2019 እስከ 2020 ባለው ጊዜም ፋይዳ በዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አካል ሆነ። ከዚያም ምዝገባው በመላ ኢትዮጵያ ተስፋፍቶ፣ ከመንግሥት አገልግሎቶች፣ ከባንኮች፣ ከዲጅታል ክፍያ ሥርዓት እና ከመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል አገልግሎት ጋር ተሳስሯል። በኢትዮጵያ እያንዳንዱን ነዋሪ የአንድ ልዩ የዲጅታል መለያ ባለቤት ማድረግ የፕሮጀክቱ ዋነኛ ግብ ነው። ይህም የመንግሥትና የግል አገልግሎቶችን በቀላሉ ማግኘት የሚቻልበትን ሥርዓት ለመዘርጋት፣ የማንነት ማጭበርበርና ድርብ ምዝገባን ለማስቀረት እንዲሁም የኢትዮጵያን ዲጅታል ኢኮኖሚ ለመደገፍ ያስችላል። ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የነዋሪዎችን የባዮሜትሪክና ዲሞግራፊክ መረጃ በመሰብሰብ፣ ''አንድ ሰው፣ አንድ ማንነት” በሚል መርህ እያንዳንዱን ሰው ልዩ በሆነ ሁኔታ መለየት የሚያስችል ሥርዓት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለፋይዳ አስፈላጊነት ሲናገሩ፣ “ፋይዳ በአማርኛ፣ በኦሮሚኛ፣ በትግርኛ፣ በሱማሊኛ፣ በአፋርኛ እንዲሁም በአረብኛ፣ በሂንዱኛና በተርኪሽ ቋንቋዎች ፋይዳ ነው። … ዲጅታል መታወቂያ /ፋይዳ/ በጣም ጠቃሚ ነገር ነው፤ ከሕዳሴ የሚያንስ አይደለም። እንደ ሀገር ዲጅታል መታወቂያ ብንሠራ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት በሰባት ፐርሰንት ይጨምራል። ፋይዳ የመተማመኛ ሥርዓት ነው…” በማለት የፋይዳን መልከ ብዙ ፋይዳ ገልጸዋል። ፋይዳ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የዲጅታል ኢኮኖሚ ሽግግሩን ለማሳለጥ ቁልፍ መሣሪያ መሆኑንም አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ከ150 በላይ ተቋማት ጋር ተሳስሯል። ከ48 ሚሊዮን በላይ ዜጎችም ተመዝግበዋል። እስከ 2020 ዓ.ም ድረስ የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ወደ 115 ሚሊዮን ለማድረስ ጉዞው ቀጥሏል። በዚህም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ወደ መደበኛ የፋይናንስ ሥርዓት ለማስገባት እያገዘ ይገኛል። መንገዶች ሁሉ ኢትዮጵያን ወደ ዲጅታል ሽግግር በሚወስዱበት ሀዲድ፣ ፋይዳ መሪ ተዋናይ ሆኖ ይቀጥላል። ዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት እንዲያገኙ፣ የባንክና የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲጠቀሙ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ምህዳር ይፈጥራል። መንግሥትም ማጭበርበርን ለመከላከል፣ በተቋማት መካከል ግልጽና የተቀናጀ ትብብርን ለመዘርጋት እና የተሻለ የሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥበትን ዕድል እውን ለማድረግ ፋይዳን ይጠቀማል። የቢዝነስ አንቀሳቃሾችም ዲጅታል ግብይትን፣ ፋይናንስንና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሥራቸውን የበለጠ ቀልጣፋና ተደራሽ ማድረግ ይችላሉ። በአጭሩ፣ ፋይዳ ''ሁሉ በእጄ፣ ሁሉ በደጄ” የሚለውን የዲጅታል ኢኮኖሚ ራዕይ እውን ለማድረግ የሚያግዝ ቁልፍ መሠረተ ልማት ነው። መሶብ፤ የአንድ ማዕከል ዲጅታል አገልግሎት የጊዜና የቦታ ልጓም ''ሀገራዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሠረታዊ የሆነ የባህል ለውጥ ያስፈልጋል። ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን እንገኛለን። መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ የጀመርነው በቅርብ ጊዜ ቢሆንም፣ በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች እርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧል። ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ያመላክታል።”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል አገልግሎት፤ የጊዜና የቦታ ልጓም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 12 የፌዴራል ተቋማት 40 የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ሥር እንዲሰጡ በማድረግ ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል። እነሆ ማዕከሉ የተቋማትንና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ቁጥር እያሳደገ የኢትዮጵያን የዲጅታል ሽግግር ፍኖት እየቀረጸ ይገኛል። ዜጎችም በዲጅታል መሠረተ ልማት የተደገፈ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል። ከዚህ በፊት የዜጎችን ጊዜ የሚያባክኑ ረጅም ወረፋዎች፣ የተለያዩ ቢሮዎችን ደጋግሞ መጎብኘት፣ “ሰነድ ይጎድላል፣ ኮፒ አድርገህ አምጣ” የሚሉ የወረቀት ሥራዎች በአዲሱ የአገልግሎት ሥርዓት እየተቀየሩ ነው። አዲስ የአገልግሎት አድማስ የሆነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከ220 በላይ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ሕንፃ ሥር በማቅረብ የዜጎችን የጊዜና የቦታ ጫና ቀንሷል። ከቀበሌ መታወቂያ ማውጣት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የንግድና የጉምሩክ አገልግሎቶች ድረስ በቀላሉ ማግኘት የሚቻልበት ምቹ ምህዳር ተፈጥሯል። ፈጣንነት፣ ቅልጥፍና፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና መርሆዎች ሆነዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተንቀሳቃሽ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ባስጀመሩበት ወቅት፤ ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል፣ እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን እንቀጥላለን ብለዋል። የዲጅታል አገልግሎት የዜጎችን ጊዜና ጉልበት የሚቆጥብ አዲስ የአስተዳደር ባህል መሆኑን ገልጸዋል። በአጠቃላይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የወረቀት እና የወረፋ ዘመንን በመቀየር ዜጋን ማዕከል ያደረገ፣ ቀልጣፋና ዲጅታል የሆነ የአገልግሎት ሥርዓት እየገነባ ያለ የለውጥ ምሳሌ ሆኗል። የ5-ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ፤ የዲጅታል ክህሎት ማበልጸጊያ መድረክ በዲጅታል ዘመን የሰው ኃይል አቅም የሀገራት የዕድገት መሰረት እሆነ ነው። ኢትዮጵያም የወጣቶቿን የፈጠራና የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ ትልቅ የዲጅታል ክህሎት ማበልጸጊያ መርሃ ግብር ጀምራለች። የ5-ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ የወጣቱን ትውልድ የፕሮግራሚንግ፣ የሶፍትዌር ልማት፣ የፈጠራ ሥራና የዲጅታል ቴክኖሎጂ አቅም ለማጎልበት የተቀረፀ ሀገራዊ አጀንዳ ነው። መርሃ ግብሩ ወጣቶችን የዲጅታል ኢኮኖሚ ተሳታፊዎች ብቻ ሳይሆኑ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችና የሀገር በቀል መፍትሔ አበልጻጊዎች ለማድረግ ያለመ ነው። ''ይህም ኢትዮጵያ በዓለም የዲጅታል ውድድር ውስጥ የምትኖራትን ሚና ለማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና በአፍሪካ የፈጠራ ማዕከል ለመሆን የሚያግዝ የወደፊት ራዕይ ነው። ኢትዮጵያ ወደፊት የሚያልሙ አሳቢ ወጣት ዜጎቿ ተስፋ አላት። የ‘አምስት ሚሊዮን ኮደርስ’ መርሃ ግብር ታላቅ እድል ነው። አምስት ሚሊዮኖቹ ኮደሮች ሀገር በቀል መፍትሔዎችን የሚሰጡ ብቻ ሳይሆኑ፣ ለአህጉራችን የተስፋ ብርሃን የሚፈነጥቁ ናቸው።''ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአጠቃላይ 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ የዲጅታል ክህሎትን ከመገንባት ባሻገር፣ የወጣቱን የፈጠራ ኃይል ወደ ሀገራዊ የዕድገት ሞተር ለመቀየር የተቀረፀ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ዋነኛ መሠረት ነው። 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ፤ የዲጅታል ክህሎት ማበልጸጊያና የወጣቱ የወደፊት አቅም በፍጥነት በሚለዋወጠው የዲጅታል ዓለም ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት መያዝ አማራጭ ሳይሆን የዘመኑ ግዴታ ሆኗል። ዛሬ ላይ በመትጋት ነገን ማልማት የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ሲሆን፣ የሀገር ዕድገትም የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ላይ ይመሰረታል። መንግሥት የበለጸገችና በቴክኖሎጂ የተደገፈች ኢትዮጵያን ለመገንባት ከለያቸው አምስት ቁልፍ የትኩረት መስኮች መካከል አይ.ሲ.ቲ (ICT) አንዱ ነው። በዚህ ራዕይ መሠረት የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማሳለጥ ሦስት ቁልፍ የዲጅታል ሽግግር ማስፈጸሚያዎች ተግባራዊ ሆነዋል። እነሱም መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል አገልግሎት፣ ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ (ፋይዳ) እና 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ናቸው። የወጣቱን የዲጅታል አቅም የሚገነባ ታላቅ ኢንሼቲቭ 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ትብብር ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ በሦስት ዓመታት ውስጥ 5 ሚሊዮን ወጣቶችን በዲጅታል ክህሎት ለማሰልጠን የተቀረጸ ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሚንግ (Programming)፣ የመረጃ ትንተና (Data Analysis)፣ የአንድሮይድ ልማት (Android Development) እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሠረቶች (Artificial Intelligence Fundamentals) የሥልጠናው ዋና የክህሎት ዘርፎች ናቸው። ኢንሼቲቩ የተያዘለትን ግብ በፍጥነት እያሳካ ይገኛል። ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል፤ ቁጥሩን እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም 7 ሚሊዮን ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል። ይህም የወጣቶችን ለሥራ ዓለም ተፈላጊነት ከማሳደግ ባሻገር፣ የሀገሪቱን የዲጅታል የሰው ኃይል ልማት ያጠናክራል። በመንግሥት ተቋማት የሶፍትዌር ልማትና የዲጅታል ሽግግር ሥራዎችን የሚያሳልጡ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችንም ያፈራል። በኢንሼቲቩ አማካኝነት 1 ሚሊዮን የዲጅታል የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ከዲጅታል ምርቶች ወጪ ንግድ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት የተቀመጠው ዕቅድ የፕሮግራሙን ሀገራዊ ፋይዳ ያመላክታል። የወጣቶች የፈጠራ ኃይል የኢትዮጵያ የዲጅታል ተስፋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየትኛውም የትምህርትና የዕውቀት ደረጃ ላይ ያሉ ወጣቶች የአምስት ሚሊዮን ኮደሮች ፕሮጀክትን በመጠቀም ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ጥሪ አቅርበዋል። የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከላት፣ አሰልጣኞችና ዩኒቨርሲቲዎችም የፕሮግራሙን ስኬት ለማስፋት የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል። የዲጅታል ሽግግር ሦስቱ ምሰሶዎች በጥቅሉ 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ፣ ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ (ፋይዳ) እና መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የኢትዮጵያን የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያስፈጽሙ ተያያዥ ምሰሶዎች ናቸው። ኮደርስ የዲጅታል ኢኮኖሚውን የሚገነባና የሚያስፋፋ የሰው ኃይል ያበረክታሉ፤ ፋይዳ ደግሞ የደህንነቱ የተጠበቀ የዲጅታል ማንነት ሥርዓት ይፈጥራል፤ መሶብም በአንድ ጣሪያ ሥር ፈጣንና ግልጽ የህዝብ አገልግሎት ያሳልጣል። ከዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይ ጋር ተጣምረው እነዚህ ሦስት የለውጥ ምሰሶዎች ኢትዮጵያን ወደ አካታች፣ ዘላቂና ተወዳዳሪ የዲጅታል ኢኮኖሚ ለማሸጋገር የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የኢትዮጵያ ተሻጋሪ ህልሞች መመልከቻ በኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እ.ኤ.አ. በ2020 የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመመስረት ተቋማዊ መሠረት የያዘ የልማት አቅጣጫ ሆኗል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲና ሕጋዊ ማዕቀፎች በመዘርጋታቸው ዘርፉ በተደራጀ አሠራር እንዲመራ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጎበኙበት ወቅት፣ ሰው የጠራ ራዕይ ካለው፣ በከፍተኛ ዲሲፕሊን የሚሠራ ከሆነ ያሰበውን ማሳካት እንደሚችል፤ ኢትዮጵያ ብቃት ያላት ሀገር መሆኗን በመግለጽ የዘርፉን ሀገራዊ ጠቀሜታ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሀገር ውስጥ የፈጠራ አቅምን በማበረታታት ዘርፈ ብዙ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች እንዲመነጩ እያደረገ ይገኛል። በግብርና፣ በጤና፣ በፋይናንስ፣ በደህንነትና በአገልግሎት ዘርፎች የሚያገለግሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መፍትሔዎች በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች መፍጠር ጀምረዋል። በአማርኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የጽሑፍና የድምፅ ማቀናበሪያ ቴክኖሎጂዎች (NLP)፣ በጤና ዘርፍ የጡት ካንሰር፣ የስኳር በሽታና የሳንባ በሽታዎችን በምስል ምርመራ ቀድመው ለመለየት የሚያግዙ የAI መፍትሔዎች፣ በግብርና ዘርፍ የቡናና የሰብል በሽታዎችን የሚለዩ መተግበሪያዎች እየተስፋፉ ነው። በተጨማሪም ለከተማ ደህንነት፣ ለፖሊስ ሥራ፣ ለጉምሩክ ቁጥጥርና ለፋይናንስ ተቋማት የሚያገለግሉ ቻትቦቶችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በመስኩ እየተተገበሩ ይገኛሉ። የታዳጊዎች የሰመር ካምፕ የAI ስልጠናዎችም የወደፊቱን የቴክኖሎጂ ባለሙያ ትውልድ ለማፍራት እያገዙ ናቸው። የኢትዮጵያ የዲጅታል ሽግግርና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉዞ በሀገር ድንበር የማይገደብ፣ የአፍሪካን ዲጂታል ሽግግር ታሳቢ ያደረገ አህጉራዊ ራዕይ ነው። ለዚህም ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስን በማዘጋጀት አፍሪካ በዲጂታል ሽግግር፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ ትብብር እንድትጠናከር ያላትን ራዕይ አሳይታለች። በአፍሪካ ቀዳሚ ከሚሆኑ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከላት አንዱ የሆነው የAI ዩኒቨርሲቲ ግንባታም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት፣ የአፍሪካን የቴክኖሎጂና የፈጠራ አቅም ለማሳደግ የተያዘ ተሻጋሪ ራዕይ ነው። በአጠቃላይ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለኢትዮጵያ የወደፊት የዕውቀት ኢኮኖሚ፣ የፈጠራ አቅምና የዲጂታል ሉዓላዊነት መሠረት እየሆነ የሚሄድ ተሻጋሪ መሣሪያ ነው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፤ የዲጅታል ሉዓላዊነት እና ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ዘብ የዓለም የዲጅታላይዜሽን ሽግግር በብርሃን ፍጥነት እየተስፋፋ ባለበት ዘመን፣ ቴክኖሎጂን መጠቀም ብቻ ሳይሆን የዲጅታል መሠረተ ልማቶችን ከሳይበር ስጋቶች መጠበቅ የሀገራት ቁልፍ ተግባር ሆኗል። በዚህ የቴክኖሎጂ ውድድር ዓለም የመረጃ ደህንነት ከቴክኒክ ጉዳይ ባለፈ የሀገር ሉዓላዊነትና ህልውና ጉዳይ እየሆነ መጥቷል። ኢትዮጵያም የዘግይቶ መግባት ጥቅም (Latecomer Advantage) በመጠቀም የዲጅታል ሽግግሯን በዘመናዊ መሠረተ ልማቶች ላይ ለመገንባት እየሠራች ትገኛለች። ይህንን የዲጅታል ጉዞ አስተማማኝ ለማድረግና የሀገሪቱን የመረጃ ሀብት ለመጠበቅ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ወሳኝ ሚና እየተወጣ ነው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኢትዮጵያን የኢንፎርሜሽን ሥርዓቶችና ቁልፍ የመረጃ መሠረተ ልማቶች ከሳይበር ጥቃት የመጠበቅ፣ የመረጃ ደህንነትን የማረጋገጥና ብሔራዊ ጥቅሞችን የማስከበር ተልዕኮ ተሰጥቶታል። የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ፣ የደህንነት ኦፕሬሽን ማዕከላት (Security Operation Centers) እና የዲጅታል ፎረንሲክ ላቦራቶሪዎች ግንባታ ለዘርፉ የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ ዘመናዊ የዲጅታል ደህንነት መሠረተ ልማቶች እንደ ባንክ፣ ቴሌኮም፣ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ቁልፍ ሀገራዊ ተቋማትን ከተወሳሰቡ የሳይበር ጥቃቶች አስቀድሞ ለመከላከል፣ አደጋ ቢከሰትም ፈጣን ሕጋዊና ቴክኒካዊ ምላሽ ለመስጠት ያስችላሉ። የመረጃ ደህንነት፤ የዲጅታል ኢኮኖሚ መሠረት በዛሬው ዓለም መረጃ (Data) እንደ አንዱ ዋና ሀብት በመቆጠሩ፣ የዜጎችን ግላዊ መረጃ፣ የፋይናንስ ግብይቶችንና የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የዲጅታል ሉዓላዊነት ዋና መሠረት ሆኗል። ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ሥርዓት መኖሩ ዜጎች በዲጅታል አገልግሎቶች ላይ እምነት እንዲያሳድሩ፣ የግልና የውጭ ባለሀብቶችም በኢትዮጵያ የዲጅታል ኢኮኖሚ ላይ የተሻለ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋል። በዚህም የሳይበር ደህንነት የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስኬትን የሚደግፍ ዋና የጥበቃ መሠረት ሆኖ ይቀጥላል። ማጠቃለያ፡ ዲጂታል ኢትዮጵያ፤ የወደፊት ተወዳዳሪነት መሠረት የኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ጉዞ ከፖሊሲ ቀረጻ እስከ ተግባራዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት ዝርጋታ በፍጥነት እየተሻገረ ይገኛል። ይህ ሀገራዊ ንቅናቄ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሚመራ ሲሆን፣ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ /ፋይዳ፣ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት፣ አምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ልማትና የሳይበር ደህንነት ሥርዓት ዋና ዋና የሽግግሩ ምሰሶዎች ሆነዋል። ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ /ፋይዳ የዜጎችን ዲጂታል ማንነት በማረጋገጥ ለዲጂታል አገልግሎቶች መሠረት ሲሆን፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሕዝብ አገልግሎትን በፍጥነት፣ በቅልጥፍናና በግልጽነት ለማቅረብ አዲስ የአሠራር ባህል እየገነባ ነው። አምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ደግሞ ለዲጂታል ኢኮኖሚው የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል በማፍራት የቴክኖሎጂ ፈጠራና የዲጂታል ሥራ ዕድል እድገትን ያፋጥናል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልማት ተቋማት የወደፊቱን የእውቀትና የፈጠራ አቅም ለመገንባት ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል። በተመሳሳይም የሳይበር ደህንነት ሥርዓት የዲጂታል ኢኮኖሚውን ከስጋቶች የሚጠብቅ፣ የመረጃ ደህንነትንና የሀገር ዲጂታል ሉዓላዊነትን የሚያስከብር ጠንካራ ጋሻ ሆኖ ይቀጥላል። በቴክኖሎጂ፣ በኢኖቬሽንና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለችው መዋቅራዊ እርምጃ የአገር ውስጥ አገልግሎቶችን ከማዘመንና የዜጎችን ኑሮ ከማቅለል ባለፈ፣ ሀገሪቱን በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ አካታችና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚ ባለቤት ለማድረግ የሚያግዝ ነው። ኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ አድማስ፡- '’ኢትዮጵያዊነት ያስተማረን ትልቁ እውነት፤ በጊዜያዊ ፈተናዎች ተሸንፎ መውደቅ ሳይሆን፣ ችግሮችን ወደ ዕድል፣ ፈተናዎችንም ወደ ስኬት መለወጥና ድልን መቀዳጀት ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ቀጣይ የልህቀት ጉዞ ጠንካራ መነሻና መሠረት ይሆናሉ። በመሆኑም ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታዋን ለማፋጠን በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በተቀናጀ መንገድ በጋራ ገቢራዊ ማድረግ ይጠበቅባታል። ዲጂታል ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ራዕይ ብቻ ሳይሆን፤ የእውቀት፣ የፈጠራና የተወዳዳሪነት ሀገራዊ መሠረት ነው።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ተስፋ ያበሰረና ለአፍሪካውያንም አርዓያ የሚሆን ስኬታማ ምርጫ ነው
Aug 7, 2026 66
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ተስፋ ያበሰረና ለአፍሪካውያንም አርዓያ የሚሆን ስኬታማ ምርጫ ነው ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ብልፅግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያገኘውን የህዝብ ውክልና ወደ ተጨባጭ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ስኬቶች ለመቀየር በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡ ብልፅግና ፓርቲ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማብራሪያ ሰጥቷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እንደገለፁት፣ ፓርቲው በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ ቁርጠኝነት በመሰነቅ እና ሁለት ዋና ዋና ግቦችን ይዞ ወደ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ገብቷል። የመጀመሪያውን ግብ አስመልከተው ሲያስረዱ፣ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ እና ነፃ በማድረግ ኢትዮጵያውያን ሀሳባቸውን እና ድምፃቸውን በነፃነት የሚገልጹበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደነበር ገልፀዋል። በዚህም በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ግንባታ ላይ የህዝቡ ተስፋ እንዲለመልም እና ዲሞክራሲ መሰረት እንዲይዝ ፓርቲው የሚጠበቅበትን ሀላፊነት በቁርጠኝነት መወጣቱን ገልፀዋል። ብልፅግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ አግኝቶ መንግስት የመመስረት አላማ ብቻ ሳይሆን የነበረው፣ ምርጫው ነፃ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የመሪነት ሚና መጫወት እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ ሂደቱም የዴሞክራሲ ተስፋን የሰጠ እና ለአፍሪካውያንም ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ውጤታማ ምርጫ እንደነበር ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ አስገንዝበዋል። ፓርቲው በበርካታ እጩዎች ተወዳድሮ ከኢትዮጵያ ህዝብ አብላጫ ድምፅ በማግኘት መንግስት ለመመስረት የሚያስችል አዲስ ህዝባዊ ውክልና ማግኘቱን አብራርተዋል። በሚቀጥሉት አምስት አመታትም የፓርቲውን ማኒፌስቶ ወደ እቅድ እና ስትራቴጂ በመቀየር ለህዝብ የገባውን ቃል ወደ ተግባር እንደሚቀይር ገልፀዋል። በዚህም ትኩረቱ የኢትዮጵያን ዲሞክራሲ ማሻገር ብቻ ሳይሆን ህዝቡን ከድህነት ማውጣት፣ የምግብ ሉአላዊነትንና ዋስትናን ማረጋገጥ እንዲሁም ኢትዮጵያን በአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ማድረግ ላይ እንደሆነ አስታውቀዋል። በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ስሁል በበኩላቸው፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድንቅ በሆነ መንገድ መከናወኑን ገልፀዋል። የዛሬው መድረክ በዋናነት ከምርጫው መጠናቀቅ በኋላ የተከናወኑ የድህረ ምርጫ የሚዲያ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራዎችን ለማስረገጥ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል። ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ እና አብረዉ ሲሰሩ የቆዩ የበርካታ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች በመድረኩ መገኘታቸውን ገልፀው፤ የዝግጅቱ ዓላማ በአጠቃላይ ሂደቱ ላይ የጋራ መግባባት እና መረዳትን ለመፍጠር ያለመ እና ውጤታማ የሆነ መድረክ እንደነበር ገልፀዋል። የብልፅግና ፓርቲ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ501 ውስጥ 438ቱን መቀመጫዎች ማግኘቱን ጠቅሰው ከክልል ምክር ቤት 2ሺህ 700 መቀመጫዎች ውስጥም 2ሺህ 410 መቀመጫዎች ማግኘቱን ተጠቅሷል፡፡ በሌላ መልኩም 8 የተፎካካሪ ፓርቲዎች መቀመጫ ማግኘታቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም 49 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን እና 246 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎችን ማግኘታቸውን በዚሁ ወቅት አብራርተዋል። በኢትዮጵያ የራሺያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴሬክሂን በሰጡት አስተያየት፤ በስኬት የተካሄደውን ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለኢትዮጵውያን ትልቅ ድል ነው ብለዋል፡፡ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የህዝቡን የሰላም፣ የብልፅግና እና የእድገት ፍላጎት ያረጋገጠ ትልቅ ክስተት በመሆኑ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ስኬትን እመኛለሁ ብለዋል። በኢትዮጵያ የኡጋንዳ አምባሳደር ሬቤካ አሙጌ ኦቴንጎ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁ ለኢትዮጵያ ህዝቡና ለብልፅግና ፓርቲ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ከማብራሪያው መጠናቀቅ በኋላ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የተቋማት ተወካዮች እና የዓለማቀፍ ማህበረሰብ አባላት የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ቋሚ ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ የዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቀቀ
Aug 7, 2026 53
ወልቂጤ፣ ነሐሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን የክልሉን ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት በማድመጥ እና የዳኞች ሹመትን በማፅደቅ ተጠናቋል። የክልሉ ዋና ኦዲተር ወይዘሮ ፈዲላ አደም በጉባዔው ላይ እንደገለጹት፥ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በተከናወነው የኦዲት ሥራ ሊባክን የነበረ የመንግሥት እና የሕዝብ ሀብት መከላከልና ተመላሽ ማድረግ ተችሏል። የኦዲት ተደራሽነትና ሽፋኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ያመለከቱት ዋና ኦዲተሯ፣ በፋይናንስ ኦዲት፣ በገቢ ግብር፣ በታክስና በሊዝ አሰባሰብ እንዲሁም በዓይነትና በአካባቢ ኦዲት ላይ የተሻለ ቢሆንም አሁንም በዘርፉ የሚታየውን የአሰራር ክፍተቶች ለማረም መረባረብ እንደሚገባ አስረድተዋል። የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ በበኩላቸው፤ በክልሉ የኦዲት ግኝቶች ውጤታማ በሆነ መልኩ ምላሽ እንዲያገኙ የክልሉ ምክር ቤት ተገቢውን ድጋፍና እገዛ ማድረጉን ገልጸዋል። የመንግስት በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በቀጣይም የኦዲት ግኝቶች በሙሉ ተመላሽ እንዲሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በሙሉ አቅማቸው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ምክር ቤቱ የቀረቡ የዳኝነት ሹመቶችን ያጸደቀ ሲሆን፣ ዛሬ ከተሾሙት 65 ዳኞች መካከል ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስምንት፣ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት 13 እና ቀሪዎች 44 ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት መሆናቸው ተገልጿል። በጉባኤው ማጠቃለያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሲያገለግሉ ለነበሩ የምክር ቤት አባለት እውቅና ተሰጥቷል።
የኤርትራ ህዝብ በአንድ ጨቋኝ ስርዓት ታፍኖ መኖር ሊበቃ ይገባል- ብርጌድ ንሓመዱ
Aug 7, 2026 86
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የኤርትራ ህዝብ በአንድ ጨቋኝ ስርዓት ታፍኖ መኖር ሊያበቃና የስርዓት ለውጥ ሊመጣ እንደሚገባ የግንባር ሕዝባዊ ማዕበል ብርጌድ ንሓመዱ አስታወቀ። የቀጣናውን ሰላም አደጋ ላይ ለመጣል በጦርነት ፍላጎት የተጠመደው ፅምዶ ተብሎ የሚጠራው የሽብር ቡድን ሕዝባዊ ድጋፍና መሠረት እንደሌለውም ነው የገለጸው። የግንባር ህዝባዊ ማዕበል ብርጌድ ንሐመዶ የድርጅቱን ሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴና ቀጣናዊ ትብብር በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። የግንባር ህዝባዊ ማዕበል ብርጌድ ንሓመዱ የፖለቲካና ዲፕሎማሲ ኃላፊ በየነ ገብረእግዚአብሔር እንዳሉት፤ ብርጌድ ንሓመዱ በኤርትራ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ማህበራዊ መሰረት ያለው እንቅስቃሴ ነው። ግንባሩ የኤርትራን ዲያስፖራ በማደራጀት፣ በኤርትራ ያለውን ህዝብ የለውጥ ፍላጎት በማጠናከር ስርዓቱን ለመለወጥ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል። ሻዕቢያ የቀጣናውን ሰላም አደጋ ላይ ለመጣል በጦርነት ፍላጎት የተጠመደው ፅምዶ ተብሎ የሚጠራ የሽብር ቡድን አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን በማነሳት፤ ይህ የጦርነት አባዜ የተጠናወተው ስብስብ ሕዝባዊ ድጋፍና መሠረት እንደሌለው አመልክተዋል። ፅምዶ ለኤርትራም ሆነ ለትግራይ ሕዝብ የማይጠቅም ቀጣናውን ለማተራመስ የተዘጋጀ ስብስብ መሆኑንም ተናግረዋል። የግንባር ህዝባዊ ማዕበል ብርጌድ ንሓመዱ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ዳዊት ይብራህ፤ ግንባሩ በኤርትራ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ህዝባዊ መሰረት ይዞ መመስረቱን ተናግረዋል። የኤርትራ ህዝብ በአንድ ጨቋኝ ስርዓት ታፍኖ መኖር ሊያበቃ እንደሚገባ ጠቅሰው፤ ለዚህ ህዝባዊ ለውጥ ማምጣት ጀምረናል ብለዋል። ኤርትራ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር መልካም ጉርብትና እንዲኖራት ለማድረግ ስርዓቱን መለወጥ እንደሚገባም ገልጸዋል። የግንባር ህዝባዊ ማዕበል ብርጌድ ንሓመዱ የዲፕሎማሲ ቡድን አባል ዳዊት ተፈሪ እንደገለጹት፤ የኤርትራ ህዝብ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በልማት እንዲተሳሰር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ጡት ማጥባት ሕፃናት የተስተካከለ እድገት እንዲኖራቸው የሚያስችል ተፈጥሯዊና ውጤታማ መንገድ ነው
Aug 7, 2026 55
ወልድያ፤ነሃሴ1/ 2018 (ኢዜአ) ፡-እናቶች ተፈጥሯዊ ስጦታቸው የሆነውን ጡት አጥብተው ልጆቻቸውን በማሳደግ ለአገር አለኝታ የሆነ ትውልድ ማፍራት እንደሚጠበቅባቸው የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ። መምሪያው በዓለም ለ35ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጡት ማጥባት ሳምንት አስመልክቶ ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 01 ቀን 2018 ዓ.ም የግንዛቤ መፍጠሪያ የውይይት መድረክ አካሂዷል። የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃን ኃይሉ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ጡት ማጥባት የህፃናትን ጤንነትና ደህንነት በማስጠበቅ የነገ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ መሰረት የሚጥል ነው። የህጻናትን የተስተካከለ እድገት ለማረጋገጥና ጤናማ ትውልድ ለማፍራት ከፅንስ ጀምሮ ህጻኑ ተወልዶ እስከ ሁለት ዓመት ያለው ጊዜ የአመጋገብ ሁኔታን ማወቅ ለእናቶች አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። አንድ ህጻን ከተወለደ ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ድረስ ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናትን ጡት ብቻ መመገብ ተገቢ መሆኑን ጠቁመው፤ እስከ ሁለት ዓመት ከተጨማሪ ምግብ ጋር ማጥባት ወሳኝ ነው ብለዋል። የዘንድሮው በዓል ሲከበርም ጡት ማጥባት በህጻናት እድገትና በእናቶች ጤና ላይ የሚያስገኘውን ጥቅምና ፋይዳ ግንዛቤ ለመፍጠርና ለማበረታታት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል። ይህም ጤናማ ትውልድ በመገንባት የማህበረሰብ ልማትንና የአገርን ዘላቂ እድገት ለማስቀጠል መሰረት በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል። በሰሜን ወሎ ዞን የሰቆጣ ቃል ኪዳን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ግዛቸው ታረቀኝ በበኩላቸው፤ ለሕፃናት የመጀመሪያው የበሽታ መከላከያ መንገድ የእናት ጡትን በተገቢው መንገድ መስጠት ነው። ለዚሁ ስኬትም ለእናቶች በቂ ምግብ፣ እረፍት እንዲያገኙና ልጆቻቸውን ጡት አጥብተው እንዲያሳድጉ የሚያደርግ ጊዜ መስጠት እንደሚገባ አስረድተዋል። ቃል ኪዳኑም የሚያጠቡና ነፍሰ ጡር እናቶችን በማቀፍ በጓሯቸው አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ፣ በፍየል እርባታና በንብ ማነብ በመሰማራት በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ እየደገፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የዞኑ ወጣት በጎ ፈቃደኞች ተወካይ ንግስት ይመር እንዳለችው፤ የውይይት መድረኩ በቀጣይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ያስችለናል ብላለች። “ጡት ማጥባት፤ ለዘላቂ የሕይወት ጅማሮ!” በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው ውይይት ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና የአጋር ድርጅት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ፖለቲካ

የሕገ-ወጡን የህወሓት ቡድን እኩይ ተግባር በመቃወም የምናደርገውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን
Aug 7, 2026 104
አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ሕገ-ወጡ የህወሓት ቡድን የሕግ የበላይነት እና ሥርዓት እንዳይኖር የሚፈጽመውን እኩይ ተግባር በመቃወም የምናደርገውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የትግራይ ክልል ወጣቶች ገለጹ። ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን ለጦርነት በግዳጅ ከሚያደርገው አፈሳ አምልጠው የመጡ የትግራይ ክልል ወጣቶች ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በፖለቲካው መድረክ የተሸነፈው ሕገ-ወጡ የህወሓት ቡድን ከተጠያቂነት ለማምለጥ እና ሥልጣኑን በሕገ-ወጥ መንገድ በኃይል ለማስቀጠል "ሕገ-አራዊት" በማውጣት ጦርነትን እንደ ብቸኛ አማራጭ አድርጎ በመውሰድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል። በዚህም የክልሉ ተወላጅ ወጣቶች ህገ-ወጥ ቡድኑ እያካሄደ ያለው ከፍላጎት ውጪ የሆነ አፈሳ በመሸሽ ወደተለያዩ ክልሎችና ወደ ውጭ ሀገራት እየተሰደዱ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ወጣት ገብረ ኪሮስ ሕሉፍ ፤ ሕገ-ወጡ የህወሓት ቡድን ሰላማዊ ሁኔታ ከተፈጠረ ተጠያቂነት ይመጣል ከሚል ስጋት እና ለሥልጣን ካለው ስግብግብነት በመነሳት ሕገ-መንግሥቱን እና የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ የሕግ የበላይነት እና ሥርዓት እንዳይኖር እየሠራ መሆኑን አስረድቷል። ቡድኑ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ትጥቁን ለመፍታት ቢስማማም ባለፉት ሦስት ዓመታት ስምምነቱን በመጣስ ታጣቂ ሲያሠለጥን እና ከውጭ ኃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ለጦርነት ሲዘጋጅ መቆየቱን ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት ወደ አጥፊ ጦርነት ለመግባት ወጣቶችን ያለፍላጎታቸው በግዳጅ በማፈስ ወደ ጦር ካምፕ የማስገባትና ወደ ኤርትራና ሱዳን የመሸጥ ስራ ላይ ተጠምዶ እንደሚገኝ ጠቁሟል። ወጣት ፀጋልኡል በርሔ በበኩሉ፤ የሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን በፖለቲካዊ መንገድ የተሸነፈ መሆኑን እና በአሁኑ ወቅት የሚፈጽማቸው የግዳጅ ወጣቶች ምልመላ፣ እናቶችን ማሰር፣ ግድያ እና የእንግልት ተግባራት የዚህ ውድቀቱ ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጿል። በዚህም ቡድኑ ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር ጥምረት በመፍጠር ወጣቶችን ለወታደራዊ ሥልጠና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ከመላክና በተጨማሪ ወደ ኤርትራ እና ሱዳን እየሸጠ እንደሚገኝ ተናግሯል። ቡድኑ እኛ በሥልጣን ላይ ካልኖርን ትግራይ ክልልንም ሆነ ሀገርን እናፈርሳለን በሚል አጥፊ አስተሳሰብ እየተመራ መሆኑንም አክሎ ገልጿል። በመሆኑም የክልሉ ተወላጅ ወጣቶች ሕገ ወጥ ቡድኑ የሚያደርገውን ተግባር መቃወማችንን ማጠናከር አለብን ብለሏል። የሕገ-ወጡ ህወሓት ቡድን መሪዎች የትግራዋይነትም ሆነ የኢትዮጵያዊነት ሥነ-ልቦና እንደሌላቸው እና አስተሳሰባቸውም ሆነ ተግባራቸው ፀረ-ትግራዋይነት እና ፀረ-ኢትዮጵያዊነት መሆኑን የገለጸው ደግሞ ወጣት ዮሐንስ ገብሩ ነው። ትግራይ ክልልን በሕገ-ወጡ ቡድን ምክንያት ከገባችበት ሁለንተናዊ ቀውስ ለማውጣት ወጣቶች ተደራጅተው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አመልክተው፤ በግዳጅ ምልመላ እና በጦርነት ቅስቀሳ ላይ የምናደርገውን ትግል ማጠናከር አለብን ብለዋል።
ብልፅግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያገኘውን የህዝብ ውክልና ወደ ተጨባጭ ስኬት ለመቀየር በሙሉ አቅሙ ይሰራል
Aug 7, 2026 125
አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ብልፅግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያገኘውን የህዝብ ውክልና ወደ ተጨባጭ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ስኬቶች ለመቀየር በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ የፓርቲው የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ። ብልፅግና ፓርቲ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማብራሪያ ሰጥቷል። በዚሁ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ጠንካራ ሀገር ለመገንባትና ዜጎችን ከድህነት ለመውጣት ዋናው መነሻ በርዕይ፣ በአመራር፣ በሰው ኃይል፣ በአደረጃጀትና በቁሳቁስ የበቃና ውጤታማ ፓርቲ መገንባት ነው። ብልፅግና ፓርቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከህዝቡ ጋር ትብብርና ተሳትፎን መሰረት ያደረገ ጠንካራ ቁርኝት መፍጠሩን አስረድተዋል። ባለፉት ዓመታት በፓርቲው መሪነት የተነደፉትና የተተገበሩት በርካታ ስትራቴጂዎች በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያገኙና በየደረጃው ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማንቀሳቀስ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸው ተናግረዋል። ባለፉት ሶስትና አራት ዓመታት በተተገበሩ የግብርና ማሻሻያዎች ኢትዮጵያ የምግብ ሉዐላዊነቷን ማረጋገጥ ጉዞ መጀመሯን ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ውስጥ ትልቅ የስንዴ አምራች ሀገር መሆኗን ተናግረዋል። በአረንጓዴ ዐሻራ ባለፉት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል አካባቢን የመንከባከብና የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም መገንባቷን ጠቅሰዋል። በከተሞች ልማትና ገጽታ ግንባታ አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የሀገሪቷ ከተሞች ዘመናዊና አጠቃላይ የከተማ ደረጃን የሚያሻሽሉ የኮሪደርና የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል። ብልፅግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከህዝብ ያገኘውን አዲስ የህዝብ ውክልና መነሻ በማድረግ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ቃል የገባቸውን የማኒፌስቶ ሃሳቦች ወደ ዝርዝር የድርጊት መርሃ ግብሮች በመቀየር ላይ ይገኛል ብለዋል። በቀጣይ አምስት ዓመታት በርካታ የልማት እንቅስቃሴዎች እንደሚተገብሩ ጠቅሰው፤ ዜጎችን ከድህነት በማውጣት ሀገሪቷንና ማህበረሰቡን ወደ መካከለኛ ገቢ ደረጃ ለማሸጋገር ይሰራል ብለዋል። በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ግብርናን፣ ማኑፋክቸሪንግን፣ ቱሪዝምን፣ ማዕድንና ዲጂታል ኢኮኖሚን በማስፋፋት በቤተሰብና በግለሰብ ደረጃ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ገልጸዋል። የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ በማረጋጋት፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በባህልና በቋንቋ እድገት ላይ ትኩረት በማድረግ ማህበራዊ ልማትን ለማፋጠን እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። የህዝቦችን አንድነት፣ ዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት የሚያረጋግጡ ታላላቅ የወል ግንባታ ስራዎች እንደሚሰራም ጠቁመዋል። ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር ምክክር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት 4 ሺህ ኢትዮጵያውያን በመሳተፍ ላይ የሚገኙበት አካታች ሀገራዊ የምክክር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና በኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ እምርታ ላይ ትገኛለች
Aug 7, 2026 128
አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና በኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ እምርታ ላይ እንደምትገኝ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ስሁል ገለጹ። ብልፅግና ፓርቲ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማብራሪያ ሰጥቷል። የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ያደረጉ አምባሳደሮች እንዲሁም የተለያዩ የዲፕሎማቲክ ማሕበረሰብ አባላት በማብራሪያው ወቅት ተገኝተዋል። በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ስሁል በዚሁ ወቅት ባቀረቡት ማብራሪያ፤ የምርጫ ሂደቱ በሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች ተከፍሎ የተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫው ከመካሄዱ አንድ ዓመት በፊት ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው የዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን ተናግረዋል። በዚህም በመገናኛ ብዙኃን፣ በየደረጃው በሚገኙ የፓርቲ አወቃቀሮችና የማህበረሰብ ንቅናቄዎች አማካኝነት ሰፊ የምርጫና የዜግነት ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል። በምርጫው ዕለት ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ የተመዘገበበትና ሰላማዊ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት መካሄዱን ገልጸዋል። በበርካታ የምርጫ ጣቢያዎች እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ረጅም ሰልፎች የታዩ መሆኑን አውስተው፤ የምርጫ ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ታዛቢዎች እንዲሁም የፀጥታ አካላት በቅንጅት መስራታቸውን ገልጸዋል። ከምርጫ በኋላ ሕዝቡ የምርጫ ውጤት ማረጋገጫና ይፋ ማድረጊያ የሁለት ሳምንት ጊዜን በትዕግስት መጠባበቁን ጠቁመው፤ ይህም የተቋማትን መገንባትና የህዝቡን ዴሞክራሲ ብስለት ያሳየ ነው ብለዋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተመዘገቡ መሆኑን አስታውሰው፤ በዚህም 94 በመቶ መራጮች ድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ መሣተፋቸውን ተናግረዋል። በአጠቃላይ 501 የምርጫ ክልሎች እና 52,000 የምርጫ ጣቢያዎች እንደነበሩ አውስተው፤ በምርጫ ዕለት ከ195 ሺህ በላይ የምርጫ አስፈፃሚዎች መሰማራታቸውን ተናግረዋል። በመራጮች ምዝገባ ወቅት ደግሞ 187 ሺህ ባለሙያዎች ተሳታፊ መሆናቸው የተቋማትን አቅም ያሳያል ብለዋል። በምርጫው 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች 10 ሺህ 934 ዕጩዎች መወዳደራቸውን ጠቅሰው፤ ከእነዚህም መካከል 2 ሺህ 198 የፌዴራል፣ 8 ሺህ 736 የክልል እና ከተማ አስተዳደር ዕጩዎች እንዲሁም 73 የግል ተወዳዳሪዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በምርጫው ሂደት ከ64 በላይ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የተወጣጡ 1 ሺህ 814 የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች፣ 169 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና 55 እውቅና የተሰጣቸው የሀገር ውስጥ ታዛቢ ድርጅቶች መሳተፋቸውን ጠቁመዋል። ከዓለም አቀፍ ታዛቢዎች አኳያም 73 አባላት ያሉት የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን፣ 26 የኢጋድ አጭር ጊዜ ታዛቢዎች እና በርካታ አዲስ አበባ የሚገኙ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ታዛቢዎች ሂደቱን መታዘባቸውን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና በኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ እምርታ ላይ ትገኛለች ያሉት የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ማሸነፏን ተናግረዋል። የብልፅግና ፓርቲ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ501 ውስጥ 438ቱን መቀመጫዎች ማግኘቱን ጠቅሰው ከክልል ምክር ቤት 2ሺህ 700 መቀመጫዎች ውስጥም 2ሺህ 410 መቀመጫዎች ማግኘቱን ጠቅሰዋል። በሌላ መልኩም 8 የተፎካካሪ ፓርቲዎች መቀመጫ ማግኘታቸውን ጠቅሰው በዚህም 49 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን እና 246 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎችን ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።
የምክክር ጉባኤው አለመግባባቶችን በመፍታት ዘላቂ ሰላምና ልማትን ያመጣል
Aug 7, 2026 240
አሶሳ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦የምክክር ጉባኤው ይስተዋሉ የነበሩ አለመግባባቶችን በመፍታት ዘላቂ ሰላምና ልማትን እንደሚያመጣ ተስፋ ማድረጋቸውን የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለምክክር በተለዩ አጀንዳዎች ላይ በምክክር ጉባዔው የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮችን እያወያየ ይገኛል። ነዋሪዎቹ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ተወያዮች በምክክር ጉባኤው በጥልቀት በመወያየት የኢትዮጵያን አሸናፊነት የሚያበስር ሐሳብ ይዘው እንደሚወጡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። የምክክር ጉባኤው ይስተዋሉ የነበሩ አለመግባባቶችን በመፍታት ዘላቂ ሰላምና ልማትን እንደሚያመጣ ተስፋ ማድረጋቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ ወሊድ አንዋር እንደገለጹት፤ የምክክር ጉባኤው በሀገሪቱ ሲስተዋሉ የነበሩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምና ልማትን ያመጣል ብለዋል። ወይዘሮ መብራቴ ገረመው በበኩላቸው፤ ምክክሩ ኢትዮጵያውያን የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለማጎልበትና በውይይት ችግሮች የሚፈቱበትን አዲስ የፖለቲካና ማኅበራዊ ሥሪት ለመገንባት እንደሚያግዝ ተናግረዋል። ሀገራዊ ምክክሩ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሁሉንም በአንድ መድረክ ያሰባሰበ መሆኑ ሀገራዊ መግባባትን ለማሳካት የራሱ ድርሻ አለው ያሉት ደግሞ አቶ ሐመደነላህ አብደላህ ናቸው። ምክክሩ ቀጣይነት ላለው ዕድገትና ብልፅግና ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ገልጸዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ ሥር የሰደዱ ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል
Aug 7, 2026 156
ቦንጋ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ሀገራዊ ምክክሩ ሥር የሰደዱ ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ሰላሟ የጸና ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደሚያስችል የካፋ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ። በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ባለው የምክክር ጉባኤ የህብረተሰብ ተወካዮች በስምንት የምክክር አጀንዳዎች ላይ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየመከሩ ይገኛሉ። ኢዜአ ያነጋገራቸው የካፋ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ምክክሩ የቆዩና ሥር የሰደዱ ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ሰላሟ የጸና ጠንካራ ሀገር ለመገንባት መሰረት ይጥላል ብለዋል። በዞኑ የቦንጋ ከተማ የሀገር ሽማግሌ ወርቁ ወልደማርያም፤ ሀገራዊ ምክክሩ ከዚህ ቀደም የነበሩና አሁንም ድረስ ሳይፈቱ የቆዩ አለመግባባቶችን በሰለጠነ መንገድ መክሮ ለመፍታትና ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል። ምክክሩ ትውልዱ አብሮነቱን የሚያጠናክርበትና በሀገሩ ጉዳይ እኩል የሚወስንበትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል። እንደ ሀገር ሽማግሌው ገለጻ፣ ሁሉንም አሳታፊና አካታች በሆነ መልኩ እየተካሄደ ያለው ምክክር የቆዩ ሀገራዊ ችግሮችን በውይይት በመፍታት ጠንካራ ሀገር ለትውልድ ለመገንባት ወርቃማ ዕድል ነው። በካፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ ኡፋ ከተማ ሀገር ሽማግሌ ጊምቤራሻ መለሰ መሸሻ በበኩላቸው፣ ሀገራዊ ምክክሩ በህዝቦች መካከል አንድነትን የሚያጠናክር ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ የሚመክሩበትና ሀሳብ የሚለዋወጡበት ምቹ ምህዳር ባለመፈጠሩ አለመግባባቶችን በሀይል ለመፍታት መሞከር ባህል ሆኖ ቆይቷል ያሉት የሀገር ሽማግሌው፣ ምክክሩ ይህን ታሪክ ይቀይራል ብለዋል። ለዘመናት የቆዩ ችግሮችን ለመፍታት ኢትዮጵያውያን በጋራ ቁጭ ብለው መምከራቸው ታሪካዊ ዕድል መሆኑን ጠቅሰው፣ በኮሚሽኑ የተለዩ የውይይት አጀንዳዎች በየደረጃው በህዝብ የተነሱ መሆናቸውን ተናግረዋል። በምክክሩ የመጨረሻ ምዕራፍ ጉባኤ ላይ የተለያየ አመለካከት፣ ፍላጎት፣ እምነትና ባህል ያላቸው ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ በጋራ ሲመክሩ መመልከት መታደል መሆኑንም ገልፀዋል።
የሕገ -ወጡ ሕወሃትን የጦርነት ቅስቀሳና አፈና ልንታገለው ይገባል - የትግራይ ወጣቶች
Aug 7, 2026 233
አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦የታሪካዊ ጠላቶች ተላላኪ የሆነውን ሕገ-ወጡን የሕወሃት ቡድን የጦርነት ቅስቀሳና አፈና የትግራይ ህዝብና ወጣቶች አጥብቀው ሊቃወሙትና ሊታገሉት እንደሚገባ ከቡድኑ ግፍና አፈና ሸሽተው የመጡ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ገለጹ። ሕገ -ወጡ የሕወሃት ቡድን በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመቀናጀት የትግራይ ወጣቶችን ለጦርነት በግዳጅ እያፈሰና ወደ ሱዳን በመሸጥ አስከፊ ግፍ እየፈጸመ ይገኛል። በርካታ ወጣቶችም ይህን ግፍ በመስጋት አካባቢያቸውን ጥለው እየሸሹ ይገኛሉ። ወጣት ገብረኪሮስ ሕሉፍ ፤ ሕገ-ወጡ ቡድን እያፈጸመ ያለው የጦርነት ጉሰማና ግፍ በፈጸመው ወንጀል ላለመጠየቅ የሚያደርገው ጥረት መሆኑን ለኢዜአ ተናግሯል። የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የትግራይ ሕዝብን ፍላጎት ለመመለስ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስታውሶ፤ የፌደራል መንግሥትም በስምምነቱ የተቀመጡ ጉዳዮችን ሲፈጽም መቆየቱን ተናግሯል። በተቃራኒው ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን ግን ስምምንቱን በመጣስ ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ምንም ዓይነት ደንታ እንደሌለው በተግባር አሳይቷል ነው ያለው። የትግራይ ሕዝብ የሚሻው ሰላም ቢሆንም፣ ቡድኑ ከሕዝቡ ፍላጎት ውጭ ወጣቶችን በግዳጅ እያፈሰና ጦርነት እየቀሰቀሰ መሆኑንም ነው የተናገረው። ይህም የቡድኑን ውድቀትና በሕዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ማጣቱን ያመላክታል ብሏል። ሕገ-ወጥ ቡድኑ ከሻዕቢያና ከሌሎች ተላላኪ ሃይሎች ጋር በመሆን ጦርነት በመቀስቀስ የትግራይ ህዝብን ለከፋ ችግር ለመዳረግ እየተንቀሳቀስ መሆኑን የሚናገረው ወጣት ኪሮስ፤ በመሆኑም ይህን ሕገ-ወጥ ቡድን አምርረን ልንታገለው ይገባል ነው ያለው። ወጣት ፀጋልዑል በርሄ በበኩሉ፤ የትግራይ ህዝብ ሕገ-ወጡ ቡድንን ጦርነትና ውጊያ ይበቃናል በሚል አጥብቆ እየተቃወመው እንደሚገኝ ተናግሯል። ሕገ-ወጥ ቡድኑ የሚቃወሙትን ወጣቶች ብቻ ሳይሆን ልጆቻችንን ለምንድን ነው የምትወስዱት ብለው ጥያቄ እያነሱ ያሉ እናቶች ላይ ሳይቀር ግፍ እየፈጸመ ይገኛል ብሏል። የሕገ-ወጡ ቡድን አመራሮች እኛ ካልገዛንና ካልዘረፍን ወጣቱና ሕዝቡ አይኖርም በሚል በተለመደው እኩይ ተግባራቸው መቀጠላቸው የመጨረሻ ውድቀታቸውን የሚያሳይ መሆኑን በማንሳት፤ እኛ ወጣቶች በሕገ ወጥ ቡድኑ ላይ የጀመርነውን ተቃውሞና ትግል አጠናክረን መቀጠል አለብን በማለትም ጥሪ አቅርቧል።

ማህበራዊ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ የዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቀቀ
Aug 7, 2026 53
ወልቂጤ፣ ነሐሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን የክልሉን ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት በማድመጥ እና የዳኞች ሹመትን በማፅደቅ ተጠናቋል። የክልሉ ዋና ኦዲተር ወይዘሮ ፈዲላ አደም በጉባዔው ላይ እንደገለጹት፥ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በተከናወነው የኦዲት ሥራ ሊባክን የነበረ የመንግሥት እና የሕዝብ ሀብት መከላከልና ተመላሽ ማድረግ ተችሏል። የኦዲት ተደራሽነትና ሽፋኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ያመለከቱት ዋና ኦዲተሯ፣ በፋይናንስ ኦዲት፣ በገቢ ግብር፣ በታክስና በሊዝ አሰባሰብ እንዲሁም በዓይነትና በአካባቢ ኦዲት ላይ የተሻለ ቢሆንም አሁንም በዘርፉ የሚታየውን የአሰራር ክፍተቶች ለማረም መረባረብ እንደሚገባ አስረድተዋል። የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ በበኩላቸው፤ በክልሉ የኦዲት ግኝቶች ውጤታማ በሆነ መልኩ ምላሽ እንዲያገኙ የክልሉ ምክር ቤት ተገቢውን ድጋፍና እገዛ ማድረጉን ገልጸዋል። የመንግስት በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በቀጣይም የኦዲት ግኝቶች በሙሉ ተመላሽ እንዲሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በሙሉ አቅማቸው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ምክር ቤቱ የቀረቡ የዳኝነት ሹመቶችን ያጸደቀ ሲሆን፣ ዛሬ ከተሾሙት 65 ዳኞች መካከል ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስምንት፣ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት 13 እና ቀሪዎች 44 ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት መሆናቸው ተገልጿል። በጉባኤው ማጠቃለያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሲያገለግሉ ለነበሩ የምክር ቤት አባለት እውቅና ተሰጥቷል።
ጡት ማጥባት ሕፃናት የተስተካከለ እድገት እንዲኖራቸው የሚያስችል ተፈጥሯዊና ውጤታማ መንገድ ነው
Aug 7, 2026 55
ወልድያ፤ነሃሴ1/ 2018 (ኢዜአ) ፡-እናቶች ተፈጥሯዊ ስጦታቸው የሆነውን ጡት አጥብተው ልጆቻቸውን በማሳደግ ለአገር አለኝታ የሆነ ትውልድ ማፍራት እንደሚጠበቅባቸው የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ። መምሪያው በዓለም ለ35ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጡት ማጥባት ሳምንት አስመልክቶ ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 01 ቀን 2018 ዓ.ም የግንዛቤ መፍጠሪያ የውይይት መድረክ አካሂዷል። የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ ብርሃን ኃይሉ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ጡት ማጥባት የህፃናትን ጤንነትና ደህንነት በማስጠበቅ የነገ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ መሰረት የሚጥል ነው። የህጻናትን የተስተካከለ እድገት ለማረጋገጥና ጤናማ ትውልድ ለማፍራት ከፅንስ ጀምሮ ህጻኑ ተወልዶ እስከ ሁለት ዓመት ያለው ጊዜ የአመጋገብ ሁኔታን ማወቅ ለእናቶች አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። አንድ ህጻን ከተወለደ ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ድረስ ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናትን ጡት ብቻ መመገብ ተገቢ መሆኑን ጠቁመው፤ እስከ ሁለት ዓመት ከተጨማሪ ምግብ ጋር ማጥባት ወሳኝ ነው ብለዋል። የዘንድሮው በዓል ሲከበርም ጡት ማጥባት በህጻናት እድገትና በእናቶች ጤና ላይ የሚያስገኘውን ጥቅምና ፋይዳ ግንዛቤ ለመፍጠርና ለማበረታታት ያለመ መሆኑን አስረድተዋል። ይህም ጤናማ ትውልድ በመገንባት የማህበረሰብ ልማትንና የአገርን ዘላቂ እድገት ለማስቀጠል መሰረት በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል። በሰሜን ወሎ ዞን የሰቆጣ ቃል ኪዳን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ግዛቸው ታረቀኝ በበኩላቸው፤ ለሕፃናት የመጀመሪያው የበሽታ መከላከያ መንገድ የእናት ጡትን በተገቢው መንገድ መስጠት ነው። ለዚሁ ስኬትም ለእናቶች በቂ ምግብ፣ እረፍት እንዲያገኙና ልጆቻቸውን ጡት አጥብተው እንዲያሳድጉ የሚያደርግ ጊዜ መስጠት እንደሚገባ አስረድተዋል። ቃል ኪዳኑም የሚያጠቡና ነፍሰ ጡር እናቶችን በማቀፍ በጓሯቸው አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ፣ በፍየል እርባታና በንብ ማነብ በመሰማራት በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ እየደገፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የዞኑ ወጣት በጎ ፈቃደኞች ተወካይ ንግስት ይመር እንዳለችው፤ የውይይት መድረኩ በቀጣይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ያስችለናል ብላለች። “ጡት ማጥባት፤ ለዘላቂ የሕይወት ጅማሮ!” በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው ውይይት ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና የአጋር ድርጅት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በክልሉ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል
Aug 7, 2026 72
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የጤና አገልግሎት ተደራሽነትንና ፍትሃዊነትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱከሪም መንግስቱ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የዕድሳት የማስፋፊያ ግንባታና ዲጂታላይዜሽን ሥራ ምረቃ እና ሥራ ማስጀመሪያ መርሃግብር ተከናውኗል። በመርሃ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱከሪም መንግስቱ እንደገለጹት ለነገው ትውልድ ዘላቂና የማይበገር የጤና ስርዓት ላይ ለመገንባት እየተሰራ ነው። ፈጠራንና የአመራር ቅንጅትን በማጠናከር ጤናማ፣ አምራች፣ የበለጸገና ደስተኛ ማህበረሰብ ዜጋን ለመፍጠር በትጋት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል። በክልሉ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ለማስጠበቅ በተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ለውጦች መገኘታቸውን ገልጸዋል። እነዚህ ለውጦች የተገኙት መንግስት ቁርጠኛ እርምጃዎችን በመውሰዱና የለውጥ ሀሳቦችንና ተግባራትን ተግባራዊ በማድረጉ ነው ብለዋል። በዚህም ዜጎች ተደራሽ፣ ጥራት ያለውና ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት በአቅራቢያቸውና እና በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ማስቻሉን ተናግረዋል። የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎትን ማጠናከር፣ የጤና ተቋማትን ማስፋፋት፣ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያ አቅርቦትን ማሻሻል ላይ የተገኙ ስኬቶችንም አንስተዋል። በዚህም የጤና ተቋማት በህክምና መሳሪያዎች እጥረት ሳቢያ ቀደም ሲል የማይሰጡ አገልግሎቶችን መስጠት ችለዋል ብለዋል። ክልላዊና ሀገራዊ ኤንሼቲቮችን በመተግበርና ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ውጤቶችን ማሳደግ መቻሉንም ገልጸዋል። የተገኙ ውጤቶችን በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል በሀሳብ ከፍታና አንድነት እንተጋለን ብለዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል
Aug 7, 2026 76
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተደመረ አቅም በመንቀሳቀስ የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ፡፡ በሀረሪ ከልል በክረምት በጎ ፍቃድ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። በዚህ ወቅትም በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንደገለጹት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተደመረ አቅም ዜጎችን በማገዝና ሃብትን አቀናጅቶ በመምራት ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በተለይም በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ አቅመ ደካሞችንና አረጋዊያንን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ስራዎች እውን ማድረግ መቻሉን አንስተዋል። በዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። በመርሃ ግብሩም በ14 መስኮች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በዚህም በአሁኑ ወቅት የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት እድሳትና መልሶ ግንባታ፣ የአካባቢ ንጽህና ጥበቃ፣ ችግኝ ተከላ፣ ደም ልገሳ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና ሌሎች ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ማዕድ ማጋራት፣ አዳዲስና ነባር የመማሪያ ክፍል ግንባታ እና እድሳት፣ የትምህርት ቤቶች የተማሪ ወንበሮች ጥገና፣ ጽዳትና ውበት ስራዎችን ጨምሮ የማጣቀሻ መጽሀፍት የማሰባሰብ ስራ በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ መደጋገፍ፣ የመተጋገዝና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ጠቁመው የዜጎችን እውቀት፣ ገንዘብ፣ ጉልበት እና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎችን በሚገባ መጠቀምና ከድህነት መላቀቅ እንደሚያስፈልግ ነው የጠቆሙት። አመራሩም በመርሃግብሩ የታቀዱ እቅዶች ወደ ተግባር ለመቀየር በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለበት አሳስበዋል።
ኢኮኖሚ
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአርሶ አደሮችን ምርታማነት አሳድጓል
Aug 7, 2026 88
አለታ ወንዶ ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ያለፉት ዓመታት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ተግባራት ምርታማነታቸው እንዲጨምር ማድረጉን በደቡባዊ ሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ፡፡ በወረዳው የዊቾ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ታፈሰ ዩጤ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በየዓመቱ በግል ማሳቸውና በአካባቢው የወል መሬቶች ላይ ተከላ ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል። በዚህም በአካባቢያቸው ተራቁተው የነበሩ ቦታዎች ለምልመው ወደ አረንጓዴነት መቀየራቸውን ጠቁመዋል። በመርሃ ግብሩ የተከሏቸው የአቮካዶ፣ የማንጎ፣ የሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች አሁን ላይ ለምርት በመድረሳቸው ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደጋቸውን ገልጸዋል። የጎዋዳሞ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ካሰች ዳንሳሞ በበኩላቸው፤ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተከሏቸውን የፍራፍሬና የጥላ ችግኞች በመንከባከብ ለፍሬ እንዲበቁ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ችግኞቹ አድገው ለቡና ማሳቸው ጥላ ከመሆናቸውም በላይ፣ ፍራፍሬዎቹ ከምግብ ፍጆታ ባለፈ የገቢ ምንጫቸውን ለማሳደግ እንዳስቻላቸው አስረድተዋል። የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎችን በስፋት በማልማት ምርቱን ለኢንዱስትሪና ለሌሎች ገበያዎች እያቀረበ ተጠቃሚ መሆኑን ያነሳው ደግሞ የዶቤ ሰዴቃ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ወጣት ቹቹ ቢረጋ ነው። በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የፍራፍሬ ችግኞች በመትከል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል። የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደበበ ሻላ፤ በዞኑ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአካባቢ ሥነ-ምህዳር መጠበቁንና የአርሶ አደሩ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማደጉን ገልጸዋል። በዚም ለደንና ለምግብ የሚሆኑ ችግኞች መተከላቸውን በማንሳት፤ የአፈር ለምነትን ለመጠበቅና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ማስቻሉን ጠቅሰዋል። ለአብነትም በመርሃ ግብሩ ከተተከሉ ጥምር ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች መካከል የቡና ምርታማነት በአማካይ ከ8 ነጥብ 5 ወደ 9 ነጥብ 2 ማደጉን ተናግረዋል። በፍራፍሬ ምርትም አርሶ አደሮች በማኅበር በመደራጀት ምርታቸውን ለይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርት ኢንዱስትሪ ፓርክና ለአዲስ አበባ ገበያ እያቀረቡ ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙም አስረድተዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ለአሪ ዞን አርሶ አደሮች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ እየሆነ ነው
Aug 7, 2026 96
ጂንካ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ለአካባቢ ጥበቃ ካለው ፋይዳ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመሆን ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአሪ ዞን አርሶ አደሮች ገለፁ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ የጎምር ቀበሌ አርሶ አደር ታደሰ ሸዋዬ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ አካባቢያቸው ተራራማና ተዳፋት በመሆኑ በተደጋጋሚ ለአፈር መሸርሸርና ለጎርፍ አደጋ ሲጋለጡ ቆይተዋል። ባለፉት ዓመታት መንግስት የአካባቢውን አርሶ አደሮች በማሳተፍ በተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የአፈር መሸርሸርና ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭነታቸው እየቀነሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የተፋሰስ ልማት በተከናወነባቸው አካባቢዎች ፍራፍሬ በማልማት በአሁኑ ወቅት ገቢ እያገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ችግኝ በስፋት መትከል ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአካባቢያቸው ተጨባጭ ለውጦች መታየታቸውን የገለጹት ደግሞ አርሶ አደር ገዛህኝ ገሚጋንሶ ናቸው። ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በተከናወኑ ተግባራት ያገኘነውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በመገንዘብ ዘንድሮም ልማቱን አጠናክረን ቀጥለናል ያሉት አርሶ አደሩ፣ ልማቱ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ሙዝ፣ አቮካዶ እና ቡና ተክለው በማልማት ተጨማሪ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ይህን ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በየዓመቱ በመርሀግብሩ የሚያደርጉትን ተሳትፎ እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል። አካባቢው በስፋት ቡና አብቃይ በመሆኑ ለእርሻ ሥራ ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች ጭምር ቡና ተክለው እያለሙ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላው የቀበሌው አርሶ አደር ነሽራይ ከራልቆ ናቸው። ባለፉት ዓመታት የተከሏቸው የቡና ችግኞች ምርት መስጠት እንደጀመሩ ጠቅሰው፣ ቡና ካስገኘላቸው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንጻር በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብርም በስፋት መትከላቸውን ተናግረዋል። ቀደም ሲል በአካባቢው በተራቆቱ አካባቢዎች የደን ችግኞችን ብቻ የማልማት ልምድ እንደነበር ያስታወሱት ደግሞ አርሶ አደር ማርታ ማቲዮስ ናቸው። ለደን ልማት ብቻ የሚያገለግሉ ችግኞች ጥቅማቸው ውስን በመሆኑ አሁን ላይ ለምግብነት፣ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለገቢ ምንጭነት የሚውሉ ችግኞችን ጭምር በማልማት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። የአሪ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅ በበኩላቸው እንዳሉት የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብርን ተከትሎ በዞኑ እንደ ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ ማንጎ እና አፕል ያሉ ፍራፍሬዎች በስፋት እየለሙ ይገኛሉ። ይህም የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ካለው ፋይዳ ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን እያሳደገው መምጣቱን ተናግረዋል። የሀገር በቀል ዛፎች እንደ ኮሶ፣ ዋንዛ፣ ጽድ እና ዝግባ ያሉና ሥነ-ምኅዳርን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ችግኞች በተራቆቱ ተራራማ አካባቢዎች በስፋት እየተተከሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የአካባቢ ጥበቃ ሥራውን ከዘመናዊ የንብ ማነብ ሥራ ጋር በማስተሳሰር አርሶ አደሮች በዘርፉ ተሰማርተው ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ጉራልቅ አስታውቀዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችንን እያረጋገጠ ነው
Aug 7, 2026 85
አርባምንጭ ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት መርሃ ግብር የአካባቢያችንን ሥነ-ምህዳር በማስተካከል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችንን እያረጋገጠ ነው ሲሉ የጋሞ ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ። በዞኑ የጋጮ ባባ ወረዳ የጋጼ ቀበሌ ነዋሪዎች አርሶ አደር አልቤ አለሙ እና አርሶ አደር አቡሽ አማሮ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ለሰብል ምርትና ለእንስሳት መኖ ልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል። መርሃ ግብሩ የደን ዛፎችን በመትከል ገላጣ የነበሩ ተራሮች እንዲለሙ ማደረጉን ጠቁመው፤ የአቮካዶ፣ የማንጎ እና የአፕል ፍራፍሬ ችግኞችን በማልማት የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ ማስቻሉን ገልጸዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የደን ሽፋን እንዲጨምር በማድረጉ በንብ ማነብ ሥራ ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ በምዕራብ አባያ ወረዳ የ«ጦይሎ» ንብ አናቢ ማኅበር ሰብሳቢ አቶ ደሴ ኡታሎ ናቸው። ማኅበሩ በ52 አባላት በ2014 ዓ.ም መመስረቱን የጠቀሱት ሰብሳቢው፤ አሁን ላይ በ19 ሄክታር ደን ውስጥ ንብ ከማነብ ባለፈ የደን ጥበቃ ሥራ እያከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የሚያመርቱትንም ማር ለአካባቢው ገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ በማግኘታቸው አባላቱ በከተማ መኖሪያ ቤት መገንባታቸውንና የሸቀጥ ሱቆችን መክፈታቸውን ገልጸዋል። የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ማጌሶ ማሾሌ በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና ኢኮኖሚያዊ አቅምን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ድርሻ እያበረከተ መሆኑን አስረድተዋል። መርሃ ግብሩ የዞኑን የደን ሽፋን በማሳደግ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ የልማት ስራዎች እንዲተገበሩ፣ እንዲሁም የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙ በማድረጉ የከርሰ ምድር ውሃ መጠንና የአፈር ለምነት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። በዚህም ምርትና ምርታማነት ከመጨመሩም ባሻገር አርሶ አደሩ በንብ ማነብ ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻሉን አክለዋል። በተጨማሪም በዞኑ የሚገኙ ተራሮች እየለሙ በመምጣታቸው በአባያና ጫሞ ሀይቆች ህልውና ላይ አደጋ እያስከተለ የነበረው የደለል አፈር በእጅጉ መቀነሱን አቶ ማጌሶ ገልጸዋል።
አገልግሎቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል
Aug 7, 2026 130
አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን አስታወቀ። አገልግሎቱ የ2018 በጀት ዓመት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት እና የፋይናንስ አፈጻጸሙን እንዲሁም በ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱ ዙሪያ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፤ አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ በተከናወኑ በርካታ ተግባራት የደንበኞቹን ቁጥር 5 ነጥብ 88 ሚሊየን ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል። ከደንበኞች አገልግሎት አንጻር በቅድመ ክፍያ 82 ነጥብ 6 እንዲሁም በድህረ ክፍያ 15 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱንም አክለዋል። በበጀት ዓመቱ 664 ሺህ 505 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸው፤ ይህም ከዕቅዱ አንጻር 83 ነጥብ 1 በመቶ መከናወኑን ተናግረዋል። አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ 118 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ለደንበኞች ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ መሰብሰቡን ተናግረዋል። በኤሌክትሪክ ሀይል ማሰራጫ መስመር መሰረተ ልማት ዝርጋታና ጥገና ላይም ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል። በዚህም ያረጁ የማሰራጫ መስመሮችን ከመጠገን አንጻርም በበጀት ዓመቱ 4 ሺህ 892 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ የጥገና ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
አዲስ አበባ የ"ስማርት ሲቲ" ግንባታ ልምዷን ለቤኒን ሪፐብሊክ አካፍላለች
Aug 7, 2026 96
አዲስ አበባ፤ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቤኒን ሪፐብሊክ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ኢኖቬሽን እና ፈጠራ ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን ለተመራ የልዑክ ቡድን አዲስ አበባ እየተገበረች ያለውን ስማርት ሲቲ ግንባታ ጋር በተያያዘ ልምድ አካፍለዋል። ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ቤኒን የጀመረችውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት በከተማችን ተግብረነው ውጤታማ እየሆነ ያለውን Smart City (ስሉጥ ከተማ) ግንባታን በተመለከት ልምድ ማካፈላቸውን ገልጸዋል። በተለይም በዋና ዋና ግቦች (Smart Economy, Smart Environment, Smart Governance, Smart Living, Smart Mobility, Smart People) እና ለስኬቶቻችን መሰረት የሆኑት የተቋማት ቅንጅት፣ የህጎችና ደንቦች ትግበራ፣ የሕዝብ ተሳትፎ፣ የመንግሥትና የግል ዘርፍ ቅንጅታዊ ሥራዎችን ለልዑክ ቡድኑ አካፍለናል ነው ያሉት።
የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር ጉልህ ሚና ይኖረዋል
Aug 7, 2026 125
አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ የሳይበር ደህንነትን በማረጋገጥ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ። ዋና ዳይሬክተሯ ትዕግስት ሃሚድ አዋጁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ አዋጁ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን ጠቅሰዋል። ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ጉዞ በጠንካራ የሳይበር ደህንነት መሰረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል መሆኑንም አንስተዋል። የዲጂታል መታወቂያ መርሃ ግብር፣ የሞባይል ክፍያና የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት እና መሰል ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ዳታ እንደሚያመነጩ አመልክተው፤የእነዚህን መረጃዎች እና ሲስተሞች ደህንነት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል። በመሆኑም የአዋጁ ወደ ስራ መግባት የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የዜጎች እና የሀገርን መረጃ ከጥቃት በመጠበቅ የመረጃ ሉዐለዊነትን ለማረጋገጥ ትልቅ እርምጃ መሆኑን አብራርተዋል። በቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚቃጡ ጥቃቶች እየጨመረ መምጣት ለአዋጁ መውጣት ምክንያት መሆኑን ገልጸው፤አዲሱ አዋጅ የሳይበር ስጋትን መሰረት ያደረገ ቁጥጥር እና የተማከለ የክስተት ምላሽ ስርአትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በአዋጁ መሰረት አስተዳደሩ ቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማት ማሟላት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ማገዝ ፣ ለቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ የሚረዱ መመሪያዎችና ስታንዳርዶችን ማዘጋጀት በህግ ማዕቀፉ ከተካተቱ ጉዳዮች መካከል እንደሚገኝበት አክለዋል። በቁልፍ መሰረተ ልማት ጥበቃ ዙሪያ ብቁ ባለሙያና በስነ ምግባር የታነጸ የሰው ሃይል የማደረጀት ስራዎች ይሰራሉም ብለዋል። በአዋጁ ዙሪያ ለህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባራት እንደሚከናወኑም ገልጸዋል። ቁልፍ መሰረተ ልማት ባለቤት የሆኑ ተቋማት ደግሞ የሰለጠነ ባለሙያ ማሰማራት፣ማብቃት እና ተገቢውን ደህንነት ማጣሪያ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አዋጁ እንደሚደነግግም ጠቁመዋል። ከሳይበር ጥቃት ራሳቸውን መጠበቅ የሚችሉበት ቴክኖሎጂዎችን መታጠቅ ከተቋማቱ የሚጠበቅ ሌላው ሃላፊነት መሆኑን አብራርተዋል።
የሲቪል ምዝገባ የዲጂታል ስርዓት ዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ ነው
Aug 6, 2026 222
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የጀመረው ዲጂታል የአሰራር ስርዓት ዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አሰራሩን ለማዘመንና ለማቀላጠፍ አገልግሎቶቹን በኦንላይን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የኦንላይን አገልግሎቱ ገፅ ለ ገፅ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተሻለ ሁኔታ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው በሞባይል፣ በላፕቶፕና በሌሎች ዲጂታል መሳሪያዎች በአጭር ጊዜ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሤ ለኢዜአ እንደገለጹት ፤ ተቋሙ በአጠቃላይ ከሚሰጣቸው ሰባት ዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል በአሁኑ ወቅት የመታወቂያ፣ የልደት እና ያላገባ ማረጋገጫ አገልግሎቶችን በኦንላይን እየሰጠ ይገኛል። እስከ አሁን ከ15 ሺህ በላይ ተገልጋዮች በኦንላይን ሥርዓቱ አገልግሎት ማግኘታቸውን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፤ አዲሱ አሰራር የተገልጋዮችን ጊዜና ወጪ ከመቆጠቡም በላይ እንግልትን እያስቀረ መሆኑን አስረድተዋል። በተጨማሪም አሰራሩ ለባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታ በመፍጠር የሥራ ቅልጥፍናንና ውጤታማነትን ማሳደጉን ገልጸዋል። ኤጀንሲው መረጃዎችን በዲጂታል ሥርዓት በማደራጀት ዘመናዊ የኦንላይን አገልግሎቶችን በስፋት ተደራሽ የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። በቀጣይም የጋብቻ፣ የፍቺ፣ የሞትና የጉዲፈቻ አገልግሎቶችን ጨምሮ ሌሎችንም አገልግሎቶች ወደ ኦንላይን ሥርዓት በማስገባት ተደራሽነታቸውን ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከጤና ተቋማትና ከፍርድ ቤቶች ጋር በመቀናጀት እንደ ልደትና ሞት ያሉ ኩነቶች በተከሰቱበት ቦታ ላይ በቀጥታ እንዲመዘገቡ የሚያስችል አሰራር እየተጠናከረ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል። በኤጀንሲው እየተከናወነ ያለው ይህ የዲጂታል ሽግግር የኢትዮጵያን የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ እና የከተማዋን የስማርት ከተማ ግንባታ ግብ እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረውም አብራርተዋል፡፡ አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ በመገናኛ ብዙኃንና በተለያዩ አማራጮች ህብረተሰቡ ስለ ኦንላይን አገልግሎቱ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ሀገሪቱ ግቧን በፍጥነት ለማሳካት የምታደርገውን ጥረት ያሳያል
Aug 5, 2026 415
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ ዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሀገሪቱ ግቧን በፍጥነት ለማሳካት የምታደርገውን ጥረት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን የቤኒን የዲጂታል ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን ገለጹ፡፡ በቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የአምስት ቀን የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ሚኒስትሩና የልዑካን ቡድናቸው በኢፌዴሪ መሶብ አገልግሎትና በፋይዳ ቨርስ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ፈጣን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግር እየተደረገ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በአጭር ጊዜ አስገራሚ የዲጂታል መሰረተ ልማት በመገንባትና ፈጣን የመንግሥት አገልግሎት ስርዓት ላስመዘገቡት ዕምርታ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያና ቤኒን መካከል ያለው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክፍተት በጋራ መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ልምድ መለዋወጥ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሀገሪቱ ግቧን በፍጥነት ለማሳካት የምታደርገውን ጥረት በግልጽ እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዲጂታል መሰረተ ልማት እያደገች መሆኑን መታዘባቸውን በመጥቀስ፤ ከዚህ መማር አጀንዳችንን ለማቀላጠፍ ያግዘናል ብለዋል፡፡ ቤኒን በሳይበር ደህንነት ያላትን ጠንካራ አቅም ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለማሳደግ በአቅም ግንባታና በዕውቀት ልውውጥ በጋራ መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ የፋይዳ ቨርስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮዳሔ አርዓያሥላሴ በበኩላቸው፤ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ለዲጂታል ዲፕሎማሲ አቅም ግንባታ የጎላ አበርክቶ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ብዙ የተለመደው ከአውሮፓ ወይም ከኤዥያ የሚመጣን ስርዓት ማስተዳደር ነው ያሉት አቶ ዮዳሔ፤ ቴክኖሎጂን በራስ አቅም መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ሁሉም መገንዘቡን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የራሷን ቴክኖሎጂዎች በማፍለቅ ለሌሎች ትምህርት መስጠቷ አፍሪካውያን በራሳቸው እንዲተማመኑና ዕምነት እንዲኖራቸው ያስችላል ብለዋል፡፡ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ስያሜውንና ተልዕኮውን በመቀየር ራሱን ችሎ የመንግሥት የልማት ድርጅት ሆኖ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሥር መካተቱን አንስተዋል፡፡ ይሄውም አገልግሎቱን ከኢትዮጵያ ውጪ በማስፋት በአፍሪካ ሀገራት ጭምር የማማከርና ስርዓት የመገንባት ዕድሎችን የምናገኝበት ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ የኢፌዴሪ የመሶብ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ አለማየሁ፤ መሶብ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን አሻሽሏል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ 108 የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በመክፈት ከ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ማገልገል ተችሏል ብለዋል፡፡ ከ220 በላይ አገልግሎቶችን በላቀ ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊ አሰራር በመስጠት የተገልጋዮችን እርካታ 98 በመቶ ማድረስ እንደተቻለም ገልጸዋል፡፡ መሶብ የኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የመሻገር ህልም መሆኑን ገልጸው፤ የአፍሪካ ሀገራት ልምድ የሚወስዱበትና የዲፕሎማሲ ተግባቦት የሚፈጠርበት ነው ብለዋል፡፡ የቤኒን ብቻ ሳይሆን የሌሎች ዓለም ሀገራት ጭምር አይተው የሚደነቁበት መሆኑን በማንሳት ጉብኝቱ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ ብዙ ርቀት መጓዟን እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያውያን ኢንጂነሮችና በኢትዮጵያ ሀብት የለማ መሆኑ ኢትዮጵያውያን እውቀትና አቅማችንን አስተባብረን መስራት እንደምንችል አሳይቷል ብለዋል፡፡
ስፖርት
ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል
Aug 6, 2026 157
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ)፦ የ2026/27 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እና የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ በግብጽ ካይሮ ተካሄዷል። በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፈው ሲዳማ ቡና ከቻዱ ክለብ ኤግሎንስ ጋር ይጫወታል። ሲዳማ ቡና በደርሶ መልስ ውጤት ድል ከቀናው በቀጣዩ ዙር ከቡሩንዲው ኤግሌ ኖይር እና ከሱዳኑ አል ሂላል አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል። የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሲዳማ ቡና በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሱዳኑ አል ሂላል አልሳሂል ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። ወልዋሎ ወደ ቀጣዩ ዙር ካለፈ ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም እና ከሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል። የዘንድሮው የኢትዮጵያ ዋንጫ ባለቤት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን በነሐሴ 2018 ዓ.ም እና መስከረም 2019 ዓ.ም ያከናውናሉ።
ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች
Aug 6, 2026 168
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 አመት በታች ሻምፒዮና ትናንት ማምሻውን በአሜሪካ ኦሬጎን ተጀምሯል። ዛሬ ማለዳ ላይ በተካሄደው የሴቶች 5000 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ሽቶ ጉሚ 15 ደቂቃ ከ07 ሴኮንድ ከ21 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። በዚሁ ውድድር ላይ የተሳተፈችው አትሌት እመቤት ጥላሁን 15 ደቂቃ ከ32 ሴኮንድ ከ51 ማይክሮ ሴኮንድ ስድስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ዩጋንዳዊቷ አትሌት ቻሪቲ ቼሮፕ 15 ደቂቃ ከ03 ሴኮንድ ከ88 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ወጥታለች። ኬንያዊቷ ጆይሊን ቼፕኬሞይ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። በወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ዳምጠው ከበደ 13 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ ከ38 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቷል። በርቀቱም የግል ምርጥ ሰዓቱን አስመዝግቧል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ማማሩ ጎዴ 13 ደቂቃ ከ44 ሴኮንድ ከ41 ማይክሮ ሴኮንድ አምስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ኬንያዊው አትሌት ፍራንክሊን ኪቤት 13 ደቂቃ ከ28 ሴኮንድ ከ27 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል። ሌላኛው ኬንያዊ ኔሄሚያ ኪፕጌንዮ ሁለተኛ ወጥቷል። ከፍጻሜው በተጨማሪም በሻምፒዮናው መክፈቻ የማጣሪያ ውድድሮች ተደርገዋል። በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል የመጀመሪያ ማጣሪያ አትሌት አልማዝ ዮሀንስ 9 ደቂቃ ከ42 ሴኮንድ ከ45 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት ወደ ፍጻሜ አልፋለች። አትሌት ወሰኔ አሰፋ 9 ደቂቃ ከ56 ሴኮንድ ከ36 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ፍጻሜው ውድድር ተሸጋግራለች። የፍጻሜው ውድድር ነገ ይካሄዳል። በወንዶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ማጣሪያ የተሳተፈው አትሌት ነጋሄ እያሱ 1 ደቂቃ ከ51 ሴኮንድ ከ16 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፏል። በሌላኛው የወንዶች 800 ሜትር የማጣሪያ ምድብ የተሳተፈው የሮሰን ግርማ 1 ደቂቃ ከ47 ሴኮንድ ከ57 ማይክሮ ሴኮንድ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። በሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ማጣሪያ የተሳተፈችው ደራርቱ ሽብሩ 2 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ ከ28 ማይክሮ ሴኮንድ አምስተኛ በመውጣት ወደ ፍጻሜው አልፋለች። እንዲሁም በሴቶች 800 ሜትር ምድብ አራት የተወዳደረችው ሀብታም ገበየሁ 2 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ ከ66 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ተሸጋግራለች። የ800 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያ ውድድሮች ነገ ይካሄዳሉ።
በዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና የመክፈቻ ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ
Aug 5, 2026 229
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ከዛሬ ጀምሮ በአሜሪካ ኦሬጎን ይካሄዳል። ዛሬ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በሄይዋርድ ፊልድ ስታዲየም በሚጀመረው ሻምፒዮና ላይ ከ147 ሀገራት የተውጣጡ ከ1800 በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ። ኢትዮጵያም በሻምፒዮናው ላይ በ5000 ሜትር፣ 3000 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 800 ሜትር (በሁለቱም ፆታዎች)፣ 3000 ሜትር መሰናክል (በሴቶች)፣ 400 ሜትር (በሴቶች) እንዲሁም በርምጃ ውድድር (በሁለቱም ፆታዎች) ትሳተፋለች። በውድድሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ትናንት ኦሬጎን ደርሷል። በሻምፒዮናው መክፈቻ ቀን በሁለቱም ጾታዎች የ5000 ሜትር የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ። ንጋት 11 ሰዓት ከ53 ላይ በ5000 ሜትር ሴቶች አትሌት ሽቶ ጉሜ እና አትሌት እመቤት ጥላሁን ይወዳደራሉ። በአጠቃላይ 27 አትሌቶች በፍጻሜው ውድድር ላይ ይሳተፋሉ። ነገ ጠዋት 12 ሰዓት ከ20 ላይ በሚደረገው የወንዶች የ5000 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ዳምጠው ከበደ እና አትሌት ማማሩ ጎዴ የሚሳተፉ ይሆናል። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የማጣሪያ ውድድሮች ይከናወናሉ። ምሽት 4 ሰዓት ከ35 ላይ በሚካሄደው የ800 ሜትር ወንዶች የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ነጋሄ እያሱ እና የሮሳን ግርማ ይሳተፋሉ። በአምስት ምድቦች ተከፍሎ በሚደረገው የማጣሪያ ውድድር ከየምድቡ ከአንድ እስከ አምስት የሚወጡ አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያው በቀጥታ ያልፋሉ። ምርጥ ሰዓት ያስመዘገቡ ሁለት ተጨማሪ አትሌቶች ግማሽ ፍጻሜ ይገባሉ። ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ በሚደረገው የ800 ሜትር ሴቶች የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ደራርቱ ሽብሩ እና ሀብታም ገበየሁ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። በአምስት ምድቦች በሚካሄደው የማጣሪያ ውድድር፣ ከእያንዳንዱ ምድብ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ የሚወጡ አትሌቶች በቀጥታ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ያልፋሉ። ከዚህ በተጨማሪ፣ የተሻለ ሰዓት ያስመዘገቡ ሁለት ተጨማሪ አትሌቶች ግማሽ ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ። 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። እ.አ.አ በ2024 በፔሩ ሊማ በተካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 6 የወርቅ፣ 1 የብር እና 2 የነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም ሁለተኛ በመሆን ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።
በበጀት ዓመቱ ህብረ-ብሔራዊ አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክሩ ተግባራት ተከናውነዋል
Aug 5, 2026 189
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ) ፦ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ህብረ-ብሔራዊ አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክሩ ተግባራት መከናወናቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገለፁ። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት እና የቀጣይ ሶስት ዓመት የመካከለኛ ዘመን እና ዓመታዊ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በዚሁ ወቅት፤ በጉባኤው የባህል፣ የጥበባት እና ስፖርት ለሀገር ኢኮኖሚና ማህበራዊ ህይወት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ በሳይንሳዊ መንገድ ለመደገፍና በቀጣይ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመቀየስ የሚያስችል ውይይት እንደሚደረግበት ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ያነሱት ሚኒስትሯ፤ በበጀት ዓመቱ 47 የብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላት እና 5 ሀገር አቀፍ ክብረ በዓላት በተሳካ መንገድ መከበራቸውን ተናግረዋል። በነዚህ በዓላት ላይ ከ46 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በመሳተፍ ህብረ-ብሔራዊ አብሮነትን ይበልጥ ማጠናከሩን አስረድተዋል። በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ባለፉት 28 ዓመታት ስራ ላይ የነበረው የስፖርት ፖሊሲ መሻሻሉን ገልጸው፤ ፖሊሲው ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ታስቦ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በ2019 በጀት ዓመት ሙሉ ተቋማዊ ሪፎርም የማድረግና አሰራሮችን የማዘመን ስራዎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው እንደሚከናወኑ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ በበኩላቸው፤ በበጀት ዓመቱ ስፖርት ቱሪዝምን ማስፋፋት የሚያስችሉ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ባለሃብቶች ወደ ስፖርቱ ዘርፍ በብዛት እንዲገቡ የማበረታታት ስራ መሰራቱን ጠቅሰው 29 ዓለም አቀፍ የስፖርት ኮንፈረንሶችና ውድድሮች በኢትዮጵያ መካሄዳቸውን አብራርተዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የህዝብን አቅም በማስተባበር የተከናወነ ታሪካዊ ስኬት ነው
Aug 7, 2026 110
ጅማ ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በመደመር መንግስት እሳቤ የህዝብ አቅምን በማስተባበር የተከናወነ ታሪካዊ ስኬት መሆኑን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ። የመደመር መንግሥት የተበታተነን አቅም በማቀናጀትና የዜጎችን ንቁ ተሳትፎ በማጎልበት፣ በአንድ ቀን ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን መትከልን የመሰሉ በተግባር የተገለፁና የሚገለፁ እውነታዎችን የያዘ እሳቤ ነው። ይህም የኢትዮጵያውያን በጋራ መቆም፣ የውስጥ አቅምን አሟጦ መጠቀም እና የትብብር ባህልን ማሳደግ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚያስችል በተግባር ያረጋገጠና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነው። ምሁራኑ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት እንደገለፁት፤ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በመደመር መንግሥት እሳቤ የሕዝብ አቅምን በማስተባበር የተከናወነ ታሪካዊ ስኬት ነው። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ጥናት ትምህርት ክፍል መምህር ጌታቸው ጥላሁን (ዶ/ር) ፤ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በመደመር መንግሥት እሳቤ የሕዝብ አቅምን በማስተባበር የተከናወነ ታሪካዊ ስኬት ነው ብለዋል። ይህንንም ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ለሀገራዊ ጥሪው ስኬት የድርሻውን በመወጣት ማሳየቱን ተናግረው ከመንግሥት ጎን በመቆምም ለኢኮኖሚው ዕድገት ያለውን ቁርጠኝነት መግለፁን ጠቁመዋል። ሕዝቡ በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ያሳየውን የተቀናጀ መረዳዳትና ከፍተኛ ተሳትፎ፣ በሀገር ግንባታ፣ በኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሁም በሕብረተሰብ አቀፍ በጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ማስቀጠል የሚገባው መሆኑን አስረድተዋል። ባለፉት ዓመታት እየጎለበቱ የመጡትን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የማዕድ የማጋራት እንቅስቃሴዎችን በምሳሌነት የጠቀሱት ምሁሩ፤ በጥቂቱ ታስቦ የተጀመረው ሥራ ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደሚችል ማሳያ ነው ብለዋል። በተለይም በሁሉም ዘርፎች የተጀመሩ ዘላቂ የልማት ስራዎችን ከዳር ለማድረስ የዜጎች ሕብረትና አንድነት ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት ምሁሩ፤ ይህ የሕዝቡ ቀናነትና ለልማት የመቆም ባህል በሁሉም መስክ ሊስፋፋ እንደሚገባም አመልክተዋል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሥነ-ምግብ መምህርና ተመራማሪ ዋሲሁን ሀሰን (ዶ/ር)፤ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ትልቅ ሀገራዊ ድል በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን በጋራ በመቆም የተቀዳጁትን የዓድዋን ድል የሚያስታውስ ነው ብለዋል። ሕዝባዊ ትብብርና መግባባት በሚገባ ከተፈጠረ በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ገልፀው ይህንንም ለሀገር ዕድገትና ብልፅግና ማዋል እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅም እየተገነባ ነው
Aug 6, 2026 177
ሀዋሳ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥና ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል አቅም እየተገነባ መሆኑን የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። የሚኒስቴሩ እና የተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የአረንጓዴ አሻራና የበጎ አድራጎት መርሃ ግብርን በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በሸበዲኖ ወረዳ አካሄደዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥና ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል አቅም እየተገነባ ነው። በየዓመቱ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እየተተከለ ያለው ችግኝ የአካባቢ መራቆትና የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ የውሃ ምንጮችን በማጎልበት የውሃ ሀብት መጠንን ያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ የዛሬውም መርሃ ግብር የዚሁ አካል እንደሆነ ጠቁመዋል። ከችግኝ ተከላው ጎን ለጎንም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሚኒስቴሩ አጋዥ የሌላቸው ወገኖችን በመደገፍ አጋርነቱን እያሳየ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በዛሬው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሚኒስቴሩ በሸበዲኖ ወረዳ ዲላ አፈራራ ቀበሌ የሰባት አቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት አፍርሶ ለመገንባት መረከቡንና ቤቶቹ ደረጃቸውን ጠብቀው ተገንብተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ርክክብ እንደሚደረግም ገልጸዋል። የሲዳማ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ከበደ ጋኖሌ በበኩላቸው፤ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለፉት አምስት ዓመታት በመጠጥ ውሃና ኢነርጂ አቅርቦት ረገድ በክልሉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል። በዚህም የክልሉ የመጠጥ ውሃ ሽፋን ወደ 75 በመቶ ማደጉንና በኢነርጂው ዘርፍ እየገነባቸው ካሉ አምስት ፕሮጀክቶች ሁለቱ ተመርቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ገልጸዋል። በሚኒስቴሩ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ የውብዳር አሚኖ፤ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በአካባቢው የገጽና ከርሰ ምድር ውሃን በማጎልበት ውሃ ፍለጋ ረጅም ርቀት የሚጓዙ እናቶችን ድካም አስቀርቷል ብለዋል። የሰሜን ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፃዲቁ ባጢሶ፤ ሚኒስቴሩ በመጠጥ ውሃ አቅርቦትና በኢነርጂው ዘርፍ እያከናወነ ያለው ተግባር በዞኑ በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረጉን ጠቁመው፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በችግኝ ተከላው እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በሸበዲኖ ወረዳ የዲላ አፈራራ ቀበሌ ነዋሪው አቶ አበራ ካሼራ ቤታቸው በመፍረሱ በክረምት ዝናብና ብርድ ሲፈተኑ መቆየታቸውን ገልጸው አሁን ቤታቸውን ሊታደስላቸው በመሆኑ መደሰታቸውን ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ ለ500 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን፣ የሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ ሠራተኞች የፍራፍሬና ሌሎች ሀገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሀገራዊ ግብን በተደመረ አቅም የማሳካት ባህልን እያጎለበተ ነው
Aug 6, 2026 412
ሮቤ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሀገራዊ ግብን በተደመረ አቅም የማሳካት ባህልን ከማጎልበት ባሻገር ለቀጣዩ ትውልድ አሻራ ማኖርን ያስተማረ ነው ሲሉ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ። ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው ይታወሳል። በዚህም ሀገሪቱ ከራሷ አልፋ ለመላው አፍሪካ ታላቅ ምሳሌ ለመሆን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብስረዋል። የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን አንድምታ በተመለከተ ኢዜአ ከመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን ጋር ቆይታ አድርጓል። ምሁራኑ እንዳሉት፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ሀገራዊ ግብን በተደመረ አቅም የማሳካት ባህልን ከማጎልበት ባሻገር ለቀጣዩ ትውልድ አሻራ ማኖርን ጭምር ያስተማረ ነው። ከዩኒቨርሲቲው ምሁራን መካከል የውኃና አካባቢ ጥበቃ ረዳት ፕሮፌሰር አለማየሁ አባታ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሲቆሙ ተአምር መስራት እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ ነው። በሀገሪቱ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በየጊዜው በሚተከሉ ችግኞች የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ እያገዘ መምጣቱንም ገልጸዋል። በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል፣ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግና የሥራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን አብራርተዋል። የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን በአንድነት ለተመሳሳይ ዓላማ ሲቆሙ ተአምር መስራት እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ነው ያስረዱት። በሀገሪቱ ዜጎች በ"ይቻላል" መንፈስ እውን የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የዚሁ ህብረትና የተደመረ ሀገራዊ አቅም ማሳያ እንደሆነ አውስተዋል። በዩኒቨርሲቲው የአካባቢ ሳይንስ መምህርና የደን ዘርፍ ተመራማሪው አቶ ኡመር አብደላ በበኩላቸው፣ ሀገሪቱ እያሳካችው ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር ዘለቄታዊና ሁለንተናዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመታት በዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት የአፈር ለምነትን በመጠበቅና የመሬት መራቆትን በመከላከል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተሰሩ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች መታየት መጀመራቸውን አክለዋል። እንዲሁም ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነውን የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅን በመቋቋም የግብርና ምርታማነትን ማሳደጉን አመልክተዋል። በተጨማሪም በደንና አካባቢ ጥበቃ ዘርፍ በተሰሩ ሥራዎች ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ከመቻሉም ባሻገር፣ ህዝቡ ለአንድ ሀገራዊ ግብ በጋራ ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ የህብረትና የአብሮነት ባህሉን የሚያጠናክርበት ትልቅ መድረክ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል። ምሁራኑ እንዳመለከቱት፣ እነዚህ ስኬቶች ኢትዮጵያውያን በራሳቸው እቅድ፣ አቅምና በጸና ህብረት ከተንቀሳቀሱ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚችሉ በተግባር ያረጋገጡ ማሳያዎች ናቸው።
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የብዝሃሕይወት መመናመንን በመከላከል ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው
Aug 6, 2026 188
አሶሳ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ብክለትን እና የብዝሃሕይወት መመናመንን በመከላከል ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። ንቅናቄው የህብረተሰቡን የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ እያሳደገ መምጣቱም ተመላክቷል። የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢ፣ ደን ሃብት ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ጋር በመተባበር "ጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" በሚል መሪ ሃሳብ 3ኛውን ዙር የአካባቢ ብክለት መከላከል የ6 ወራት ንቅናቄ አስጀምሯል። የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ እንደተናገሩት፤ የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሥራን ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ አበረታች ውጤት አስገኝቷል። የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ብክለትን፣ የብዝሃሕይወት መመናመን እና የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል። ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (COP-32) በፈረንጆቹ ህዳር 2027 ለማዘጋጀት መመረጧ በአገር አቀፍ ደረጃ ለምታከናውናቸው ውጤታማ የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች የተሰጠ ትልቅ ዓለም አቀፍ እውቅና መሆኑንም ጠቁመዋል። ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና ብዝሀ ህይወትን ለመጠበቅ በትኩረት መሰራቱን ያነሱት ደግሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢ፣ ደን ሃብት ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሉቅማን አብዱልቃድር ናቸው። የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን በማዘመን አካባቢን ውብ እና ጹዱ ከማድረግ ባለፈ ጤናማ ማኅበረሰብን ለመገንባት የተጀመረውን ጥረት ማጠናከር እንዳስቻለም ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 332
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 374
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች። ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 685
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል - አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና
Jul 29, 2026 1147
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርጉ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው እና የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ምክር ቤቱ አጀንዳ 2063 እና የህብረቱ መሪ ሀሳብን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የእርስ በእርስ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያሳዩት ፍላጎት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ በበጎ ፈቃደኝነት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይፋ ማድረጋቸው የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት የኢትዮጵያንና የኬንያን ፈለግ በመከተል ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራት የገቧቸውን ቃል ኪዳኖችና ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መተግበር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ለሚኒስትሮችና ሌሎች ልዑካን ላደረገችው አቀባበልም አመስግነዋል።
ሐተታዎች
ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የአፍሪካ ኃያል ሀገር እየሆነች ነው-ታዋቂው የህንድ ሚዲያ ፈርስት ፖስት
Aug 7, 2026 147
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሪነት የመጪው ዘመን የአፍሪካ ኃያል ሀገር ወደመሆን እየተሸጋገረች ነው ሲል ታዋቂው የህንድ ሚዲያ ፈርስት ፖስት ዘግቧል። ፈርስት ፖስት ሚዲያ ኢትዮጵያን በተመለከተ በሠራው ትንታኔው የሰው ዘር መገኛ፣የጥንታዊ መንግስታት ምድር፣የንግድ መስመሮች እና ከፍ ያለ የአፍሪካ ታሪካዊ መሰረት ያላት ሀገር መሆኗን አውስቷል። ሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከቀድሞ ገናና ታሪኳ እኩል ታላቅ የሆነ አዲስ ምዕራፍ ለመገንባት በትጋት ላይ መሆኗን አንስቷል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት በቀጣናው እና የአፍሪካ ኃያል ሀገር መሆን የሚያስችላትን እንዲሁም የአህጉሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚበይንና የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሠራች መሆኗንም እንዲሁ። ለረጅም ዓመታት ዓለም ኢትዮጵያን የሚያውቃት በጦርነት፣በድርቅ እና በፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንደነበር በማስታወስ፥ዛሬ ግን ሀገሪቱ ይህንን የተዛባ ትርክት በኢነርጂ መሠረተ ልማት፣ በአቪየሽን፣ በማዕድን እና በዲጂታል ኢኮኖሚ አስደማሚ ለውጦች ለመቀየር እየሠራች ነው ብሏል። ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ተሻግራ እንዴት በአፍሪካ ፈጣን ዕድገት ካላቸው ኢኮኖሚዎች ቀዳሚዋ ሆና ልትቀጥል ቻለች? የሚለውን ጥያቄ በማንሳትም በዝርዝር መልሶቹን ያብራራል። የዚህ ዋና ጥያቄ ዝርዝር ምላሽ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት እየተተገበሩ የሚገኙ የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ ነው ያለው ሲል አንስቷል። • የመጀመሪያው የኢነርጂ አብዮት እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ነው። በዚህ የኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ጎልቶ የሚነሳው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሲሆን፣ ከ5 ሺህ ሜጋዋት በላይ የማመንጨት አቅም ያለው የአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት መሆኑን ፈርስት ፖስት በዘገባው ጠቅሷል። ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ መሻቶች መሰረት፣የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የውጭ ምንዛሬ እና የቀጣናዊ ተጽዕኖ መፍጠሪያ አቅም መሆኑንም አብራርቷል። የሕዳሴ ግድብ ልዩ የሚያደርገው የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ከዓለም ባንክ ወይም ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አንድ ሳንቲም ሳይበደር በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደም፣ ላብና ገንዘብ የተገነባ አፍሪካውያን በራሳቸው ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየነው ብሏል። ለኢትዮጵያውያን ግድቡ ከኮንክሪት እና ከተርባይን በላይ ትርጉም አለው ያለው ይህ የፈርስት ፖስት ዘገባ፥ እጅግ የላቀ እራስን የመቻል እና የኢኮኖሚ ነፃነት ማሳያ ሐውልት መሆኑንም ተንትኗል። ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ለኬንያ፣ ለጂቡቲ እና ለሱዳን በመሸጥ ኤሌክትሪክን ወደ ከፍተኛ ገቢ ማመንጫነት እየቀየረች ከመሆኑም በላይ የመላው ምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የትስስር ማዕከል ሆናለች ነው ያለው። • የኢትዮጵያ የዕድገት ምሰሶ አቪዬሽን እና ቀጣናዊ ትስስር ኢነርጂ ብቻውን ኢኮኖሚያዊ አቅምን አይገነባም፤ ይልቁንም ኢነርጂ ኢንዱስትሪን ያነቃቃል፣ ትስስር ዓለም አቀፍ ንግድን ይመግባል ያለው ፈርስት ፖስት፥የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ለላቀ የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ጉዞ መጀመሩን አንስቷል። በ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በየዓመቱ እስከ 110 ሚሊዮን ተጓዦችን እና ወደ 4 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የዕቃ ጭነት ማስተናገድ አቅም አለው። ሙሉ በሙሉ ግንባታው ሲጠናቀቅም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከታላላቅ የአቪዬሽን ማዕከላት አንዱ ይሆናል ብሏል። ይህ ፕሮጀክት የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ መናኸሪያ የሆነችውን አዲስ አበባንና አፍሪካን፣ከሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚያስተሳስር ዋና የመተላለፊያ ማዕከል እንደሚሆንም ተገልጿል። ስለዚህ አዲሱ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እና ለቱሪዝም፣ ለዓለም የዲፕሎሲ ትብብር ጉልህ ሚና እንዲያበረክት ታስቦ እየተገነባ ነው ብሏል። • የማዕድን ኢንቨስትመንትና በምግብ ራስን መቻል በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ መሬት በታች ላለው የማዕድን ሀብቷ ትኩረት በመስጠት የልማት አብዮት እያካሄደች ስለመሆኑም ተንትኗል። ሀገሪቱ የወርቅና ሌሎች ማዕድናት ማውጫ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት አዳዲስ የውጭ ምንዛሬ ምንጮችን እያፈራች የማዕድን ኢንዱስትሪዋን እያሳደገች ነው። ወርቅ በፍጥነት ከኢትዮጵያ ቀዳሚ የወጪ ንግድ ምርቶች አንዱ በመሆን ለረጅም ጊዜ በግብርና ላይ ብቻ ጥገኛ ሆኖ የቆየውን ኢኮኖሚ ወደ ብዝኃ ዘርፍ እያሸጋገረ ይገኛል። በሌላ በኩል በምግብ ራስን ከመቻል ውጭ የትኛውም ኢኮኖሚያዊ ለውጥ የተሟላ ሊሆን አይችልም ያለው የፈረስት ፖስት ዘገባ፥ ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት መሆኑን ጠቅሷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሚመራው መንግሥት ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን እንድትችል በጀመረው የለውጥ ጉዞ አስደማሚ ውጤት እያመጣ ነው ብሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከጉባ ብስራቶች አንዱ የሆነውና በሶማሌ ክልል እየተገነባ የሚገኘው የማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ ዩሪያ ማዳበሪያ ማምረት የሚችል ነው። ይህም ከውጭ የሚገባውን ማዳበሪያ ጥገኝነት በመቀነስ የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ እንደሚያስችል አብራርቷል። "የምግብ ዋስትና የእኛ ስትራቴጂካዊ ጣልቃ ገብነት ነው።ያንን ግብ እውን ለማድረግ ግብአቶች ላይ መስራት አለብን።በግብአት ላይ መስራት ካልተቻለ የምግብ ዋስትናን እውን ለማድረግ መንገድ የለውም" የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ በማካተት ዘገባው ሰፊ ሽፋን ሰጥቷል። ዲጂታላይዜሽን እና የኢንቨትመንትና የገበያ ማሻሻያዎች በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ወደ ዲጂታልም እየተሸጋገረ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እንደተናገሩት የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ከዕቅዱ ቀድም ከመሳካቱም በላይ በርካታ ወጣቶች የዲጂታል እውቀት ባለቤት አድርጓል። በተመሳሳይ የዲጂታል ትስስር እየሰፋ ሲሆን የ4ጂ እና 5ጂ አገልግሎቶች በበርካታ ከተሞች ተደራሽ ሆኗል። ኢትዮጵያ ለበርካታ አስርት ዓመታት ተዘግተው የቆዩ እንደ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ባንክ እና የካፒታል ገበያዎች ያሉ ዘርፎችን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጓንም አድንቋል። የካፒታል ገበያን መጀመሯም የግል ካፒታል ልውውጥን በማጎልበት ለኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተንትኗል። እነዚህ ማሻሻያዎች በአጠቃላይ በመንግስት ቁጥጥር ስር ከነበረው የኢኮኖሚ ወደ ግል ዘርፍ ኢንቨስትመንት እያደገ የሚሄድ ኢኮኖሚ መሰረታዊ ለውጥን እየተገነባ መሆኑን ያሳያሉ ነው ያለው። ኢትዮጵያ ካላት የጂኦ ፖለቲካ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ አኳያ እድልና ፈተናዎች ከፊቷ መሆናቸውን በማንሳት፥ አዲሱን የዓለም አቀፍ የትብብር ጥምረት ብሪክስ አባል መሆኗን አውስቷል። ከቻይና፣ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት፣ ከምዕራባውያን አጋሮችና ከአፍሪካ ኢንቨስተሮች ኢንቨስትመንትን እየሳበች እንደምትገኝም እንዲሁ። ኢትዮጵያ ጎራ ሳትለይ ከሁሉም የዓለም ሀገራት ጋር ትብብሯን እያጠናከረች ነው ብሏል። ዓለም ኢትዮጵያን የምታስታውሰው በጦርነት ቢሆንም፥ኢትዮጵያ ዓለም በአዲሱ የለውጥና የስኬት ጉዞዋ እንዲያስታውሳት እየሠራች ነው። ለዚህም በመላው ሀገሪቱ በሁሉም ዘርፍ ግዙፍ የኢኮኖሚ ሽግግር እየተካሄደ ሲሆን፥ ይህ የኢትዮጵያ ጉዞ ለቀጣዮቹ ዓመታት የቀጣናውንና የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊና አጠቃላይ ገጽታ በአዲስ መልኩ የሚቀርጽ ነው ሲል ፈርስት ፖስት ዘገባውን አብራርቷል።
ያቀደችውን በተግባር የምታሳካ ታላቅ ሀገር
Aug 3, 2026 650
የአንድ ሀገር ታላቅነት ከሚለካባቸው ጉዳዮች አንዱ የተያዙ ሀገራዊ እቅዶችን በተግባር የመለወጥ አቅም ዋነኛው ነው። ኢትዮጵያም በዛሬው እለት በአንድ ጀምበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ያስመዘገበችው አዲስ ታሪካዊ ስኬት፣ ሀገሪቱ ያቀደችውን በተግባር ማሳየት የምትችልና ትልልቅ ህልሞችን የመተርጎም አቅም ያላት ታላቅ ሀገር መሆኗን ለመላው ዓለም በተግባር ያስመሰከረ ነው። ይህ በአንድ ጀምበር የተከናወነ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በርካታ ጥልቅ ትርጉሞችን የያዘ ነው፡ በአንድ ጀንበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል ግዙፍ የሎጂስቲክስ፣ የዝግጅትና የህዝብ ንቅናቄ ስራን ይጠይቃል። ይህ ስኬት ሀገሪቱ ማንኛውንም ታላቅ አገራዊ እቅድ አቅዳ እስከ መጨረሻው የትግበራ ምዕራፍ ድረስ በብቃት የመምራትና የማስተባበር ተቋማዊና ህዝባዊ አቅም እንዳላት ማረጋገጫ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ዕድሜ፣ ጾታ፣ ወይም ልዩነት ሳይለያያቸው በአንድ ቀን ለተመሳሳይ አገራዊ ዓላማ መቆማቸው፣ ኢትዮጵያውያን ለጋራ እድገታቸውና ለሀገራቸው የወደፊት ተስፋ ያላቸውን ጽኑ ፍላጎትና አንድነት አሳይቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥና የበረሃማነት መስፋፋት ዋና ስጋት በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ እርምጃ ለችግሩ መፍትሔ በመስጠት ረገድ የዓለም አቀፍ መሪነቷን ያስመሰከረችበት አጋጣሚም ጭምር ነው። ይህ ስኬት ሀገሪቱ የገጠሟትን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች ተሻግራ፣ አቅሟን አስተባብራ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማሳካት እንደምትችል ለዜጎቿም ሆነ ለውጭው ዓለም የሰጠችው ትልቅ የራስ መተማመንና የተስፋ መልእክት ነው። በአጠቃላይ፣ በአንድ ጀምበር የተከናወነው ይህ ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያ አርቆ የማሰብና የማቀድ ችሎታዋን ብቻ ሳይሆን፣ ያቀደችውንም በአንድነትና በቁርጠኝነት ወደ መሬት በማውረድ በተግባር የምታሳይ ታላቅ ሀገር መሆኗን በግልጽ ያረጋገጠ አኩሪ ተግባር ነው።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ የአምራች ኢንዱስትሪ ትንሳኤ ብስራት!!
Aug 2, 2026 462
በሐዊ አጫሉ መግቢያ፡- የኢንዱስትሪ ዘርፍ የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ጥንካሬን ከሚወስኑ ዋነኛ የብልፅግና ማረጋገጫ ምሰሶዎች መካከል በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ዘርፉ ምርትን ከማሳደግ ባሻገር የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እና የሀገር ውስጥ ምርታማነትን የሚያፋጥን የልማት ሞተር ነው። ኢትዮጵያም ከግብርና መሠረት የተነሳ ኢኮኖሚዋን ወደ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪና ሁሉን አቀፍ የምርት ሥርዓት ለማሸጋገር ከምታደርገው ጥረት መካከል ኢንዱስትሪውን በቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶነት በማካተት እየሰራችበት ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና ቴክኖሎጂ አምስት ዐበይት የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት ምሰሶዎች ተመሥርቶ እየተመራ ይገኛል። ከእነዚህ ውስጥ ኢንዱስትሪው የምርት አቅምን በማሳደግ የግብርና ምርቶችን ወደ ተጨማሪ እሴት በመቀየርና ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ ፋይዳ እያስገኘ ነው። ይህንን ሽግግር እውን ለማድረግ የምርት አቅምን ማሳደግ፣ የግብርናና ኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን እና የሰው ኃይል ልማት ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ የቀድሞ ገጽታ፤ ከመዋቅራዊ ተግዳሮት ወደ ለውጥ መንገድ!! በቀደሙት ዓመታት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተለያዩ ዕድሎችንና ፈተናዎችን በማስተናገድ በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል። ሀገሪቱን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር በተደረጉ ጥረቶች የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተዋል። እነዚህ ፓርኮችም በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም በግብርና ምርት ማቀነባበር ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የተሞከረበት ወሳኝ ምዕራፍ እንደነበር ይታወሳል። ይሁን እንጂ ይህ ጉዞ በበቂ መሠረተ ልማት፣ በተሟላ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትና በተቀናጀ የምርት ሰንሰለት እጥረት ምክንያት በበርካታ ፈተናዎች ለመውደቅ ተገዶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ውስንነት፣ ዕውቅትና ክህሎትን የተሰላበሰ የሰው ኃይል አለመኖር፣ የፋይናንስ እጥረት፣ ውስብስብና አስቸጋሪ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትና የገበያ ትስስር እጥረት የዘርፉን እድገት ገድበው የነበሩ ሁነኛ ተግዳሮቶች ናቸው። ከመዋቅራዊ ተግዳሮት ወደ ምርታማነት፤ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ የለውጥ ፍኖት!! ባለፉት ዓመታት በኢንዱስትሪ ዘርፉ የተስተዋሉ መዋቅራዊ ችግሮችን ለመፍታትና የሀገሪቱን የማምረት አቅም ለማሳደግ አዳዲስ የለውጥ አቅጣጫዎች ተነድፈው ተተግበረዋል። በተለይም ኢንዱስትሪን ከተለመደው የምርት ሥርዓት በማሻገር ወደ ተወዳዳሪ ዘመናዊና ውጤታማ የማምረቻ ማዕከል ለመቀየር የተለያዩ የፖሊሲማሻሻያዎች ተደርገዋል። የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ ማሳደግ፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን ማስፋት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን፣ የሰው ኃይል አቅምን ማሳደግና የግብርና-ኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር በዘርፉ የተወሰዱ ሁነኛ የለውጥ እርምጃዎች ናቸው። በዚህም የኢትዮጵያን አምራች ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት በማጎልበት ከሀገር ውስጥ ገበያ እስከ ዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ድረስ ውጤት እያስገኘ ነው። የግል ባለሃብቱ ሚና፤ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሞተር!! የኢንዱስትሪ ልማት በመንግሥት ጥረት ብቻ የሚሳካ አይደለም። የግል ዘርፉ በካፒታል፣ በፈጠራ፣ በቴክኖሎጂና በአስተዳደር ብቃት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ለዘርፉ ዕድገት የማይተካ ሚና አለው። በዚህ ረገድ የግል ባለሃብቱ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ዋና አጋር እንዲሆን የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተሻሽለው እየተሰራባቸው ይገኛል። ይህም የግሉን ዘርፍ የኢንቨስትመንት በማሻሻል፣ የንግድ ሥራ ሂደቶችን በማቀላጠፍ፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋትና የምርት አቅምን በማሳደግ የግሉን ዘርፉ የምርታማነት አቅም እያጎለበተ ነው። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ የአምራች ኢንዱስትሪ የትንሳኤ ብስራት!! በሀገራችን የኢኮኖሚ አቅጣጫ ውስጥ የምርትና አገልግሎት አሰጣጥን በማቀናጀት አዲስ ምዕራፍ ከከፈቱ ዐበይት ሀገራዊ መርሃ-ግብሮች መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጠቃሽ ነው። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዘርፍ የማምረት ባህልን በማሳደግ ዘርፉ ወደ አዲስ የልማት ምዕራፍ የሚሸጋገርበት ሁነኛ ዕድልን ፈጥሯል። ንቅናቄው የማምረት አቅምን በማሳደግ ሥራ ያቆሙ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ መመለስ፣ የአምራቾችን ችግሮች በፍጥነት መፍታትና አዳዲስ ባለሃብቶችን ወደ ዘርፉ በመሳብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፤ እያበረከተም ይገኛል። በዚህ ሂደት በፋይናንስ፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በውጭ ምንዛሬና በተቋማዊ ቅንጅት ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎች የአምራች ዘርፉን የምርታማነት አቅም በማጎልበት ጉልህ ሚና ተጫውቷል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄም የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲያንሰራራ በማድረግ የምርታማነት አብዮት እንዲቀጣጠል እያደረገ ይገኛል። የንቅናቄው ዋና ዓላማ በአምራች ዘርፉ የነበሩ ማነቆዎችን በመፍታት የኢትዮጵያን የማምረት አቅም ማሳደግ ነው። ይህም ሥራ ያቆሙ ወይም በአቅማቸው ልክ ያልሠሩ ፋብሪካዎችን ወደ ሙሉ ምርት በመመለስ የአምራቾችን ችግር በተቀናጀ መንገድ መፍታት፣ የፋይናንስና የግብዓት ተደራሽነትን ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጓል። በዚህ ሂደት የማምረቻ ዘርፉ በአዲስ የሥራ ባህል፣ በተቋማዊ ቅንጅትና በፈጣን ውሳኔ አሰጣጥ እየተመራ መሆኑ የለውጡን ፍጥነት እያሳደገው ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የውጭ ምንዛሬ ተደራሽነትን ማሻሻልና የምርት ጥራትን ማረጋገጥ የኢንዱስትሪው ትንሳኤ ዋና ማሳያዎች ናቸው። ለአብነትም፡- የፋይናንስ አቅምና የብድር አቅርቦት ማሻሻል፡- የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ዋነኛ እንቅፋት የሆነውን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ በተደረገው ርብርብ፣ የብድር አቅም ቀደም ሲል ከነበረበት 40 ቢሊዮን ብር ወደ 115 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል በማድረግ ለአምራቾች ሰፊ የካፒታል አቅም መፍጠር ተችሏል። የውጭ ምንዛሬ ግኝትና የግብዓት ድጋፍ ማደግ፡- ንቅናቄው ከመጀመሩ በፊት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ይቀርብ የነበረው የውጭ ምንዛሬ መጠን አሁን ላይ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንዲደርስ ተደርጓል። ይህም ፋብሪካዎች ከአቅማቸው በታች እንዲሠሩ ያስገድድ የነበረውን የምርት ውስንነት በከፍተኛ ደረጃ አቃሎታል። የምርት ዕድገት፣ ተኪ ምርትና የኤክስፖርት አፈጻጸም፡- ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ረገድ ከነበረበት 348 ሚሊዮን ዶላር ወደ 5.9 ቢሊዮን ዶላር በማደግ ግዙፍ ሀገራዊ ድል ተመዝግቧል። እንዲሁም በኤክስፖርት ገበያ የሚገኘው ገቢ ከ385 ሚሊዮን ዶላር ወደ 607 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ማለት ችሏል። ተቋማዊ ቅንጅትና አዲስ የሥራ ባህል ማዳበር፡- በክልሎችና በፌዴራል ተቋማት መካከል የነበረውን የቢሮክራሲ ጫና በመቀነስ ፈጣን ውሳኔዎች እንዲሰጡ መደረጉ፤ እንዲሁም ህብረተሰቡ የሀገር ውስጥ ምርትን በኩራት የመጠቀም እና የሀገር ፍቅር ስሜትን ከአምራችነት ጋር የማስተሳሰር ትልቅ ማህበራዊ ንቃተ-ህሊና መገንባት ተችሏል። የወደፊት ተስፋ፤ ኢትዮጵያ አዲሲቷ አፍሪካዊት የኢንዱስትሪ ምርታማነት ተምሳሌት ሀገር!! የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ በቀጣይ ዓመታት ከተለመደው ማምረት ወደ ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የምርት ሥርዓት እንዲሸጋገር ይጠበቃል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና የፈጠራ ሥርዓቶችን ወደ ማምረቻ ዘርፉ ማስገባት የወደፊቱ ትኩረት ይሆናል። በተመሳሳይም ጠንካራ የግብርናና ኢንዱስትሪ ትስስር፣ አረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአህጉራዊ ገበያ ተደራሽነት የሀገሪቱ ቀጣይ የኢንዱስትሪ ግቦች ናቸው። የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) የሚፈጥረውን ሰፊ የገበያ ዕድል በመጠቀም ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል እንድትሆን የሚያስችል መሠረት እየጣለች ትገኛለች። ማጠቃለያ፡- ማምረት፤ የኢትዮጵያ የብልፅግና ቁልፍ መሳሪያ!! የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ ከፈተና ወደ ዕድል፣ ከጥገኝነት ወደ ራስን መቻል፣ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ተጨማሪ እሴት ያለው ምርት አቅራቢነት በማምራት እመርታዊ ውጤቶችን እያስገኘ ነው። የኢንዱስትሪውን አቅም ማሳደግ ማለት ፋብሪካዎችን ብቻ ማስፋፋት ሳይሆን የሀገርን ምርታማነት፣ የወጣቶችን ዕድል፣ የኢኮኖሚ ነፃነትንና የልማት ዘላቂነትን ማረጋገጥ ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን የዛሬ ልማት ብቻ ሳይሆን የነገውን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚገነባ ሀገራዊ ራዕይ ነው።
የክልሎች ቅኝት - በወፍ በረር
Aug 2, 2026 348
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 26/2018 (ኢዜአ) የክልሎች ቅኝት - በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርናውን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል። በክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5 ዓመት 3ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም በክልሉ የግብርናውን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን አንስተዋል። የሜካናይዜሽን እርሻም ተግባራዊ በመደረጉ ከ55 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱንም ጠቅሰዋል። ከማዕድን ዘርፍም በበጀት ዓመቱ ከ 8 ሺህ 900 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል። ኦሮሚያ ክልል በኦሮሚያ ክልል የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለበት በማድረግ የሙስና እና የብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ሪፎርም እየተተገበረ ይገኛል። ለዚህም የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ይፋ የማድረጊያ መርሃ ግብር ''የአገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ለሁለንተናዊ ብልጽግና'' በሚል መሪ ሀሳብ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ፤ የመንግስትን አገልግሎት አሰጣጥን የተሳለጠ ለማድረግ የሚያስችል እስከ ቀበሌ የደረሰ አሰራር መዘርጋቱን በወቅቱ አንስተዋል። አልግሎቶችን በዲጂታል ስርዓት በመደገፍ የህዝቡን እንግልት፣ ጊዜና ወጪ በመቆጠብ ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል። ይህም በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ሲዳማ ክልል የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ የ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ሥራ ምቹ ማድረግና በግብአት ለማሟላት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል። ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ በማድረግ በትምህርት ጥራት ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲታይ መደረጉንም አስረድተዋል። ጋምቤላ ክልል የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ''ተስፋን እንትከል'' በሚል መሪ ሀሳብ የ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በማጃንግ ዞን በመንገሺ ወረዳ ያስጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው። በክልሉ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን ለማረጋገጥ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች በህዝብ ተሳትፎ እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል ። ባለፉት ዓመታት የተከናወኑት የአረንጓዴ አሻራ ልማት የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ ከማድረጋቸው ባለፈ የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማስቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሯ ገልፀዋል። አማራ ክልል በአማራ ክልል የግብርናን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢንዱስትሪዎች ግብአት ማምረት ተችሏል። የዚሁ አካል የሆነው በክልሉ በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ 837 አርሶ አደሮች በማህበር በመደረጃት “የጅሩ-አግሮ ቢዝነስ“ ኩባንያን መስርተዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት ኩባንያው የአርሶ አደሮችን ምርት በማቀነባበር ለገበያ የሚያቀርብ ነው። የአግሮ-ቢዝነስ ኩባንያውም ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። ይህም አርሶ አደሩ ከጥሬ ግብአት አቅራቢነት ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ኢንቨስተርነት በማደግ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል። ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳዳር ዙሪያ ጨታ ቀበሌ የተገነባውን የባቾ ገጠር ሞዴል መንደር መርቀው ለነዋሪዎች አስረክበዋል። በወቅቱም የሞዴል የገጠር መንደሩ መገንባት የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ ብሎም ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል። በሌላ በኩል በክልሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ገንብቶ በማጠናቀቅ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። በተለይም የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን በመገንባት የወረዳና ቀበሌዎች ማህበራዊ ትስስር እንዲጠናከርና የግብይት ሰንሰለትም እንዲቀላጠፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ለአብነትም በክልሉ ኮንታ ዞን በአመያ ዙሪያ ወረዳ በኡማ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ የአካባቢውን ነዋሪዎች የዘመናት ችግር ያቃለለና ለመሰረተ ልማት ጥያቄያቸው ምላሽ የሰጠ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ በክልሉ ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል። በመልእክታቸውም በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እየተደረገ ባለው ጥረት ውጤት እየተገኘ ስለመሆኑ ተናግረዋል። በ2019 በጀት ዓመትም በክልሉ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ 48 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግብር ለመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። ለዚህም በህግና የአሠራር ስርአት በመታገዝ የገቢ አቅምን በማስፋት የክልሉን ዕድገት ዘላቂነት በማረጋገጥ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እየተደረገ ባለው ጥረት ውጤት እየተገኘ ነው ብለዋል ። በ2019 በጀት አመትም የክልሉን የገቢ አቅም ለይቶ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ የግብር እቅድን ለማሳካት እንደሚሰራ ተናግረዋል። በዚህም በበጀት አመቱ 48 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። ገቢውን ለማሳካትም የህግና የአሠራር ስርአት በመዘርጋት የክልሉ ዕድገት በዘላቂነት በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል። አፋር ክልል በአፋር ክልል የእንሰሳትና ዓሳ ሀብትን በማልማት ለወጣቶች የስራ እድልን ለማስፋት የተሰሩ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የክልሉ የእንሰሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ ኢብራሂም መሐመድ ገልጸዋል። ለዚህም ስምንት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሐይቆች ላይ ወጣቶችን አደራጅቶ ወደ አሳ ልማት ስራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል። ለአብነትም በአፋምቦ ሐይቅ ላይ 200 ወጣቶች በዓሳ ሀብት ልማት ላይ በመሰማራት ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር መዘርጋቱን አስረድተዋል። በዓሳ ሀብት ልማቱ ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ ወጣቶች እንዳሉት የአሳ ሀብትን አልምተው ተጠቃሚ ለመሆን በማህበር ተደራጅተው በመስራት ላይ ናቸው። ስራውንም ለማሳካት ክልሉ እያደረገ ያለው የሙያ ስልጠናና ድጋፍ የማይተካ ድርሻ አለው ብለዋል። ማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል "ሁሉ አቀፍ እመርታ ፣ ለሁለንተናዊ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራ አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል። ርዕስ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል። የህዝቦችን አብሮነት በማጠናከር ክልሉን የህብረ ብሄራዊነት ተምሳሌት ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገቡን አመልክተዋል። በበጀት ዓመቱ የተገኙ ስኬቶችን ማጠናከርና የተስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ የመድረኩ ዋና ዓላማ ስለመሆኑም ገልጸዋል። ሐረሪ ክልል የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ሮዛ ኡመር እንደገለፀት፤ በክልሉ ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ስራ በገጠር ወረዳዎች የመስኖ ልማት በስፋት ተከናውነዋል። ተግባሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ የ2018 የግብርና ልማት እቅድ አፈጻጸምና የ2019 የግብርና ልማት መሪ እቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የእንስሳት ተዋጽኦና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ትልቅ እመርታ የተገኘበት ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ባሻገር የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል ብለዋል። ሶማሌ ክልል የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባዔውን ሲያካሂድ ርእሰ መስተዳድሩ ሙስጠፌ ሙሀመድ፤ የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም በክልሉ የሰላምና የልማት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ስራዎችና የመጡ ውጤቶችን አብራርተዋል። የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ጠቁመው፤ የፍትህ አካላትን አቅም ለመገንባት በተደረገ ጥረት የፍትህ ሂደቱ የተሳለጠ እንዲሆን መቻሉንም አንስተዋል። በክልሉ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በድህነት ቅንሳ፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ የሚመጡ አደጋዎች ቅነሳም ከፍተኛ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ፤ አዲሲቷ የዘመን ተሻጋሪ ዲጂታል ክህሎት የተስፋ አድማስ!!
Aug 7, 2026 23
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በወፍ በረር “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ ተጠናቋል። በዛሬው ዕለትም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን በይፋ አስጀምረናል። ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል ዕድል መፍጠር፣ እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሠረታዊ ትልሞች ናቸው። እነዚህ ትልሞች እንዲሳኩም በተለይ የሕዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማትን ማስፋት ላይ ትልቅ ሥራ የሚከናወን ሲሆን፣ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ሥራዎች የመደመር መንግሥት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ ናቸው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ዲጅታላይዜሽን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚመራ ብሔራዊ የልማትና ዕድገት ፕሮግራም ነው። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2020 በዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ማዕቀፍ ይፋ የተደረገው ብሔራዊ አጀንዳ በዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂም ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ ተይዟል። ግቡም ሁሉንም ተቋማት በኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ በማስተሳሰር በኢትዮጵያ ፈጣን የዲጅታል ኢኮኖሚ ሽግግር መፍጠር ነው። ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት፣ የኢንተርኔትና የዲጅታል ትስስርን ማስፋፋት፣ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎትን ማላቅ፣ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ የጤና አጠባበቅና የትምህርት ሥርዓትን ማሻሻል፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የዲጅታል ኢኮኖሚ መገንባት፣ በኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም በኢኖቬሽን የሥራ ዕድል መፍጠር እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን መደገፍ የዲጅታላይዜሽን መሠረቶች ናቸው። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የዲጅታል ኢኮኖሚ መሠረት ጥሏል። በመንግሥት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን በዲጅታል ቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል፤ ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋትም ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የሚያስችል መሠረት ጥሏል። የዲጅታል ማንነትን በማስፋፋት ዜጎች አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ማግኘት እንዲችሉ ያስቻለ ሲሆን፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን፣ ቅንጅትንና ተደራሽነትንም አሳድጓል። ቀደም ሲል ዜጎች ዲጅታል ማንነት መጠቀም በማይችሉበት ወቅት በርካታ የወረቀት ሰነዶችን ከማቅረብ ጀምሮ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትን በመዳረስ ረጅም ጊዜና ጉልበት ያጠፉ ነበር። አሁን ግን ሁኔታው ተለውጧል። በወረቀት አልባ ሥርዓት ፈጣንና ፍትሐዊ የመንግሥት አገልግሎት ማግኘት የሚቻልበት የዲጅታል ምህዳር ተፈጥሯል፤ የዜጎች እንግልት ቀንሷል፤ ወረፋና ጥበቃም ተረት ሆኗል። የዲጅታል ክፍያ ሥርዓትም በኢትዮጵያውያን ዘንድ እንደዕለት ተዕለት አጠቃቀም ቀላልና የተለመደ እየሆነ መጥቷል። የቴሌኮም መሠረተ ልማትን የማስፋፋት ሥራም ተጠናክሯል፤ የዲጅታል ክህሎት በተለይም በወጣቶች ዘንድ አዲስ የእውቀትና የተወዳዳሪነት መሣሪያ ሆኗል። ለዲጅታል መሠረተ ልማት መስፋፋት ቁልፍ የሆኑ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፎችም ተፈጥረዋል። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ለኢትዮጵያ የዲጅታል ኢኮኖሚ ሽግግር መሠረት ጥሏል፤ የኢትዮጵያን መጪ ጊዜ በተስፋ መመልከት የሚያስችል አጉሊ መነጽር አቅርቧል። በዲጅታል ክፍያዎች የታገዘ የጥሬ ገንዘብ አልባ ግብይትም የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እያዘመነ ይገኛል። ጥሬ ገንዘብ በእጅ የመያዝ ልማድ መቀነሱ የገንዘብ ማተሚያና ማጓጓዣ ወጪን ቀንሷል፤ የገንዘብ ዝውውርን ግልጽና ፈጣን በማድረግም ሕገወጥ አሠራሮችንና ሙስናን ለመከላከል አስችሏል። ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ከተደረገለት የፋይናንስ ሥርዓት ጋር ሲቀናጅም፣ ሕዝቡ በዲጅታል ክፍያዎች ላይ ያለው መተማመን እንዲጎለብት ያደርጋል፤ የሀገሪቱንም የዲጅታል ሽግግር ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል። ይህም ለዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መሠረት ጥሏል። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030፤ የሽግግሩ ቀጣይ ምዕራፍ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነትን በማጠናከር፣ የኤሌክትሮኒክ የመንግሥት አገልግሎቶችን ፍጥነት፣ ተደራሽነትና ግልጽነት ለማሳደግ ያለመ ነው። ይህም የመንግሥትን ወጪ ለመቀነስና የአገልግሎት ብቃትን ለማሳደግ ዕድል ይፈጥራል። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬትም በኢኮኖሚ፣ በትምህርትና በአገልግሎት ዘርፎች አዎንታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል። የሀገሪቱ የዲጅታል ሽግግር በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ በተመሠረተው የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ የተቃኘ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በስትራቴጂ ማስጀመሪያው ወቅት፦ ስትራቴጂው በከተማም ሆነ በገጠር የዲጅታል ሥርዓትን በማስረጽ የዲጅታል ኢኮኖሚን እውን የምናደርግበት ነው ብለዋል። ቁሳዊ ዕድገት የሚጀምረው የሰው ኃይል አቅምን በመገንባት እንደሆነ ጠቅሰው፣ ወጣቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ የፈጠራ ባለቤቶችና ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ በዲጅታል ክህሎት ማስታጠቅ እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል። የዲጅታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ግቦች ኢትዮጵያ የብሮድባንድና ኢንተርኔት ተደራሽነትን በመላ ሀገሪቱ በመዘርጋት፣ የዜጎችና ተቋማትን የዲጅታል ክህሎት በማሳደግ፣ እንደ ግብርና፣ ቱሪዝም፣ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ስታርትአፖችን በቴክኖሎጂ በማዘመን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትና ንግድን መሳብ፣ እንዲሁም አካታች የዲጅታል ኢኮኖሚ መገንባት ናቸው። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የመንግሥት የዲጅታል አገልግሎት ማስፋፊያ፣ የቴሌኮም ሪፎርም፣ ዲጅታል ክፍያ፣ ብሔራዊ የዲጅታል መታወቂያ/ፋይዳ፣ እንዲሁም በሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ ዲጅታል የሕዝብ መሠረተ ልማት፣ የሳይበር ደህንነትና ብሔራዊ የዲጅታል አካታችነትን መርህ ያደረገውን የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አዋልዷል። የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጅታል ሽግግር ስትራቴጂ ነው። ከዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬት የተቀዳ ታላቅ የመሆን ህልም ሥጋ ለብሶ የታየበት ግልጽ ፍኖተ ካርታም ነው። የዲጅታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2030 ቀልጣፋ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ፣ የአስተዳደር ሥርዓትን በማጠናከር አገልግሎትን ማሻሻል፣ በዲጅታል ቴክኖሎጂ የበቃ ማኅበረሰብ በመፍጠር ሀገርን ማበልጸግ፣ ለነገ ዛሬ የሚኖር አደራና ዛሬ የነገ ስንቅ ሆኖ በግልጽ ሰፍሯል። የኢትዮጵያ የዲጅታል ሽግግር ግብ አንድ ነው፤ አካታችና ዘላቂ ዲጅታል ኢኮኖሚ መገንባት፣ በዋጋ ተመጣጣኝና ተደራሽ የኢንተርኔትና የኮሙኒኬሽን አገልግሎትን ማስፋት፣ በዲጅታል ኢኮኖሚ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የመረጃ አስተዳደርና የሳይበር ደህንነት ጥበቃን ሕልው ማድረግ፣ የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትን መጨመር፣ ዲጅታል ክህሎትና ኢኖቬሽንን ማሳለጥ ነው። ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ /ፋይዳ/፤ የዲጅታል ሽግግር መልህቅ ''በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ ዲጅታል ማንነት ተስፋ ሰጪ ከሆነው ፈጠራ ወደ ዲጅታል ሽግግር መሠረታዊ ምሰሶ ተሻሽሏል። ከአሁን በኋላ አማራጭ ሳይሆን፣ ሰዎችን ከአገልግሎቶች፣ ከማኅበረሰቦች፣ ከተቋማት እና ከመንግሥታት ጋር የሚያገናኝ አስፈላጊ መሠረተ ልማት ነው። ፋይዳ ካርድ ብቻ አይደለም። የግለሰቦችን የግል መረጃ ምሥጢራዊነት በመጠበቅና አስፈላጊ የሆነውን መረጃ ብቻ በማጋራት ማንነትን የሚያረጋግጥ ልዩ መለያ ቁጥር ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ /ፋይዳ/፤ የዲጅታል ሽግግር መልህቅ የዲጅታል ብሔራዊ መታወቂያ /ፋይዳ/ (National Digital ID) በኢትዮጵያ ሥራ የጀመረው እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2023 ነበር። ምንም እንኳን የፕሮጀክቱ ዝግጅትና ሕጋዊ መሠረት ቀደም ብሎ የተጀመረ ቢሆንም፣ በአዋጅ ቁጥር 1284/2015 በሕግ ተቋቁሟል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር ከ2019 እስከ 2020 ባለው ጊዜም ፋይዳ በዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አካል ሆነ። ከዚያም ምዝገባው በመላ ኢትዮጵያ ተስፋፍቶ፣ ከመንግሥት አገልግሎቶች፣ ከባንኮች፣ ከዲጅታል ክፍያ ሥርዓት እና ከመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል አገልግሎት ጋር ተሳስሯል። በኢትዮጵያ እያንዳንዱን ነዋሪ የአንድ ልዩ የዲጅታል መለያ ባለቤት ማድረግ የፕሮጀክቱ ዋነኛ ግብ ነው። ይህም የመንግሥትና የግል አገልግሎቶችን በቀላሉ ማግኘት የሚቻልበትን ሥርዓት ለመዘርጋት፣ የማንነት ማጭበርበርና ድርብ ምዝገባን ለማስቀረት እንዲሁም የኢትዮጵያን ዲጅታል ኢኮኖሚ ለመደገፍ ያስችላል። ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የነዋሪዎችን የባዮሜትሪክና ዲሞግራፊክ መረጃ በመሰብሰብ፣ ''አንድ ሰው፣ አንድ ማንነት” በሚል መርህ እያንዳንዱን ሰው ልዩ በሆነ ሁኔታ መለየት የሚያስችል ሥርዓት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለፋይዳ አስፈላጊነት ሲናገሩ፣ “ፋይዳ በአማርኛ፣ በኦሮሚኛ፣ በትግርኛ፣ በሱማሊኛ፣ በአፋርኛ እንዲሁም በአረብኛ፣ በሂንዱኛና በተርኪሽ ቋንቋዎች ፋይዳ ነው። … ዲጅታል መታወቂያ /ፋይዳ/ በጣም ጠቃሚ ነገር ነው፤ ከሕዳሴ የሚያንስ አይደለም። እንደ ሀገር ዲጅታል መታወቂያ ብንሠራ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት በሰባት ፐርሰንት ይጨምራል። ፋይዳ የመተማመኛ ሥርዓት ነው…” በማለት የፋይዳን መልከ ብዙ ፋይዳ ገልጸዋል። ፋይዳ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የዲጅታል ኢኮኖሚ ሽግግሩን ለማሳለጥ ቁልፍ መሣሪያ መሆኑንም አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ከ150 በላይ ተቋማት ጋር ተሳስሯል። ከ48 ሚሊዮን በላይ ዜጎችም ተመዝግበዋል። እስከ 2020 ዓ.ም ድረስ የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ወደ 115 ሚሊዮን ለማድረስ ጉዞው ቀጥሏል። በዚህም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ወደ መደበኛ የፋይናንስ ሥርዓት ለማስገባት እያገዘ ይገኛል። መንገዶች ሁሉ ኢትዮጵያን ወደ ዲጅታል ሽግግር በሚወስዱበት ሀዲድ፣ ፋይዳ መሪ ተዋናይ ሆኖ ይቀጥላል። ዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት እንዲያገኙ፣ የባንክና የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲጠቀሙ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ምህዳር ይፈጥራል። መንግሥትም ማጭበርበርን ለመከላከል፣ በተቋማት መካከል ግልጽና የተቀናጀ ትብብርን ለመዘርጋት እና የተሻለ የሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥበትን ዕድል እውን ለማድረግ ፋይዳን ይጠቀማል። የቢዝነስ አንቀሳቃሾችም ዲጅታል ግብይትን፣ ፋይናንስንና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሥራቸውን የበለጠ ቀልጣፋና ተደራሽ ማድረግ ይችላሉ። በአጭሩ፣ ፋይዳ ''ሁሉ በእጄ፣ ሁሉ በደጄ” የሚለውን የዲጅታል ኢኮኖሚ ራዕይ እውን ለማድረግ የሚያግዝ ቁልፍ መሠረተ ልማት ነው። መሶብ፤ የአንድ ማዕከል ዲጅታል አገልግሎት የጊዜና የቦታ ልጓም ''ሀገራዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሠረታዊ የሆነ የባህል ለውጥ ያስፈልጋል። ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን እንገኛለን። መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ የጀመርነው በቅርብ ጊዜ ቢሆንም፣ በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች እርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧል። ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ያመላክታል።”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል አገልግሎት፤ የጊዜና የቦታ ልጓም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 12 የፌዴራል ተቋማት 40 የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ሥር እንዲሰጡ በማድረግ ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል። እነሆ ማዕከሉ የተቋማትንና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ቁጥር እያሳደገ የኢትዮጵያን የዲጅታል ሽግግር ፍኖት እየቀረጸ ይገኛል። ዜጎችም በዲጅታል መሠረተ ልማት የተደገፈ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል። ከዚህ በፊት የዜጎችን ጊዜ የሚያባክኑ ረጅም ወረፋዎች፣ የተለያዩ ቢሮዎችን ደጋግሞ መጎብኘት፣ “ሰነድ ይጎድላል፣ ኮፒ አድርገህ አምጣ” የሚሉ የወረቀት ሥራዎች በአዲሱ የአገልግሎት ሥርዓት እየተቀየሩ ነው። አዲስ የአገልግሎት አድማስ የሆነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከ220 በላይ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ሕንፃ ሥር በማቅረብ የዜጎችን የጊዜና የቦታ ጫና ቀንሷል። ከቀበሌ መታወቂያ ማውጣት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የንግድና የጉምሩክ አገልግሎቶች ድረስ በቀላሉ ማግኘት የሚቻልበት ምቹ ምህዳር ተፈጥሯል። ፈጣንነት፣ ቅልጥፍና፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና መርሆዎች ሆነዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተንቀሳቃሽ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ባስጀመሩበት ወቅት፤ ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል፣ እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን እንቀጥላለን ብለዋል። የዲጅታል አገልግሎት የዜጎችን ጊዜና ጉልበት የሚቆጥብ አዲስ የአስተዳደር ባህል መሆኑን ገልጸዋል። በአጠቃላይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የወረቀት እና የወረፋ ዘመንን በመቀየር ዜጋን ማዕከል ያደረገ፣ ቀልጣፋና ዲጅታል የሆነ የአገልግሎት ሥርዓት እየገነባ ያለ የለውጥ ምሳሌ ሆኗል። የ5-ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ፤ የዲጅታል ክህሎት ማበልጸጊያ መድረክ በዲጅታል ዘመን የሰው ኃይል አቅም የሀገራት የዕድገት መሰረት እሆነ ነው። ኢትዮጵያም የወጣቶቿን የፈጠራና የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ ትልቅ የዲጅታል ክህሎት ማበልጸጊያ መርሃ ግብር ጀምራለች። የ5-ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ የወጣቱን ትውልድ የፕሮግራሚንግ፣ የሶፍትዌር ልማት፣ የፈጠራ ሥራና የዲጅታል ቴክኖሎጂ አቅም ለማጎልበት የተቀረፀ ሀገራዊ አጀንዳ ነው። መርሃ ግብሩ ወጣቶችን የዲጅታል ኢኮኖሚ ተሳታፊዎች ብቻ ሳይሆኑ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችና የሀገር በቀል መፍትሔ አበልጻጊዎች ለማድረግ ያለመ ነው። ''ይህም ኢትዮጵያ በዓለም የዲጅታል ውድድር ውስጥ የምትኖራትን ሚና ለማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና በአፍሪካ የፈጠራ ማዕከል ለመሆን የሚያግዝ የወደፊት ራዕይ ነው። ኢትዮጵያ ወደፊት የሚያልሙ አሳቢ ወጣት ዜጎቿ ተስፋ አላት። የ‘አምስት ሚሊዮን ኮደርስ’ መርሃ ግብር ታላቅ እድል ነው። አምስት ሚሊዮኖቹ ኮደሮች ሀገር በቀል መፍትሔዎችን የሚሰጡ ብቻ ሳይሆኑ፣ ለአህጉራችን የተስፋ ብርሃን የሚፈነጥቁ ናቸው።''ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአጠቃላይ 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ የዲጅታል ክህሎትን ከመገንባት ባሻገር፣ የወጣቱን የፈጠራ ኃይል ወደ ሀገራዊ የዕድገት ሞተር ለመቀየር የተቀረፀ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ዋነኛ መሠረት ነው። 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ፤ የዲጅታል ክህሎት ማበልጸጊያና የወጣቱ የወደፊት አቅም በፍጥነት በሚለዋወጠው የዲጅታል ዓለም ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት መያዝ አማራጭ ሳይሆን የዘመኑ ግዴታ ሆኗል። ዛሬ ላይ በመትጋት ነገን ማልማት የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ሲሆን፣ የሀገር ዕድገትም የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ላይ ይመሰረታል። መንግሥት የበለጸገችና በቴክኖሎጂ የተደገፈች ኢትዮጵያን ለመገንባት ከለያቸው አምስት ቁልፍ የትኩረት መስኮች መካከል አይ.ሲ.ቲ (ICT) አንዱ ነው። በዚህ ራዕይ መሠረት የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማሳለጥ ሦስት ቁልፍ የዲጅታል ሽግግር ማስፈጸሚያዎች ተግባራዊ ሆነዋል። እነሱም መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል አገልግሎት፣ ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ (ፋይዳ) እና 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ናቸው። የወጣቱን የዲጅታል አቅም የሚገነባ ታላቅ ኢንሼቲቭ 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ትብብር ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ በሦስት ዓመታት ውስጥ 5 ሚሊዮን ወጣቶችን በዲጅታል ክህሎት ለማሰልጠን የተቀረጸ ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሚንግ (Programming)፣ የመረጃ ትንተና (Data Analysis)፣ የአንድሮይድ ልማት (Android Development) እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሠረቶች (Artificial Intelligence Fundamentals) የሥልጠናው ዋና የክህሎት ዘርፎች ናቸው። ኢንሼቲቩ የተያዘለትን ግብ በፍጥነት እያሳካ ይገኛል። ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰልጣኞች ተመዝግበዋል፤ ቁጥሩን እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም 7 ሚሊዮን ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል። ይህም የወጣቶችን ለሥራ ዓለም ተፈላጊነት ከማሳደግ ባሻገር፣ የሀገሪቱን የዲጅታል የሰው ኃይል ልማት ያጠናክራል። በመንግሥት ተቋማት የሶፍትዌር ልማትና የዲጅታል ሽግግር ሥራዎችን የሚያሳልጡ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችንም ያፈራል። በኢንሼቲቩ አማካኝነት 1 ሚሊዮን የዲጅታል የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ከዲጅታል ምርቶች ወጪ ንግድ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት የተቀመጠው ዕቅድ የፕሮግራሙን ሀገራዊ ፋይዳ ያመላክታል። የወጣቶች የፈጠራ ኃይል የኢትዮጵያ የዲጅታል ተስፋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በየትኛውም የትምህርትና የዕውቀት ደረጃ ላይ ያሉ ወጣቶች የአምስት ሚሊዮን ኮደሮች ፕሮጀክትን በመጠቀም ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ጥሪ አቅርበዋል። የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከላት፣ አሰልጣኞችና ዩኒቨርሲቲዎችም የፕሮግራሙን ስኬት ለማስፋት የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል። የዲጅታል ሽግግር ሦስቱ ምሰሶዎች በጥቅሉ 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ፣ ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ (ፋይዳ) እና መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የኢትዮጵያን የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያስፈጽሙ ተያያዥ ምሰሶዎች ናቸው። ኮደርስ የዲጅታል ኢኮኖሚውን የሚገነባና የሚያስፋፋ የሰው ኃይል ያበረክታሉ፤ ፋይዳ ደግሞ የደህንነቱ የተጠበቀ የዲጅታል ማንነት ሥርዓት ይፈጥራል፤ መሶብም በአንድ ጣሪያ ሥር ፈጣንና ግልጽ የህዝብ አገልግሎት ያሳልጣል። ከዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይ ጋር ተጣምረው እነዚህ ሦስት የለውጥ ምሰሶዎች ኢትዮጵያን ወደ አካታች፣ ዘላቂና ተወዳዳሪ የዲጅታል ኢኮኖሚ ለማሸጋገር የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የኢትዮጵያ ተሻጋሪ ህልሞች መመልከቻ በኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እ.ኤ.አ. በ2020 የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመመስረት ተቋማዊ መሠረት የያዘ የልማት አቅጣጫ ሆኗል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲና ሕጋዊ ማዕቀፎች በመዘርጋታቸው ዘርፉ በተደራጀ አሠራር እንዲመራ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጎበኙበት ወቅት፣ ሰው የጠራ ራዕይ ካለው፣ በከፍተኛ ዲሲፕሊን የሚሠራ ከሆነ ያሰበውን ማሳካት እንደሚችል፤ ኢትዮጵያ ብቃት ያላት ሀገር መሆኗን በመግለጽ የዘርፉን ሀገራዊ ጠቀሜታ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሀገር ውስጥ የፈጠራ አቅምን በማበረታታት ዘርፈ ብዙ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች እንዲመነጩ እያደረገ ይገኛል። በግብርና፣ በጤና፣ በፋይናንስ፣ በደህንነትና በአገልግሎት ዘርፎች የሚያገለግሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መፍትሔዎች በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች መፍጠር ጀምረዋል። በአማርኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የጽሑፍና የድምፅ ማቀናበሪያ ቴክኖሎጂዎች (NLP)፣ በጤና ዘርፍ የጡት ካንሰር፣ የስኳር በሽታና የሳንባ በሽታዎችን በምስል ምርመራ ቀድመው ለመለየት የሚያግዙ የAI መፍትሔዎች፣ በግብርና ዘርፍ የቡናና የሰብል በሽታዎችን የሚለዩ መተግበሪያዎች እየተስፋፉ ነው። በተጨማሪም ለከተማ ደህንነት፣ ለፖሊስ ሥራ፣ ለጉምሩክ ቁጥጥርና ለፋይናንስ ተቋማት የሚያገለግሉ ቻትቦቶችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በመስኩ እየተተገበሩ ይገኛሉ። የታዳጊዎች የሰመር ካምፕ የAI ስልጠናዎችም የወደፊቱን የቴክኖሎጂ ባለሙያ ትውልድ ለማፍራት እያገዙ ናቸው። የኢትዮጵያ የዲጅታል ሽግግርና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉዞ በሀገር ድንበር የማይገደብ፣ የአፍሪካን ዲጂታል ሽግግር ታሳቢ ያደረገ አህጉራዊ ራዕይ ነው። ለዚህም ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስን በማዘጋጀት አፍሪካ በዲጂታል ሽግግር፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ ትብብር እንድትጠናከር ያላትን ራዕይ አሳይታለች። በአፍሪካ ቀዳሚ ከሚሆኑ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከላት አንዱ የሆነው የAI ዩኒቨርሲቲ ግንባታም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት፣ የአፍሪካን የቴክኖሎጂና የፈጠራ አቅም ለማሳደግ የተያዘ ተሻጋሪ ራዕይ ነው። በአጠቃላይ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለኢትዮጵያ የወደፊት የዕውቀት ኢኮኖሚ፣ የፈጠራ አቅምና የዲጂታል ሉዓላዊነት መሠረት እየሆነ የሚሄድ ተሻጋሪ መሣሪያ ነው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፤ የዲጅታል ሉዓላዊነት እና ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ዘብ የዓለም የዲጅታላይዜሽን ሽግግር በብርሃን ፍጥነት እየተስፋፋ ባለበት ዘመን፣ ቴክኖሎጂን መጠቀም ብቻ ሳይሆን የዲጅታል መሠረተ ልማቶችን ከሳይበር ስጋቶች መጠበቅ የሀገራት ቁልፍ ተግባር ሆኗል። በዚህ የቴክኖሎጂ ውድድር ዓለም የመረጃ ደህንነት ከቴክኒክ ጉዳይ ባለፈ የሀገር ሉዓላዊነትና ህልውና ጉዳይ እየሆነ መጥቷል። ኢትዮጵያም የዘግይቶ መግባት ጥቅም (Latecomer Advantage) በመጠቀም የዲጅታል ሽግግሯን በዘመናዊ መሠረተ ልማቶች ላይ ለመገንባት እየሠራች ትገኛለች። ይህንን የዲጅታል ጉዞ አስተማማኝ ለማድረግና የሀገሪቱን የመረጃ ሀብት ለመጠበቅ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ወሳኝ ሚና እየተወጣ ነው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኢትዮጵያን የኢንፎርሜሽን ሥርዓቶችና ቁልፍ የመረጃ መሠረተ ልማቶች ከሳይበር ጥቃት የመጠበቅ፣ የመረጃ ደህንነትን የማረጋገጥና ብሔራዊ ጥቅሞችን የማስከበር ተልዕኮ ተሰጥቶታል። የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ፣ የደህንነት ኦፕሬሽን ማዕከላት (Security Operation Centers) እና የዲጅታል ፎረንሲክ ላቦራቶሪዎች ግንባታ ለዘርፉ የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህ ዘመናዊ የዲጅታል ደህንነት መሠረተ ልማቶች እንደ ባንክ፣ ቴሌኮም፣ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ቁልፍ ሀገራዊ ተቋማትን ከተወሳሰቡ የሳይበር ጥቃቶች አስቀድሞ ለመከላከል፣ አደጋ ቢከሰትም ፈጣን ሕጋዊና ቴክኒካዊ ምላሽ ለመስጠት ያስችላሉ። የመረጃ ደህንነት፤ የዲጅታል ኢኮኖሚ መሠረት በዛሬው ዓለም መረጃ (Data) እንደ አንዱ ዋና ሀብት በመቆጠሩ፣ የዜጎችን ግላዊ መረጃ፣ የፋይናንስ ግብይቶችንና የመንግሥት ሚስጥራዊ መረጃዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የዲጅታል ሉዓላዊነት ዋና መሠረት ሆኗል። ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ሥርዓት መኖሩ ዜጎች በዲጅታል አገልግሎቶች ላይ እምነት እንዲያሳድሩ፣ የግልና የውጭ ባለሀብቶችም በኢትዮጵያ የዲጅታል ኢኮኖሚ ላይ የተሻለ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋል። በዚህም የሳይበር ደህንነት የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስኬትን የሚደግፍ ዋና የጥበቃ መሠረት ሆኖ ይቀጥላል። ማጠቃለያ፡ ዲጂታል ኢትዮጵያ፤ የወደፊት ተወዳዳሪነት መሠረት የኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ጉዞ ከፖሊሲ ቀረጻ እስከ ተግባራዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት ዝርጋታ በፍጥነት እየተሻገረ ይገኛል። ይህ ሀገራዊ ንቅናቄ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሚመራ ሲሆን፣ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ /ፋይዳ፣ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት፣ አምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ልማትና የሳይበር ደህንነት ሥርዓት ዋና ዋና የሽግግሩ ምሰሶዎች ሆነዋል። ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ /ፋይዳ የዜጎችን ዲጂታል ማንነት በማረጋገጥ ለዲጂታል አገልግሎቶች መሠረት ሲሆን፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሕዝብ አገልግሎትን በፍጥነት፣ በቅልጥፍናና በግልጽነት ለማቅረብ አዲስ የአሠራር ባህል እየገነባ ነው። አምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ደግሞ ለዲጂታል ኢኮኖሚው የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል በማፍራት የቴክኖሎጂ ፈጠራና የዲጂታል ሥራ ዕድል እድገትን ያፋጥናል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልማት ተቋማት የወደፊቱን የእውቀትና የፈጠራ አቅም ለመገንባት ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል። በተመሳሳይም የሳይበር ደህንነት ሥርዓት የዲጂታል ኢኮኖሚውን ከስጋቶች የሚጠብቅ፣ የመረጃ ደህንነትንና የሀገር ዲጂታል ሉዓላዊነትን የሚያስከብር ጠንካራ ጋሻ ሆኖ ይቀጥላል። በቴክኖሎጂ፣ በኢኖቬሽንና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለችው መዋቅራዊ እርምጃ የአገር ውስጥ አገልግሎቶችን ከማዘመንና የዜጎችን ኑሮ ከማቅለል ባለፈ፣ ሀገሪቱን በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ አካታችና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚ ባለቤት ለማድረግ የሚያግዝ ነው። ኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ አድማስ፡- '’ኢትዮጵያዊነት ያስተማረን ትልቁ እውነት፤ በጊዜያዊ ፈተናዎች ተሸንፎ መውደቅ ሳይሆን፣ ችግሮችን ወደ ዕድል፣ ፈተናዎችንም ወደ ስኬት መለወጥና ድልን መቀዳጀት ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ቀጣይ የልህቀት ጉዞ ጠንካራ መነሻና መሠረት ይሆናሉ። በመሆኑም ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታዋን ለማፋጠን በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በተቀናጀ መንገድ በጋራ ገቢራዊ ማድረግ ይጠበቅባታል። ዲጂታል ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ራዕይ ብቻ ሳይሆን፤ የእውቀት፣ የፈጠራና የተወዳዳሪነት ሀገራዊ መሠረት ነው።
የመደመር ፍሬ፡አረንጓዴዋ ኢትዮጵያ
Aug 5, 2026 411
በሙሴ መለሰ የመደመር እሳቤ ዋና መሠረቱ እውቀትን፣ጉልበትን፣ሀብትንና አቅምን አስተባብሮ ለአንድ የጋራ ዓላማ በጋራ ማቆምን ያመለክታል። ይህን የሃሳብ ልዕልና በተግባር ፈትሾ ተጨባጭ ውጤት የታየበት ላለፉት ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ የተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ነው። አረንጓዴ ዐሻራ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በ2011 ዓ.ም ጅማሮውን አግኝቷል። የአረንጓዴ ዐሻራ ትልቁ ማሳያ የህዝብ ህብረት የታየበት መሆኑ ነው። በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እድሜ፣ ጾታ እና ልዩነት ሳይበግራቸው በነቂስ በመውጣት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል አኩሪ ታሪክ የሰሩበት ህዝባዊ ንቅናቄ የመደመርን አስተሳሰብ በተግባር ያረጋገጠ ነው። ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ ከተካሄደው የአንድ ጀምበር መርሃ ግብር እንደታየው፣መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያለ ምንም ክፍያ በሙሉ ፈቃደኝነት እና በዝናብ ውስጥ ውሎ ከ805 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ሰርቷል። በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላው 26 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ ኢትዮጵያውያን ተደምረው ለነገ ልጆቻቸው መሰረት ለመጣል ሲወስኑ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለዓለም ህዝብ ያሳዩበት ህያው አብነት ነው። የመደመር እሳቤ በቃላት ሳይሆን በተጨባጭ ውጤት የሚለካ ነው፤ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ ዘመቻ እስካሁን 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ቀሪው 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ደግሞ በቀጣይ ጊዜያት ይተከላል። በአንድ ወቅት ከ40 በመቶ በላይ የደን ሽፋን የነበራት ኢትዮጵያ ዘላቂ ያልሆነ የተፈጥሮ ሃብትና የመሬት አጠቃቀም ምክንያት የደን ሽፋኗ ወደ 3 በመቶ ወርዶ ነበር። አረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ የደን ሽፋን ከነበረበት 17.2 ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ በማሳደግ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ችግኝ ተከላው ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ ከምግብ ዋስትና እና ከሀገር ኢኮኖሚ ጋርም የተሳሰረ ነው። በፍራፍሬ እንደ አቮካዶ፣ማንጎ እና ቡና ባሉ ምርታማ ችግኞች ላይ በማተኮሩ የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባሻገር፣ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የምትበለጽግ፣የማትለምን እና ለተቸገሩት የምትደርስ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል የዜጎችን ገቢ የማሳደግ ድርሻ አለው። ኢትዮጵያ ችግኞችን ለጎረቤት ሀገራት በመስጠት ያከናወነቻቸው የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ስራዎች የመደመር እሳቤ ድንበር አቋርጦ ለአህጉራዊ ትስስር እና ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ የሚሆን ድንበር ተሻጋሪ እሴት እንዳለው ያሳያል። ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዋ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ ምክንያት ሆኗል። ይህም የኢትዮጵያውያን የጋራ ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅናን አስገኝቷል። በአጠቃላይ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን በቀና እሳቤ እና በትብብር በመቆም ተስፋን ለልጆቻቸው መዝራት እንደሚችሉ በተግባር፣በስራና በውጤት ያረጋገጡበት ትልቅ ሀገራዊ ኩራት ነው።
በተቃርኖ የተሞላው ሕገ ወጡ ሕወሓት የጥፋት ጉዞ
Jul 30, 2026 664
የሕገ ወጡ የሕወሓት ቡድን የፖለቲካ ጉዞ በበርካታ መሠረታዊ ተቃርኖዎችና የፖለቲካ ስህተቶች የተሞላ ነው። ቡድኑ በትግል ጊዜም ይሁን ሀገርን በመምራት ባደረገው የፖለቲካ ተሳትፎ ታሪክ ይቅር የማይላቸው ስህተቶችን ፈጽሟል። ከሁሉም በላይ የትግራይን ሕዝብ ለዘመን ተሻጋሪ መከራና ስቃይ ዳርጓል። የወጣቶችን ተስፋ እና ሕልም አጨልሟል። የሕገ ወጡ ቡድን በተቃርኖ የተሞላ ጉዞ በጨረፍታ እንመልከት። ተቃርኖ አንድ፦ የሀገር ገዥነት እና የነጻ አውጪነት መንፈስ ሕገ ወጡ ሕወሓት ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ግንባር ፈጥሮ ሀገር በመራበት ዘመንም ጉዞው በተቃርኖ የተሞላ ነበር። በዚህ የሥልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን፤ ከኅብረት ይልቅ መነጠልን ሥር እንዲሰድ አድርጓል። በስም ደረጃ ሕብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት እንደሚያራምድ ቢናገርም ለኢትዮጵያውያን የተለያየ የዳቦ ስም በመስጠት እርስ በእርስ እንዲጠራጠሩ በማድረግ የጥላቻ ፖለቲካን አንግሷል። የሕግ የበላይነት እና የሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት በአንዱ ቡድን ላይ የማይተገበር ሌላው ላይ ግን ተግባራዊ እንዲሆን አድርጓል። ከቡድኑ ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸው ቡድኖች ለሕግ የማይገዙ፣ ከኮንትሮባንድ እስከ ዓለም አቀፍ ወንጀሎች ውስጥ የሚሳተፉ ነበሩ። ሌላው ጽንፈኛ፣ አክራሪ እና ተስፋፊ ተደርጎ በሽብር እየተወነጀለ በየማረሚያ ቤቱ እንዲንገላታ ተደርጓል። በጥቅሉ ሕገ-መንግሥት እና የፌዴራል ሥርዓትን ለራሱ በሚያመች መልኩ ሲጠቀምበት ቆይቷል። ከዚህም ባለፈ ሕገ ወጡ ቡድን ሀገርን እየመራ እንደ አንድ የክልል ነጻ አውጪ ድርጅት በብሔሮች መካከል ጥርጣሬና ልዩነት እንዲሰፋ የሚያደርጉ የከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካዎችንም አንግሷል። ‘እኛ እና እነሱ’ የሚል ፖለቲካን ከማካሄድ ባለፈ ‘ልዩ ኃይል’ በሚል ወታደራዊ አደረጃጀት ፈጥሮ መንግሥት መስሎ ሀገርን የማፍረስ እና የማዳከም ተግባር ውስጥ ተሳትፏል። ተቃርኖ ሁለት፦ ሰሜን እዝን ባጠቃበት ጊዜ ሕገ ወጡ ቡድን ራሱ ያደራጀውን እና ሲያሞካሸው የቆየውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 2013 ዓ.ም. በማጥቃት የተቃርኖ ጉዞውን መቀጠሉን አረጋግጧል። በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ የትግራይ ሕዝብ ጋሻና መከታ፣ የችግር ጊዜ ደራሽ እና ከሻዕቢያ ተከላካይ ሆኖ ላቡንና ደሙን ገብሯል። ሕገ ወጡ ቡድን የሀገር ሉዓላዊነትና የሕገ-መንግሥት ጠባቂ ነኝ ሲል ቆይቶ፣ ለ20 ዓመታት በትግራይ ሕዝብ ደህንነት ጥበቃ ላይ የነበረውን እና የትግራይ ተወላጆችንም በሠራዊቱ ውስጥ ያቀፈውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አጥቅቷል። ሴረኛው እና በተቃርኖ የተሞላው ቡድን የማይመርዝና የማይለውጠው መሆኑን ያረጋገጠበትን ድርጊት ፈጽሞ የሀገር ጋሻና መከታን አዋርዷል። ይህ ድርጊት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ እጅግ አሳፋሪ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል። የተቃርኖው ውጤት ግን መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልተጠበቀ ሁኔታ አንድ ላይ አስተሳሰረ፤ ለሉዓላዊነትና ለግዛት አንድነት የአባቶቹን ታሪክ እንዲደግም ዕድል ፈጠረ። ተቃርኖ ሦስት፦ የሰላም ውል እና የውስጥ ክፍፍል ሕገ ወጡ ቡድን የሥልጣን ጥመኝነቱን ለማርካት ስፍር ቁጥር የሌላቸው የትግራይ ክልል ተስፋ የሆኑ ወጣቶችን በጦርነት ከማገደ በኋላ የሰላም ስምምነት ተፈረመ። በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ጦርነቱን ለማስቆም የተደረገ ወሳኝ እርምጃ ነበረ። ነገር ግን ከስምምነቱ በኋላ አሁንም ከስህተቱ የማይማረው ይህ ቡድን የተቃርኖ ጉዞውን መቀጠሉን ያረጋገጠበት ጥፋት ፈጸመ። ሕገ ወጡ ቡድን ስምምነቱን በይፋ ከተቀበለው በኋላ ስምምነቱን የሚጥሱ ድርጊቶችን መፈጸም ቀጠለ። መሣሪያ ለማስረከብ ተስማምቶ በስምምነቱ መሠረት መሄድ አቃተው፣ እንቅፋት ፈጠረ። በትጥቅ ውስጥ የቆዩ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ማድረግ ነበረበት፣ አላደረገም። ይልቅስ ለሌላ ጥፋት ውስጥ ለውስጥ መዘጋጀቱን ተያያዘው። ጊዜያዊ አስተዳደር ለመመስረት ተስማምቶ ወደ ተግባር ከተገባ በኋላ የጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮችን አልቀበልም በማለት ሕገ ወጥነቱን ቀጥሎ ለትግራይ ሕዝብ ሰላም እና እፎይታ የሰጠውን የሰላም ስምምነት አፈረሰ። ከጦርነቱ ማብቃት በኋላ ትኩረት መደረግ የነበረበት የወደሙ አካባቢዎችን መገንባት፣ የተፈናቀሉትን መመለስ እና ሰብዓዊ እርዳታ ማፋጠን ላይ መሆን ሲገባው፣ ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ውጭ ይፋ በወጣ የሥልጣን ሽኩቻና የእርስ በእርስ ውንጀላ ውስጥ መዘፈቁ ለሕዝቡ ያለው ግድየለሽነት ማሳያ ሆኖ ተወሰደ። ለጥፋት ተልዕኮው ስኬት በፍጹም የዓላማም ይሁን የትግል አንድነት የለኝም ሲላቸው ከነበሩ የጥፋት ቡድኖች ጋር አበረ። ይህ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመመሳጠር ሉዓላዊነትን ለማስደፈር እና ሀገር ለማፍረስ በሙሉ አቅሙ መንቀሳቀስ ጀመረ። ልብ ማለት የሚገባን ባህር በርን የሚያክል ጉዳይ እንደ ተራ ሸቀጥ ያየው ቡድን እንዴት ስለ ብሔራዊ ክብር እና ሉዓላዊነት ሊያስብ ይችላል? ሊሆን አይችልም። ተቃርኖ አራት፦ የሕገ ወጡ ቡድን የመጨረሻው የጥፋት ጉዞ ዓለምና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ቢቀየርም፣ ሕገ ወጡ ሕወሓት ግን አሁንም በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የትግል ስልት ተከተሏል። ቡድኑ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከሆኑት ባዕዳን ተልዕኮ ተቀብሎ ከሀገር ውስጥ ባንዳዎች ጋር አብሯል። ‘ጽምዶ’ ከተባለው የጥፋት ስብስብ ፊት አውራሪ በመሆን የለመደውን የተቃርኖ ጉዞ ለመቀጠል ተቅበዝብዟል። የወጣቱን የሥራ፣ የዲሞክራሲ፣ የኢኮኖሚና የዘመናዊነት ጥያቄ በትክክለኛ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ወደ ሥልጣን ለመመለስ ለሚያደርገው የቀቢጸ ተስፋ ሙከራ እያደረገ ነው። ከምርጫ ቦርድ ጋር ያለው ሕጋዊ ሰውነት የማጣት አለመግባባት እና በሕጋዊ መንገድ ራሱን ለማደስ ፈቃደኛ አለመሆኑ ቡድኑን በሕግ ፊትም ሆነ በፖለቲካዊ ምህዳሩ ውስጥ ወደ መጨረሻው የመገለልና የውድቀት ምዕራፍ መርቶታል። ዛሬ ግን ትናንት አይደለም። ኢትዮጵያ ዘመኑን በዋጀ አመራር እየተመራች ትገኛለች። ዘመኑን ሙሉ የተቃርኖ ጉዞ ያደረገው ሕገ ወጡ ቡድን ወደ መጨረሻው የፖለቲካ ውድቀት እያመራ ነው። የሕገ ወጡ ቡድን የተቃርኖ ጉዞም የበቃል።
የኢትዮጵያዊያን ምክክር፤ የጋራ ነገን የሚያሻግር የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ድልድይ
Jul 22, 2026 982
በሚኪያስ ጎቡ መግቢያ፡- ሀገራት ከጦርነት በላይ የሚፈትናቸው ጠላት አለ፤ እርሱም በአንድ ሀገር ልጆች መካከል የሚፈጠረው የመተማመን መሰናክል ነው። መሣሪያ የፈጠረውን ጉዳት እንደገና መገንባት ይቻላል። የተሰበረ ልብና የጠፋ መተማመን ግን በጉልበት አይመለስም። ለዚህም ነው ብዙ ሀገራት ከግጭት በኋላ ወደ ምክክር የሚመለሱት። ብሔራዊ ምክክር የአንድ መንግሥት ፕሮጀክት ወይም የፖለቲካ ውድድር አይደለም። የአንድ ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው የሰላም ውርስ ነው። የሚጋጩ ሃሳቦች በጠመንጃ ሳይሆን በቃል ሲገናኙ፣ የተለያዩ ትርክቶች በመደማመጥ ሲቀራረቡ፣ ልዩነቶችም የጥላቻ ምንጭ ሳይሆኑ የመግባባት መነሻ ሲሆኑ ነው እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር የሚፈጸመው። የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳየው ብሔራዊ ምክክር አንድ ዓይነት ቀመር የለውም። እያንዳንዱ ሀገር በታሪኩ፣ በባህሉ፣ በፖለቲካዊ እውነታውና በማኅበራዊ መዋቅሩ መሰረት የራሱን መንገድ ይመርጣል። ነገር ግን የሁሉም ግብ አንድ ነው፤ ግጭትን በመግባባት፣ ጥላቻን በመተማመን፣ ፍርሃትን በተስፋ መተካት። በአውሮፓ ከኮሙኒዝም ውድቀት በኋላ፣ በአፍሪካ ከአምባገነናዊ አስተዳደሮች ሽግግር ወቅት፣ በደቡብ አሜሪካ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሂደቶችና በዓረቡ ዓለም ከፖለቲካ አብዮቶች በኋላ የተካሄዱ ምክክሮች አንድ ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ። ምክክር ሲታመን ሀገር ያድናል፤ ለፖለቲካ ጥቅም ሲውል ግን ቀውስን ያባብሳል። ይህ የኢትዮጵያም ትልቁ ፈተና ነው። ሀገራዊ ምክክር የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ወገን ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት ነው። የምንናገረው ቃል፣ የምንጽፈው ሐሳብ፣ የምናዳምጠው አቋምና የምንቀበለው ልዩነት የነገዋን ኢትዮጵያ ይቀርጻሉ። ምክክር የሚጀምረው በአዳራሽ ሳይሆን በሰዎች ልብ ውስጥ ነው፤ የሚሳካውም ከመናገር በላይ በመደማመጥ ሲቻል ነው። ስለዚህ የዛሬው ጥያቄ "ምክክር ይካሄድ ወይ?" የሚል አይደለም። "ምክክሩን ለሀገር የሚበጅ፣ ለትውልድ የሚተርፍ፣ ለታሪክ የሚያስከብር እንዴት እናድርገው?" የሚለው ነው። መልሱም በአካታችነት፣ በእውነት፣ በመከባበርና በሀገርን ከግል ጥቅም በላይ በማስቀደም ውስጥ ይገኛል። ምክክር፤ የሀገር መድኃኒት ወይስ የትውልድ ፈተና? ምክክር ለምን ያስፈልጋል?፡- ማንኛውም ሀገር የሚያድገው በሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ግንባታ ብቻ አይደለም። በሕዝቦቿ መካከል በሚኖረው መተማመን ጭምር እንጂ። መንገድ፣ ድልድይና ፋብሪካ መገንባት ይቻላል፤ ነገር ግን የተሰበረ ማኅበራዊ ትስስር ካልተጠገነ የልማቱ መሠረት ይናወጣል። ስለዚህ ብሔራዊ ምክክር የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን የሀገር የወደፊት ዕጣ ፋንታ የሚወሰንበት የጋራ አስተሳሰብ ሂደት ነው። የምክክሩ ዋና ዓላማ አሸናፊና ተሸናፊ መፍጠር አይደለም። ይልቁንም ሁሉም ወገኖች የራሳቸውን እውነት እየገለጹ፣ የሌላውንም እውነት በማዳመጥ የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት ሂደት ነው። እውነተኛ የምክክር ድል የሚለካውም የማን ሃሳብ አሸነፈ ሳይሆን ለሀገር ምን ያህል ሰላምና መተማመን ፈጠረ በሚለው ነው። የዓለም ተሞክሮ የሚያስተምረን፡- የታሪክ ገጾች እንደሚያሳዩት ሀገራት የብሔራዊ ምክክርን መንገድ የመረጡት ሌሎች አማራጮች ሲያቅቷቸው ነው። አንዳንዶቹ የረዥም ጊዜ የፖለቲካ ቀውስ ነበራቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ በዘር፣ በሃይማኖት ወይም በሥልጣን ሽኩቻ ተከፋፍለው ሲራኮቶ የሰነባበቱ ናቸው። ነገር ግን የተሳካላቸው ሀገራት አንድ የጋራ መርህ ነበራቸው፤ የሀገርን ጥቅም ከፓርቲ፣ ከቡድንና ከግል ጥቅም በላይ አስቀድመዋል። ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ወደ ዴሞክራሲ የተሸጋገረችው በበቀል ሳይሆን በሰለጠነ ምክክር ነው። ፖላንድና ሀንጋሪ የፖለቲካ ሽግግራቸውን በየጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር አሳልፈዋል። ላይቤሪያና ሊባኖስ የጦርነት ቁስላቸውን ለማዳን የመደማመጥን መንገድ መርጠዋል። በተቃራኒው ግን ምክክርን ለፖለቲካ ሕጋዊነት ማግኛ፣ ለሥልጣን ማራዘሚያ ወይም ለውጭ ጫና ማስታገሻ ብቻ ያደረጉ ሀገራት የበለጠ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። ይህም አንድ ግልጽ ትምህርት ይሰጠናል፤ የምክክር ስኬት የሚወሰነው በመድረኩ ሳይሆን በተመካካሪዎች ቅንነት መሆኑን ያስረዳናል። ምክክር የሚጠይቀው ከባድ ኃላፊነት፡- ሀገራዊ ምክክር የኮሚሽን ወይም የመንግሥት ሥራ ብቻ አይደለም። የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነትን የሚጠይቅ የጋራ ነገ አሻጋሪ ድልድይና የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ነው። ፖለቲከኛው የሀገርን ጥቅም ማስቀደም፣ የሚዲያው እውነትን በሚዛናዊነት ማቅረብ፣ የሲቪክ ማኅበራት የተገለሉ ድምፆችን ማሰማት፣ የኃይማኖት ተቋማት ይቅርታና መቻቻልን ማስፋፋት፣ ወጣቱ ከጥላቻ ይልቅ ውይይትን መምረጥና ምሁራን በማስረጃ የተደገፈ ሃሳብ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ማንም ወገን የራሱን አቋም ብቻ ለማስገደድ ከሞከረ፣ ምክክሩ ወደ ክርክር ይቀየራል። ሁሉም ለመረዳት እንጂ ለማሸነፍ ካልመጡ ደግሞ የምክክሩ መንፈስ ይጠፋል። የሀገራዊ ምክክር ትልቁ ድል የሌላውን አቋም መለወጥ ሳይሆን፣ የሌላውን ህመም መረዳት ነው። ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር፤ ልዩነታቸው ምንድን ነው?፡- ብዙ ጊዜ ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር የሚሉት ቃላት በአንድ ትርጉም ይጠቀሳሉ። ነገር ግን በፖለቲካዊና በማኅበራዊ ሂደቶች እያንዳንዳቸው የተለየ ዓላማና ባህሪ አላቸው። ይህንን ልዩነት አለማወቅ ሀገራዊ ምክክርን ከመጀመሪያው ሊያዛባው ይችላል። ውይይት የሐሳብ ልውውጥ ነው። ሰዎች ስለ አንድ ጉዳይ አመለካከታቸውን ይገልጻሉ፣ ይደማመጣሉ። ሁልጊዜ ውሳኔ ላይ ላይደርስ ይችላል። ክርክር የሚያተኩረው የማን ሃሳብ ትክክል እንደሆነ ላይ ነው። የራስን አቋም በማስረጃ ለማስረዳት ይደረጋል፤ አንድ አሸናፊና አንድ ተሸናፊ ሊኖር ይችላል። ድርድር ደግሞ የጥቅም ግጭትን በመካከለኛ መፍትሔ ለመፍታት የሚደረግ ሂደት ነው። እያንዳንዱ ወገን ከአቋሙ በመቀነስ የጋራ መፍትሔ ለማግኘት ይሞክራል። ሀገራዊ ምክክር ግን ከእነዚህ ሁሉ የላቀ ሂደት ነው። ዓላማው ማንንም ማሸነፍ ወይም ማስሸነፍ ሳይሆን የሀገር የወደፊት አቅጣጫ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ነው። በምክክር ውስጥ የሚሸነፍ ሰው የለም፤ የሚያሸንፈው ሀገር ነው። የኢትዮጵያ ልዩ እውነታ፡- ኢትዮጵያ ሦስት ሺህ ዘመናትን የተሻገረ በሕብር ያሸበረቀ ታሪክ፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ፣ ቋንቋ፣ ባህልና ኃይማኖት ያላት ሀገር ናት። ይህ በሕብር ያሸበረቀ ልዩነት የኢትዮጵያ ጥንካሬ መሆን ሲገባው በተለያዩ ወቅቶች የፖለቲካ አለመግባባቶችና የታሪክ ትርክቶች የመከፋፈል መሣሪያ ሆነው ቆይተዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ፈተናም ይህ ነው። ሁሉም የራሳቸውን ታሪክ ይዘው ወደ ጠረጴዛው ይመጣሉ፤ ነገር ግን ከጠረጴዛው የሚወጡት አንድ የጋራ የወደፊት ርዕይ ይዘው መሆን አለባቸው። ይህ ቀላል አይደለም። ስለዚህ ምክክሩ ከቃላት በላይ በተግባር የሚገለጥ ቅንነትን ይፈልጋል። የዋናው ምክክር ጉባኤ የህዝብ ወኪል ተመካካሪዎችም ሀገርን የማስቀደም ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ስኬታማ ምክክር የሚመሰረትባቸው አምስት ምሰሶዎች፡- ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ቢያንስ አምስት መሠረታዊ ምሰሶዎች ሊኖሩት ይገባል። እነሱም መተማመን፣ አካታችነት፣ እውነት፣ ፍትሕና የጋራ ርዕይ ናቸው። ከሁሉም ክልሎች፣ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እና በውጭ ከሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበራሰብ የሕዝብ ወኪል 4 ሺ ተመካካሪ ኢትዮጵያዊያንም በሀገር ግንባታ ጉዳይ፣ የመንግስት አደረጃጃትና ስርአት ጉዳይ፣ የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ ከተሞች ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ ሙስናና የመልካም አስተዳዳር ጉዳዮች፣ የሰላም ግንባታ ጉዳዮች በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽ ማዕከል እየመከሩ ይገኛል። ሀገራዊ ምክክር ያለፈውን ለመቁጠር ሳይሆን፣ የወደፊቱን ለመገንባት የሚደረግ የጋራ ጉዞ ነው። የኢትዮጵያ መንገድም የልዩነት ግድግዳን የሚያፈርስ የትውልድ አደራና የብሔራዊ መግባባት ማሰሪያ ጥበብና ትልም ሆኖ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፤ የተገኙ ዕድሎች፣ ዋና ፈተናዎች እና የወደፊት አቅጣጫ በታሪክ ጉዞዋ ውስጥ ኢትዮጵያ ብዙ የፈተና ዘመናትን አልፋለች። አንዳንዶቹ ፈተናዎች ከውጭ ጥቃት የመጡ ቢሆኑም፣ አብዛኞቹ ግን ከውስጣዊ አለመግባባቶች፣ ከተለያዩ የታሪክ ትርክቶች፣ ከፖለቲካ ፉክክርና ከመተማመን እጥረት የተፈጠሩ ናቸው። ስለዚህ የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት የዛሬን ችግር ለመፍታት ብቻ ሳይሆን፣ የትውልድ ዕዳን ለማቃለል የተጀመረ ታሪካዊ ሂደት ነው። ይህ ሂደት ቀላል አይደለም። በርካታ ዓመታት የተከማቹ ቅሬታዎች፣ የተለያዩ እውነታዎች፣ የተቃራኒ ትርክቶችና የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መገናኘታቸው በራሱ ትልቅ ፈተና ነው። ነገር ግን ከዚህ በላይ ትልቁ ፈተና ልዩነትን ወደ መግባባት መቀየር ነው። ዕድሎች፤ ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ወሳኝ መስኮቶች፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ የምታነሳበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። የታሪክ አተረጓጎም፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የሥልጣን ክፍፍል፣ የሀብት አጠቃቀም፣ የፍትሕ ጉዳዮችና የአብሮነት ዕሴቶች በጦርነት ሳይሆን በሐሳብ የሚፈቱበት ዕድል ይፈጥራል። ከዚህም በላይ ምክክሩ የፖለቲካ ባህልን ለመቀየር የሚያስችል ዕድል ነው። ለብዙ ዓመታት "አሸናፊና ተሸናፊ" በሚለው አስተሳሰብ የተመራውን ፖለቲካ ወደ "አብሮ ማሸነፍ" የሚሸጋግር ከሆነ እውነትም የኢትጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ጠንካራ መሠረት ያገኛል። በሂደቱ ፊት የሚቆሙ ፈተናዎች፡- ማንኛውም ሀገራዊ ምክክር ከፍተኛ ተስፋ እንደሚፈጥር ሁሉ ከባድ ፈተናዎችንም ይዞ ይመጣል። የመጀመሪያው ፈተና የመተማመን እጥረት ነው። ለብዙ ዓመታት የተገነባ ጥርጣሬ በጥቂት ወራት አይጠፋም። ስለዚህ የምክክሩ ተዓማኒነት በእያንዳንዱ እርምጃ ሊገነባ ይገባል። ሁለተኛው ፈተና የተለያዩ የታሪክ ትርክቶች ናቸው። አንድ ክስተት በአንዱ ወገን የድል ታሪክ ሲሆን፣ በሌላው ወገን የመከራ ታሪክ ሊሆን ይችላል። ይህን ልዩነት በክብር መቀበል እንጂ መግፋት አይቻልም። በሌላ መልኩም የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ ስርጭት ነው። በዲጂታል ዘመን አንድ ያልተረጋገጠ መረጃ በጥቂት ደቂቃዎች ሺዎችን ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ የሚዲያ ተቋማትና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚወስዱት ኃላፊነት ከመቼውም በላይ ወሳኝ ይሆናል። የምሁራንና የመገናኛ ብዙኅን ሚና፡- በብሔራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ምሁራን ስሜትን ሳይሆን ማስረጃን ማቅረብ አለባቸው። የማኅበረሰብ ችግሮችን በሳይንሳዊ ጥናት መተንተን፣ ከሌሎች ሀገራት ልምድ መማርና አማራጭ መፍትሔዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። መገናኛ ብዙኅንም በዚህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው። መገናኛ ብዙኅን ወሬን ከማባዛት ይልቅ እውነትን ማጣራት፣ ልዩነትን ከማባባስ ይልቅ መግባባትን ማጎልበት፣ ስሜትን ከማቀጣጠል ይልቅ እውነታን ማቅረብ አለበት። ምክክሩን የሚያጠናክር የመገናኛ አውታር ታሪክ ይሠራል፤ የሚያደናቅፍ ደግሞ በታሪክ ይጠየቃል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ቀን የሚጠናቀቅ ክስተት አይደለም። ምክክር በትውልድ የሚገነባ የፖለቲካ ባህል ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራውን ሊጨርስ ይችላል፤ ነገር ግን የመደማመጥ ባህል በሕዝብ ውስጥ ካልሰረጸ የምክክሩ እውነተኛ ዓላማ አይሳካም። የዛሬ ውሳኔ፤ የነገ ኢትዮጵያ፡- አንዳንድ የታሪክ ወቅቶች በየቀኑ አይመጡም። አንዳንድ ውሳኔዎችም የአንድ መንግሥት ዘመንን ብቻ ሳይሆን የትውልዶችን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ሀገራዊ ምክክር የእነዚህ ታሪካዊ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ዛሬ በምንመርጠው የምክክር ባህል፣ በምንገነባው መተማመንና በምናሳየው የፖለቲካ ብስለት ላይ የነገዋን የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ተምሳሌት ኢትዮጵያ ያንፃል። ምክክር ሁሉንም ችግር በአንድ ጊዜ የሚፈታ አስማታዊ መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ጦርነትን ከውይይት፣ ጥላቻን ከመቻቻል፣ መከፋፈልን ከመተባበር የሚተካ ብልህ መንገድ ነው። የሚያደርገውም ልዩነቶችን ማጥፋት ሳይሆን ልዩነቶችን በአንድ ሀገር ጣሪያ ስር እንዴት እንደሚኖሩ የጋራ ሕግና ሥርዓት መፍጠር ነው። በእርግጥ ኢትዮጵያ ከባድ ፈተናዎችን አሳልፋለች። የፖለቲካ አለመተማመን፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የፀጥታ ችግሮች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎችና የማኅበራዊ ስብራቶች በቀላሉ የሚያልፉ አይደሉም። ይሁን እንጂ እነዚህን ችግሮች በጥይት ከመፍታት ይልቅ በምክክር ለመፍታት መሞከር በራሱ የታሪክ ለውጥ ነው። ይህ ጉዞ ግን የአንድ ተቋም ብቻ አይደለም። የመንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኅን ተቋማት፣ የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶችና የእያንዳንዱ ዜጋ የጋራ ኃላፊነት ነው። የሀገር ዕጣ ፋንታ ለአንድ ቡድን ብቻ የሚተው አይደለም፤ በጋራ የሚገነባ እንጂ። ከምክክር ወደ ባህል፡- ምክክሩ ተጠናቀቀ ማለት የሀገሪቱ ችግሮች ተፈቱ ማለት አይደለም። እውነተኛው ስኬት የሚለካው የመደማመጥ ባህል በማኅበረሰቡ ውስጥ ሲሰርጽ ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመገናኛ ብዙኅን፣ በፖለቲካ ተቋማትና በየቤቱ የመነጋገር ባህል ካልጠነከረ፣ ምክክሩ የሰነድ ውጤት ብቻ ሆኖ ይቀራል። የእውነተኛ ዴሞክራሲ መሠረት ተመሳሳይ አስተሳሰብ መኖር አይደለም፤ የተለያዩ አስተሳሰቦችን በሰላም የመቀበል ባህል መኖር ነው። ልዩነት የችግር ምንጭ ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ ሲሆን ነው አንድ ሀገር ዘላቂ ሰላም የምታገኘው። የማጠቃለያ፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚያስፈልገው ብልህ አመራር ብቻ አይደለም፤ ታጋሽ ዜጎችንም ይፈልጋል። ሀገር የምትገነባው በግንብ ሳይሆን በመተማመን ነው። ሰላም የሚጸናውም በፍርሃት ሳይሆን በፍትሕ ነው። ዛሬ የምንመርጠው የምክክር መንገድ ነገ ለልጆቻችን የምንተወው ታሪክ ይሆናል። ስለዚህ በኢትዮጵያን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተደራጅተው የሚመከርባቸው ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች የዛሬ አጀንዳ ብቻ አይደሉም፤ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚቀርጽ የትውልድ አደራ እንጂ። የዋናው ምክክር ጉባኤ ተመካካሪ የሕዝብ ወኪሎችም ከግልና ቡድን ፍላጎት ይልቅ የቀጣዩን ትውልድና ሀገርን ማስቀደም ይጠበቅባቸውል። ምክክር የቃላት ልውውጥ ብቻ አይደለም፤ የተሰበረ መተማመንን የሚጠግን፣ የተከፋፈለ ማኅበረሰብን የሚያቀራርብ፣ የትውልድ ታሪክን በአዲስ ተስፋ የሚጽፍ ሀገራዊ ጥበብ ነው። የምንወስነው ዛሬ የምንወርሰውን ነገ ይበይናል። ምክክር የሀገር መድኅን ነው፤ ኢትዮጵያም እየመከረች ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 11525
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 21396
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 14424
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20176
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
ከካይሮ ሴራ ጀርባ፤ የCNN ዘገባ የገለጠው የኢትዮጵያ እውነት
Aug 4, 2026 1089
ግብፅ በታሪኳ የዓባይን ወንዝ በብቸኝነት ለመጠቀም የተከተለችው ዋና ስልት "ጠንካራና የተረጋጋች ኢትዮጵያ ለካይሮ ስጋት ናት" የሚል ቀመርን ነው። በመሆኑም በየዘመናቱ የተነሱ የካይሮ መንግስታት ኢትዮጵያ ተረጋግታ ሀብቷን እንዳታለማ ለማድረግ ረዥም ርቀት ተጉዘዋል። በታሪክ አጋጣሚ የዓባይን መነሻ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር በርካታ የወረራ ሙከራዎችን ያደረገችው ግብጽ፣ በጉንደት (1875) እና በጉራዕ (1876) በተደረጉ ታሪካዊ ውጊያዎች በኢትዮጵያውያን ጠንካራ ክንድ መራራ ሽንፈትን አስተናግዳለች። ከቀጥታ ጦርነት ከተመለሰች በኋላ ካይሮ ስልቷን ወደ "ውስጥ ለውስጥ ማበጣበጥ" ቀይራለች። ይህም የኢትዮጵያን መንግስት ትኩረትና የፋይናንስ አቅም ከልማት ፕሮጀክቶች (በተለይም ከታላቁ ህዳሴ ግድብ እና መሰረተ ልማቶች) ወደ ጸጥታ ማስከበር እንዲዞር ለማድረግና ሀገሪቱን ወደማያልቅ የውስጥ ብጥብጥ ለመክተት በርካታ ሴራዎችን ስታከናውን ቆይታለች። ይህ አልሳካ ሲላት ደግሞ የሀሰት መረጃዎችን ማሰራጨትን እንደ አማራጭ መንገድ ስትጠቀም ቆይታለች፤ እየተጠቀመችም ትገኛለች። የግብፅ የፖለቲካ ምሁራንና ዲፕሎማቶች የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ “ግድቡ በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ የከፋ ጉዳት ያደርሳል” በሚል የሐሰት ትረካቸውን ሲያሰራጩና ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ሲያሳስቱ ቆይተዋል። ሆኖም ግን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥበብ የተሞላበት አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ የውጭ ተፅዕኖዎችንና የውስጥ ፈተናዎችን በመሻገር ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት ከፍፃሜ ማድረስ ችላለች። ይህም የመደመር እሳቤ የሆነው ፈተናን ወደ እድል የመቀየር ትልቁ ማሳያ ነው። የግድቡን እውን መሆን ተከትሎም የካይሮ ተደጋጋሚ የሀሰት ቅሬታና የተዛባ ፕሮፓጋንዳም ዘግይቶም ቢሆን እውነቱ በዓለም ፊት እየተገለጠ ይገኛል።በCNN “Connecting Africa” ወርሃዊ ፕሮግራም ላይ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ ያቀረበችው ዘገባ የዚሁ እውነት ማሳያ ነው። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2020 የቢቢሲ የኮምላ ዱሞር ሽልማት አሸናፊ የሆነችው ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ፣ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ በሚገኝበት ጉባ ተገኝታ ባከናወነችው ዘገባ የካይሮን ምናባዊ ቅዥት የሚያፈርሱ ተግባራዊ እውነቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ አድርጋለች። የምህንድስና ልህቀት እና የጋራ ልማት ማሳያ፦ CNN በዘገባው ስለ ሕዳሴ ግድብ ለዓመታት ሲነገር የቆየውን የሀሰት ሴራ ሳይሆን፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የምህንድስናና የግንባታ ባለሙያ ኢትዮጵያዊያን ጥረትን እውን ያደረገ የኢንጂነሪንግ ልህቀት አብነት መሆኑን አጉልቶ አሳይቷል። የግብፅ መንግስት ግድቡን “የስጋት ምንጭ” አድርጎ ለማሳየት ቢጥርም፣ የCNN ዘገባ ግን ግድቡ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ ቀጣናው የተዘረጋ የጋራ እድገት መድረክ መሆኑን አብራርቷል። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር መስከረም 2025 በይፋ የተመረቀው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት በማሳደግ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት እያበራ መሆኑን በማሳየትም፤ ግድቡ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑን በተግባር ገልጧል። የጋዜጠኛ ሩባዲሪ ዘገባ የግብፅን ተደጋጋሚ ቅሬታና ሴራ በሶስት ዋና ዋና ነጥቦች ውድቅ ያደርጋል። የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ፦ ግድቡ የታችኞቹን የተፋሰሱ ሀገራት የማይጎዳ፣ ይልቁንም የውሃ ፍሰትን በማስተካከልና ደለልን በመቀነስ ረገድ አዎንታዊ ሚና የሚጫወት፣ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ ፕሮጀክት መሆኑን የግድቡ ግንባታ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ሃሳብን በማካተት ጭምር አሳይታለች። ቀጣናዊ የመደመር እሳቤ ማሳያ ፦ ግድቡ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ በመሸጥ ገቢ ከማግኘቷም ባለፈ፣ የቀጣናውን ሀገራት በኃይልና በኢኮኖሚ የሚያስተሳስር ነው። ይህ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሚመራው የመደመር መንግስት እሳቤ ማለትም “በጋራ ማደግ እና እርስ በእርስ መደጋገፍ” የሚለውን ቀጣናዊ ራዕይ በተግባር የሚያረጋግጥ እንጂ ግብፅ እንደምትለው ቀጣናውን ወደ አለመረጋጋት የሚከት አለመሆኑን ያመላክታል። ሰው ተኮር የኢኮኖሚ ሽግግር፦ በCNN ዘገባ የተካተቱት የኢንተርናሽናል ግሮውዝ ሴንተር (IGC) የኢትዮጵያ ኃላፊ ቴዎድሮስ መኮንን በግልጽ እንዳስቀመጡት፤ 70 በመቶው ህዝቧ ከ30 ዓመት በታች የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ከ15 ዓመታት በፊት ከነበረችበት ከአማካይ በታች የነበረ የነፍስ ወከፍ ገቢ አሁን በአፍሪካ ከሚገኙ ግዙፍ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት አንዷ መሆን ችላለች። ግድቡም ይህንን ወጣት ኃይል ወደ ዘላቂ ምርታማነት ለመቀየር የሚደረገው ጥረት አካል ነው። መደምደሚያ፦ በአጠቃላይ ግብፅ ግድቡን መሰረት በማድረግ የምታካሂደው የዲፕሎማሲና የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የፖለቲካ ቁማር እንጂ ከሳይንሳዊና መሬት ላይ ካለው እውነት ጋር እንደማይገናኝ የCNN ዘገባ በግልጽ አሳይቷል። በሀገር ውስጥ አቅም እና በጥበብ በተሞላ ሀገራዊ አመራር እውን የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያን መጻኢ የኢኮኖሚ ጊዜ የሚቀርጽ፣ የአፍሪካ ቀጣናን በኃይልና በንግድ የሚያስተሳስር የልማት ማማ እንጂ የትኛውንም ሀገር የሚጎዳ ስጋት አይደለም። የመደመር እሳቤ ያጎናፀፈው ይህ የታሪካዊ ድል ብርሃንም መላውን ቀጣና ማብራቱን ቀጥሏል።
ዓይነ ስውሩ የቧንቧ ሰራተኛ
Jul 31, 2026 1246
ዋግ ኽምራ፤ሐምሌ 24/2018 (ኢዜአ) ፦"ዓይኖቼ ማየት ባይችሉም እጆቼ ተዓምር ይሰራሉ'' -ዓይነ ስውሩ የቧንቧ ሰራተኛ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መለስ ጌታነህ የ62 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ አዛውንት ናቸው፤ ከጊዜ በኋላ በመጣ ችግር የሁለት ዓይኖቻቸውን ብርሃን ያጡ ቢሆንም በአካባቢው ስመ ጥር የቧንቧ ሠራተኛ ናቸው። ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ገና በወጣትነት ዕድሜያቸው የቧንቧ ሥራ ሙያን ቀስመው፣ በዋግ ኽምራ በሚገኙ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ለንጹሕ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት አሻራቸውን እያሳረፉ ያሉ ትጉህ ባለሙያ ናቸው። ቆላ በመውረድ፣ ደጋ በመውጣት፣ ተራራና ሸንተረሩን ሳይበግራቸው የውሃ መስመር በመዘርጋት ህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ እንዲደርሰው እያደረጉ ያሉ አዛውንት ናቸው። ለዚህም በተደጋጋሚ የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በ1991 ዓ.ም የተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ ሲጀምር እሳቸው በቧንቧ ባለሙያነት በቋሚነት በመቀጠር፣ የውሃ መስመር በመዘርጋትና በመጠገን የሕክምና ክፍሎች ያልተቋረጠ ውሃ እንዲያገኙ ማድረግ ችለዋል። ይሁን እንጂ ከዕለታት በአንድ ቀን ሥራቸውን እያከናወኑ ባሉበት ወቅት ባላወቁት ምክንያት የሁለት ዓይኖቻቸውን ብርሃን ያጡበት አጋጣሚ በመከሰቱ ከቤት ለመዋል መገደዳቸውን ያወሳሉ። እንደ አቶ መለስ ገለጻ፡ “ዓይኔ ማየት ባለመቻሉ ራሴን ችዬ መንቀሳቀስ፣ እንደልቤ ሜትር ዘርግቼ ለክቼ መቁረጥና ገደል ላይ ተንጠልጥዬ የቧንቧ መስመር መዘርጋት አልችልም የሚል የተሸናፊነት ስሜት አድሮብኝ ተስፋ ቆርጬ ተቀምጬ ነበር” ይላሉ። በዚህ ወቅት ትጋታቸውንና ብርታታቸውን የሚያውቁ የሆስፒታሉ ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር ዓለማየሁ ትኩ፣ ወደ ሆስፒታሉ በመውሰድና በመምከር ሥራቸውን እንዲቀጥሉ እንዳገዟቸው አውስተዋል። ቀስ በቀስም አቶ መለስ ሜትር በመዘርጋትና መጋዝ በመጨበጥ ልኬታን አስተካክለው፣ መገጣጠሚያ ቦታዎችን በዳበሳ ለይተው የቧንቧ ሙያ ሥራቸውን እንደገና “ሀ” ብለው ማስቀጠላቸውን አመልክተዋል። ምንም እንኳን ከወረዳ ወረዳ ተንቀሳቅሶ መሥራት ባይችሉም፣ በግለሰብ ቤቶችና ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱ የቧንቧ ጥገና ሥራቸውን በብቃት እያከናወኑ ያሉ ብቁ ባለሙያ ሆነው ቀጥለዋል። በሆስፒታሉም ከአገልግሎት ውጭ የነበሩ የውሃ መስመሮችን በመለየትና በአግባቡ በመጠገን፣ ለሐኪሞችና ለሕመምተኞች ወጥ የሆነ የንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ “አንቱ” የተባሉ ባለሙያ ሆነዋል። አቶ መለስ በቧንቧ ሥራ ሳይገደቡ፣ በራዲዮ በሚቀርቡ የቴክኖሎጂ ፕሮግራሞች ባገኙት እውቀት ከአገልግሎት ውጭ የነበረውን የሆስፒታሉን የላውንድሪ (ልብስ ማጠቢያ) ማሽን በዳበሳ ጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ሆስፒታሉን ከወጪ ታድገዋል። “ብርሃን ከዓይን ብቻ ሳይሆን ከልብና ከመዳፋችንም ይገኛል” የሚሉት አቶ መለስ፣ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ምጣዶችን በመጠገንና ሌሎችንም የቴክኒክ ሥራዎች በመሥራት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩ ጠንካራ የዕድሜ ባለፀጋ ናቸው። "የዓይን ብርሃኔን አጣሁ ብዬ አንድም ቀን አስቤ አላውቅም” የሚሉት አቶ መለስ፣ አሁን ላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ጣራ ላይ በመውጣት ጭምር ቧንቧ ጠግነው የሚወርዱ ባለሙያ ሆነዋል። “እኔ ሥራ ሳልሠራ ስውል ያመኛል” የሚሉት አቶ መለስ፣ ወጣቱ ሥራን ሳይንቅ ከሰራ ከትንሽ ነገር ተነስቶ ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችል ምክራቸውን ለግሰዋል። ስለ ጉዳዩ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተፈራ ኃይሉ ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ቢምረው እንዳሉት፡ ጋሽ መለስ የዓይን ብርሃናቸውን ቢያጡም በሙያቸው የትጋትና የ“ይቻላል” ተምሳሌት የሆኑ አዛውንት ናቸው። አዛውንቱ በሙያቸው የሆስፒታሉ የውሃ አቅርቦት እንዳይቋረጥ በማድረግ ለሕክምና ሥራ መቀላጠፍ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ገልጸው ለሌሎች ባለሙያዎች በታታሪነት፣ በሥራ ፍቅር እና በጥንካሬ አርዓያ መሆናቸውንም ገልጸዋል።