ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
ሮተሪ ኢትዮጵያ በ70 ዓመታት የኢትዮጵያ ቆይታው በጤናው ዘርፍ ትርጉም ያለው ሥራ ሰርቷል - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Jan 28, 2026 54
አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2018(ኢዜአ)፦ ሮተሪ ኢትዮጵያ በ70 ዓመታት የኢትዮጵያ ቆይታው በጤናው ዘርፍ ትርጉም ያለው ሥራ መስራቱን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። ሮተሪ ኢትዮጵያ የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመቱን በብሔራዊ ቤተ-መንግስት አክብሯል። በዝግጅቱም የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንትና የሮተሪ ኢትዮጵያ የበላይ ጠባቂ ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ፍራንሲስኮ ኦሬዞ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።   ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ሮተሪ ኢትዮጵያ ባለፉት 70 ዓመታት በጤና አገልግሎቶችና ሌሎች የልማት ዘርፎች ትርጉም ያለው ሥራ ሰርቷል። የጤና አገልግሎት ጥራትና ደረጃን ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራትም ፖሊዮን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ተናግረዋል። ሮተሪ ኢትዮጵያ ልዩ እሴቶች እና ቁርጠኝነት ያለው ተቋም ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ የፖሊዮ በሽታን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦም አመስግነዋል።   የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ ሮተሪ ኢትዮጵያ ፖሊዮን ከኢትዮጵያ በማጥፋትና በሌሎች የጤና ዘርፎች ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም ከሮተሪ ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር የጤና ሥርዓቱን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።   የሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ፍራንሲስኮ ኦሬዞ በበኩላቸው፤ ሮተሪ ኢንተርናሸናል በኢትዮጵያና ሌሎች ሀገራት ፖሊዮን የማጥፋት ዘመቻ ላይ በቢሊዮን ዶላር በላይ መድቦ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎትና ደረጃ ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ገንቢ ሚና ለመወጣት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩልም ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ፍራንሲስኮ አሬዞን ጋር በጤና፣ በትምህርት፣ በሰላም ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተወያይተዋል።   በውይይቱም ሮተሪ ኢትዮጵያ የፖሊዮ በሽታን ከኢትዮጵያ በማጥፋት እና በሌሎች መስኮች ያከናወናቸው ተግባራት ገለፃ ተደርጓል። በቀጣይም በኢትዮጵያ በጤና፣ በሰላም ግንባታና ተያያዥ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት መስኮች በትብብር መስራት የሚስችል የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል። ሮተሪ ኢንተርናሽናል በዓለም ከ46 ሺህ በላይ ክለቦች ያሉት ሲሆን፤ በኢትዮጵያም በአዲስ አበባ፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ በጅማና በአዋሳ የሚገኙ ክለቦቹ በማህበረሰብ ተኮር ሥራዎች ላይ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።
የኢኮኖሚና የንግድ ዕድሎችን በማስፋት የበለፀገች አፍሪካን ለመገንባት በትብብር እንሰራለን
Jan 28, 2026 90
አዲስ አበባ፤ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡-የኢኮኖሚና የንግድ ዕድሎችን በማስፋት የበለፀገች አፍሪካን ለመገንባት በትብብር እንደሚሰሩ የአፍሪካ ሕብረትና አሜሪካ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው ጋር በትብብር መስራት በሚቻልባቸው የሰላምና ልማት ጉዳዮች ላይ በመወያየት የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ፤ አፍሪካ በብዙ ፀጋዎችና ሀብቶች የተሞላች አህጉር ናት ብለዋል። የአፍሪካን ሃብቶች ለዜጎቿ ተጠቃሚነት ለማዋልም በሚከናወኑ ተግባራት አህጉሪቷ የአሜሪካንን የዕውቀት፣ የሙያ፣ የአቅም ግንባታና ቴክኖሎጂ ትብብር ትፈልጋለች ብለዋል፡፡   የህብረቱ አባል ሀገራት የውስጥ አቅማቸውን በማሳደግ፣ በሲቪል እና ንግድ ማህበረሰብ አማካኝነት የልማት መርሃ ግብሮችን በራሳቸው ገንዘብ በመደገፍ ተስፋ ሰጪ አቅም እየገነቡ መሆኑን አንስተዋል። የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲና ትብብር ስርዓት ተጠናክሮ መቀጠል በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም ገልጸዋል፡፡ በአፍሪካ ሀገራትና በአሜሪካ መካከል በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ የጋራ ዕድገትን ማስፋት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው በበኩላቸው፤ የአፍሪካ ህብረት የአህጉሪቷን ሰላምንና የኢኮኖሚ ልማት ለማረጋገጥ ከአባል ሀገራት ጋር በመተባበር ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል ብለዋል። ​የአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ በጋራ ደኅንነት፣ ሰላምና እና ብልጽግና ጉዳዮች በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የበለፀገች አፍሪካ መኖር ለአሜሪካም ጥቅም ነው ያሉት የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ አፍሪካ ያላትን ዕምቅ የኢኮኖሚና የንግድ ዕድሎችን በጋራ ጥቅም ላይ ለማዋል እንሰራለን ብለዋል፡፡ አሜሪካ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ መርህ እንዳላት በማንሳት፤ የኢኮኖሚ ዕድገት ዕድሎችን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል። ከአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄነራል አንደርሰን ጋር ያደረጉት የሥራ ጉብኝትም አሜሪካ የአሕጉሪቷን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ካላት ቁርጠኝነት የሚመነጭ መሆኑን አስረድተዋል። አፍሪካውያን ችግራቸውን በራሳቸው አቅም መፍታት እንደሚችሉ በማንሳት፤በአፍሪካውያን የውስጥ ጉዳይ ማንም ጣልቃ መግባት እንደሌለበት እናምናለን ብለዋል፡፡
አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን ኢንቨስትመንት የማስፋት ፍላጎት አላት-የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው
Jan 28, 2026 116
አዲስ አበባ፤ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፦አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት ተደራሽነት ለማስፋት እና ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት የሀገሪቷ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው ገለጹ። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው ጋር ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች እና የኢትዮጵያና አሜሪካን ትብብር እንዲሁም እያደገ የመጣውን አጠቃላይ አጋርነት ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው።   የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል። የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች ጠንካራ ለውጥ እንደታየባቸው ገልጸው፥ የኢኮኖሚ እድገት አዝማሚያ እና በቁልፍ ዘርፎች ያለው የኢንቨስትመንት ምህዳር የተሻለ መሻሻል እንዳሳየ የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ጠንካራ አጋርነት እንዳላቸው ገልጸው፥ በቅርቡ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ጤና ዘርፍ ያደረገችውን ድጋፍ ጠቅሰዋል። አሜሪካ ለኢትዮጵያ ልማት እያደረገች ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል። በሌላ በኩል ሚኒስትሩ ለአሜሪካው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቅርቡ ግንባታው ስለተጀመረው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ገለጻ አድርገዋል። አየር ማረፊያው ለእድገት፣ ቀጣናዊ ትስስር እና ንግድ መሳለጥ ያለውን ስትራቴጂካዊ ሚና ያነሱ ሲሆን የአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማት እና ተቋራጮች ፕሮጀክቱን እንዲደግፉ ጠይቀዋል።   የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው፥ የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች በማድነቅ አሜሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ያላትን ተሳትፎ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል። አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያ እና አሜሪካን አጋርነት ለማጠናከር፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን ለመደገፍ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በኢነርጂ ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ
Jan 28, 2026 93
አዲስ አበባ፤ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በኢነርጂ መስክ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትስስር ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በ27ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ሶማሊያ ሞቃዲሾ ገብተዋል። የገንዘብ ሚኒስትሩ ከስብስባው አስቀድሞ ከአውሮፓ ኮሚሽን የዓለም አቀፍ አጋርነት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሜሪያም ፌራን ጋር ውይይት አድርገዋል። በስብስባው ላይ ሚኒስትሩ እና ምክትል ዳይሬክተር ጀነራሏ የሁለቱን ወገኖች ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተወያዩ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ አካል የሆነው የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የትራንስፖርት ኮሪዶር በሚያደርገው የፋይናንስ ድጋፍ አስመልክቶ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአውሮፓ ህብረት ለማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የሚያደርገውን ድጋፍ ማጠናከር እንደሚገባም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል። በተለይም ህብረቱ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅራቢ መስመሮችን በታዳሽ ኃይል እና በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች በማዘመን ዘላቂ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ የኃይል አቅርቦት የማረጋገጥን አላማ ላለው ፕሮግራም (RISED) የሚያደርገውን ድጋፍ ለአብነት አንስተዋል። 27ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብስባ ለኃይል ማሰራጫ መሰረተ ልማቶች እና ለቀጣናዊ የኢነርጂ ትስስር ስራዎች የፋይናንስ አቅርቦትን በማሳደግ አስተማማኝ እና ተመጣጣኝ የኢነርጂ አቅርቦትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክር የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
የዴሞክራሲ ተቋማት ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ለመልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ ነው
Jan 28, 2026 51
ባህር ዳር፣ጥር 20/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የዴሞክራሲ ተቋማት ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ለመልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በክልሉ የሚገኙ የዴሞክራሲ ተቋማት ስራ ክንውን የግብረመልስ ሪፖርት ላይ ከአማራ ክልል ምክር ቤት አመራሮችና ከተቋማቱ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ እውነቴ አለነ፤ በክልሉ የዴሞክራሲና የሚዲያ ተቋማት የስራ እንቅስቃሴ በጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ተቋማቱ በተለይም ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ለመልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን አንስተው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትና የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋማትም ለሰብአዊ መብት መከበርና አስተዳደራዊ በደሎችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ተገንዝበናል ሲሉ ተናግረዋል። የቋሚ ኮሚቴው አባል አቶ ጋሻው ዳኘው፤ በክልሉ የሚገኙ የፌደራል የሚዲያና የዴሞክራሲ ተቋማት ተልዕኳቸውን በመፈጸም ረገድ ውጤታማ ስለመሆናቸው አንስተዋል። በሰላም እና የጋራ ትርክት ግንባታ፣ ሀገራዊ የምክክር ሂደት፣ የልማት ስራዎችን የማስተዋወቅና ሌሎች ተግባራት ላይ የሚዲያዎቹ ጥረት መልካም መሆኑን አንስተው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ፤ የዴሞክራሲ ተቋማት የክልሉን ህዝብ በማገልገል ረገድ አበረታች ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን አይተናል ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም የሚዲያና የዴሞክራሲ ተቋማቱ መልካም ጅምሮች ቀጣይነት እንዲኖራቸው አስፈላጊውን ትብብርና እገዛ እናደርጋለን ብለዋል።
የሚታይ

በቀን እስከ 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውኃ ማቅረብ የሚያስችለው የጭቋላ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ እየተፋጠነ ነው-የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
Jan 28, 2026 69
አዲስ አበባ፤ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡-በቀን እስከ 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውኃ ማቅረብ የሚያስችለው የጭቋላ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑን የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ገለጸ። በሌላ መልኩም የገርቢ ንጹህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር አስታውቋል። የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በቀን እስከ 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውኃ የማቅረብ አቅም ያለው የጭቋላ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ በአሁኑ ወቅት በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል። 22 የውኃ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ የሲቪልና የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራዎችን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትም በተሳለጠ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።   የጭቋላ ፕሮጀክት በተያዘው በጀት ዓመት በከፊል እንደሚጠናቀቅ ጠቁመው፥ በ2019 በጀት ዓመት ደግሞ ሙሉ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስረድተዋል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም የምዕራብ አዲስ አበባ፣ ጀሞ፣ ቤቴል፣ ሳር ቤት እንዲሁም የአቃቂ አካባቢ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። በሌላ በኩል፣ ለመዲናዋ ተጨማሪ ውኃ የማቅረብ አቅምን የሚያሳድገው የገርቢ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታን ለመጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ፕሮጀክቱ በቀን ከ73 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ውኃ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን፤ በርካታ የመዲናዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አብራርተዋል። ፕሮጀክቱ በመዲናዋ ያለውን የውኃ አቅርቦትና ፍላጎት ለማጣጣም በሚደረገው ጥረት ውስጥ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ፕሮጀክቱ ወደ ግንባታ ምዕራፍ እንደሚሸጋገር አስታውቀዋል። የውኃ አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ከእነዚህ በተጨማሪ ወደ ሥራ ለማስገባት ተጠንተው የተቀመጡ ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ የግንባታ ሥራቸውን ለማስጀመርም የፋይናንስ ማፈላለግ ሥራዎች ጎን ለጎን እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
Jan 28, 2026 103
አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፦ ዜጎች በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ አማራጮች ለሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች እና የማጭበርበር ድርጊቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አሳሰበ። ማህበረሰቡ የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርቧል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ)፤በኢትዮጵያ የዲጂታል ትስስር መስፋፋትን ተከትሎ በዋትሳፕ (WhatsApp)፣ በቴሌግራም (Telegram) እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ ፕላትፎርሞች አማካኝነት በዜጎች ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችና የማጭበርበር ድርጊቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸዉን በተለያዩ መንገዶች ማረጋገጥ መቻሉን ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በሀገሪቷ የሚካሄዱ የተለያዩ ሲምፖዚየሞችን፣ ዓለም አቀፍ መድረኮችን እና የኦንላይን ስብሰባዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ የሳይበር ወንጀለኞች የእነዚህን ኩነቶች ስም ለሀሰተኛ ድርጊቶቻቸው መጠቀሚያ እያደረጉት እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካላት የማህበረሰቡን የግል መረጃ ለመስረቅ፣ የባንክ ሂሳቦችን ለመመዝበር እና የዲጂታል ደህንነትን ለማናጋት በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ መሆኑን አስተዳደሩ በክትትልና በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል። የሳይበር ጥቃቶች የሚፈጸሙት ማህበረሰቡ ትኩረት የሚሰጣቸውን "ተፈላጊ" እና "ወቅታዊ" የሆኑ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ በተዘረጋ ስልታዊ የማታለያ ዘዴ መሆኑን ተጠቁሟል። አጭበርባሪዎቹ "ለሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች የተዘጋጀ ነጻ የኢንተርኔት ፓኬጅ"፣ "ልዩ የስራ ቅጥር" ወይም "ይህ የስብሰባ መሳተፊያ ሊንክ ነው፤ ከፍተው ይግቡ" የሚሉ አሳሳችና ማራኪ መልዕክቶችን በማሰራጨት ተጠቃሚዎች በመልዕክቱ ውስጥ የተካተተውን ሊንክ (Link) እንዲጫኑ እንደሚያደርጉ የገለጸው አስተዳደሩ፥ ይህ ድርጊት ተጠቃሚው ሳያውቀው ወደ አጥፊ ተልዕኮ ወዳላቸዉ ድረ-ገጾች እንዲያመራና ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርግ የመጀመሪያው የወንጀለኞች እርምጃ እንደሆነ አመልክቷል። ጥቃት አድራሾቹ የአንዳንድ ግለሰቦች የግንዛቤ እጥረትና ትኩረት ማጣት የተነሳ የሚላኩላቸውን ሊንኮችና መልዕክቶች በጥንቃቄ የመመርመር ዕድላቸው አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ ወንጀለኞቹ ይህን ሁኔታ እንደ ምቹ አጋጣሚ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ነው ያለው። ይህ አይነቱ ጥቃት ከግለሰቦች መረጃ ስርቆት ባለፈ፣ በእጃቸው የሚገኙ ሚስጥራዊ መረጃዎች በጠላፊዎች እጅ እንዲወድቁ በማድረግ በሀገር ደህንነትና ሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የሚጋርጥ መሆኑን አስተዳደሩ በጥብቅ አሳስቧል። በዚህም ተጠቃሚዎች የተላከላቸውን ሊንክ ሲጫኑ ወይም የተጠየቁትን መረጃ ሲሞሉ፣ የዋትሳፕ ወይም የቴሌግራም አካውንታቸው ወዲያውኑ በጠላፊዎች ቁጥጥር ስር እንዲዉል እንደሚያደርግም ነው በመግለጫው ላይ የሰፈረው። ወንጀለኞቹ አንዴ የአንድን ሰው አካውንት ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ የተጠለፈውን አካውንት በመጠቀም በተጎጂው ስም ለቅርብ ወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ "ድንገተኛ ችግር አጋጥሞኛል" የሚሉ የሀሰት የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄዎችን ይልካሉ። ይህም ድርጊት በማህበረሰቡ መካከል ያለውን መተማመን ከመሸርሸሩ ባለፈ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በማጭበርበር እንዲመዘበር በማድረግ መጠነ-ሰፊ የኢኮኖሚና የስነ-ልቦና ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ነው ተቋሙ ያስታወቀው። ከላይ የተጠቀሱና መሰል የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ፣ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኢመደአ አሳስቧል። ከማይታወቁ ወይም ካልተረጋገጡ አድራሻዎች በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች መድረኮች የሚላኩ ሊንኮችን ካለመክፈት ባለፈ፣ አጠራጣሪ መልዕክቶች ሲደርሱ ወዲያውኑ "Report" እና "Block" በማድረግ የጥቃቱን ስርጭት መግታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል። በተጨማሪም ማንኛውንም አይነት ሚስጥራዊ የይለፍ ቃል ወይም በስልክ የሚላክ የማረጋገጫ ኮድ (Verification Code) ለማንም አካል አለመስጠት ለዲጂታል ደህንነት ወሳኝ መሆኑን አመልክቷል። አስተዳደሩ እያንዳንዱ ተጠቃሚ በተለይም ማህበረሰቡ በመተግበሪያዎቹ ላይ የሁለትዮሽ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) በአስቸኳይ እንዲተገብር መክሯል። ይህ የቴክኖሎጂ የመረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን አካውንት በቀላሉ እንዳይቆጣጠሩ የሚያደርግ እና ተጨማሪ የደህንነት ቁልፍ የሚፈጥር አስተማማኝ የመከላከያ ዘዴ እንደሆነ ገልጾ ዜጎች ይህንን ቀላል ግን ውጤታማ የሆነ የደህንነት ጥንቃቄ ተግባራዊ በማድረግ፣ ራሳቸውን በቴክኖሎጂ ከታገዙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሊታደጉና የሳይበር ወንጀለኞችን ሴራ ሊያከሽፉ እንደሚገባ አስተዳደሩ ያሳሰበው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እነዚህን የሳይበር ወንጀለኞች በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው የጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል። ማህበረሰቡ ማንኛውም የሳይበር ጥቃት ሙከራ ሲያጋጥመው ወይም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት በነጻ ስልክ መስመር 933 በመደወል ለኢመደአ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል። የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በንቃትና በጥንቃቄ በመምራት የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በጋራ መጠበቅ እንደሚገባም መግለጫው አትቷል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን ስኬታማ ለማድረግ ድጋፍና ክትትል ይጠናከራል 
Jan 28, 2026 114
ጂንካ ፤ ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡-የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን ስኬታማ ለማድረግ ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አለማየሁ ባውዲ ገለፁ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ የተመራ ቡድን በደቡብ ኦሞ ዞን በና-ፀማይ፣ ሐመር እና ኛንጋቶም ወረዳዎች በመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።   ቡድኑ የመስኖ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድ፣ የአዳሪ እና መደበኛ ትምህርት ቤቶች፣ የእንስሳት ህክምናና የሽያጭ ማዕከላትን ጨምሮ ሌሎች የግንባታ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ጎብኝቷል። የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አለማየሁ ባውዲ፤ በደቡብ ኦሞ ዞን ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ፕሮጀክቶች በመገንባት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። በክልሉ ተግባራዊ የተደረጉት እነዚሁ የልማት ፕሮጀክቶች በነዋሪዎች ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ መሆኑንም ነው የተናገሩት።   መንግስት የክልሉ ህዝብ ለሚያነሳቸው የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተግባራዊ ያደረጋቸው የልማት ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑም ምክር ቤቱ ድጋፍና ክትትሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያረጋገጡት። የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤካል ነትር በበኩላቸው፥ ምክር ቤቱ የድጋፍና ክትትል ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉ ይበልጥ ስኬታማና የተሻሉ ስራዎችን ለመስራት ያግዛል ነው ያሉት። በአሁኑ ወቅት ተጠናቀው አገልግሎት በመስጠት ላይ ካሉት ፕሮጀክቶች ባሻገር ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ 68 የሚደርሱ የመስኖና የውሃ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን ተናግረዋል።   በግንባታ ላይ ያሉ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመስኖ፣ የመንገድና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ከተያዘላቸው ጊዜ ቀድሞ ለማጠናቀቅ እና ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል። የኦሞ ወንዝ ቀደም ሲል በነበረው ጊዜ ለመጓጓዣነት እና ለዓሳ ማስገር ብቻ ይውል እንደነበር የገለጹት ደግሞ የካራ -ዱስ ቀበሌ ነዋሪ አርብቶ አደር ላሌ ሙኮ ናቸው። አሁን መንግስት በአካባቢው የመስኖ አውታር በመገንባቱ ወንዙን ለተለያዩ አገልግሎቶች ለማዋል መቻሉን አክለዋል።   በአካባቢው በተገነቡት የጤና ተቋማትና ትምህርት ቤቶችም ነዋሪውን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል 
Jan 28, 2026 140
አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡-39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲካሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ አዲስ አበባ የምታስተናግዳቸው ታላላቅ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች በስኬት እንዲጠናቀቁ ተቋሙ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ የሀገራት መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎችና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች የተሳተፉባቸው ስብሰባዎች በመዲናዋ መካሄዳቸውን አስታውሰዋል። እነዚህ መድረኮች ያለምንም ችግር በስኬት መጠናቀቃቸው የፖሊስን እና የሌሎች የጸጥታ ተቋማትን የዝግጁነት ደረጃ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።   ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የውጭ ሀገር መሪዎችና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት የሚሳተፉባቸውን ታላላቅ ስብሰባዎች የማስተናገድ የዳበረ ተሞክሮ እንዳላት ጠቅሰዋል። 39ኛውን የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ በስኬት ለማካሄድ ከጉባኤው በፊት መከናወን ያለባቸው የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በውጤታማነት መፈጸማቸውን ገልፀዋል። ለጉባኤው ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ የበርካታ ሀገራት መሪዎችና እንግዶችን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ፣ የትራፊክና የጸጥታ እንቅስቃሴን ማቀናጀት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።   ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የሀገሪቱን ገጽታ በሚመጥን መልኩ ለጉባኤው ስኬታማነት የጸጥታና ደህንነት ሥራዎች በተደራጀ አግባብ እንደሚከናወኑም አረጋግጠዋል። እንግዶች ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገቡበት ጊዜ ጀምሮ ጉባኤውን አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው እስኪመለሱ ድረስ ተገቢው የእጀባና ሌሎች አገልግሎቶችን የተቀላጠፈና አስተማማኝ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ነው ያስታወቁት። የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በየዓመቱ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ መድረክ ሲሆን፣ የፀጥታው ዘርፍ ዝግጁነት ለጉባኤው ስኬታማነት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።   39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 7-8 ቀን 2018 ዓ.ም “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓትን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ የህብረቱ ዋና መስሪያ ቤት ይካሄዳል።
በዞኑ የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ህዝቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ያለው ቅንጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል
Jan 28, 2026 77
ነጋዴ ባህር፤ ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡-በምእራብ ጎንደር ዞን የተገኘውን ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ ህዝቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ያለው ቅንጅት ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በምእራብ ጎንደር ዞን በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ "ሠላም ለሁሉም ሁሉም ለሠላም" በሚል መሪ ሀሳብ ህዝባዊ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የምእራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ፤ የተገኘውን ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ ህዝቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በአካባቢው ሰላም በመስፈኑ የልማት ስራዎች እየተፋጠኑ መሆኑን ገልጸዋል።   የተገኘውን ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላም ግንባታ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አመልክተዋል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተወካይ ብርጋዴር ጀኔራል ሙላው በየነ፣ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ማህበረሰቡ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል። በተለይም የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ታጣቂ ኃይሉ መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ እንዲቀበል በማድረግ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን ተናግረዋል። ህዝቡ ከጸጥታ ሃይሉ ጎን በመሰለፍ በተከናወነ የህግ ማስከበር ስራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን አመልክተዋል። በቀጣይም ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ ህዝቡ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።   ከውይይት ተሳታፊዎች መካከል የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነዋሪ አቶ አበበ ቢሰጥ እንዳሉት፤ የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ የሚጠበቅባቸውን መወጣታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። አካባቢያቸውን ተደራጅተው በመጠበቅ የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ከጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ የተናገሩት ደግሞ የወረዳው ነዋሪ አቶ እሸቱ መልካሙ ናቸው። በመድረኩ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች፣ የዞንና ወረዳ የስራ ኃላፊዎችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አከባበር ላይ መሳተፋችን ግንኙነታችንን ለማደስ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል - የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አርኤም
Jan 27, 2026 171
አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አከባበር ላይ መሳተፋችን ግንኙነታችንን ለማደስ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አርኤም ገለጹ። የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው ዕለት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ (ዩኤስ-አፍሪኮም) አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አርኤም አንደርሰንን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ በዚሁ ወቅትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት ለማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን የጋራ መግለጫም ሰጥተዋል፡፡ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በውይይታቸው ሁለቱ ሀገራት የቆየ ግንኙነት ቢኖራቸውም አሁን እያደገ የመጣውን ከፍተኛ የዲፕሎማሲና ወታደራዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማሳደግ እኩል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡   በተጨማሪም በሰላምና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸውንና የሁለቱንም ሀገራት ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ አሸባሪነትን በጋራ ለመዋጋት መስማማታቸውንም ተናግረዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ (ዩኤስ-አፍሪኮም) አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አርኤም አንደርሰን በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ለማክበር ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ታሪክን ለማሰላሰልና የወደፊት ትብብርን ለማጠናከር ትርጉም ያለው አጋጣሚ እንደሆነ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አከባበር ላይ ለመገኘትና ለመሳተፍ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንደገና ለማየትም ዕድል እንደሰጣቸው በመግለጫቸው ጠቅሰዋል፡፡ ጉብኝቱ በተለይም የጋራ ቀጣናዊ የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታትና የአጋርነት ዕድሎችን ለመጠቀም እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ትልቅ አጋጣሚ ስለመፍጠሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ከመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ ዕድል የፈጠረ በመሆኑ ለስኬቱ የበኩላችንን እንወጣለን  
Jan 27, 2026 160
አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018(ኢዜአ)፦ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት የቆዩ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ ዕድል የፈጠረ በመሆኑ ለስኬታማነቱ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡት የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ ምክክሩ ለዘላቂ ልማትና ለሕዝቦች ትስስር መሠረት የሚጥል ነው። ሂደቱ የኢትዮጵያውያንን ነባር የመመካከርና የመቻቻል እሴቶች መሠረት ያደረገ መሆኑ ደግሞ ይበልጥ ውጤታማና ለሕዝብ ቅርብ ያደርገዋል ብለዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል ሀጂ ሀሰን ቀላ በሰጡት አስተያየት፤ የምክክር ኮሚሽኑ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የሚያስችል መልካም አጋጣሚ ይዞ መምጣቱን ገልጸዋል።   ምክክሩ የሕዝብ በመሆኑ እኛም እንደ ሀገር ሽማግሌ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት ለመወጣት ተዘጋጅተናል ያሉት ሀጂ ሀሰን በጠረጴዛ ዙሪያ መመካከር ወንድማማችነትን በማጎልበት አንድነትን ለማጠናከር የላቀ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ቦሩ ሮባ በበኩላቸው፤ ከምክክር የተሻለ የችግር መፍቻ አማራጭ እንደሌለ በማንሳት፥ የተፈጠረውን ዕድል በመጠቀም ሁሉም ዜጋ ከግብ ማድረስ እንዳለበት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።   ሀገራዊ ምክክሩ የሕዝቡን ነባር የችግር መፍቻ እሴቶች በመጠቀም ስኬታማ እንደሚሆን ገልጸዋል። በተመሳሳይ አቶ ጎሊቻ አሬሮ እንደገለጹት፤ ምክክር በኢትዮጵያ ባሕል ውስጥ የቆየ የችግር መፍቻ ጥበብ ነው።   በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰከን ብሎ መመካከር ከተቻለ፣ ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርግና ለትውልዱ መሰረት የሚሆን አሻራ ማኖር ይቻላል ነው ያሉት። ወይዘሮ ሞሌ ቦሩ፤ በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ላይ በንቃት በመሳተፍ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ በምክክር እንዲቀረፉ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።   ሴቶች ያላቸውን ባሕላዊና ማኅበራዊ እሴቶች ተጠቅመው ለተረጋጋች ሀገር ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል። ነዋሪዎቹ ሀገራዊ ምክክሩ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በዘላቂነት ለማስቀጠል ዓይነተኛ መፍትሔ መሆኑንም ገልጸዋል።
በሐረሪ ክልል በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችን የማስቀጠል ተግባር በትኩረት ይከናወናል - ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
Jan 27, 2026 87
ሀረር፤ ጥር 19/2018(ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል በሁሉም ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን የማስቀጠል ተግባር በትኩረት እንደሚከናወን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ። የሐረሪ ክልል ብሔራዊ ጉባዔ 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት አካሄዷል።   ጉባዔው ባለፉት ስድስት ወራት በቅርስ ጥበቃና የሐረሪ ቋንቋን በማሳደግ ረገድ የተከናወኑ ተግባራትን በክልሉ ባህል ቅርስ፣ ቱሪዝምና ትምህርት ቢሮዎች በኩል ቀርበው ገምግሟል። የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በጉባዔው ላይ እንዳሉት፤ ባለፉት 6 ወራት በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል። በክልሉ በቅርስ ጥበቃና የሐረሪ ቋንቋን በማሳደግ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል። በተለይም የጁገል ቅርስን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ላይ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን አመልክተዋል።   በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እና ለዜጎች ተስፋ የሰጡ መሆናቸውንም አክለዋል። ሆኖም የክልሉን ልማት ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች መኖራቸውን በመጠቆም ፅንፈኞችን በመታገል የጀመርናቸውን የልማት ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። በዚህም በተጀመሩ የልማት ስራዎች ላይ የአስተሳሰብና የአመለካከት አንድነትን በማጎልበትና ማህበረሰቡን በባለቤትነት በማሳተፍ ረገድ የተሰሩ ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ጉባዔው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

ማህበራዊ
ሮተሪ ኢትዮጵያ በ70 ዓመታት የኢትዮጵያ ቆይታው በጤናው ዘርፍ ትርጉም ያለው ሥራ ሰርቷል - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Jan 28, 2026 54
አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2018(ኢዜአ)፦ ሮተሪ ኢትዮጵያ በ70 ዓመታት የኢትዮጵያ ቆይታው በጤናው ዘርፍ ትርጉም ያለው ሥራ መስራቱን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። ሮተሪ ኢትዮጵያ የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመቱን በብሔራዊ ቤተ-መንግስት አክብሯል። በዝግጅቱም የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንትና የሮተሪ ኢትዮጵያ የበላይ ጠባቂ ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ፍራንሲስኮ ኦሬዞ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።   ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ሮተሪ ኢትዮጵያ ባለፉት 70 ዓመታት በጤና አገልግሎቶችና ሌሎች የልማት ዘርፎች ትርጉም ያለው ሥራ ሰርቷል። የጤና አገልግሎት ጥራትና ደረጃን ለማሻሻል በተከናወኑ ተግባራትም ፖሊዮን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ተናግረዋል። ሮተሪ ኢትዮጵያ ልዩ እሴቶች እና ቁርጠኝነት ያለው ተቋም ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ የፖሊዮ በሽታን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦም አመስግነዋል።   የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ ሮተሪ ኢትዮጵያ ፖሊዮን ከኢትዮጵያ በማጥፋትና በሌሎች የጤና ዘርፎች ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም ከሮተሪ ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር የጤና ሥርዓቱን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።   የሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ፍራንሲስኮ ኦሬዞ በበኩላቸው፤ ሮተሪ ኢንተርናሸናል በኢትዮጵያና ሌሎች ሀገራት ፖሊዮን የማጥፋት ዘመቻ ላይ በቢሊዮን ዶላር በላይ መድቦ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም የኢትዮጵያን የጤና አገልግሎትና ደረጃ ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ገንቢ ሚና ለመወጣት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩልም ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከሮተሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት ፍራንሲስኮ አሬዞን ጋር በጤና፣ በትምህርት፣ በሰላም ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተወያይተዋል።   በውይይቱም ሮተሪ ኢትዮጵያ የፖሊዮ በሽታን ከኢትዮጵያ በማጥፋት እና በሌሎች መስኮች ያከናወናቸው ተግባራት ገለፃ ተደርጓል። በቀጣይም በኢትዮጵያ በጤና፣ በሰላም ግንባታና ተያያዥ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት መስኮች በትብብር መስራት የሚስችል የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል። ሮተሪ ኢንተርናሽናል በዓለም ከ46 ሺህ በላይ ክለቦች ያሉት ሲሆን፤ በኢትዮጵያም በአዲስ አበባ፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ በጅማና በአዋሳ የሚገኙ ክለቦቹ በማህበረሰብ ተኮር ሥራዎች ላይ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።
የዴሞክራሲ ተቋማት ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ለመልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ ነው
Jan 28, 2026 51
ባህር ዳር፣ጥር 20/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የዴሞክራሲ ተቋማት ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ለመልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በክልሉ የሚገኙ የዴሞክራሲ ተቋማት ስራ ክንውን የግብረመልስ ሪፖርት ላይ ከአማራ ክልል ምክር ቤት አመራሮችና ከተቋማቱ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ እውነቴ አለነ፤ በክልሉ የዴሞክራሲና የሚዲያ ተቋማት የስራ እንቅስቃሴ በጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ተቋማቱ በተለይም ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ለመልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን አንስተው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትና የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋማትም ለሰብአዊ መብት መከበርና አስተዳደራዊ በደሎችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ተገንዝበናል ሲሉ ተናግረዋል። የቋሚ ኮሚቴው አባል አቶ ጋሻው ዳኘው፤ በክልሉ የሚገኙ የፌደራል የሚዲያና የዴሞክራሲ ተቋማት ተልዕኳቸውን በመፈጸም ረገድ ውጤታማ ስለመሆናቸው አንስተዋል። በሰላም እና የጋራ ትርክት ግንባታ፣ ሀገራዊ የምክክር ሂደት፣ የልማት ስራዎችን የማስተዋወቅና ሌሎች ተግባራት ላይ የሚዲያዎቹ ጥረት መልካም መሆኑን አንስተው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ፤ የዴሞክራሲ ተቋማት የክልሉን ህዝብ በማገልገል ረገድ አበረታች ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን አይተናል ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም የሚዲያና የዴሞክራሲ ተቋማቱ መልካም ጅምሮች ቀጣይነት እንዲኖራቸው አስፈላጊውን ትብብርና እገዛ እናደርጋለን ብለዋል።
ቡሳ ጎኖፋን ለማጠናከር የለማ የመኸር ሰብል እየተሰበሰበ ነው
Jan 28, 2026 116
ሮቤ ፤ ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡-በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ባሌ ዞን ቡሳ ጎኖፋን ለማጠናከር የለማው የመኸር ሰብል በሜካናይዜሽን ታግዞ እየተሰበሰበ መሆኑን የዞኑ ቡሳ ጎኖፋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ። ቡሳ ጎኖፋ የገዳ ስርዓት አካል ሲሆን፤ የኦሮሞ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥመው እርስ በእርስ ተደጋግፎ ችግሩን የሚያልፍበት ዘዴ ነው።   አሁን ላይ ሥርዓቱ ህጋዊ መሰረት እንዲኖረው ከተደረገ በኋላ የተፈጥሮ አደጋዎችን ጨምሮ የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት ጥረት እየተደረገ ነው። የዚሁ እንቅስቃሴ አካል የሆነው የቡሳ ጎኖፋ ሥርዓት ውጤታማ ከሆነባቸው የክልሉ አካባቢዎች የምሥራቅ ባሌ ዞን ተጠቃሽ ነው።   የምሥራቅ ባሌ የቡሳ ጎኖፋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፉአድ አብዱ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የቡሳ ጎኖፋ ስርዓትን ይበልጥ ለማጠናከርና ተቋማዊ መሰረት እንዲኖረው ለማድረግ ባለፈው መኸር አዝመራ በ2 ሺህ 153 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ማልማት ተችሏል። የለማው መሬት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ1 ሺህ 700 ሄክታር ብልጫ እንዳለው አስታውቀዋል።   በመኸር አዝመራው ከለማው መሬትም ከ65 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ ምርት ለማግኘት መታቀዱን ገልጸው እስካሁን በተካሄደው እንቅስቃሴ በሜካናይዜሽን በመታገዝ 38 ሺህ ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል። ቀሪው በመኸር አዝመራ የለማ ስንዴ ከብክነት በጸዳ መልኩ በሜካናይዜሽንና በሰው ኃይል ታግዞ እየተሰበሰበ እንደሚገኝ አውስተዋል። የቡሳ ጎኖፋ ስርዓትን ይበልጥ ለማጠናከር ከሰብል ልማቱ ጎን ለጎን የሥርዓቱን ዓላማ ብዙዎች ዘንድ በማስረጽ 370 ሺህ አባላት ማፍራት መቻሉን አስረድተዋል።   ቡሳ ጎኖፋ በአሁኑ ወቅት ከ28 ሚሊዮን በላይ አባላት በክልሉ ያሉት ሲሆን ከአባላቱ የሚሰበሰበው ዓመታዊ መዋጮ 3 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉ ተመልክቷል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ በምሥራቅ ባሌ ዞን በመገኘት የቡሳ ጎኖፋን ለማጠናከር እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትና ሌሎች የልማት ሥራዎችን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ የውሃ አቅርቦትና ጤናማ ምኅዳር ግንባታ ውጤቶች ለአሕጉራዊ አጀንዳ 2063 ግቦች ስኬት ወሳኝ ድርሻ ይኖራቸዋል
Jan 28, 2026 190
አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ ዘላቂ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ጤናማ ምኅዳር ግንባታ ውጤቶች ለአሕጉራዊ አጀንዳ 2063 ግቦች ስኬት ወሳኝ ድርሻ እንደሚኖራቸው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። የዘንድሮው 39ኛ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ’’ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ ከየካቲት 7- 8/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የውሃ አቅርቦት ዘላቂነትና ንጽህና አጠባበቅ፣ ጤናማ ማህበረሰብና ጠንካራ ምኅዳር ግንባታ፣ የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀምና የዜጎች ኑሮ ማሻሻያ ከአጀንዳ 2063 ግቦች ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ናቸው። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ የንጹህ ውሃና የኃይል አቅርቦት የልማት ስኬቶች ከአፍሪካ ሕብረት አጀንዳዎች ጋር ተጣጥመው እየተተገበሩ ነው።   በንጹህ መጠጥ ውሃና ኃይል አቅርቦት እንዲሁም በዜጎች ጤናማ የመኖሪያ ምኅዳር ግንባታ መስክ በአሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዘላቂ ልማት ግቦች ጋር ተሰናስለው የሚተገበሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ለአብነትም ኢትዮጵያ በዘላቂ የልማት ግቦች መነሻነት ከ80 ሚሊየን በላይ ዜጎቿን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ እንደቻለች አስረድተዋል። በ2030 ዓ.ም ዕቅድም ሁሉም ኢትዮጵያውያን በቤታቸው ወይም በአቅራቢያቸው የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ስኬታማ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ተጋላጭ በሆኑ የኢትዮጵያ አካባቢዎችም በመንግስትና በፕሮጀክት በጀት ድርቅን የሚቋቋም አስደናቂ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት መሠረተ ልማት መገንባቱን አስታውቀዋል። በኃይል አቅርቦት ዘርፍም የኃይል አማራጭ ልማትን በማስፋት በከተማና ገጠር ከሥነ-ምኅዳር ደኅንነት ጋር የተጣጣመ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ አንስተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት የተተገበረው የወንዝ ዳር ልማት የውሃ ሀብት ደኅንነትን በመጠበቅ ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ለአብነትም በአዲስ አበባ እና በሁሉም የውሃ አካላት በወንዝ ዳር ልማት የውሃ ሀብት ብክለትን በማስቀረት ዜጎች ንጹህና ጤንነቱ በተጠበቀ አካባቢ የሚኖሩበትን ዕድል እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ በንጹህ መጠጥ ውሃና በኃይል አቅርቦት እንዲሁም በውሃ አካላት ደኅንነት ያስመዘገበችው ውጤት ዘላቂ የልማት ግቦች በማሳካት አህጉራዊ ተምሳሌትነቷን እያስመሰከረች እንደሚገኝ አስረድተዋል።   የኢትዮጵያ የዘላቂ ልማት ግቦች ስኬታማ ጉዞም የአየር ንብረት ተጽዕኖን በመቀነስ አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎችን እውን እንዲሆኑ ለማስቻል ከፍተኛ ሚና እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል። በአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ መነሻነት የተሰሩ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የጽዱ-ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የከተሞችን ጽዳትና ውበት በመጠበቅ የዜጎችን ጤናማ የኑሮ ምኅዳር እያጎናጸፈ መሆኑን ገልጸዋል። በሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤም ኢትዮጵያ በውሃ ደህንነትና ንጽህናቸው የተጠበቁ ከተሞችን ለመገንባት ያስመዘገበችውን ስኬት በተሞክሮነት ለማጋራት እንደሚሰራ አንስተዋል። በአፍሪካ ሕብረት የዘንድሮው ጉባኤ በውሃ አቅርቦትና ንጽህና አጠባበቅ ላይ ትኩረት ማድረጉ የውሃና ሥነ-ምኅዳር ደህንነትን በማስጠበቅ አጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል።
ኢኮኖሚ
የኢኮኖሚና የንግድ ዕድሎችን በማስፋት የበለፀገች አፍሪካን ለመገንባት በትብብር እንሰራለን
Jan 28, 2026 90
አዲስ አበባ፤ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡-የኢኮኖሚና የንግድ ዕድሎችን በማስፋት የበለፀገች አፍሪካን ለመገንባት በትብብር እንደሚሰሩ የአፍሪካ ሕብረትና አሜሪካ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው ጋር በትብብር መስራት በሚቻልባቸው የሰላምና ልማት ጉዳዮች ላይ በመወያየት የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ፤ አፍሪካ በብዙ ፀጋዎችና ሀብቶች የተሞላች አህጉር ናት ብለዋል። የአፍሪካን ሃብቶች ለዜጎቿ ተጠቃሚነት ለማዋልም በሚከናወኑ ተግባራት አህጉሪቷ የአሜሪካንን የዕውቀት፣ የሙያ፣ የአቅም ግንባታና ቴክኖሎጂ ትብብር ትፈልጋለች ብለዋል፡፡   የህብረቱ አባል ሀገራት የውስጥ አቅማቸውን በማሳደግ፣ በሲቪል እና ንግድ ማህበረሰብ አማካኝነት የልማት መርሃ ግብሮችን በራሳቸው ገንዘብ በመደገፍ ተስፋ ሰጪ አቅም እየገነቡ መሆኑን አንስተዋል። የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲና ትብብር ስርዓት ተጠናክሮ መቀጠል በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም ገልጸዋል፡፡ በአፍሪካ ሀገራትና በአሜሪካ መካከል በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ የጋራ ዕድገትን ማስፋት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው በበኩላቸው፤ የአፍሪካ ህብረት የአህጉሪቷን ሰላምንና የኢኮኖሚ ልማት ለማረጋገጥ ከአባል ሀገራት ጋር በመተባበር ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል ብለዋል። ​የአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ በጋራ ደኅንነት፣ ሰላምና እና ብልጽግና ጉዳዮች በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የበለፀገች አፍሪካ መኖር ለአሜሪካም ጥቅም ነው ያሉት የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ አፍሪካ ያላትን ዕምቅ የኢኮኖሚና የንግድ ዕድሎችን በጋራ ጥቅም ላይ ለማዋል እንሰራለን ብለዋል፡፡ አሜሪካ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ መርህ እንዳላት በማንሳት፤ የኢኮኖሚ ዕድገት ዕድሎችን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል። ከአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄነራል አንደርሰን ጋር ያደረጉት የሥራ ጉብኝትም አሜሪካ የአሕጉሪቷን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ካላት ቁርጠኝነት የሚመነጭ መሆኑን አስረድተዋል። አፍሪካውያን ችግራቸውን በራሳቸው አቅም መፍታት እንደሚችሉ በማንሳት፤በአፍሪካውያን የውስጥ ጉዳይ ማንም ጣልቃ መግባት እንደሌለበት እናምናለን ብለዋል፡፡
አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን ኢንቨስትመንት የማስፋት ፍላጎት አላት-የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው
Jan 28, 2026 116
አዲስ አበባ፤ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፦አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት ተደራሽነት ለማስፋት እና ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት የሀገሪቷ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው ገለጹ። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው ጋር ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች እና የኢትዮጵያና አሜሪካን ትብብር እንዲሁም እያደገ የመጣውን አጠቃላይ አጋርነት ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው።   የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል። የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች ጠንካራ ለውጥ እንደታየባቸው ገልጸው፥ የኢኮኖሚ እድገት አዝማሚያ እና በቁልፍ ዘርፎች ያለው የኢንቨስትመንት ምህዳር የተሻለ መሻሻል እንዳሳየ የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ጠንካራ አጋርነት እንዳላቸው ገልጸው፥ በቅርቡ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ጤና ዘርፍ ያደረገችውን ድጋፍ ጠቅሰዋል። አሜሪካ ለኢትዮጵያ ልማት እያደረገች ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል። በሌላ በኩል ሚኒስትሩ ለአሜሪካው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቅርቡ ግንባታው ስለተጀመረው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ገለጻ አድርገዋል። አየር ማረፊያው ለእድገት፣ ቀጣናዊ ትስስር እና ንግድ መሳለጥ ያለውን ስትራቴጂካዊ ሚና ያነሱ ሲሆን የአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማት እና ተቋራጮች ፕሮጀክቱን እንዲደግፉ ጠይቀዋል።   የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው፥ የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች በማድነቅ አሜሪካ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ያላትን ተሳትፎ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል። አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያ እና አሜሪካን አጋርነት ለማጠናከር፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን ለመደገፍ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በኢነርጂ ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ
Jan 28, 2026 93
አዲስ አበባ፤ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በኢነርጂ መስክ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትስስር ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በ27ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ሶማሊያ ሞቃዲሾ ገብተዋል። የገንዘብ ሚኒስትሩ ከስብስባው አስቀድሞ ከአውሮፓ ኮሚሽን የዓለም አቀፍ አጋርነት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሜሪያም ፌራን ጋር ውይይት አድርገዋል። በስብስባው ላይ ሚኒስትሩ እና ምክትል ዳይሬክተር ጀነራሏ የሁለቱን ወገኖች ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የተወያዩ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ አካል የሆነው የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የትራንስፖርት ኮሪዶር በሚያደርገው የፋይናንስ ድጋፍ አስመልክቶ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአውሮፓ ህብረት ለማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የሚያደርገውን ድጋፍ ማጠናከር እንደሚገባም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል። በተለይም ህብረቱ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅራቢ መስመሮችን በታዳሽ ኃይል እና በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች በማዘመን ዘላቂ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ የኃይል አቅርቦት የማረጋገጥን አላማ ላለው ፕሮግራም (RISED) የሚያደርገውን ድጋፍ ለአብነት አንስተዋል። 27ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብስባ ለኃይል ማሰራጫ መሰረተ ልማቶች እና ለቀጣናዊ የኢነርጂ ትስስር ስራዎች የፋይናንስ አቅርቦትን በማሳደግ አስተማማኝ እና ተመጣጣኝ የኢነርጂ አቅርቦትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክር የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
በቀን እስከ 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውኃ ማቅረብ የሚያስችለው የጭቋላ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ እየተፋጠነ ነው-የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
Jan 28, 2026 69
አዲስ አበባ፤ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡-በቀን እስከ 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውኃ ማቅረብ የሚያስችለው የጭቋላ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑን የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ገለጸ። በሌላ መልኩም የገርቢ ንጹህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር አስታውቋል። የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በቀን እስከ 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውኃ የማቅረብ አቅም ያለው የጭቋላ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ በአሁኑ ወቅት በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል። 22 የውኃ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ የሲቪልና የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራዎችን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትም በተሳለጠ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።   የጭቋላ ፕሮጀክት በተያዘው በጀት ዓመት በከፊል እንደሚጠናቀቅ ጠቁመው፥ በ2019 በጀት ዓመት ደግሞ ሙሉ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስረድተዋል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም የምዕራብ አዲስ አበባ፣ ጀሞ፣ ቤቴል፣ ሳር ቤት እንዲሁም የአቃቂ አካባቢ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። በሌላ በኩል፣ ለመዲናዋ ተጨማሪ ውኃ የማቅረብ አቅምን የሚያሳድገው የገርቢ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታን ለመጀመር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ፕሮጀክቱ በቀን ከ73 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ውኃ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን፤ በርካታ የመዲናዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አብራርተዋል። ፕሮጀክቱ በመዲናዋ ያለውን የውኃ አቅርቦትና ፍላጎት ለማጣጣም በሚደረገው ጥረት ውስጥ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ፕሮጀክቱ ወደ ግንባታ ምዕራፍ እንደሚሸጋገር አስታውቀዋል። የውኃ አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። ከእነዚህ በተጨማሪ ወደ ሥራ ለማስገባት ተጠንተው የተቀመጡ ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ የግንባታ ሥራቸውን ለማስጀመርም የፋይናንስ ማፈላለግ ሥራዎች ጎን ለጎን እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
Jan 28, 2026 103
አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፦ ዜጎች በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ አማራጮች ለሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች እና የማጭበርበር ድርጊቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አሳሰበ። ማህበረሰቡ የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርቧል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ)፤በኢትዮጵያ የዲጂታል ትስስር መስፋፋትን ተከትሎ በዋትሳፕ (WhatsApp)፣ በቴሌግራም (Telegram) እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ ፕላትፎርሞች አማካኝነት በዜጎች ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችና የማጭበርበር ድርጊቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸዉን በተለያዩ መንገዶች ማረጋገጥ መቻሉን ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በሀገሪቷ የሚካሄዱ የተለያዩ ሲምፖዚየሞችን፣ ዓለም አቀፍ መድረኮችን እና የኦንላይን ስብሰባዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ የሳይበር ወንጀለኞች የእነዚህን ኩነቶች ስም ለሀሰተኛ ድርጊቶቻቸው መጠቀሚያ እያደረጉት እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካላት የማህበረሰቡን የግል መረጃ ለመስረቅ፣ የባንክ ሂሳቦችን ለመመዝበር እና የዲጂታል ደህንነትን ለማናጋት በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ መሆኑን አስተዳደሩ በክትትልና በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል። የሳይበር ጥቃቶች የሚፈጸሙት ማህበረሰቡ ትኩረት የሚሰጣቸውን "ተፈላጊ" እና "ወቅታዊ" የሆኑ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ በተዘረጋ ስልታዊ የማታለያ ዘዴ መሆኑን ተጠቁሟል። አጭበርባሪዎቹ "ለሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች የተዘጋጀ ነጻ የኢንተርኔት ፓኬጅ"፣ "ልዩ የስራ ቅጥር" ወይም "ይህ የስብሰባ መሳተፊያ ሊንክ ነው፤ ከፍተው ይግቡ" የሚሉ አሳሳችና ማራኪ መልዕክቶችን በማሰራጨት ተጠቃሚዎች በመልዕክቱ ውስጥ የተካተተውን ሊንክ (Link) እንዲጫኑ እንደሚያደርጉ የገለጸው አስተዳደሩ፥ ይህ ድርጊት ተጠቃሚው ሳያውቀው ወደ አጥፊ ተልዕኮ ወዳላቸዉ ድረ-ገጾች እንዲያመራና ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርግ የመጀመሪያው የወንጀለኞች እርምጃ እንደሆነ አመልክቷል። ጥቃት አድራሾቹ የአንዳንድ ግለሰቦች የግንዛቤ እጥረትና ትኩረት ማጣት የተነሳ የሚላኩላቸውን ሊንኮችና መልዕክቶች በጥንቃቄ የመመርመር ዕድላቸው አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ ወንጀለኞቹ ይህን ሁኔታ እንደ ምቹ አጋጣሚ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ነው ያለው። ይህ አይነቱ ጥቃት ከግለሰቦች መረጃ ስርቆት ባለፈ፣ በእጃቸው የሚገኙ ሚስጥራዊ መረጃዎች በጠላፊዎች እጅ እንዲወድቁ በማድረግ በሀገር ደህንነትና ሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የሚጋርጥ መሆኑን አስተዳደሩ በጥብቅ አሳስቧል። በዚህም ተጠቃሚዎች የተላከላቸውን ሊንክ ሲጫኑ ወይም የተጠየቁትን መረጃ ሲሞሉ፣ የዋትሳፕ ወይም የቴሌግራም አካውንታቸው ወዲያውኑ በጠላፊዎች ቁጥጥር ስር እንዲዉል እንደሚያደርግም ነው በመግለጫው ላይ የሰፈረው። ወንጀለኞቹ አንዴ የአንድን ሰው አካውንት ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ የተጠለፈውን አካውንት በመጠቀም በተጎጂው ስም ለቅርብ ወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ "ድንገተኛ ችግር አጋጥሞኛል" የሚሉ የሀሰት የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄዎችን ይልካሉ። ይህም ድርጊት በማህበረሰቡ መካከል ያለውን መተማመን ከመሸርሸሩ ባለፈ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በማጭበርበር እንዲመዘበር በማድረግ መጠነ-ሰፊ የኢኮኖሚና የስነ-ልቦና ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ነው ተቋሙ ያስታወቀው። ከላይ የተጠቀሱና መሰል የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ፣ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኢመደአ አሳስቧል። ከማይታወቁ ወይም ካልተረጋገጡ አድራሻዎች በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች መድረኮች የሚላኩ ሊንኮችን ካለመክፈት ባለፈ፣ አጠራጣሪ መልዕክቶች ሲደርሱ ወዲያውኑ "Report" እና "Block" በማድረግ የጥቃቱን ስርጭት መግታት እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል። በተጨማሪም ማንኛውንም አይነት ሚስጥራዊ የይለፍ ቃል ወይም በስልክ የሚላክ የማረጋገጫ ኮድ (Verification Code) ለማንም አካል አለመስጠት ለዲጂታል ደህንነት ወሳኝ መሆኑን አመልክቷል። አስተዳደሩ እያንዳንዱ ተጠቃሚ በተለይም ማህበረሰቡ በመተግበሪያዎቹ ላይ የሁለትዮሽ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) በአስቸኳይ እንዲተገብር መክሯል። ይህ የቴክኖሎጂ የመረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን አካውንት በቀላሉ እንዳይቆጣጠሩ የሚያደርግ እና ተጨማሪ የደህንነት ቁልፍ የሚፈጥር አስተማማኝ የመከላከያ ዘዴ እንደሆነ ገልጾ ዜጎች ይህንን ቀላል ግን ውጤታማ የሆነ የደህንነት ጥንቃቄ ተግባራዊ በማድረግ፣ ራሳቸውን በቴክኖሎጂ ከታገዙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሊታደጉና የሳይበር ወንጀለኞችን ሴራ ሊያከሽፉ እንደሚገባ አስተዳደሩ ያሳሰበው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እነዚህን የሳይበር ወንጀለኞች በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው የጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል። ማህበረሰቡ ማንኛውም የሳይበር ጥቃት ሙከራ ሲያጋጥመው ወይም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት በነጻ ስልክ መስመር 933 በመደወል ለኢመደአ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል። የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በንቃትና በጥንቃቄ በመምራት የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በጋራ መጠበቅ እንደሚገባም መግለጫው አትቷል።
በአዲስ አበባ ተጨማሪ ዘጠኝ የ"አዲስ መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎችን ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው 
Jan 27, 2026 157
አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ተጨማሪ ዘጠኝ የ"አዲስ መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎችን ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዮናስ ዓለማየሁ ገለጹ፡፡ ለዜጎች የሚሰጠው አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በፌዴራል ደረጃ፣ በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በሁሉም ክልሎች ተደራጅቶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡   የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዮናስ ዓለማየሁ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ማዕከሉ አገልግሎት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ከ55ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት መስጠት ተችሏል። በማዕከሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት የሚሰጠው አገልግሎት በተገልጋዮች ዘንድ እርካታን እንደፈጠረ ማመልከቱን ጠቁመው፤ ማዕከሉ ሥራ ሲጀምር 107 የነበሩት የአገልግሎት ዓይነቶች አሁን ላይ ወደ 132 ማደጋቸውን አስታውቀዋል። በቅርቡ ተጨማሪ አራት ተቋማት ወደ ማዕከሉ እንደሚገቡ ገልጸው፤ ይህም የአገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት ረገድ ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።   የአገልግሎት ሰጪ ባለሙያዎችም ሥነ-ምግባርን ከቴክኖሎጂ ክህሎት ጋር አጣምረው እንዲሰሩ መደረጉ ለተመዘገበው ውጤት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ በዋና መሥሪያ ቤትና በአንድ ቅርንጫፍ ብቻ እየተሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ይህንን ተደራሽነት ለማስፋት ዘጠኝ ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ለመክፈት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በተለይም በጉለሌ፣ አዲስ ከተማ፣ ቂርቆስና ልደታ ክፍለ ከተሞች አማካይ ቦታዎች ላይ የሚገኙ አራት ቅርንጫፎች የሕንጻ እድሳታቸው እየተጠናቀቀ በመሆኑ በቅድሚያ ወደ ሥራ ይገባሉ ብለዋል፡፡   በቀሪዎቹ አምስት ክፍለ ከተሞችም በተመሳሳይ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱን መጀመር የሚያስችሉ የግንባታ ሥራዎች እየተፋጠኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። ከአገልግሎት መስፋፋቱ ጎን ለጎን ማዕከላቱን ለተገልጋዮች ይበልጥ ምቹ የማድረግ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን አቶ ዮናስ ገልጸዋል። ለዚህም ማሳያ እንዲሆን ሕጻናትን ይዘው ለሚመጡ ተገልጋዮች የሕጻናት ማቆያ ከመገንባት ባለፈ፣ ተገልጋዮች የጤና እርዳታ የሚያገኙበት ሥርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም መንጃ ፈቃድ የሚያሳድሱ ተገልጋዮች ለማሽከርከር ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የጤና ምርመራ አገልግሎትን በዚያው በማዕከሉ እንዲያገኙ ለማስቻል ከከተማዋ ጤና ቢሮ ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የፋይናንስ ወንጀሎችን ለመከላከል የሰው ሠራሽ አስተውሎትን መሰረት ያደረገ ሥርዓት ሊለማ ነው
Jan 27, 2026 116
አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018 (ኢዜአ)፡- በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ የመጠቀምና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን መከላከል የሚያስችል በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ ሥርዓት ለማልማት ስምምነት ተፈረመ። ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እና የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ ናቸው።   የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ ስምምነቱ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ የመጠቀምና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያደረገውን ጥረት ያግዛል ብለዋል፡፡ ሥርዓቱ ሰው ሠራሽ አስተውሎትን መሰረት በማድረግ ረቂቅ ወንጀሎች ከመፈጸማቸው በፊት ማስቀረትና ችግሩ ሲፈጠር የከፋ ጉዳት ሳይደርስ በፍጥነት መፍታት የሚያስችል መሆኑንም አስገንዝበዋል። ይህን ሥርዓት ለማልማት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አውስተው፤ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የላቀ ሥራና በተያዘለት ጊዜ ሠርቶ ለማስረከብ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡   የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ኅብረት እና የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጊት ግብረ-ኃይል አባል እንደመሆኗ የፋይናንስ ወንጀል መረጃዎችን ከሌሎች ሀገራት ጋር እንደምትለዋወጥ ገልጸዋል፡፡ በዚህም በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ የመጠቀምና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎች ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው የቴክኖሎጂ ድጋፍ ያስፈልጋል ነው ያሉት። የሥርዓቱ መልማት ውስብስብ የሆነውን ወንጀል ከሀገራት ጋር በትብብር ብሎም ከሕግ አስከባሪዎች ጋር በጋራ በመሥራት ከወንጀል ማትረፍ እንደማይቻል ለማሳየት እንደሚያግዝ አመላክተዋል። ኢትዮጵያ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ የመጠቀምና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከልና ደኅንነቷን ለማረጋገጥ ሥርዓት ማልማቷ ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ ይሆናል ብለዋል፡፡
የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶቹ የኢትዮጵያን የሩቅ ዘመን የልዕልና ህልም በተጨባጭ በቅርቡ እንደምናሳካው ማረጋገጫዎች ናቸው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jan 27, 2026 143
አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018(ኢዜአ)፦ በአየር ኃይል ኤክስፖው የታዩ የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች የኢትዮጵያን የሩቅ ዘመን የልዕልና ህልም በተጨባጭ በቅርቡ እንደምናሳካው ማረጋገጫዎች ናቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዓለም አቀፍ የአየር ኃይል ኤክስፖን ዛሬ ጎብኝተዋል።   ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ አየር ኃይል የ90 ዓመታት ጉዞ በድልና በጀግንነት ብቻ የተገደበ አይደለም፤ በፈጠራና የቴክኖሎጂ ልዕልና ውጤትም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል። በአየር ኃይል ዋና መሥሪያ ቤት በተከፈተው ዓለም አቀፍ የአየር ኃይል ኤክስፖ ዛሬ የተመለከትነው እውነትም ይሄንኑ የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።   በኤክስፖው የተመለከትናቸው የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች የኢትዮጵያን የሩቅ ዘመን የልዕልና ህልም በተጨባጭ በቅርቡ እንደምናሳካው ማረጋገጫዎች ናቸው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት።
ስፖርት
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ወደ ጥሎ ማለፍ በቀጥታ የሚያልፉ ክለቦች የሚለዩባቸው ተጠባቂ ጨዋታዎች
Jan 28, 2026 148
አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ወደ ጥሎ ማለፍ በቀጥታ የሚያልፉ ክለቦች የሚለዩባቸው ተጠባቂ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።   ‎የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጨረሻ ዙር መርሐ-ግብር ዛሬ ይካሄዳል። በዕለቱ 18 ጨዋታዎች በተመሳሳይ ምሽት አምስት ላይ ይደረጋሉ። በስታዲዮ ደ ሉዝ ቤኔፊካ ከሪያል ማድሪድ ይጫወታሉ። ቤኔፊካ በስድስት ነጥብ 29ኛ፣ 15 ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ በ15 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ሪያል ማድሪድ ማሸነፍ በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ያስገባዋል። አቻ ማውጣትም ሊያሳልፈው የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። ሊቨርፑል ከካራባግ በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ይጫወታል። ከሰባት ጨዋታዎች 15 ነጥብ ያገኘው ሊቨርፑል በ15 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። ካራባግ በ10 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዟል። እንደ ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑል ካሸነፈ በቀጥታ 16 ውስጥ ይገባል። አቻ ከወጣ በሂሳባዊ ስሌት የማለፍ እድል ይኖረዋል። ኢንትራክት ፍራንክፈርት ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በ14 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ማሸነፍ ወደ ጥሎ ማለፍ ያስገባዋል። አቻ መውጣት የሌሎች ቡድኖችን ውጤት እንዲጠብቅ ያደርገዋል። የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ ከኒውካስትል ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ፒኤስጂ እና ኒውካስትል ዩናይትድ በተመሳሳይ 13 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ስድስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን ይዘዋል። የሁለቱም ቡድኖች ወደ ጥሎ ማለፉ የመቀላቀል ሂሳባዊ ስሌት ተመሳሳይ ነው። ያሸነፈ ቡድን 16 ውስጥ ይገባል። ናፖሊ ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታም ትኩረት ስቧል። የጣልያኑ ክለብ ናፖሊ በስምንት ነጥብ 25ኛ ደረጃን ይዟል። ቼልሲ በ13 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ናፖሊ በቀጥታ የጥሎ ማለፍ የመግባት እድል የለውም። ማሸነፍ በሁለት የማጣሪያ ዙሮች ተጫውተው የሚያልፉ ክለቦችን እንዲቀላቀል ያደርገዋል። ቼልሲ በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ማንንም ሳይጠብቅ ወደ ጥሎ ማለፍ እንዲገባ ያደርገዋል። ባርሴሎና፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን፣ ማንችስተር ሲቲ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና አትላንታ በተመሳሳይ 13 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከ9ኛ እስከ 13ኛ ደረጃን ይዘዋል። አምስቱ ክለቦች ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ከማሸነፍ ባለፈ በነጥብ የሚበልጧቸውን ክለቦች ውጤት ይጠብቃሉ። 14ኛ እና ከዛ በታች ያሉ ክለቦች በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት እድላቸው እጅጉን የጠበበ ነው። አርሰናል እና ባየር ሙኒክ አስቀድመው ወደ ጥሎ ማለፉ መግባታቸውን ያረጋገጡ ክለቦች ናቸው። አርሰናል ከካይራት አልማቲ እና ባየር ሙኒክ ከፒኤስቪ አይንድሆቨን ጋር ማምሻውን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በዘንድሮው ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ፎርማትን በማስቀረት 36 ክለቦች በአራት ቋቶች (Pots) በመከፋፈል እንዲጫወቱ የሚያደርግ አዲስ አሰራር ከባለፈው የውድድር ዓመት አንስቶ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። ከ36 ክለቦች መካከል በስምንት ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ስምንት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ይገባሉ። ቀሪዎቹ ስምንት ወደ ጥሎ ማለፉ የሚገቡ ቡድኖች በሁለት የማጣሪያ ዙሮች ተጫውተው ወደ 16ቱ ያልፋሉ። በሻምፒዮንስ ሊጉ ከ9ኛ እስከ 24ኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ክለቦች በማጣሪያ ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ይጫወታሉ። ከ25ኛ እስከ 36ኛ የሚያጠናቅቁ ቡድኖች ከውድድሩ ይሰናበታሉ። ኢንትራክት ፍራንክፈርት፣ ስላቪያ ፕራግ፣ ቪያሪያል እና ካይራት አልማቲ ከውድድሩ የተሰናበቱ ክለቦች ናቸው። ከጥሎ ማለፉ አንስቶ ያለው የውድድር ፎርማት ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ድል ተመልሷል 
Jan 27, 2026 87
አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ተስፋዬ ታምራት በ78ኛው ደቂቃ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል። ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ20 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ አራተኛ ድሉን አሳክቷል።   በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ለስምንተኛ ጊዜ የተሸነፈው ኢትዮጵያ ቡና በ19 ነጥብ ከነበረበት 13ኛ ደረጃ ወደ 14ኛ ዝቅ ብሏል። ቡናማዎቹ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፉም። ዛሬ በተደረጉ ሌሎች መርሐ-ግብሮች ነገሌ አርሲ የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ሸገር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ 17ኛ ሳምንት ተጠናቋል። የ18ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እንደሚካሄድ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።
በክልሉ ሲካሄድ በቆየው ስፖርታዊ ውድድር አቅም ያላቸው ታዳጊ ስፖርተኞች ተለይተዋል
Jan 27, 2026 85
ቦንጋ፤ ጥር 19/2018(ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሲካሄድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድር አቅም ያላቸው ታዳጊ ስፖርተኞች የተለዩበት መሆኑን የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ገለጸ። ለተከታታይ ስድስት ቀናት በቦንጋ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 5ኛው ክልል አቀፍ የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫልና ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቋል።   በመድረኩ ማጠቃለያ ለይ የተገኙት የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ፣ ስፖርታዊ ውድድሩ ለክልልና ለሀገር የሚበቁ ታዳጊ ስፖርተኞች የተለዩበት እንደሆነ ገልፀዋል።   ስፖርት ከውድድርነት አልፎ የቱሪዝም ዘርፉን የሚያነቃቃ ትልቅ መሳሪያ መሆኑን ያነሱት አቶ ፋንታሁን፣ የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል በህዝቦች መካከል አንድነትን፣ አብሮነትንና የእርስ በእርስ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ናቸው ብለዋል። በተለያዩ ስፖርት ዘርፎች ክልሉን ወክለው በሀገር ደረጃ ለሚሳተፉ ስፖርተኞች መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል። የካፋ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ታሪኳ ታከለ በበኩላቸው፣ ስፖርታዊ ውድድሩ የዞኑን እና የከተማውን ያነቃቃ ነበር ብለዋል።   ብዙ የባህል ልውውጥ የተካሄደበት፣ አቅምና ብቃት ያላቸው ስፖርተኞችን የተመለከትንበት እና በቀጣይም በዘርፉ መሰራት ያለባቸው ስራዎች የተለዩበት ነበር ሲሉም ገልጸዋል፡፡ በታዳጊ ወጣቶች ምዘና በእግር ኳስ ስፖርት ዋንጫ ያነሳው የሸካ ዞን የታዳጊ ወጣቶች እግር ኳስ ዋና አሰልጣኝ ገብርኤል ዜና፣ ታዳጊ ላይ የተጀመረው ስራ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን እንዲኖር የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰዋል።   ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ቀጣይነት ያለው ውድድር ባለመኖሩ በርካታ አቅም ያላቸው ታዳጊዎች ወደ ኋላ ይቀሩ እንደነበር ጠቅሰው፣ አሁን ላይ የተጀመረው ስራ መንግስት ለስፖርቱ ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት ያሳያል ብለዋል። የሚዛን ስፖርት አካዳሚ ስራ አስኪያጅ አቶ ተክሌ ነገሪ በበኩላቸው፤ በ2016 ዓ.ም ከክልሉ ሁሉም ዞኖች አትሌቶችን በመመልመል ወደስራ በመግባት አሁን 38 ታዳጊዎችን በ8 የስፖርት አይነቶች እያሰለጠኑ መሆኑን ተናግረዋል።   ‎‎አካዳሚው ለዚሁ ውድድር ከ35 በላይ ታዳጊዎችን ማሳተፉን ጠቁመው በውድድሩም የወርቅ፣ የብርና የነሃስ ሜዳሊያ ማግኘት መቻላቸውን ገልፀዋል። ‎በመዝጊያው መርሃ ግብር ላይ በባህል ስፖርቶች ውድድር፣ በባህል ፌስቲቫል፣ በታዳጊዎች ምዘና እና በሌሎችም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞችና የባህል ቡድኖች የሜዳሊያ፣ የዋንጫና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በነገሌ አርሲ ተሸነፈ 
Jan 27, 2026 111
አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ-ግብር ነገሌ አርሲ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል። በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳዊት ተፈራ በ94ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ በ29 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ ስምንተኛ ድሉን አስመዝግቧል።   በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና 33 ነጥብ ላይ ረግቷል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ሸገር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በ17 ነጥብ ከነበረበት 17ኛ ደረጃ ወደ 16ኛ ከፍ በማለት ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል። ሸገር ከተማ የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ስምንት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። ድሬዳዋ ከተማ በ20 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም። ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
አካባቢ ጥበቃ
በተፋሰስ ልማት ስራ የአፈር ለምነት በመጨመሩ የአርሶአደሮች ምርታማነት አድጓል
Jan 28, 2026 121
ወላይታ ሶዶ ፤ ጥር 20/2018 (ኢዜአ)፡- በተፋሰስ ልማት ስራ የአፈር ለምነት በመጨመሩ ምርታማነታቸው ማደጉን በወላይታ ዞን የኦፋ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ። "እመርታ በተቀናጀ ተፋሰስ ለብልፅግናችን!" በሚል መሪ ሃሳብ የ2018 ዓ.ም ዞናዊ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዞኑ ኦፋ ወረዳ ቡሻ ቀበሌ ጋዬ ንዑስ ተፋሰስ ላይ ተካሄዷል። በወቅቱም ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ አርሶ አደሮች እንዳሉት፤ በተፋሰስ ልማት ስራው የአፈር ለምነት በመጨመሩ ምርታማነታቸው አድጓል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል አርሶ አደር በቀለ ቶጋ፤ ለበርካታ ዓመታት በተፋሰስ ልማት ስራ ላይ ሲሳተፉ መቆየታቸውን ገልፀው በአካባቢው የልማት ስራው ከመከናወኑ በፊት በነበረው የአፈር በጎርፍ መሸርሸር ሳቢያ መሬቱ ተራቁቶ እንደነበር ገልጸዋል።   ሆኖም ባለፉት ዓመታት የተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የአፈር ለምነት እንዲጨምርና ምንጮች እንዲፈልቁ በማድረጉ በስራው በዘላቂነት እንድንሳተፍ መነሳሳትን ፈጥሮልናል ብለዋል። የአየር መዛባትና የአካባቢ መራቆት ከሁሉም በላይ አካል ጉዳተኞች ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽዕኖ የከፋ በመሆኑ አካል ጉዳተኝነት ሳይበግረኝ የሚጠበቅብኝን እየተወጣሁ እገኛለሁ ያሉት ደግሞ አርሶ አደር መሰለ መንገሻ ናቸው። የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራው ከዚህ ቀደም የተራቆቱ አካባቢዎች አገግመው ምርት እንዲሰጡ ከማድረጉም ባሻገር ለኑሮ ምቹ አካባቢን ፈጥሮልናል ብለዋል። የአፈር ለምነት በጨመረባቸው እና ምንጭ በፈለቀባቸው አካባቢዎች የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን በማምረት ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውን ተናግረዋል። የኦፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዲሱ ወርቁ በበኩላቸው፤የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ለዘላቂ የግብርና ልማት ወሳኝ በመሆኑ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።   ‎‎በወረዳው በዘንድሮ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ከ31 ሺህ በላይ ህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ በ20 ንዑስ ተፋሰሶች ከ2 ሺህ 400 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት መታቀዱን ገልጸዋል። በዞኑ ባህል ሆኖ የቀጠለው የተፋሰስ ልማት ስራ በስነ-አፈር እና በስነ-አካላዊ ስራዎች የተራቆቱ አካባቢዎች በማገገማቸው ምርታማነታቸው እያደገ መምጣቱን የተናገሩት ደግሞ የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ ዘማች ሶርሳ (ዶ/ር) ናቸው። ይህንን ውጤት ለማስቀጠል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው በዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ስራ በዞን ደረጃ በ315 ተፋሰሶች ከ46 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ለመሸፈን ታቅዶ ስራ መጀመሩን ነው የገለጹት።   በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የወላይታ ዞን ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አማረ አቦታ (ዶ/ር)፤ በዞኑ የተፋሰስ ልማት ስራ ከተጀመረ ወዲህ የተራቆተ መሬት በማገገሙ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል። የግብርና ምርታማነትን ለማሻሻል የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተገቢው ማስረጽ እንደሚገባ ገልጸው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ስራ በመሳተፍ ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል።
በመጪው ክረምት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ ችግኞች ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል
Jan 27, 2026 84
ጊምቢ፤ ጥር 19/2018(ኢዜአ)፦ በምዕራብ ወለጋ ዞን በመጪው ክረምት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ዝግጅት ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ። በኦሮሚያ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካል የሆነው የችግኝ ዝግጅት ስራ በተለያዩ ዞኖች በሰፊው እየተካሄደ ይገኛል።   በምዕራብ ወለጋ ዞንም ከበጋ ወራት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ጎን ለጎን የችግኝ ዝግጅት በሰፊው እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል። በዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ቡድን መሪ አቶ ፍቅሩ ብርሃኑ እንደገለጹት፤ በመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ዝግጅት በስፋት እየተከናወነ ነው።   እየተዘጋጁ ከሚገኙ ችግኞች መካከል አብዛኛዎቹ ለምግብነት የሚውሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞች ሲሆኑ ለደን እና ለውበት አገልግሎት የሚውሉ ችግኞችም እየተዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም የአቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ማንጎ፣ ሙዝና የአናናስ ችግኞች በስፋት እየተዘጋጁ መሆኑን አንስተው ችግኞቹ የሚተከሉት በ66 ሺህ 827 ሄክታር መሬት ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።   የችግኝ ዝግጅቱ እየተደረገ ያለው ከ2 ሺህ 900 በላይ በሆኑ የመንግስትና የግል ችግኝ ማፊያ ጣቢያዎች መሆኑን ጠቅሰው በችግኝ ዝግጅት ስራው ከ3 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል። በአጠቃላይ በዞኑ ከ3 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ለተከላ እየተዘጋጁ መሆኑን አስረድተዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ህብረተሰቡን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ አስችሏል 
Jan 27, 2026 234
አሶሳ፤ ጥር 19/2018 (ኢዜአ)፡- የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ ህብረተሰቡን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ ማስቻሉን የኢትዮጵያ የደን ልማት አስታወቀ። በኢትዮጵያ እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በርካታ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው እንዲሁም የደን ሽፋንን የሚያሳድጉ ችግኞች እንዲተከሉ አድርጓል። በተለይም የመሬት መራቆት እና የአየር ንብረት ለውጥ በስነ ምህዳር ላይ አሉታዊ ተዕፅኖ እንዳያመጣ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደው እርምጃ ለሌሎች ሀገራትም ምሳሌ መሆን ችሏል። የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ ከለውጡ በፊት በየዓመቱ እስከ 92 ሺህ ሄክታር ደን እንደሚወድም አስታውሰዋል።   መንግስት በጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋንን በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2030 ላይ 30 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የደን ሽፋን በአሁኑ ሰዓት 23 በመቶ ላይ ያለ መሆኑን ጠቅሰው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ችግኞችን ከመትከል ባለፈ ህብረተሰቡ የደን ምርት አስፈላጊነትን እንዲገነዘብ አድርጓል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ለቀጠናው ሀገራት የውሃ ሀብት እንዲጨምር እና የአየር ንብረት ለውጥ እንዲስተካከል በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። የአሁኑ የበጋ ወቅት ደግሞ በአንዳንድ የሀገሪቱ የተፈጥሮ ደኖች አካባቢ የሰደድ እሳት እንዳይነሳ ቀድመው መከላከል እንዲችሉ በሳተላይት የታገዘ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠ እንደሆነ ገልጸዋል።   ህብረተሰቡ ለደን ልማት የሰጠው ትኩረት እና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው በተሰራው ስራ በየዓመቱ የሚወድመው ደን እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ጨምሮ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በስፋት የሚገኘው የቀርከሃ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል እና የቀርከሃ ችግኞችን በመትከል ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተደረገ ነው ብለዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር በላይ የቀርከሃ ደን እንደሚገኝ ጠቁመው፣ የቀርከሃ ደን ሽፋንን ለማሳደግ በየዓመቱ ከ50 ሚሊዮን በላይ ችግኝ እየተተከለ መሆኑን አብራርተዋል።
በወረዳው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራው በግብርናው ዘርፍ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እያሳደገ ነው
Jan 26, 2026 116
አምቦ፤ ጥር 18/2018 (ኢዜአ)፡- በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ ባለፉት ዓመታት በተከታታይ ሲከናወን የቆየው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ በግብርና ዘርፍ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እያሳደገ መምጣቱ ተገለጸ፡፡ ኢዜአ ያነጋገራቸው በዞኑ የቶኬ ኩታዬ ወረዳ አርሶ አደሮች ባለፉት ዓመታት ባከናወኑት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በርካታ ጥቅም እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል።   የተቀናጀ የአፈርና የውሀ ጥበቃ ስራው ቀደም ሲል በጎርፍ የሚጠረገውን ለም አፈር በማስቀረት ምርታማነት እንዲጨምር ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ በወረዳው የዋጅራ ቀበሌ ነዋሪው ባይሳ ሚደቅሳ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የሰሩት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የግብርና ልማት ስራዎቹን ውጤታማ አድርጓል። ባለፉት ዓመታት ባከናወኑት ስራ በጎርፍ ተጠርጎ ተራቁቶ የነበረው መሬት ማገገም በመቻሉ ከአንድ ሄክታር መሬት አራት ኩንታል ምርት ማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል።   ሌላው በቶኬ ኩታዬ ወረዳ የማሩፍ ቀበሌ አርሶ አደር አቦምሳ ፊጣ፤ በአካባቢያቸው በተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ደርቀው የነበሩ ምንጮች ጭምር መመለስ መጀመራቸውን ገልጸዋል። በዚህም የተፋሰስ ልማት የተከናወነበት መሬት በማገገሙ የዝናብ ወቅትን ብቻ ጠብቀው ከማምረት ወጥተው በአመት ሁለቴ በማምረት ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። ተፋሰስ ልማት በተሰራባቸው አካባቢዎች ከሰብል ምርት ከሚያገኙት ገቢ በተጨማሪ ለእንስሳት መኖ ልማትም እየጠቀማቸው መሆኑን ጠቁመዋል። የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ከግብርና ባለሙያዎች ስልጠና መውሰዳቸውን የጠቀሱት ደግሞ በወረዳው የዋጅራ ቀበሌ አርሶ አደር ጋዲሳ ደንደና ናቸው፡፡ የቶኬ ኩታዬ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት የተፈጥሮ ሃብት ቡድን መሪ ወይዘሮ ባዳዲ ዱጋሳ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በወረዳው በተሰሩ የተፋሰስ ልማት ስራዎች የገጸ ምድርና የከርስ ምድር ውሃ በመጎልበቱ የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ጨምሯል፡፡ ስራውን በዘንድሮው ዓመትም በማስቀጠል ከ23 ሺህ በላይ ሰዎችን ክፍሎችን በማሳተፍ 2 ሺህ 234 ሄክታር መሬት የማልማት ስራዎች መጀመራቸውን ተናግረዋል ፡፡   የምዕራብ ሸዋ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብዲሳ ሀይሉ በበኩላቸው፤ በዘንድሮ የበጋ ወራት ከ 273 ሺህ ሄክታር መሬት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች በሁሉም ወረዳዎች መጀመሩን ገልጸዋል ። ባለፈው ዓመታት በዞኑ በተሰሩ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችም የአፈር ለምነትን መጠበቅና የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል የአርሶአደሩን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አልፎ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው ማረጋገጥ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ የማግኘት የጋራ ፍላጎት ታሪካዊ ፍትህን የሚያሰፍን ነው - መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Jan 27, 2026 108
አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2018(ኢዜአ):- የአፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ አባል የመሆን የጋራ መሻት ታሪካዊ ፍትህን ማስፈንና እኩልነትን ማረጋገጥ እንደሚያስችል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። አፍሪካ ለዘመናት ቋሚ ውክልና አለማግኘቷ የምክር ቤቱን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው ሲሉም ተናግረዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ከፍተኛ ደረጃ የህዝብ የክርክር መድረክ ትላንት ማምሻውን አድርጓል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት በበይነ መረብ ባደረጉት ንግግር አፍሪካ የዓለም ፈተናዎች በተናጠል እንደማይፈቱ በጽኑ ታምናለች ብለዋል። ሊቀ መንበሩ ዓለም አቀፍ ህግ ከታሪክ ግንዛቤ ጋር በተሰናሰለ መልኩ መተግበር አለበት ያሉ ሲሆን በተለይም የቅኝ ግዛት እና የመዋቅራዊ ኢ-ፍትሃዊነት አሻራዎች የተለየ ትኩረት እንደሚያሻቸው አመልክተዋል። ዩሱፍ አፍሪካ ለሰላም ያላት ቁርጠኝነት ተጨባጭ መሆኑን ገልጸው በሰላም አስከባሪ አስተዋጽኦዎች፣ የጸጥታ አካላት የህይወት መስዋዕትነቶችን በመክፈል፣ ከኃይል ይልቅ ለሕጋዊ ስርዓት መስፈን በቁርጠኝነት በመስራትና የአፍሪካ ህብረት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በሰላም ጉዳይ ያለውን ጠንካራ አጋርነት በማሳያነት ገልጸዋል። አፍሪካ ለዓለም ሰላም እና ደህንነት መረጋጋጥ ብዙ ብታበረክትም አሁን በዓለም መድረክ ላይ ባላት ውክልና ላይ የኢ-ፍትሃዊነት ጉዳይ መሰረታዊ ችግር ሆኖ መቀጠሉንም ነው የተናገሩት። 55 ሀገራት እና 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ህዝብ የያዘችው አፍሪካ 80 ዓመታትን ባስቆጠረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ አለማግኘቷ ኢ-ፍትሃዊ ብቻ ሳይሆን የምክር ቤቱን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው ብለዋል። የአፍሪካ የጋራ ፍላጎት በምክር ቤቱ ቋሚ ውክልና ከነሙሉ መብቶቿ ማግኘት ነው ያሉት ሊቀ መንበሩ ይህም እኩልነት፣ በዓለም ስርዓት ውስጥ ውጤታማነትና ታሪካዊ ፍትህ እንዲሰፍን ያደርጋል ሲሉ መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢጋድ የ40 ዓመታት ጉዞ፤ ከድርቅ አደጋ ምላሽ ሰጪነት እስከ ቀጣናዊ ትስስር ተዋናይነት
Jan 21, 2026 262
በሙሴ መለሰ ምስራቅ አፍሪካ በአፍሪካ አህጉር በየጊዜው ከፍተኛ ለውጥ የሚያስተናግድ እና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ቀጣና ነው። ከ300 ሚሊየን በላይ ህዝብ የሚኖርበት ይህ ቀጣና ከፍተኛ የሰው ሀብት ያለው ሲሆን ፈጣን የወጣት ህዝብ እድገት እና የገበያ ተደራሽነት መስፋት እየታየበት ይገኛል። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የምስራቅ አፍሪካ አጠቃላይ ዓመታዊ ጥቅል ምርት(ጂዲፒ) እ.አ.አ በ2025 598 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ገልጿል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ያሉ ሀገራት የሚገኙበት ቀጣና ነው ምስራቅ አፍሪካ። ምስራቅ አፍሪካ ግብርና፣ ቁም እንስሳት፣ ኢነርጂ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ንግድ፣ ትራንስፖርት፣ የኢኮኖሚ ኮሪደሮች እና በፍጥነት እያደገ የመጣው ዲጂታል ኢኮኖሚ እምቅ የኢኮኖሚ አቅሞቿ ናቸው። ከመልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ አንጻርም የኢትዮጵያ ከፍታማ ስፍራዎች፣ የታላላቅ ሀይቆች ተፋሰስ እና የአፍሪካ ቀንድ ዝቅተኛ ቦታዎች ይጠቀሳሉ። ከቀይ ባህር እስከ ህንድ ውቅያኖስ ምስራቅ አፍሪካን የአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና የዓለም የማሪታይም ንግድ መተላለፊያ መስመሮች ይገናኙባታል።   ይህ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ምስራቅ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ንግድ፣ ሎጂስቲክስ እና ጂኦ ፖለቲካ ውስጥ ያላትን ሚና አሳድጓል። ቀጣናው ለመረጋገት እና ለትብብር ያለው ጠቀሜታም በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ለብዙ ክፍለ ዘመናት በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰቦች በንግድ፣ በፍልሰት እና የባህል ትስስር ተጋምደዋል። በዘመናዊው ዓለም ይህ ታሪካዊ ትስስር ለቀጣናዊ ትስስር ጠንካራ አስተዋጽኦ ያለው ነው። በሀገራት በጋራ የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች፣ የተሳናሰኑ ፖሊሲዎች እና የሰዎችና እቃዎች ነጻ ዝውውር የኢኮኖሚ እድገት እና አጠቃላይ ልማትን የሚያሳልጥ ነው። ቀጣናዊ ትስስር የተበታተነ ገበያ ወደ አንድ ማዕቀፍ ለማምጣት፣ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎች በተለይም ወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ አስተዋጽኦወ ቁልፍ ነው። ምስራቅ አፍሪካ እንደ እድሎቹ ሁሉ በርካታ ፈተናዎች ያሉበት ቀጣና ነው። በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚፈጠረው ድርቅ እና ጎርፍ፣ ግጭት፣ መፈናቀል እና የልማት ተደራሽነት ፍትሃዊ አለመሆን በዋናነት የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው። እነዚህ ድንበር ተሻጋሪ ፈተናዎች ከተናጠል ይልቅ የጋራ የተግባር ምላሽ ይፈልጋሉ። ፈተናዎችን ከግምት በማስገባት በቀጣናው በተደጋጋሚ ለሚከሰተው ድርቅ እና የከባቢ አየር ችግር የተቀናጀ ምላሽ መስጠት የሚያስችለው ተቋማዊ ማዕቀፍ ከ40 ዓመታት በፊት ወደ ስራ ገባ። ይህ ተቋም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ነው። የኢጋድ መቋቋም እርሾ በወቅቱ በቀጣናው ያጋጥሙ የነበሩ ቀውሶች ናቸው። እ.አ.አ በ1980ዎቹ መጀመሪያ በቀጣናው የነበረው ድርቅ እና ረሃብ የብዙ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ይህም ቀጣናው ለአየር ንብረት ለውጥ ያለውን ተጋላጭነት በግልጽ የሚያሳይ ነው። አደጋዎቹ ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው የተቀናጀ የጋራ ምላሽ የሚፈልጉ ናቸው።   ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ዩጋንዳ ለአንገብጋቢው ቀጣናዊ ጉዳይ ምላሽ በመስጠት ኢጋድን እ.አ.አ በ1986 አቋቋሙ። ኢጋድ በወቅቱ ሲቋቋም ዋነኛ የስራ ድርሻው የነበረው ድርቅ፣ በረሃማነት እና ሁለቱ የሚያደርሷቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖዎችን ለመከላከል የሚደረጉ ቀጣናዊ ጥረቶችን ማስተባበር ነው። ይሁንና የከባቢ አየር ፈተናዎቹ ከፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ግጭት እና ካለመልማት ጋር ጥልቅ ቁርኝት ያላቸው መሆኑ አድማሱ የሰፋ ግብ ያለው ቀጣናዊ ተቋምን መፍጠር እንደሚያስፈልግ በወቅቱ ይነሳ ነበር። በዚሁ መሰረት ኢጋድ እ.አ.አ በ1996 በድጋሚ አደረጃጀቱ ተስተካክሎና የስራ ድርሻው ሰፍቶ እንደገና ተቋቋመ። ከድርቅ እና ከባቢ አየር ጉዳዮች በመሻገር ኢጋድ ሰላም እና ደህንነትን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትብብር እና ትስስር እንዲሁም ቀጣናዊ ትስስርን ማጎልበት የተቋሙ ቁልፍ የትኩረት መስኮች ሆነዋል። የኢጋድ ዋና መቀመጫ ጅቡቲ ነው። የሰፋው የስራ ድርሻ ኢጋድን በአፍሪካ ቀንድ የምክክር፣ የውይይት እና የተቀናጀ ልማት የጋራ ማዕቀፍ እንዲሆን አድርጎታል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) እ.አ.አ በ2026 የተመሰረተበትን 40ኛ ዓመት እንደሚያከብር ከሰሞኑ አስታውቋል። ኢጋድ በአራት አስርት ዓመታት ውስጥ በስኬት ደረጃ ሊነሱ የሚችሉ ተግባራትን አከናውኗል። ከሰላም እና ደህንነት አንጻር ኢጋድ በቀጣናው ውስብስብ የሚባሉ ግጭቶች በእርቅ እና በውይይት እንዲፈቱ አስተዋጽኦ አድርጓል። ለዓመታት በሱዳን ሲካሄድ የነበረውን የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲያበቃ እ.አ.አ በ2005 ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነት እንዲፈረም በሰላም ሂደት ውስጥ የድርሻውን ተወጥቷል። ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ደቡብ ሱዳን በህዝበ ውሳኔ ራሷን የቻለች ሀገር ሆናለች። ኢጋድ በሶማሊያ የሰላም ጥረቶች ቁልፍ ተዋናይ ነበር። በሶማሊያ የፖለቲካ እርቅ እና መረጋጋት እንዲፈጠር ሲከናወኑ በነበሩ ስራዎች ላይ ተሳትፎ አድርጓል። ቀጣናዊ ተቋሙ ባለው የእርቅ የስራ ክፍል ግጭቶች እንዳይከሰቱና ከተከሰቱም እንዲፈቱ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣም ይገኛል። ከተቋቋመበት የስራ ድርሻ አኳያ ኢጋድ በምግብ ደህንነት፣ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና አደጋ ስጋት አስተዳደር ላይ ሰፋፊ ተግባራትን አከናውኗል። ለአብነትም የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያና ትግበራ ማዕከል (ICPAC) የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን በማጠናከር፣ በአየር ትንበያዎች እና የፖሊሲ ድጋፎች አማካኝነት አባል ሀገራት ለድርቅ እና ጎርፍ አደጋዎች ምላሽ እንዲሰጡ የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል። ይህም ቀጣናዊ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽን ለማጠናከርና የመንግስታትን አቅም ከመገንባት አኳያ ትልቅ ድርሻ እንደተወጣ ማዕከሉ ይገልጻል። ከኢኮኖሚ ትብብር እና ቀጣናዊ ትስስር አኳያም ኢጋድ ድንበር ተሻጋሪ ንግድ እንዲያድግ፣ መሰረተ ልማት እንዲስፋፋና ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲጠናከሩ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በትራንስፖርት ኮሪደሮች፣ በአርብቶ አደሮች እንቅስቃሴዎችና ቀጣናዊ ገበያዎች ላይ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ በአባል ሀገራት እንዲተገበር ከማድረግ ባለፈ ድጋፉን እየሰጠ ነው። ኢጋድ በቀጣናው ለንግድ እና ለእንቅስቃሴ የሆኑ መሰናክሎች እንዲቀንሱ አስተዋጽኦ አድርጓል። ኢጋድ ከፍልሰተኞች ና ተፈናቃዮች ጋር ያሉ ችግሮች እንዲፈቱና ጉዳዩ ከፈተና ባለፈ የልማት እድል እንደሆነ በማንሳት ሁሉን አቀፍ እይታ እንዲፈጠር እየሰራ ይገኛል። በአራት አስርት ዓመታት ውስጥ ኢጋድ ተቋማዊ አቅሙን በማጠናከርና አጋርነቱን በማስፋት ረገድ የተለያዩ ስራዎችን አከናውኗል። ኢጋድ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር እየሰራ ነው። ተቋሙ በቴክኒካዊ እና ፖለቲካዊ ደረጃዎች ለአባል ሀገራት ቋሚ የምክክር ማዕቀፍ ሆኖ እያገለገለ ሲሆን ይህም በሀገራት መካከል የጋራ መተማመንና የጋራ መግባባት እንዲኖር ያለው አስተዋጽኦ ወሳኝ የሚባል ነው። የኢጋድ የ40 ዓመታት ጉዞ በስኬቶች ብቻ የታጀበ አይደለም። ቀጣናዊ ተቋሙ ከፍተኛ ፈተናዎችም አጋጥመውታል። የመጀመሪያው በተደጋጋሚ ጊዜ የሚቀሰቀሱ እና ዘላቂ መቋጫ ያላገኙ ግጭቶችና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ናቸው። ጉዳዮቹ የኢጋድን የእርቀ ሰላም ጥረቶች ፈተና ውስጥ ከተውታል። አንዳንድ ጊዜ በአባል ሀገራት መካከል ያሉ መከፋፈሎች ኢጋድ ቆራጥ ውሳኔ እንዳይወስን ሲገድበው ታይቷል። የፋይናንስና ተቋማዊ አቅም ውስነነቶች የኢጋድ የተለያዩ ማዕቀፎች ትግበራ ላይ መስተጓጎሎችን ፈጥረዋል። ኢጋድ ከውጭ አጋሮች የሚያገኘው ፈንድ ከራስ ዘላቂ የፋይናንስ አቅርቦት ጋር ማመጣጠን አለመቻል የተቋሙን የዘላቂነት እና የባለቤትነት ጉዳይ ላይ ተጽእኖ አሳድረዋል። የፖለቲካ ተንታኞች ተቋሙ ከአባል ሀገራቱ የሚያገኝውን ጨምሮ ገቢ እና የፋይናንስ ቅሙን የሚያጠናክርባቸውን መንገዶች በሚገባ ማየት እንዳለበት ይመክራሉ። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ሌላኛው የኢጋድ ፈተና ነው። በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ደጋግመው የሚከሰቱ ድርቆች እና የጎርፍ አደጋዎች በተቋማዊ ምላሽና አቅም ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድረዋል። ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የከተሜነት መስፋፋትና መፈናቀል ጫናዎቹ ይበልጥ እንዲበረቱ አድርገዋል። ቀጣናዊ ስምምነቶችና የአሰራር ማዕቀፎችን ወደ ተጨባጭ የሀገራት ትግበራ የማሸጋገር ጉዳይም ትኩረት እንደሚያሻውም ይነሳል። የሀገራት የሚለያዩ የትኩረት መስኮች እና አቅሞች በቀጣናዊ ማዕቀፎች ሂደትና ትግበራ ላይ የራሳቸውን ተጽእኖ ያሳድራሉ። 40 ዓመታትን ያስቆጠረው ኢጋድ በምስራቅ አፍሪካ እና የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ትብብር ያለውን ወሳኝ ጠቀሜታ የሚያሳይ ህያው ተቋማዊ ምስክር ነው። ለድርቅ እና ረሃብ ምላሽ ከመስጠት በቀጣናዊ ሰላም፣ ደህንነት፣ አንድነት እና ልማት ቁልፍ ተዋናይነት ተሸጋግሯል። አንድነት እና የፖለቲካ ቁርጠኝነትን በኢጋድ አባል ሀገራት መካከል ማጠናከር ለቀጣናዊ የተግባር ምላሽና ለተቋሙ ዘላቂ ውጤታማነት ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች ናቸው። የአባል ሀገራት የጋራ አንድነት የተረጋገጠበት ኢጋድ ለቀውሶች ምላሽ ከመስጠት ባለፈ ለጋራ ፍላጎቶች መሳካት ያለው ሚናም ያድጋል። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አቅም ግንባታና ዘላቂ ልማት ላይ ቀጣይነት ባለው መልኩ መዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ የኢጋድ የትኩረት አጀንዳ ሊሆን ይገባል። የኢጋድ የሰላም እና መረጋጋት ጥረቶች በሁሉን አቀፍ አስተዳደር፣ በወጣቶችና ሴቶች የነቃ ተሳትፎ እንዲሁም በዘላቂ የሀገር ግንባታ አካሄዶች ሊደገፍ እንደሚገባ የፖለቲካ ባለሙያዎች ምክረ ሀሳባችውን ያስቀምጣሉ። የልማት ፍላጎት አለመሟላት እና የኑሮ ውድነትን ለግጭቶች አበይት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን ከስር መሰረቱ መፍታት ለዘላቂ መረጋጋት ወሳኝ ነው። ኢጋድ የተጣለበትን ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር እውን የማድረግ ኃላፊነቱን የበለጠ ለመወጣት የመሰረተ ልማት ትስስሮች ማጠናከር፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ማድረግና በቀጣናው በፍጥነት እያደገ ለመጣው ዜጋ የስራ ፈጠራና እድሎችን የሚያሰፉ ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶችን የማስፋት ስራ ላይ አበክሮ መስራት ይኖርበታል። ፈተናዎች እንዳሉ ሆነው የኢጋድ የ40 ዓመታት ጉዞ የሚያሳየው አንድ ግልጽ ሀቅ አለ። ይህም እውነታ የምስራቅ አፍሪካ መጻኢ ጊዜ እርስ በእርስ መተሳሰርና በትብብር መቆም እንደሆነ ነው። የተቋቋመበትን አላማ ዳግም ቃል ኪዳኑን በማደስ በቁርጠኝነት መስራት ከቻለ፣ ተቋማዊ አቅሙን በሚገባ ካጎለበተ፣ በሀገራት መካከል አጋርነትና ትብብርን ካጠናከረና የዲጂታል ዘመን በሚገባ በመዋጀት ከሰራ ኢጋድ ቀጣዩ ትውልድ ሰላማዊ፣ አይበገሬናና የበለጸገ ቀጣና እንዲረከብ በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና መጫወቱን መቀጠል ይችላል።
የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ትብብራቸውን ለማጽናት ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Jan 14, 2026 244
አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን በባለብዙ ወገን መድረኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አያኖ ኩኒሚትሱ ጋር በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተወያይተዋል።   የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ትብብር እንዳላቸው አውስተው በጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም (ቲካድ) ማዕቀፍ ያላቸውን ግንኙነት አንስተዋል። በዮካሃማ በነሃሔ ወር 2017 ዓ.ም የተካሄደው ዘጠነኛው የጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም(ቲካድ) በሁለቱ ወገኖች አጋርነት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን አመልክተዋል። ውይይቱ የሁለትዮሽ ትብብሩን የበለጠ ማጠናከርን ያለመ ነው። ጃፓን ለአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል (African CDC) እያደረገች ያለው ድጋፍ እንዲሁም የአፍሪካ ዘላቂ እድገት እና ትስስር ለሚደግፉ የመሰረተ ልማት ስራዎች እያፈሰሰች ያለው መዋዕለ ንዋይ እያደገ መምጣቱ ተመላክቷል። የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አያኖ ኩኒሚትሱ ዘጠነኛው የጃፓን አፍሪካ ልማት ዓለም አቀፍ ፎረም (ቲካድ) በስኬት መካሄዱን አድንቀዋል። 10ኛው ቲካድ በአፍሪካ እንዲካሄድ ጃፓን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አመልክተዋል።   ሀገራቸው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) እና የአፍሪካ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (ፒዳ) ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ቁልፍ ኢኒሼቲቮች መደገፏን እንደምትቀጥል ገልጸዋል። በሌላ በኩል ሚኒስትር ዴኤታዋ በዓለም አስተዳደር ውስጥ እያደገ የመጣውን የአፍሪካ ሚና በማንሳት የአፍሪካ ህብረት በቡድን 20 ቋሚ አባል መሆኗ ትልቅ ሽግግር መሆኑን ተነግረዋል። ባለስልጣናቱ በአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን የከፍተኛ ደረጃ የምክክር መድረክ እና ቲካድ አማካኝነት ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር እና የባለብዙወገን ዲፕሎማሲ እንዲጸና በጋራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ህብረት እና ጃፓን እ.አ.አ በ1993 አጋርነት መመስረታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሰላም እና ደህንነት፣ ኢኮኖሚ፣ ልማት፣ ንግድ፣ ጤና ፣ ግብርና፣ ቴክኖሎጂ እና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ከሁለቱ ወገኖች የትብብር መስኮች መካከል ይጠቀሳሉ።
ውኃ ለአፍሪካ የኅልውና ጉዳይ ነው - መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Jan 12, 2026 346
አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2018 (ኢዜአ)፦ ውኃ ሁሉንም ዘርፍ የሚነካ አህጉራዊ የኅልውና ጉዳይ መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ (PRC) መደበኛ ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ የሕብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። ስብሰባው"ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2026 መሪ ሐሳብ የሚደረግ ነው።   በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ፣ የአፍሪካ ሕብረትና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች፣ የሕብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ተሳትፈዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዘንድሮው የአፍሪካ ሕብረት ትኩረቱን ያደረገው በውኃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ውኃ በሁሉም አይነት እጅጉን ወሳኝ የሆነ ሀብት እና የኅልውና ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ አህጉራዊ ግቦቹን ለማሳካት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አስገንዝበዋል። በብራዚል ቤለም የተካሄደው 30ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30) ትኩረት ከተሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ መሆኑንም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) ውኃ አንዱ አጀንዳ እንደሚሆንም ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ለማዘጋጀት በመመረጧ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ያሉ ሲሆን፤ ለጉባኤው ስኬታማነት ሕብረቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ሰላም እና ደኅንነት የአፍሪካ አንገብጋቢ አጀንዳ መሆኑን የገለጹት ሊቀ መንበሩ ሱዳን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሊቢያን በማሳያነት ጠቅሰዋል። ኢ-ሕገመንግሥታዊ ለውጦች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ጠቅሰው፤ ሀገራት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንዲያከብሩ አሳስበዋል። የአፍሪካ ሕብረት ተቋማዊ ሪፎርም እና ኢኮኖሚያዊ ትሥሥርን ጨምሮ ለአህጉራዊ አጀንዳዎች እየሠራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። አህጉራችን ፈተናዎች ቢኖሩባትም በጋራ ከቆምን እናልፋቸዋለን ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። የዛሬው ስብስባ የካቲት 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲሁም የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከናወነው 39ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። 51ኛው የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ የኮሚቴው መደበኛ ስብስባ ለዋናው ጉባኤ እንደ ይፋዊ የዝግጅት ስብስባ የሚያገለግል ነው። የአፍሪካ ሕብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ የሕብረቱን ቋሚ ተወካዮችና የአባል ሀገራቱን አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ያቀፈ መሆኑ ይታወቃል።
ሐተታዎች
ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች
Jan 25, 2026 313
የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ ፍላጎት በመገንዘብ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች። ዶክተር አብዱራህማን ሮኔ ይባላሉ። ትውልድና ዕድገታቸው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልተሌ በተሰኘ አካባቢ ነው። የቀለም ትምህርት በሀገር ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ሀገረ አሜሪካ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው አድርገዋል። ለበርካታ ዓመታት ሕይወታቸውን በአሜሪካን ሀገር እየመሩ የሚገኙት ዶክተር አብዱራህማን ከሁለት ዓመታት በፊት ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ቦረና አቀኑ። የጉዟቸው ዓላማ ለዓመታት የናፈቋቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ብቻ እንደነበር ያስታውሳሉ።   በቤተሰብ ጥየቃ ቆይታቸውም በቦረና ዞን ተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የሚጎበኙበት አጋጣሚ ተፈጠረ። ጉብኝታቸውም ሆስፒታሉ በኪነ-ሕንፃ የተዋበ መሆኑን ነገር ግን የህክምና ግብዓት እጥረት ያለበት ሆኖ ማግኘታቸውን ይናገራሉ። በተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ምልከታቸው በሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ታካሚዎች ሲቸገሩ ማየታቸው የወቅቱ አሳዛኝ ትውስታ እንደነበርና ይህን እጥረት ወደ አሜሪካን ሀገር ሲመለሱ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መወሰናቸውን አስታውሰዋል። ዶክተር አብዱረሃማን በተልተሌ አካባቢ ተወልደውና አድገው ለሕክምና ባለሙያነት ያበቃቸውን ትምህርት የቀሰሙ ሰው በመሆናቸው በሆስፒታሉ የተመለከቱት የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት የሺዎችን ሕይወት የሚታደግ ሰብዓዊ ፕሮጀክት የሚቀረጽበት ሃሳብ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። ከዚያም የራሳቸውን የሕክምና ሙያ ዕውቀትና በውጭ ያካበቱትን ግንኙነት በመጠቀም መነሻቸውን ባለፈው ዓመት ለተልተሌ እና ሜጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁስ በድጋፍ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ዓመትም የሞያሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ ለሶስት ትላልቅ የጤና ተቋማት ዘመናዊ ሕክምና መሳሪያዎችን አበርክተዋል። እነኚህ የሕክምና መሳሪያዎች አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያስታወሱበት በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ያስተማራቸውን ማህበረሰብ በማስታወስ መንግስት የዜጎችን የሕክምና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል። ሌላኛው በአሜሪካን ሀገር በሕክምና ሙያ የሚያገለግሉት ዶክተር ዋቆ ዳደቻ በበኩላቸው፤ ሁሉም ዜጋ በትብብር መስራት ከቻለ የማህበረሰብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል ይላሉ። ይህ የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ለማሟላት የሚደረገውን ተሳትፎ ሁሉም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ሊማሩበት የሚገባ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት የሕክምና ተቋማትን ጥራትና ደረጃ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ማሰብ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በውጭ የሚኖሩ የሕክምና ሙያተኞች የሚያደርጉት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በአርዓያነት የሚወሰድ ነው ብለዋል። በዶክተር አብዱራህማን መሪነት ለቦረና አካባቢ ሆስፒታሎች የተደረገው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍም የተቋማቱን የጤና አገልግሎት ጥራት በማስጠበቅ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በመግለጽ። በቀጣይም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህዝባቸውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማገዝ በኩል የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 679
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
አፍሪካውያን ሀገር በቀል አሰልጣኞች ጎልተው የታዩበት የአፍሪካ ዋንጫ !
Dec 28, 2025 624
35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው። በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ 24 ሀገራት 12ቱ በአፍሪካውያን የሚሰለጥኑ ናቸው። የአዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከዛው ከሀገራቸው ናቸው። የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሞሮኮን ለግማሽ ፍጻሜ አድርሰዋል።ሀገሪቷ በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከእ.አ.አ 2022 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እየመሩት የሚገኙት ሬግራጉዊ ሞሮኮን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቭዋር አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋች ኤመርሰን ፋኤ ነው። ፋኤ እ.አ.አ በ2023 በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን በመምራት ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል። በውድድሩ መሐል በውጤት ማጣት የተሰናበቱትን ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ ጂን-ሉዊስ ጋሴት በመተካት በጊዜያዊነት አሰልጣኝ የተሾመው ፋኤ ቡድኑን ለዋንጫ ማብቃቱ አስወድሶታል። በዘንድሮው ውድድር ዋንጫውን ለማንሳት የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ተርታ የተመደበችው ሴኔጋል አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፓፔ ታው ነው። ፓፔ ታው በተጫዋችነት ዘመኑ ለሴኔጋል ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። አሰልጣኙ ሴኔጋል ለ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እንድታልፍ አድርጓል። ከሶስት ዓመት በፊት በአልጄሪያ በተካሄደው የሰባተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) ሴኔጋል ዋንጫውን ስታነሳ የቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ መርቷል። የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ግብጽ የምትሰለጥነው በቀድሞ ኮከቧ ሆሳም ሀሰን ነው። በተጫዋችነት ዘመኑ በአፍሪካ ዋንጫ 11 ግቦችን አስቆጥሯል። በ177 ጨዋታዎች 69 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የብሄራዊ ቡድኑ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ሆሳም ሀሰን የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ በተጫዋችነት በማንሳት ስኬታማ አሰልጣኝ ነው። ሌላኛው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን አሰልጣኝ የ56 ዓመቱ ዴቪድ ፓጉ ነው። ካሜሮናዊው አሰልጣኝ የተሾሙት ከሰሞኑ ነው። ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን በመተካት ቡድኑን እንዲመሩ ኃላፊነት ተጠሎባቸዋል። በካሜሮን እግር ኳስ ባላቸው የታክቲክ መረዳት እና ብቃት የሚሞካሹት ፓጉ ቡድኑን አንድ በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጣሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል። ሌላኛው የውድድሩ ተሳታፊ ሀገር ዛምቢያ ናት።የ48 ዓመቱ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተከላካይ ሞሰስ ሲቾኔ የቡድኑ የወቅቱ ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2022 እስከ 2024 በጊዜያዊነት እና በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት ሲቾኔ በ2025 ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል። ምስራቅ አፍሪካን በውድድሩ ከሚወክሉ ሶስት ሀገራት መካከል አንዷ ሱዳና ናት። ጋናዊው ጀምስ ክዌሲ አፒያ የቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። አፒያ ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የጋቦን አሰልጣኝ ቲዬሪ ሞዩማ የብሄራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነበር። ለ11 ዓመታት ለጋቦን ተጫውተዋል። ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመሩ ይገኛል። የ44 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ሞሬና ራሞሬቦሊ የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2025 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛል። ሞሬና ከዚህ ቀደም የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነበሩ። የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን የአማካይ ተጫዋች ብራማ ትራኦሬ ነው። አሰልጣኙ ከእ.አ.አ ማርች 2024 አንስቶ ቡርኪናፋሶን እየመራ ይገኛል። ትራኦሬ ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የአንድ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ቱኒዚያ አሰልጣኝ የቀድሞ የቡድኑ የተከላከይ መስመር ተጫዋች ሳሚ ትራቤልሲ ናቸው። የ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ለቱኒዚያ ብሄራዊ ቡድን ለ10 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግሏል። ብሄራዊ ቡድኑን ከእ.አ.አ 2025 ቱኒዚያን እየመራ ይገኛል። በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ሞዛምቢክ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ፍራንቺስኮ ኩዌሪዮል ኮንዴ ጁኒየር (ቺኩዊኒዮ ኩንዴ) የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። የ60 ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሞዛምቢክ ለ15 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግለዋል። ለሀገራቸው በ43 ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኩንዴ ከእ.አ.አ 2021 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የናይጄሪያ አሰልጣኝ የሆነው ኤሪክ ቼሌ የኮትዲቭዋር፣ ማሊ እና ፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላቸው አሰልጣኝ ናቸው። ይሁንና ቼሌ የአፍሪካ የዘር ግንድ ቢኖራቸውም በፈረንሳይ መወለዳቸው የውጭ ሀገር ዜጋ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። የአፍሪካውያን አሰልጣኞች በአፍሪካ ዋንጫ የማሰልጠን ምጣኔ ከሌሎቹ ወቅቶች አንጻር የአሁኑ የተሻለ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ሀገር በቀል አሰልጣኞች እየተሰጣቸው ያለውን ትኩረት ያሳያል። 12 ሀገራት በውጭ ሀገር ዜጎች ይሰለጥናሉ። በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አፍሪካውያን የሚያሰለጥኗቸው ወይስ የውጭ ሀገር ዜጋዎች የሚመሯቸው ሀገራት ዋንጫውን ያነሳሉ? የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል።  
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን
Dec 22, 2025 842
የኢትዮጵያ ዲጂታል ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ የተጀመረው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በወቅቱ የኤሌክትሮኒክ መሳሪዎችን ተጥቅሞ መረጃን በመተንተን እና መረጃን እንደ ልዩ ገጽታ በመጠቀም እና መለያ ቁጥር (ኮድ) በመስጠት አገልግሎት ላይ ይውል ነበር። ከዛ ጊዜ በኋላ በርካታ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞች እና ማሽኖች ተፈብርከው ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል። እ.አ.አ በ1946 በአሜሪካ የፔንሲሊቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ጥቅል አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያውን የኤሌክትሮኒክ ዲጂታል ኮምፒዩተር በመስራት የዲጂታል ዘመን ጅማሮን አበሰረ። ከእ.አ.አ 1943 እስከ 45 ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰራው ይህ ኮምፒዩተር ባለቤቶች ጆን ማውችሊ እና ጄ ፕሬስፐርት ኤከርት ናቸው። በ150 ኪሎ ዋት ኃይል የሚሰራው ኮምፒዩተር በሴኮንዶች ውስጥ በርካታ ስራዎችን ያከናውን ነበር። ኮምፒውተሩ በወቅቱ በነበሩ ባለሙያዎች ማርሽ ቀያሪ እና መሰረት ጣይ የሚል ስያሜ አግኝቷል። የዘመናዊ የዲጂታል ስርዓቶች ምሰሶ ነው የሚባለው ኢንተርኔት የተጀመረው እ.አ.አ በ1960ዎቹ መጀመሪያ ነበር። “አርፓኔት” የተሰኘ የአሜሪካ የጥናት ፕሮጀክት ኮምፒዩተሮችን ዘመኑ ከደረሰበት የኔትወርክ ስርዓቶች ጋር በማገናኘት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል። እንግሊዛዊው የኮምፒዩተር ሳይንቲስት ቲም በርነርስ ሊ እ.አ.አ 1969 “ወርልድ ዋይድ ዌብ” (WWW) በመፍጠር ትስስርን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ አሸጋግሯል። ድረ ገጾችን በመፍጠር እና በህዝብ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሰፋ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ዲጂታል ቴክኖሎጂ ከኮምፒዩተር መሰራት ተነስቶ ወደ ዓለም አቀፍ የትስስር መሰረተ ልማትነት የተቀየረ ሲሆን በየዕለት ተዕለት የሰዎች ኑሮ፣ማህበራዊ መስተጋብር፣ ንግድ እና የመንግስታት አሰራር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ከማምጣት ባለፈ ዘርፎች በቴክኖሎጂ እንዲቃኙ አድርጓል። ዓለም ላይ አሁን ካለው ህዝብ 73 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። የዲጂታል ኢኮኖሚ የዓለምን ጥቅል ዓመታዊ ምርት (ጂዲፒ) የ15 በመቶ ድርሻን እንደሚያግዝ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ። ሞባይል ለኢንተርኔት መስፋፋት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል። ሀገራት እ.አ.አ 2025 በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ፣ ኔትወርኪንግ እና ለሌሎች ትራንስፎርሜሽ ስራዎች ያወጡት ኢንቨስትመንት ከአራት ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንደሚልቅም ይገመታል። በአፍሪካ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ480 ሚሊዮን በላይ ተሻግሯል። ዲጂታል ስርዓቱን የሚያሳልጡ መሰረተ ልማቶች እና የዳታ ማዕከላት በአፍሪካ መንግስታት እና የልማት አጋሮች ትብብር እየተገነቡ ነው። ዲጂታል ኢኮኖሚ ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለትምህርት እና ክህሎት፣ ለመንግስት የአሰራር ውጤታማት፣ ለፋይናንስ አካታችነት እና ኮሙኒኬሽን ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 በፊት የዲጂታል ምህዳሯ የተገደበ ነው ማለት ይቻላል። ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት፣ ለቴሌኮም አገልግሎት ከፍተኛ ክፍያ ወጪ የሚወጣበት እና በቴሌኮም አገልግሎት የመንግስት ብቻ የበላይነት የሚታይበት ነበር። ከለውጡ በኋላ መንግስት የቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች አማካኝነት ዲጂታል ተጠቃሽ ነው። የዲጂታል ዘርፍ ከብዝሃ የኢኮኖሚ ምንጮች አንዱ ሆኖ ነው።ዲጂታላይዜሽን ለኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። ኢትዮጵያ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አካታች የሆነ የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ካስገባች ሰነባብታለች። ኢትዮጵያ ከእ.አ.አ 2020 አንስቶ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በማዘጋጀት ስተገብር ቆይታለች። ስትራቴጂው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና መንግስታዊ አገልግሎቶችን ዲጂታል የማድረግ አላማ ያደረገ ነው። በዚህም 900 ገደማ የሚሆኑ መንግስታዊ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ ሆነዋል።3000 የሚሆኑ የዲጂታል አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አግኝተዋል። የፋይዳ መታወቂያ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል። የሞባይል እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። የአራተኛ እና አምስተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰፋ መጥቷል።የዲጂታል ክህሎትም ተስፋ ሰጪ እድገት ታይቶበታል። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ክፍት እንዲሆን መንግስት ባስቀመጠው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት ሳፋሪኮም ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን “ምፔሳ” የተሰኘ የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል። የመንግስት የዲጂታል ፖሊሲዎች እና የህግ ማዕቀፎች ለዘርፉ ምቹ ምህዳር በመፍጠር ትስስር እንዲሰፋ እና አገልግሎቶች እንዲዘምኑ አስችሏል። ኢትዮጵያ ከአምስት በፊት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በማቋቋም በርካታ ስራዎችን አከናውናለች። ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት በክረምት መርሃ ግብር (ሰመር ካፕም) ወጣቶች ሲማሩ እንደቆዩ አውስተው በዘርፉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያሳያል። ሁሉንም ዘርፍ የሚነካው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በግብርና፣ጤና፣ አገልግሎት እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በመግባት ስራን እያቀላጠፈ ይገኛል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት የሚሰበሰቡ ዳታዎች ለመንግስት እና ግል ተቋማት አገልግሎት ላይ እየዋሉ እንደሚገኝም ተገልጿል። መንግስት ወጣቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ሀገርን አልፎም ዓለምን የሚጠቅሙ ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያቀርቡ የሚያደርገውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ቴሌብር፣ መሶብ እና ዘመንን ጨምሮ ያሉ የዲጂታል አገልግሎቶች የዘርፉን እድገት በማሳለጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የዲጂታል 2030ን ስትራቴጂ ይፋ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ መጠናቀቁን ገልጸዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ ያበሰሩ ሲሆን ተደራሽነትን ማስፋት፣ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን አመልክተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና አስተማማኝ የዲጂታል ምህዳር መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሦስት ቁልፍ ትልሞች እንዳሉት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህም ተደራሽነትን ማስፋት፤ እኩል እድል ማመቻቸትና በተቋማትና ህዝብ መካከል መተማመንን መፍጠር መሆናቸውን አብራርተዋል። ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፥ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው። ለአብነትም የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል ሲሉ አንስተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለው እንደገለጹት፥ አንድ ሺህ ሰላሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ሆነዋል ነው ያሉት። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ከተሞች ይደርሳል ብለዋል። በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሰራል ሲሉም አረጋግጠዋል።ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት፣ አካታችነት እና ማህበራዊ ለውጥ ቁልፍ ምሰሶ ነው። ስትራቴጂው በሚገባ ከተተገበረ፣ በቂ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች ከተገነቡ እና ዜጎች በንቃት ከተሳተፉ ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘመን ትሩፋቶች ተጠቅማ ትልሞቿን ማሳካት እንደምትችል አያጠራጥርም።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 671
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል።   ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር።   ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ።   ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ   ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ   ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።   ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው።   መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ 
Jan 1, 2026 627
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው።   በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል።   ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ   ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ 
Dec 8, 2025 1246
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።  
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3562
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 3218
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2070
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7884
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6369
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 59933
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 53933
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 34556
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 32111
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 27434
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 26354
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 25890
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 25722
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 59933
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 53933
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 34556
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 32111
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ዕድሜ  ያልገደበው የልማት አርበኝነት 
Jan 14, 2026 329
ዕድሜ ያልገደበው የልማት አርበኝነት ብርቱዎች ነገን በማሰብ ሁሌም ታትረው ይሰራሉ፤ ይደክማሉ፤ ይጥራሉ…ለቀጣዩ ትውልድም ጥሪት በማስቀመጥ አሻራቸውን ያኖራሉ። አገር የምትገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው። “አባት ያበጀው፤ ለልጅ ይበጀው” እንደሚባለው ልጆች ከአባቶቻቸው ያገኙትን ጥሪት በአዲስ እውቀትና አሰራር ለአገር እድገት በሚበጅ መልኩ አጠናክረው መጠቀማቸው አይቀርም። “ዕድሜ ጸጋ ነው” የሚለው አባባል አንዳንዴ በዕድሜ ብንገፋም ጠንክረን ከሰራን ብዙ ነገር እናያለን ከሚለው ጋር የተያያዘ ነው። በሰቆጣ ከተማም እድሜ ሳይገድባቸው በልማት ውጤታማ የሆኑ ግለሰቦች ለዚህ ማሳያ ናቸው። የከተማዋ ነዋሪ የ67 ዓመቱ አቶ ብርሃኑ አወቀ እና የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ዕድሜያቸው ቢገፋም ጠንክሮ ከተሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻልና ዕድሜ ጸጋ ሆኖ ብዙ ለውጥ ማየት እንደሚቻል ማሳያ ናቸው። ግለሰቦቹ ከዕድሜ ብዛት ጉልበቴ ደከመ፣ አይኔ ፈዘዘ፣ እጄም ተሳሰረ…ሳይሉ ጊዜያቸውን በደን፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራ በማሳለፍ ለወጣቶች የልማት አርአያነት ያለው ተግባር እየፈጸሙ ነው። አቶ ብርሃኑ አወቀ በሰቆጣ ከተማ ዳርቻ የሚገኝ አለቱ ያገጠጠና የተራቆተ አካባቢን ከሌላ አካባቢ ለም አፈር በማምጣትና በመደልደል አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ደን በማልማት ውጤታማ ስራ እያከናወኑ ነው።   ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከወጣሁ ጀምሮ ጠንክሬ በመስራት የምለወጥበትን ሥራ ማሰብ ስነበረብኝ፤ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ ለዘመናት የቆየን ጭንጫ መሬት ጠርጌና ደልድዬ ማልማት ችያለሁ ይላሉ ወደኋላ መልስ ብለው የተነሱበትን ሁኔታ ሲያስታውሱ። ግማሽ ሄክታር በማይሞላ መሬት ላይ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ዘይቱና፣ ጌሾ፣ ቡና፣ ማንጎና አቮካዶ አልምተዋል። በተጨማሪም ቆስጣ፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመንና ሽንኩርት በማምረት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ጥሪት አፍርተዋል።   ጊዜን በአግባቡ ተጠቅሞ ተግቶ መስራት ከተቻለ ሀብት ማፍራትና ህይወትንም መለወጥ እንደሚቻል የገለጹት አቶ ብርሀኑ፣ ወጣቱም ከእሳቸው የሥራ ትጋት በመማር በአካባቢው ያለውን ፀጋ ለይቶ በማልማት ሊጠቀም ይገባል ሲሉ ይመክራሉ። ሌላው የ83 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ ታደሰ አዳነ ባለፉት 18 ዓመታት በተሰማሩበት የአትክልትና ደን ልማት ሥራ የአካባቢያቸውን ገጽታ ቀይረዋል። የዕድሜ ዘመናቸውን በውትድርናና በመንግስት ሠራተኝነት በማገልገል ሃገራዊ ግዳጃቸውን ሲወጡ ነው የቆዩት።   ከመንግስት ሥራ በጡረታ ከተገለሉ በኋላም ቤት ውስጥ መቀመጥን አልመረጡት። አካፋና ዶማቸውን ይዘው ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ ጌሾ፣ ዘይቱና እና ማንጎ በማልማት ምርቱን ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ሆነዋል። በአካባቢያችን ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ ለይተን ማልማት ከቻልን ድህነትን ማስወገድ የሚከብድ አይሆንም ያሉት አቶ ታደሰ፣ የተራቆተና በጎርፍ የተጎዳን መሬት በማልማት አካባቢውን ሳቢና ማራኪ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት። ወጣቱም ከእሳቸው አርአያነት ያለው ተግባር በመማር በአካባቢው እጁ ላይ ባለ ሀብት ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል በተግባር ማሳየት እንዳለበት መክረዋል።   የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ ውሃ አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ ደሳለኝ አዳነ እንደገለጹት፤ በብሔረሰብ አስተዳደሩ 24ሺህ 847 አርሶ አደሮች በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተሰማርተዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል ዕድሜ ሳይገድባቸው ወደ ልማት የገቡ አረጋዊያን እያከናወኑት ያለው የግብርና ልማት ሥራ ለወጣቱ ትልቅ ትምህርት እንደሚሆንም ተናግረዋል። ከእነሱ ልምድ በመውሰድ በዞኑ ወጣቶች፣ ሴቶችና አረጋዊያን በጓሮና ባላቸው መሬት ላይ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ይህም በዞኑ የሚስተዋለውን የስርዓተ ምግብ ችግር ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል።
ከማላጋ እስከ አፍሪካ ዋንጫ፤ የሞሮኮው አዲስ እንቁ ብራሂም ዲያዝ
Jan 13, 2026 339
  የግል ክህሎት፣ ፈጣን አስተሳሰቡ እና በጠባብ ክፍተቶች ውስጥ ሰብሮ የመግባት አቅሙ ሙገሳ እንዲጎርፍለት አድርጓል። አንድ ለአንድ ሲገናኝ ተከላካዮችን በፈጣን አካላዊ ቅልጥፍና እና በድንገት አቅጣጫ በመቀየር የሚያልፍበት መንገድ እንዲሁም የመፍጠር አቅሙ የተመልካቾችን ቀልብ የሚይዝ ነው። የአማካይ እና የአጥቂ መስመርን በማገናኘት እና በአስገራሚ ሁኔታ አጭር ኳሶችን በማቀበልም የተዋጣለት ተጫዋች ነው ማለት ይቻላል። በቦታ አያያዙ የእግር ኳስ ልኅቀቱ ከፍተኛ ነው የሚል አድናቆት ከእግር ኳስ ባለሙያዎች አግኝቷል። ኳስን ሲያንከባልልም ለዐይን ይስባል። ከክህሎቱ እና ከማራኪ እንቅስቃሴው ባለፈ ወደ ኋላ እየመለሰ ተከላካዮችን ያግዛል፣ ኳስ ይነጥቃል። ይህ ተጫዋች የ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ክስተት የሆነው የሞሮኮው ብራሂም ዲያዝ ነው። የ26 ዓመቱ የሪያል ማድሪድ የክንፍ መስመር ተጫዋች ዲያዝ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አምስት ጨዋታዎችን አድርጎ አምስት ግቦችን በማስቆጠር የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ ነው። አዘጋጇ ሞሮኮ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ መክፈቻ ኮሞሮስን 2 ለ 0 ስታሸንፍ የውድድሩን የመጀመሪያ ግብ አስቆጥሯል።   ብራሂም አብዱልቃድር ዲያዝ የተወለደው እ.አ.አ ኦገስት 3 ቀን 1999 በስፔን ማላጋ ግዛት ነው። እናቱ ስፔናዊ አባቱ ሞሮኳዊ ናቸው። ዲያዝ ያደገው በማላጋ ነው። እግር ኳስንም በአንዳሉሺያዊቷ ከተማ ሲጫወት ቆይቷል። በ16 ዓመቱ ካደገበት ማላጋ በመውጣት እ.አ.አ በ2015 ወደ ማንችስተር ሲቲ ወጣት አካዳሚ በ200 ሺህ ፓውንድ ወጪ ተዘዋወረ። ዲያዝ እ.አ.አ ሴፕቴምበር 21 ቀን 2016 በካራባኦ ካፕ (በቀድሞ አጠራሩ ሊግ ካፕ) ማንችስተር ሲቲ ከስዋንሲ ሲቲ ባደረገው ጨዋታ በ80ኛው ደቂቃ በኬሌቺ ኢናቺዩ ተቀይሮ በመግባት ለውኃ ሰማያዊዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የመጀመሪያውን ጨዋታ ካደረገ ከሶስት ቀናት በኋላ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ለሶስት ዓመታት የሚያቆየውን ፕሮፌሽናል ኮንትራት ተፈራርሟል። እ.አ.አ ኖቬምበር 21 ቀን 2017 ማንችስተር ሲቲ ከፌይኖርድ ሮተርዳም ጋር ባደረገው የሻምፒዮናስ ሊግ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ የአውሮፓ መድረክ ጨዋታውን ማድረግ ችሏል። በወቅቱ ብራሂም ስተርሊን መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በጭማሪ ሰዓት ላይ ነበር ተቀይሮ የገባው። ዲያዝ በውኃ ሰማያዊዎቹ ማልያ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብቶ የተጫወተው እ.አ.አ ዲሴምበር 19 ቀን 2017 ነው። ማንችስተር ሲቲ ከሌስተር ሲቲ በካራባኦ ካፕ ጨዋታ ላይ ለ88 ደቂቃዎች ተሰልፎ ተጫውቷል።   እ.አ.አ ጃንዋሪ 20 ቀን 2018 ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። በወቅቱ ማንችስተር ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን፤ በውድድር ዓመቱ አራት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሳትፎ ያደረገው ብራሂም ዲይዝ የሜዳሊያ ሽልማት አግኝቷል። እ.አ.አ ኦገስት 5 ቀን 2018 ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን 2 ለ 0 ባሸነፈበት የኮሙዩኒቲ ሺልድ ጨዋታ ላይ በፊል ፎደን ተቀይሮ በመግባት ለ15 ደቂቃዎች ተጫውቷል። ዲያዝ እ.አ.አ 2018/19 ማብቂያ ላይ ማንችስተር ሲቲ ፉልሃምን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የመጀመሪያ ግቦቹን ለሲቲ አስቆጥሯል። በማንችስተር ሲቲ ያለው ውል እ.አ.አ 2019 ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ወቅት ስሙ ከዝውውር ጋር በስፋት ይነሳ ነበር። ዲያዝ እ.አ.አ ጥር 2019 በ17 ሚሊዮን ዩሮ ከማንችስተር ሲቲ ወደ ሪያል ማድሪድ ተዘዋወረ። ለስድስት ዓመታት የሚያቆየውን ውልም ፈርሟል። የክንፍ ተጫዋቹ የመጀመሪያ ጨዋታውን በነጮቹ ማልያ ያደረገው እ.አ.አ ጥር 9 ቀን 2019 ሪያል ማድሪድ ሌጋኔን በስፔን ጥሎ ማለፍ ዋንጫ 3 ለ 0 ባሸነፈበት ወቅት ነው። ከአራት ቀናት በኋላ በስፔን ላሊጋ ሪያል ማድሪድ ሪያል ቤቲስን 2 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ ተቀይሮ በመግባት በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የመጀመሪያ ግቡን ለማስቆጠር ሶስት ወራትን ጠብቋል። እ.አ.አ ግንቦት 12 ቀን 2019 ሪያል ማድሪድ በላሊጋው በሪያል ሶሲዬዳድ 3 ለ 1 ሲሸነፍ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። በወቅቱ ዲያዝ ስድስት ጨዋታዎች ላይ በላሊጋው የተጫወተ ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዓመቱ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል። ሪያል ማድሪድ እ.አ.አ በ2021/21 የውድድር ዓመት ብራሂም ዲያዝ ወደ ኤሲ ሚላን በውሰት ማምራቱን ይፋ አደረገ። ዲያዝ ሚላን እ.አ.አ መስከረም 27 ቀን 2020 ክሮቶኔን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል። እ.አ.አ ግንቦት 2021 ኤሲ ሚላን ጁቬንቱስን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ ያስቆጠረው ግብም ተጠቃሽ ነው። ዲያዝ በኤሲ ሚላን የውሰት ውሉ ሲያበቃ በድጋሚ ለሁለት ዓመታት በውሰት የሚቆይበት ስምምነት ሪያል ማድሪድ ከጣልያኑ ክለብ ጋር የተፈራረመ ሲሆን፤ ውሉ ሚላን ተጫዋቹን የማቆየት መብት ሰጥቶታል። እ.አ.አ መስከረም 15 ቀን 2021 ኤሲ ሚላን በሻምፒዮንስ ሊጉ የ3 ለ 2 ሽንፈት ሲያስተናግድ የመጀመሪያ የአውሮፓ መድረክ ግቡን አስቆጥሯል። በ2023 ኤሲ ሚላን ቶተንሃም ሆትስፐርስን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ 1 ለ 0 ሲያሽንፍ ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። እ.አ.አ በ2023 ሰኔ ወር ላይ ሪያል ማድሪድ ዲያዝ ከኤሲ ሚላን የሶስት ዓመታት የውሰት ቆይታ በኋላ ወደ ክለቡ መመለሱን አሳውቋል። ተጫዋቹ በኤሲ ሚላን ቆይታው 91 ጨዋታዎችን አድርጎ 13 ግቦችን ከመረብ ጋር አገናኝቷል። ዲያዝ ወደ ሪያል ማድሪድ ከተመለሰ በኋላ ኮንትራቱን እስከ 2027 አራዝሟል። እ.አ.አ መስከረም 27 ቀን 2023 ወደ ክለቡ ከተመለሰ በኋላ ሪያል ማድሪድ ላስ ፓልማስን 2 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል።   የክንፍ መስመር ተጫዋቹ ሪያል ማድሪድ በሀገር ውስጥ እና በአውሮፓ መድረክ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር እና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ዲያዝ እስከ አሁን ለሪያል ማድሪድ ባደረጋቸው 129 ጨዋታዎች 20 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ከነዚህም ውስጥ 13ቱ በላሊጋው ያስቆጠራቸው ናቸው። ከክለብ ወጣ ስንል የተጫዋቹን የብሔራዊ ቡድን ቆይታ እናገኛለን። ዲያዝ በታዳጊነቱ በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ለስፔን ወጣት ቡድኖች ተጫውቷል። እ.አ.አ በ2016/17 የውድድር ዘመን ለስፔን ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ16 ዓመቱ ተሰልፎ መጫወት ችሏል። በተለይም አዘርባጃን እ.አ.አ በ2017 ባዘጋጀችው 15ኛው የአውሮፓ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ላይ ያሳየው ድንቅ ብቃት አድናቆት አስችሮታል። በዚያ ቀጥለው በነበሩ ዓመታትም ለስፔን ከ19 እና ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ተጫውቷል። ብራሂም ዲያዝ በስፔን ታዳጊና ወጣት ቡድኖች ላይ በአጠቃላይ 28 ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል። የስፔን ታዋቂ የስፖርት ጋዜጣ ማርካ እ.አ.አ ጥር 23 ቀን 2023 ለሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ማቀዱን የሚመለከት ዘገባ ይዞ ወጥቷል። ከዜግነቱ ጋር በተያያዘ ያሉ አንዳንድ የአስተደዳር ጉዳዮች በወቅቱ መፍትሄ አግኝተዋል። ይሁንና ኮትዲቯር እ.አ.አ በ2023 ባዘጋጀችው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሞሮኮው አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከተጫዋቹ ጋር በተደረገ የቅድሚያ ስምምነት ለተጫዋቹ ጥሪ አልተደረገለትም። ዲያዝ እ.አ.አ መጋቢት 10 ቀን 2024 ለሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሀገሪቷ ብሔራዊ መጫወት እንደሚፈልግ በይፋ ማሳወቁን ማርካ በወቅቱ ዘግቧል። ጥያቄውም ተቀባይነት አገኘ። በወቅቱ የሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ብሔራዊ ቡድኑ ከአንጎላ እና ሞሪታኒያ ጋር ለነበረበት የወዳጅነት ጨዋታ ለዲያዝ ጥሪ አድርገውለታል። እ.አ.አ መጋቢት 22 ቀን 2024 ሞሮኮ አንጎላን 1 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ለብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። እ.አ.አ ጥቅምት 6 ቀን 2024 ሞሮኮ ለ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከጋቦን ጋር ባደረገችው ጨዋታ 4 ለ 1 ስታሸንፍ የመጀመሪያ ግቡን ለሞሮኮ ማስቆጠር ቻለ። እ.አ.አ ሕዳር 15 ቀን 2024 ሞሮኮ በማጣሪያው ጋቦንን 5 ለ 1 ስትረታ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል። ከሶስት ቀናት በኋላ ሞሮኮ ከሌሴቶ ጋር ባደረገችው የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ 7 ለ 0 ስታሸንፍ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር በሀገሩ ማልያ የመጀመሪያ ሀትሪኩን ሰርቷል። እ.አ.አ ጥቅምት 2025 ሞሮኮ ራባት ላይ ኮንጎ ሪፐብሊክን 1 ለ 0 በማሸነፍ በስፔን ከዚህ ቀደም በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ተይዞ የነበረውን 15 ተከታታይ ጨዋታዎችን የማሸነፍ ክብረ ወሰን በመስበር ወደ 16 ማድረስ ችላለች። በዚህ ታሪካዊ ጨዋታ ላይ ዲያዝ ተሰልፎ ተጫውቷል። የሞሮኮ ተከታታይ የማሸነፍ ጉዞ 19 ጨዋታዎች ደርሶ የነበረ ሲሆን በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከማሊ ጋር አንድ አቻ ስትለያይ አብቅቷል።   ሞሮኮ ለ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በማጣሪያ ብታልፍም አስቀድማ ውድድሩን እንድታዘጋጅ እድል አግኝታ የነበረው ጊኒ በዝግጅት ማነስ ምክንያት በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከሁለት ዓመት በፊት አዘጋጅነቷ ተነጥቆ ለሞሮኮ ተሰጥቷል። ሞሮኮ የዘንድሮውን ውድድር በደማቅ ሁኔታ እያካሄደች ትገኛለች። በውድድሩ ላይ ጎልተው ከታዩ ተጫዋቾች መካከል ብራሂም ዲያዝ ተጠቃሽ ነው። በአፍሪካ ዋንጫው እስከ አሁን ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። በተሰለፈባቸው በእያንዳዱ ጨዋታዎች ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል። ለሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በአምስት የአፍሪካ ዋንጫ ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ጽፏል። ሞሮኮ በሩብ ፍጻሜው ማሊን 2 ለ 0 ስታሸንፍ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሯል። ሀገሩ ወደ ግማሽ ፍጻሜ እንድታልፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱንም እየመራ ይገኛል። ሞሮኮ በዚሁ ግስጋሴዋ ከቀጠለች ዲያዝ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እና ኮከብ ተጫዋች የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ሞሮኮ በግማሽ ፍጻሜው ከናይጄሪያ ጋር ረቡዕ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም ታደርጋለች። ዲያዝ በዚህ ጨዋታ ላይ ልዩነት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንድ የእግር ኳስ ተንታኞች ብራሂም ዲያዝ እ.አ.አ በ2026 ወጥነት ያለው ብቃት ማሳየት ከቻለ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋችነት ሽልማቱን የሚወስድበት የለም እያሉ ይገኛሉ። ሞሮኳውያን በተጫዋቹ ፍቅር ልባቸው ከንፏል። በየጨዋታው ዲያዝ ዲያዝ እያሉ ከፍተኛ ድጋፍ እና ሙገሳ እየሰጡት ይገኛሉ። እሱም በድንቅ ብቃቱ ምላሽ እየሰጣቸው ነው። በተወለደበት ማላጋ ከተማ የጀመረው የእግር ኳስ ሕይወት በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የበለጠ አብቧል። የሞሮኮው አዲሱ ኮከብ ብራሂም ዲያዝ ቀጣይ የእግር ኳስ ሕይወት በስኬት እና በድል የደመቀ እንደሚሆን ከአሁኑ ድንቅ ብቃቱ ተነስቶ መናገር ይቻላል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም