ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቦሌ ክፍለ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 26/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ጨዋታ ቦሌ ክፍለ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳሳሽ ሰውአገኝ በ30ኛው ደቂቃ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

ውጤቱን ተከትሎ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ቦሌ ክፍለ ከተማ በ16 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ12 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ጨዋታውን ተከትሎ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።

የ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሕዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም