ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ መድን እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ተጋርተዋል 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 26/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ አቻ ተለያይተዋል። 

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ረመዳን የሱፍ በ12ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረው ግብ ኢትዮጵያ መድን መሪ ሆኗል።

ከእረፍት መልስ አብነት ተስፋዬ በ80ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ኢትዮ ኤሌክትሪክን አቻ አድርጓል። 

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 14ኛ ከፍ አድርጓል። መድን ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ16 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። 

ቀን ላይ በተደረገ የዘጠነኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ወላይታ ድቻ እና ምድረገነት ሽሬ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም