ቀጥታ፡

አገልግሎቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል

አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን አስታወቀ።

አገልግሎቱ የ2018 በጀት ዓመት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት እና የፋይናንስ አፈጻጸሙን እንዲሁም በ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱ ዙሪያ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፤ አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ በተከናወኑ በርካታ ተግባራት የደንበኞቹን ቁጥር 5 ነጥብ 88 ሚሊየን ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።

ከደንበኞች አገልግሎት አንጻር በቅድመ ክፍያ 82 ነጥብ 6 እንዲሁም በድህረ ክፍያ 15 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱንም አክለዋል።

በበጀት ዓመቱ 664 ሺህ 505 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸው፤ ይህም ከዕቅዱ አንጻር 83 ነጥብ 1 በመቶ መከናወኑን ተናግረዋል።

አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ 118 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ለደንበኞች ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

በኤሌክትሪክ ሀይል ማሰራጫ መስመር መሰረተ ልማት ዝርጋታና ጥገና ላይም ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

በዚህም ያረጁ የማሰራጫ መስመሮችን ከመጠገን አንጻርም በበጀት ዓመቱ 4 ሺህ 892 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ የጥገና ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም